No summary available.
ጥር 25/2014 ዓ.ም ዳኞች፡ እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሳዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡- አቶ እምራን ታጁ ተጠሪ፡- የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበው ጉዲይ በህገ ወጥ መንገድ ቡና ማጓጓዝ ወንጀልን የሚመለከት ነው።
ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ የቀረበውም አመልካች ጥፊተኛ ተበል በተቀጣበት በህገ ወጥ መንገድ ቡናን የማጓጓዝ ወንጀል አግባብነት ያለው ህግ በፋዳራል መንግስቱ የወጣው አዋጅ ቁጥር 1051/2009 ነው? ወይስ በኦሮሚያ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት የወጣው አዋጅ ቁጥር 160/2002 ነው? የሚለውን እና ተያያዥ ነጥቦችን መርምሮ ለመወሰን ነው።
ክርክሩ የተጀመረው የአሁን ተጠሪ ሐምል 15/2012 ዓ.ም ፅፍ በአሁን አመልካች እና በልላ አንድ ግለሰብ ላይ የኢ.ፋ.ዳ.ሪ. የወንጀል ህግ አንቀፅ 32(1(ሀ)) እና የኦሮሚያ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት የቡና ጥራትን ለመወሰን የወጣው አዋጅ ቁጥር 160/2002 አንቀፅ 23(4) እና 23(7) ድንጋጌን ጠቅሶ በቡኖ በደላ ወረዲ ፍርድ ቤት ባቀረበው የወንጀል ክስ ነው። የቀረበውም ክስ ሁለት ነው። የመጀመሪያው አመልካች እና ላላኛው ግለሰብ የኢ.ፋ.ዳ.ሪ. የወንጀል ህግ አንቀፅ 32(1(ሀ)) እና ክስ የቀረበበትን አዋጅ አንቀፅ 23(4) ድንጋጌን በመተላለፍ በህገ ወጥ መንገድ ቡናን ለማጓጓዝ አስበው ሐምል 13/2012 ዓ.ም መጀመሪያ ከላሉቱ 9፡50 ሰዓት ላይ በክሱ ዝርዝር ውስጥ በተጠቀሰው የስልክ ቁጥር የኬላ ጥበቃ ሰራተኛ ወደሆኑት ም/ሳጅን አሉ አባሚልኪ ወደተባለት የፖሉስ ባልደረባ የእጅ ስልክ ላይ “ትንሽ እቃ ነው! 1,500 ብር!” የሚል እና “እሺ 2000 ብር!” የሚል የስልክ የፅሁፍ መልዕክት ከላኩ በኋላ የንግድ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ እና የይለፍ ወረቀት ሳይኖራቸው ጠቅላላ የዋጋ ግምቱ ብር 442,000(አራት መቶ አርባ ሁለት ሺህ ብር) የሆነ 65 ኩንታል ቀሽር ቡና የሰላዲ ቁጥሩ በክሱ ዝርዝር በተጠቀሰው አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ በህገ ወጥ መንገድ ጭነው ከጮራ ከተማ ወደ በደላ ከተማ በመጓዝ ላይ እንዲለ ኬላ ላይ በተደረገ ፍተሻ እጅ ከፈንጅ የተያዙ በመሆኑ በህገ ወጥ መንገድ ቡና የማጓጓዝ ወንጀል ፈፅመዋል የሚል ነው።
ሁለተኛው ክስ ደግሞ ተከሳሾቹ የኢ.ፋ.ዳ.ሪ. የወንጀል ህግ አንቀፅ 32(1(ሀ)) እና ክስ የቀረበበትን አዋጅ አንቀፅ 23(7) ድንጋጌን በመተላለፍ በ1ኛ ክስ የተገለፀውን ድርጊት ሲፈፅሙ የተጠቀሰውን ቡና የቡናውን ጥራት በሚጎዲ እና ባልተፈቀደ ማዲበሪያ ጨምረው ያጓጓዙ በመሆኑ በጥራት አሰራር እና ቡና ገበያ ላይ ህገወጥ ተግባር ፈፅመዋል የሚል ነው።
