አንድ ግለሰብ የያዘውን የገጠር እርሻ መሬት በሕግ ስልጣን የተሰጠው የመንግስት አካል ካልሆነ በቀር ላላ ግለሰብ መሬቱ የተያዘው በሕገ-ወጥ መንገድ ነው በማለት አስለቅቆ ሉይዝ የማይችል አቶ የሸዋስ አስማረ እና አቶ ያሲን አሉ
No summary available.
የሰ/መ/ የካቲት 25 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ ተሾመ ሽፈራዉ ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግሥቱ ነጻነት ተገኝ አመልካች፡- አቶ በየነ ከበደ ተጠሪዎች፡-
ጉዲዩ በኪራይ ዉል ተሰጠ የተባለ የገጠር እርሻ መሬት ይዞታ አስለቅቆ ለመረከብ የቀረበ ክስ በተመለከተ በተሰጠ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል የቀረበ የሰበር አቤቱታ የሚመለከት ነዉ። አመልካች በአማራ ክልል በጃዊ ወረዲ ፍርድ ቤት በተጠሪዎች ላይ በመሰረቱት ክስ በወረዲዉ በዱር ማርያም ቀበላ ክልል ዉስጥ የሚገኘዉን በክሱ አዋሳኞቹ የተጠቀሰዉን 6 ቃዲ የገጠር እርሻ መሬቴን ለ5 ዓመታት ለብር 500.00 ለ1ኛ ተጠሪ አከራይቻቸዉ የኪራይ ዘመኑ 2007ዓ/ም ቢያልቅም ተጠሪዎች መሬቴን በጉልበት በመያዝ ኪራይም ባለመክፈል ለመልቀቅ ፈቃደኛ አልሆኑም።ስለሆነም ተጠሪዎች መሬቱን ለቀዉ እንዱያስረክቡኝ ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል።
1ኛ ተጠሪ ለክሱ ባቀረቡት መልስ ለክሱ መነሻ የሆነዉን መሬት ለ10 ዓመት ይዤ እየተጠቀምኩ ስለምገኝ የአመልካች ክስ በይርጋ ቀሪ የሆነ ነዉ በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርበዋል።ፍሬ ነገሩን በተመለከተም መሬቱን የያዝኩት አመልካች የእኔና የባለቤቴ(የሚስቴ) የጡት አባት ስለሆኑ በ1990 ዓ/ም አካባቢዉን ለቀዉ ሲሄደ መሬቴን ያዘዉ ብለዉ በስጦታ ሰጥተዉኛል።በ1996ዓ/ም የመሬት ምዝገባ ሲደረግ ይህ መሬት በእኔ ስም እንዱመዘገብ በኮሚቴዎች ፉት ቀርበዉ ፈርመዋል።አመልካች ክሱን ያቀረቡት የስጦታ ዉለን በመጣስ ስለሆነ ክሱ ዉድቅ ይደረግልኝ በማለት ተከራክረዋል።2ኛ ተጠሪ በተናጠል በሰጡት መልስ መሬቱን የያዝኩት ከ1ኛ ተጠሪ በመከራየት በመሆኑ አመልካች ሉጠይቁኝ አይችለም በማለት ተከራክረዋል።
ፍርድ ቤቱም በመ/ቁጥር 0875 ላይ የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃዎች መርምሮ በቀን 07/10/2010 ዓ/ም በሰጠው ውሳኔ በአማራ ክልል የገጠር መሬት አዋጅ ቁጥር 252/2009 አንቀጽ 55 የገጠር መሬት ክርክር ጋር በተያያዘ የሚነሳ ይርጋ ቀሪ ስላደረገዉ 1ኛ ተጠሪ የአመልካች ክስ የማቅረብ መብት በይርጋ ይታገዲል በማለት ያቀረቡት መቃወሚያ ተቀባይነት የለዉም በማለት ዉድቅ አድርጓል።ፍሬ ነገሩን በተመለከተ በሰጠዉ ዉሳኔ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ መሬት የአመልካች ሕጋዊ ይዞታ መሆኑን 1ኛ ተጠሪ አልካደም። መሬት ሉገኝ የሚችለዉ በአዋጁ ቁጥር 252/2009 አንቀጽ 11 መሰረት በሽግሽግ፣ በስጦታና በዉርስ እንደሆነ በተደነገገዉ መሰረት 1ኛ ተጠሪ መሬቱን በስጦታ አግኝቻለሁ በማለት የተከራከሩ ቢሆንም ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ መሬት በስጦታ የተሰጣቸዉ ስለመሆኑ በአዋጁ አንቀጽ 16/7 መሰረት በጽሁፍ የተደረገና በወረዲዉ የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም ጽ/ቤት የተመዘገበ የስጦታ ዉል በማስረጃነት አላቀረቡም።