የፍደራል ፍርድ ቤት ዳኞች በጡረታ ከተሰናበቱ በኋላ መብትና ጥቅማቸውን ለመወሰን በክልል ፍርድ ቤቶች በዲኝነት ስለተሰጠ የአገልግልት ዘመን በፋደራል መንግስት ታሳቢ የሚደረግ ስለመሆን አለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 653/2001 አንቀጽ 53/3 የደነገገው ባይኖርም ዳኞች በክልል ፍርድ ቤቶች በዲኝነት እና በፕሬዝዲንትነት ማገልገላቸው እስከተረጋገጠ ድረስ በገንዘብ ተሰልተው የሚከፈለ የመቋቋሚያ አበል፤ የመኖሪያ ቤት አበል እና የተሽከርካሪ አበል ክፍያዎችን ለማግኘት በፋደራል ፍርድ ቤት ያገለገለበት ዘመን ሲቆጠር በክልል በዲኝነት እና በፕሬዝዲንትነት የሰጡት አገልግልት ታሳቢ የሚደረግ አቶ ጳውልስ አርሺሶ እና የኢ.ፋ.ዱ.ሪ. ገንዘብ ሚኒስቴር የኢ.ፋ.ዱ.ሪ. ህገ-መንግስት አንቀጽ አንቀጽ 50/2፣ አዋጅ ቁጥር 653/2001 እና ማሻሻያው አዋጅ ቁጥር 1003/2009
No summary available.
የሰ/መ/ ሚያዝያ 26 ቀን 2013 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ ተሾመ ሽፈራዉ ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግስቱ ነጻነት ተገኝ አመልካች፡- አቶ ጳውልስ አርሺሶ ኦልንጄ ቀረቡ ተጠሪ፡- የኢ.ፋ.ዱ.ሪ. ገንዘብ ሚኒስቴር ነ/ፈ ተወዲጅ መሀመድ ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የፍደራል ፍርድ ቤት ዳኞች በጡረታ ከዲኝነት ስራቸው ሲነሱ ማግኘት የሚገባቸውን ጥቅሞች ለመወሰን በክልል ፍርድ ቤቶች በዲኝነት የሰሩበት የአገልግልት ዘመን ታሳቢ የሚደረግ መሆን አለመሆኑን የሚመለከት ነው። የክርክሩን አመጣጥ ስንመለከት አመልካች ለተጠሪ በመስከረም 12 ቀን 2013 ዓ.ም. ጽፈው ባቀረቡት ማመልከቻ የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዲኛ በመሆን ሳገለግል ቆይቼ በጡረታ የተሰናበትኩ በመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 653/2001 እና በማሻሻያው አዋጅ ቁጥር 1003/2009 መሰረት መብትና ጥቅሜ ይከበርልኝ በማለት ጠይቀዋል። ተጠሪም በቁጥር ገ/ኢ/1/33/39 በቀን 15/5/2013 ዓ.ም. በተጻፈ ምላሽ(ደብዲቤ) የአመልካችን አቤቱታ መርምሮ በሰጠው አስተዲደራዊ ውሳኔ በአዋጅ ቁጥር 653/2001 መሰረት ከሀላፉነት የተነሱ የፍደራል ፍርድ ቤት ዳኞች በገንዘብ ተሰልተው ለባለመብቶች በአንድ ጊዜ የሚሰጡት መብቶች እና ጥቅሞች ለማግኘት ባለመብቱ ቢያንስ አንድ የምርጫ ዘመን ለአምስት አመት ማገልገል እንዲለበት ተደንግጓል። አመልካች በፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዲኝነት የሰጡት አገልግልት ግን ከአንድ የምርጫ ዘመን ያነሰ በመሆኑ የስራ ስንብት ክፍያ ከሚያገኙ በስተቀር ላልች በገንዘብ ተሰልተው የሚገኙ መብቶች እና ጥቅሞችን ማግኘት አይችለም። አመልካች በፋደራል ደረጃ በዲኝነት ከመሾማቸው በፉት በክልል መንግስት በተለያዩ የኃላፉነት ደረጃ የሰጡት አገልግልት በአዋጁ አንቀጽ 53/3 መሰረት ሉያዝ አይችልም በማለት የአመልካችን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል።
አመልካች በተጠሪ ጥያቄያቸው ውድቅ መደረጉን በመቃወም ለፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ያቀረቡ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን አስቀርቦ ካከራከረ በኋላ በፋደራል ፍርድ ቤት በዲኝነት ሲያገለግል ቆይቶ በጡረታ የተሰናበተ ዲኛ በክልል መንግስት የተለያዩ የዲኝነት ደረጃዎች ላይ የሰጠው አገልግልት እንዱታሰብ አዋጅ ቁጥር 653/2001 እና ማሻሻያው አዋጅ ቁጥር 1003/2009 ስለማይፈቅድ አመልካች መብት እና ጥቅማ ጥቅም እንዱከበርላቸው ያቀረቡት ጥያቄ በተጠሪ ውድቅ መደረጉ ተገቢ ነው በማለት የተጠሪን ውሳኔ አጽንቷል።
አመልካች የሰበር ቅሬታ ያቀረቡት በተጠሪ እና በስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ለማሳረም ሲሆን የቅሬታቸው ይዘት ሀምላ ወር 2003 ዓ.ም.
