No summary available.
ህዲር 27/2014 ዓ.ም ዳኞች፡- ሰለሞን አረዲ እትመት አሰፊ ኑረዱን ከድር መላኩ ካሳዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡- የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን አዱስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ተጠሪ፡- አቶ ጌታቸው ታደሰ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበው ጉዲይ የሁከት ይወገድልኝ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን የተጀመረውም የአሁን ተጠሪ በአመልካች ላይ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ ነው። ተጠሪ ያቀረቡት ክስ ጭብጥም ለፍርድ አፈፃፀም በወጣ የፍርድ ቤት የተሽከርካሪ ሽያጭ የሃራጅ ጨረታ ላይ ተወዲድረው የሰላዲ ቁጥሩ ኮድ 3-18474 አ/አ የሆነ ተሽከርካሪ ገዝተው የተሽከርካሪው ስመ ሀብት ወደ ስማቸው የዞረላቸው መሆኑን፤ ይህንኑ ተሽከርካሪ በማሽከርከር ላይ እያለ የአሁን አመልካች መስከረም 07/2012 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት አካባቢ በአዱስ አበባ ከተማ ለገሃር ተብል በሚጠራ አካባቢ ጉልበቱ እና ሥልጣኑ ተጠቅሞ የነጠቃቸው መሆኑን በመግለፅ ድርጊቱ የሁከት ተግባር ነው ተብል በተሽከርካሪው ውስጥ የነበሩትን ንብረቶች ግምት እና ተሽከርካሪው በመቆሙ ምክንያት የተቋረጠባቸውን ገቢ በጠቅላላው ብር 347,800(ሶስት መቶ አርባ ሰባት ሺህ ስምንት መቶ ብር) ከፍል ንብረቱን እንዱለቅላቸው ዲኝነት የሚጠይቅ ነው።
በዚሁ ክስ ላይ መልስ እንዱሰጥ በታዘዘው መሰረት የአሁን አመልካች ቀርቦ ለክሱ ምክንያት የሆነው ተሽከርካሪ ለመንገድ ሥራ ፕሮጀክት በሚል ከቀረጥ ነፃ ወደ ሀገር የገባ ነው፤ የመንገድ ስራው እንደተጠናቀቀ ተሽከርካሪው ተመልሶ ከሀገር ሉወጣ አልያም ተገቢው ቀረጥ እና ታክስ ሉከፈልበት የሚገባው ነው፤ ተሽከርካሪውን ወደ ሀገር ያስገባው ድርጅት ሀገር ጥል በመጥፊቱ ምክንያት ከድርጅቱ ላይ የሚፈለገው ቀረጥ እና ታክስ ሂሳብ ተሰርቶ በጠቅላላው ወደ ብር 98,474,585.17(ዘጠና ስምንት ሚሉዮን አራት መቶ ሰባ አራት ሺህ አምስት መቶ ሰማንያ አምስት ከ17/100 ብር) የሚፈለግበት መሆኑ ተረጋግጦ ክስ በቀረበበት ንብረት ላይ በአመልካች በኩል የእግድ ትዕዛዝ ተላልፎል፤ ተሽከርካሪው ለፍርድ አፈፃፀም በሚል በፍርድ ቤት ትዕዛዝ የተሸጠውም ይኸው በአመልካች የተሰጠው የእግድ ትዕዛዝ ፀንቶ ባለበት ነው፤ አመልካች መስሪያ ቤት ተገቢው ቀረጥ እና ታክስ ያልተከፈለባቸውን ንብረቶች ተከታትል የመያዝ እና የሚፈለግበትን እዲ የማስከፈል በህግ የተሰጠው ሥልጣን አለው፤ ለክሱ ምክንያት የሆነው ተሽከርካሪም በዚሁ ምክንያት በቁጥጥር ስር የዋለ በመሆኑ ድርጊቱ ህገ ወጥ የሁከት ተግባር የሚባል አይደለም፤ ተሽከርካሪው ውስጥ አለ የተባለትን ንብረቶች ያልተረከብኩ እና ተቋረጠ የተባለውን ገቢም ልጠየቅ የማይገባ በመሆኑ ክሱ ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክሯል።
