የተሻሻለ የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም አዋጅ ከመውጣቱ በፉት በነባር ህግ መሰረት በሕይወት ያለ ሰው የገጠር መሬት ይዞታውን በሚመለከት የመሬት ስጦታ ውል አድርጓል የሚባለዉ በሥራ ላይ በነበረዉ አዋጅ መሰረት እንጂ ከዛ ወዱህ የክልል መንግስት የፖሉሲ ለዉጥ በማድረግ ያወጣዉን ሕግ መሰረት ተደርጎ ስላለመሆኑ የአማራ ክልል የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 133/1998 እና የተሻሻለው የአማራ ክልል የገጠር መሬት አዋጅ ቁጥር 252/2009
No summary available.
ሚያዚያ 28 ቀን 2013 ዓ.ም ዳኞች፡ ….1. ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) 2. ቀነዓ ቂጣታ 3. ፈይሳ ወርቁ 4. ደጀኔ አያንሳ 5. ብርቅነሽ እሱባለዉ አመልካች፡ ……..አቶ ጌታሰዉ አገሩ ለማ ተጠሪዎች፡ ……...1. አቶ አስማማዉ ለማ 2. ወ/ሮ አባይ ለማ 3. ወ/ሮ እማምላክ ለማ ይህ መዝገብ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የእርሻ መሬት ክርክር የተጀመረዉ በአማራ ክልል በምስራቅ ጎጃም ዞን በሸበል በረንታ ወረዲ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካች የሥር ተከሳሽ፣ የአሁን ተጠሪዎች የሥር 1ኛ፣ 3ኛና 5ኛ ከሳሾች፣ በዚህ ችልት የክርክሩ ተካፊይ ያልሆኑት ሁለት ሰዎች ከሳሾች ሆነው ሲከራከሩ ነበር። ጉዲዩ ለዚህ ችልት ላቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ.ቁ.03-77218 ጥቅምት 24 ቀን 2012 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱታረምልኝ በማለት በማመልከታቸዉ ነዉ።
የጉዲዩ አመጣጥ ሲታይ የሥር ከሳሾች በሥር በወረዲ ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ የከሳሾች ሟች አባት አቶ ለማ አይችለህም በቀን 3/9/2009 ዓ.ም በተደረገ የስጦታ ውል የመሬት ይዞታዉን ለተከሳሽ ያስተላለፈ ቢሆንም አባታችን እድሜዉ በመግፊቱ ተታል ያደረገዉ ዉል በመሆኑ፤ ተከሳሽም ሟችን ያልጦረ እና ከውርስም የነቀለን ዉል በመሆኑ እንዱፈርስልን በማለት ዲኝነት ጠይቋል።
የስር ተከሳሽ በዚህ ክስ ላይ በሰጠዉ መልስ የስጦታ ዉለ የተደረገው ስጦታ ሰጪው ወድና ፈቅድ በህጉ መሰረት በመሆኑ ሉፈርስ አይገባዉም በማለት ተከራከሯል።
ከዚህ በኋላ የወረዲዉ ፍ/ቤት ግራ ቀኙን በማከራከር፣ የሰዉ ምስክሮችን በመስማት፣ በሰጠዉ ዉሳኔ በዚህ ጉዲይ ተፈጻሚነት ሉኖረዉ የሚገባዉ የስጦታ ዉለ ተደረገ በተባለበት ወቅት ስራ ላይ የነበረዉ የተሻሻለዉ የአማራ ክልል የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 133/98 አንቀጽ 17 (1) በመሆኑ፣ በዚህ አዋጅ መሰረት የመሬት ስጦታ ከመደረጉ ሶስት አመት በፉት የስጦታ ተቀባዩ የስጦታ ሰጪዉን የመጦር ግዳታ ያለበት ስለሆነ፣ ይሁን እንጂ በዚህ ጉዲይ ስጦታ ሰጪዉን ስጦታዉ ከመደረጉ በፉት ከ2 አመት ከ4 ወር ጀምሮ ሲጦረዉ የነበረዉ የተከሳሽ አባት እንጂ ተከሳሽ ባለመሆኑ የህጉን መስፈርት ስለማያሟላ የስጦታ ውለ ፈርሷል በማለት ዉሳኔ አሳልፎል።