በወጣው የፍደራል ፍርድ ቤቶች እጩ ዳኞች ምልመላ ስርአት አፈጻጸም መመሪያ የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዲኛ ሆኖ ለመሾም ካስቀመጣቸው መስፈርቶች አንደ የዲኝነት ሙያ አገልግልት ዘመንን የሚመለከት ነው። አመልካችም ለፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዲኛ ሆኜ የተሾምኩት በከምባታ ጠንባሮ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና በደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዲኝነት ስራ ለ19 አመት ከ5 ወር የሰጠሁት አገልግልት ከትምህርት ደረጃዬ ጋር ታይቶ ነው። የዲኝነት ሙያ አገልግልት በክልልም ይሁን በፋደራል አንድ አይነት ሙያ ነው። የዲኝነት ሙያ አገልግልት አያያዝን አዋጁ በአንቀጽ 53/3 በዝምታ ያለፈው ዲኝነት የሙያ ተግባር ስለሆነ በክልል ፍርድ ቤት የተሰጠ የዲኝነት አገልግልት ወደ ፋደራል ፍርድ ቤት በሹመት ሲኬድ የክልል አገልግልቱ የሚያዝ መሆኑን ታሳቢ በማረግ እንጂ የክልል አገልግልት እንዲይያዝ ለመከልከል አይደለም። አዋጁ በዚህ መልኩ የማይተረጎም ከሆነ በመንግስት ከፍተኛ መሪዎች እና በዳኞች መካከል አድልአዊ አሰራርን የሚፈጥር እና በህገ-መንግስቱ የተደነገገውን የእኩልነት መርህ የሚጥስ ነው። በክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዲኝነት ስራ ላይ በነበርኩበት ወቅት በፋደራል ጉዲዮች ላይ የዲኝነት አገልግልት የሰጠሁ ከመሆኑም በላይ በክልልም ሳገለግል የቆየሁት የአገራችንን ዜጎች እንጂ የላላ አገር ዜጎችን አይደለም። አዋጁም ቢሆን መብትና ጥቅሞችን ለማግኘት ቢያንስ አምስት አመት ዲኛው ማገልገል እንዲለበት ከሚገልጽ ውጪ በፋደራል ፍርድ ቤት ብቻ ያገለገለ በሚል አያስቀምጥም። በመሆኑም በክልል የሰጠሁት አገልግልት ሉያዝ አይገባም መባለ የህግ አተረጓጓም ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ ታርሞ የማቋቋሚያ፤ የመኖሪያ ቤት፤ የተሽከርካሪ አበል እና የስንብት ክፍያ በመጨረሻ ላይ በወር ይከፈለኝ በነበረው የወር ደሞዝ ተሰልቶ እንዱከፈለኝ ይወሰንልኝ የሚል ነው።
የሰበር አጣሪ ችልትም የአመልካችን የሰበር ቅሬታ መርምሮ አመልካች በክልል ፍርድ ቤቶች የሰጡት የዲኝነት አገልግልት በአዋጅ ቁጥር 653/2001 የተመለከቱት ጥቅሞች እና መብቶች ለማግኘት ሉያዝላቸው አይገባም የመባለን አግባብነት በኢ.ፋ.ድ.ሬ. ህገ-መንግስት አንቀጽ 78 እና 80 መሰረት በክልል ፍርድ ቤቶች በውክልና የሚሰጠው የፍደራል ዲኝነት አገልግልት እና ከአዋጁ አንቀጽ 53/3 ድንጋጌ ጋር የተጣጣመ መሆን አለመሆኑን ለማጣራት ያስቀርባል በማለት ተጠሪ መልስ እንዱያቀርብ ትእዛዝ ሰጥቷል።
