የኢንሹራንስ ፕለሲ የኢንሹራንስ ዉል አካል በመሆኑ በኢንሹራንስ ፕሉሲዉ ላይ የተመለከተዉ ቃል የኢንሹራንስ ዉል ቃል ተደርጎ ሉወሰድ የሚገባ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1733፣የንግድ ሕግ ቁጥር 657(1 እና 2) (19) እና ጀነራል ኢንሹራንስ ብሮከርስ
No summary available.
የሰ.መ.
ታሕሣሥ 30 ቀን 2011 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ በዔዉቀት በላይ እንዲሻዉ አዲነ ሃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካች:- አቶ ቦጃ በየነ ተጠሪ፡- የኦሮሚያ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ መዛገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነው ጉዲይ ወንጀልን የሚመለከት ነው። የአሁን ተጠሪ በአሁን አመልካች ላይ በስር ፍ/ቤት ያቀረበው ክስ ይዖት አመልካች የኦሮሚያ ክልል የቡና ጥራትና ንግድ ቁጥጥር ለመወሰን የወጣውን አዋጅ ቁጥር 160/2002 አንቀጽ 13/2፤19(1)(2)(5)(6) እና 23(6) ድንጋጌን በመተላለፍ ሆን ብል አስቦበት በቀን 26/05/2010 ዓ.ም ከምሽቱ በግምት 3፡00 ሰዓት በምዔራብ ጉጂ ዜን ገላና ወረዲ ፕሬ ከተማ ልዩ ቦታው ኬላ በተባለው ሕገ-ወጥ ቡና ንብረትነቱ የአመልካችበሆነ የሰላዲ ቁጥሩ 3-38518 አ.አ በሆነ የጭነት መኪና ግምቱ ብር 6፣3520 የሆነ 14 ኩንታል ታጥቦ የተቀሸረ ቡና በመጫን ለጊዚው እጁ ካልተያዖ ሹፋር ጋር በመሆን ያለምንም ፈቃድ ከቡናው ላይ ላላ ዔቃ በመጫን በማጓጓዛ ላይ እያለ ተይዝል የሚል ነው።
አመልካች ቀርቦ ማንነቱ ከተረጋገጠ በኋላ ክሱ የደረሰው መሆኑን ለችልቱ የገለጸ መሆኑን፤
ችልቱም በሚገባው ቋንቋ የዓቃቤሕግን ክስ አንብቦለት ገብቶኛል በማለት ከገለጸ በኋላ መቃወሚያ የላለው መሆኑን በመግለጽ የእምነት ክህደት ቃለን ሲጠየቅ ድርጊቱን እንዲልፈጸመ እና ከመኪናው ረዲት እና ሹፋር ጋር ወደ ዱላ ከተማ በመጓዛ ላይ እንዲለ ህገወጥ ቡና ጭነሃል በማለት የተያዖ መሆኑን እና መኪናው ምን እንደጫነ የማያውቅ መሆኑን በመግለጽ ክሱን ክድ የተከራከረ መሆኑን፤
ፍ/ቤቱም የዓቃቤሕግን ምስክሮች ሰምቶ አመልካች የቀረበበትን ክስ እንዱከላከል በማለት ብይን የሰጠ መሆኑን፤ አመልካች የመከላከያ ምስክር እንዱያቀርብ እድል ቢሰጠውም የመከላከያ ምስክር የለኝም በማለት ቅጽ ሞልቶ ያቀረበ መሆኑን እና ፍ/ቤቱም መከላከያ ምስክር ማቅረብ መብት እንጂ ግዳታ አይደለም በማለት የአመልካችን ምስክር የማቅረብ መብት አልፍ አመልካችን ጥፊተኛ በማለት በሶስት ዓመት ጽኑ እሥራት እና በብር 25,000 መቀጮ እንዱቀጣ የወሰነ መሆኑን መዛገቡ ያሳያል።
