በመንግስት ሰራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር 907/2007 አንቀጽ 5(2) የዘለቄታ ጡረታ አበል ለማግኘት ቢያንስ አስር አመት ማገልገል እና በአዋጅ ቁጥር 714/2003 አንቀጽ 18 መሰረት የጡረታ እድሜ መድረስ ቅድመ ሁኔታ በመሆኑ ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ ቢያንስ አስር አመት ያገለገለ እና በራሱ ፈቃድ ወይም በአዋጁ ከተጠቀሱት ውጪ በሆነ ምክንያት አገልግልት ካቋረጠ የጡረታ መውጫ እድሜው ሲደርስ የአገልግልት ጡረታ አበል ለዘለቄታው የማያገኝ ስለመሆኑ (የፋ/ፍ/ቤቶችን አዋጅ እንደገና ለማሻሻል በወጣው በአዋጅ ቁጥር 454/1997 መሰረት በፋ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ቀደም ሲል በሰ/መ/ ተሰጥቶ የነበረው የህግ ትርጉም ተለውጧል።)
No summary available.
መጋቢት 27 ቀን 2013 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ ተሾመ ሽፈራዉ ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግሥቱ ነጻነት ተገኝ አመልካች፡- አቶ የሽዋስ አስማረ ተጠሪ፡- አቶ ያሲን አሉ መዝገቡ ተመርምሮ ከዚህ የሚከተለዉ የፍርድ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የመሬት ይዞታ ለማስለቀቅ የቀረበ ክርክር የሚመለከት ነዉ።አመልካች በጉራፈርዲ ወረዲ ፍርድ ቤት በተጠሪ ላይ በመሰረቱት ክስ በጉራፈርዲ ወረዲ በበርጂ ቀበላ መድሃኒአለም ቤተክርስቲያን ጀርባ 3ኛ ደረጃ ተብል በሚጠራዉ አካባቢ የሚገኝ አዋሳኙ በክሱ የተጠቀሰዉን 50ሜትር በ600ሜትር የሆነ 3 ሄክታር የእርሻ መሬት የበርጂ ቀበላ አስተዲደር ጽ/ቤት በቀን 10/06/1999ዓ/ም በተጻፈ ቃለ ጉባኤ (ቬርባል) ሰጥቶኛል።እስከ 2004ዓ/ም ደረስ ግብር እየገበርኩ የተለያዩ ተክልችን ተክዬ የምጠቀምበትን እንዱሁም ዓመታዊ ሰብል የማመርትበትን መሬት በ2004ዓ/ም በአካባቢዉ በተነሳዉ አለመረጋጋት ምክንያት ቤተሰቦቼን ይዤ ከተፈናቀልኩበት ስመለስ ተጠሪ ይህንን መሬቴን በመያዝ እየተጠቀሙ እንደሚገኝ በማወቅ እንዱለቁልኝ ስጠይቃቸዉ ፈቃደኛ ስላልሆኑ የመሬት ይዞታዬን እንዱለቁ እንዱወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል።
ተጠሪ ለክሱ በሰጡት መልስ የአመልካችን ይዞታ በኃይል ወይም በሕገ-ወጥ መንገድ አልያዝኩም።ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ይዞታ በ2004ዓ/ም ከዲንቅላ ቀበላ ስፈናቀል በነበረኝ ይዞታ ምትክ በልዋጭ በወረዲዉ መንግስት ፈቃድ የተሰጠኝ ነዉ።በቁጥር 150 የሚሆኑ የተለያዩ አትክልቶች ተክዬ ለፍሬ ካበቃሁ በኋላ አመልካች መጥተዉ የእኔ ነዉ አለ እንጂ ተጠሪ የአመልካችን ይዞታ አልወሰድኩም።የመንግስት የነበረ መሬት ስለሆነ ክሱ ዉድቅ ይደረግልኝ በማለት ተከራክረዋል።
የወረዲዉ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ የግራ ቀኙን ክርክርና ምስክሮች ሰምቶና ማስረጃ አስቀርቦ መርምሮ በቀን 18/10/2011ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ ክርክር ያስነሳዉ የመሬት ይዞታ አመልካች አስቀድሞ በሕጋዊ መንገድ ተመርተዉ የያዙት መሆኑ ተረጋግጧል። ይህ ይዞታ ቃለ-ጉባኤ(ቨርባል) ተይዞ ለአመልካች የተመራ መሆኑን አመልካች በእጃቸዉ በሚገኘዉ ሰነድ(ቬርባል) አስረድተዋል። በፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ከጉራፈርዲ ወረዲ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽ/ቤት የመጣዉ ማስረጃ ተጠሪ ይዞታዉን የተመሩበትን ሁኔታ የሚያሳይ ምንም ማስረጃ በጽ/ቤቱ ዘንድ እንደማይገኝ ገልጿል።በ2004 ዓ/ም በአካባቢዉ በተፈጠረ አለመረጋጋት ምክንያት አመልካች ከአካባቢዉ ተፈናቅለዉ መሬቱን ለቀዉ ሲሄደ ተጠሪ ከክልለ የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 110/1999 አንቀጽ 9 አግባብ ዉጭ በመያዝ አመልካች በ2009ዓ/ም ወደ አካባቢዉ ተመልሰዉ ሲጠይቁ ለመልቀቅ ፈቃደኛ እንዲልሆኑ በማስረጃ ማረጋገጡን ገልጾ ተጠሪ ሕጋዊ ባልሆነ ምሪት የያዙትን ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን መሬት ለአመልካች ሉለቁ ይገባል በማለት ወስኗል።
