ፍ/ቤቶች የፍ/ቤቱን የስራ ቋንቋ የማይችለ ተከሳሾች በቀረቡላቸው ጊዚ አስተርጓሚ በመመደብ ክሱ በሚገባቸው ቋንቋ በዛርዛር የመንገር እና በጠበቃ ታግዖው የመከራከር መብት እንዲላቸው፤ ጠበቃ ለማቆም የሚያስችል ዓቅም ከላላቸው በመንግሥት ወጪ ጠበቃ የማግኘት መብት እንዲላቸው የመንገር ሀላፉነት ያለባቸው ስለመሆኑ የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገመንግሥት አንቀጽ አንቀጽ 9/4 እና 13(1)(2)፣20፣የሲቪል እና የፕለቲካ መብት አንቀጽ 14 160916 አቶ ቦጃ በየነ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ታሕሣሥ 30 ቀን 2011 ዓ.ም 2. ተከራካሪ ወገኖች ጉዲያቸው በሽማግላዎች እንዱታይ ወደውና ፈቅደው ከተስማሙ በኋላ ሽማግላዎች የሰጡት ውሳኔ ባለበት ሁኔታ በሕጉ በተዖረጋው ሥርዓት ይግባኝ በመጠየቅ እንዱታረም ከማድረግ በስተቀር አዱስ ክስ ማቅረብ ተገቢ ስላለመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 3325፣የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ 244/2/ረ/
No summary available.
ቀን 26/04/2011 ዓ.ም ዳኞች፡- ተኽሉት ይመሰል ተፈሪ ገብሩ /ዶ/ር/ ቀነዓ ቂጣታ ተሾመ ሽፈራው ፀሐይ መንክር አመልካች፡- አቶ መህዱ ሸረፊ ጠበቃ መስፍን አለማየሁ ቀረቡ:: ተጠሪ፡- አቶ ሻፉ ሸረፊ - የቀረበ የለም:: መዛገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
በዘህ መዛገብ አከራካሪ የሆነው ነጥብ በዖመድ ሽማግላ ውሳኔ መቋጫ ያገኝው ጉዲይ የውሳኔው ተገቢነት የሚመረምርበት ሥርዓት መኖር አለመኖሩን ነው። የጉዲዩ አመጣጥ ሲታይ በስር አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ተከሳሽ በመሆን ተከራክሯል። አመልካች በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ ህዲር 08 ቀን 2008 ዓ.ም ያቀረቡት ክስ ባጭሩ በቦላ ክፍለ ከተማ ወረዲ 11 የቤት ቁጥር አዱስ ካርታ ቁጥር 1648-11/9/4/7 የሆነውን ቤት ለተጠሪ እንዱያስተዲድሩለት በአደራ የሰጡዋቸው ቢሆንም ተጠሪ እንዱያስተዲድሩ የተሰጣቸው ቤት በስማቸው ካርታ ያሰሩ በመሆኑ ቤቱን ለቀው እንዱያስረክቡ ይወሰን ዖንድ ዲኝነት ጠይቋል።
የአሁን ተጠሪ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እንዱሁም በፍሬ ነገሩ ዛርዛር መልስ ያቀረቡ ሲሆን ተጠሪ ያቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ ይዖት ሲታይም ጉዲዩ በዖመድ ሽማግላዎች ተመርምሮ ውሳኔ የተሰጠበት በመሆኑ በፍርድ ቤት ድጋሚ ክስ ላቀርብ አይገባም በማለት መከራከራቸውን የሚያመለክት ነው።
በዘሕ አግባብ ክርክሩ የቀረበለት የስር ፍርድ ቤትም የግራቀኙ ክርክር ከመረመረ በኋላ አመልካች እና ተጠሪ የሚከራከሩበት ጉዲይ ጥቅምት 20 ቀን 2008 ዓ.ም በዖመድ ሽማግላዎች ውሳኔ ማግኘቱን፤የውሳኔው ይዖትም ንብረቱ የጋራ ስለሆነ ከተስማሙ በስምምነት እንዱጠቀሙበት፤የማይስማሙ ከሆነ ግን ቤቱን ሽጠው እንዱከፊፈለ መወሰናቸውን፤አመልካች ሽማግላዎች መምረጣቸውን ሳይክደ ሽማግላዎች በሰጡት ውሳኔ ላይ አልፈረምኩም በማለት የሚያቀርቡት ክርክር ተገቢ አለመሆኑን በመግለጽ የአመልካች ክስ በብይን ውድቅ አድርጎታል።