አመልካች ይህን ውሳኔ በመቃወም በየደረጃው ላለ የክልለ ፍ/ቤቶች አቤቱታ ያቀረበ ቢሆንም አቤቱታው ተቀባይነት አላገኘም። የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዖትም፡- የስር ፍ/ቤት አመልካች በጠበቃ እንድከራከር በራሱ ተነሳሽነት ሉያመቻችልኝ ሲገባ በዛምታ አልፍታል፤ አመልካች መንግስት ጠበቃ እንዱያቆምልኝ ያቀረብኩትን ጥያቄ በማለፍ የግል ጠበቃ እንዲቆም ጊዚ ሳይሰጠኝ በማልሰማው እና መናገር በማልችለው ቋንቋ ያለአስተርጓሚ የተከሰስኩበትን ነገር ሳላውቅ የተሰጠው ውሳኔ አመልካች በሕገመንግስቱ የተሰጠኝን መብት የሚነፍግ ነው፤ አመልካች የተከሰስኩበት ሕግ ከተጠረጠርኩበት ወንጀል ጋር አግባብነት የለውም፤ አመልካች መኪናውን አላሽከረከርኩም የጫነውንም ነገር አላወቅኩም፤ ሹፋሩ መኪናውን ትቶ በመሸሹ በመኪናው አጠገብ ስለተገኘሁ ብቻ ጥፊተኛ ልባል የማይገባ በመሆኑ የስር ፍ/ቤቶች እነኚህን ሁኔታዎች ሳያገናዛቡ የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ሥሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ አመልካች የመኪናው ባለቤት ቢሆንም ለሾፋር ሰጥቶ ሲያሽከረክር ከነበረበት ሾፋሩ ማምለጡ ተረጋግጦ ባለበት፤ አመልካች የቡና ነጋዳ ወይም አምራች መሆኑ ባልተረጋገጠበት፤ በልላ በኩል አመልካች የቡናውን መጫን ያውቅ የነበረ መሆኑ ባልተረጋገጠበት እና በሚገባው ቋንቋ በአግባቡ ስለመተርጎሙ እና የመከላከል መብቱን ስለማወቁ ጥርጣሬ በፈጠረ ሁኔታ የመከላከል መብቱ ታልፍ የመኪናው ባለቤት በመሆኑ ብቻ ጥፊተኛ የመባለን አግባብነት ከወንጀል ሕግ አንቀጽ 23 እና ከተጠቀሰው አዋጅ ጋር በማገናዖብ ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ በዘህ ችልት እንዱታይ ተደርጓል። ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎም ግራቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የተጠሪ መልስ ይዖት በአጭሩ፡- አመልካች የመኪናው ባለቤት ሆኖ ፈቃድ ሳይኖረው በክሱ የተጠቀሰውን ቡና በልላ ዔቃ ስር ጭኖ ሲሄድ መያዘ ተረጋግጦበታል፤ ቡናው የተጫነው ከአመልካች ዔውቅና ውጪ ነው የሚለው ክርክር አሳማኝ አይደለም፤ ቡናው በላሉት የተጫነ እና ከላላ ዔቃ ስር የተጫነ በመሆኑ አመልካች የወንጀል ሀሳብ እንዲለው የሚያሳይ ነው፤ አመልካች በአዋጁ መሰረት ሀላፉነት ስላለበት የመኪናው ባለቤት ስለሆንኩ ተጠያቂ ልሆን አይገባም በማለት የሚያቀርበው ክርክር አግባብነት የለውም፤ ፍ/ቤቱ ለአመልካች ክሱን ካነበበለት በኋላ በሚገባው መልኩ በድጋሚ የተነበበለት መሆኑ ተገልጿል፤ የክልለን ፍ/ቤቶች እንደገና ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 141/200 አንቀጽ 17/2 ፍ/ቤቱ ተከላካይ ጠበቃ ለማቆም የሚገደደው የተከሰሰበት ወንጀል ከአምስት ዓመት ጽኑ እሥራት በማያንስ የሚያስቀጣ ከሆነ እና በራሱ ጠበቃ ለማቆም የማይችል ከሆነ ነው፤የተሰጠው የቅጣት ውሳኔ አመልካችን የሚጠቅም በመሆኑ የስር ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሳኔ ሉጸና ይገባል የሚል ነው።