ተጠሪም በሰጠው መልስ በክልል የተሰጠ የአገልግልት ዘመን በፋደራል ፍርድ ቤቶች በዲኝነት ለመሾም የሚያገለግል የስራ ልምድ ቢሆንም መብትና ጥቅሞችን ለማግኘት ታሳቢ የሚደረግ አይደለም። በአዋጅ ቁጥር 653/2001 የተቀመጡት መብትና ጥቅሞች ተፈጻሚ የሚሆኑት በፋደራል ደረጃ ቢያንስ ለአምስት አመት ለተሰጡ አገልግልቶች ብቻ ነው። አመልካች መብትና ጥቅማቸውን መጠየቅ የሚችለት አገልግልት ከሰጡበት ክልል እንጂ ከፋደራል መንግስቱ አይደለም። አመልካች በፋደራል ደረጃ የሰጡት አገልግልት ለ3 ዓመት ከ11 ወር ብቻ ስለሆነ በዚህ ጊዜ ታስቦ የስንብት ክፍያ ብቻ ከሚከፈላቸው በስተቀር ላልች መብትና ጥቅሞችን ማግኘት አይችለም በማለት ተከራክሯል።
አመልካችም የመልስ መልስ በማቅረብ ክርክራቸውን አጠናክረዋል።
የክርክሩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም አመልካች በፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለ3 ዓመት ከ11 ወር በዲኝነት አገልግለው በጡረታ ሲሰናበቱ በክልል ፍርድ ቤቶች በዲኝነት ሙያ የሰጡት የአገልግልት ዘመን መብትና ጥቅማቸውን ለማግኘት በፋደራል መንግስት ታሳቢ ላደረግ አይችልም የተባለበትን አግባብ ለቅሬታ መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ከተገቢው ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምረናል።
እንደመረመርነው አመልካች በፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዲኝነት ለ3 ዓመት ከ11 ወር ካገለገለ በኋላ ከሐምል 1 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ በጡረታ ተሰናብተዋል። አመልካች ለፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዲኝነት ከመሾማቸው በፉት በደቡብ ክልል ከምባታ ጠንባሮ ዞን ከፍተኛ እና በደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች በፕሬዝዲንትነት እና በዲኝነት ማገልገላቸው አከራካሪ አይደለም። በግራ ቀኙ መካከል እያከራከረ ያለው አመልካች በጡረታ ሲሰናበቱ መብትና ጥቅማቸውን ለመወሰን በክልል ፍርድ ቤቶች ያገለገለበት የአገልግልት ዘመን ሉታሰብ ይገባል ወይስ አይገባም የሚለው ነው። ለዚህ ክርክር ምላሽ ለማግኘት ከሀላፉነት የተነሱ የሀገርና የመንግስት መሪዎች፤ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፉዎች፤ የምክር ቤት አባላት እና ዳኞች የሚያገኟቸውን መብቶች እና ጥቅሞች ለመወሰን የወጣውን አዋጅ ቁጥር 635/2001 እና ማሻሻያውን አዋጅ ቁጥር 1003/2009 መመርመሩ ተገቢ ነው።
