በወንጀል ምስክሮችና ጠቋሚዎች ጥበቃ አዋጅ 699/2003 አንቀጽ 4/1 (ተ) እስከ (ሰ) እና (ዘ) ስር የተዘረዘሩት ጥበቃዎች በባሕርያቸው ከክርክር ሂደቱ ጋር የተያያዙ ሆነው በአስፈፃሚ አካል የሚወሰደ ሳይሆን በአዋጁ አንቀጽ 23 (1) እና (2) ድንጋጌ መሰረት በምክንያት ተደግፈው የሚቀርቡ የፍርድ ቤቶች የመጀመሪያ ደረጃ ስልጣን ስለመሆናቸው በወንጀል ምስክሮችና ጠቋሚዎች ጥበቃ አዋጅ 699/2003 አንቀጽ 4 ስር የተዘረዘሩ የጥበቃ ዓይነቶች ውስጥ የጥበቃ ዓይነቱ ሲወሰን የተከሳሾችን ሕገ መንግስታዊ መብት ሉጎዲ በማይችል መልኩ መሆን እንዲለበት የሚደነግገውን የአዋጁን አንቀጽ 5/3 ከግምት ያስገባ፣ በአንቀጽ 3/ሀ ስር የተገለፀውን ቅድመ ሁኔታ ሉያሟላና የሚቀርብ ምክንያትም በቂ፤ አሳማኝ እና በአዋጁ ምስክሮች ከመጋረጃ ጀርባ እና በዝግ ችልት ሆነው እንዱሰሙ የተፈቀደበትን ዓላማ የሚያሳካ ሆኖ በተገኘ ጊዜ የፍደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ እና እነ እስክንድር ነጋ (5 ሰዎች)
No summary available.
ጥቅምት 29/2014 ዓ.ም ዳኞች፡ እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሳዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡- የአማራ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ተጠሪ፡- ባህሩ ታዬ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበው ጉዲይ ህግ ወጥ የጦር መሣሪያ ማዘዋወር ወንጀል ክስን የሚመለከት ነው። የሰበር አቤቱታው የቀረበው የአማራ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ/99038 ላይ ጥር 24/2012 ዓ.ም በዋለው ችልት የስር ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ በመሻር ተጠሪን ጥፊተኛ ከተባለበት ወንጀል በነፃ በማሰናበት የሰጠውን የመጨረሻ ውሳኔ በመቃወም ነው።
ክርክሩ የተጀመረው የአሁን አመልካች በአሁን ተጠሪ ላይ የኢ.ፋ.ዱ.ሪ. የጦር መሣሪያ አስተዲደር እና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1177/2012 አንቀፅ 4(2) ድንጋጌን ጠቅሶ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጠዲ ንዐስ ወረዲ ፍርድ ቤት ባቀረበው የወንጀል ክስ ነው። የክሱም ጭብጥ ተጠሪ በተጠቀሰው የአዋጁ ድንጋጌ የተመለከተውን ክልከላ በመተላለፍ የንምራ ቁጥሩ C21 mm 16-08-04-167 የሆነ የቱርክ ሽጉጥ፤ ሶስት የአብራራው ጥይት እና አንድ የክላሽ ጥይት በህገ ወጥ መንገድ ይዞ ከጎንደር ወደ ማክሰኚት አቅጣጫ በመኪና በመጓዝ ላይ እያለ ሐምል 11 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ በግምት 4፡00 ሰዓት አካባቢ ጠዲ ከተማ ዩኒቨርሲቲው አካባቢ ኬላ ላይ በተደረገ ፍተሻ የተያዘ በመሆኑ ህገ ወጥ የጦር መሣሪያ ማዘዋወር ወንጀል ፈፅሟል የሚል ነው።
ተጠሪም ለዚሁ ክስ በሰጠው መልስ የተጠቀሰውን ሽጉጥ ለራሱ መጠበቂያነት በሚል ገዝቶ ይዞ የተገኘ መሆኑን፤ የተጠቀሱትን ጥይቶች ግን የፈተሸው ፖሉስ ኪሱ ውስጥ ከትቶ ከኪሱ አገኘሁ ያለ እንጂ የእርሱ አለመሆናቸውን ጠቅሶ ክዶል። በዚሁ ምክንያት የአመልካች ምስክሮች ቀርበው እንዱሰሙ ተደርጓል። የቀረቡት ምስክሮችም በተባለው ቀን፣ ቦታ እና ሰዓት ተጠሪ በክሱ ዝርዝር ውስጥ የተጠቀሱትን የጦር መሳሪያዎች ይዞ ሲጓዝ ኬላ ላይ በተደረገ ፍተሻ መያዙን በመግለፃቸው ተጠሪ ክሱን እንዱከላከል ተነግሮታል። ሆኖም ተጠሪ የመከላከያ ማስረጃ እንደላለው በማሳወቁ የመከላከል መብቱ ታልፍ ክሰ በቀረበበት አንቀፅ ስር ጥፊተኛ ተብል በ2 ዓመት ከ3 ወር እስራት እና በብር 1,000(አንድ ሺህ ብር) መቀጮ እንዱቀጣ ተወስኗል።