ተጠሪ በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለቤንች አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበዉ ፍርድ ቤቱም በመ/ ላይ በቀን 26/10/2011 ዓ/ም በሰጠዉ ትእዛዝ ይግባኙን ሰርዞባቸዋል።በመቀጠል ተጠሪ ለደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርበዉ ፍርድ ቤቱም በመ/ ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ በቀን 30/12/2011ዓ/ም በአብላጫ ድምጽ በሰጠዉ ዉሳኔ የሥር የወረዲ ፍርድ ቤት አከራካሪዉን ይዞታ ተጠሪ በቀበላ አመራር አማካኝነት ማግኘታቸዉን ተረጋግጧል። የአሁን አመልካች ይዞታዉን ያገኙት በሕገ-ወጥ መንገድ ነዉ ተብል በ2004ዓ/ም ሳይለካላቸዉ እንደቀረ በሰዉና በሰነድ ማስረጃዎች ተረጋግጦ ባለበት እንዱሁም አመልካች ሕገ ወጥ ይዞታ መሆኑን ተቀብለዉ የነበረዉን የቆርቆሮ ቤት አፍርሰዉ ሄደዉ የመብት ጥያቄ ሳያቀርቡ ቆይተዉ በአከራካሪዉ ይዞታ ላይ መብት እንዲለዉ ሰዉ በመሆን ተጠሪ ከስድስት አመት በላይ ቋሚ ተክልችን በመትከልና ቤት በመስራት ግብር እየገበሩበት ይዘዉ የቆዩትን ይዞታ ለቀዉ ለአመልካች እንዱያስረክቡ በስር ፍርድ ቤቶች መወሰኑ ስህተት ነዉ።ስለሆነም አመልካች በአከራካሪዉ ይዞታ ላይ የተከሎቸዉ ቋሚ ተክልች ካለ በማስረጃ አረጋግጠዉ ግምት የመጠየቅ መብት ያላቸዉ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ተጠሪ አከራካሪዉን ይዞታ ለአመልካች ሉለቁ አይገባም በማለት የሥር ፍርድ ቤቶችን ዉሳኔ በመሻር ወስኗል።
አመልካች በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ አቅርበዉ ችልቱ በመ/ ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ በቀን 25/03/2012ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠዉን ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል። አመልካች በቀን 14/04/2012 ዓ/ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረቡት በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ እና ሰበር ሰሚ ችልቶች በተሰጡ ዉሳኔዎች መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን የአቤቱታቸዉ ይዘት በአጭሩ የሚከተለዉ ነዉ።
ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን 3 ሄክታር መሬት አመልካች በሕጋዊ መንገድ በቀን 10/06/1999ዓ/ም በተያዘ ቃለ ጉባኤ ተሰጥቶኝ የተለያዩ አትክልቶችን በመትከል እየተጠቀምኩ እስከ 2004ዓ/ም ግብር እየገበርኩ ይዤ የቆየሁት ነዉ።በ2004ዓ/ም አከራካሪዉን የመሬት ይዞታ ለቅቄ የወጣሁት በወቅቱ በአካባቢዉ የሚኖር የአማራ ተወላጅ ለቆ ይዉጣ በሚል በተፈጠረ አለመረጋጋት ከቤተሰቤ ጋር ጥቃት ይደርስብኛል በሚል ነዉ።አካባቢዉ ላይ መረጋጋት ሲፈጠር ከ3 ወር በኋላ ወደ አካባቢዉ ተመልሼ ይዞታዬን በመያዝ ንብረቴን እየተጠቀሙ የሚገኙት የአሁን ተጠሪ ይዞታዬን እንዱለቁ ለማስደረግ ለሚመለከታቸዉ የመንግስት አካላት አቤቱታ ሳቀርብ ቆይቼ አቅጣጫ ሲሰጥ ቢቆይም ተጠሪ ይዞታዬን እንዱለቁ ማድረግ ስላልቻለ በፍርድ ኃይል ለማስለቀቅ ያቀረብኩት ክስ ሆኖ እያለ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የመብት ጥያቄ ሳላቀርብ እንደቆየሁ አድርጎ የሥር ፍርድ ቤትን ዉሳኔ መሻሩ ስህተት ነዉ። ተጠሪ አከራካሪዉን መሬት በምሪት ተሰጥቷቸዉ ስለመያዛቸዉ በምንም አይነት ማስረጃ አላስረደም።ተጠሪ በአመልካች የለማዉን መሬት ተሰጥቶኛል በማለት የሚያነሱት ክርክር ተቀባይነት የለዉም።