አመልካች በዘህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የይግባኝ ቅሬታ ያቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ግራቀኙን ከአከራከረ በኋላ የስር ፍ/ቤት ብይን አጽንቷል።የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔና ብይን በመቃወም ለማሳረም ነው።
አመልካች ሀምላ 6 ቀን 2010 ዓ.ም የተፃፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረቡ ሲሆን መሰረታዊ ይዖቱ እንደተመለከትነው ሽማግላዎች ጭብጥ በመለየት የግራቀኙ ማስረጃ በመስማት ውሳኔ ያልሰጡ ስለመሆኑና፤በሽማግላዎች ጉዲዩ እንዱታይ ወላጅ አባታቸው ጫና ያሳደሩ በመሆኑ ብይኑ ተሽሮ በፍርድ ቤት ታይቶ እንዱወሰን የሚጠይቅ ነው።የአመልካች አቤቱታ የመረመረው አጣሪ ችልትም በ18/12/2010ዓ.ም በሰጠው ትዔዙዛ ጉዲዩ በዖመድ ሽማግላ ታይቷል የመባለ አግባብነት ተጠሪ ባለበት ማጣራት ይቻል ዖንድ ለዘህ ችልት ያስቀርባል የተባለ ሲሆን ተጠሪም በሕጉ አግባብ ጥሪ ተደርጎላቸው ጥቅምት 20 ቀን 2011 ዓ.ም የተፃፈ መልስ አቅርበው ጉዲዩ በሽማግላዎች ተመርምሮ ከተወሰነ በኋላ አመልካች ይግባኝ እንዲልጠየቁ ፤ጉዲዩም በሚገባ ተጣርቶ የተወሰነ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤቶች ብይንና ፍርድ ሉጽና ይገባል በማለት ተከራክሯል።አመልካች ህዲር 13 ቀን 2011 ዓ.ም የተፃፈ መልስ አቅርቧል።ፍርድ ቤቱም ለትክክለኛ ፍትህ አሰጣጥ ይረዲ ዖንድ የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የካ ምድብ ችልት የኮ/መ/ በማስቀረብ ተመልክቷል።
ከስር የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጽው ሲሆን እኛም የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ብይን እና ፍርድ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት መሆን አለመሆኑን ክርክሩን እንደሚከተለው መርምረናል።
መዛገቡ እንደመረመርነው አመልካች አጥብቀው የሚከራከሩት ከተጠሪ ጋር ባደረጉት ስምምነት ጉዲዩ በዖመድ ሽማግላዎች ውሳኔ እንዱያገኝ ፈቃድ የሰጡ ቢሆንም ሽማግላዎች ግራቀኙ ሳያነጋግሩ በውሳኔውም ሳይፈርሙ የተሰጠ ውሳኔ በመሆኑ ተገቢ አይደለም በሚል ነው።ተጠሪ በበኩላቸው የዖመድ ሽማግላዎች ጉዲዩን አጣርተው የሰጡት ውሳኔ በመሆኑ ሉነቀፍ አይገባም በማለት ተከራክሯል።ከመዛገቡ እንደሚታየው አመልካች እና ተጠሪ ጥቅምት 20 ቀን 2008 ዓ.ም ለዖመድ ሽማግላዎች የዔርቅ ስልጣን መስጠታቸውን ያከራከረ ጉዲይ አይደለም።በግራቀኙ የተመረጡ ሽማግላዎች ጥቅምት 20 ቀን 2008 ዓ.ም በሰጡት ውሳኔ ለክርክር መነሻ የሆነው ቤት የጋራ ንብረት በመሆኑ እንደ መጀመሪያው ተስማምተው እንዱኖሩ ካልተስማሙ ግን ንብረቱ የታላቅና የታናሽ የጋራ ንብረት ስለሆነ ሸጠው በጋራ በእኩል እንዱካፈለ በሙለ ድምጽ መወሰናቸውን የሚያሳይ ነው።አመልካች ይህ ውሳኔ መኖሩን ሳይክደ ውሳኔ በተሰጠበት ሂደት ተሳትፍ ያልነበራቸው በተለይም ማስረጃ ሳያቀርቡ መወሰኑ ተገቢ አይደለም የሚል ክርክር ማቅረባቸውን ተመልክተናል።
