በፍትሐ ብሓር ሕግ አግባብ የተደረገ የስጦታ ዉል መኖር ሳይረጋገጥ ክርክርን ከስጦታ ዉል ከማስመዝገብ አንጻር ብቻ በማየት የስጦታ ዉል እንዱመዘገብ የሚያስገድድ ሕግ ስለላለ መሬትን ይዞ በመጠቀም ብቻ በስጦታ የተላለፈ ነዉ ወደሚል ድምዲሜ የሚያደርስ ስላለመሆኑ የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 881 ወይም 882 የገጠር የእርሻ መሬት በስጦታ ማስተላለፍ በሚመለከቱ ጉዲዮች ላይ ልዩ ሕግ ሆነዉ ተፈጻሚ መሆን ያለባቸዉ ስለገጠር መሬት አጠቃቀምና አስተዲደር የወጡ ሕጎች ቢሆኑም በእነዚህ ሕጎች ባልተሸፈኑ ጉዲዮች አቶ ሻረው ወርቅዬ እና እነ ልክዬ ወርቅዬ (2 ሰዎች) ሕጎቹ ስራ ላይ ባልዋለበት ጊዜ የተፈጸሙ ሕጋዊያን ተግባራት ላይ እንደ ነገሩ ሁኔታ በፍትሐ ብሓር ሕግ የማይንቀሳቀስ ንብረት በስጦታ ስለሚተላለፍበት የተደነገገዉ ተፈጻሚነት ያለው ስለመሆኑ
No summary available.
መጋቢት 29 ቀን 2013 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ ተሾመ ሽፈራዉ ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግሥቱ ነጻነት ተገኝ አመልካች፡- አቶ ሻረው ወርቅዬ ተጠሪ፡-
ጉዲዩ የገጠር የእርሻ መሬት ይዞታ በስጦታ የሚተላለፍበት የሕግ አግባብ የሚመለከት ነዉ። ክርክሩ በተጀመረበት በአማራ ክልል መሀል ሳይንት ወረዲ ፍርድ ቤት ተጠሪዎች በአመልካች ላይ በሞግዚታቸዉ አማካኝነት በመሰረቱት ክስ በዚሁ ወረዲ 041 ቀበላ ጠጅ ዉሃ እየተባለ በሚጠራበት ቦታ አዋሳኞቹ በክሱ የተጠቀሰዉን የመሬት ይዞታ ከሟች አባታቸዉ ወርቅዬ መለሰ ላይ ወርሰዉ በይዞታ ማረጋገጫ ደብተር አስመዝግበዉ የሚጠቀሙበትን መሬት አመልካች እንደያዘባቸዉ በመግለጽ እንዱለቁላቸዉ እንዱወሰን ዲኝነት ጠይቀዋል። ተጠሪ ለክሱ በሰጡት መልስ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን መሬት የያዝኩት ሟች አባቴ ወርቅዬ መለስ በ1991 ዓ/ም በህይወት እያለ በስጦታ አስተላልፍልኛል።
አባቴ በ1995 ዓ/ም በሞት በመለየቱ ማንም ሰዉ ሰጥቶ የሞተዉን ላላ ሰዉ ማፍረስ አይችልም በማለት ተከራክረዋል።
የግራ ቀኙን ክርክር እና ምስክሮች በመስማትና በመመዘን የወረዲዉ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 29/10/2010 ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ ክስ የተነሳበት መሬት የአሁን አመልካች በስጦታ ያገኙት ስለሆነ ለተጠሪዎች ሉለቁ አይገባም በማለት ወስኗል።በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት የአሁን አመልካቾች ይግባኝ ለደቡብ ወል ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበዉ ፍርድ ቤቱ የሥር ፍርድ ቤት የሰጠዉን ዉሳኔ በመሻር ክስ የተነሳበት መሬት ለአመልካች በስጦታ ተላልፍ አድሯል ወይ?ደብተር ለተጠሪዎች ተሰርቶ ለአመልካች ለምን አልተሰራም የሚለትን ከወረዲዉ ገጠር መሬት አስተዲደር እና አጠቃቀም ጽ/ቤት ማስረጃ በማስቀረብ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘም ተጨማሪ ምስክሮችን በመስማት ካጣራ በኋላ መሬቱ ለማን ይገባል የሚለዉን የመሰለዉን እንዱወስን በማለት መልሶለታል።
የወረዲዉ ፍርድ ቤት መዝገቡን አንቀሳቅሶ ከወረዲዉ ገጠር መሬት አስተዲደር እና አጠቃቀም ጽ/ቤት ማስረጃ በማስቀረብ፣አስቀድሞ የሰማቸዉ የግራ ቀኝ ምስክሮች የሰጡትን ምስክርነት ቃል እና የሰነድ ማስረጃዎችን በመመርመር በቀን 04/03/2012ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ መሬት ለአሁን አመልካች በስጦታ የተላለፈ ስለመሆኑ የሚያሳይ ማስረጃ በወረዲዉ የገጠር መሬት አስተዲደር እና አጠቃቀም ጽ/ቤት ስለላለ ለአመልካች መሬቱ በስጦታ አለመተላለፈ ተረጋገጧል።ምንም እንኳን የግራ ቀኙ ምስክሮች መሬቱ በአመልካች ስለማደሩ የመሰከሩ ቢሆንም በአማራ ብሓራዊ ክልል መንግስት የገጠር መሬት አዋጅ ቁጥር 252/2009 መሰረት የመሬት ይዞታ በስጦታ ተላልፎል የሚለዉን የማያሟላ በመሆኑና የማይንቀሳቀስ ንብረት ከመሆኑ አንጻር ሉረጋገጥ የሚችለዉ በሰነድ ማስረጃ በመሆኑ በተሻለ ሁኔታ ግልጽ ማስረጃ በማቅረብ ተጠሪዎች መሬቱን በዉርስ እንዲገኙ ስላስረደ አመልካች መሬቱን በስጦታ አላገኙም ሲል ወስኗል።
በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት አመልካች ይግባኝ ለደቡብ ወል ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ አቅርበዉ ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶና የቀረቡትን ማስረጃዎች በመመዘን በቀን 11/04/2011 ዓ/ም በሰጠው ውሳኔ ለክርክሩ መነሻ የሆነውን መሬት አመልካች ከ1991 ዓ/ም ጀምሮ ይዘዉ እየተጠቀሙ እንደሚገኙ በማስረጃ ተረጋግጧል።የአሁን ተጠሪዎች አከራካሪዉን መሬት ለ10 ሆነዉ በዉርስ መሬትነት በወረዲዉ ገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም ጽ/ቤት በ2008ዓ/ም ያስመዘገቡ ቢሆንም አመልካች ደግሞ በለጠ ወርቅዬ ከተባለዉ ጋር በመሆን መሬቱን ከ1991 ዓ/ም ጀምሮ በመያዝ ይጠቀሙ እንደነበር ተረጋግጧል። በ1991 ዓ/ም ላይ ደግሞ የመሬት ስጦታ ምዝገባ ያልነበረ እና በወቅቱ የነበረዉ የመሬት አዋጅ ቁጥር 89/1989 ስለመሬት ስጦታ ምዝገባ ስለማይደነግግ የምዝገባ ስርዓት ባልነበረበት ወቅት የተቋቋመ መብት(የስጦታ ዉል) አልተመዘገበም በሚል በወረዲ ፍርድ ቤት ዉድቅ መደረጉ ተገቢ አይደለም።የወረዲ መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም ጽ/ቤት የተመዘገብ ስጦታ የለም አለ እንጂ ከጅምሩም ስጦታ የለም አላለም። በመሆኑም አመልካች የስጦታ ዉል ምዝገባ ባልነበረበት ወቅት በሰጦታ የያዙትን ይዞታ ወደ ዉርስ ይዞታ በመቀላቀል የሚያስረክቡበት ምክንያት የለም በማለት የስር ፍርድ ቤትን ዉሳኔ በመሻር ወስኗል።