በተሰጣቸዉ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር የአከራካሪዉ መሬት ባለይዞታ ተደርገዉ የሚቆጠሩት በሕግ አግባብ የወጣ ማስረጃ ሲሆን ነዉ። መሬቱ በ1989ዓ/ም በሽግሽግ ለአመልካች የተሰጠ መሆኑ በግራ ቀኙ ምስክሮችና በሰነድ ማስረጃዎች ተረጋግጧል።2ኛ ተጠሪ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን መሬት ከ1ኛ ተጠሪ በኪራይ መያዛቸዉን አምነዉ ተከራክረዋል።ስለሆነም ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን 6 ቃዲ መሬት ለአመልካች ለቀዉ ሉያስረክቡ ይገባል በማለት ወስኗል።
ተጠሪዎች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለአዊ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ፍርድ ቤቱ በመ/ቁጥር 09-00202 ላይ በቀን 14/10/2010 ዓ/ም በሰጠዉ ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞባቸዋል።
በመቀጠል ተጠሪዎች የሰበር አቤቱታ ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቅርበዉ ችልቱ በመ/ቁጥር 03-79166 ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ በቀን 20/02/2012ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ መሬት በወረራ ወይም በማንኛዉም ሕገ-ወጥ መንገድ ይዞ የሚገኝ ሰዉ የይርጋ ጊዜ ገደብን በይርጋ መቃወሚያነት ሉያነሳ የማይችል መሆኑ በተሻሻለዉ የክልለ የገጠር መሬት አዋጅ ቁጥር 252/209 አንቀጽ 55 ላይ ተደንግጓል።በተያዘዉ ጉዲይ የወረዲ ፍርድ ቤት የተጠሪዎችን የይርጋ መቃወሚያ ዉድቅ ያደረገዉ አዋጁ የይርጋ መቃወሚያ ቀሪ አድርጓል በሚል ቢሆንም ድንጋጌዉ የሚያሳየዉ በሕገወጥ መንገድ መሬት የያዘን ሰዉ እንጅ በሕጋዊ ግንኙነት መሬት የያዘን ሰዉ እንደማይመለከት በመሆኑ የወረዲዉ ፍርድ ቤት የይርጋ መቃወሚያ ዉድቅ በማድረግ የሰጠዉ ዉሳኔ የሕጉን መንፈስ የተከተለ አይደለም።በመሆኑም 1ኛ ተጠሪ መሬቱን ከ10 ዓመት በላይ ይዘዉ እየተጠቀሙበት መሆኑ ያልተካደና የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነዉ።አመልካች በክሳቸዉ መሬቱን ከ2007ዓ/ም ጀምሮ በኪራይ ከዚያ ወዱህ ደግሞ በሕገ-ወጥ መንገድ 1ኛ ተጠሪ ይዘዋል ቢለም ባቀረቧቸዉ ምስክሮች 1ኛ ተጠሪ በኪራይ ስለመያዛቸዉ አላስረደም። በ1ኛ ተጠሪ በኩል የተደመጡት 2ኛ እና 3ኛ መከላከያ ምስክሮች 1ኛ ተጠሪ መሬቱን የያዙት አመልካች ሰጥተዋቸዉ ስለመሆኑ ከመመስከራቸዉም በተጨማሪ የአመልካች 2ኛ ምስክርም በስጦታ መያዛቸዉን እንደሰሙ ከመገለጹ አኳያ ሲታይ የተሻለ ስላስረደ የአመልካች ክስ በአዋጅ ቁጥር 252/2009 አንቀጽ 55 እና በሰ/መ/ ላይ በተሰጠዉ ዉሳኔ መሰረት በ10 ዓመት ይርጋ ቀሪ የሆነ ነዉ በማለት የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡትን ዉሳኔ ሽሯል።