መሬቱ ለተጠሪ ተመርቷል ቢባል እንኳን አመልካች በተመራሁበት እና ባለማሁበት መሬት ላይ ለተጠሪ ደርቦ ለመምራት የሚያስችል የሕግ ስርዓት የለም። የጉራፈርዲ ወረዲ መንግስት አመልካች ከይዞታዬ እንዱፈናቀል የወሰነዉ ዉሳኔ የለም።የወረዲዉ እርሻ እና ተፈጥሮ ሀብት በጻፈዉ ደብዲቤ ላይ እንደተመለከተዉ የአመልካች ይዞታ በወቅቱ ያልተለካዉ ሕገ-ወጥ ስለሆነ ነዉ ያለበት ምክንያት አመልካች ከመጀመሪያዉም ይዞታዉን የያዝኩት በሕገ-ወጥ መንገድ ነዉ ለማለት ፈልጎ ሳይሆን በ2004ዓ/ም በጉራፈርዲ ወረዲ በነበረዉ የፖለቲካ አለመረጋጋት ከወረዲዉ የነበሩ አማራ አርሶአደሮች ከአካባቢዉ ይዉጡ ተብል ስለነበር አማራዎች የያዙት ይዞታ በሕጋዊ መንገድ የተያዘ ቢሆንም ከክልላቸዉ ዉጭ መስፈራቸዉ ሕገ-ወጥ ነዉ የሚል የተሳሳተ ስያሜ ተሰጥቶት እንጂ ከመነሻዉም መሬቱ በሕገ-ወጥ መንገድ የተያዘ ነዉ ለማለት አይደለም።ይህንን ባለሙያ ጭምር በማስቀረብ ማጣራት እየተቻለ የተሳሳተ ግንዛቤ በመያዝና አመልካች ከተጠሪ የተሻለ ማስረጃ በማቅረብ በሕጋዊ መንገድ የያዝኩት ይዞታ መሆኑን አስረድቼ እያለሁ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሥር ፍርድ ቤትን ዉሳኔ መሻሩ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ።እንዱሁም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠዉ ዉሳኔ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ.ሕገ መንግስት አንቀጽ 40/4 ላይ የኢትዮጵያ አርሶአደሮች መሬት በነጻ የማግኘትና ከመሬታቸዉ ያለሕጋዊ ምክንያት ያለመፈናቀል መብት አላቸዉ የሚለዉን የሚቃረን ስለሆነ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ተሽሮ የወረዲ እና የከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ወሳኔ ይጽናልኝ በማለት አቤቱታቸዉን አቅርበዋል።
የሰበር አጣሪ ችልት አቤቱታውን መርምሮ ተጠሪ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን መሬት በሕግ አግባብ ስላለመያዛቸዉ የሚመለከተዉ አካል እየገለጸ ባለበት አመልካች ከ1999 ዓ/ም ጀምሮ ሲጠቀሙበት ቆይተዉ በ2004 ዓ/ም ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት መልቀቃቸዉ ተረጋግጦ እያለ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ እና ሰበር ሰሚ ችልቶች አከራካሪዉ ይዞታ ለተጠሪ ይገባል በማለት የወሰኑበትን አግባብ ከመሰረታዊዉ የማስረጃ ምዘና መርህ አንጻር እንዱመረመር ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልት እንዱቀርብ ትዕዛዝ በመስጠቱ ተጠሪ በቀን 16/11/2012 ዓ/ም የተፃፈ መልስ ያቀረቡ ሲሆን ይዘቱም በአጭሩ፡- የጉራፈርዲ ወረዲ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ጽ/ቤት ለፍርድ ቤቱ በጻፈዉ ደብዲቤ ‛ተጠሪ ይዞታዉን በወረዲዉ በስግሰጋ መልክ መዉሰዲቸዉን የሚያሳይ ምንም ገላጭ የሆነ መረጃ በጽ/ቤቱ ደረጃ እንደላለ እንገልጻለን“ በማለት የጻፈዉ ደብዲቤ መረጃ እንደላለዉ የገለጸበት ነዉ እንጂ ተጠሪ ይዞታዉን በሕግ አግባብ አልያዙም ወይም አያያዙ ሕገ-ወጥ ነዉ በሚል የሰጠዉ ማረጋገጫ አይደለም።የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዉሳኔ ከመሰጠቱ በፉት ደብዲቤዉን የጻፈዉ ኃላፉ የአከራካሪዉ መሬት ሕጋዊ ባለይዞታ የአሁን ተጠሪ ስለመሆኔ አረጋግጧል። በቀን 02/12/2011ዓ/ም ለተጠሪ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ተሰጥቶኛል። ሁለም አቅርቤ ያሰማኋቸዉ ምስክሮቼ አከራከሪዉ መሬት የተሰጠኝ በዲንቅላ ቀበላ በሕጋዊ መንገድ በሰፈራ የተመራሁት መሬት በአካባቢዉ በነበረ አለመረጋጋት ምክንያት ተወስድብኝ ስለነበር የወረዲዉ መሬት አስተዲደር ከቀበላ አስተዲደር ጋር በመሆን በልዋጭ መርቶኝ በቅጽ ተመዝግቦ ያገኘሁት መሆኑን አስረድተዋል።መሬቱ በእጄ የሚገኝና ግብር የምገብርበት ነዉ።አመልካች ይዞታዉን ከ1999ዓ/ም ጀምሮ በእጃቸዉ አድርገዉ በ2004ዓ/ም ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት የለቀቁ ስለመሆኑ በማስረጃ አላረጋገጡም።