በመጀመሪያም አዋጅ ቁጥር 653/2001ን መደንገግ ያስፈለገበትን መሰረታዊ አላማ ከአዋጁ መግቢያ (preamble) ላይ ስንመለከት የሀገር እና የመንግስት መሪዎች፤ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፉዎች፤ የምክር ቤት አባላት እና ዳኞች የሀገርንና የህዝብን ጥቅም ለማስከበር ከፍተኛ የሀገር ሀላፉነትን በመሸከም የሚሰሩ በመሆናቸው ከሀላፉነት ሲነሱ ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ ችግር ሳይገጥማቸው የሀገርንና የራስን ክብር የሚያስጠብቅ ኑሮ እንዱኖሩ ለማስቻል፤ ከነበሩበት ኃላፉነት ቦታ አንጻር በሚሰጡት ውሳኔ ለጥቃት ተጋላጭ እንዲይሆኑ ጥበቃና ከለላ ለመስጠት፤ በኃላፉነት በነበሩበት ወቅት ያካበቱትን እውቀት እና ልምድ ለመጠቀም አመቺ ሁኔታን ለመፍጠር እንዱሁም ለሀገር እድገት እና ልማት በቅንነት በታማኝነትና በትጋት እንዱሰሩ ለማበረታታት መሆኑን ያስገነዝባል። በዚህ አዋጅ የተመለከቱት ከፍተኛ የመንግስት ኃላፉዎች በጡረታ ወይም በልላ ህጋዊ ምክንያት ከሀላፉነት ሲነሱ የተለያዩ መብትና ጥቅሞች እንዱከበርላቸው ያስፈለገበት ዋናው ምክንያት ከሀላፉነት ከተነሱ በኋላ ስለሚገጥማቸው ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር ሳይጨነቁ ኃላፉነታቸውን በቅንነት፣በታማኝነት፣በገለልተኛነት እና በአጠቃላይ የስራውን ወይም የሙያውን ስነ-ምግባር በመጠበቅ የተጣለባቸውን ከፍተኛ የመንግስትና የህዝብ ሃላፉነት እንዱወጡ ለማስቻል ነው። እንደዚሁም በመንግስት ሃላፉነት ላይ በመቆየት ህዝብና ሀገርን ማገልገል እየቻለ ሀላፉነታቸውን በመልቀቅ ወደላላ የተሻለ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ወደሚያስገኝ ስራ ለመሄድ በማሰብ ከሃላፉነታቸው እንዲይለቁ በማድረግ ያካበቱትን እውቀት እና ልምድ ለመጠቀም አመቺ ሁኔታ መፍጠር ላላው አዋጁን ማውጣት ያስፈለገበት ምክንያት ነው። የአዋጁ አላማ ይህ ከሆነ በአዋጅ ላይ የተመለከቱትን መብትና ጥቅሞች ለማግኘት ምን አይነት ሁኔታዎች መሟላት አለባቸው የሚለውን ቀጥል መመልከቱ ተገቢ ነው።
በተለይም ለዚህ ክርክር መነሻ የሆነው አመልካች ከዲኝነት ኃላፉነታቸው በጡረታ ከተሰናበቱ በኋላ ያቀረቡት የመብት እና የጥቅማ ጥቅም የክፍያ ጥያቄ በመሆኑ ዳኞች ከዲኝነት ኃላፉነታቸው ከተሰናበቱ በኋላ በአዋጅ ቁጥር 653/2001 እና ማሻሻያ አዋጁ መሰረት የመብት እና የጥቅማ ጥቅም ክፍያ ማግኘት የሚችለት መቼ ነው? የሚለውን ስንመለከት በአዋጅ ቁጥር 653/2001 አንቀጽ 2/12-15 ባለት ድንጋጌዎች መሰረት የመጀመሪያው መስፈርት የፍደራል ፍርድ ቤቶች ማለትም የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ወይም የከፍተኛ ወይም ደግሞ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዲኛ ሆኖ ማገልገል ነው። ይህም ማለት ዲኛው ከኃላፉነት በጡረታ ወይም በልላ ህጋዊ ምክንያት በተነሳበት ወቅት በፋደራል ፍርድ ቤቶች በዲኝነት ሙያ ላይ ሲያገለግል የነበረ መሆን እንዲለበት የሚያስገነዝብ ነው።