አመልካችም ሆኑ ላላኛው ተከሳሽ የቀረበባቸውን ክስ ክደው በመከራከራቸው የግራ ቀኙ ክርክር እና ማስረጃ ተሰምቷል። በመጨረሻም የዐቃቤ ህግ ማስረጃዎች በክሱ መሰረት አስረድተው እያለ አመልካች እና ላላኛው ግለሰብ ባቀረቧቸው የሰው ምስክሮች የዐቃቤ ህግ ክስ እና ማስረጃውን አላስተባበለም በሚል በተከሰሱባቸው ሁለቱም ክሶች ጥፊተኛ ተብለው እያንዲንዲቸው በ6 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እስራት እና በብር 5,000(አምስት ሺህ ብር) መቀጮ እንዱቀጡ ተወስኗል።
በስር ፍርድ ቤት ተከሳሾች ይግባኝ ባይነት ይህንኑ ውሳኔን በይግባኝ የተመለከተው የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን የይግባኝ ክርክር ከሰማ በኋላ ከአመልካች ጋር ተከስሶ የነበረውን ግለሰብ በነፃ አሰናብቷል። አመልካችን በተመለከተ ደግሞ በ1ኛ ክስ ብቻ ጥፊተኛ በማለት በስር ፍርድ ቤት የተሰጠውን ውሳኔን በማሻሻል አመልካች በ4 ዓመት ከ2 ወር እስራት እና በብር 4,500(አራት ሺህ አምስት መቶ ብር) እንዱቀጣ ወስኗል። በዚሁ ውሳኔ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የአመልካችን ይግባኝ በወንጀል ህግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 195(1) መሰረት ሰርዟል። የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በበኩለ “በጉዲዩ ላይ ተፈፃሚነት ያለው በፋዳራል መንግስት የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1051/2009 ነው? ወይስ የክልለ አዋጅ ቁጥር 160/2002 ነው?” የሚል ነጥብ ይዞ ጉዲዩን በማስቀረብ ካራከረ በኋላ “ተፈፃሚነት ያለው የክልለ አዋጅ መሆን አለበት!” በማለት በአብላጫ ድምፅ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔን አፅንቷል። ከአብላጫው ድምፅ የተለየ አቋም የያዙት ሁለት ዳኞች ደግሞ ለጉዲዩ ተፈፃሚ ላሆንም የሚገባውም ሆነ ለአመልካች የሚጠቅመው በፋዳራል መንግስቱ የወጣው አዋጅ በመሆኑ ይኸው አዋጅ ተፈፃሚ ላደረግ ይገባል በማለት በሀሳብ ተለይተዋል።
የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ነው። አመልካች ሰኔ 22/2013 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ በስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ ተፈፅጽሟል ያለውን መሰረታዊ የህግ ስህተት ጠቅሶ በዚህ ችልት እንዱታረምለት ጠይቋል። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ከላይ በዚህ ፍርድ መግቢያ ላይ የተጠቀሰውን ነጥብ ለማጣራት ሲባል ጉዲዩ ለዚህ ሰበር ሰሚ ችልት እንዱቀርብ በመታዘዙ ግራ ቀኙ በፅሁፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ችልቱም ጉዲዩን ከግራ ቀኙ የፅሁፍ ክርክር፣ ከማስቀረቢያ ነጥቡ እና ከስር ፍርድ ቤቶች መዝገብ ይዘት አንፃር አግባብነት ካለው ህግ ጋር በማገናዘብ መርምሯል።