አመልካች መሬቱን በምሪት ደብዲቤ(በቬርባል) አግኝቻለሁ በማለት የተከራከሩ ቢሆንም ሰነደን ለስር ፍርድ ቤት በማስረጃነት አቅርበዉ አላስረደም። አንዲችም የግብር ደረሰኝ በማስረጃነት አላቀረቡም።አመልካች አከራካሪዉን ይዞታ መንግስት ሳይመራቸዉ በሕግ አግባብ ዉጭ በመሬት ወረራ መያዛቸዉ በ2004ዓ/ም በተደረገ ማጣራት ተረጋግጦ እንደለቀቁ በስር ፍርድ ቤቶች በማስረጃ የተረጋገጠ ነዉ።አመልካች ከሕግ ዉጭ እንድለቅ ተደርጌያለሁ የሚለ ከሆነ ያፈናቀላቸዉን አካል ከሚጠይቁ በስተቀር የነበራቸዉን ቤት አፍርሰዉና ንብረት አንስተዉ አካባቢዉን ለቀዉ ከሄደ በኋላ ተጠሪ መሬቱን በጉልበት እንዲልያዝኩ እያወቁ በመንግስት ምሪት በሕጋዊ መንገድ የያዝኩትን እንድለቅላቸዉ ሉጠይቁኝ አይችለም። ስለሆነም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ማስረጃዎችን በአግባቡ መዝኖ ተጠሪ ይዞታዉን መልቀቅ እንደማይገባኝ በመወሰኑ የተፈጸመ ስህተት የለም በማለት ተከራክረዋል። አመልካችም በቀን 18/02/2013 ዓ/ም የተጻፈ የመልስ መልስ በማቅረብ ተከራክረዋል።
ከዚህ በላይ የተመለከተዉ የግራ ቀኝ ክርክርና በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ዉሳኔዎች ይዘት ሲሆን እኛም የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩ ለሰበር ችልት ያስቀርባል ሲል ከያዘዉ ጭብጥ አንጻር የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ መርምረናል።
እንደመረመርነውም ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን የመሬት ይዞታ አመልካች ከ1999ዓ.ም ጀምሮ በጉራፈርዲ ወረዲ በበርጂ ቀበላ አስተዲደር ጽ/ቤት በቃላ ጉባኤ መርቶኝ የተለያ ቋሚ ተክልችን በመትከልና አመታዊ ሰብል በማምረት የየዝኩትን በ2004ዓ/ም በአካባቢዉ በተፈጠረ ግጭት ምክንያት ከጥቃት ለመዲን ቤተሰቦቼን ይዤ ከሄድኩበት ስመለስ ተጠሪ ያለማሁትን ይዞታዬን ይዘዉ ለመልቀቅ ፈቃደኛ ስላልሆኑ እንዱለቁልኝ ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል። ተጠሪ ደግሞ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ የመንግስት ይዞታ እንደሆነና በዚያዉ ወረዲ ዲንቅላ ቀበላ በሚባልበት ከነበራቸዉ ይዞታ ሲፈናቀለ በልዋጭ በወረዲዉ መንግስት በ2004ዓ/ም ተመርተዉ በመያዝ የተለያዩ ተክልችን ተክለዉ የያዙት የመንግስት መሬት እንደሆነ ገልጸዉ አመልካች ይዞታዉን ለማስለቀቅ ያቀረቡት ክስ ዉድቅ እንዱደረግላቸዉ በመግለጽ ተከራክረዋል።
በወረዲዉ ፍርድ ቤት አመልካች አቅርበዉ ያሰሙት አራት ምስክሮች የሰጡት ምስክርነት ቃል ነዉ ተብል በዉሳኔዉ የሰፈረዉ“…ክርክር የተነሳበት ይዞታ የአመልካች ነዉ።በ1999ዓ/ም የካቲት 7 ቀን ከቀበላዉ ይዞታዉ የተሰጠዉ በቬርባል በመፈራረም ነዉ።ከሳሽ ይዞታዉ ከተሰጠዉ በኋላ ይዞታዉን እያለማ 42 ቅጠል ቆርቆሮ ቤት ሰርቶበት ሲኖር ሳለ በ2004ዓ/ም ከአካባቢዉ አማራ ይዉጣ የሚል ብጥብጥ ተነስቶ ስለነበር ከሳሽ ሆነ ላልች አርሶ አደሮች አካባቢዉን ለቀዉ ሄደዉ ነበር።የአካባቢዉ ሁኔታ መረጋጋቱን አዉቆ ከሳሽ ተመልሶ ሲመጣ ቤቱን አጥቷል።በይዞታዉ ላይ የነበሩ አትክልቶች አሁንም አለበት።በ2009 ዓመት መጥቶ በይዞታ ጉዲይ አቤቱታ እያቀረበ ምንም ምላሽ አላገኘም።በኋላ በዞኑ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ጽ/ቤት አመልክቶ በወረዲዉ አስተዲደር በኩል ይዞታዉ እንዱመለስለት ጽፍለት ነበር።ሆኖም አልተፈጸመለትም።ተከሳሹ በምን ሁኔታ የከሳሽን ይ+ዞታ ለመያዝ እንደቻለ አናዉቅም በማለት መስክረዋል።“የሚል ነዉ።እንዱሁም ከክሳቸዉ ጋር ከ1999ዓ/ም እስከ 2004ዓ/ም ግብር የገበሩበትን ሰነድች እና ከመሬት አስተዲደርና አጠቃቀም ኮሚቴና ከሚመለከታቸዉ አካላት የተጻፈላቸዉን ሰነድች አያይዘዉ እንዲቀረቡ የወረዲዉ ፍርድ ቤት ዉሳኔ ይዘት ያሳያል።
