ከገጠር የእርሻ መሬት ኪራይ ውል ጋር በተያያዘ በልዩ ሕግ የተደነገገ የይርጋ ጊዜ ከላለ ተፈፃሚነት የሚኖረው የይርጋ ጊዜ በፍ/ብ/ህ/ቁጥር 1845 ስር የተደነገገው ስለመሆኑ ይርጋን በሚመለከት መቃወሚያ ላይ ውሳኔ ላሰጥ የሚገባው የክስ ምክንያትን መሰረት በማድረግ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.33 (2 እና 3)፣ 80፣ 222 (1/ረ እና ሸ) እና 234(1/ሐ)
No summary available.
የሰ.መ.
ነሐሴ 10 ቀን 2013 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሣዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡- የፍደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ተጠሪዎች፡-
የሰበር አቤቱታው ላቀርብ የቻለው አመልካች ሐምል 12 ቀን 2013 ዓ.ም ጽፍ ባቀረበው የሰበር አቤቱታ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ. ግንቦት 04 ቀን 2013 ዓ.ም የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዓቃቤ ሕግ ምስክሮች ላይ ተጋረጡ የሚላቸውን ስጋቶች በምክንያት አስደግፍ እንዱያቀርብ በማድረግ መርምሮ እንዱወስን ሲል የሰጠው ውሳኔ፤ ጉዲዩ የተመለሰለት የስር ከፍተኛው ፍርድ ቤትም በመ. ሰኔ 22 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለው ችልት ምስክሮች በግልጽ ችልት እንዱሰሙ ሲል የሰጠው ውሳኔ እና ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ. የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት አቤቱታ በማቅረቡ ነው።
የአሁን አመልካች በአሁን ተጠሪዎች ላይ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረበውን ክስ ለማስረዲት የቆጠራቸው ምስክሮች ስለ ወንጀል ምስክሮች እና ጠቋሚዎች ጥበቃ የወጣ አዋጅ ቁጥር 699/2003 አንቀጽ 6/1/ለ መሰረት ጥበቃ የተደረገላቸው መሆኑን በመግለጽ አስራ ስድስቱ ምስክሮች በአዋጁ አንቀጽ 4/1/ቀ መሰረት ምስክርነታቸው በዝግ ችልት እንዱሰማ፤ አምስቱ ምስክሮች ደግሞ በአዋጁ አንቀጽ 4/1/በ መሰረት በአካል ሳይታዩ ከመጋረጃ ጀርባ ሆነው እንዱመሰክሩ ይታዘዝለት ዘንድ ዲኝነት ጠይቋል።
ጉዲዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት ተጠሪዎች በጉዲዩ ላይ አስተያየት እንዱሰጡበት ካደረገ በኋላ የምስክሮች ማንነት ቀድሞ የታወቀ በመሆኑ የጥበቃውን አስፈላጊነት ዋጋ ያሳጣዋል፤ በልላ በኩል ዓቃቤ ሕግ ምስክሮች በተጨባጭ ሉደርስባቸው የሚችል ከባድ አደጋ/ስጋት እንዲለ በበቂ ሁኔታ ያላረጋገጠ በመሆኑ አቤቱታ ተቀባይነት የለውም በማለት ውድቅ አደርጎታል።
አመልካች ይህን ብይን በመቃወም ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የይግባኝ አቤቱታ ያቀረበ ቢሆንም ይግባኙ የቀረበለት ፍርድ ቤት የአመልካች አቤቱታ በጊዜያዊ ትዕዛዝ ላይ የቀረበ ነው በማለት ውድቅ አድርጎታል።
አመልካች በመቀጠል ይህን ትዕዛዝ በመቃወም ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ አቅርቦ ችልቱ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ የካቲት 10 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለው ችልት አመልካች ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ያቀረበው ይግባኝ በጊዜያዊ ትዕዛዘ ላይ የቀረበ ሳይሆን የመጨረሻ ውጤት ባለው ብይን ላይ የቀረበ እና ይግባኝ የሚባልበት በመሆኑ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በውሳኔ የዘጋውን መዝገብ በማንቀሳቀስ አመልካች ያቀረበውን የይግባኝ ክርክር መርምሮ ተገቢውን እንዱወስን ሲል ጉዲዩን መልሶለታል።
ጉዲዩ የተመለሰለት የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትም ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ የምስክሮችን ጥበቃ በተመለከተ ስልጣኑ የዓቃቤ ሕግ ብቻ ነው፤ ፍርድ ቤቶች ጉዲዩን መርመረው መወሰን አይችለም በማለት በዓቃቤ ሕግ የቀረበውን መከራከሪያ ውድቅ በማድረግ ዓቃቤ ሕግ በዝግ ችልት እና ከመጋረጃ ጀርባ ምስክሮች ሉሰሙ ይገባል የሚልበትንና ምስክሮች ላይ ተጋረጡ የሚላቸውን ስጋቶች በምክንያት አስደግፍ እንዱያቀርብ ካደረገ በኋላ መርምሮ ተገቢውን እንዱወስን ሲል ጉዲዩን ለስር ከፍተኛው ፍርድ ቤት መልሶለታል።
ጉዲዩ የተመለሰለት የስር ከፍተኛው ፍርድ ቤት በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ትዕዛዝ መሰረት አመልካች ምክንያቶቹን በዝርዝር እንዱያቀርብ በሰጠው ትዕዛዘ አመልካች በቀን 19/09/2013 ዓ.ም ጽፍ ባቀረበው ማመልከቻ የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ተቋም ምስክሮች ጥበቃ ላደረግላቸው እንደሚገባ የወሰነው ስለምስክሮች እና ሉደርስባቸው ስለሚችል ጥቃት ዝርዝር የስጋት ትንተና ከሰራ በኋላ ነው፤ ከጥበቃ ስምምነት ጋር ተያያዥነት ያላቸው ጉዲዮች በሕግ በጥብቅ ሚስጥርነት ተፈርጀው በጥብቅ የሚጠበቁ ናቸው፤ ፍርድ ቤቱ በአዋጁ አንቀጽ 23 ላይ በተሰጠው ስልጣን መሰረት የተወሰኑ የጥበቃ ዓይነቶች በአግባቡ መደረጉን የማረጋገጥ ሃላፉነቱን ሲወጣ እያንዲንደን የምስክር ጥበቃ ውሳኔ መነሻ የስጋት ትንታኔ ከዓቃቤ ሕግ መስሪያ ቤቱ አመራሮች እጅ እንዱቀርብ በማዘዝ አልያም ተከራካሪ ወገኖች ባልተገኘንበት እና የሚቀርቡ ምስክሮች እነማን እንደሆኑ አንዲች ቦታ ሆኖ መከታተል በማይቻልበት ስፍራ አስቀርቦ በማድመጥ ለመረዲት ወይም ፍርድ ቤቱ ማናቸውንም አግባብነት ያላቸውን ከችልት ውጭ ያለ ማጣሪያዎችን እንዱያደርግ እንጠይቃለን፤ በምስክሮች ወይም በቤተሰቦቻቸው ላይ ሉደርስ የሚችለውን ጥቃት ስጋት የሚያመላክቱ ሁኔታዎችን በስጋት ትንተናው መሰረት ለችልቱ በእያንዲንደ ምስክር ደረጃ የሚቀርብ ቢሆን የምስክሮቹን ማንነት እንዱታወቅ የሚያደርግ ውጤት ይኖረዋል፤ ጥበቃ ተደርጎላቸው ቃላቸውን እንዱሰጡ የምንጠይቃቸው ምስክሮች በምንም ሁኔታ ፍርድ ቤት በግልጽ ችልት ቀርበው ለመመስከር እንደማይችለ ማረጋገጫ ሰጥተውናል፤ ምስክሮቹ በግልጽ ችልት ቀርበው ለመሰማት ፍቃደኛ ያልሆኑት ማንነታቸው ቢታወቅ ከተጠሪዎች ደጋፉዎች የሚደርስባቸውን የበቀል እርምጃ በመፍራት ነው፤ ተጠሪዎች የፖለቲካ ርዕዮትን በሀይል ለማሳካት ሰዎችን ለመግደል እና ሰዎች ላይ ጥቃት ለማድረስ ደጋፉዎችን መልምለው ጥቃት ያደረሱ እና ጥቃት ለማድረስ ዝግጅት ላይ የነበሩ እንደሆኑ ምስክሮቻችን በቅርበት ከማወቃቸው በተጨማሪ ለመርማሪ ፖሉስ ቀርበው የምስክርነት ቃላቸውን በመስጠት የሕግ ምስክር ሆነዋል፤ ተጠሪዎች ለፖለቲካ ዓላማ መሳካት ባለስልጣኖችን ለመግደል ሰዎችን እንደሚያሰለጥኑ በክሳችን ተመልክቷል፤ ተጠሪዎች አዘጋጅተዋል ካልናቸው ምልምል እርምጃ ወሳጆች መሀከል የተወሰኑትን መቆጣጠር ቢቻልም ቀሪዎቹ በማሕበረሰብ ውስጥ ተደብቀው የሚገኙ ናቸው፤ በጥበቃ ስር የሚንቀሳቀስ የመንግስት ባለስልጣንን ለመግደል የሚዘጋጅ ሀይል መንገደ ላይ እንቅፊት የሚሆን ማናቸውንም ሰው በማሕበረሰብ ውስጥ በቀሩና ተጠሪዎች ባደራጅዋቸው ሰዎች ወይም ላልች ዓላማውን በሚደግፈ ሀይልች ምስክሮች ላይ ጥቃት ሉያደርሱ ይችላለ የሚል ግምት መውሰድ ተገቢ ነው፤ በዋነኝነት ሉታወቅ የሚገባው ምስክሮች ያለባቸውን ስጋት በልላ በማንኛውም የጥበቃ ዓይነት ማስወገድ የሚቻል አለመሆኑ ነው፤ በዚሁ መሰረት፡ቁጠራቸው አምስት ለሆኑት ምሰክሮች በአዋጁ አንቀጽ 4/1/በ መሰረት በአካል ሳይታዩ ከመጋረጃ ጀርባ በመሆን የምስክርነት ቃላቸውን እንዱሰጡ የምንጠይቀው ምስክሮቻችን እና ቤተሰቦቻቸው ከታወቁ በቀላለ በሕይወታቸው ላይ ጭምር አደጋ ሉደርስ እንደሚችል ከባድ ስጋት ያደረባቸው በመሆኑ፤
