የግልግል ዲኝነት ስምምነት ላይ የሕጋዊነት ጉድለት በመኖሩ ምክንያት ለመፈጸም እምቢተኛ መሆንን በሚመለከት የሚቀርብ ክርክር የግልግል ሥምምነቱ በፍርድ ቤት ክስ ቀርቦበት እንዱፈርስ መወሰኑን ሳይጠብቅ የግልግል ጉባዔው ጉዲዩን ተመልክቶ ሉወስን የሚችል ቢሆንም የግልግል ዲኝነት ስምምነቱ ዋጋ ስለማጣቱ እንዱሁም የግልግል ጉባኤው ጉዲዩን ለመመልከት ስልጣን የለውም በሚል የሚቀርብ ክርክርን ሰምቶ የመወሰን ስልጣን የመደበኛ ፍርድ ቤት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ.1809፣3330
No summary available.
ሚያዚያ 26 ቀን 2012 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግሥቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- አቶ ያሬድ ተስፊይ /ያሬድ ተስፊይ ኤላክትሮ መካኒካል ኢንጂነሪንግ/ ተጠሪ፡- ዓዱግራት ዩንቨርስቲ መዝገቡ ተምርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጠ።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው። የክርክሩን አመጣጥ ከመዝገብ ግልባጩ እንደተረዲነው ጉዲዩ በግልግል ጉባዔ የታየ ሲሆን አመልካች በሥር የግልግል ጉባዔ ከሳሽ ሲሆኑ ተጠሪ ተከሳሽ ነበር። አመልካች ያቀረቡት ክስ ከተጠሪ ጋር ሕዲር 30 ቀን 2009 ዓ/ም የማሕበረሰብ ኤፍ ኤም ሬዱዮ ተከላ ለመፈጸም ውል አድርገናል። በውላቸው አለመግባባት ካለ ጉዲዩን ለመፍታት በግልግል ጉባዔ እንዱታይ ተስማምተዋል። በዚህ ሥምምነት መሰረት ግራ ቀኙ ተዋዋዮች የግልግል ዳኞችን መሰየም ባለመቻላቸው አመልካች የግልግል ዳኞች ይሾሙልኝ ጥያቄ ለትግራይ ክልል ምሥራቃዊ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው በመዝገብ ጥቅምት 22 ቀን 2010 ዓ/ም በሰጠው ውሳኔ ሦስት የግልግል ዳኞችን ፍርድ ቤቱ ሾሟል። አመልካች ለተሰየመው የግልግል ጉባዔ በውለ መሰረት እንዱፈጸም እና ለደረሰባቸው ኪሣራ እንዱከፈላቸው ክስ አቅርበዋል። ተጠሪ በበኩለ የግልግል ዳኞች ምርጫና መቋቋም መብቴ ስላልተከበረልኝ የግልግል ጉባዔ ሉፈርስ ይገባል ሲል ተቃውሞ ያቀረበ ሲሆን ለክሱም ዝርዝር መልስ አቅርቦ ተከራክሯል። የግልግል ጉባዔው ተጠሪ ያቀረበውን መቃወሚያ መርምሮ የግልግል ጉባዔው የተቋቋመው በፍርድ ቤት ውሳኔ ስለሆነ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 212 እንደተመለከተው በይግባኝ እስካልተለወጠ ድረስ የጸና በመሆኑ ክርክሩ ተቀባይነት የለውም። በፍሬ ጉዲዩም ሕዲር 30 ቀን 2009 ዓ/ም በተደረገው ውል መሰረት ተጠሪ እንዱፈጽምና አመልካች ላይ የደረሰውን ኪሣራ እንዱከፍል ወስኗል።
የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ተጠሪ ያቀረበውን ይግባኝ መሰረት አድርጎ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ አመልካችና ተጠሪ ያደረጉት የማሕበረሰብ ኤፍ ኤም ሬዱዮ ተቋም ተከላ ውል ለሕዝብ ጥቅም የተደረገና ለውለ አፈጻጸም የተጠሪን የማያቋርጥ ተካፊይነት የሚጠይቅ በመሆኑ በፍ/ሕ/ቁ.3132(ለ) መሰረት የአስተዲደር ውል ነው። በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 315(2) ላይ እንደተመለከተው የአስተዲደር መሥሪያ ቤት ውልችን በግልግል ዲኝነት እንዱታዩ ሕጉ በግልጽ ክልከላ አድርጓል። ፍርድ ቤት ሕግን በመጣስ ግልግል ጉባዔ ማቋቋም አይችልም። እንዱሁም የሥረ-ነገር ሥልጣን በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 9(2) እንደተደነገገው በማናቸውም ጊዜ የሚነሳ በመሆኑ ጉባዔውን ያቋቋመው ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሳይሻር የጉባዔውን ሥልጣን መቃወም አይቻልም የሚለውን የአመልካችን ክርክርን አልተቀበልነውም በማለት የትግራይ ክልል ምሥራቃዊ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ጥቅምት 22 ቀን 2010 ዓ/ም እና የግልግል ጉባዔው ጥቅምት 03 ቀን 2011 ዓ/ም የሰጡት ውሳኔን በመሻር ጉዲዩን የማየት ሥልጣን የመደበኛ ፍርድ ቤት ነው በማለት ወስኗል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘትም የግልግል ጉባዔው በፍርድ ቤት ውሳኔ የተቋቋመ ነው። ውሳኔው እስካልተሻረ ድረስ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 212 እንደተደነገገው የጸና ነው። ውላችንም አለመግባባት በግልግል እንዱፈታ ይፈቅዲል። ሥለሆነም ጉባዔው በሕግ የተቋቋመና ሥልጣን ያለው ሆኖ እያለ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው የሚል ነው። የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩን ተመልክቶ ውላቸው ጉዲዩን በግልግል ጉባዔ እንዱታይ የሚፈቅድ ሆኖ እያለ እና የግልግል ዳኞች ሲመረጡ ተጠሪ ባልተቃወመበት ክርክሩ በግልግል ጉባዔ የሚታይ አይደለም መባለ ሕጋዊነቱን ለማጣራት ተጠሪ መልስ እንዱያቀርብ አዟል። ተጠሪ ያቀረበው መልስ የግልግል ዳኞች ምርጫ በፍርድ ቤት በተከናወነበት ወቅት ጊዜ እንዱሰጠን ጠይቀን እያለ ሳይቀበለን ቀርቷል። በፍ/ሕ/ቁ. 3132 እና በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 315(2) መሰረት የአስተዲደር ውል በግልግል ጉባዔ የሚታይ አይደለም። ጉባዔው ሥልጣን እንደላለው መቃወሚያ አቅርበናል። የሥልጣን ክርክርም በማናቸውም ጊዜ ሉነሳ የሚችል በመሆኑ ውሳኔው ሉጸና ይገባል ብሎል።
የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም ጉዲዩ በግልግል ጉባዔ የሚታይ አይደለም መባለ ሕጋዊ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ መዝገቡን መርምረናል።
የመጀመሪያውን ጭብጥ እንደመረመርነው ሰዎች በመካከላቸዉ ከፈጠሩት ሕጋዊ ተግባራት በመነጨ ወይም ከዚህ ጋር በተያያዘ ለወደፉት በመካከላቸዉ የሚፈጠረዉን አለመግባባት ወይም ተፈጥሮ ያለዉን አለመግባባት ከመደበኛ ፍርድ ቤት ዉጭ በግልግል ዲኝነት በኩል ለመፍታት የመዋዋል ነጻነታቸዉን በመጠቀም መስማማት እንደሚችለ የፍ/ሕ/ቁ. 3328 እና የፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 315(1) ያስረዲለ።
የግልግል ዲኝነት ሥምምነት በጽሁፍ በተዋዋለት በዋናዉ ዉላቸዉ በሚያደርጉት የግልግል ዲኝነት ስምምነት ቃል (Arbitration Clause) ወይም አስቀድሞ በመካከላቸዉ ተከስቶ ያለዉን አለመግባባት በግልግል ዲኝነት ለመፍታት ራሱን በቻለ የጽሁፍ የግልግል ዲኝነት ስምምነት (Arbitral Submission) ሉመለከት ይቻላል።