ላላው መስፈርት የአገልግልት ዘመንን የሚመለከት ነው። የአዋጁ አንቀጽ 44/1፣46/1 እና 47/1 ድንጋጌዎች ማንኛውም ዲኛ ቢያንስ አምስት አመት አገልግል ወይም ከሁለት አመት ተኩል ያላነሰ አገልግል በህመም፣ በአካል ጉዲት እና በልላ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ከሃላፉነት ከተነሳ የመቋቋሚያ አበል፣ የስራ ስንብት ክፍያ፣ የመኖሪያ ቤት አበል እና የተሽከርካሪ አበል ክፍያ እንደሚያገኝ ያመለክታለ።
እነዚህን መብትና ጥቅሞች ለማግኘት ዲኛው ከሀላፉነት በሚነሳበት ወቅት የፍደራል ፍርድ ቤት ዲኛ የነበረ መሆን እንዲለበት ግልጽ ነው። ነገር ግን አነስተኛ የአገልግልት ዘመን ተብል በህጉ የተቀመጠው የአገልግልት ጊዜ በፋደራል ፍርድ ቤት የተሰጠ የአገልግልት ዘመን ብቻ መሆን ያለበት ስለመሆኑ የተጠቀሱት ድንጋጌዎች በግልጽ አያመለክቱም። በልላ አነጋር አንድ የፍደራል ፍርድ ቤት ዲኛ በአዋጅ የተመለከቱትን መብት እና ጥቅሞች ለማግኘት ወደ ፋደራል ፍርድ ቤት ከመምጣቱ በፉት በክልል ፍርድ ቤቶች የሰጠው የአገልግልት ዘመን ታሳቢ ይደረጋል ወይስ አይደረግም? ለሚለው አዋጁ በግልጽ ምላሽ አይሰጥም። አንድ ህግ ግልጽነት የላለው ወይም አሻሚ ሲሆን ወይም ከላላ ህግ ጋር ግጭት ሲኖረው ተቀባይነት ያገኙ የህግ አተረጓጎም መርሆዎችን በመከተል ህጉን ውጤታማ እና ተፈጻሚ እንዱሆን ማድረግ የዲኝነት አካል ዋነኛ ተግባር መሆኑ እሙን ነው።
በህግ አተረጓጎም ረገድ ጥቅም ላይ ከሚውለ የአተረጓጎም መርሆዎች ውስጥ አንደ ወርቃማ የአተረጓጎም ዘዳ (Golden rule of interpretation) ሲሆን የዚህ አይነት አተረጓጎም መሰረተ ሀሳብ ህጉ በአጠቃላይ ወይም በህጉ በተወሰኑ ድንጋጌዎች ለማሳካት የታሰበውን አላማ ተግባራዊ ማድረግ የሚያስችል ትርጉም መስጠት ነው። ይህን የአተረጓጎም መርህ ተግባራዊ ለማድረግ ህጉን ለማውጣት ያስፈለገበትን አጠቃላይ ምክንያት ከህጉ መግቢያ፣ ህግ አውጪው ህጉን ሲያወጣ የተወያየበትን ሰነድ (ሀተታ ዘምክንያት) እና መሰል ሰነድችን እንዱሁም በህጉ በተለያዩ ድንጋጌዎች ላይ የተመለከቱትን መሰረተ ሀሳቦች ከግምት ውስጥ በማስገባት አንደን ከላላው ጋር በማዛመድ መመልከት ያስፈልጋል።
በዚህም መሰረት አንደኛ ከአጠቃላይ የአዋጅ ቁጥር 653/2001 አላማና መንፈስ አንጻር ከፋደራል ፍርድ ቤቶች ውጪ በክልል ፍርድ ቤቶች የተሰጠ የዲኝነት የአገልግልት ዘመን ታሳቢ ላደረግ ይገባል አይገባም የሚለውን መመርመር ተገቢ ነው። በአዋጁ መግቢያ(preamble) ላይ አንደ አዋጁን ማውጣት ያስፈለገበት አላማ ዳኞች እና ከፍተኛ የመንግስት ኃላፉዎች እንዱሁም የምክር ቤት አባላት ያካበቱትን እውቀት እና ልምድ ለመጠቀም አመቺ ሁኔታን ለመፍጠር ነው። የዲኝነት ሙያ በክልልም ሆነ በፋደራል ፍርድ ቤቶች ለመሾም ዋነኛው መስፈርት የትምህርት ደረጃ እና የአገልግልት ዘመን መሆኑ አከራካሪ አይደለም።