ምስክርነት ቃላቸውን የሰጡባቸው ተጠሪዎች ብዛት ያላቸው ደጋፉዎች እና ተከታዮች ያሎቸው ከመሆኑ የተነሳ በአንድ ቀን በተደረገላቸው ጥሪ እና ቅስቀሳ በመነሳሳት ቁጥራቸው 14 የሆኑ ሰዎች ሕልፈት እና በሚልዮኖች የሚደርስ ንብረት ውድመት እንዱደርስ ያደረጉ መሆናቸውን ጠቅሰው ቀጥታ በእነርሱ እና በደጋፉዎቻቸው ፉት ብንመሰክር ሕይወታችን አደጋ ላይ ይወድቃል የሚል ስጋት ያለባቸው በመሆኑ፤ ከቀጥታ አካላዊ ጥቃት እና ዛቻ በዘለለ የተጠሪዎች ደጋፉዎች የተለያዩ ሰዎችን ስም በማሕበራዊ ሚድያ በመዘርዘር በተጠሪዎች ላይ የመሰከሩ ናቸው በማለት በፋስቡክ የግለሰቦችን ስም ሲለጥፈ የነበረና በዚህ ጽሁፍ ስም ከመዘርዘሩ በተጨማሪ ስማቸው የተዘረዘረ ግለሰቦች የዓቃቤ ሕግ ምስክር ናቸው በሚል ማሕበረሰቡ እንዱያገላቸው እና ማንኛውም እርምጃ እንዱወሰድባቸው ሲዛት እና ቅስቀሳ ሲደረግ የነበረ መሆኑ፤ በሽብር ክስ ላይ ምስክር የሆነ ግለሰብ ያለምንም ጥፊት እንዱገደል ሰው ተመድቦበት የነበረ በመሆኑ፤ እንዱህ ዓይነት ምደባ በርካታ ሰው ላይ የተደረገ በመሆኑ በተከሳሾች እና በደጋፉዎቻቸው ፉት ብንመሰክር ድጋሚ ለሞት መቅረብ ይሆናል በማለት ስጋታቸውን በማቅረባቸው ነው።
ቁጥራቸው 16 የሆኑት የዓቃቤ ሕገ ምሰክሮች በአዋጁ አንቀጽ 4/1/ቀ መሰረት በዝግ ችልት እንዱሰሙልን የምንጠይቀው ከዚህ ቀደም በቀዲሚ ምርመራ ወቅት በተጠሪዎች ተከታዮች እና ደጋፉዎች አማካኝነት ምስክር ናቸው በሚል የጠረጠሯቸውን ግለሰቦች ላይ ማስፈራሪያ ዛቻ የተሰነዘረባቸው በመሆኑ ከጉዲዩ ጋር በተያያዘ በአንድ ምስክር ላይ ሽጉጥ በመተኮስ የመግደል ሙከራ የተፈጸመበት በመሆኑ፤ ምስክሮቹ በግልጽ ችልት መመስከር ለጥቃት የሚዲርጋቸው መሆኑን በተደጋጋሚ በመግለጻቸው ነው፤ ስለሆነም ቁጥራቸው 5 የሆኑት ምስክሮች በአካል ሳይታዩ ከመጋረጃ ጀርባ በመሆን የምስክርነት ቃላቸውን እንዱሰጡ፤ ቁጥራቸው 16 የሆኑት ምስክሮች ደግሞ በዝግ ችልት እንዱሰሙ ትዕዛዝ እንዱሰጥልን በማለት ጠይቋል።
ተጠሪዎች በሰጡት አስተያየት ዓቃቤ ሕግ ግን ሰራሁት ባለው የስጋት ትንተና ላይ በምስክሮች ላይ ብቻ ሉደርስ ይችላል የሚለውን አደጋ ከመተንተን በቀር በተጠሪዎች መብት ላይ የሚያስከትለውን የመብት ጥሰት ታሳቢ አላደረገም፤ ምስክሮች ከመጋረጃ ጀርባ እንዱመሰክሩ ቢደረግ ተጠሪዎች መስቀለኛ ጥያቄ በመጠየቅ የቀረበባቸውን ክስ የመከላከል መብታቸውን ያጣብባል፤ ከጥበቃ ተጠቃሚ ያልቀረበን ስጋት ዓቃቤ ሕግ ትንተና እንዱሰራበት አያደርግም፤ ዓቃቤ ሕግ በምስክሮች ላይ ደርሷል የሚለውን ስጋት በተጨባጭ ሁኔታ ያላረጋገጠ በመሆኑ አቤቱታው ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
ፍርድ ቤቱም ዓቃቤ ሕግ ምስክሮቼ ከመጋረጃ ጀርባ ሆነው ይሰሙልኝ ሲል ላቀረበው ጥያቄ በቂ ምክንያት ቀርቧል? ወይስ አልቀረበም? በዝግ ችልት ይሰሙልኝ የሚላቸው 16 ምስክሮች በተመለከተ ዓቃቤ ሕግ ያቀረበው ምክንያት ከዚህ ቀደም ማንነታቸው ታውቆ ዛቻና ማስፈራራት የደረሰባቸው ምስክሮች በዝግ ችልት ቀርበው እንዱሰሙ ቢደረግ በዓቃቤ ህግ በኩል የሚነሳውን ስጋት ይቀርፊል?
ወይስ አይቀርፍም? የሚለትን ጭብጦችን በመያዝ ጉዲዩን መርምሮ በአዋጅ ቁጥር 699/2003 አንቀጽ 3/1 የወንጀል ድርጊቱ ያለምስክሩ ወይም ያለጠቋሚው ምስክርነት ወይም ጥቆማው በልላ በማናቸውም መንገድ ሉረጋገጥ ወይም ሉደረስበት የማይችል ሲሆን እና በምስክሩ፤ በጠቋሚው ወይም በቤተሰቡ ሕይወት፤ አካላዊ ደሕንነት፤ ነጻነት ወይም ንብረት ላይ ከባድ አደጋ ይደርሳል ተብል ሲታመን ነው በማለት ይደነግጋል፤ በዚህ አንቀጽ ‛ከባድ አደጋ“ በሚል የተገለጸው ሀረግ በከፍተኛ ጥንቃቄና የተከሳሾችን መብቶች ባማከለ እና በማያጣብብ መልኩ መተርጎም አለበት፤ ዓቃቤ ሕግ ተጠሪዎች የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች በመሆናቸው እና ብዙ ደጋፉዎች ያላቸው በመሆኑ በምስክሮች እና በቤተሰቦቻቸው ላይ ጉዲት ሉያደርሱ ይችላለ በማለት የሰጠው ምክንያት መላምትና ይህንኑ ምስክሮቹ ቀርበው ለፍርድ ቤት እንዱያስረደ ከመጠየቁ በቀር የተጠሪዎችን እና የደጋፉዎቻቸውን የቀደመ የሕይወት ታሪክና ባሕርይ የወንጀል አደገኝነት በተመሳሳይ ለመረዲት የሚያስችል አይደለም፤ ከዚሁ በተቃራኒ ተጠሪዎችም ሆኑ ደጋፉዎቻቸው ከዚህ ቀደም