ለቀረበው ጉዲይ አግባብነት ያለው ህግ በፋዳራል መንግስቱ የወጣው አዋጅ ነው? ወይስ በክልል መንግስቱ የወጣው አዋጅ ነው? የሚለውን ነጥብ ከማየታችን በፉት ስለ የፋዳራል መንግስት እና የክልል መንግስታት የስልጣን ምንጭ፤ ስላላቸው ስልጣን ምንነት እና ተግባራዊ ውጤቱ በትንሹ ማየት ያስፈልጋል። እንግዱህ የኢትዮጵያ ፋዳራላዊ ዳሞክራሲያዊ ህገ መንግስት በአዋጅ ቁጥር 1/1987 ከታወጀ በኋላ በሀገሪቱ የስልጣን አወቃቀር በፋዳራል እና በክልልች የተዋቀረ መሆኑን በህገ መንግስቱ አንቀፅ 50(1) ተመልክቷል። የፋዳራልም ሆነ የክልል መንግስታት የስልጣን ምንጭም ህገ መግስቱ ስለመሆኑ በዚሁ የህገ መንግስቱ አንቀፅ ንዐስ አንቀፅ 8 ስር ተደንግጓል።
ለሁለቱም መንግስታት የተሰጠው ስልጣንም የህግ አውጪነት፣ የህግ አስፈፃሚነት እና የዲኝነት ስልጣን ስለመሆኑ በአንቀፅ 50(2) ስር ተመልክቷል። በዚህ መልኩ ለፋዳራል መንግስቱ የተሰጠው ስልጣን በህገ መንግስቱ አንቀፅ 51 ስር የተዘረዘረ ሲሆን ለክልልች የተሰጠው ስልጣን ደግሞ በአንቀፅ 52 ስር በዝርዝር ተመልክቷል።
በህገ መንግስቱ ለሁለቱም መንግስታት የተሰጠውን ስልጣን በጥቅለ በሶስት ከፍል ማየት ይቻላል። የመጀመሪያው ለፋዳራል መንግስቱ ብቻ ተለይቶ የተሰጠ ስልጣን(Exclusive Federal Jurisdiction) ነው። ሁለተኛው ለክልል መንግስታት ብቻ ተለይቶ የተሰጠ ስልጣን(Exclusive Regional Jurisdiction) ነው። ሶስተኛው ደግሞ ለሁለቱም መንግስታት በጋራ የተሰጣቸው ስልጣን(Concurrent Jurisdiction) ነው። በህገ መንግስቱ ለክልል መንግስታት ከተሰጠው ስልጣን ውስጥ አንደ በግልፅ ተለይቶ ለፋዳራል መንግስቱ ብቻ ወይም ለፋዳራል መንግስት እና ለክልል መንግስታት በጋራ ባልተሰጠ ጉዲይ ላይ ስለመሆኑ የህገ መንግስቱ አንቀፅ 52(1) ይደነግጋል።
የፋዳራልም ሆነ የክልል መንግስታት በዚህ መልኩ የተሰጣቸው መንግስታዊ ስልጣን ተግባራዊ ሲያደርጉ አንዲቸው የላላኛቸውን ስልጣን ማክበር እንዲለባቸው የህገ መንግስቱ አንቀፅ 50(8) ያዝዛል።
በቀረበው ጉዲይ የቡና ጥራት ቁጥጥርን አስመልክቶ የህግ አውጪነት ስልጣኑ የፋዳራል መንግስቱ አልያም የክልል መንግስታት ስለመሆኑ በህገ መንግስቱ በግልፅ የተመለከተ ነገር የለም።
በተጨባጭ ደግሞ የፋዳራል መንግስቱ አዋጅ ቁጥር 1051/2009፤ የኦሮሚያ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ደግሞ አዋጅ ቁጥር 160/2002 አውጥተው ሁለቱም ህግጋት በስራ ላይ ይገኛለ። ከዚህ አንፃር በአጠቃላይ በሁለቱ ህግጋት መካከል መጣረስ ቢኖር አልያም በተለያየ ምክንያት የህግ መረጣ ውስጥ የሚገባበት አስገዲጅ ሁኔታ ቢፈጠር “የትኛው ህግ ተፈፃሚ ላሆን ይገባል?” የሚለው ጉዲይ በዚህ ችልት ትርጉም የሚሰጥበት አይደለም። ሆኖም የቀረበው ጉዲይ ወንጀልን የሚመለከት በመሆኑ ይህንኑ ነጥብ አስመልክቶ በሁለቱ ህግጋት የተመለከተውን የወንጀል ኃላፉነት እና የቅጣት ድንጋጌዎችን ብቻ በመመርመር ከወንጀል ህግ ጠቅላላ መርህ እና ከህገ መንግስቱ አንፃር እልባት መስጠት ያስፈልጋል።