አመልካች በቀን 08/04/2012 ዓ/ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረቡት ከላይ በተገለጸዉ መሰረት በተሰጠ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን የአቤቱታቸዉ ይዘት በአጭሩ፡- የአመልካች ክስ የማቅረብ መብት በይርጋ ቀሪ ሆኗል የሚል ድምዲሜ ላይ የተደረሰዉ የአመልካች ክርክር በአግባቡ ሳይሰማና 1ኛ ተጠሪ መሬቱን የያዙት በኪራይ ነዉ ወይስ በስጦታ የሚለዉ ሳይጣራ ነዉ።ይልቁንም ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ መሬት ሕጋዊ ባለይዞታ አመልካች እንደሆንኩ፣ 1ኛ ተጠሪ መሬቱን በስጦታ አለመያዛቸዉን እና 1ኛ ተጠሪ መሬቱን እስከ 2007ዓ/ም ድረስ በኪራይ እንደያዙና ዉለም እስከ 2007ዓ/ም ድረስ እንዲልተቋረጠ አመልካች ባቀረብኩት ማስረጃዎችና በስር ፍርድ ቤት እንዱቀርቡ በተደረጉ ማስረጃዎች ተረጋግጦ እያለ ክሱ በይርጋ ይታገዲል ተብል በክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የተሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ ይታረምልኝ በማለት አቤቱታቸዉን አቅርበዋል።
የሰበር አጣሪ ችልት አቤቱታውን መርምሮ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን መሬት 1ኛ ተጠሪ በስጦታ ነዉ የያዙት ክሱም በ10 ዓመት ይርጋ ይታገዲል በማለት በክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የተወሰነበትን አግባብ ተጠሪዎች ባለበት እንዱመረመር ትእዛዝ ሰጥቶ ተጠሪዎች በቀን 09/02/2009ዓ/ም የተጻፈ መልስ ያቀረቡ ሲሆን የመልሳቸዉ ይዘት በአጭሩ፡-ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን መሬት የአመልካች የነበረ ቢሆንም መሬቱን 1ኛ ተጠሪ የያዝኩት በኪራይ ሳይሆን አመልካች የጡት አባት በመሆን በ1991 ዓ/ም በአገራችን ወግና ባህል መሰረት በስጦታ ሰጥተዉኝ ነዉ።ኪራይም ከፍዬ አላዉቅም።ከዚህ በኋላም የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር በ1996ዓ/ም ተሰጥቶኛል።የስጦታ ዉለ ተመዘገበም አልተመዘገበ መሬቱ ለ21 ዓመታት በእጄ የሚገኝ ይዞታ መሆኑ ስለተረጋገጠ የአመልካች ክስ በ10 ዓመት ይርጋ ቀሪ የሆነ ነዉ ተብል በመወሰኑ የተፈጸመ ስህተት የለም በማለት ተከራክረዋል።አመልካችም በቀን 16/02/2014ዓ/ም የተጻፈ የመልስ መልስ በማቅረብ ተከራክረዋል።
ከዚህ በላይ አጠር ባለመልኩ የተገለጸዉ የግራ ቀኙን ክርክርና በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ዉሳኔዎች ይዘት የሚመለከት ሲሆን እኛም ሰበር አጣሪ ችልት የያዘዉን ጭብጥ መሰረት በማድረግ በክልለ ፍርድ ቤቶች በተሰጡ ዉሳኔዎች በዚህ ችልት ደረጃ ሉታረም የሚችል የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ መርምረናል።