የሥር ተከሳሽ በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለምስራቅ ጎጃም ዞን ከፍተኛ እና የሰበር አቤቱታ ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ቅሬታ ያቀረበ ቢሆንም ፍ/ቤቶቹ ቅሬታዉን ዉድቅ በማድረግ የሥር ፍ/ቤት ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል። የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ በዚህ ዉሳኔ እና ትዕዛዝ በመቃወም ለማስለወጥ ነዉ።
የአሁን አመልካች በ9/3/2012 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ፡ የአመልካች አያት የሆኑት አቶ ለማ አይችለህም የመሬት ይዞታ ለአመልካች ስጦታ ያደረገዉ በህይወት እስካለ ድረስ እንዱጦረዉ በመሆኑ፤ የመሬት ስጦታ ዉለም በክፍለ ወረዲ መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም ጽ/ቤት የፀደቀ በመሆኑ፣ አመልካች ከዚህ ዉጭ ላላ መሬት የላለኝ ሲሆን ተጠሪዎች ግን የራሳቸዉ መሬት ያላቸዉ በመሆኑ፣ የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ዉሳኔ ፍትሐዊ ስላልሆነ እንዱሻርልኝ ወጪና ኪሳራ እንዱወሰንልኝ በማለት አመልክቷል።
የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩን በማየት ፣አከራካሪው የስጦታ ውል ላታይ የሚገባዉ የተሻሻለዉ የአማራ ክልል የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 133/98 ነዉ ወይስ በአዱሱ አዋጅ ቁጥር 252/2009 ነዉ? የሚለዉን ለማጣራት ሲባል የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል በማለት ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡ ባዘዘዉ መሰረት በ6/6/2012 ዓ.ም የተጻፈ መልስ አቅርቧል።
የመልሱም ይዘት በአጭሩ፡ አመልካች የሟች አባታችን አቶ ለማ አይችለህም የልጅ ልጅ ስለሆነ ከአባታችን ጋር ለአንድ ቀንም አብሮት አልኖረም እርሱ የሚኖረዉም አዱስ አበባ ከተማ በመሆኑ፣ የስጦታ ዉለ በተደረገበት ቀን በሥራ ላይ የነበረዉ አዋጅ ቁጥር 133/98 ነዉ፤ የስጦታ ዉለ ከአዋጅ ቁጥር 133/98 አንቀጽ 17 እና አዋጅ ቁጥር 252/2009 አንቀጽ 16 ጋር የሚጋጭ በመሆኑ የስር ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሳኔ አግባብ ስለሆነ እንዱጻናልን ወጪና ኪሳራ እንዱወሰንልን በማለት ተከራክሯል። አመልካች የመልስ መልስ ስላልሰጠ ታልፎል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና ግራ ቀኙ ያደረጉት የጽሐፍ ክርክር ከፍ ሲል የተጠቀሰዉ ሲሆን ይህ ችልት የግራ ቀኙ ክርክር አግባብነት ካላቸዉ የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ እንዱሁም የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል ሲባል ከተያዘዉ ጭብጥ አንጻር እንደሚከተለዉ መርምሮታል።