ባለው የፍርድ ቤት ውልም ሆነ ጊዜያት ምንም ዓይነት የፍርድ ሂደቱን የሚያውክ ተግባር አለማሳየታቸው የወንጀል አደገኝነታቸውን የሚስረዲ አይደለም፤ ተጠሪዎች የፖለቲካ አመራር መሆናቸውና ደጋፉዎቻቸውም የነዚሁ ግለሰቦች ደጋፉ መሆናቸውም በአደገኝነት የሚያስፈርጅ አይደለም፤ በክሱ የተዘረዘረው የወንጀል ተግባር በማስረጃ እስካልተረጋገጠ ድረስ ክሱን ግምት ማድረግ የተጠሪዎችን ነጻ ሆኖ የመገመት መብት ወደ ጎን የሚያደርግ ነው፤ በዝግ ችልት እንዱሰሙ ከተጠየቀው 16 ምስክሮች ውስጥ አንድ ምስክር በሽጉጥ የመግደል ሙከራ የተደረገበት እና የተጠሪዎች ደጋፉዎች በማሕበራዊ ሚዱያ ምስክሮች ናቸው ያለትን ሰዎች ስም ሲያጠፈ እንደነበር በዓቃቤ ሕግ መገለጹ ምስክሮች በተጠሪዎች ደጋፉዎች መለየታቸውን የሚያስረዲ በመሆኑ ምስክሮች በዝግ ችልት የሚሰሙበትን ዓላማ ያሳጣዋል፤ ተጠሪዎች የፖለቲካ አመራር መሆናቸው እና ብዙ ደጋፉዎች አላቸው መባለ ብቻውን ዓቃቤ ሕግ ለሚያቀርበው ስጋት በቂ ምክንያት ላሆን አይችልም፤ ዓቃቤ ሕግ በአዋጁ አንቀጽ 4 ስር ከተዘረዘሩ የጥበቃ ዓይነቶች ውስጥ የጥበቃ ዓይነቱን ሲወስን የተጠሪዎችን ሕገ መንግስታዊ መብት ሉጎዲ በማይችል መልኩ መሆን እንዲለበት የሚደነግገውን የአዋጁን አንቀጽ 5/3 ከግምት ያላስገባ እና ከመጋረጃ ጀርባ እና ዝግ ችልት ምስክር ይሰሙልኝ በማለት ያቀረበው ምክንያት በአዋጁ ቁጥር 699/2003 አንቀጽ 3/ ሀ ስር የተቀመጠውን ቅድመ ሁኔታ የሚያሟላ ባለመሆኑ ጥያቄው ተቀባይነት የለውም በማለት ወስኗል። ይህ ውሳኔ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትም ጸንቷል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም ሲሆን ይዘቱም፡- የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ጉዲዮች ለስር ፍርድ ቤት እንዱመለሱ ከሚደረግበት ሥርዓት ውጪ ጉዲዩን ለስር ፍርድ ቤት መመለሱ አግባብ አይደለም፤ የምስክሮችን ጥበቃ በሚመለከት ዓቃቤ ሕግ በምክንያት አስደግፍ ፍርድ ቤት አቅርቦ ማጸደቅ የሚጠበቅበት አካለ መጠን ካላደረሰ ልጅ ጋር የተደረገ ልዩ የጥበቃ ስምምነት ብቻ ነው፤ ከምስክሮች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 699/2003 አንቀጽ 7፤ 8 እና 23/1 መገንዘብ እንደሚቻለው ለፍርድ ቤት የተሰጠው ስልጣን በጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ለምስክሮች የተደረገን ጥበቃ የመፍቀድ እና የመከልከል ሳይሆን ዓቃቤ ሕግ አምኖበት ጥበቃ ላደረገላቸው ምስክሮች ጥበቃው መፈጸሙን ማረጋገጥ ነው፤ ለፍርድ ቤት ማመልከቱም ያስፈለገበት ምክንያት በአዋጁ አንቀጽ 4/1 (ተ) እስከ (ሰ) እና (ዘ) ስር የተዘረዘሩት ጥበቃዎች በባሕርያቸው ከክርክር ሂደቱ ጋር የተያያዙ በመሆናቸው ነው፤ በዘርፈ የዲበረው ዓለም አቀፊዊ ልምድም የምስክሮች ጥበቃ እርምጃ የሚወሰደው በአስፈጸሚው መሆኑን እና ፍርድ ቤቶች የመጀመሪያ ደረጃ ስልጣን የላላቸው መሆኑን የሚያሳይ ነው፤
በምስክሮች ላይ የተጋረጠውን ስጋት በዝርዝር ማቅረብ የምስክሩን ማንነት የመግለጽ ያህል ነው፤
አመልካች ተከራካሪ ወገኖች በላለበት ምስክሮችን ብቻ አስቀርቦ ፍርድ ቤቱ በራሱ መንገድ እንዱያረጋግጥ የጠየቀ ቢሆንም ጥያቄው ተቀባይነት አላገኘም፤ አዋጁ ተፈጻሚ የሚሆነው በሕብረተሰቡ ላይ ስጋት በሚፈጥሩ ከባድ ወንጀልች ላይ ነው፤ ተጠሪዎችም ሆነ ደጋፉዎቻቸው በችልት የሚያሳዩት ባሕርይ መልካም ነው የሚለው ምክንያት ነገሩን ለመወሰን እንደ በቂ መነሻ ሆኖ ሉወሰድ የሚችል አይደለም፤ ዓቃቤ ሕግ ሁለት ምስክሮችን በተመለከተ ያቀረበውን ስጋት ለሁለም ምስክሮች እንደቀረበ ተደርጎ ያልታወቁትን ምስክሮች እንደታወቁ አድርጎ የተሰጠው ውሳኔ ተገቢ አይደለም፤ ስለሆነም በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ የስር ፍርድ ቤት ምስክሮች በግልጽ ችልት እንዱሰሙ ሲል የሰጠው ውሳኔ አግባብነት የወንጀል ምስክሮች እና ጠቋሚዎች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 699/2003 አንቀጽ 3፤ 4/1 (ቀ)፤ 5(1)(3)፤ 7፤ 8፤ 23(1)(2) እንዱሁም ከአዋጁ ዓላማ እና ፍርድ ቤቱ ካለው ሚና ጋር በማገናዘብ ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ በዚህ ችልት እንዱታይ ተደርጓል። ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርጎም አመልካች እና ከ1ኛ- 4ኛ ያለት ተጠሪዎች በጽሐፍ እንዱከራከሩ የተደረገ ሲሆን 5ኛ ተጠሪ መጥሪያ ደርሷቸው መልስ ስላላቀረቡ መብታቸው ታልፎል።