እንደመረመርነዉም አመልካች በተጠሪዎች ላይ ክስ የመሰረቱት የገጠር እርሻ መሬታቸዉን ለ1ኛ ተጠሪ በማከራየት የፈጸምኩት ኪራይ ዉል ዘመን በ2007 ዓ/ም ቢጠናቀቅም የኪራይ ገንዘብ ሳይከፍለ ተጠሪዎች በጉልበት የእርሻ መሬቴን በመያዝ ለመልቀቅ ፈቃደኛ ስላልሆኑ እንዱለቁ ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት በመጠየቅ ነዉ።ይህም የክሱ ስረ ነገር የኪራይ ዉል እንደሆነና የኪራይ ዘመን ከተጠናቀቀ በኋላ ተጠሪዎች መሬቱን ለመልቀቅ ፈቃደኛ አይደለም በሚል በክሱ የተገለፀዉ ፍሬ ነገር ደግሞ የክሱ ምክንያት ሆኖ እንደቀረበ የሚያሳይ ነዉ። ለዚህ ክስ 1ኛ ተጠሪ መሬቱን በስጦታ እንጂ በኪራይ አለመያዛቸዉን የሚገልጽ ክርክር ከማቅረባቸዉም በተጨማሪ መሬቱ ለረጅም ጊዜ በእጃቸዉ መቆየቱን ገልጸዉ የአመልካች ክስ በ10 ዓመት ይርጋ ቀሪ ስለሆነ ክሱ ዉድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተቃዉመዋል።
እንደሚታወቀዉ በልዩ ሕግ በተለየ አኳኋን ካልተደነገገ በስተቀር የፍትሐ ብሓር ክርክር የሚመራዉ በፍትሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት ሕጉ በተዘረጋዉ የክርክር አመራር ሥነ ሥርዓት ነዉ።
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 33(2 እና 3) ፣80 እና 222(1/ረ እና ሸ) ላይ እንደተመለከተዉ በክስ አቤቱታ ላይ ለክሱ መሰረት የሆነዉ ነገር ፣ የክሱ ምክንያት ፣ተከሳሹ በክሱ ተጠሪ የሆነበት ምክንያት እና ለክሱ ምክንያት የሆኑ ነገሮች የተፈጠሩበት ጊዜ…እንዱገለጽ ሥነ ሥርዓት ሕጉ ይጠይቃል።የክስ አቤቱታ በዚህ አግባብ ተዘጋጅቶ እንዱቀርብ አስፈላጊ ካደረጉ ምክንያቶች መካከል አንደ ተከሳሽ የሆነዉ ወገን ለክሱ መልሱን አዘጋጅቶ ሲያቀርብ ክሱ በይርጋ ይታገዲል በሚል የመቃወም ፍላጎት ካለዉ ተገቢዉን የይርጋ መቃወሚያ በማቅረብ መከራከር እንዱችል እና ላልች መከራከሪያዎችን በማቅረብ ክሱን የመከላከል መብቱን በተሟላ መልኩ መጠቀም እንዱችል ሥርዓት ለመዘርጋት ነዉ(የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 222(1/ረ እና ሸ) እና 234(1/ሐ) ጣምራ ንባብ ይመለከቷል)።ከዚህም ሥነ ሥርዓት የምንረዲዉ የይርጋ መቃወሚያ የሚቀርበዉ ከሳሽ በክሱ ላይ የገለጸዉን ሥረ ነገርና የክስ ምክንያት መሰረት በማድረግ እንደሆነ ነዉ።
በመሰረቱ ይርጋ ከሚያስከትለዉ ዉጤት አንጻር ሁለት ገጽታዎች አለት።ይኸዉም መብት የሚሰጥ(የሚያስገኝ) ይርጋ (acquisitive prescription) እና መብት የሚያሳጣ ይርጋ(extinctive prescription) በሚል የሚታወቁ ናቸዉ። ኋለኛዉ አይነት ይርጋ ባለመብቱ (ባለገንዘቡ) በሕግ በተመለከተዉ የጊዜ ገደብ ዉስጥ መብቱን(ጥቅሙን ወይም ገንዘቡን) ሳይጠይቅ ቆይቶ ጊዜዉ ካለፈበት መብቱን መጠየቅ እንዲይችል የሚያደርግ (right killer limitation) ነዉ።ይህ ኋለኛዉ አይነት ይርጋ መብት ለማስከበር የሚቀርብን ክስ ቀሪ የሚያደርግ(limitation of action)ጭምር ነዉ። አንድ ተከራካሪ ወገን ክሱ በይርጋ ይታገዲል ብል መቃወሚያ ሲያቀርብ እየተቃወመ ያለዉ ይህንን የክስ ምክንያት መሰረት በማድረግ ክስ ለማቀርብ የሚቻልበት ጊዜ ነዉ ተብል በሕጉ በተመለከተዉ የጊዜ ገደብ ዉስጥ ክሱ ስላልቀረበ በዚህ የክስ ምክንያት ክስ የማቅረብ መብቱ ቀሪ ሆኗል በሚል ነዉ።