ተጠሪዎች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበው ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን በመ/4 ላይ አከራክሮ በቀን 03/02/2012 ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ አመልካች የስጦታ ውል ከሟች የተደረገላቸዉ ለመሆኑ አላስረደም። የስጦታ ውለ አለመመዝገቡ ብቻ ሳይሆን በእርግጥ ሟች በስጦታ ስለማስተላለፊቸው አልተረጋገጠም። አመልካች መሬቱን ከ1991 ዓ/ም ጀምሮ ይጠቀሙበት የነበረ መሆኑ ብቻውን በስጦታ አግኝተዉታል የሚያስብል መደምደሚያ ላይ የሚያደርስ አይደለም።እንዱሁም ተጠሪዎች በሞግዚት የሚተዲደሩና በጊዜዉ መብታቸዉን ሉጠይቁ የሚችለ አለመሆናቸዉና ሥልጣን ያለዉ አካል መሬቱን ለአመልካች አለማጥናቱና ስለስጦታዉ የሚያዉቀዉ ነገር አለመኖሩ ተደምሮ ሲታይ አመልካች መሬቱን በስጦታ አግኝተዋል የሚያስብል ሆኖ አልተገኘም በማለት የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዉሳኔ በመሻር የመሀል ሳይንት ወረዲ ፍርድ ቤት ውሳኔ በማፅናት ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ቅር በመሰኘት አቤቱታቸውን ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ቢያቀርቡም ችልቱ በመ/2 ላይ በቀን 04/05/2012 ዓ/ም በሰጠዉ ትእዛዝ ሰርዞባቸዋል።
አመልካች በቀን 07/05/2012 ዓ/ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረቡት በዚህ መልኩ በተሰጠ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን የአቤቱታቸዉ ይዘት በአጭሩ የሚከተለዉ ነዉ።
ለክርክር መነሻ የሆነው መሬት አባቴ በ1991 ዓ/ም ላይ በስጦታ ሰጥቶኝ እስካሁን ድረስ ይዤ እየተጠቀምኩ የምገኝ ነዉ። ስጦታውም በጊዜው ስጦታ መዝጋቢ መስሪያ ቤት ባለመቋቋሙ የተነሳ በመስሪያ ቤት ያልተመዘገበ እና ስጦታው በቃል የተደረገ ስለመሆኑ በግራ ቀኝ ምስክሮች በስር ፍርድ ቤት ባስረዲም የሰነድ ማስረጃ አልቀረበም ሲል የወረዲዉ ፍርድ ቤት የሰጠዉ ዉሳኔ ስህተት ነዉ።በአንጻሩ ከፍተኛው ፍርድ ቤት አመልካች ስጦታውን በሰው ማስረጃ በአጥጋቢ ሁኔታ ማስረዲቴን አረጋግጦ የሰጠዉ ዉሳኔ በሰ/መ/ ላይ የተሰጠውን አስገዲጅ የሕግ ትርጉም መሰረት ያደረገ ነዉ።አከራካሪውን መሬት ወላጅ አባቴ በቃል በስጦታ ተሰጥቶኝ ከ1991 ዓ/ም አንስቶ መያዜ እስከተረጋገጠ ድረስ የፅሁፍ ውል አላቀረብክም በሚል ተጠሪዎች የሟች አባቴን ክስ ከቀረበበት መሬት ውጪ ያለ አራት መሬቶችን ወርሰው ይዘዉ እያለ አመልካች ደግሞ ሟች አባቴ በህይወት እያለ የሰጠኝን ይሀንን ክርክር የተነሳበትን መሬት ብቻ እንደያዝኩ እየታወቀ ፍትህንና ርትእን በሚቃረን መልኩ መሬቱን እንዱለቅ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት መወሰኑ ስህተት ስለሆነ ተሽሮ የደቡብ ወል ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ እንዱፀናልኝ በማለት የሰበር አቤቱታቸውን አቅርበዋል።
የሰበር አጣሪ ችልት አቤቱታውን መርምሮ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን መሬት ለአመልካች ከአባታቸዉ በ1991 ዓ/ም በስጦታ ተላልፍላቸዉ አባታቸው በ1995 ዓ/ም መሞታቸው ተረጋግጦ እያለ የስጦታ ዉለ አልተመዘገበም በሚል የአመልካች ክርክር ውድቅ የተደረገበትን አግባብ የስጦታ ውለ መመዝገብ አለበት የሚለዉ የክልለ የመሬት አዋጅ ቁጥር 133 የወጣው 1998 ከመሆኑ አንጻር የተሰጠውን ውሳኔ አግባብነት እንዱመረመር ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልት አንዱቀርብ ትዕዛዝ በመስጠቱ ተጠሪዎች በቀን 24/06/2012 ዓ/ም የተፃፈ በአጭሩ የሚከተለዉን መልስ አቅርበዋል።
አንድ የስጦታ ውል ላደረግ የሚችለው በሕጉ አግባብ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2171 መሰረት መሆን ሲገባዉ አመልካች ምንም አይነት የስጦታ ውል አላቀረቡም። የስጦታ ውለም በሕግ ፉት አልጸደቀም። የሟችን ንብረት በውርስ ያገኘነው ልጆች እያለን አመልካችም እንደ ልጅ ተቆጥረዉ ድርሻ መሬት ካገኙ በኋላ የእኛን ድርሻ ለመካፈል የስጦታ ውል አለኝ አለ እንጂ የሟች አባታችንን በውርስ ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር በ2008 ዓ/ም ወስደን ክፍፍል ስለተፈጸመ ድርሻችንን ሉወሰደ ስለማይችለ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰጠዉ ዉሳኔ የተፈጸመ ስህተት የለም በማለት ተከራክረዋል። አመልካች በቀን 07/07/2012 ዓ/ም የተጻፈ የመልስ መልስ በማቅረብ ተከራክረዋል።
ከዚህ በላይ የተመዘገበዉ የግራ ቀኝ ክርክርና በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ዉሳኔዎች ይዘት ሲሆን እኛም የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩ ለሰበር ችልት ያስቀርባል ሲል ከያዘዉ ጭብጥ አንጻር የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ መርምረናል።