በልላ በኩል በወረዲ ፍርድ ቤት ዉሳኔ ላይ እንደተመለከተዉ ተጠሪ አቅርበዉ ያሰሟቸዉ ሶስት ምስክሮች በሰጡት ምስክርነት ቃል፡-‛…ክርክር የተነሳበት ይዞታ የለማና የተለያዩ አትክልቶች እያለበት በወቅቱ በነበረ የቀበላ ተወካዮች እንደተሰጠዉ ገልጸዉ ከሳሽም ይዞታዉ የእኔ ነዉ ብል መከራከሩን እንደሚያዉቁ አስረድተዋል።ይዞታዉ የለማዉ በከሳሽ ሲሆን አትክልቶቹን ተንከባክቦ ያሳደገዉ ተከሳሽ ነዉ ብለዋል።ተከሳሽም ቀደም ብል በአቱዋ ቀበላ በኬራንባ ጎጥ ዉስጥ እያለ ከላልች ጋር በመሆን ይዞታ እንዱሰጣቸዉ በጠየቁት መሰረት ይዞታዉ ለተከሳሽ እንደተሰጠዉ አስረድተዋል።“በሚል መመስከራቸዉ ተመዝግቧል።እንዱሁም ከመልሳቸዉ ጋር የ6 ዓመት የግብር ካርኒ በማስረጃነት አያይዘዉ እንዲቀረቡ በዉሳኔዉ ላይ ተመልክቷል።
ፍርድ ቤቱ ተጨማሪ ማስረጃ ከጉራፈርዲ ወረዲ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽ/ቤት ማስረጃ እንዱቀርብለት አዝዞ ጽ/ቤቱ በላከዉ ምላሽ ‛አሁን ክርክር ያስነሳዉን ይዞታ ከሳሽ ይዞ እያለማዉ ሲኖርበት ሳለ በቀበላዉ መሬት አስተዲደር በሚለካበት ጊዜ ከሳሽ በሕገ-ወጥ መንገድ ነዉ የያዘዉ ተብል አልተለካለትም።የከሳሽም ስም አሁን በጽ/ቤቱ ዉስጥ የሚገኝ ሲሆን ተከሳሽ ይዞታዉን ተመርቷል ይባላል እንጂ ግን ምንም መረጃ በጽ/ቤታቸዉ እንደላለዉ በመግለጽ ጽፎል።“ የሚል ነዉ።
በስር ፍርድ ቤቶች የቀረቡ የሰዉና የሰነድ ማስረጃዎች ከላይ በአጭሩ የተመለከተዉ ሲሆን ከእነዚህ ማስረጃዎች ዉጭ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተጨማሪ ማስረጃ አስቀርቦ ስለመመርመሩ ዉሳኔዉ አያሳይም።በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዉሳኔ ላይ ተጠሪ ይዞታዉን በ2004ዓ/ም የተመሩበትን ማስረጃ እንዲላቀረቡ ገልጿል።
በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 40/4 እና በተሻሻለዉ በደቡብ ብሓር በሓረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ሕገ መንግስት ላይ በተመሳሳይ በተደነገገዉ መሰረት አርሶ አደሮች ዝርዝሩ በሕግ በሚወሰነዉ መሰረት መሬት በነጻ የማግኘትና ከመሬታቸዉ ያለመፈናቀል መብት አላቸዉ።በፋደራለም ሆነ በክልል ሕገ መንግስታት አንቀጽ 40(7 እና 8) ስር እንደተደነገገዉ የመሬት ባለቤትነት የመንግስትና የሕዝብ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ግለሰቦች ባለይዞታ በሆኑበት የመሬት ይዞታ የመጠቀም መብታቸዉ ሉቋረጥ የሚችለዉ አግባብ ባለዉ ሕግ መሰረት እንደነገሩ ሁኔታ በቅድሚያ ካሳ እና/ወይም ምትክ ቦታ ከተሰጣቸዉ ብቻ እንደሆነ፣ማንኛዉም በክልለና ከክልለ ዉጭ የሚኖር ኢትዮጵያዊ በጉልበቱ ወይም በገንዘቡ በመሬት ላይ ለሚገነባዉ ቋሚ ንብረት ወይም ለሚያደርገዉ ቋሚ ማሻሻል ሙለ መብት እንዲለዉና ግለሰቦችም የመሬት ባለይዞታነት መብት ተጠቃሚ ሉሆኑ የሚችለት አግባብ ባለዉ ሕግ በተደነገገዉ ስርዓት መሰረት ነዉ።
እንዱሁም በክልለ የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 110/1999 አንቀጽ 2/13 ስር በተመለከተዉ ትርጓሜ መሰረት የግል ይዞታ ማለት አርሶ አደሮች፣ ከፉል አርብቶ አደሮች እና ወይንም በላልች በሕግ መብት በተሰጣዉ አካላት በግል ይዞታ ስር ያለ የገጠር መሬት ነዉ።በአዋጁ አንቀጽ 5/1 የገጠር መሬት ስለማግኘትና ስለመጠቀም በተደነገገዉ ስር በግብርና ሥራ የሚተዲደሩ አርሶ አደሮች፣ ከፉል አርብቶ አደሮችና አርብቶ አደሮች የገጠር መሬት በነጻ የማግኘትና የመጠቀም መብት እንደላቸዉ ተመልክቷል።የአርሶ አደሮች፣ የከፉል አርብቶ አደሮችና አርብቶ አደሮች ላልተወሰነ ጊዜ በገጠር መሬት የመጠቀም መብት እንዲላቸዉ በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 7/1 ላይ ተመልክቷል።በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 13/14 ስር በተደነገገዉ መሰረትም ማንኛዉም ግለሰብ ወይም ድርጅት ያለይዞታ ማረጋገጫ ደብተር የገጠር መሬትን መጠቀም እንደማይችል ተመልክቷል።