በፋዳራል መንግስቱም ሆነ በክልለ መንግስት የወጡት ህግጋት በህገ ወጥ የቡና አጓጓዦች ላይ የወንጀል ኃላፉነትን የሚጥለ ቢሆንም በወንጀለ ጥፊተኛ በተባለት አጥፉዎች ላይ ሉጣል ስለሚገባው የወንጀል ቅጣት አስመልክቶ በመካከላቸው ጉልህ የሆነ ልዩነት አለ። በፋዳራል መንግስቱ የወጣው አዋጅ በወንጀል ጥፊተኛ ሆነው በተገኙት ላይ ከ1 ዓመት የማያንስ እና ከ3 ዓመት የማይበልጥ እስራት እና ከብር 20,000(ሃያ ሺህ ብር) እስከ 40,000(አርባ ሺህ ብር) የሚደርስ የገንዘብ ቅጣት ሉወሰን እንደሚችል በአዋጁ አንቀፅ 19(10) ደንግጓል። በአንፃሩ በኦሮሚያ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት የወጣው አዋጅ ደግሞ ለተመሳሳይ የወንጀል ጥፊት በአጥፉው ላይ በወንጀል ህግ የበለጠ የሚያስቀጣ ካልሆነ በቀር ከ3 ዓመት የማያንስ እና ከ5 ዓመት የማይበልጥ እስራት እና በብር 50,000(ሃምሳ ሺህ ብር) የገንዘብ ቅጣት ሉወሰን እንደሚችል በአዋጁ አንቀፅ 23(4) ስር ደንግጓል።
እንግዱህ እነዚህ ሁለቱም ህግጋት በወንጀል ረገድ ቅጣትን የሚደነግጉ ልዩ ህጎች ናቸው። የዚህ ዓይነት ልዩ ህጎች በተለየ አኳኋን ካልደነገጉ በቀር በመደበኛው የወንጀል ህግ በተመለከቱት መርሆዎች የሚመሩ ለመሆኑ የኢ.ፋ.ዳ.ሪ. የወንጀል ህግ አንቀፅ 3 ይደነግጋል። በወንጀል ህጉ ከተመለከቱት ጠቅላላ የወንጀል ህግ መርሆዎች ውስጥ አንደ ስለ ወንጀል እና አፈፃፀሙ የሚደነግገው በአንቀፅ 23 ስር የተመለከተው ነው። በዚሁ መሰረት አንድ ድርጊት ወንጀል ነው ተብል የሚያስቀጣው ህገ ወጥነቱ እና አስቀጪነቱ በህግ በተደነገገ ጊዜ መሆኑን፤ ወንጀል ተደረገ የሚባለውም ወንጀለን የሚያቋቁሙት ህጋዊ፣ ግዙፊዊ እና ሞራላዊ ፍሬ ነገሮች በአንድነት ተሟልተው ሲገኙ ብቻ ለመሆኑ የዚሁ አንቀፅ ንዐስ አንቀፅ 1 እና 2 ድንጋጌ ያስገነዝባል።
በዚህ መልኩ ስለ ወንጀልች እና አፈፃፀማቸው እንዱሁም ስለሚያስከትለት ቅጣት አጠቃላይ መርህን እና ዝርዝር ድንጋጌዎችን የያዘውን የወንጀል ህግ የማውጣት ስልጣን ያለው የፋዳራል መንግስቱ የህገ አውጪ አካል የሆነው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስለመሆኑ በህገ መንግስቱ አንቀፅ 55(5) ይደነግጋል። የወንጀል ጉዲይን በተመለከተም ክልልች ያላቸው ብቸኛ ስልጣን በፋዳራል ህግ አውጪው አካል ስለ ወንጀል በተደነገገው ህግ በግልፅ ባልተመለከቱ ጉዲዮች ላይ ህግ ማውጣት ስለመሆኑ በዚሁ አንቀፅ ስር በግልፅ ተመልክቷል። ከዚህ ውጭ ክልልች የወንጀል ጉዲይን አስመልክቶ በፋዳራል መንግስቱ ህግ በግልፅ በተደነገገባቸው ጉዲዮች ላይ የፋዳራል መንግስቱን ህግ በሚቃረን መልኩ የራሳቸውን ህግ የሚያውጁበት የህግ አግባብ የለም።
ከዚህ ጋር በተያያዘ አንድ አብነት ማንሳት ይቻላል። የኢ.ፋ.ዳ.ሪ. ህገ መንግስት ከታወጀ በኋላ የቡና ንግድ እና ጥራት ቁጥጥርን አስምልክቶ የታወጀው የመጀመሪያው ህግ በፋዳራል መንግስቱ የወጣው የቡና ጥራት ቁጥጥርና ግብይት አዋጅ ቁጥር 602/2000 ነው። ይህ አዋጅ በህገ ወጥ እና አግባብ ባልሆነ መንገድ ቡናን ከቦታ ቦታ የሚያዘዋውሩ ሰዎችን በወንጀል ተጠያቂ በማድረግ በልላ ህግ የበለጠ የሚያስቀጣ ካልሆነ በቀር ከ3 ዓመት በማያንስ እና ከ5 ዓመት በማይበልት እስራት እና በብር 50,000(ሃምሳ ሺህ ብር) የሚቀጡ መሆኑን በአንቀፅ 15(4) ስር ደንግጓል።