እንደተመረመረውም ተጠሪዎች ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ የመሬት ይዞታ ከአባታቸዉ በዉርስ ተላልፍላቸዉ ከ2008ዓ/ም ጀምሮ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ተሰጥቷቸዉ በስማቸዉ የተመዘገበዉን አመልካች እንደያዙባቸዉ በመግለጽ አመልካች በፍርድ ኃይል ተገደዉ እንዱለቁ እንዱወሰንላቸዉ በመጠየቅ ተከራክረዋል። አመልካች ደግሞ መሬቱን አባቴ በ1991 ዓ/ም በስጦታ ሰጥቶኝ እስካሁን ይዤ እየተጠቀምኩ ስለምገኝ ልለቅ አይገባም በማለት ተከራክረዋል።የስር የወረዲ ፍርድ ቤት አመልካች በአማራ ክልል የገጠር መሬት አጠቃቀምና አስተዲደር አዋጅ ቁጥር 252/2009 መሰረት አከራካሪዉ የመሬት ይዞታ በስጦታ የተሰጣቸዉ ስለመሆኑ የሚያሳይ በመሬት አጠቃቀምና አስተዲደር ጽ/ቤት የተመዘገበ ሰነድ በማስረጃነት ስላላቀረቡ መሬቱ በስጦታ የተላለፈላቸዉ አይደለም በማለት ወስኗል።
የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ደግሞ ለአመልካች አከራካሪዉ ይዞታ በ1991 ዓ/ም በስጦታ እንደተሰጣቸዉ ምስክሮች ስላስረደ በወቅቱ ተፈጻሚ ሲሆን የነበረዉ አዋጅ ቁጥር 89/1889 መሬት በስጦታ ሲተላለፍ የስጦታ ዉለ መመዝገብ አለበት ብል ስለማይደነግግ የስር ፍርድ ቤት በወቅቱ ስራ ላይ ያልነበረዉን ሕግ መሰረት በማድረግ መሬቱ በስጦታ ስለመተላለፈ አመልካች የተመዘገበ ዉል በማስረጃነት አላቀረቡም ማለቱ ስህተት ስለሆነ አመልካች በስጦታ ተላልፍላቸዉ ይዘዉ ሲጠቀሙ የነበረዉ መሬት መሆኑን አስረድተዋል በማለት የስር ፍርድ ቤትን ዉሳኔ ሽሯል። በልላ በኩል የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመልካች መሬቱን በስጦታ አግኝቻለሁ ይበለ እንጂ የስጦታ ዉለ አለመመዝገቡ ብቻ ሳይሆን በሟች አባታቸዉ ስጦታ የተደረገላቸዉ ስለመሆኑም ባለማስረዲታቸዉ አመልካች መሬቱን ከ1991 ዓ/ም ጀምሮ ይጠቀሙበት የነበረ መሆኑ ብቻውን በስጦታ አግኝተዉታል የሚያስብል መደምደሚያ ላይ የሚያደርስ አይደለም በማለት የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዉሳኔ ሽሯል።
ለአመልካች አከራካሪዉ የመሬት ይዞታ በሕግ አግባብ በተደረገ የስጦታ ዉል ተላልፎል ወይስ አልተላለፈም የሚለዉ መመርመር ያለበት አመልካች መሬቱ በስጦታ ተላልፍልኛል ባለበት በ1991ዓ/ም ተፈጻሚ ሲሆን በነበረው ሕግ ላሆን ይገባል። ይህም ሕግ ወደ ኋላ ተመልሶ አይሰራም ከሚለዉ አጠቃላይ መርህ (the principle of non-retroactivity of laws) ጋር የተያያዘ ነው። ሕግ በዜጎች መካከል ያለዉን ግንኙነት ለመቆጣጠር ሲባል በሕግ አዉጪዉ አካል የሚወጣ ነዉ። ሕግ የሚወጣዉም ሕጉ በስራ ላይ ባለበት ወቅት በዜጎች መካከል ያለዉን ወይም ወደ ፉት የሚፈጠረዉን ግንኙነት ለመቆጣጠር ወይም ለመዲኘት በመሆኑ ሕጉ ከመዉጣቱ በፉት ወይም ከተሻረ በኋላ በተፈጠረ/በሚፈጠር ግንኙነት ላይ ተፈፃሚ ማድረግ አይቻልም። ሕግ ወደ ኋላ ተመልሶ አይሰራም የሚለዉም መርህ ከዚሁ የመነጨ ሲሆን፣ መሰረተ ሃሳቡም ዜጎች በሚያዉቁት ሕግ መተዲደር አለባቸዉ የሚለዉን ታሳቢ ያደረገና ሕጉ በስራ ላይ ከዋለ በኋላ ለተፈጠረ መብትና ግዳታ ወይም ፍሬ ነገር ላይ ተፈጻሚ መሆን ስላለበት ነዉ። በልላ አገላለጽ አንድ ሕግ ተፈፃሚ መሆን የሚጀምርበትን ጊዜ አስመልክቶ በሕግ አዉጪዉ ከተደነገገዉ ቀን በፉት ለተፈጠሩት ክስተቶች ወይም መብትና ግዳታዎች ተፈፃሚነት አይኖረዉም የሚል ሃሳብ ያለዉ ነዉ። ይህ መርህ ከሕግ የበላይነት መገለጫዎች ዉስጥ አንደ ነዉ። ስለሆነም፣ አንድ መሰረታዊ ሕግ (substantive law) ወደ ኋላ ተመልሶ እንዱሰራ ሕግ አዉጪዉ እራሱ በልዩ ሁኔታ ካላመላከተ በስተቀር፣ ፍርድ ቤት ወይም ላላ የዲኝነት ስልጣን የተሰጠዉ አካል ለያዘዉ ጉዲይ ተፈፃሚነት ያለዉን መሰረታዊ ህግ ሲወስን መሰረት ሉያደርግ የሚገባዉ ወይም መሰረት እንዱያደርግ የሚጠበቅበት ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ጉዲይ በተፈጠረበት ጊዜ በስራ ላይ የነበረዉን ሕግ ላሆን ይገባል። ስለሆነም ሕጋዊ ተግባሩ(Juridical act) ወይም መብትና ግዳታ በተፈጠረበት ጊዜ የነበረዉ ሕግ በልላ ሕግ የተተካ ሆኖ ሲገኝ እና ክርክሩ ለፍርድ ቤት ወይም ለዲኝነት ሰጪ አካል የቀረበዉ አዱሱ ሕግ በስራ ላይ ከዋለ በኋላ ሆኖ ከተገኘ ፍርድ ቤቱ ክርክሩን መምራት እና ዉሳኔ መስጠት ያለበት በመብትና ግዳታው በተፈጠረበት ጊዜ ተፈጻሚ በነበረው ሕግ መሰረት ይሆናል፤ ክርክሩ አዱሱ ሕግ ስራ ላይ ከዋለ በኋላ ለፍርድ ቤት መቅረቡ ጉዲዩ በአዱሱ ሕግ መሰረት እንዱመራ ምክንያት ላሆን አይገባም። ይህን ማድረግ ሕግ ወደ ኋላ ተመልሶ አይሰራም የሚለዉን የሕግ መርህ የሚጥስ ከመሆኑም በላይ የሕግ የበላይነት እንዲይረጋገጥ ወይም እንዱሸረሸር ምክንያት ይሆናል።
ለያዝነዉ ጉዲይ ተገቢዉን እልባት መስጠት ይቻል ዘንድ ለጉዲዩ ተፈጻሚነት ያለዉን ሕግና የሕጉን ድንጋጌ በጥንቃቄ መለየት ያስፈልጋል። አመልካች አከራካሪዉ መሬት በስጦታ ተላልፍልኛል በሚል ይዘዉ መጠቀም የጀመሩት ከ1991 ዓ/ም ጀምሮ እንደሆነ በበታችኞቹ ፍርድ ቤቶች በማስረጃ የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነዉ። በ1991 ዓ/ም በአማራ ክልላዊ መንግስት የገጠር መሬት በስጦታ ሲተላለፍ በምን አግባብ መተላለፍ እንዲለበትና ስለዉለ ፍርማሉቲ የሚደነግግ ሕግ እንዲልነበረ ተገንዝበናል። የፋዳራል መንግስት የገጠር መሬት አስተዲደር አዋጅ ቁጥር 89/1989 ከሰኔ 30 ቀን 1989 ዓ/ም ጀምሮ ከመጽናቱ በፉት በሥራ ላይ የነበረዉ የገጠር መሬትን የሕዝብ ሀብት ለማድረግ የወጣዉ አዋጅ ቁጥር 31/1967 ነዉ። ይህ አዋጅ ቁጥር 31/1967 የገጠር መሬት በስጦታ ስለሚተላለፍበት ሁኔታና ሲተላለፍም በምን የዉል ፍርማሉቲ መተላለፍ እንዲለበት የሚደነግግ አይደለም።ይልቁንም ከዚህ አዋጅ አንቀጽ 5 የምንገነዘበዉ የገጠር መሬት በስጦታ ጭምር እንዲይተላለፍ መደንገጉን ነዉ። ሆኖም ይህ አዋጅ በ1989 በወጣዉ አዋጅ ቁጥር 89/1989 ከመተካቱ በፉት የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት ከነሐሴ 15 ቀን 1987 ዓ/ም ጀምሮ ወጥቶ ሥራ ላይ በመዋለ በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 40/3 ላይ መሬት የማይሸጥ የማይለወጥ በኢትዮጵያ ብሓሮች ብሓረሰቦችና ሕዝቦች በጋራ ባለቤትነት የሚታወቅ ንብረት እንደሆነ ቢደነግግም መሬት በሕግ በሚደነገገዉ ስርዓት መሰረት በዉርስ ወይም በስጦታ ማስተላለፍ አይቻልም ሲል ሕገ መንግስቱ ያስቀመጠዉ ክልከላ የለም።ሕገ መንግስቱን ተከትል በወጣዉ የገጠር መሬት አስተዲደር አዋጅ ቁጥር 89/1989 አንቀጽ 2/3 ላይ የይዞታ መብት ለቤተሰብ አባል በዉርስ ማስተላለፍን ጭምር የሚያካትት እንደሆነ መደንገጉ ሲታይ ከአዋጅ ቁጥር 31/1967 በኋላ የወጡ ሕጎች የገጠር መሬት በዉርስና በስጦታ እንዲይተላለፍ የሚያግደ አይደለም።