በመሆኑም የይርጋ መቃወሚያ የሚያቀርበዉ ተከራካሪ የክሱን ምክንያት መሰረት አድርጎ መቃወሚያ ማቅረብ አለበት እንዲልነዉ ሁለ በክርክሩ ላይ ዉሳኔ የሚሰጠዉም ፍርድ ቤት ክስ የማቅረብ መብቱ በይርጋ ቀሪ ሆኗል ወይም አልሆነም የሚለዉን ጭብጥ ይዞ ሲወስን መሰረት ማድረግ ያለበት የክሱን ስረ ነገር እና ምክንያት ላሆን ይገባል።
በተያዘዉ ጉዲይ የክሱ ሥረ ነገር የገጠር እርሻ መሬት ላይ ተደረገ የተባለ የኪራይ ዉል ሲሆን የክሱ ምክንያት ደግሞ 1ኛ ተጠሪ ከ2ኛ ተጠሪ ጋር በመሆን የኪራይ ዘመኑ በ2007ዓ/ም ካለቀ በኋላ መሬቱን ለመልቀቅ ፈቃደኛ አልሆኑም ተብል የተገለጸዉ ምክንያት ነዉ።1ኛ ተጠሪ ደግሞ ክሱ በ10 ዓመት ይርጋ ቀሪ የሆነ ነዉ የሚል መቃወሚያ ያቀረቡ ቢሆንም ከአመልካች ጋር የኪራይ ዉል ግንኙነት የለኝም በማለት ክደዋል።እንዱሁም 1ኛ ተጠሪ መሬቱን መልቀቅ የነበረብኝ በ2007ዓ/ም ሳይሆን ክሱ ከመቅረቡ ከ10 ዓመት በፉት ጀምሮ ነዉ በማለት በግልጽ ያቀረቡት ክርክር የለም።እንዱህ አይነት ክርክር ሲቀርብ ከላይ እንደገለጽነዉ የክሱን ምክንያት መሰረት በማድረግ ከ2007ዓ/ም ጀምሮ ክሱ እስከቀረበበት ቀን ድረስ ያለዉን ጊዜ በመቁጠር እና ለክሱ ስረ ነገር አግባብነት ያለዉን የይርጋ ሕግ ድንጋጌ በመለየት መወሰን ይገባል።
የክርክሩ ስረ ነገር በገጠር የእርሻ መሬት ላይ ተደረገ የተባለ የኪራይ ዉል የሚመለከት በመሆኑ የክልለ የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም አዋጅ በጉዲዩ ላይ ተፈጻሚነት አለዉ።የኪራይ ዉለ ጊዜ ተጠናቀቀ በተባለበት በ2007ዓ/ም በክልለ ተፈጻሚ ሲሆን የነበረዉ አዋጅ ቁጥር 133/1998 አንቀጽ 18 ላይ የገጠር መሬት በኪራይ ስለሚተላለፍበት አግባብ የተደነገገ ቢሆንም ከኪራይ ዉል ጋር የተያያዘ ክስ የሚቀርብበትን የይርጋ ጊዜ በተመለከተ በአዋጁ አልተደነገገም።ክሱ በቀረበበት በቀን 10/08/2010 ዓ/ም ተፈጻሚ ሲሆን በነበረዉ በተሻሻለዉ የክልለ የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 252/2009 በተመሳሳይ ከኪራይ ዉል ጋር በተያያዘ ለሚቀርብ ክስ ተፈጻሚ የሚደረገዉን የይርጋ ጊዜ በተመለከተ አልደነገገም።ይልቁንም በዚህ አዋጅ ቁጥር 252/2009 አንቀጽ 54 ላይ አዋጁ ባልሸፈነባቸዉ ጉዲዮች ላይ የፍትሐ ብሓር ሕግ ተፈጻሚነት እንደሚኖረዉ ደንግጓል። በእነዚህ ሕግጋት የተቀመጠ የይርጋ ጊዜ ስለላለ በአመልካችና በ1ኛ ተጠሪ መካከል ያለዉ ግንኙነት ዉልን መሰረት ያደረገ በመሆኑ ተፈጻሚነት የሚኖረዉ የይርጋ ጊዜ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1845 ስር የተደነገገዉ የ10 ዓመት ጊዜ ነዉ።አመልካች የኪራይ ዉለ ጊዜ የተጠናቀቀዉ በ2007ዓ/ም ነዉ በማለት በክሳቸዉ ገልጸዉ ክሳቸዉን ያቀረቡት ደግሞ በቀን 10/08/2010ዓ/ም በመሆኑ ክሱ የቀረበዉ የ10 ዓመት ይርጋ ጊዜ ሳያልፍ ነዉ።