የክልል መንግስታትም አዋጁን ለማስፈፀም የሚያስፈልጋቸውን ህግ ማውጣት እንደሚችለ በአዋጁ አንቀፅ 19(3) ስር ተመልክቷል።
በልላ በኩል የኦሮሚያ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት የህግ አውጪ አካል ለሆነው ጨፋ በክልለ ህገ መንግስት የተሰጠው የህግ አውጪነት ስልጣን ከፋዳራል ህገ መንግስቱ እና የፋዳራል መንግስቱ ላልች ህጎችን የማይፃረሩ ልዩ ልዩ ህጎችን ማውጣት ስለመሆኑ የተሻሻለው የክልለ ህገ መንግስት አዋጅ ቁጥር 46/1994 አንቀፅ 49(3(ሀ)) ይደነግጋል። አሁን ለክርክር ምክንያት የሆነው የክልለ ጨፋ ያወጣው አዋጅም ከዚህ አዋጅ በኋላ በ2002 ዓ.ም የወጣ ሲሆን የወንጀል ኃላፉነቱን እና ቅጣቱን አስመልክቶ ሙለ በሙለ ልባል በሚችል ደረጃ ከዚሁ አዋጅ የተቀዲ መሆኑን ከድንጋጌዎቹ ይዘት መገንዘብ ይቻላል። ከዚህ በግልፅ መረዲት የሚቻለው የክልለ ጨፋ ከቡና ንግድ እና ጥራት ቁጥጥር ጋር በተያያዘ ቢያንስ ከወንጀል ኃላፉነት እና ቅጣት አንፃር በፋዳራል መንግስቱ አዋጅ የተደነገገውን ህግ መቀበለን እና ያከበረ መሆኑን ነው። አሁን ላይ ችግሩ የተፈጠረው ለክልለ ህግ መውጣት መሰረት የነበረው የፋዳራለ መንግስት አዋጅ በአዋጅ ቁጥር 1051/2009 ተሻሽል በቀደመው አዋጅ ከፍ ተደርጎ የተቀመጠው የወንጀል ቅጣት በአዱሱ አዋጅ ሲቀንስ የክልለ አዋጅ ባለበት መቆየቱ ነው።
መነሻ ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን የወንጀል ጉዲይን አስመልክቶ ክልልች በፋዳራል መንግስቱ የወጣውን የወንጀል ይዘት ያለው ህግ በሚቃረን መልኩ ህግ ሉያወጡ አይችለም። ወጥቶ እንኳን ቢገኝ ተፈፃሚ ላሆን የሚገባው በፋዳራል መንግስት የወጣው ህግ ነው። ከዚህ አንፃር አመልካች ጥፊተኛ በተባለበት በህገ ወጥ መንገድ ቡናን የማጓጓዝ ወንጀል በፋዳራል መንግስቱ አዋጅ ቁጥር 1051/2009 አንቀፅ 19(10) እና በኦሮሚያ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት አዋጅ ቁጥር 160/2002 አንቀፅ 23(4) መካከል በወንጀል ቅጣት ረገድ አለመጣጣም ያለ በመሆኑ ከላይ በፍርድ ሀተታው ውስጥ በተጠቀሰው ምክንያት ለጉዲዩ አግባብነት ያለው እና ተፈፃሚም ላደረግ የሚገባው የፋዳራል መንግስቱ አዋጅ ቁጥር 1051/2009 ነው። ጉዲዩ ይህ ሆኖ እያለ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ለጉዲዩ ተፈፃሚነት ያለው የክልለ አዋጅ ነው በሚል ትርጉም የስር ፍርድ ቤቶችን ስህተት ሳያርም ማለፈ የጉዲዩን ልዩ ባህሪ እና በህገ መንግስቱ ለፋዳራል መንግስት እና ለክልል መንግስታት የተሰጠውን ስልጣን መሰረት ያላደረገ መሰረታዊ የህግ አተረጓጎም ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል።