ሆኖም ሕገ መንግስቱን ተከትል የወጣዉ አዋጅ ቁጥር 89/1989 የገጠር መሬት በስጦታ ሉተላለፍ አይችልም በሚል ያስቀመጠዉ ክልከላ ባይኖርም ይህ አዋጅ የገጠር መሬት አስተዲደርን በተመለከተ የክልል መንግስታት ሕግ ሲያወጡ መሰረት ሉያደርጉ የሚገባቸዉን ሁኔታዎች በመደንገግ ላይ ትኩረት ያደረገ በመሆኑ የገጠር መሬት በስጦታ ሲተላለፍ የስጦታ ዉለን ፍርማሉቲና ዉለ ስለሚመዘገብበት አግባብ አልደነገገም። በዚህ ሕግ መነሻ በ1991 ዓ/ም ሆነ ከዚያ በፉት በተለይም የገጠር መሬት በስጦታ የሚተላለፍበትን አግባብ የሚደነግግ ሕግ በአማራ ክልል ወጥቶ ስራ ላይ አልዋለም። ምንም እንኳን የገጠር መሬት አጠቃቀምና አስተላለፍ በሚመለከቱ ጉዲዮች ላይ ልዩ ሕግ ሆነዉ ተፈጻሚ መሆን ያለባቸዉ ስለገጠር መሬት አጠቃቀምና አስተዲደር የወጡ ሕጎች ቢሆኑም በእነዚህ ሕጎች ባልተሸፈኑ ጉዲዮች ላይ እና እነዚህ ሕጎች ወጥተዉ ስራ ላይ ባልዋለበት ጊዜ የተፈጸሙ ሕጋዊያን ተግባራት ላይ እንደነገሩ ሁኔታ በፍትሐ ብሓር ሕግ የማይንቀሳቀስ ንብረት በስጦታ ስለሚተላለፍበት የተደነገገዉ ተፈጻሚ ላሆን ይገባል።
በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2443 ስር እንደተደነገገዉ የማይንቀሳቀስ ንብረት ለማስተላለፍ ወይም በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ መብት የሚሰጥ ስጦታ በግልጽ በሚደረግ ኑዛዜ አሰራር አይነት ካልተደረገ ፈራሽ እንደሆነ ተደንግጓል።በግልጽ የሚደረግ ኑዛዜ አሰራር በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 881 ስር ተመልክቷል። በዚህ ድንጋጌ ለግልጽ ኑዛዜ በተደነገገዉ ፍርማሉቲ መሰረት የማይንቀሳቀስ ንብረት በስጦታ ለመስጠት የሚደረገ ዉል በጽሁፍ ተደርጎ በአራት ምስክሮችና በስጦታ ሰጪዉ መፈረም አለበት።የምስክሮቹ ቁጥር ሁለት ላሆን የሚችለዉ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 882 ስር እንደተደነገገዉ የስጦታ ዉለ በዉል አዋዋይ ፉት ተደርጎ የተመዘገበ ሲሆን ነዉ።የስጦታ ዉለ በዉል አዋዋይ ፉት ተደርጎ የተመዘገበ ከሆነ አዋዋዩ ኦፉሰር ምስክር እንደሆነ ተገልጾ በስጦታ ዉለ ላይ ባይጻፍም የስጦታ ዉለ ያለምንም ተጽእኖ በነጻነት እንዱደረግ ሂደቱን የመራ ሰዉ በመሆኑ እንደምስክር ሉቆጠር እንደሚገባ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ (ቅጽ 8 ላይ እንደታተመዉ)ትርጉም ሰጥቷል።በዚሁ ሕግ ቁጥር 2447/1 ስር ስጦታ አለ የሚለዉ ሰዉ ስጦታ መኖሩን ማስረዲት እንዲለበት ተደንግጓል።
በተያዘዉ ጉዲይ አመልካች አከራካሪዉ መሬት በሕጉ አግባብ በስጦታ ዉል የተላለፈላቸዉ መሆኑን ማስረዲት ይጠበቅባቸዋል። ሆኖም አመልካች መሬቱን የያዝኩት በቃል በተደረገ የስጦታ ዉል ተላልፍልኝ ነዉ በሚል የተከራከሩ በመሆኑ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 881 ወይም 882 አግባብ በጽሁፍ ተደርጎ በስጦታ ሰጪዉና በምስክሮች የተፈረመ የስጦታ ዉል በማስረጃነት በማቅረብ አላስረደም።
አመልካች በሕጉ ተቀባይነት ያለዉን ማስረጃ አቅርበዉ ካላረጋገጡ አከራካሪዉ መሬት ለአመልካች በስጦታ ተላልፍላቸዋል ብል መወሰን አይቻልም። እንዱሁም አመልካች በሕጉ አግባብ በተቋቋመ የስጦታ ዉል መሬቱን ከአባታቸዉ በስጦታ ስለማግኘታቸዉ ካላስረደ መሬቱን ይዘዉ በመጠቀማቸዉ ብቻ መሬቱ በስጦታ ተላልፍላቸዋል ብል መደምደም አይቻልም። በሰ/መ/ ላይ በቀን 30/08/2009ዓ/ም የተሰጠዉ ትርጉም ላይ የሥጦታ ዉለ በጽሁፍ እንደተደረገ የተረጋገጠዉን ፍሬ ነገር መሰረት ተደርጎ የተሰጠ የሕግ ትርጉም በመሆኑ በተያዘዉ ጉዲይ ላይ በጽሁፍ የተደረገ የስጦታ ዉል በማስረጃነት ስላልቀረበ በተጠቃሹ መዝገብ ላይ የተሰጠ ትርጉም ለዚህ ጉዲይ ተፈጻሚነት የለዉም።
ሲጠቃለል የመሀል ሳይንት ወረዲ ፍርድ ቤት አመልካች አከራካሪዉን የገጠር መሬት በስጦታ ዉል ያገኙ ስለመሆኑ አላስረደም ሲል የደረሰበት ድምዲሜ የሚነቀፍ ባይሆንም የስጦታ ዉለ ተደረገ በተባለበት በ1991ዓ/ም ተፈጻሚነት የላለዉን በአማራ ብሓራዊ ክልል መንግስት የወጣዉን የገጠር መሬት አዋጅ ቁጥር 252/2009 ወደኋላ ተመልሶ ተፈጻሚ እንዱሆን በማድረግ የስጦታ ዉል የለም በማለት መወሰኑ ሕግ ወደኋላ ተመልሶ እንዲይፈጸም የሚከለክለዉን መርህ የሚጥስ በመሆኑ ከዚህ አኳያ የተፈጸመዉ ስህተት በደቡብ ወል ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት መታረሙ ተገቢ ነዉ ብለናል። ሆኖም የደቡብ ወል ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፍትሐ ብሓር ሕግ አግባብ የተደረገ የስጦታ ዉል መኖር አለመኖሩን መርምሮ መወሰን ሲገባዉ ጉዲዩን የስጦታ ዉል ከማስመዝገብ አንጻር ብቻ በማየት የስጦታ ዉል እንዱመዘገብ የሚያስገድድ ሕግ ስለላለ አከራካሪዉ መሬት ለአመልካች በስጦታ የተላለፈ ነዉ ወደሚል ድምዲሜ ላይ መድረሱ የሕግ አተገባበር ጉድለት ያለበት ስለሆነ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት መሻሩ ተገቢ ነዉ። ጉዲዩን በይግባኝ እና በሰበር ያየዉ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምንም እንኳን ከዚህ በላይ በተመለከተዉ አግባብ ተፈጻሚነት ያለዉን ሕግ በመለየትና ለአከራካሪዉ ፍሬ ነገር ተፈጻሚ በማድረግ የሰጠዉ ዉሳኔ አለመሆኑ ስህተት ቢሆንም ከዉጤት አንጻር ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን የገጠር መሬት አመልካች በስጦታ ተላልፍላቸዉ የያዙ ስለመሆኑ አላስረደም በማለት የወረዲዉን ፍርድ ቤት በማጽናት በመወሰኑ የተፈጸመ ስህተት የለም ብለናል። ስለሆነም ተከታዩን ወስነናል።