ከትምህርት ደረጃ በተጨማሪ የአገልግልት ዘመን ለሹመት አስፈላጊ የሆነበት ምክንያት በሙያው የዲበረ ክህልት እና ልምድ ሉገኝ የሚችለው ከህግ ትምህርት በተጨማሪ በሙያው ላይ ለረጅም አመት አገልግልት በመስጠት መሆኑ ስለታመነበት ነው። በክልልም ሆነ በፋደራል ፍርድ ቤት በዲኝነት የተሰጠ አገልግልት ዘመን በሹመት ወቅት ታሳቢ ተደርጎ ጥቅማ ጥቅም ለማግኘት ግን በክልል በዲኝነት ሙያ የተሰጠበት የአገልግልት ዘመን ታሳቢ አይደረግም ማለት እርስ በርሱ የሚጋጭ ከመሆኑም በላይ በክልል የተሰጠ የዲኝነት የአገልግልት ዘመን በአዋጁ መሰረት ተጠቃሚ ለመሆን ታሳቢ የማይደረግ ከሆነ በረጅም የአገልግልት ዘመን የዲበረ የዲኝነት ሙያ ያላቸው ዳኞች ከክልል ወደ ፋደራል ፍርድ ቤት መጥተው በዲኝነት ሙያ ለማገልገል ፍቃደኛ እንዲይሆኑ በማድረግ የካበተ እውቀት እና ልምድ ለመጠቀም የሚያስችል ሁኔታ ለመፍጠር አዋጁ ታሳቢ ያደረገው አላማ እንዲይሳካ ያደርጋል። በመሆኑም ህጉን በዚህ አግባብ ተግባራዊ ማድረግ ህጉ ውጤታማ በሆነ መንገድ ተግባራዊ እንዲይሆን ስለሚያደርግ ተቀባይነት ያለው አይደለም።
ሁለተኛ የህጉን ይዘት ወይም አውድ መመልከቱ ተገቢ ነው። አዋጅ ቁጥር 653/2001 አንቀጽ 53 የአገልግልት ዘመን አቆጣጠርን በሚመለከት በንዐስ ቁጥር 3 ላይ የተደነገገውን ስንመለከት ከኃላፉነት የተነሳ ከፍተኛ የመንግስት ሃላፉ ወይም የምክር ቤት አባል ከመሾሙ በፉት በክልል በድንጋጌው ላይ የተመለከቱት ኃላፉነቶች ላይ አገልግልት ከሰጠ በዚህ አዋጅ መሰረት ለሚያገኘው መብት እና ጥቅም በክልል ያገለገለበት ዘመን ታሳቢ እንደሚደረግለት ተደንግጓል። ከላይ እንደተገለጸው በክልል የተሰጠ አገልግልትን ታሳቢ ማድረግ ያስፈለገበት አንደ ምክንያት በአዋጁ መግቢያ ላይ የተመለከተውን የአዋጁን መሰረታዊ አላማ ለማሳካት ሲሆን ላላው ከሃላፉነት የሚነሱ የክልል መንግስት መሪዎችን፣ ከፍተኛ የመንግስት ሃላፉዎችን፣ የክልል ምክር ቤት አባላት የሚያገኟቸውን መብቶች እና ጥቅሞች እያንዲንደ ክልል ባወጣው አዋጅ የተጠበቁ መብቶች ስለሆኑ እነዚህ ኃላፉዎች ወደ ፋደራል መንግስት ሲመጡም የፍደራል መንግስቱ ባወጣው አዋጅ የተጠበቁ እንዱሆኑ ለማድረግ ነው። እንደዚሁም በህገ-መንግስቱ የተቀመጠውን የመንግስት አወቃቀር ተከትል የፍደራል መንግስት እና የክልል መንግስት በሚል የተዋቀረ ቢሆንም በክልል ይሁን በፋደራል መንግስት የተሰጠ አገልግልት ለሀገር እና ለህዝቦቿ የተሰጠ አገልግልት ተደርጎ ስለሚቆጠር ነው።
ነገር ግን የአዋጁ አንቀጽ 53/3 በክልል ፍርድ ቤቶች በዲኝነት ስለተሰጠ የአገልግልት ዘመን በፋደራል መንግስት ታሳቢ የሚደረግ ስለመሆን አለመሆኑ የሚለው ነገር የለም። ዲኝነትን በሚመለከት ድንጋጌው በክልል ስለተሰጠ የአገልግልት ዘመን ታሳቢ መደረግ አለመደረግ በዝምታ ማለፈ በዲኝነት ሙያ በክልል የተሰጠ አገልግልት ዘመን በፋደራል ፍርድ ቤት እያገለገለ ቆይቶ ለተሰናበተ ዲኛ ታሳቢ እንዲይደረግ ለመከልከል ነው ልባል አይችልም። ለዚህም አንደኛው ምክንያት በህግ አተረጓጎም መርህ በግልጽ ያልተከለከለ እንደተፈቀደ ስለሚቆጠር ነው። ይህም ማለት አዋጁ በክልል የተሰጠ የዲኝነት አገልግልት ዘመን ታሳቢ እንዱደረግ የማይፈልግ ቢሆን ኖሮ በግልጽ ታሳቢ ላደረግ እንደማይችል ያመለክት ነበር።