በልላ በኩል አንድ በክልለ የገጠር መሬት ባለይዞታ የሆነ ሰዉ የባለይዞታነት መብቱን ሉያጣ የሚችልበትም አግባብ በሕጉ በዝርዝር ተመልክቷል። ይኸዉም በአዋጁ አንቀጽ 9/1 ስር ስለገጠር መሬት ሽግሽግ እንደተደነገገዉ ባለይዞታዎች በሕይወት የላለና ወራሽ የላላቸዉ ወይም በሰፈራ ወይም በፍላጎታቸዉ ከተወሰነዉ ጊዜ በላይ አካባቢዉን ለቀዉ የቆዩ ከሆነ ይዞታቸዉ መሬት አልባ ለሆኑ ወይም መሬት ላነሳቸዉ አርሶ አደሮች ከፉል አርብቶ አደሮችና አርብቶ አደሮች በደንብ ላይ ተዘርዝሮ በሚደነገገዉ መሰረት በሽግሽግ ላሰጥ ይችላል።በአዋጁ አንቀጽ 7/3 እና 13/11 በግል ባለይዞታነት የተያዘ የገጠር መሬትን ባለይዞታዉ በመሬቱ ላይ ላደረገዉ ማሻሻያና ላፈራዉ ንብረት አግባብ ባለዉ ሕግ መሰረት ተመጣጣኝ ካሳ ተከፍልትና በለቀቀዉ ምትክ ተለዋጭ መሬት እንዱያገኝ በማድረግ መሬቱን ለሕዝብ ጥቅም ለማዋል እንዱለቅ ማድረግ የሚቻል ሲሆን ከዚህ ዉጭ ባለይዞታዉ በመሬቱ የመጠቀም መብቱን ሉያጣ የሚችለዉ በአንቀጽ 10/1 እና 13/12 ስር እንደተደነገገዉ ዝርዝር አፈጻጸሙ በደንብ በተወሰነዉ መሰረት ባለይዞታዉ መሬቱን በአግባቡ የመጠቀምና የመንከባከብ ግዳታዉን ባለመወጣቱ የተነሳ በመሬቱ ላይ ጉዲት(በቅጣት ብቻ ሉታለፍ የማይችል ጉዲት) ማድረሱ ሲረጋገጥ ነዉ።ከዚህ ዉጭ ባለይዞታዉ አግባብ ላለዉ አካል በግልጽ አሳዉቆ በመሬቱ የመጠቀም መብቱን በፈቃደ ካልተወ በስተቀር የገጠር መሬት ባለይዞታነት መብቱን ሉያጣ አይችልም(የአዋጁ አንቀጽ 10/4 ይመለከቷል)።
ከላይ በተጠቀሱት ሕጎች የተደነገገዉንና በግራ ቀኝ ምስክሮችና ማስረጃዎች የተረጋገጡትን ፍሬ ነገሮች ከግምት በማስገባት አከራካሪዉን ይዞታ ተጠሪ ለአመልካች ሉለቁ አይገባም ተብል በመወሰኑ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን መርምረናል። ከላይ እንደተመለከተዉ አመልካች ያቀረቡት ምስክሮች አመልካች አከረካሪዉን መሬት በ1999ዓ/ም ተመርተዉ እንደያዙ የመሰከሩላቸዉ ሲሆን ተጠሪ ያቀረቡት ምስክሮች ደግሞ አመልካች አልምተዉ ይዘዉ የነበረዉን መሬት በቀበላ አስተዲደር አማካኝነት ለተጠሪ ተሰጥቷቸዉ ስለመያዛቸዉ መስክረዉላቸዋል።ሆኖም አመልካችም ሆኑ ተጠሪ በሥነ ሥርዓት ሕጉ አግባብ በስር ፍርድ ቤቶች ካቀረቡት የጽሁፍ ክርክር ጋር ወይም ሕጉ በሚፈቅደዉ የክርክር ደረጃ ላይ አከራካሪዉን መሬት አግባብ ባለዉ ሕግ መሰረት በሚመለከተዉ የመንግስት አካል ተመርተዉ(በድልድል) ስለማገኘታቸዉ የሚያሳይ ማስረጃ ወይም በስማቸዉ ተመዝግቦ የተሰጣቸዉን የባለይዞታነት ማረጋገጫ ምስክር ደብተር በማቅረብ አላስረደም።አመልካች መሬቱን በቀበላ አስተዲደር ጽ/ቤት በቀን 10/06/1999ዓ/ም በተጻፈ ቃለጉባኤ(ቬርባል)ተሰጥቶኝ ነዉ የያዝኩት በሚል በክሳቸዉ ቢገልጹም ይህንን ማስረጃ በማስረጃነት ያቀረቡ ስለመሆኑ የስር ፍርድ ቤቶች ዉሳኔ ግልባጭ ባያሳይም የስር ፍርድ ቤቶች ይህ ማስረጃ እንዱቀርብ በማድረግ አለማጣራታቸዉን ተገንዝበናል።ተጠሪም በይዞታዉ ላይ በስሜ ተመዝግቦ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር በቀን 02/12/2011ዓ/ም ተሰጥቶኛል ብለዉ ቢከራከሩም ይህንን ማስረጃ አግኝተዉ ከሆነም የወረዲ እና የዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች በጉዲዩ ላይ ዉሳኔ በመስጠት ይዞታዉን ለአመልካች እንዱያስረክቡ ከተወሰነና ጉዲዩ በይግባኝ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ታይቶ ተጠሪ ይዞታዉን ሉለቁ አይገባም ተብል የስር ፍርድ ቤቶች ዉሳኔ ተሽሮ ከመወሰኑ በፉት በመሆኑ ለስር ፍርድ ቤቶች የቀረበ ማስረጃ ባለመሆኑ ተጠሪ በሥነ ሥርዓት ሕጉ አግባብ እንዲቀረቡት ማስረጃ ተቆጥሮ ሉመዘን የሚችል አይደለም። እንዱሁም የወረዲዉ ፍርድ ቤት ከወረዲዉ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ጽ/ቤት ግራ ቀኝ ይዞታዉን በምን አግባብ እንደያዙ ለማጣራት ትእዛዝ ቢሰጥም አከራካሪዉን መሬት አስቀድመዉ የያዙትና ያለሙት አመልካች ቢሆኑም መሬቱ በቀበላ መሬት አስተዲደር በሚለካበት ጊዜ አመልካች መሬቱን በሕገ-ወጥ መንገድ ነዉ የያዙት በሚል ምክንያት ሳይለካላቸዉ መታለፈንና በኋላም ተጠሪ መሬቱን ተመርተዋል ከሚባል በስተቀር ሁለቱም ወገኖች መሬቱን በምን አግባብ አግኝተዉ እንደያዙ ለጽ/ቤቱ መረጃ እንደላለዉ በመግለጹ ሳይረጋገጥ ቀርቷል።