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው። እኛም በስር ፍ/ቤት የተሰጠው ውሳኔ የአመልካች የመሰማት መብት ተጠብቆ የተሰጠ ውሳኔ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ በመያዛ ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዖብ እንደሚከተለው መርምረነዋል።
በመሰረቱ የተከሰሱ ሰዎች በሕግ የመሰማት መብት / the right to fair trial / ያላቸው ሲሆን ክስ ከቀረበባቸው በኋላ ተገቢ በሆነ አጭር ጊዚ ውስጥ በመደበኛ ፍ/ቤት በመቅረብ ጉዲዩ በዛግ ችልት እንዱታይ የሚያስችል ሕጋዊ ምክንያት ከላለ በቀር ለሕዛብ ግልጽ በሆነ ችልት የመሰማት መብት ያላቸው መሆኑን የሕገመንግሥቱ አንቀጽ 20/1 ድንጋጌ ያስገነዛበናል። ኢትዮጲያ የተቀበለችው የሲቪል እና የፕለቲካ መብቶች ዓለምዓቀፍ የቃልኪዲን ሰነድ አንቀጽ 14 ድንጋጌም ……..everyone shall be entitled to a fair and public hearing by a competent, independent and impartial tribunal established by law……. በማለት ይደነግጋል። ይህ መብት በሕገ-መንግስቱም ሆነ ኢትዮጲያ በተቀበለችው ዓለምዓቀፍ ስምምነት እውቅና የተሰጠው መሰረታዊ መብት እንደሆነ እና በየደረጃው ያለ ፍ/ቤቶችም ይህን መሰረታዊ የሆነ መብት የማክበር እና የማስከበር ሀላፉነት እንዲለባቸው ከሕገመንግስቱ አንቀጽ 9/4 እና 13(1)(2) ድንጋጌዎች መገንዖብ ይቻላል።
የተከሰሱ ሰዎች ክሱ በቂ በሆነ ዛርዛር እንዱነገራቸው እና በጽሐፍ የማግኘት መብት ያላቸው መሆኑን፤ በፍርድ ሂደት ባለበት ወቅት በተከሰሱበት ወንጀል እንደ ጥፊተኛ ያለመቆጠር እና በምስክርነት እንዱቀርቡ ያለመገደድ፤ የቀረበባቸውን ማንኛውንም ማስረጃ የመመልከት፤ምስክሮችን የመጠየቅ፤ ለመከላከል የሚያስችላቸውን ማስረጃ የማቅረብ፤ ምስክሮቻቸው ቀርበው እንዱሰሙላቸው የመጠየቅ፤በመረጡት የሕግ ጠበቃ የመወከል፤ ጠበቃ ለማቆም አቅም በማጣታቸው ፍትሕ ሉጓደል የሚችልበት ሁኔታ ሲያጋጥም ከመንግስት ጠበቃ የማግኘት መብት፤ ይግባኝ የመጠየቅ እና የፍርደ ሑደት በማይገባቸው ቋንቋ በሚካሄድበት ሁኔታ በመንግስት ወጪ ክርክሩ እንዱካሄድላቸው የመጠየቅ መብት ያላቸው ስለመሆኑ የሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 20 በዛርዛር የተደነገገ ሲሆን የሀገሪቱ ሕግ አካል በሆነው የሲቪል እና የፕለቲካ መብት አንቀጽ 14 ድንጋጌም ላይ በዛርዛር ተመልክቷል።