በክልል ያገለገለ ዳኞች የክልለ መንግስት ባወጣው አዋጅ መብት እና ጥቅም እስከተጠበቀላቸው ድረስ ይሄው በክልል ያገኙት መብት በፋደራል አዋጁ ሉጠበቅላቸው ስለሚገባ አዋጁ በግልጽ በክልል የተሰጠ አገልግልት ዘመን ታሳቢ እንዲይደረግ ለመከልከል በህግ አውጪው ታስቦ ነው ለማለት አይቻልም።
ሁለተኛው ምክንያት የአዋጁ አንቀጽ 53/3 ከአዋጁ መሰረታዊ አላማ ጋር በሚጣጣም መልኩ መተርጎም አለበት። የአዋጁ አንደ አላማ የካበተ እውቀት እና ልምድ ለመጠቀም ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር በመሆኑ በክልል መንግስት በዲኝነት ሙያ ላይ የተሰጠ አገልግልትም አዋጁ ታሳቢ እንዱደረግ ያሰበ መሆኑን አመልካች ነው። ሶስተኛው ምክንያት እንደሚታወቀው የኢ.ፋ.ድ.ሪ. ህገ መንግስት አንቀጽ 50/2 የፍደራልም ሆነ የክልል መንግስት ሶስት አካላት እንደሚኖሩት እነርሱም ህግ አውጪ፣ ህግ አስፈጻሚ እና ህግ ተርጓሚ ወይም የዲኝነት አካል መሆናቸው ተመልክቷል። የአዋጅ ቁጥር 653/2001 መግቢያ የሚያሳየውም በአዋጁ የተጠቀሱ መብቶች እና ጥቅሞች የተጠበቁት በእነዚህ ሶስቱ የመንግስት አካላት ውስጥ ከፍተኛ መሪነት፣ ኃላፉነት፣ በምክር ቤት እና በዲኝነት ላገለገለት ነው። የአዋጅ ቁጥር 653/2001 አንቀጽ 53/3 ድንጋጌ ከአገልግልት አቆጣጠር አንጻር በክልል የተሰጠ አገልግልት በፋደራል ደረጃ ለህግ አውጪው እና ለህግ አስፈጻሚው ታሳቢ እንደሚደረግ ለዲኝነት አካለ ግን ታሳቢ እንደማይደረግ አድርጎ መተርጎም በሶስቱ የመንግስት አካላት መካከል አድልአዊ አሰራርን የሚፈጥር ይሆናል። የፍደራል ፍርድ ቤቶች በዲኝነት የሚሾሙትን የሰው ኃይል የሚያገኙት በየደረጃዉ ካለት የፋዳራል ፍርድ ቤቶች ብቻ ሳይሆን በህገ-መንግስቱ የተዘረጋውን በመተባበር ላይ የተመሰረተ የፋደራሉዝም ስርአት በመከተል ከክልል ፍርድ ቤቶች ጭምር በመሆኑ ይህንን ታሳቢ አለማድረግ የፋደራሉዝም መንግስት አወቃቀሩን እና የስልጣን ክፍፍል አላማ ያላገናዘበ ይሆናል። በመሆኑም በነዚህ ከላይ በተጠቀሱ ሶስት ምክንያቶች የአዋጁ አንቀጽ 53/3 በፋደራል መንግስት በዲኝነት አገልግል ለተሰናበተ ዲኛም በክልል በዲኝነት የሰጠው አገልግልት ዘመን ሉታሰብለት እንደማይገባ ክልከላ የሚያደርግ ተደርጎ ሳይሆን በክልል የዲኝነት ሙያ የተሰጠበት የአገልግልት ዘመን ታሳቢ ማድረግን እንደማይከለክል ተደርጎ ሉተረጎም ይገባል።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስ አመልካች በደቡብ ክልል እና በከምባታ ጠንባሮ ዞን በፕሬዝዲንትነት እና በዲኝነት ሙያ ማገልገላቸው አከራካሪ አይደለም። በፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዲኝነት የተሾሙበት አንደ መስፈርትም በክልለ በዚህ መልኩ ያካበቱት እውቀት እና ልምድ ታሰቢ በማድረግ ነው። አመልካች በክልል ፍርድ ቤቶች በዲኝነት እና በፕሬዝዲንትነት ማገልገላቸው እስከተረጋገጠ ድረስ በክልል ያገለገለበት ዘመን ከላይ በተገለጸው ምክንያት በአዋጅ ቁጥር 653/2001 እና በማሻሻያው አዋጅ ቁጥር 1003/2009 ላይ የተመለከቱት በገንዘብ ተሰልተው የሚከፈለ ክፍያዎችን ለማግኘት በፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያገለገለበት ዘመን ሲቆጠር አመልካች በክልል በዲኝነት እና በፕሬዝዲንትነት የሰጡት አገልግልት ታሳቢ ላደረግላቸው ይገባል።