በመሰረቱ ተከራካሪ ወገኖች ጉዲያቸው በዖመድ ዲኛ ለመጨረስ መስማማት እንደሚችለ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 3325 እና ተከታይ ድንጋጌዎች ተመልክቷል።አመልካች ጉዲያቸው በሽማግላዎች እንዱታይ ወደውና ፈቅደው ከተስማሙ በኋላ ሽማግላዎች የሰጡት ውሳኔ ባለበት ሁኔታ አዱስ ክስ ማቅረባቸው በሕጉ አግባብ ነው ለማለት አልተቻለም። አመልካች ሽማግላዎች የሰጡት ውሳኔ የሚነቅፍ ነገር ካለው በሕጉ በተዖረጋው ሥርዓት ይግባኝ በመጠየቅ ከሚያሳርሙ በስተቀር አዱስ ክስ ማቅረብ ተገቢ አለመሆኑን፣ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያቀረበለት ፍርድ ቤትም በዘህ ጉዲይ ብይን መስጠቱ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ 244/2/ ረ/ ያገናዖበ ነው ከሚል በቀር መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት አልተቻለም። አመልካች ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ቤት በተመለከተ የቤተ ዖመድ ሽምግልና ዳኞች የሰጡት ውሳኔ ተገቢ አይደለም በማለት የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 350 እና ተከታይ ድንጋጌዎች በሚፈቅደው አግባብ ይግባኝ ጠይቀው ውሳኔውን ስለማሻራቸው ያቀርቡት ክርክር የለም እንዱህ ከሆነ ደግሞ የፀና የቤተዖመድ ሽምግልና ዳኞች ውሳኔ ባለበት ሁኔታ በሕጉ ያልተመልከቱ መስፈርቶች በመጥቀስ ውሳኔውን መቃወም ተገቢነት የለውም ብለናል። በመሆኑም አመልካች የሽምግልና ዲኝነት ውሳኔ ከሚያሳርሙ በስተቀር በውሳኔው አልፈረምኩም በሚል ምክንያት በድጋሚ ክስ ማቅረብ የህግ ድጋፍ ያለው ሆኖ አልተገኘም። በዘህ ሁለ ምክንያት የስር ፍርድ ቤቶች አመልካች ያቀረቡት ክስ በድጋሚ የቀረበ ነው በማለት የሰጡት ብይን እና ውሳኔ በሕጉ አግባብ ነው ከሚል በስተቀር መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት አልተቻለም። በዘሕም ተከታዩን ወስነናል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ በ03/05/2009 ዓ.ም የሰጠው ብይን፣የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ በ13/10/2010 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ ጸንቷል።
የዘህ ፍ/ቤት ክርክር ያስከተለው ወጪና ኪሳራ ግራቀኙ የየራሳቸው ይቻለ ብለናል ዔግድ ካለ ተነስቷል።ይፃፍ። የስር ፍ/ቤት መዛገብ በመጣበት አኳኃን ይመለስ ብለናል።
መዛገቡ ውሳኔ ያገኘ በመሆኑ ወደ መ/ቤት ተመለሰ ውሳኔ በ02/05/2011 ዓ/ም ተነበበ።
No topics extracted.