ጉዲዩ የቀረበለት ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃን ከሰማ በኋላ በሰጠው ውሳኔ ክስ የቀረበበት ተሽከርካሪ ለፍርድ አፈፃፀም በሚል በፍርድ ቤት በወጣ ጨረታ ተገዝቶ የተያዘ በመሆኑ አመልካች መብቱን መጠየቅ ያለበት ህጋዊ ሂደቶችን ተከትል መክፈል ሲኖርበት ያልከፈለው ድርጅት መሆን ሲገባው በፍርድ ቤት የአፈፃፀም ትዕዛዝ ንብረቱን ተረክቦ እና ሰመ ሀብቱን በራሱ አዙሮ ከያዘው ሰው ላይ መቀበለ የሁከቱ ተግባር በመሆኑ ሁከቱ ተወግድ ንብረቱ ለተጠሪ ሉመለስ ይግባል፤ በተሽከርካሪው ውስጥ አለ የተባለትን ንብረቶች እና ታጣ የተባለው ገቢ ያልተረጋገጠ በመሆኑ አመልካች የመክፈል ግዳታ የለበትም በማለት ወስኗል።
በዚሁ ጉዲይ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በበኩለ የግራ ቀኙን የይግባኝ ክርክር ከሰማ በኋላ አመልካች ክስ በቀረበበት ንብረት ላይ የቀደምትነት መብት አለኝ ካለ መብቱን ሉያስከብር የሚገባው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 418 ስር በተመለከተው አግባብ ላሆን ይገባል፤ በዚህ መልኩ የቀረበ ጥያቄ ሳይኖር በአፈፃፀም የተሸጠን ንብረት በጉልበት መያዙ የሁከት ተግባር ነው በሚል የስር ፍርድ ቤት ውሳኔን በምክንያት በማጠናከር አጽንቷል።
የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ነው። አመልካች ሰኔ 29/2013 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ በስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ ተፈጽሟል ያለውን መሰረታዊ የህግ ስህተት ተጥቅሶ በዚህ ችልት እንዱታረምለት ጠይቋል። መሰረታዊ ይዘቱም የስር ፍ/ቤት አመልካች በተሸከርካሪው ላይ አለኝ ያለውን ያልተከፈለ ቀረጥና ታክስ መጠየቅ ያለበት ተሸከርካሪውን ወደ ሀገር ካስገባው ድርጅት እንጂ ከአሁን ተጠሪ ላይ አይደለም በማለት የሰጡት ፍርድ አግባብ አለመሆኑን፤ ክስ የቀረበበትን ተሸከርካሪ ጨምሮ ዩቲኤ ኤልሳሜክስ ኢትዮጵያ በተሰኘ የመንገድ ስራ ተቋራጭ ድርጅት ቀረጥና ታክስ ሳይከፍል የመንገድ ስራው እንደተጠናቀቀ ተመልሰው ከሀገር ሉወጡ ወይም ተገቢውን ቀረጥና ታክስ ተከፍልባቸው በሀገር ውስጥ እንዱቆዩ በአዋጁ አንቀጽ 71፣ እና 130 መሰረት ወደ ሀገር የገባ መሆኑን፤ ተቋራጩ የመንገድ ስራ ፕሮጀክቱን በመቋረጥ ከሀገር በመውጣቱ የአመልካች ኦዱት ለመንግስት ሉከፈል ከነበረው የኦዱት ጉድለት የተገኘ መሆኑን፣ በአዋጁ አንቀጽ 130 መሰረት ክርክር ያስነሳው ተሸከርካሪ ለላላ ሰው ሉተላለፍ የሚችለው ቀረጥና ታክስ ከተከፈለበት ወይም የሚተላለፍለት ሰው ተመሳሳይ የቀረጥ ነጻ መብት ያለው ሲሆን ብቻ መሆኑን፣ አመልካች ተሸከርካሪውን በመያዝ ከተሸከርካሪው ላይ የሚፈለገውን ቀረጥና ታክስ ለመሰብስብ ሥልጣን ያለው አካል መሆኑንና የቀደምትነት መብት ያለው መሆኑን፤ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት በመ/ቁ/49889 ላይ አመልካች የጉሙሩክ ህግን በማስከበር ረገድ በሚወስደው እርምጃ ወጭና ኪሳራ እንደማይጠየቅ አስገዲጅ የህግ ትርጉም ሰጥቶ እያለ በስር ፍርድ ቤቶች ተጠሪ የወጪ ኪሳራ ዝርዝር እንዱያቀርብ መብት መጠበቃቸው አግባብ አለመሆኑን በመግልፅ የሰር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ እንዱሻር የሚጠይቅ ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ቀረጥና ታክስ ሳይከፍል ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ የገባ ተሸከርካሪ በተጠሪ እጅ አግኝቶ ቀረጥና ታክስ ለማስከፈል አመልካች ተሸከርካሪውን መያዙ የሁከት ተግባር ነው በሚል በስር ፍርድ ቤቶች የመወሰኑን አግባብነት ከጉሙሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 130 አንጻር ለዚህ ችልት ቀርቦ እንዱመረመር በመታዘዙ ግራ ቀኙ ተጠሪ የፅሁፍ መልስ እንዱሰጡበት ተደርጓል።
