የክልል የገጠር መሬት አጠቃቀም ለመወሰን በወጣ አዋጅ መሰረት የገጠር መሬትን በሽያጭ ውል ማስተላለፍ ክልከላ የተደረገበት ከሆነ መሬቱ ላይ ቤት ቢኖርበትም ባይኖርበትም የሽያጭ ውለ ከመጀመሪያውኑ ህጉን ያልተከተለ ስለሆነ በህግ ፉት የማይፀና ስለመሆኑ የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 40(3) ፣ የትግራይ ብሄራዊ ወ/ሮ አዝመራ መኮንን እና እነ አቶ ገ/ሂወት መኮንን (2 ሰዎች) መንግስት የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 239/2006
No summary available.
የሰ/መ/ ሚያዝያ 26 ቀን 2013 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሣዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡ ወ/ሮ አዝመራ መኮንን ገ/መድን ተጠሪዎች፡ 1ኛ አቶ ገ/ሂወት መኮንን ገ/መድን 2ኛ ወ/ሮ አኸዛ ሃ/ስላሴ መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን በዚሁ አግባብ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ለዚህ የሰበር ክርክር መነሻ የሆነው ጉዲይ የይዞታ/የከተማ ቦታ/ ክርክር የተመለከተ ሲሆን አመልካች 1ኛ ተጠሪ ወንድሜ በቀን 21/05/1994 ዓ.ም ከነባር ይዞታው ውስጥ 200 ካ.ሜ ሽጦልኝ እየኖርኩ እያለ 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች ፍቺ በመፈፀማቸው ምክንያት የአመልካችም ቤትና ቦታ በፍ/ቤት የጋራ ሃብት ተብል የተወሰነ ስለሆነ የአመልካችን ቤትና ቦታ 10ሜ x 20ሜ = 200 ካ.ሜ እንዱያስረክቡኝ ይወሰንልኝ በማለት ያቀረቡትን ክስ መነሻ ያደረገ ሲሆን አመልካች በዓዱ ሓቂ ወረደ ፍርድ ቤት ከሳሽ የነበሩ ሲሆን ተጠሪዎች ተከሳሾች ነበሩ።
አመልካች በስር ፍርድ ቤት ባቀረቡት ክስም 1ኛ ተጠሪ ወንድሜ ሲሆን አዋሳኙ በክሱ የተገለፀውን 200 ካ.ሜ በቀን 21/05/1994 ዓ.ም በብር 2,500.00 በቤተዘመድ ሽማግላዎች ፉት በጽሁፍ የሸጠልኝ ሲሆን 1ኛ ተጠሪ ወንድሜ በመሆኑ በእምነት እየኖርኩ እያለሁ ለኔ የሸጠልኝ ቤትና ቦታ ከራሱ ጋር ጨምሮ ጠቅላላ 20x20 = 400 ካ.ሜ በከተማ ማስፊፊት ምክንያት ወደ መቐለ ስለገባ በስሙ እንዱጠና ከተደረገ በኋላ 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪ ጋብቻ በመፈፀም አንድ ላይ እየኖሩ እያለ በመካከላቸው በተፈጠረ አለመግባባት ፍቺ ፈጽመው የንብረት ክፍፍል እንዱያድርጉ ሲወሰን የ1ኛ ተጠሪ ቤትና ቦታ እንዱሁም የአመልካች ቤትና ቦታ ጨምሮ የጋራ ሃብት ተብል የተወሰነ መሆኑን በዚህ ሳምንት የሰማሁ በመሆኑ 1ኛ ተጠሪ የሸጠልኝ ቤትና ቦታ 10x20 ካ.ሜ እንዱያስረክበኝ ወይም 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች ከ400 ካ.ሜ ውስጥ የ1ኛ ተጠሪ ድርሻ 10x20 = 200 ካ.ሜ ለአመልካች ይገባል ተብል ይወሰንልኝ በማለት አመልክተዋል።
ተጠሪዎች በተናጠል በሰጡት መልስም 1ኛ ተጠሪ በክሱ አዋሳኝ እና ስፊቱ የተገለፀው ቤትና ቦታ የ1ኛ ተጠሪ እና የ2ኛ ተጠሪ የጋራ ሃብትና ንብረት ሆኖ እያለ ለብቻዬ ከባለቤቴ እውቅና ውጭ እና ያላመነችበትን ለአመልካች በብር 2,500.00 ብር ሽጬላት ነበር ነገር ግን ስሕተት መሆኑን በማመን ገንዘቡን ለአመልካች በቀን 07/10/2008 ዓ.ም ከወንድሜ አቶ ወ/ገብርኤል መኮንን ተቀብዬ በአምስት ምስክሮች ፉት መልሼላታለሁ። ቤትና ቦታውም በፍርድ ያለቀ እና ሸጠን የተካፈልነው ስለሆነ ልጠየቅበት አይገባም በማለት መልስ ሰጥተዋል።
2ኛ ተጠሪ በበኩላችው በሰጡት መልስም 1ኛ ተጠሪ እና አመልካች ወንድምና እህት በመሆናቸው 2ኛ ተጠሪን ለማጉላላት እያደረጉ ያለት ሴራ እንጂ ከጋራ ሃብታችን 400 ካ.ሜ ውስጥ አንድ ክፍል የያዘ ቤት እንደሸጠላቸው አላውቅም አልጠየቅበትም። ሆኖም ግን አመልካች የ1ኛ ተጠሪ እህት ሲሆኑ እኔ እና 1ኛ ተጠሪ ከማህበራዊ ፍ/ቤት ጀምሮ እስከ ፋደራል ሰበር ችልት በዚህ የጋራ ሃብት ስንከራከር የእውነት ቢሆን ኖሮ በዋና ጉዲያችን ከውሳኔ በኋላ ይሁን ወይም በአፈፃፀም ወቅት በሕጉ ጣልቃ ገብተው በተከራከሩ ነበር ስለሆነም ክሱ አግባብነት ስለላለው ውድቅ እንዱደረግ በማለት ተከራክረዋል።
የዓዱ ሓቂ ወረደ ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ምስክሮች ሰምቶ ተገቢውን ማጣራት አድርጎ በሰጠው ውሳኔም በአመልካች እና በ1ኛ ተጠሪ መካከል በሕግ የሚፀና የሽያጭ ውል ሳይኖር አመልካች በተጠሪዎች ላይ ያቀረቡት ክስ በአግባቡ አይደለም።ተጠሪዎች እንዱያስረክቧቸው የሚወሰን ቤትና ቦታ የለም በማለት እና 1ኛ ተጠሪ ከአመልካች ገንዘብ ተቀብለው የሸጡላቸው የነበረው ቦታ ውል አፍርሰው ቦታቸውን ስለወሰደ ብር 2,500.00 ለአመልካች እንዱመልሱ በማለት ወስኗል።
ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የመቐለ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በበኩለ የዓዱ ሓቂ ወረደ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ የሚነቀፍበት ነጥብ አልተገኘም በማለት በፍ/ስ/ስ/ሕ/ቁ 337 መሰረት የይግባኝ ባይ ቅሬታውን በመሰረዝ የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ አጽንቷል።የክልለ ሰበር ሰሚ ችልትም የመቐለ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት አልተገኘበትም በማለት የቀረበውን የሰበር አቤቱታ በፍ/ስ/ስ/ሕ/ቁ 337 መሰረት ሰርዞታል።
አመልካች ባቀረቡት የሰበር አቤቱታም የወረዲ ፍ/ቤት ለውሳኔው መነሻ ያደረገው በአመልካችና በ1ኛ ተጠሪ መሀል የተፈፀመ የቦታና ቤት ሽያጭ ውል፤ ውል ለማጽደቅ ስልጣን ባለው አካል ፉት ቀርቦ አልፀደቀም የሚል ሲሆን የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1723 እና 1815 መሰረት በማድረግ ውለ በሕግ ፉት የፀና አይደለም በሚል ክሴን ውድቅ ማድረጉ ወረዲ ፍ/ቤት በፍርድ ሐተታው ላይ 1ኛ ተጠሪ ከአመልካች ጋር ያደረገው የቦታ እና ቤት ሸያጭ ውል መኖሩን አልካደም አምኗል ሲል ሓተታው ላይ ካሰፈረው ጋር ሲታይ እርስ በርሱ የሚጋጭ ከመሆኑም በላይ የፍደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በቅጽ 13 በሰ/መ/ በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ ያሽያጭ ውል መኖሩን በማመን ነገር ግን በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1723 መሰረት ውል ለማፅደቅ ስልጣን ባለው አካል ፉት ቀርቦ አልፀደቀም በሚል ክርክር የቀረበው ክስ ተቀባይነት የለውም ልባል እንደማይገባው የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1723(1) ፤ 2878 በማያያዝ አስገዲጅ የሕግ ትርጉም የሰጠበት በመሆኑ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ከዚህ አስገዲጅ የህግ ትርጉም የሚቃረን ከመሆኑም በላይ 1ኛ ተጠሪ ያቀረበው ክርክር ከአመልካች ጋር የቦታና ቤት ሽያጭ ውል እንደነበራቸው አምኖ ነገር ግን ውለ ፈርሶ ገንዘቡን መልሼላታለሁ ሲል የተከራከረው ውለ ፈርሶ ገንዘቧን መመለሱን በማስረጃ ያልተረጋገጠ ሆኖ እያለ ወረዲ ፍ/ቤት ውለ በሚመለከተው አካል አልፀደቀም በሚል ክሴን ውድቅ ማድረጉ እና ጉዲዪን በይግባኝ የቀረበላቸው ፍ/ቤቶችም ስሕተቱን ያለማረማቸው መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈፀመበት በመሆኑ ውሳኔያቸው ተሽሮ ዲኝነት የጠየኩት 200 ካ.ሜ እንዱያስረክቡኝ እንዱወሰንልኝ በማለት አመልክተዋል።