ስለሆነም የወረዲዉ ፍርድ ቤት ጉዲዩ የኪራይ ዉልን መሰረት ያደረገ ሆኖ እያለ ከዚህ ዉጭ በሆነ ሥረ ነገርና የክስ ምክንያት ለሚቀርብ ክስ በአዋጅ ቁጥር 252/2009 አንቀጽ 55 ስር የተደነገገዉን ይርጋ መሰረት በማድረግ የሰጠዉ ዉሳኔ ሉታረም የሚገባዉ ነዉ።እንዱሁም በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 80(3/ሀ እና ለ) ስር እንደተመለከተዉ ለዚህ ሰበር ሰሚ ችልትም ሆነ ለክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የተሰጣቸዉ ሥልጣን መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበትን የመጨረሻ ዉሳኔ በሕግ በዝርዝር በሚወሰነዉ አግባብ መርምረዉ እንዱያርሙ እንጂ ማስረጃ መርምረዉና መዝነዉ የአንድን ፍሬ ነገር መኖር አለመኖር እንዱያረጋግጡ ሥልጣን አልተሰጣቸዉም።ከዚህ አንጻር የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠዉን ዉሳኔ ስንመለከት ችልቱ በስር ፍርድ ቤት 1ኛ ተጠሪ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን መሬት የያዙት በኪራይ ነዉ ወይስ በስጦታ ? የሚል ጭብጥ ተይዞ ከዚህ አንጻር ማስረጃ ተመርምሮና ተመዝኖ የተረጋገጠ ፍሬ ነገር በላለበት፤ በስር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙ ምስክሮች ቀርበዉ የመሰከሩትን ቃል መርምሮና መዝኖ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን መሬት 1ኛ ተጠሪ ሉይዙ የቻለት በኪራይ ሳይሆን በስጦታ መሆኑንና ከ10 ዓመት በላይ 1ኛ ተጠሪ ይዘዉ መቆየታቸዉን በተሻለ ሁኔታ 1ኛ ተጠሪ አስረድተዋል የሚል ድምዲሜ ላይ በመድረስ የአመልካች ክስ የማቅረብ መብት በአዋጅ ቁጥር 252/2009 አንቀጽ 55 እና በሰ/መ/ ላይ በተሰጠዉ ዉሳኔ መሰረት በ10 ዓመት ይርጋ ቀሪ ሆኗል በሚል ወስኗል።በዚህ መልኩ የሰጠዉ ዉሳኔ በሕገ መንግስቱ ከተሰጠዉ ሥልጣን ዉጭ ማስረጃ መርምሮና መዝኖ መወሰኑን የሚያሳይ ከመሆኑም በተጨማሪ ከላይ እንደተመለከተዉ የይርጋ መቃወሚያ ሉወሰን የሚገባዉ በክሱ ስረ ነገርና ምክንያት ላይ ተመስርቶ ነዉ በሚል የተመለከትነዉን የክርክር አመራር ሂደት የሚቃረንና ለጉዲዩ አግባብነት የላለዉን ሕግና የሰበር ሰሚ ችልት መሰረት ያደረገ በመሆኑ ሉታረም የሚገባዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ። በመሆኑም የአመልካች ክስ በይርጋ አልታገደም ብለናል።
በተጨማሪም የሥነ ሥርዓት ሕጉም ዓላማ ክርክሮች ምክንያታዊ በሆነ አጭር ጊዜ እና በዉስን የሰዉና የገንዘብ ሀብት ተገቢዉን እልባት እንዱያገኙ ማስቻል ነዉ። ይህንን ዓለማ ማሳካት ይችል ዘንድ የፍትሐ ብሓር ጉዲይ የቀረበለት ፍርድ ቤት የክርክሩን ሥረ ነገርና የክስ ምክንያት እንዱሁም በተከራካሪዎች የቀረበዉን ክርክር መሰረት አድርጎ ግራ ቀኙ ተለያይተዉ የተከራከሩበትን የሕግ እና/ወይም የፍሬ ነገር ትክክለኛ ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን የመምራት፣በተጠየቀዉ ዲኝነት እና በአከራካሪዉ ጭብጥ ላይ ተገድቦ ዉሳኔ የመስጠት ኃላፉነቱን በአግባቡ ሉወጣ ይገባል።ከዚህ ዉጭ በሆነ አኳኋን ክርክሩን የሚመራ ከሆነ ክርክሩ ከጊዜ እና ከወጪ አንፃር ዉጤታማ እንዲይሆን በማድረግ ፍትህ የሚያጓድል ድምዲሜ ላይ ይደርሳል።