በዚሁ መሰረት ተጠሪ መስከረም 27/2014 ዓ.ም በተፃፈ መልስ የስር ፍ/ቤት አመልካች ቀረጥና ታክስ መጠየቅ ያለበት ተሸከርካሪውን ወደ ሀገር ካስገባው ድርጀት እንጅ በህጋዊ መንገድ ተሸከርካሪውን ገዝቶ ስመ-ንብረቱን ጭምር አዙሮ ከያዘው ተጠሪ አይደለም ማለታቸው በአግባቡ ነው፤ አመልካች በስር ፍ/ቤት ክርክርም ሆነ አፈጻጸም ጣልቃ ገብቶ የቀደምትነት መብቱን በህግ አግባብ ማስከበር ሲገባው በፍ/ቤት ትዕዛዝ የተረከቡትን ተሸከርካሪ መያዝ ሁከት መሆኑን በመግለጽ የሥር ፍ/ቤት ውሳኔ እንዱፀናላቸው ተከራክረዋል። አመልካችችም መከራከሪያውን የሚያጠናክር የመልስ መልስ በመስጠት የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ሉሻር ይገበዋል በማለት ሞግቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና መሰረታዊ የክርክሩ ይዘት ጠቅለል ባለ መልኩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ችልቱም የግራ ቀኙን ክርክር ጉዲዩ ለዚህ ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ማስቀረቢያ ነጥብ አኳያ አግባብነት ካለው ህግ ጋር በማገናዘብ መርምሯል።
ከክርክሩ አመጣጥ መረዲት እንደሚቻለው ተጠሪ ክስ ያቀረቡት በፍርድ አፈፃፀም በጨረታ በመግዛት በህግ አግባብ የባለቤትነት መብት ባቋቋምኩበት ተሽከርካሪ ላይ አመልካች ሁከት ፈጥሮ በጉልበት የወሰደብኝ በመሆኑ ሁከቱ ተወግድ ንብረቱን ሉመልስልኝ ይገባል በሚል ነው።
አመልካች በበኩለ ክስ የቀረበበትን ንብረት የያዘው ከቀድሞ የንብረቱ ባለቤት ከሆነው ድርጅ ላይ መሰብሰብ የሚገባው ቀረጥ እና ታክስ በመኖሩ፤ እንዱሁም ተሽከርካሪው ከቀረጥ ነፃ ወደ ሀገር የገባ ሲሆን በተሽከርካሪው ላይ ሉከፈል የሚገባው ቀረጥ እና ታክስ ሳይከፈል የቀረጥ እና ታክስ ነፃ መብት ላልተሰጠው ሰው የተላለፈ በመሆኑ ለማስከፈል በሚል እንደሆነ ገልፆ ድርጊቱ የሁከት ተግባር አይደለም በማለት ተከራክሯል። ተጠሪ ክስ የቀረበበትን ተሽከርካሪ በህግ አግባብ በጨረታ ገዝቻለሁ ከማለት ባለፈ ከንብረቱ ላይ የሚፈለግ ቀረጥ እና ታክስ የለም በሚል ያቀረቡት ክርክር የለም።
በመሰረቱ አመልካች መስሪያ ቤት ከቀረጥ እና ታክስ ጋር በተያያዘ የጉምሩክ ቁጥጥር የማድረግ ስልጣን በህግ የተሰጠው አካል ነው። ይህም ስልጣን የጉምሩክ ህጉ መከበሩን ለማረጋገጥ የሚያስችል ማናቸውንም እርምጃ መውሰድን የሚያጠቃልል ሆኖ ከዚህ ውስጥ አንደ ቀረጥ እና ታክስ ያልተከፈለባቸውን ወይም አስፈላጊው የጉምሩክ ስነ ስርዓት ያለተፈፀመባቸውን ንብረቶች እና እቃዎች ተከታትል በመያዝ የሚፈለገውን እዲ ማስከፈል ስለመሆኑ ከጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀፅ 141፣ 2(22)፣ 2(38)፣ 143 እና 147 ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብ መረዲት ይቻላል። በጉምሩክ ህጉ መሰረት ቀረጥ እና ታክስ ሉከፈልባቸው ከሚገባቸው ንብረቶች ውስጥ አንደ ከቀረጥ ነፃ መብትን በመጠቀም ወደ ሀገር የገባ እቃ ተመሳሳይ መብት ለላለው ሰው/አካል በሚተላለፍበት ጊዜ ስለመሆኑ ከአዋጁ አንቀፅ 130(1 እና 2)ድንጋጌ መገንዘብ ይቻላል። እንግዱህ በአዋጁ መሰረት ቀረጥ የሚከፈለው በገቢ እና ወጭ ንብረት ላይ በመሆኑ መከፈል ሲገባው ያልተከፈለ እዲ ካለ ከንብረቱ ተለይቶ የማይታይ በመሆኑ በአዋጁ መሰረት ለአመልካች መስሪያ ቤት የተሰጠው መከፈል ሲገባው ያልተከፈለ የቀረጥ እዲን ተከታትል የማስከፈል ሥልጣን በዋናነት የንብረቱን ባለቤት ሳይሆን ንብረቱን እራሱን የሚከተል ይሆናል። እናም አመልካች ከአንድ ንብረት ላይ የሚፈለግ ቀረጥ እና ታክስ ስለመኖሩ እስካረጋገጠ ድረስ ንብረቱ በማናቸውም መንገድ በተላለፈላቸው ሶስተኛ ወገኖች እጅ ጭምር በመያዝ መከፈል ያለበትን የመንግስት እዲ የማስከፈል በህግ የተረጋገጠ መብት አለው ማለት ነው።
ወደ ተያዘው ጉዲይ ስንመለስ አመልካች የተከሰሰው በፍርድ አፈፃፀም በሀራጅ ተሽጦ ተጠሪ እጅ የገባን ንብረት በቁጥጥር ስር በማዋል የሁከት ተግባር ፈፅሟል በሚል ነው። የሁከት ክስ የቀረበበት አካል ደግሞ የሥራውን አደራረግ የሚፈቅድ ለእርሱ የሚናገርለት መብት መኖሩን በፍጥነት እና በማይታበል ዓይነት ማስረዲት ከቻለ ድርጊቱ የሁከት ተግባር ልባል የማይቻል ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1149(3) ድንጋጌ ተቃራኒ ንባብ መረዲት ይቻላል። ከዚህ አንፃር ለክሱ መሰረት የሆነው ተሽከርካሪ ከቀረጥ ነፃ በሆነ መብት ወደ ሀገር የገባ ሆኖ ተገቢው ቀረጥ እና ታክስ ሳይከፈልበት በፍርድ አፈፃፀም ምክንያት በሀራጅ ተሽጦ ለአሁን ተጠሪ የተላለፈላቸው ስለመሆኑ ግራ ቀኙን ያላከራከረ ጉዲይ ነው። ከንብረቱ ላይ የሚፈለግ እዲ መኖሩ ከተረጋጠ ደግሞ ንብረቱ በፍርድ ቤት የአፈፃፀም ሃራጅ ለተጠሪ መተላለፈ በአመልካች የመቆጣጠር ህጋዊ ስልጣን ላይ የሚያስከትለው ለውጥ አይኖርም። እናም አመልካች ክስ የቀረበበትን ተሽከርካሪ በቁጥጥር ስር እንዱውል ማድረጉ በህግ የተሰጠውን የመቆጣጣር ኃላፉነት ተግባራዊ አድርጓል ከሚባል በቀር ድርጊቱ ህገ ወጥ የሁከት ተግባር ነው የሚያስብል አይደለም። ጉዲዩ ይህ ሆኖ እያለ የስር ፍርድ ቤቶች የአመልካች እርምጃ የሁከት ተግባር ነው ማለታቸው የጉዲዩን ባህሪ እና በአዋጁ መሰረት ለአመልካች የተሰጠውን የጉምሩክ ቁጥጥር ስልጣን ያላገናዘበ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/90002 ላይ ታህሳስ 26/2013 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/267595 ላይ ግንቦት 23/2013 ዓ.ም በዋለው ችልት የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
ተገቢው ቀረጥ እና ታክስ ያልተከፈለበት ንብረት በፍርድ አፈፃፀም ምክንያት በሀራጅ በልላ ሰው እጅ የገባ ቢሆንም እንኳን አመልካች ከንብረቱ ላይ የሚፈለገውን ቀረጥ እና ታክስ ለማስከፈል ንብረቱን ተከታትል የመያዝ ከህግ የመነጨ ስልጣን ያለው በመሆኑ ድርጊቱ የሁከት ተግባር ነው የሚባል አይደለም።
የዚህን ሰበር ሰሚ ችልት ክርክር ወጪ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
በመዝገቡ ላይ የተሰጠ የእግድ ትዕዛዝ ካለ ተነስቷል። ይፃፍ።
መዝገቡ ተዘግቷል። ይመለስ።
No topics extracted.