እንደመረመርነዉ አመልካች የሟች አቶ ለማ አይችለህም የልጅ ልጅ ሲሆን ተጠሪዎች ደግሞ የሟች ልጆች መሆናቸዉ ያከራከረ ጉዲይ አይደለም። ሟች በሕይወት እያለ በ3/9/2009 ዓ.ም በተደረገዉ የመሬት ስጦታ ዉል ይዞታዉን ለአመልካች የሰጠ በመሆኑ፣ ተጠሪዎች ባቀረቡት ክርክር ሟች ይህን ስጦታ ያደረገዉ ተታል እና አመልካች ሟችን ያልጦረና ተጠሪዎችን ከዉርስ የነቀለ ስለሆነ ሉፈርስ ይገባል የሚል ሲሆን፤ አመልካች በበኩለ ስጦታዉ ሕጋዊ ስለሆነ ሉፈርስ አይገባም የሚል ክርክር አቅርቧል። በዚህ መሰረት በሥር ፍ/ቤቶች በማስረጃ የተረጋገጠዉ ፍሬ ነገር ሲታይ አመልካች አያቱን ሟች አቶ ለማ አይችለህምን እንዲልጦራቸዉ፣ ሟችን ለ2 ዓመትና 4 ወራት የጦራቸዉ የአመልካች አባት አቶ አገሩ ለማ መሆኑን የሥር ፍ/ቤቶች የዉሳኔ ግልባጭ ያሳያል። ይህ ከሆነ የሥር ፍ/ቤቶች ሟች ለአመልካች ያደረጉት የመሬት ስጦታ ዉል ሉፈርስ ይገባል በማለት የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ወይስ አይደለም? በዚህ ጉዲይ ተፈጻሚነት ያለዉ ሕግ የትኛዉ ነዉ? የሚለዉን ነጥብ ማየቱ ተገቢ ነዉ። ከፍ ሲል እንደተጠቀሰዉ ሟች አቶ ለማ በሕይወት እያለ የስጦታ ዉል ያደረጉት በመሬት ይዞታ ላይ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል።
እንደሚታወቀዉ ስጦታን በአጠቃላይ በሚመለከት በፍትሐ ብሕር ሕጉ አንቀጽ 2427 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ሥር የተጠቀሰ ሲሆን፣ በእነዚህ ድንጋጌዎች ሥር የስጦታ ትርጉም፣ ስጦታ ሉያሟላ የሚገባቸዉ መስፈርቶች፣ ስጦታ የሚያስከትለዉ ዉጤት እና ስጦታን ሉያስፈርሱ የሚችለ ምክንያቶችም ተመልክተዉ እናገኛለን። የስጦታ ሰጪ ወራሾች አዉራሻቸዉ ያደረገዉ ስጦታ እንዱሻርላቸዉ ክስ አቅርበዉ ዲኝነት የሚጠይቁበት ምክንያቶች በዚህ ሕግ አንቀጽ 2449 ሥር ተዘርዝረዉ ይገኛለ። የስጦታ ሰጪ ወራሾች በዚህ ድንጋጌ መሰረት ስጦታዉ እንዱሻርላቸዉ የሚያቀርቡት ክስ ስጦታ መኖሩን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ያሳያል። ከፍ ሲል እንደተመለከተዉ ሟች ለአመልካች ስጦታ አድርጓል የተባለዉ የመሬት ይዞታ በመሆኑ ከአማራ ክልል የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 133/1998 አንቀጽ 17 መሰረት የመሬት ባለይዞታ የይዞታና የመጠቀም መብትን በስጦታ ዉል ለማስተላለፍ የሚችልበትን አግባብ ይደነግጋል።
አሁን በተያዘዉ ጉዲይ ሟች መሬቱን በስጦታ ዉል ለአመልካች አስተላልፎል በተባለ ጊዜ ሥራ ላይ የነበረዉ ሕግ አዋጅ ቁጥር 133/1998 መሆኑን ያከራከረ ጉዲይ አይደለም። በዚህ አዋጅ አንቀጽ 17 ሥር እንደተመለከተዉ የመሬት ስጦታ ዉል ተደርጓል ለማለት በድንጋጌዉ የተመለከቱት ቅድመ ሁኔታዎች ተሟልተዉ ሲገኙ ብቻ ነዉ። ከእነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች መካከል አንደ በዚህ አንቀጽ 17 (1፣ ለ) ሥር የተደነገገዉ ሲሆን፣ ይዘቱም ስጦታ ተቀባዩ የባለይዞታዉን መሬት እያረሰ ወይም ላላ ሥራ እየሰራ ስጦታዉ ከመከናወኑ በፉት ላለት ሶስት ተከታታይ አመታት ሰጭዉን በነጻ ሲጦር መቆየቱ የታወቀ መሆን እንደሚገባዉ ይደነግጋል።