አመልካች እና ተጠሪም ሕዲር 30 ቀን 2009 ዓ/ም ባደረጉት የማሕበረሰብ ኤፍ ኤም ሬዱዮ ተከላ ውል አለመግባባት ቢከሰት በግልግል ዲኝነት እንዱታይ የሚያዝ የሥምምነት ቃል (Arbitration Clause) ማድረጋቸውን ከክርክሩ ተረድተናል። በዚህ ሥምምነታቸው መሰረት አለመግባባት በመከሰቱ እና ተዋዋዮች የግልግል ዳኞችን መምረጥ ባለመቻላቸው አመልካች በፍርድ ቤት የግልግል ዳኞች እንዱመረጡ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 316 መሰረት አቤቱታ አቅርበው የትግራይ ክልል ምሥራቃዊ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ጥቅምት 22 ቀን 2010 ዓ/ም በሰጠው ውሳኔ ሦስት የግልግል ዳኞችን ሾሟል። የግልግል ጉባዔው ከተቋቋመ በኋላ ግራ ቀኙን አከራክሮ በፍሬ ጉዲዩ ውሳኔ ሰጥቷል።
አለመግባባት ቢከሰት በግልግል ዲኝነት እንዱታይ የሚያዝ የሥምምነት ቃል (Arbitration Clause) መደረጉና የግልግል ጉባዔው አከራክሮ መወሰኑ ጉዲዩ የአስተዲደር ውል በመሆኑ እና የአስተዲደር ውል ጋር የተያያዘ አለመግባባት በግልግል ዲኝነት እንዲይታይ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 315(2) መሰረት የተከለከለ በመሆኑ ጉባዔው ሥልጣን የለውም የሚለው ግልጽ ክርክር የቀረበው ጉዲዩ በይግባኝ በፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ደረጃ በሚታይበት ጊዜ ነው። ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱም አመልካችና ተጠሪ ያደረጉት የማሕበረሰብ ኤፍ ኤም ሬዱዮ ተቋም ተከላ ውል ለሕዝብ ጥቅም የተደረገና ለውለ አፈጻጸም የተጠሪን የማያቋርጥ ተካፊይነት የሚጠይቅ በመሆኑ በፍ/ሕ/ቁ. 3132(ለ) መሰረት የአስተዲደር ውል ነው።
በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 315(2) ላይ እንደተመለከተው የአስተዲደር መሥሪያ ቤት ውልችን በግልግል ዲኝነት እንዱታዩ ሕጉ በግልጽ ክልከላ የተደረገበት በመሆኑ የግልግል ጉባዔውን ጉዲዩን አይቶ የመወሰን ሥልጣን የለውም በማለት ወስኗል።
ውል ሉመሰረት የሚገባው ችልታ ባላቸው፣ በተዋዋዮች ነጻ ፈቃድ፣ የሚቻልና ሕጋዊ በሆነ ዓላማና ጉዲይ ላይ በሕግ የተመለከተውን የውል አጻጻፍ ፍርም ተከትል ላሆን እንደሚገባ በፍ/ሕ/ቁ. 1678 ላይ ተመልክቷል። የግልግል ስምምነት እንደማንኛዉም የዉል ስምምነት ልዩ ባህሪዉን ባገናዘበ ሁኔታ የተዋዋዮች የመዋዋል ችልታ ማጣት፣ የፈቃድ ጉድለት፣ ዓላማዉ የግብረ ገብነት ጉድለት ያለበት መሆን፣ ዓላማዉ ከሕግ ዉጭ ወይም ሕገ-ወጥ መሆንን (immoral, illegal and unlawful object) ፣ በህግ የተቀመጠለትን የአጻጻፍ ስርዓት ያልተከተለ ከመሆን ጋር በሚያያዙ ምክንያቶች ፈራሽ ላሆን ይችላል።
በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 3330(1)(2) ስር ከግልግል ዲኝነት ስምምነት አተረጓጎም ጋር የተያያዘ ክርክር ቢነሳ አከራካሪዉ ነጥብ ላይ ዉሳኔ መስጠት እንዱችል በግልግል ስምምነቱ ላይ ለግልግል ዲኛዉ ስልጣን ሉሰጠዉ እንደሚችል እና በተለይ የራሱን ሥልጣን አስመልክቶ የሚነሱ ክርክሮች በራሱ እንዱወስን በግልግል ስምምነቱ ላይ ሉፈቀድለት እንደሚችል ተደንግጓል። ይህም በተምሳላታዊ ሕግ (UNCITRAL Model Law እ.ኤ.አ በ1985 ወጥቶ በ2006 እንደተሻሻለዉ) አንቀጽ 16 ስር ከተደነገገዉና በዘመናዊዉ የግልግል ዲኝነት የህግ ዘርፍ The Rule of Competence-Competence ተብል ከሚታወቀዉ መርህ ጋር ከሞላ ጎደል የሚመሳሰል ነዉ። ይህ መርህ የግልግል ዲኛዉ የግልግል ዲኝነት ስምምነቱ ዋጋ ያለዉ መሆን አለመሆኑን በተመለከተ የሚነሳ ክርክር ጭምር ሰምቶ መወሰን እንዱችል ስልጣን የሚሰጠዉ ቢሆንም ይህ መርህ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 3330(3) ስር እንደተመለከተዉ በአገራችን በከፉል ተቀባይነት ባለማግኘቱ በዚህ ድንጋጌ መሰረት በአገራችን የግልግል ዲኛ የግልግል ዲኝነት ስምምነቱ ዋጋ የለዉም በሚል የሚነሳ ክርክር ሰምቶ በራሱ መወሰን እንዱችል ሥልጣን አልተሰጠዉም። ስለሆነም በአገራችን የግልግል ዲኝነት ስምምነት ዋጋ የለዉም በሚል የሚቀርብ ክርክር ሰምቶ የመወሰን ስልጣን ያለዉ ገላጋይ ዲኛዉ ወይም የግልግል ዲኝነት አካለ ሳይሆን መደበኛ ፍርድ ቤት ነዉ።
የግልግል ስምምነቱ ፈራሽ ላሆን ይገባል የሚለት የተዋዋዮች የመዋዋል ችልታ ማጣት ወይም የፈቃድ ጉድለት መሰረት በማድረግ ከሆነ የግልግል ጉባዔው ክርክሩን በማቆም ተዋዋዮች መብታቸውን በመደበኛ ፍርድ ቤት አስከብረው እንዱቀርቡ ማድረግ ይገባዋል። በልላ በኩል የግልግል ስምምነቱ ተቀባይነት የለውም የሚለት በሕጋዊነት ጉድለት ከሆነ እና ተጠሪ እንደሚከራከረው የግልግል ጉባዔውም ጉዲዩን ለመመልከት ሥልጣን የለውም የሚል ከሆነ በፍ/ሕ/ቁ. 1809 እንደተመለከተው ውለ ባይፈርስም ሕገ-ወጥ የሆነን ውል የመፈጸም ግዳታ ተዋዋዮች የላለባቸው ስለመሆኑና ውለ የማይረጋበትን ምክንያት በማንሳት ውለ ከመፈጸም እንዱቆም መከራከርን ሕጉ የሚፈቅድ ስለሆነ እንዱሁም ጉዲዩ በግልግል ጉባዔ እንዲይታይ ሕግ ክልከላ ያደረገበት ነው የሚለው የሥረ-ነገር ሥልጣን ክርክርንም የያዘ በመሆኑ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 9(2) እንደተመለከተው በማናቸውም ጊዜ ላታይ የሚችል ጉዲይ በመሆኑ የግልግል ጉባዔው የግልግል ሥምምነቱ በፍርድ ቤት ክስ ቀርቦበት እንዱፈርስ መወሰኑን ሳይጠብቅ ጉዲዩን ተመልክቶ ሉወስነው የሚገባው ነው። የውሳኔው ውጤትም የግልግል ሥምምነቱን ፈራሽ የሚያደርግ ሳይሆን ሕገ-ወጥ ውልን መሰረት በማድረግ ለመፈጸም እምቢተኛ መሆንን የሚመለከት ነው።
በግልግል ዲኝነት ሉታዩ የሚችለ ጉዲዮችን (Arbitrability) በሚመለከት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 315(2) ስር እንደተደነገገዉ በግልግል ዲኝነት ሉዲኙ የማይችለ ጉዲዮች ናቸዉ ተብል በሕግ በግልጽ ከተደነገገዉ እና ከአስተዲደር ዉልች ጋር ከተያያዘዉ ዉጭ የሆኑ ሕጋዊ ተግባራትን መነሻ ያደረጉ አለመግባባቶች በግልግል ዲኝነት ታይተዉ እልባት እንዱያገኙ ለማድረግ ማናቸዉም ችልታ ያላቸዉ ተዋዋይ ወገኖች የመዋዋል ነጻነታቸዉን በመጠቀም የግልግል ዲኝነት ስምምነት መዋዋል እንደሚችለ በግልጽ ተደንግጓል። አመልካችና ተጠሪ ያደረጉት የማሕበረሰብ ኤፍ ኤም ሬዱዮ ተቋም ተከላ ውል ለሕዝብ ጥቅም የተደረገና ለውለ አፈጻጸም የተጠሪን የማያቋርጥ ተካፊይነት የሚጠይቅ በመሆኑ በፍ/ሕ/ቁ.