በመሀል ሳይንት ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 04/03/2012ዓ/ም ተወሰኖ በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/4 ላይ በቀን 13/02/2012ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ እና በክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በመ/2 ላይ በቀን 04/05/2012 ዓ/ም በተሰጠ ትእዛዝ መጽናቱ ተገቢ በመሆኑ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ጸንተዋል።
ግራ ቀኝ በዚህ ችልት ያወጡትን ወጭ የየራሳቸዉን እንዱችለ ተወስኗል።
ት እ ዛ ዝ
የዉሳኔዉ ግልባጭ ለሥር ፍርድ ቤት ይተላለፍ። ግራ ቀኙ ሲጠይቁም ግልባጩ ይሰጣቸዉ።
በመዝገቡ ላይ የተሰጠ እግድ ካለ ተነስቷል።ይጻፍ።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
የሰ/መ/ መጋቢት 30 ቀን 2011 ዓ/ም ዳኞች- መዓዛ አሸናፉ ሰለሞን አረዲ አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ ፈይሳ ወርቁ ጳውልስ ኦርሺሶ አመልካች፡- የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ነ/ፈጅ ፈርተውኃል ኃ/ጊዮርጊስ -ቀረቡ ተጠሪ፡- ተስፊዬ መብራቴ ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቶአል።
ጉዲዩ በመንግስት ሰራተኞች የጡረታ መብት አከባበር ጋር ተያይዞ የተነሳውን ክርክር የሚመለከት ነው።
ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ ለማህበራዊ ዋስትና ኤጂንሲ የዘላቂ ጡረታ መብት ይከበርልኝ ጥያቄ በማቅረባቸው ነው። አቤቱታው የቀረበለት ኤጂንሲውም የተጠሪ አገልግልት ከሃያ አመት በታች ነው፣ የተሰናበትከውም በጡረታ ሳይሆን በልላ ምክንያት ነው፣ በመሆኑም የሚወሰንልህ የዘለቄታ የጡረታ አበል የለም፣ ሉወሰንልህ የሚገባው ከጡረታ መዋጮ ተመላሽ ብቻ ነው በሚል ለተጠሪ በ26/07/2008 ዓ/ም ውሳኔውን ያሳወቃቸው ሲሆን ይህንኑ የኤጄንሲውን ውሳኔ ተከትል የአሁኑ ተጠሪ ይግባኛቸውን ለማህበራዊ ዋስትና ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ አቅርበዋል።
የአሁኑ ተጠሪ ለማህበራዊ ዋስትና ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ባቀረቡት ይግባኝም የዘለቄታ ጡረታ አበል እንዱወሰንላቸው አሰሪ መሰሪያ ቤቱ ቢጠይቅላቸውም አገልግልትህ ከሃያ ዓመት በታች፣ ከስራ የተሰናበቱትም በልላ ምክንያት ስለሆነ የሚወሰን የዘለቄታ ጡረታ አበል የለም ተብል መወሰኑ በተለያዩ መስሪያ ቤቶች ለ17 አመታት ከ11 ወራት አገልግለው በመስሪያ ቤቱ አደረጃጀት ለውጥ ምክንያት በእጩነት በእውነት ከቀረቡት ውስጥ ሳይታቀፈ በመቅረታቸው የተሰናበቱ ከመሆኑም በላይ ስራውን በለቀቁበት ጊዜ ስራ ላይ በነበረው የአዋጅ ቁጥር 22/23 1955 መሰረት የጡረታ መብታቸው ሉከበርላቸው የሚገባ መሆኑንና ከዚህ በኋላ በወጣው ህግ ደግሞ ጉዲዩ ሉገዛ የማይችል መሆኑን ዘርዝረው የኤጀንሲው ውሳኔ ተሽሮ የዘለቄታ ጡረታ መብታቸው እንዱከበርላቸው ይወሰን ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
የአሁኑ አመልካች በበኩለ በሰጠው መልስ፡- ተጠሪ አገልግልታቸው ከ20 ዓመት በታች በመሆኑ ከስራ የተሰናበቱት በጡረታ ሳይሆን በልላ ምክንያት ስለሆነ ሉያገኙ የሚገባቸው የአንድ ጊዜ የጡረታ መዋጮ ተመላሽ ብቻ ነው በማለት ተከራክሯል። ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የማህበራዊ ዋስትና ይግባኝ ሰሚ ጉባኤም የአሁኑ ተጠሪ አገልግልታቸው ከ10 ዓመት በላይ በመሆኑ በቀድሞው የጡረታ አዋጅ መሰረት የዘለቄታ ጡረታ መብት እንዱከበርላቸው ያቀረቡት ጥያቄ በአዋጅ ቁጥር 22/23/1955 መሰረት ቢያንስ 10 ዓመት ካገለገለ እና እድሜው ለጡረታ የደረሰ ከሆነ የጡረታ መብት እንዱከበርለት ቢደነግግም አመልካች ከስራ በሚሰናበቱበት ወቅት እድሜያቸው ለጡረታ ያልደረሰ ስለሆነ በዚህ አዋጅ መሰረት ሉስተናገደ የሚችለ አይደለም፣ ጉዲያቸው መታየት የሚገባው በአዋጅ ቁጥር 714/2003 መሰረት ሲሆን በዚህ አዋጅ አንቀጽ 19/2/ ድንጋጌ ስር ደግሞ ቢያንስ 20 ዓመት ያገለገለ የመንግስት ሰራተኛ በራሱ ፈቃድ ወይም በልላ ምክንያት አገልግልት ካቋረጠ የጡረታ እድሜው መውጫ ሲደርስ የአገልግልት ጡረታ አበል እስከ እድሜ ልኩ ይከፈለዋል በማለት ደንግጓል፣ አመልካች 17 አመት ከ11 ወር አገልግለው በልላ ምክንያት የስራ ውላቸው የተቋረጠ በመሆኑ እና የአገልግልት ዘመናቸው ከ20 ዓመት በታች መሆኑ ተረጋግጧል የሚለ ምክያቶችን በማስፈር ተጠሪ ሉኖራቸው የሚችለው መብት የጡረታ መዋጮ ተመላሽ ማግኘት እንጂ ዘላቂ የጡረታ መብት ተጠቃሚነት አይደለም በማለት ደምድሞ የአሁኑ አመልካች የሰጠውን ውሳኔ በማጽናት ወሰኗል። በዚህ ውሳኔ የአሁኑ ተጠሪ ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርበው ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ የአሁኑ ተጠሪ የዲኝነት ጥያቄ መስተናገድ የሚገባው በየትኛው ህግ ነው?
የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምሮ ጉዲዩ መሰተናገድ የሚገባው ጉዲዩ በቀረበበት ጊዜ በስራ ላይ ባለው ህግ በአዋጅ ቁጥር 714/2003 በአዋጅ ቁጥር 907/2007 እንደተሻሻለ ነው፣ ይህ አዋጅ ደግሞ ቢያንስ 10 ዓመት ያገለገለ የመንግስት ሰራተኛ ይህ ማሻሻያ ከፀናበት ቀን አንስቶ በራሱ ፈቃድ ወይም በዚህ አዋጅ ከተጠቀሱት ውጪ በሆነ መንገድ አገልግልት ያቋረጠ የጡረታ እድሜው ሲደርስ የአገልግልት የጡረታ አበል እስከ እድሜ ልኩ ይከፈለዋል በማለት ደንግጓል፣ የአሁኑ ተጠሪ በዳኞች ምርጫ አልታቀፈም ተብለው ከስራ የተሰናበቱት 17 ዓመት ከ11 ወር ካገለገለ በኋላ ቢሆንም ስራውን የለቀቁት አዋጅ ቁጥር 714/2003 (በአዋጅ ቁጥር 907/20007 እንደተሻሻለ) ስራ ላይ ከመዋለ በፉት ቢሆንም በዚህ ድንጋጌ መሰረት ተጠቃሚ ሉሆኑ የሚገባቸው ናቸው፣ የአሁኑ አመልካች መስሪያ ቤት ይህ አዋጅ ተፈፃሚ መሆን የሚገባው አዋጁ ከፀናበት ጊዜ ጀምሮ ከስራ በተሰናበቱ ሰራተኞች ላይ ነው ብል ያቀረበው ክርክርም የተጠሪ ጉዲይ የቀረበው ይህ አዋጅ ፀንቶ ባለበት ወቅት ስለሆነ ለጉዲዩ ተፈፃሚነት ያለው ነው የሚለ ምክንያቶችን አስፍሮ የማህበራዊ ዋስትና ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ በመ/ቁጡ/ይ/1/1/16/2008 ሐምል 29 ቀን 2008 ዓ.ም የሰጠውን ውሳኔ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው በማለት በአዋጅ ቁጥር 714/2003 አንቀጽ 56/4/ መሰረት መሻሩን ገልጾ የአሁኑ ተጠሪ ዘላቂ የጡረታ መብት ተጠቃሚ መሆን ይገባቸዋል ሲል ውሳኔ ሰጥቷል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች መስሪያ ቤት ነገረ ፈጅ ሐምል 03 ቀን 2010 ዓ/ም ፅፈው ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ በፋደራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል የሚለባቸውን ምክንያቶችን ዘርዝረው አቅርበዋል። የአቤቱታው መሰረታዊ ይዘትም፡- ለጉዲዩ ተፈፃሚነት ያለው የአዋጅ ቁጥር 714/2003 በአዋጅ ቁጥር 907/2007 እንደተሻሻለ በአንቀፅ 19(2) ድንጋጌ ቢያንስ 10 ዓመት ያገለገለ የመንግስት ሰራተኛ ይህ ማሻሻያ ከፀናበት ቀን አንስቶ በራሱ ፈቃድ ወይም በዚህ አዋጅ ከተጠቀሱት ውጪ በሆነ መንገድ አገልግልት ያቋረጠ የጡረታ እድሜው ሲደርስ የአገልግልት የጡረታ አበል እስከ እድሜ ልኩ ይከፈለዋል በማለት በግልጽ በደነገገበትና ተጠሪ ስራውን በለቀቁበት ጊዜ ስራ ላይ የነበረው 205/55 በአዋጅ ቁጥር 5/1967 እንደተሻሻለ በአንቀፅ 4(1) ስር የዘለቄታ ጡረታ መብት ተጠቃሚ ለመሆን የሚቻለው ቢያንስ አስር አመት ያገለገለና በስራ ላይ እያለ የመጦሪያ እድሜው በመድረሱ ከስራ ሲሰናበት ስለመሆኑ ደንግጎ እያለ ተጠሪ ከስራቸው የተሰናበቱት እድሜአቸው ለጡረታ ደርሶ ሳይሆን ስራ ላይ ባለመመደባቸው ምክንያት ስለመሆኑ በተረጋገጠበት ሁኔታ ለጉዲዩ አግባብነት ያላቸው የሕግ ማእቀፍች ከደነገጉት ውጪ ተጠሪ የዘላቂ ጡረታ መብት ተጠቃሚ እንዱሆኑ ተብል መወሰኑ ያላግባብ ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታቸው ተመርምሮም ተጠሪ የመንግስት ሰራተኛ ሆነው 17 አመት ከ11 ወር አገልግለው ሰኔ 01 ቀን 1988 ዓ/ም ከስራ የተሰናበቱ ሲሆን የተጠሪ የጡረታ መብት ጉዲይ የቀረበው አዋጅ ቁጥር 714/2003 በአዋጅ ቁጥር 907/2007 እንደተሻሻለ ፀንቶ ባለበት ወቅት ስለሆነ ተጠሪ የዘላቂ ጡረታ መብት ተጠቃሚ ሉሆኑ ይገባል ተብል የተወሰነበትን አግባብ ከአዋጅ ቁጥር 907/2007 አንቀፅ 5(2) ድንጋጌ ጋር አገናዝቦ ለመመርመር ተብል ነው። በዚህ መሰረት ተጠሪ ቀርበው ግራ ቀኙ በፅሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ፣ አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች እና በሰ/መ/ ከተሰጠው አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን ለዚህ ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር እንደሚከተለው ተመልክተናል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪ ከስራ በተሰናበቱበት ወቅት በስራ ላይ የነበረው አዋጅ ቁጥር 22/23/1955 መሰረት የዘላቂ ጡረታ መብት ተጠቃሚ መሆን የሚችለ መሆኑን ጠቅሰው የሚከራከሩ መሆኑን፣ አመልካች በበኩለ ተጠሪ ስራ በለቀቁበት ጊዜ ስራ ላይ የነበረው ተጠሪ የጠቀሱት ሳይሆን አዋጅ ቁጥር 209/55 በአዋጅ ቁጥር 5/67 እንደተሻሻለ ሆኖ በአዋጅ ቁጥር 5/67 አንቀጽ 4(1) ድንጋጌ ስር ደግሞ የጡረታ መብት ተጠቃሚ ለመሆን ቢያንስ 10 ዓመት ያገለገለና በስራ ላይ እያለ የመጦሪያ እድሜው በመድረሱ ከስራ የተሰናበት የመንግስት ሰራተኛ መሆኑን ጠቅሶ ተጠሪው ከስራ የተሰናበቱበት እድሜያቸው ለጡረታ ደርሶ ሳይሆን ስራ ላይ ባለመመደባቸው ምክንያት በመሆኑ በዚህ አዋጅ መሰረት ጥያቄአቸው የሚስተናገድበት አግባብ የላለ መሆኑን፣ ጉዲዩ መታየት የሚገባው ተጠሪ ስራ በለቀቁበት ጊዜ በስራ ላይ በነበረው አዋጅ ቁጥር 209/55 በአዋጅ ቁጥር 5/67 እንደተሻሻለ አንቀጽ 9(2) ድንጋጌ መሰረት ሆኖ በዚህ ድንጋጌ መሰረትም ተጠሪ አገልግልታቸው ከ20 ዓመት በታች በመሆኑ መብታቸው