ከዚህ አንጻር በሥር ፍ/ቤቶች የተረጋገጠዉ ፍሬ ነገር ሲታይ አመልካች ሟች በሕይወት እያለ ያልጦራቸዉ መሆኑ ነዉ። ስለሆነም አመልካች ሟች በሕይወት እያለ አለመጦሩ እስከተረጋገጠ ድረስ፣ ከፍ ሲል በተጠቀሰዉ የገጠር መሬት አዋጅ መሰረት የመሬት ስጦታ ዉል አለ ለማለት በአዋጁ የተመለከተዉ ቅድመ ሁኔታ ያልተሟላ መሆኑን ነዉ። በመሆኑም ሟች ለአመልካች የመሬት ስጦታ ዉል አድርጓል፣ የመሬት ስጦታ ዉል አለ ለማለት የሚቻል አይደለም። ይህ ጉዲይ የሚመለከተዉ የመሬት ስጦታ ዉል በመሆኑ፣ በቅድሚያ ተፈጻሚነት ሉኖረዉ የሚገባዉ የገጠር መሬት አዋጁ መሆኑ ብቻም ሳይሆን በመሬት አዋጁ መሰረት የመሬት የስጦታ ዉል አለ ለማለት በሕጉ የተገለጸዉ ቅድመ ሁኔታ ያልተሟላ ስለሆነ ከፍ ሲል የተጠቀሰዉ የፍትሐ ብሕር ሕግ ድንጋጌ ተፈጻሚነት አይኖረዉም። በልላ በኩል ሟች በሕይወት እያለ የስጦታ ዉል አድርጓልና በወቅቱ ስጦታዉ ተደርጓል የሚባለዉ በሥራ በነበረዉ አዋጅ መሰረት እንጂ ከዛ ወዱህ የክልለ መንግስት የፖሉሲ ለዉጥ በማድረግ ያወጣዉን ሕግ መሰረት ተደርጎ መሆን የለበትም።
በመሆኑም አዱሱ የአማራ ክልል የገጠር መሬት አዋጅ ቁጥር 252/2009 በዚህ ጉዲይ ላይ ተፈጻሚነት ሉኖረዉ አይገባዉም ብለናል። የሰበር አጣሪ ችልት በዚህ ረገድ የያዘዉ ጭብጥ ተቀባይነት የለዉም ብለናል።
በዚህ አግባብ ሲታይ ሟች በ3/9/2009 ዓ.ም ለአመልካች አድርጓል የተባለዉ የመሬት ስጦታ ዉል በአዋጅ ቁጥር 133/1998 አንቀጽ 17 (1፣ ለ) መሰረት በድንጋጌዉ የተመለከተዉን ቅድመ ሁኔታ ያላሟላ በመሆኑ፣ ከመነሻዉ የመሬት ስጦታ ዉል አለ ለማለት ስለማይቻል፣ የሥር ፍ/ቤቶች በዚህ ረገድ የሰጠው ዉሳኔ ተገቢ ነዉ። ይህ ችልት በኢፋዳሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 80 (3፣ ሀ) እና በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 መሰረት ከተሰጠዉ ስልጣን አንጻር አመልካች ያቀረበዉ ቅሬታ የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት መሆኑን ስለማያሳይ ተቀባይነት የለዉም ብለናል።
ሲጠቃለል የሥር ፍ/ቤቶች ሟች በሕይወት እያለ ለአመልካች አድርጓል የተባለዉን የመሬት ስጦታ ዉል ሉፈርስ ይገባል በማለት የሰጡት ዉሳኔ በሕግ አግባብ ነዉ ከሚባል በስተቀር መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ለማለት ስለማይቻል የሚከተለዉ ተወስኗል፡፤
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ.ቁ.03-77218 ጥቅምት 24 ቀን 2012 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ በውጤት ደረጃ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያልተፈጸመበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 (1) መሰረት ጽንቷል።
የዚህ ዉሳኔ ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤቶች ይድረስ።
በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት በተደረገዉ ክርክር ምክንያት የደረሰዉን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸዉን ይቻለ።
No topics extracted.