ከላይ በተመለከተዉ መሰረት ለስር ፍርድ ቤቶች የቀረቡ ማስረጃዎች የሚያሳዩት ከ1999ዓ/ም ጀምሮ እስከ 2004 ዓ/ም ድረስ አከራካሪዉን መሬት የያዙትና የተለያዩ ተክልችን በመትከል እንዱሁም 2004ዓ/ም እስከፈረሰበት ጊዜ ድረስ ቤት ጭምር ሰርተዉ በይዞታዉ ሲጠቀሙ የቆዩት አመልካች መሆናቸዉ ቢረጋገጥም ይህንን ይዞታ አመልካች በምን አግባብና በማን ፈቃጅነት ይዞዉ ሲጠቀሙ እንደቆዩ ግን ተገቢዉን ማስረጃ በማስቀረብና የቀረቡትንም በመመዘን በሚገባ ባለመጣራቱ የፍሬ ነገሩ መኖር አለመኖር አለመረጋገጡን ተገንዝበናል። በወረዲዉ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ጽ/ቤት ለወረዲ ፍርድ ቤት በተላከ ማስረጃ ላይ ይዞታዉን አመልካች በሕገ-ወጥ መንገድ ይዘዋል በሚል በአመልካች ስም ሳይለካ ቀርቷል በሚል የገለጸዉ አገላለጽ መሬቱን አመልካች ከመነሻዉ በሕገ-ወጥ መንገድ በመያዛቸዉ ምክንያት ነዉ ወይስ በወቅቱ በአካባቢዉ በነበረ ግጭት ጋር በተያያዘ ለአመልካች መሬቱ አይገባቸዉም በሚል ነዉ የሚለዉን በግልጽ የማያሳይ በመሆኑ ተገቢዉ ማብራሪያ እንዱሰጥበት ላደረግና ትክክለኛዉ ምክንያት ማረጋገጥ ይገባዉ ነበር። እንዱሁም ይዞታዉ በአመልካች የተያዘበት መንገድ ካለመረጋገጡም በተጨማሪ አመልካች በአካባቢዉ በተፈጠረ አለመረጋጋት አማራ ናቸዉ በሚል ምክንያት ተፈናቅለዉ ከቤተሰቦቻቸዉ ጋር ጥቃት እንዲይደርስባቸዉ ያለፍላጎታቸዉ ይዞታዉን ለቀዉ በ2004 ዓ/ም ወደ ላላ አካበባቢ ሲሄደ ደግሞ ተጠሪ አከራካሪዉን መሬት በመያዝ ከ2004ዓ/ም ጀምሮ እየተጠቀሙ እንደሚገኙ ቢረጋገጥም ተጠሪም መሬቱን በምን አግባብና በማን ፈቃጅነት እንደያዙ ማስረጃዎችን ከሚመለከተዉ አካል በማስቀረብና የቀረቡትን ማስረጃዎች በመመዘን በአግባቡ እንዲልተጣራ ተረድተናል።
ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን መሬት አስቀድመዉ ይዘዉ ሲጠቀሙ የቆዩት አመልካች ሲሆኑ መሬቱ ለሕዝብ ጥቅም ያስፈልጋል በሚል ወይም መሬቱን ባለመንከባከብ ጉዲት እንዱደርስበት አድርገዋል በሚል እንዱለቁ ተደርገዋል የሚል ክርክር አልቀረበም።እንዱሁም አመልካች በ2004 ዓ/ም መሬቱን የለቀቁት በአካባቢዉ በተፈጠረ ግጭት ምክንያት ከቤተሰቦቻቸዉ ጋር ጥቃት ይደርስብኛል በሚል ተፈናቅለዉ እንጂ በሰፈራ ወይም በፍላጎታቸዉ በሕግ ከተወሰነዉ ጊዜ በላይ አካባቢዉን ለቀዉ በመቆየታቸዉ ምክንያት ባለመሆኑ የወረዲዉ ፍርድ ቤት በዉሳኔዉ ላይ እንደገለጸዉ በክልለ አዋጅ ቁጥር 110/1999 አንቀጽ 9/1 መሰረት በመሬት ሽግሽግ ምክንያት አመልካች ከያዙት መሬት እንዱለቁ የሚደረግበት አግባብ ባለመኖሩ ተጠሪ መሬቱን በሽግሽግ ያገኘሁት ነዉ ብለዉ ያሰሙት ክርክር አመልካች የያዙትን መሬት እንዱለቁ የሚያደርግ ምክንያት አይደለም።
እንዱሁም አንድ የገጠር መሬት ባለይዞታ መሬቱን የያዘዉ አግባብ ባላቸዉ የፋዳራልም ሆነ የክልለ ሕግጋት ላይ ከተደነገገዉ አግባብ ዉጭ ቢሆን እንኳን ግለሰቡ በዚህ አግባብ የያዘዉን መሬት በሕግ በተደነገገዉ ስርዓት አግባብ ባለዉ የመንግስት አካል እንዱለቅ ይደረጋል እንጂ መሬቱን ከሕግ አግባብ ዉጭ ይዟል በሚል ባለይዞታዉን አስለቅቆ ላላ ግለሰብ መሬቱን በመያዝ ባለይዞታ የመሆንበት አግባብ በሕግ የተፈቀደ ተግባር አይደለም።በዚህ መሰረት ግለሰቦች አንደ የላላዉን መሬት በማስለቀቅ የሚይዙ ከሆነ የሕግ የበላይነት መርህ ተጥሶ በምትኩ በጉልበት መመራትን ስለሚተካ በሕግ የሚደገፍ አይደለም።በመሆኑም አመልካች አከራካሪዉን መሬት በሕግ አግባብ ባይዙ እንኳን በሕግ በተዘረጋዉ ስርዓት መሰረት አግባብ ያለዉ አካል እንዱያስለቅቃቸዉ ይደረጋል እንጂ አመልካች በጸጥታ ችግር ምክንያት ተፈናቅለዉ መሬቱን በለቀቁበት ጊዜ ዉስጥ ተጠሪ መሬቱን በቀጥታ ይዘዉ አልለቅም ለማለት የሚችለበት የሕግ አግባብ የለም። ተጠሪ አከራካሪዉን መሬት አለቅም በማለት መከራከር የሚችለት በሕግ አግባብ በሚመለከተዉ የመንግስት አካል አመልካች መሬቱን እንዱለቁ ተደርጎ መሬቱ በድልድል(በምሪት) ሲሰጣቸዉ ብቻ ነዉ።