አከራካሪ የሆነው የቤት ሽያጭ ውል በአመልካችና በተጠሪ መካከል መደረጉን ባልተካካደበት ሁኔታ ውለ በሚመለከተው አካል ዘንድ አልተመዘገበም በማለት ውለ ይፍረስ ተብል በስር ፍ/ቤቶች የተወሰነበት አግባብነት ለማጣራት የሰበር አቤቱታው ያስቀርባል ከተባለ በኋላ 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች መጥሪያ ደርሷቸው መልሳቸውን አቅርበዋል።
1ኛ ተጠሪ በሰጡት መልስም በአመልካች እና በ1ኛ ተጠሪ መካከል በ21/5/1994 ዓ.ም 200 ካ.ሜ በብር 2,500 ብር ቤትና ቦታ ለመሸጥ ቦታው ገና ወደ ከተማ ከመካለለ በፉት በገጠር እያለ በመንደር ውል መስማማታችን የማይካድ ነው። ስለሆነም የሽያጭ ውለ በሚፈፀምበት ጊዜ 1994 ቦታው በወቅቱ በገጠር ይተዲደር እንደነበረና 1ኛ ተጠሪ ለአመልካች የሸጥኩላቸው ቤትና ቦታ ከመነሻውም መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የነበረበትና የገጠር ጥሻ ቦታ ተቆርጦ የተሸጠ በመሆኑ አካባቢው ወደ ከተማ ሲካለል አመልካች ከገጠር ወደ ከተማ ቦታው ርክክብ ሲደረግ በአመልካች ስም ተመዝግቦ ከገጠር ወደ ከተማ ሉተላለፍ አልቻለም። ይህም በገጠር የመሬት አስተዲደር እና አጠቃቀም እንዱሁም በሀገራችን ሕገ መንግስት አንቀጽ 40 የአርሶ አደር ቤት መሸጥ መለወጥ እንደማይቻል የፋ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችልት በተለያዪ ጊዜያትና መዛግብት አስገዲጅ የሕግ ትርጉም የሰጠባቸው ናቸው። ስለሆነም የሽያጭ ውል መኖሩ ባይካድም ተፈፀመ የተባለው ውል ከሕግ ውጭና ቮይድ በሆነ ውል ስለነበረ 1ኛ ተጠሪ በዚህ ከሕግ ውጭ ተፈፀመ በተባለው የሽያጭ ውል የምገደድበት ምክንያት የለም። አመልካች ቦታው በ1ኛ ተጠሪ ስም እኔ በማላውቀው ሁኔታ እንዱጠና አድርገዋል የሚለት አመልካች ውለ ትክክል ነበር ቢለ ጥናቱ ተከታትለው ማስጠናት የነበራባቸው ራሳቸው እንጂ 1ኛ ተጠሪ እንዱጠና አላደረገም የሚለት አግባብነትና የሕግ መሰረት የላለው በመሆኑ አቤቱታው ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
2ኛ ተጠሪ በበኩላቸው 1ኛ ተጠሪ ምንም እንኳን 200 ካ.ሜ መሸጡን ባይገልጽም ቤትና ቦታው የጋራ ሃብት ነው ተብል ከስር ፍ/ቤት ጀምሮ እስከ ፋደራል ሰበር ድረስ ከ1ኛ ተጠሪ ጋር በነበረን ክርክር ባለቤቴ አይደለችም ቦታው ወደድኩሽ ወደድኩህ ከመባባላችን በፉት የተፈራ ሃብት ነው ብል ክርክር በማንሳቱ ምክንያት ተከራክረን ቤትና ቦታው የጋራ ሃብት መሆኑን በፋደራል ደረጀ የተወሰነ ቢሆንም 1ኛ ተጠሪ እኔ በማላውቀውና በሽያጭ ውለ ላይ ባልፈረምኩበትና ባልተስማማሁበት ሁኔታ 2ኛ ተጠሪ በኃላፉነት የምጠየቅበት የሕግ ምክንያት የለም።የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1723 መሰረት ውለ በሕጋዊ አካል አለመመዝገቡ እኔን 2ኛ ተጠሪ በመንደር ውል ባላወኩትና ባላመንኩበት የምገደድበት የሕግ ምክንያት የለም። በዚህ ደረጃም ለክርክር መነሻ የሆነው ቤትና ቦታው በሽያጭ ወደ ሶስተኛ ወገን በቀን 12/03/2011 ዓም ለአቶ ኃይላይ ገ/ዪሃንስ ለተባለው በሽያጭ ተላልፎል።ስለሆነም የአመልካች አቤቱታ ውድቅ በማድረግ በነፃ እንዱያሰናብተኝ በማለት ተከራክረዋል። አመልካች የመልስ መልሳቸውን በማቅረብ ክርክራቸውን አጠናክረዋል።