ከ1ኛ እስከ 4ኛ ያለት ተጠሪዎች የሰጡት መልስ ይዘት በአጭሩ፡- በምስክሮች ላይ የተጋረጡ አደጋዎች እና ስጋቶች ካለ በቂ ምክንያት እና ማስረጃ አቅርቦ መከራከር የፍሬ ነገር ክርክር በመሆኑ በሰበር ሰሚ ችልት የሚታይ አይደለም፤ ዓቃቤ ሕግ የይግባኝ አቤቱታ ውድቅ ከተደረገበት በኋላ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ አስቀድሞም ቢሆን ጉዲዩን ለስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሉመልሰው አይገባም ነበር በማለት የሚያቀርበው ክርክር ስነ ስርዓታዊ አይደለም፤ ለምስክሮች ጥበቃ ላሰጥ የሚችለው የጥበቃ ተጠቃሚው ሉደርስበት ይችላል ተብል የሚገመተውን የአደጋ ሁኔታ ብቻ ከግንዛቤ በማስገባት ላሆን እንደማይገባ በአዋጁ አንቀጽ 5/3 ላይ ተደንግጎአል፤ ዓቃቤ ሕግ የምስክሮች ጥበቃን በሚመለከት ፍርድ ቤቱ ስልጣን የለውም በማለት የሚያቀርበው ክርክር የፍርድ ቤቶችን ተፈጥሮአዊ የዲኝነት ስልጣን የሚጻረር ነው፤
የስር ከፍተኛው ፍርድ ቤት ዓቃቤ ሕግ በምስክሮች ላይ የተጋረጠ አደጋ መኖሩን ማረጋገጥ ባለመቻለ ምስክሮች በግልጽ ችልት እንዱመሰክሩ ሲል የሰጠው ውሳኔ ተገቢ ስለሆነ ሉጸና ይገባል የሚል ነው።
አመልካችም የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ የተገለጸው ነው። ይህ ችልትም በሰበር አጣሪው ችልት ያስቀርባል ተብል የተያዘውን ነጥብ ከግራ ቀኙ ክርክር፤ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምሮታል።
ከክርክሩ ሑደት መገንዘብ የቻልነው የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ዓቃቤ ሕግ በተጠሪዎች ላይ ያቀረበውን ክስ ለማስረዲት ከቆጠራቸው ምስክሮች ውስጥ አምስቱ ከመጋረጃ ጀርባ ሆነው እንዱመሰክሩ፤ አሥራ ስድስቱ ደግሞ በዝግ ችልት እንዱመሰክሩ እንዱፈቀድለት የጠየቀ መሆኑን፤ ጉዲዩ የቀረበለት ፍርድ ቤትም ዓቃቤ ሕግ በአዋጁ አንቀጽ 4 ስር ከተዘረዘሩ የጥበቃ ዓይነቶች ውስጥ የጥበቃ ዓይነቱን ሲወስን የተጠሪዎችን ሕገ መንግስታዊ መብት ሉጎዲ በማይችል መልኩ መሆን እንዲለበት የሚደነግገውን የአዋጁን አንቀጽ 5/3 ከግምት ያላስገባ ሲሆን ከመጋረጃ ጀርባ እና ዝግ ችልት ምስክር ይሰሙልኝ በማለት ያቀረበው ምክንያትም በአዋጅ ቁጥር 699/2003 አንቀጽ 3/ ሀ ስር የተቀመጠውን ቅድመ ሁኔታ የሚያሟላ አይደለም በማለት ጥያቄውን ውድቅ ያደረገው መሆኑን ነው። በልላ በኩል ዓቃቤ ሕግ የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ ተገቢ አይደለም በማለት በዋነኝነት የሚከራከረው የምስክሮች ጥበቃ እርምጃ የሚወሰደው በአስፈጸሚው በመሆኑ በምክንያት አስደግፈን ለፍርድ ቤቱ ማጸደቅ አይጠበቅብንም፤ ፍርድ ቤቶችም በዓቃቤ ሕግ የተወሰደውን የምስክሮች ጥበቃ እርምጃ መርምሮ ለማጽደቅ ስልጣን የላቸውም፤ ዓቃቤ ሕግ ሁለት ምስክሮችን በተመለከተ ያቀረበውን ስጋት ለሁለም ምስክሮች እንደቀረበ ተደርጎ ያልታወቁትን ምስክሮች እንደታወቁ ተደርጎ መወሰደ ተገቢ አይደለም በሚል ነው። ስለሆነም በዚህ ችልት ምላሽ ማግኘት ያለበት የክርክሩ መሰረታዊ ጭብጥ:-
ዓቃቤ ሕግ የወሰደውን የምስክሮች ጥበቃ እርምጃ በምክንያት አስደግፍ ለፍርድ ቤቱ ማቅረብ ይኖርበታል? ወይስ አይኖርበትም?
ዓቃቤ ሕግ የወሰደውን የምስክሮች ጥበቃ እርምጃ በምክንያት አስደግፍ ለፍርድ ቤቱ በማቅረብ ማጸደቅ ይኖርበታል ከተባለ አቤቱታው የቀረበለት ፍርድ ቤት የሚኖረው ሚና ምንድነው?
ጉዲዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት ዓቃቤ ሕግ ከመጋረጃ ጀርባ እና በዝግ ችልት ሆነው እንዱሰሙ በማለት በሁለት ዘርፍ በመክፈል ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ የሰጠው ውሳኔ ተገቢ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለት ናቸው።
የመጀመሪያውን ጭብጥ በተመለከተ፡ዓቃቤ ሕግ ከመጋረጃ ጀርባ እና በዝግ ችልት ሆነው እንዱሰሙ የምስክር ጥበቃ እርምጃ ተወስዶል በማለት የሚከራከረው በአዋጁ አንቀጽ 4/1 (ተ) እስከ (ሰ) እና (ዘ) ስር የተዘረዘሩት ጥበቃዎች በባሕርያቸው ከክርክር ሂደቱ ጋር የተያያዙ በመሆናቸው እንጂ አቤቱታችንን በምክንያት አስደግፈን በፍርድ ቤት የማጸደቅ ግዳታ ስላለብን አይደለም በሚል ነው።
በመሰረቱ የዲኝነት ስልጣን በሕግ ተለይቶ ለላላ አካል የተሰጠ ካልሆነ በቀር የፍርድ ቤቶች ስለመሆኑ የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 37 ይደነግጋል። ስለ ወንጀል ምስክሮች እና ጠቋሚዎች በተመለከተ የወጣው አዋጅ ቁጥር 699/2003 አንቀጽ 7 እና 8 ሚንስቴሩ ዓቃቤ ሕግ በሚመለከተው አካል የቀረበለትን የጥበቃ ማመልከቻ መርምሮ ውሳኔ እንደሚሰጥ፤ የቀረበለትን የጥበቃ ማመልከቻ መርምሮ ውሳኔ በሰጠ ጊዜም ከጥበቃ ተጠቃሚው ጋር ስምምነት መፈራረም እንዲለበት ይደነግጋል። ስለ ፍትሕ አካላት ሀላፉነት የሚደነግገው የአዋጁ አንቀጽ 23 (1) እና (2) ድንጋጌ ጉዲዩ የሚመለከተው ፍርድ ቤት በአዋጁ አንቀጽ 4/1 ከፉደል ተራ (ሰ) እስከ (ተ) የተደነገጉት የጥበቃ እርምጃዎች እንደ አግባቡ መወሰዲቸውን የማረጋገጥ ሀላፉነት፤ ጉዲዩ የሚመለከተው ዓቃቤ ሕግም በአዋጁ አንቀጽ 6/1(ለ) መሰረት ጥበቃ ላደረግለት የሚገባ ሰው መጠየቅ በማይችልበት ጊዜ እርሱን በመወከል ለጥበቃ ተጠቃሚነት የሚቀርብ ማመልከቻ ማቅረብ ያለበት ስለመሆኑ፤ በአዋጁ አንቀጽ 4/1 ከፉደል ተራ (ሰ) እስከ (ተ) እንዱሁም በፉደል ተራ (ዘ) የተደነገጉት የጥበቃ እርምጃዎች እንዱወሰደ ለፍርድ ቤት ማመልከት የሚችል ስለመሆኑ ይደነግጋል። እነኚህም ድንጋጌዎች መረጃ በሚሰጥበት የወንጀል ጉዲይ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ከመሰጠቱ በፉትም ሆነ በኋላ ተከሳሽ በጥበቃ ተጠቃሚው መኖሪያ ወይም የስራ ቦታ ወይም ትምህርት ቤት አካባቢ እንዲይደርስ ማገድ፤ የፍርድ ሂደት ተጀምሮ ምስክርነት እስኪሰጥ ድረስ የምስክር ማንነት እንዲይገለጽ ማድረግ፤ ምስክር በዝግ ችልት እንዱሰጥ ማድረግ፤ ምስክርነት በአካል ሳይታይ ከመጋረጃ በስተጀርባ ሆኖ ማንነትን በመሸፈን እንዱሰጥ ማድረግ፤ ማስረጃ በኤላክትሮኒክስ ወይም በልላ የተለየ ዘዳ እንዱቀርብ ማድረግ እና ለምስክሩ ወይም ለጠቋሚው የምክር አገልግልት መስጠት ወይም እንዱያገኝ ማድረግ የሚለት ናቸው። ዓቃቤ ሕግ ተወስዶል የሚለው የጥበቃ እርምጃ እነኚህን ድንጋጌዎች መሰረት በማድረግ የተወሰደ ስለመሆኑ ለስር ፍርድ ቤቱም ሆነ ለዚህ ችልት ባቀረበው ክርክር የገለጸ በመሆኑ በአዋጁ አንቀጽ 23 (1)እና(2) ድንጋጌ መሰረት የጥበቃ እርምጃዎቹ እንዱወሰደ ለፍርድ ቤት ማመልከቻ ማቅረብ ይኖርበታል። ስለሆነም ዓቃቤ ሕግ የምስክሮች ጥበቃ እርምጃ በምክንያት አስደግፋ ለፍርድ ቤት ለማቅረብ አልገደድም በማለት የሚያቀርበው ክርክር ተቀባይነት ያለው አይደለም።
ሁለተኛውን ጭብጥ በተመለከተ፡በአንደኛው ጭብጥ ላይ እንደተገለጸው ዓቃቤ ሕግ ተወስዶል የሚለውን የጥበቃ እርምጃ ለፍርድ ቤት ማመልከት አለበት ከተባለ በቀጣይነት ፍርድ ቤቱ የሚኖረው ሚና ምንድነው የሚለውን እንመልከት።
በአዋጁ አንቀጽ 23/1 ላይ በግልጽ እንደተመለከተው ጉዲዩ ለሚመለከተው ፍርድ ቤት የተሰጠው ሀላፉነት በአዋጁ አንቀጽ 4/1 ከፉደል ተራ (ሰ) እስከ (ተ) የተደነገጉት የጥበቃ እርምጃዎች እንደአግባቡ መወሰዲቸውን የማረጋገጥ ሀላፉነት ነው። ፍርድ ቤቱ ይህ ሀላፉነት እስከ ተሰጠው ጊዜ ድረስ ዓቃቤሕጉ ተወስዶል የሚላቸውን የጥበቃ እርምጃዎች በአግባቡ የተወሰደ መሆናቸውን ባረጋገጠ ጊዜ ማጽደቅ እንደሚችል፤ የጥበቃ እርምጃዎቹ በአግባቡ ያልተወሰደ መሆናቸውን ባረጋገጠ ጊዜ ደግሞ የጥበቃ እርምጃዎቹን ውድቅ ማድረግ እንደሚችል ድንጋጌው ራሱ አመላካች ሲሆን ፍርድ ቤቶች በፉታቸው የቀረቡላቸውን ጉዲዮች ዓይተው ለመወሰን የሚያስችላቸውን ተፈጥሮአዊ ስልጣን መሰረት በማድረግ በመፍቀድ ወይም በመንፈግ ውሳኔ ሉሰጡበት የሚችል ጉዲይ መሆኑን የሚያሳይ ነው።