በዚሁ አግባብ በክልለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተሻሽል በተሰጠው የጥፊተኝነት ፍርድ መሰረት የወንጀል ቅጣቱ በፋዳራል መንግስቱ የቡና ግብይትና ጥራት ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1051/2009 አንቀፅ 19(10) መሰረት ተሰልቷል። በዚህ አንቀፅ ስር የተቀመጠው ቅጣት ከ1 ዓመት የማያንስ እና ከ3 ዓመት የማይበልጥ እስራት እና ከብር 20,000(ሃያ ሺህ ብር) እስከ ብር 40,000(አርባ ሺህ ብር) የሚደርስ የገንዘብ ቅጣት ነው። ለዚህ የወንጀል ድርጊት ስራ ላይ ባለው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 ደረጃ እና እርከን ያልወጣለት በመሆኑ በከፍተኛው ፍርድ ቤት በተገለፀው አግባብ የወንጀለ ደረጃ ከባድ በሚል ተወስዶል። በቅጣት አወሳሰን መመሪያው አንቀፅ 19 መሰረት በሚደረግ ስላትም “ከባድ የወንጀል ደረጃ” ለሚለው ያለው ቅጣት ከ2 ዓመት እስከ 2 ዓመት ከ6 ወር እስራት እና እስከ ብር 26,666.67(ሃያ ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ከ67/100) የሚደርስ ነው። በተጨማሪም በስር ፍርድ ቤት ተቀባይነት ያገኙት አንድ የቅጣት ማክበጃ እና አንድ የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች በዚህም ችልት ተወስደዋል።
ይኸው ታሳቢ ተደርጎ በአጠቃላይ አመልካች ጥፊተኛ በተባለበት የወንጀል ድርጊት በ2(ሁለት) ዓመት ከ6(ስድስት) ወር እስራት እና በብር 4,500(አራት ሺህ አምስት መቶ ብር) የገንዘብ ቅጣት እንዱቀጣ ተወስኗል። በመሆኑም ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
የኦሮሚያ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ/337085 ላይ ግንቦት 11/2013 ዓ.ም በዋለው ችልት በክልለ የበታች ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች የተሰጠውን የጥፊተኝነት ፍርድ እና የቅጣት ውሳኔን በማፅናት የሰጠው ውሳኔ በወንጀል ህግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 195(2(ለ(2))) መሰረት ተሻሽሎል።
በኢ.ፋ.ዳ.ሪ. ህገ መንግስት መሰረት የክልል መንግስታት የወንጀል ጉዲይን አስመልክቶ በፋዳራል መንግስቱ ከወጣው ህግ ጋር የሚቃረን ወይም የማይጣጣም ህግ የማውጣት ስልጣን ያልተሰጣቸው በመሆኑ በህገ ወጥ መንገድ ቡናን ከማጓጓዝ ወንጀል ጋር በተያያዘ ተፈፃሚነት ያለው በፋዳራል መንግስቱ የወጣው አዋጅ ቁጥር 1051/2009 ነው።
በውሳኔ ተራ ቁጥር 2 ስር በተገለፀው አግባብ በስር ፍርድ ቤቶች በአመልካች ላይ የተላለፈው የጥፊተኝነት ፍርድ እና የቅጣት ውሳኔ በወንጀል ህግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 195(2(ለ(2))) መሰረት ተሻሽል አመልካች በአዋጅ ቁጥር 1051/2009 አንቀፅ 19(10) ስር በ2(ሁለት) ዓመት ከ6(ስድስት) ወር እስራት እና በብር 4,500(አራት ሺህ አምስት መቶ ብር) የገንዘብ ቅጣት እንዱቀጣ ተወስኗል።
ተሻሽል በተሰጠው የቅጣት ውሳኔ መሰረት ተከታትል እንዱያስፈፅም ለክልለ ማረሚያ ቤቶች አስተዲደር ይፃፍ።
መዝገቡ ተዘግቷል ይመለስ።
No topics extracted.