በዚሁ ውሳኔ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተጠሪን ይግባኝ በወንጀል ህግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 195(1) መሰረት ሰርዟል። የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በበኩለ የግራ ቀኙን የሰበር ክርክር ከሰማ በኋላ በሰጠው ውሳኔ ክስ የቀረበበት አዋጅ ከመፅናቱ በፉት በነበሩት ህጎች እና አሰራሮች ሳይመዘገብ ወይም ፈቃድ ሳይሰጣቸው የጦር መሳሪያ የያዙ ወይም የሚጠቀሙ ሰዎች በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ተቆጣጣሪ ተቋሙ በሚያወጣው የጊዜ ሰላዲ መሰረት ቀርበው ማስመዝገብ እንደሚችለ የሚደነግግ መሆኑን፤ ሆኖም በወቅቱ ተቆጣጣሪ ተቋሙ የጊዜ ሰላዲ አውጥቶ ወደ ተግባር ያልገባ በመሆኑ ተጠሪ ለክሱ ምክንያት የሆነውን የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘቱ ብቻውን ወንጀል አለመሆኑን ጠቅሶ የስር ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ በመሻር ተጠሪን በነፃ አሰኗብቷል።
የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ነው። አመልካች መጋቢት 23/2013 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ በክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ውሳኔ ላይ ተፈፅሟል ያለውን መሰረታዊ የህግ ስህተት ጠቅሶ በዚህ ችልት እንዱታረምለት ጠይቋል። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ተጠሪ ለክሱ ምክንያት የሆነውን የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘቱ በወንጀል የሚያስቀጣ ተግባር አይደለም በሚል በነፃ የተሰናበተበት አግባብ ከጦር መሣሪያ አስተዲደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1177/2012 አንቀፅ 4(2)፣ 6 እና 23(2) አንፃር በዚህ ችልት እንዱመረምር በመደረጉ ተጠሪ የፅሐፍ መልስ እንዱሰጥበት ታዟል። ሆኖም ተጠሪ በተደረገለት የጋዜጣ ጥሪ መሰረት ቀርቦ መልስ ባለመስጠቱ ክርክሩ በላለበት ታይቶ እንዱወሰን ታዟል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት በአጭሩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ችልቱም በሰበር አጣሪው ችልት ሉጣራ ይገባዋል ተብል የተያዘውን ነጥብ ከአመልካች የሰበር ቅሬታ፤ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ መርምሯል።
እንደተመረመረውም የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ተጠሪን ከቀረበበት ክስ በነፃ ያሰናበተው ክስ የቀረበበትን አዋጅ ለማስፈፀም የመቆጣጣር ስልጣን የተሰጠው አካል አዋጁ ከመውጣቱ በፉት ፈቃድ የላለውን የጦር መሳሪያ የያዙ ሰዎች መሳሪያውን አስመዝግበው ፈቃድ ለመውሰድ የሚችለበትን የጊዜ ሰላዲ ወስኖ ወደ ስራ ያልገባ በመሆኑ ተጠሪ በዚሁ ጊዜ ውስጥ መሳሪያውን ይዞ መገኘቱ ወንጀል አይደለም በሚል ምክንያት ነው። በመሰረቱ ክስ የቀረበበት አዋጅ አዋጁ ከመውጣቱ በፉት በፍቃድም ሆነ ያለፈቃድ የተያዙ መሳሪያዎች በአዋጁ መሰረት ሉመዘገቡ የሚገባበትን ሁኔታ ከማስቀመጥ ባለፈ በተቀመጠው የጊዜ ወሰን ውስጥ መሳሪያውን ይዞ መገኘት አያስጠይቅም በሚል የተቀመጠ የእፍይታ ጊዜ የለም። ከመነሻውም ቢሆን ህጋዊ ፈቃድ የላለውን የጦር መሳሪያን ይዞ መገኘት ወንጀል ስለመሆኑ በወንጀል ህጉ አንቀፅ 808 ስር ተደንግጓል።
የአዋጅ ቁጥር 1177/2012 አንደ መሰረታዊ ዓላማም ለብዙሃን ጥቅም ሲባል በአንድም ይሁን በልላ መንገድ ያለ ፈቃድ በግለሰቦች እጅ የገቡ የጦር መሳሪያዎች ላይ ተገቢውን ህጋዊ ቁጥጥር በማድረግ ወደ ሥርዓት ማስገባት የሚቻልበትን ሁኔታ መፍጠር ስለመሆኑ በአዋጁ መግቢያ ላይ ከሰፈረው መሰረተ ሀሳብ መገንዘብ ይቻላል።