3132(ለ) መሰረት የአስተዲደር ውል ነው። የአስተዲደር ውል ጋር የተያያዘ አለመግባባትን ለመዲኘት የግልግል ጉባዔ የማይችል ስለመሆኑ በሕግ ክልከላ የተደረገበት በመሆኑ ግራ ቀኙ ያደረጉት የግልግል ሥምምነት ቃል ሕጋዊ አለመሆኑን መገንዘብ ይቻላል። የአስተዲደር ውልን መሰረት ያደረገ አለመግባባት በግልግል ዲኝነት ለመፍታት ያደረጉት የግልግል ሥምምነት ቃለ ሕጋዊ ካልሆነ የግልግል ጉባዔው ጉዲዩን ለመዲኘት እንዲይችል ያደርገዋል። የሥር ግልግል ጉባዔ በሕግ እንዱመለከት ያልተፈቀደለትን ጉዲይ አከራክሮ በፍሬ ጉዲዩ መወሰኑ ተገቢ አይደለም። ይግባኝ ሰሚ ችልቱ ይህን በማረም ከአስተዲደር ውል ጋር የተያያዘ አለመግባባት በግልግል ዲኝነት የሚታይ ባለመሆኑ ጉዲዩን ለመመልከት ሥልጣን ያለው መደበኛ ፍርድ ቤት ነው ማለቱ ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለም ብለናል።
አመልካች የግልግል ጉባዔው የተቋቋመው በትግራይ ክልል ምሥራቃዊ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ስለሆነ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ በይግባኝ ሳይለወጥ ጉባዔው ጉዲዩን የማየት ሥልጣን የለውም ልባል አይገባም በማለት ያቀረቡትን ክርክር እንደተመለከትነው የግልግል ዳኞች በተዋዋዮች ወይም በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 316 መሰረት በፍርድ ቤት ሉሾሙ ይችላል። የግልግል ዲኞቹ በተዋዋዮች ሆነ በፍርድ ቤት መመረጣቸው ልዩነት ያለው ሂደት አይደለም። የግልግል ዳኞች መምረጥ ጉዲዩን በግልግል ዲኝነት ጉባዔ እንዱታይ የማመቻቸት ሂደት አካል እንጂ በራሱ የመጨረሻ ውሳኔ አይደለም። የግልግል ዳኞች አመራረጥ ጉዲዩን የግልግል ጉባዔው ለመመልከት የሚችል መሆን አለመሆኑ ላይ ውጤት የለውም። የግልግል ዲኞቹ ከሁለቱ ሂደት በአንደ ከተመረጡ በኋላ የግልግል ጉባዔው ሲሰየም ጉዲዩ በግልግል ዲኝነት እንዱታይ በሕግ የተፈቀደ መሆን አለመሆኑን የግልግል ጉባዔው ሆነ ፍርድ ቤቱ እንዲይመለከት የሚከለክል ባለመሆኑ አመልካች በዚህ ረገድ ያቀረቡትን ክርክር አልተቀበልነውም። በልላ በኩል የትግራይ ክልል ምሥራቃዊ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ጥቅምት 22 ቀን 2010 ዓ/ም የሰጠው የግልግል ዳኞችን የመምረጥ ትዕዛዝ፤ በፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት መሻሩ የሥነ-ሥርዓት ሕግ ግድፈት ያለበት ነው። ለይግባኝ ሰሚ ችልቱ በዳኞች አመራረጥ ላይ በተሰጠው ውሳኔ ላይ ሥርዓቱን የጠበቀ ይግባኝ ሳይቀርብለት እና በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 212 እንደተመለከተው ሥርዓቱን ጠብቆ በይግባኝ ያልተለወጠ ውሳኔ እንደጸና የሚቆጠር ከመሆኑም በላይ የዳኞች አመራረጥ ጉዲዩ በግልግል ጉባዔ የሚታይ መሆን አለመሆኑ ላይ ውጤት የላለው ስለሆነ ፍርድ ቤቱ ዳኞችን ለመምረጥ የሰጠውን ትዕዛዝን መሻሩ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ ሚያዚያ 21 ቀን 2011 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ተሻሽሎል።
ጉዲዩን የመመልከት ሥልጣን የመደበኛ ፍርድ ቤት ነው ተብል የተሰጠው የውሳኔ ክፍል ጸንቷል።
የትግራይ ክልል ምሥራቃዊ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ጥቅምት 22 ቀን 2010 ዓ/ም የሰጠውን ትዕዛዝ በመሻር የሰጠው የውሳኔ ክፍል ተሽሯል።
በዚህ ችልት ለወጣ ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ።
መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.