ስለሆነም ዓቃቤ ሕግ የምስክሮች ጥበቃ እርምጃ የሚወሰደው በአስፈጸሚው እንጂ ፍርድ ቤቶች የመጀመሪያ ደረጃ ስልጣን የላቸውም በማለት የሚያቀርበው ክርክር ተቀባይነት ያለው አይደለም።
የመጨረሻውን ጭብጥ በተመለከተ፡የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 20 የተከሰሱ ሰዎች የተከራካሪዎችን የግል ሕይወት፤ የሕዝብን ሞራል ሁኔታ እና የሐገሪቱን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል ብቻ ክርክሩ በዝግ ችልት እንዱሰማ ካልተወሰነ በቀር ክስ ከቀረበባቸው በኋላ ተገቢ በሆነ አጭር ጊዜ ውስጥ በመደበኛ ፍርድ ቤት ለሕዝብ ግልጽ በሆነ ችልት የመሰማት መብት እንዲላቸው፤ የቀረበባቸውን ማናቸውንም ማስረጃ የመመልከት የቀረቡባቸውን ምስክሮች የመጠየቅ መብት እንዲላቸው ይደነግጋል።
ስለ ወንጀል ምስክሮች እና ጠቋሚዎች በተመለከተ የወጣው አዋጅ ቁጥር 699/2003 አንቀጽ 3/1 በአዋጁ መሰረት የምስክሮች ጥበቃ ተግባራዊ የሚሆነው በሕግ የተመለከተው የጽኑ እሥራት መነሻ ከግምት ሳይገባ አሥር ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆነ ጽኑ እስራት ወይም በሞት ሉያስቀጣ በሚችል የወንጀል ድርጊት ተጠርጣሪ ላይ የሚሰጥ ምስክርነትን ወይም ጥቆማን ወይም የሚካሄድ ምርመራን የሚመለከት ሆኖ የወንጀል ድርጊቱ ያለምስክሩ ወይም ያለጠቋሚው ምስክርነት ወይም ጥቆማ በልላ ማናቸውም መንገድ ሉረጋገጥ ወይም ሉደረስበት የማይችል ሲሆን እና በምስክሩ፤ በጠቋሚው ቤተሰብ፤
ሕይወት፤ አካላዊ ደንንነት፤ ነጻነት ወይም ንብረት ላይ ከባድ አደጋ ይደርሳል ተብል ሲታመን ነው በማለት ይደነግጋል። የዚሁ አዋጅ አንቀጽ 5/3 ላሰጥ የታሰበው ጥበቃ በልላ ሰው መብት እና ሕጋዊ ጥቅም ላይ የሚስከትለው ጉዲት ግምት ውስጥ መግባት እንዲለበት ይደነግጋል። ይህም የተከሰሱ ሰዎች በሕገ መንግስቱ የተረጋገጠላቸው መብት ታልፍ ምስክሮች ከመጋረጃ ጀርባ ወይም በዝግ ችልት እንዱሰሙ ሉፈቀድ የሚችለው ምስክሩ ባደረበት ስጋት ምክንያት ብቻ ሳይመሰክር ቀርቶ በምስክሩ ብቻ ሉረጋገጥ የሚችለውን ወንጀል ተዲፍኖ እንዲይቀር ለማድረግ ዓቃቤ ሕግ የሚያቀርበው ምክንያት በቂ፤
አሳማኝ እና በአዋጁ ምስክሮች ከመጋረጃ ጀርባ እና በዝግ ችልት ሆነው እንዱሰሙ የተፈቀደበትን ዓላማ የሚያሳካ ላሆን ይገባል።
በያዝነው ጉዲይ ዓቃቤ ሕግ አምስቱ ምስክሮች ከመጋረጃ ጀርባ ሆነው እንዱሰሙ በማለት ጥያቄ ያቀረበ ቢሆንም ተፈጸመ የተባለው ወንጀል የሚረጋገጠው በእነዚህ ምስክሮች ብቻ ስለመሆኑ በመግለጽ ያቀረበው ክርክር ስለመኖሩ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ይዘት አያመለክትም፤ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ዓቃቤ ሕግ ከመጋረጃ ጀርባ ሆነው ሉሰሙ ይገባል የሚላቸው ምስክሮች አለ የሚለው ስጋት ተጠሪዎች የፖለቲካ ርዕዮትን በሀይል ለማሳካት ሰዎችን ለመግደል እና ሰዎች ላይ ጥቃት ለማድረስ ደጋፉዎችን መልምለው ጥቃት ያደረሱ እና ጥቃት ለማድረስ ዝግጅት ላይ የነበሩ እንደሆኑ ምስክሮቻችን በቅርበት ከማወቃቸው በተጨማሪ ለመርማሪ ፖሉስ ቀርበው የምስክርነት ቃላቸውን በመስጠት የሕግ ምስክር ሆነዋል፤ ምስክርነት ቃላቸውን የሰጡባቸው ተጠሪዎች ብዙ ደጋፉዎች እና ተከታዮች ያሎቸው ከመሆኑ የተነሳ በአንድ ቀን በተደረገላቸው ጥሪ እና ቅስቀሳ በመነሳሳት ቁጥራቸው 14 የሆኑ ሰዎች ሕልፈት እና በሚልዮኖች የሚደርስ ንብረት ውድመት እንዱደርስ ያደረጉ መሆኑን ጠቅሰው በእነርሱ እና በደጋፉዎቻቸው ፉት ብንመሰክር ሕይወታችን አደጋ ላይ ይወድቃል የሚል ስጋት አለባቸው፤ ከቀጥታ አካላዊ ጥቃት እና ዛቻ በዘለለ የተጠሪዎች ደጋፉዎች የተለያዩ ሰዎችን ስም በማሕበራዊ ሚድያ በመዘርዘር በተጠሪዎች ላይ የመሰከሩ ናቸው በማለት በፋስቡክ የግለሰቦችን ስም ሲለጥፈ የነበረና በዚህ ጽሁፍ ስም ከመዘርዘሩ በተጨማሪ ስማቸው የተዘረዘረ ግለሰቦች የዓቃቤ ሕግ ምስክር ናቸው በሚል ማሕበረሰቡ እንዱያገላቸው እና ማንኛውም እርምጃ እንዱወሰድባቸው ሲዛት እና ቅስቀሳ ሲደረግ ነበር፤
በሽብር ክስ ላይ ምስክር የሆነ ግለሰብ ያለምንም ጥፊት እንዱገደል ሰው ተመድቦበት የነበረ ሲሆን እንዱህ ዓይነት ምደባ በርካታ ሰው ላይ ተደርጓል በሚል ነው።