ይህንን ለማድረግ ይቻል ዘንድም አዋጁ ከመፅናቱ በፉት ህጋዊ ፈቃድ ሳይኖራቸው የጦር መሳሪያ የያዙ ሰዎች በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ተቆጣጣሪው ተቋም በሚያወጣው የጊዜ ሰላዲ መሰረት በአካል ቀርበው ፈቃድ መጠየቅ እና በአዋጅ መሰረት የተመለከቱ መስፈርቶችን አሟልተው በተቆጣጣሪ ተቋሙ ፈቃድ መውሰድ ያለባቸው ስለመሆኑ በአዋጁ አንቀፅ 23(2) ስር ተመልክቷል። ከአዋጁ መሰረታዊ ዓላማ ጋር ተገናዝቦ ሲታይ የዚህ ድንጋጌ ዋናው ዓላማ ፈቃድ የላላቸው ሰዎች ፈቃድ በማውጣት ሂደት ላይ መሳሪያውን ይዘው ሲንቀሳቀሱ ሉያጋጥማቸው ከሚችለው የህጋዊነት ጥያቄ ለመጠበቅ እንጂ እስከ አንድ ዓመት ድረስ ያለማንም ጠያቂ የጦር መሳሪያ ዝውውርን ለመፍቀድ አይደለም።
በተያዘው ጉዲይ ተጠሪ በእጁ ተይዘዋል ከተባለት የጦር መሳሪያዎች ውስጥ ጥይቶቹን በተመለከተ ከመካድ ባለፈ ያመነውን የጦር መሳሪያን አስመልክቶ ህጋዊ ፈቃድ ያለው ለመሆኑ አልያም ፈቃድ በማውጣት ሂደት ላይ እያለ የተያዘ ስለመሆኑ ያቀረበው ክርክር የለም። እንዱያውም የአመልካች ማስረጃ የተሰሙት በተካደው ፍሬ ነገር ላይ መሆኑን እና በተጠሪ እጅ ተገኝቷል የተባለውን ሽጉጥ አስመልክቶ የጥፊተኝነት ውሳኔ የተሰጠው ተጠሪ በችልት በሰጠው የእምነት ቃል መነሻነት ስለመሆኑ የስር ፍርድ ቤት መዝገብ ያስገነዝባል። ተጠሪ በመሳሪያው ላይ ፈቃድ ያላወጣው ተቆጣጣሪ ተቋሙ ወደ ስራ ባለመግባቱ ምክንያት ነው በሚል ያቀረበው ክርክርም ሆነ ከዚህ አንፃር የተረጋጠ ነገር የለም። ይህ በላለበት የክልለ ሰበር ሰሚ ችልቱ የአዋጁን ድንጋጌ ባልተገባ መንገድ ተርጉሞ ተጠሪን ከወንጀል ተጠያቂነት ነፃ ማድረጉ በእርግጥም ሉነቀፍ የሚገባው መሰረታዊ የህግ አረዲድ እና አተረጓጎም ስህተት ሆኖ ተገኝቷል።
በመጨረሻም ተጠሪ ፈፅሟል የተባለው የወንጀል ድርጊት ህገ ወጥ የጦር መሳሪያን ይዞ ሲጓዝ ተገኝቷል በሚል ነው። ይህ ድርጊት የወንጀል ተግባር ተደርጎ የተደነገገው በአዋጁ አንቀፅ 4(1) ስር ሲሆን ክሱ የቀረበው አንቀፅ 4(2) ተጠቅሶ መሆኑን ለመገንዘብ ተችሎል። በተጨማሪም ይህ የወንጀል ድርጊት ስለሚያስከትለው የወንጀል ተጠያቂነት የተመለከተው በአዋጁ አንቀፅ 22(2) ስር ሆኖ እያለ የስር ፍርድ ቤት ቅጣቱን ሲያሰላ አንቀፅ 22(1) ብል ጠቅሷል። ፍርድ ቤቱ የጠቀሰው ቅጣት በአንቀፅ 22(2) ስር የተመለከተውን ቅጣት ቢሆንም በድንጋጌው አፃፃፍ ላይ የአርታዑ ግድፈት ያለ ለመሆኑ ለመገንዘብ ተችሎል። በመሆኑም እነዚሁ ጥቃቅን ስህተቶች ታርመው የወረዲው እና የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ውሳኔ ሉፀና የሚገባው ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
የአማራ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ/99038 ላይ ጥር 24/2013 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ በወንጀል ህግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 195(2(ሀ)) መሰረት ተሽሯል።
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የጠዲ ንዐስ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/020407 ላይ ሐምል 17/2012 ዓ.ም የሰጠው የጥፊተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ እንዱሁም ይህንኑ ውሳኔን በማፅናት የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/02-34525 ላይ ነሓሴ 22/2012 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ ፀንቷል።
የአማራ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ፖሉስ ኮሚሽን ተጠሪን አፈላልጎ በተገኘበት በመያዝ ለክልለ ማረሚያ ቤት አስተዲደር እንዱያስረክብ፤ የክፍለ ማረሚያ ቤት ተጠሪ ተይዞ ሲቀርብለት ቀድሞ በተሰጠው ውሳኔ መሰረት ቀሪ የእስራት ቅጣቱን ተከታትል እንዱያስፈፅም ይፃፍ።
መዝገቡ ተዘግቷል። ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.