በአጠቃላይ የግራ ቀኙ ክርክር ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም የሰበር ክርክሩን ያስቀርባል ከተባለበት ነጥብ፣ ከተገቢው ህግና፤ከስር ፍርድ ቤት ክርክር አንፃር እንደሚከተለው መርምረነዋል።አመልካች ክርክር የተነሳበትን ይዞታ ከ1ኛ ተጠሪ ገዛን የሚለት ጥር 21 ቀን 1994 ዓ.ም በተደረገ የሽያጭ ውል ሲሆን ይህንን ይዞታ ሲገዙት በቦታው ላይ አንድ ክፍል ቤት የነበረው መሆኑን ገልፀው ከመከራከራቸው በተጨማሪ ይህንን ቦታ ሲገዙ ይዞታው ከተማ ክልል ያልገባ መሆኑን በሚያመለክት መልኩ …ይዞታው በከተማ መስፊፊት ምክንያት ወደ መቐለ ስለገባ…በማለት ገልፀው መከራከራቸው ክርክር የተነሳበት ይዞታ ሽያጭ ተፈፀመ በተባለበት ወቅት የገጠር መሬት መሆኑን ያሳያል።
ክርክር ያስነሳው ይዞታ የገጠር መሬት ከሆነ ደግሞ ሽያጩ በተከናወነበት ጊዜ ተፈፃሚነት ያላቸውን የክልለን የገጠር መሬት አጠቃቀም ለመወሰን የወጡትን አዋጆች ስንመረምራቸው አዋጅ ቁጥር 23/1989 በአንቀፅ 5 የገጠር መሬትን መሸጥ የተከለከለ መሆኑ መመልከቱ ፤ይህንን አዋጅ ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር 55/1994 አንቀፅ 21(1) ይህንን ተላላፍ ሽያጭ ማከናወን የወንጀል ሀላፉነትን የሚያስከትል መሆኑ መመልከቱ፤ በአሁኑ ወቅት ተግባራዊነት ባለው አዋጅ ቁጥር 239/2006 ተመሳሳዩ ክልከላ መቀመጡ በገጠር እርሻ መሬት ላይ ቤት ይኑርበትም አይኑርበትም በሽያጭ ማስተላለፍ የተከለከለ መሆኑን ያሳያል።
በዚህ ጉዲይ ላይ አመልካች ክርክር የተነሳበትን ይዞታ አንድ ክፍል ቤት ያረፈበትን በሽያጭ እንደገዙት በፍሬ ነገር የተረጋገጠ ጉዲይ ቢሆንም ከላይ እንደተመለከተው የገጠር መሬትን በሽያጭ ማስተላለፍ በህግ ክልከላ የተጣለበት በመሆኑ የስር ፍርድ ቤቶች አመልካች ያቀረቡትን የይዞታ ልረከብ የዲኝነት ጥያቄ የሽያጭ ውለ ከመጀመሪያውኑ ህጉን ያልተከተለ ህገ ወጥ ስለሆነ ይዞታውን ለመረከብ ያቀረቡት የዲኝነት ጥያቄ ተገቢነት የለውም በማለት መወሰኑ እና በየደረጃው ያለ ፍርድ ቤቶች ይህንኑ ውሳኔ ማፅናታቸው የህገ መንግስቱን አንቀፅ 40(3) እና አግባብነት ያላቸውን የክልለን ህጎች መሰረት ያደረገ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያልተፈፀመበት ነው ብለናል። ስለሆነም ተከታዪን ውሳኔ ሰጥተናል።
የዓዱ ሓቂ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 05101 በ07/08/2011 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ፍርድ ፤ የመቐለ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 27544 በ28/10/2011 ዓ.ም በዋለው ችልት ይህንን ፍርድ በማፅናት የሰጠው ትዕዛዝ እና የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ በቀን 13/01/2012 ዓ.ም የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈፀመበት አይደለም በማለት የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ.348(1) መሰረት ፀንቷል።
ግራ ቀኙ በሰበር ክርክሩ ምክንያት ያወጡትን ወጪና ኪሳራ ይቻቻለ።
የግራ ቀኙ ክርክር ተገቢውን እልባት ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቷል።ይመለስ።