የጡረታ መዋጮ ተመላሽ ብቻ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 714/2003 በአዋጅ ቁጥር 907/2007 እንደተሻሻለ አንቀጽ 19 (2) ቢያንስ 10 ዓመት ያገለገለ የመንግስት ሰራተኛ ይህ ማሻሻያ አዋጅ ከፀናበት ጊዜ ጀምሮ በራሱ ፈቃድ ወይም በዚህ አዋጅ ከተጠቀሱት ምክንያቶች ውጪ በሆነ ምክንያት አገልግልት ካቋረጠ የጡረታ እድሜው ሲደርስ የአገልግልት ጡረታ አበል እስከ እድሜ ልኩ ይከፈለዋል ተብል የተደነገገ ቢሆንም በዚሁ አዋጅ ማሻሻያ መሰረት እድሜው ሲደርስ የዘለቄታ የጡረታ አበል ተጠቃሚ ለመሆን የሚቻለው ከ10 ዓመት አገልግልት በኋላ ሰራተኛው ስራውን ያቋረጠው ማሻሻያ አዋጅ ከፀናበት ከሐምል 03 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ ነው፣ ተጠሪ ግን አገልግልታቸውን ያቋረጡት በ1988 ዓ.ም በመሆኑ በዚህ አዋጅ መሰረት ተጠቃሚ ሉሆኑ አይችለም በማለት የሚከራከር መሆኑን ነው። እንዱሁም ለጉዲዩ ተፈፃሚነት ሉኖረው ስለሚገባው ህግ ግራ ቀኙ ክርክር አቅርበው የፋደራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በዚህ ረገድ ጭብጥ ይዞ የተጠሪ ጉዲይ መሰተናገድ የሚገባው ጉዲዩ በቀረበበት ጊዜ በስራ ላይ በነበረው ህግ መሰረት ነው፣ ምክንያቱም በወቅቱ ስራ ላይ ያለው ህግ እያለ ስራ ላይ ያልነበረ ህግ ወደ ኋላ በመሄድ ተግባራዊ የሚደረግበት አግባብ ባለመኖሩ ነው፣ ጉዲዩ (ክርክሩ) የቀረበው ደግሞ በ2008 ዓ.ም ነው፣ በዚህ ጊዜ በስራ ላይ ያለው ህግ ደግሞ አዋጅ ቁጥር 714/2003 በአዋጅ ቁጥር 907/2007 እንደተሻሻለ ነው ወደሚል ድምዲሜ የደረሰ መሆኑንና ተጠሪ በበኩላቸው አመልካች መስሪያ ቤት ለዚህ ሰበር ሰሚ ችልት የአዋጅ ቁጥር 209/55 (በአዋጅ ቁጥር 5/67 እንደተሻሻለ) ድንጋጌዎችን መሰረት አድርጎ ቅሬታ ማቅረቡ አመልካቹ መስሪያ ቤት ራሱ ቀድሞውኑ የአዋጅ ቁጥር 714/2003 ዓ/ም አንቀፅ 19 (2) ድንጋጌን መሰረት በማድረግ ጉዲዩን አይቶ ሰኔ 25 ቀን 2008 ዓ/ም አስተዲደራዊ ውሳኔ የሰጠ በመሆኑ ተቀባይነት ስለላለው ጉዲዩ ስራ ላይ ባለው ሕግ መታየቱ የሚነቀፍበት አግባብ የለም በማለት የሚከራከሩ መሆኑንም ተገንዝበናል።
ከዚህ አንጻር ለጉዲዩ ቀጥተኛ ተፈጻሚነት ያለው ህግ ክርክሩ በሚታይበት ጊዜ በስራ ላይ ያለው አዋጅ ቁጥር 714/2003 በአዋጅ ቁጥር 907/2007 እንደተሻሻለ መሆኑን ተገንዝበናል።ይህንኑ መሰረት በማድረግ የተጠሪን የዘላቂ ጡረታ አበል ተጠቃሚነት ጥያቄ የሕግ መሰረት ያለው መሆን ያለመሆኑን እንደሚከተለው ተመልክተናል።
በመሰረቱ የአዋጅ ቁጥር 714/2003 አንቀፅ 19 (2) ድንጋጌ ሙለ ይዘት ሲታይ ቢያንስ አስር አመት ያገለገለ የመንግስት ሰራተኛ በራሱ ፈቃድ ወይም በዚሁ አዋጅ ከተጠቀሱት ውጭ በሆነ ምክንያት አገልግልት ካቋረጠ የጡረታ መውጫ እድሜው ሲደርስ የአገልግልት ጡረታ አበል አስከ እድሜ ልኩ ይከፈለዋል የሚል መሆኑን የሚያስገነዝብ ሲሆን በዚሁ ድንጋጌ መሰረት የዘለቄታ ጡረታ አበል ለማግኘት ቢያንስ አስር ዓመት ማገልገል እና በአዋጁ አንቀጽ 18/1/ መሰረት የጡረታ እድሜ መድረስ ቅድመ ሁኔታዎቸ መሆናቸውን የድንጋጌዎቹ ይዘትና መንፈስ የሚያስገነዝቡን ጉዲይ ነው።
ይሁን እንጂ ይህ የአዋጁ ድንጋጌ የአዋጁ ማሻሻያ በሆነው አዋጅ ቁጥር 907/2007 አንቀፅ 5 (2) የተተካ ሲሆን የዚህ ድንጋጌ ሙለ ይዘት ሲታይ ደግሞ ቢያንስ አስር አመት ያገለገለ የመንግስት ስራተኛ ይህ ማሻሻያ አዋጅ ከፀናበት ቀን አንስቶ በራሱ ፈቃድ ወይም በዚሀ አዋጅ ከተጠቀሱት ውጪ በሆነ ምክንያት አገልግልት ካቋረጠ በዚህ አዋጅ በአንቀፅ 18 ንዐስ አንቀፅ አንድ በተደነገገው መሰረት የጡረታ መውጫ እድሜው ሲደርስ የአገልግልት ጡረታ አበል እስከ ዕድሜ ልኩ ይከፈለዋል የሚል መሆኑን ያስገነዝባል። ይህ ማሻሻያ ድንጋጌ በአዋጅ ቁጥር 714/2003 አንቀፅ 19 (2) ስር ተጠቀሰው ከነበሩት መስፈርቶች የጨመረው የሥራ ውለ የሚቋረጥበት ጊዜ አዋጁ ከፀናበት ጊዜ አንስቶ የሚለውን ሐረግ መሆኑን ከድንጋጌው ይዘት መረዲት የምንችለው ጉዲይ ነው። በመሆኑም የሥራ ውለ የሚቋረጠው አዋጁ ከጸደቀበት ጊዜ ከሆነና ላልች በሕጉ የተመለከቱ ቅድመ ሁኔታዎች አንድ ላይ ተሟልተው ከተገኙ ቢያንስ አስር አመት ያገለገለ የመንግስት ሰራተኛ የመብቱ ተጠቃሚ እንደሚሆን ሕጉ የደነገገው ጉዲይ ነው። በአዋጅ ቁጥር 714/2003 አንቀፅ 60 (2) ድንጋጌ መሰረት በተሰጠው ስልጣን መሰረት የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጄንሲ የመንግስት ሰራተኞች ጡረታ አዋጅ ማስፈፀሚያ መመሪያ ቁጥር 1/2008 ያወጣ ሲሆን በዚህ መመሪያ አንቀፅ 4 ስር በራሱ ፈቃድ ወይም በልላ ምክንያት ከስራ ማቋረጥ ምክንያት ለሚቀርብ የጡረታ አበል ጥያቄ የሚል አርዕስት ተሰጥቶ በአንቀፁ ፉደል (ሐ) ስር ደግሞ በአዋጅ ቁጥር 714/2003 (በአዋጅ ቁጥር 907/2007 እንደተሻሻለ) አንቀፅ 19 ንዐስ ቁጥር ሁለት መሰረት ማሻሻያ አዋጁ ለፀደቀበት ጊዜ ጀምሮ አገልግልቱ ከ10 አመት ያላነሰ 25 አመት ያልሞላ ከሆነ እድሜው በሕግ የተወሰነ የጡረታ መውጫ እድሜ ከደረሰበት ከሚቀጥለው ወር አንስቶ የአገልግልት የጡረታ አበል እስከ እድሜ ልኩ እንደሚከፈለው መደንገጉ ሲታይም ከአስር አመት ያላነሰ 25 አመት ያልሞላው የመንግስት ሰራተኛ የዘላቂ ጡረታ አበል ተጠቃሚ የሚሆነው እድሜው የጡረታ መውጫ እድሜ የደረሰ ሆኖ በተጨማሪም ስራውን የለለቀው አዋጁ ከፀደቀበት