ከመሰረታዊዉ አንድን ፍሬ ነገር ማስረጃ አቅርቦ ከማስረዲት ሸክም መርህ (Basic Principle of Burden of Proof) መረዲት እንደሚቻለዉ አንድ አከራካሪ ፍሬ ነገር አለ ወይም የለም ብል የሚከራከር ተከራካሪ ወገን ፍሬ ነገሩ መኖሩን ወይም አለመኖሩን ተገቢዉንና ሕጉ በተለየ ሁኔታ የሚጠይቀዉ ማስረጃ ካለም በሕግ ተቀባይነት ያለዉ ነዉ ያለዉን ማስረጃ በማቅረብ የማስረዲት ሸክም(ግዳታ) አለበት (የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2001 ይመለከቷል)።እንዱሁም የምንከተለዉ የክርክር አመራር ሥነ ሥርዓት ፍርድ ቤቶች(ዳኞች) የገለልተኛነት መርህን በጠበቀ መልኩ ክርክሮችን በማስረጃ በማንጠር አንጻራዊ እዉነታን ከመፈለግ አንጻር ንቁ ተሳትፍ እንዱኖራቸዉ የሚጠይቅ በመሆኑ በራሳቸዉ አነሳሽነት ወደ እዉነታዉ የሚያደርስ ማስረጃ በትእዛዝ አስቀርበዉ እዉነታዉን ማጣራት ይጠበቅባቸዋል (የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 136/1፣249፣264 እና 345/1 ይመለከቷል።) ሲጠቃለል አመልካች አከራካሪዉን መሬት ከ1999ዓ/ም ጀምሮ እስከ 2004 ዓ/ም ድረስ የተለያዩ ተክልችን በመትከልና ቤት ሰርተዉ ሲጠቀሙ ቆይተዉ በአካባቢዉ በተፈጠረ ግጭት ምክንያት ተፈናቅለዉ ለቀዉ መሄዲቸዉ የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነዉ።እንዱሁም ተጠሪ ከ2004ዓ/ም ጀምሮ ይህንን መሬት ይዘዉ እየተጠቀሙ እንደሚገኙ ተረጋግጧል።ሆኖም አመልካች መሬቱን በሕግ አግባብ የሚመለከተዉን የመንግስት አካል አስፈቅደዉ መያዝ አለመያዛቸዉ እንዱሁም ተጠሪ አከራካሪዉን መሬት ይዘዉ እየተገለገለ የሚገኙት አግባብ ባለዉ ሕግ መሰረት በሚመለከተዉ የመንግስት አካል ተፈቅድላቸዉ ስለመሆኑ ሳይረጋገጥ የወረዲዉ እና የዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ተጠሪ መሬቱን ለአመልካች ሉለቁ ይገባል ብለዉ መወሰናቸዉ እንዱሁም ጉዲዩን በይግባኝና በሰበር ያየዉ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተጠሪ መሬቱን ለአመልካች ሉለቁ አይገባም በማለት የስር ፍርድ ቤቶችን ዉሳኔ በመሻር የሰጠዉ ዉሳኔ በማስረጃ መረጋገጥ ያለበት ፍሬ ነገር እንዱረጋገጥ ሳያደርጉ የደረሱበትን ድምዲሜ እንደሆነ ስለሚያሳይ ሉታረም የሚገባዉ መሰረታዊ የሆነ የሕግ አተገባበርና የክርክር አመራር ጉድለት ነዉ። ስለሆነም ተከታዩን ወስነናል።
የጉራፈርዲ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 18/10/2011ዓ/ም የሰጠዉን ዉሳኔ፣ የቤንች አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 26/10/2011 ዓ/ም የሰጠዉ ትእዛዝ፣ የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 30/12/2011ዓ/ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ ላይ በቀን 25/03/2012ዓ/ም የሰጠዉ ዉሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ተሽርዋል።
የጉራፈርዲ ወረዲ ፍርድ ቤት መዝገቡን አንቀሳቅሶ አመልካች አከራከሪዉን መሬት በቀበላ አስተዲደር ተመርተዉ መያዝ አለመያዛቸዉን፣ መሬቱ በአመልካች ስም ሳይለካ የቀረበትን ምክንያት፣ይህንን አመልካች አልምተዉ ሲጠቀሙ የነበረዉን መሬት በአካባቢዉ ተፈጥሮ በነበረ የጸጥታ ችግር ምክንያት ራሳቸዉንና ቤተሰባቸዉን ከጥቃት ለመከላከል ለቀዉ ከሄደበት ሲመለሱ መሬቱን ተጠሪ ሉያዙ የቻለት በምን አግባብ እንደሆነና አመልካች መሬቱን በሕግ አግባብ እንዱለቁ ተደርጎ በሚመለከተዉ የመንግስት አካል ለተጠሪ የተላለፈ መሆን አለመሆኑን ከቀበላ አስተዲደርና ከላላ ከሚመለከተዉ አካል ማስረጃ አስቀርቦ አጣርቶና የቀረቡለትን ማስረጃዎች መዝኖ ሕግን መሰረት ያደረገ ዉሳኔ እንዱሰጥ ጉዲዩን በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 343/1 መሰረት መልሰንለታል።
ግራ ቀኝ በዚህ ችልት ያወጡትን ወጭ የየራሳቸዉን እንዱችለ ተወስኗል።
ት እ ዛ ዝ
የዉሳኔዉ ግልባጭ ለሥር ፍርድ ቤት ይተላለፍ። ግራ ቀኙ ሲጠይቁም ግልባጩ ይሰጣቸዉ።
በመዝገቡ ላይ የተሰጠ እግድ ካለ ተነስቷል።ይጻፍ።
. መዝገቡ ተዘግቷል፤ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።