ይህም የሥነ ሥርዓት ሕጉ የቆመለት ዓላማ እንዲይሳካ በማድረግ የተከራካሪ ወገኖችን የስረ ነገር መብት(substantive right) ያሳጣል እንዱሁም ዜጎች በፍርድ ቤቶች ላይ የሚኖራቸዉን እምነት ይሸረሽራል።ስለሆነም በሥነ ሥርዓት ሕጉ የተዘረጋዉን የክርክር አመራር ሂደት ተከትል ለክርክሮች ተገቢዉን እልባት መስጠት ይገባል።ከዚህ አንጻር በተያዘዉ ጉዲይ ላይ ከሥረ ነገር አኳያ በስር ፍርድ ቤት ክርክሩ የተመራበትን አግባብ መርምረናል።የወረዲዉ ፍርድ ቤት ከፍሬ ነገር አንጻር የመሰረተዉና ዉሳኔ የሰጠበት ጭብጥ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ መሬት ሕጋዊ ይዞታነት የአመልካች ነዉ ወይስ የ1ኛ ተጠሪ? የሚል ነዉ።ነገር ግን ግራ ቀኙ ተካክደዉ የተከራከሩበትና ዉሳኔ የሚሹ ጭብጦች ደግሞ 1ኛ ተጠሪ መሬቱን የያዙት አመልካች አከራይተዋቸዉ ነዉ ወይስ በስጦታ ሰጥተዋቸዉ ነዉ?
የያዙት በኪራይ ዉል ነዉ የሚባል ከሆነ መሬቱን ሉለቁ ይገባል ወይስ አይገባም? የሚለ ናቸዉ።
ስለሆነም የወረዲዉ ፍርድ ቤት ተጠሪዎች ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን መሬት ለአመልካች እንዱለቁ የወሰነዉ ተገቢዉን ጭብጥ ሳይመሰርት እና ከትክክለኛ ጭብጥ አኳያ ማስረጃ በመመርመርና በመመዘን ባላረጋገጠበት በመሆኑ ሉታረም የሚገባዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስለሆነ ተከታዩን ወስነናል።
የጃዊ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 0875 ላይ በቀን 07/10/2010 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ ፣የአዊ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 09-00202 ላይ በቀን 14/10/2010 ዓ/ም የሰጠዉ ትእዛዝ እና የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁጥር 03-79166 ላይ በቀን 20/02/2012ዓ/ም የሰጠዉ ዉሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ተሽረዋል።
የአመልካች ክስ በይርጋ ቀሪ አልሆነም ብለናል።
የጃዊ ወረዲ ፍርድ ቤት መዝገቡን አንቀሳቅሶ 1ኛ ተጠሪ መሬቱን የያዙት አመልካች አከራይተዋቸዉ ነዉ ወይስ በስጦታ ሰጥተዋቸዉ ነዉ?
የያዙት በኪራይ ዉል ነዉ የሚባል ከሆነ መሬቱን ሉለቁ ይገባል ወይስ አይገባም? የሚለ ጭብጦች ላይ ዉሳኔ ለመስጠት አስቀድሞ የተሰማዉ ክርክርና ማስረጃ በቂ ካልሆነ እንደነገሩ ሁኔታ ግራ ቀኙን በማከራከርና ምስክሮችን ሰምቶና አስፈላጊ የሚሆኑ ማስረጃዎችን አስቀርቦ መርምሮና መዝኖ ሕግን መሰረት ያደረገ ዉሳኔ እንዱሰጥ ጉዲዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 343/1 መሰረት መልስንለታል።
በዉሳኔዉ መሰረት እንዱፈጽም የዉሳኔዉ ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤት ይተላለፍ። ለግራ ቀኙም ግልባጩ ይሰጣቸዉ።
በመዝገቡ ላይ የተሰጠ የዕግድ ትእዛዝ ካለ ተነስቷል፤ይጻፍ።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.