ሲጠቃለል ተጠሪ የአዋጅ ቁጥር 653/2001 አንቀጽ 53/3 ድንጋጌን ከአዋጁ መሰረታዊ አላማ እና መንፈስ እንዱሁም ከኢ.ፋ.ድ.ሪ. ህገ-መንግስት ጋር አገናዝቦ በማየት አመልካች በክልል በፕሬዝዲንትነት እና በዲኝነት አገልግልት የሰጡበትን ጊዜ ታሳቢ አድርጎ መብትና ጥቅማቸውን አስልቶ ሉከፍል ሲገባ አመልካች በፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያገለገለበት ጊዜ የ3 ዓመት ከ11 ወር የስንብት ክፍያ ብቻ ነው የሚገባቸው ማለቱ መሰረታዊ የህግ አተረጓጎም ስህተት የተፈጸመበት ነው። የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤቱም የተጠሪን ስህተት ማረም ሲገባው ማጽናቱ መሰረታዊ ህግ ስህተት በመሆኑ የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
1ኛ. ተጠሪ ቁጥር ገ/ኢ/1/33/39 በቀን 15/03/2013 ዓ.ም. የሰጠው ውሳኔ እና የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በቀን 07/05/20113 ዓ.ም. የሰጠው ውሳኔ በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 348/1 መሰረት ተሻሽሎል።
2ኛ. ተጠሪ አመልካች በደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና በከምባታ ጠምባሮ ዞን በፕሬዝዲንትነት እና በዲኝነት ያገለገለበትን ጊዜ አጣርቶ በፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዲኝነት ካገለገለበት ዘመን ጋር ታሳቢ በማድረግ መብትና ጥቅማቸውን ማለትም የመቋቋሚያ አበል፤ የመኖሪያ ቤት አበል እና የተሽከርካሪ አበል አስልቶ እንዱከፍላቸው ተወስኗል። እንደዚሁም የስንብት ክፍያ ተጠሪ ለአመልካች እንዱከፈላቸው የወሰነው የ3ዓመት ከ11 ወር እንደተጠበቀ ሆኖ ከላይ እንደተገለጸው አመልካች በክልል የሰጡትን የአገልግልት ጊዜ ታሳቢ ሲያደርግ የሚቀረውን የስንብት ክፍያ አጣርቶ ለአመልካች እንዱከፈላቸው ተወስኗል።
3ኛ. አመልካች ስላቱ መጨረሻ ላይ ሲያገኙ በነበረው ደመወዝ እንዱሰላ እንዱወሰንላቸው የጠየቁ ቢሆንም ተጠሪ የደመወዝ መጠን አሰላልን በተመለከተ የሰጠው ውሳኔ የላለ በመሆኑ እና ጉዲዩ ከተመለሰለት በኋላ ከሚሰላው የደመወዝ መጠን ጋር በተያያዘ የሚነሳ ቅሬታ ካለ ተጠሪ ከሚሰጠው ውሳኔ በኋላ ላታይ የሚገባ በመሆኑ ታልፎል።
4ኛ. በዚህ ፍርድ ቤት የተደረገው ክርክር ያስከተለውን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
No topics extracted.