ከሐምል 01 ቀን 2007 ጀምሮ መሆኑ ሲረጋገጥ ብቻ መሆኑን ግልፅ ያደረገው መሆኑን የሚያስገነዝብ ነው። ስለሆነም የአዋጅ ቁጥር 714/2003 አንቀጽ 19(2) ማሻሻያ የሆነው የአዋጅ ቁጥር 907/2007 አንቀፅ 5(2) ድንጋጌ የዘለቄታ ጡረታ አበል ለማግኘት ቢያንስ አስር ዓመት ማገልገል እና በአዋጁ አንቀጽ 18/1/ መሰረት የጡረታ እድሜ መድረስ ቅድመ ሁኔታዎቹ ከመሆናቸውም በላይ የሥራ ውለ መቋረጥ ያለበት ግን የአዋጅ ቁጥር 714/2003 ማሻሻያ የሆነው አዋጅ ቁጥር 907/2007 ከፀናበት ከሐምል 01 ቀን 2007 ዓ/ም ጀምሮ መሆን ያለበት መሆኑን ሕጉ አሰገዲጅነት ባለው ሁኔታ የደነገገ መሆኑን በግልፅ የሚያሳይ እና የመንግስት ሰራተኞችን በሚመለከት በወጣው አዋጅ ስር ያለትን ድንጋጌዎችን ለማስፈፀም የሚያስችል መመሪያ እንዱያወጣ በሕግ አውጪው የውክልና ስልጣን የተሰጠው አካል ያወጣው የመንግስት ሰራተኞች ጡረታ አዋጅ ማስፈፀሚያ መመሪያ ቁጥር 1/2008 አንቀፅ 4 (ሐ) ድንጋጌም ይህንኑ የሚያጠናክር ሆኖ አግኝተናል።
ስለሆነም የአሁኑ ተጠሪ በዳኞች ምርጫ አልታቀፈም ተብለው ከስራ የተሰናበቱት 17 ዓመት ከ11 ወር ካገለገለ በኋላ በ1988 ዓ/ም በመሆኑና በዚህ ጊዜ ደግሞ እድሜአቸው ለጡረታ ያልደረሰ የነበረ በመሆኑ፣ እንዱሁም አዋጅ ቁጥር 714/2003 (በአዋጅ ቁጥር 907/2007 እንደተሻሻለ) ተፈፃሚ መሆን የሚገባው አዋጁ ከፀናበት ጊዜ ጀምሮ ከስራ በተሰናበቱ ሰራተኞች ላይ በመሆኑ በተጠሪ ጉዲይ አዋጁ ተፈፃሚ ላሆን የሚችልበት የሕግ አግባብ የለም። ይህ ችልት በሰ/መ/ ሀምላ 28 ቀን 2010 ዓ/ም በዋለው ችልት አዋጅ ቁጥር 907/2007 ከመፅናቱ በፉት በመንግስት መስሪያ ቤት ከአስር አመት በላይ አገልግልት በመስጠት ስራውን በራሱ ፈቃድ ወይም በልላ ምክንያት ለለቀቀ ሰራተኛ እድሜው ስልሳ አመት የሞላው እስከሆነ ድረስ የዘላቂ ጡረታ ተጠቃሚነት መብት አለው በማለት ለአዋጁ ማሻሻያ አንቀጽ 5 (2) የሰጠው አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ከላይ በተመለከቱት ሕጋዊ ምክንያቶች የሕጉን ይዘትና መንፈስ ያልተከተለና ስህተት ሆኖ ስላገኘው ይህ ችልቱ ራሱ የሰጠውን አስገዲጅ የሕግ ትርጉም በልላ ጊዜ መቀየር የሚችል መሆኑን የአዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀፅ 2(1) ድንጋጌ ያስቀመጠ በመሆኑ በሰ/መ/ በዚህ ረገድ የተሰጠው የሕግ ትርጉም ሉለወጥ የሚገባው ሆኖ አግኝተናል።ስለሆነም የአዋጅ ቁጥር 714/2003 ማሻሻያ የሆነው አዋጅ ቁጥር 907/2007 ከመፅናቱ በፉት በመንግስት መስሪያ ቤት ከአስር አመት በላይ አገልግልት በመስጠት ስራውን በራሱ ፈቃድ ወይም በልላ ምክንያት ለለቀቀ ሰራተኛ እድሜው ስልሳ አመት የሞላው እስከሆነ ድረስ የዘላቂ ጡረታ ተጠቃሚነት መብት በአዋጁ አንቀፅ 5(2) ድንጋጌ የተጠበቀ አይደለም።
ሲጠቃለልም ከላይ በተጠቀሱት ዝርዝር ሕጋዊ ምክንያቶች ተከታዩን ወስነናል።
በተሻሻለው የመንግስት ሰራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር 907/2007 አንቀጽ 5(2) የዘለቄታ ጡረታ አበል ለማግኘት መሰረቱ ቢያንስ አስር አመት ማገልገል እና በአዋጅ ቁጥር 714/2003 አንቀጽ 18 መሰረት የጡረታ እድሜ መድረስ በመሆኑ ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ ቢያንስ አስር አመት ያገለገለ እና በራሱ ፈቃድ ወይም በአዋጁ ከተጠቀሱት ውጪ በሆነ ምክንያት አገልግልት ካቋረጠ የጡረታ መውጫ እድሜው ሲደርስ የአገልግልት ጡረታ አበል ለዘለቄታው የማግኘት መብት አለው ተብል በሰ/መ/ በ28/11/2009 ዓ/ም ተሰጥቶ የነበረው አስገዲጅ የሕግ ትርጉም በአዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀጽ 2 (1) መሰረት ተለውጧል።
በፋደራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ በ22/09/2010 ዓ/ም የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የማህበራዊ ዋስትና ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ በመ/ቁጡ/ይ/1/1/16/2008 ሐምል 29 ቀን 2008 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348 (1) መሰረት ፀንቷል።
በተሻሻለው የመንግስት ሰራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር 907/2007 አንቀጽ 5 (2) ድንጋጌ መሰረት የዘለቄታ ጡረታ አበል ለማግኘት ቢያንስ አስር አመት ማገልገል እና በአዋጅ ቁጥር 714/2003 አንቀጽ 18 መሰረት የጡረታ እድሜ መድረስ ብቻ ሳይሆን ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ ቢያንስ አስር አመት ያገለገለ እና በራሱ ፈቃድ ወይም በአዋጁ ከተጠቀሱት ውጪ በሆነ ምክንያት አገልግልቱን ያቋረጠው አዋጁ ከፀናበት ከሐምል 01 ቀን 2007 ዓ/ም ጀምሮ ላሆን ይገባል ብለናል።
በአዋጅ ቁጥር 714/2003 (በአዋጅ ቁጥር 907/2007 እንደተሻሻለ) አንቀፅ 19 (2) መሰረት ተጠሪ ዘላቂ የጡረታ መብት ተጠቃሚ መሆን አይችለም ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገ ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
ሳ/ፀ
No topics extracted.