ሆኖም ዓቃቤ ሕግ ተጠሪዎች የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች በመሆናቸው እና ብዙ ደጋፉዎች ያላቸው በመሆኑ በምስክሮች እና በቤተሰቦቻቸው ላይ ጉዲት ሉያደርሱ ይችላለ በማለት የሚከራከር ቢሆንም የሰጠው ምክንያት መላምት መሆኑ እና ተጠሪዎችም ሆኑ ደጋፉዎቻቸው ከዚህ ቀደም በነበረው የፍርድ ቤት ውልም ሆነ ጊዜያት ምንም ዓይነት የፍርድ ሂደቱን የሚያውክ ተግባር ያላሳዩ መሆኑን በስር ከፍተኛው ፍርድ ቤት ተረጋግጧል። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ዓቃቤ ሕግ ስጋቱን በምክንያት አስደግፍ እንዱያቀርብ በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ባቀረበው አቤቱታ ከቀጥታ አካላዊ ጥቃት እና ዛቻ በዘለለ የተጠሪዎች ደጋፉዎች የተለያዩ ሰዎችን ስም በማሕበራዊ ሚድያ በመዘርዘር በተጠሪዎች ላይ የመሰከሩ ናቸው በማለት በፋስቡክ የግለሰቦችን ስም ሲለጥፈ የነበረና በዚህ ጽሁፍ ስም ከመዘርዘሩ በተጨማሪ ስማቸው የተዘረዘረ ግለሰቦች የዓቃቤ ሕግ ምስክር ናቸው በሚል ማሕበረሰቡ እንዱያገላቸው እና ማንኛውም እርምጃ እንዱወሰድባቸው ሲዛት እና ቅስቀሳ ሲደረግ የነበረ መሆኑ፤ በሽብር ክስ ላይ ምስክር የሆነ ግለሰብ ያለምንም ጥፊት እንዱገደል ሰው ተመድቦበት የነበረ በመሆኑ፤ እንዱህ ዓይነት ምደባ በርካታ ሰው ላይ ተደርጓል በማለት በግልጽ አመልክቷል። ይህም የዓቃቤ ሕግ ምስክሮች ጉዲት ያደርሱባቸዋል በተባለት አካላት የታወቁ መሆኑን የሚሳይ ነው። በልላ በኩል በዝግ ችልት እንዱሰሙ አቤቱታ የቀረበባቸው ምስክሮችም በቀዲሚ ምርመራ ወቅት በተጠሪዎች ተከታዮች እና ደጋፉዎች አማካኝነት ምስክር ናቸው በሚል የጠረጠሯቸው ግለሰቦች ላይ ማስፈራሪያ ዛቻ የተሰነዘረባቸው መሆኑ፤ በአንድ ምስክር ላይ ሽጉጥ በመተኮስ የመግደል ሙከራ የተፈጸመበት መሆኑ በአቃቤ ሕግ አቤቱታ ላይ በግልጽ ተመልክቷል። ይህም ዓቃቤ ሕግ በዝግ ችልት እንዱሰሙ ጥያቄ ያቀረበባቸው ምስክሮች የተለዩ መሆኑን የሚያሳይ ነው።
በአዋጁ መሰረት ምስክሮች ከመጋረጃ ጀርባ ሆነው ወይም በዝግ ችልት እንዱሰሙ ጥበቃ የሚደረግላቸው ተፈጽሟል የተባለው ወንጀል በልላ ሁኔታ ሉረጋገጥ የማይችል በሆነ ጊዜ እና ምስክሩ ባደረበት ስጋት ምክንያት ብቻ ሳይመሰክር ቀርቶ በምስክሩ ብቻ ሉረጋገጥ የሚችለውን ወንጀል ተዲፍኖ እንዲይቀር ለማድረግ ዓቃቤ ሕግ የሚቀርበው ምክንያት በቂ፤ አሳማኝ እና በአዋጁ ምስክሮች ከመጋረጃ ጀርባ እና በዝግ ችልት ሆነው እንዱሰሙ የተፈቀደበትን ዓላማ የሚያሳካ ሆኖ በተገኘ ጊዜ ነው።
በያዝነው ጉዲይ በተጠሪዎች ተፈጽሟል የተባለው ወንጀል በልላ ሁኔታ ሉረጋገጥ የማይችል መሆኑን በመግለጽ በዓቃቤ ሕግ በኩል የቀረበ ክርክር የላለ ከመሆኑ በላይ ዓቃቤ ሕግ ከመጋረጃ ጀርባ እና በዝግ ችልት እንዱሰሙ አቤቱታ ያቀረበባቸው ምስክሮች አስቀድመው የተለዩ መሆኑን ዓቃቤ ሕግ ራሱ ካቀረበው ምክንያት የተረጋገጠ በመሆኑ የዓቃቤ ሕግ ጥያቄ በአዋጁ ምስክሮች ከመጋረጃ ጀርባ እና በዝግ ችልት ሆነው እንዱሰሙ ከተፈቀደበትን ዓላማ ውጪ የቀረበ መሆኑን የሚያሳይ ነው። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖም በክሱ የተዘረዘረው የወንጀል ተግባር በማስረጃ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ክሱን ግምት ማድረግ በዓቃቤ ሕግ በኩል በምስክሮች ላይ ይደርሳል ተብል የተጠቀሰው ስጋት የተጠሪዎችን ነጻ ሆኖ የመገመት መብት የሚጋፊ ነው። ስለሆነም የስር ከፍተኛው ፍርድ ቤት ይህንኑ መሰረት በማድረግ የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ ምስክሮች በግልጽ ችልት እንደሰሙ ሲል የሰጠው ውሳኔ በአግባቡ ነው ከሚባል በቀር የተፈጸመ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት አላገኘንበትም። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ውሳኔ በአብላጫ ድምጽ ሰጥተናል።
ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ.
ሐምል 07 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ ጸንቷል።
No topics extracted.