የተከሰሱ ሰዎች የቀረበባቸውን ክስ በአግባቡ ተረድተው ክሱን መከላከል የሚችለትም ክሱ በሚገባቸው ቋንቋ በዛርዛር ሲነገራቸው እና በጠበቃ ሲታገዘ እንደሆነ ግልጽ ነው። በመሆኑም ፍ/ቤቶች የፍ/ቤቱን የስራ ቋንቋ የማይችለ ተከሳሾች በቀረቡላቸው ጊዚ አስተርጓሚ በመመደብ ክሱ በሚገባቸው ቋንቋ በዛርዛር የመንገር እና በጠበቃ ታግዖው የመከራከር መብት እንዲላቸው፤ ጠበቃ ለማቆም የሚያስችል ዓቅም ከላላቸው በመንግሥት ወጪ ጠበቃ የማግኘት መበት እንዲላቸው የመንገር ሀላፉነት አለባቸው።
የአመልካች ዋነኛ ክርክር የስር ፍ/ቤት አመልካች በጠበቃ በመታገዛ እንድከራከር አላደረገም፤
አመልካች የፍ/ቤቱን የስራ ቋንቋ የማልችል ሲሆን ያለአስተርጓሚ የተከሰስኩበትን ነገር ሳላውቅ የተሰጠው ውሳኔ ሕገ-መንግስታዊ መብቴን የሚጻረር ነው የሚል ሲሆን ተጠሪ በዘህ ፍ/ቤት ባደረገው ክርክር ፍ/ቤቱ ለአመልካች ክሱን ካነበበለት በኋላ በሚገባው መልኩ በድጋሚ የተነበበለት መሆኑ ተገልጿል፤ የክልለን ፍ/ቤቶች እንደገና ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 141/200 አንቀጽ 17/2 ፍ/ቤቱ ተከላካይ ጠበቃ ለማቆም የሚገደደው የተከሰሰበት ወንጀል ከአምስት ዓመት ጽኑ እሥራት በማያንስ የሚያስቀጣ ከሆነ እና በራሱ ጠበቃ ለማቆም የማይችል ከሆነ ነው በማለት ከሚከራከር እና በስር ፍ/ቤት ውሳኔም ላይ አመልካች በሚገባው ቋንቋ ክሱ በድጋሚ ተነቦለታል በሚል ከመገለጹ በቀር አመልካች የፍ/ቤቱን የስራ ቋንቋ የማይችል ከመሆኑ አኳያ የተከሰሱ ሰዎች በሕገመንግሥቱ በተጠበቀላቸው መብት መሰረት አስተርጓሚ ተመድቦለት ክሱ የተነበበለት እና እንዱረዲው የተደረገ መሆኑን፤በጠበቃ የመወከል መብት እንዲለው እና በግለ ጠበቃ ማቆም የማይችል ከሆነ በመንግስት ወጪ ጠበቃ የማግኘት መብት እንዲለው የተነገረው መሆኑን የስር ፍ/ቤት ውሳኔ ይዖት አያመላክትም።
አመልካች አስተርጓሚ ተመድቦለት ክሱን እንዱረዲው እስካልተደረገ እና በጠበቃ እስካልታገዖ ድረስ የቀረበበትን ክስ በአግባቡ ተረድቶ ክሱን ለመከላከል ይችላል ተብል አይገመትም። በመሆኑም ጉዲዩ የቀረበለት ፍ/ቤት አመልካች የቀረበበትን ክስ በአግባቡ ተረድቶ መከላከል ይችል ዖንድ ለአመልካች አስተርጓሚ እንዱመደብ በማድረግ፤ አመልካች ጠበቃ የማቆም መብት እንዲለው እና ጠበቃ ለማቆም የሚያስችል አቅም ከላለው በመንግስት ወጪ ጠበቃ የማግኘት መብት እንዲለው በመንገር ጉዲዩ እንዱታይ ማድረግ ሲገባው ይህን ሳያደርግ የሰጠው ውሳኔ በኢ.ፋ.ዱሪ ሕገመግስቱ እና ኢትዮጲያ በተቀበለቻቸው ዓለምዓቀፍ ስምምነቶች ለከተሰሱ ሰዎች የተጠበቁትን መሰረታዊ መብቶች ያላገናዖበ እና መሰረታዊ የሆነ የሕግ ሥሕተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል። በዘህም ምክንያት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
No topics extracted.