የገጠር መሬት በዉርስ እንዱተላለፍ ዲኝነት የሚቀርብበትን የጊዜ ገደብ በተመለከተ የተለየ የህግ ድንጋጌ በላለ ጊዜ ክርክሩ በወራሾች መካከል ሲሆን በእርሻ መሬት የዉርስ ጥያቄ ላይ ለጉዲዩ ተፈፃሚነት ያለዉ የይርጋ ደንብ ጠቅላላ የ10 አመት የይርጋ ጊዜ ሳይሆን በፍትሐ ብሓር ህጉ አንቀጽ 1000(1) ላይ የተደነገገው የ 3 አመት የይርጋ ጊዜ ስለመሆኑ የአማራ ክልል የገጠር መሬት አስተዲደር እና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 252/2009
No summary available.
መጋቢት 29 ቀን 2013 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሀኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሀኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካቾች፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ ከገጠር መሬት ጋር በተያያዘ የሚቀርብ የውርስ ጥያቄ ላይ ተፈፃሚ የሚሆነውን የይርጋ ደንብ የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በተጀመረበት አማራ ክልል ቡሬ ወረዲ ፍርድ ቤት አመልካቾች ከሳሽ፣ ተጠሪዎች ደግሞ ከላልች አራት ግለሰቦች ጋር ተከሳሾች በመሆን ተከራክረዋል። አመልካቾች በቀን 08/07/2009 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት ክስ ሟች አያታችን በ1989 ዓ.ም በድልድል ያገኙት፣ እኛም ከአባታችን ጋር እንደልጅና ቤተሰብ የተቆጥርንበትን 13 ገመድ የውርስ መሬት ተከሳሾች በተለያየ መጠን ተከፊፍለው በመያዝ እየተጠቀሙበት በመሆኑ ለቀው ያስረክቡን በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል።
ተጠሪዎች በበኩላቸው በሰጡት መልስ አባታችን (የአመልካቾች አያት) የሞተው በ1997 ዓ.ም ሲሆን አመልካቾች ደግሞ የወራሽነት ማረጋገጫ ያወጡት በ2009 ዓ.ም ስለሆነ ክሱ በይርጋ ይታገዲል በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያቀረቡ ሲሆን በፍሬ ነገሩ ደረጃም የአማራጭ መልስ ሰጥተው ተከራክረዋል።
የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ የሰማው የወረዲው ፍርድ ቤት የተጠሪዎችን የይርጋ መቃወሚያ ውድቅ በማድረግ ከስር 1ኛ ተከሳሽ ውጭ ያለት ተከሳሾች በሙለ የያዟቸውን መሬቶች በመልቀቅ ለአመልካቾች ያስረክቡ በማለት ወስኗል። በዚህ ውሳኔ ቅር የተሰኙት ተጠሪዎች የይግባኝ አቤቱታ ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል። በመቀጠል ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰበር አቤቱታቸውን ያቀረቡ ሲሆን ችልቱም በአቤቱታው ላይ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ ተጠሪዎች መሬቱን ከ2001 ዓ.ም ጀምረው እንደያዙት በማስረጃ ተረጋግጧል፤
አከራካሪውን መሬት በሚመለከት ግራ ቀኙ ወራሽ ሲሆኑ በወራሾች መካከል ለሚነሳ ክርክር ተፈፃሚነት ባለው በፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 1000(1) መሰረት ሶስት ዓመት ጊዜ ስለሆነና አመልካቾች ክሳቸውን ያቀረቡት ተጠሪዎች መሬቱን ከያዙ ከሶስት ዓመት በኋላ በመሆኑ ክሱ በይርጋ ይታገዲል በማለት የወረዲው እና የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች የሰጡትን ውሳኔ ሽሮታል። ለዚህ ፍርድ መነሻ የሆነው የሰበር አቤቱታ የቀረበው ይህንኑ ለማስለወጥ ነው።
አመልካቾች በቀን 10/04/2012 ዓ.ም በተፃፈ 03 ገጽ የሰበር አቤቱታ በስር ፍርድ ቤቶች ተፈፅመዋል ያሎቸውን ስህተቶች በመዘርዘር በዚህ ችልት እንዱታረሙላቸው ጠይቀዋል። የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ ይዘት በአጭሩ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ተጠሪዎች ወራሽ ነን ሳይለ፣ እንዱሁም የወራሽነት ማስረጃ ባላቀረቡበት ያልተነሳን የውርስ ይርጋ ክርክር እራሱ በማንሳት ክሱ በይርጋ ይታገዲል በማለት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባዋል የሚል ነው። የሰበር አቤቱታዉ በአጣሪ ችልት ተመርምሮም በፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 1000(1) ላይ የተመለከተዉ የሦስት ዓመት የይርጋ ደንብ በእርሻ መሬት የዉርስ ጥያቄ ላይ ተፈፃሚነት ያለዉ መሆን አለመሆኑን አጣርቶ ለመወሰን ሲባል ያስቀርባል ብሎል። ተጠሪዎች በጉዲዩ ላይ መልስ እንዱሰጡ በሚል መጥሪያ የተላከላቸው ቢሆንም ባለመቅረባቸዉ መልስ የማቅረብ መብታቸዉ ታልፎል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀውን ሲመስል ይህ ችልትም በሰበር አጣሪ ችልት የተያዘዉን ጭብጥ ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸዉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መዝገቡን እንደሚከተለዉ መርምሮታል። እንደመረመረዉም አዉራሽ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት በ1997 ዓ.ም ሲሆን ተጠሪዎች ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን መሬት የያዙት በ2001 ዓ.ም መሆኑ ስለመረጋገጡ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ዉሳኔ ይዘት የሚያሳይ ሲሆን፣ አመልካቾች ይህን ፍሬ ነገር በመካድ አይከራከሩም። ክርክሩ በወራሾች መካከል ስለመሆኑም የታመነ ነዉ። አመልካቾች ተጠሪዎች ይርጋ መቃወሚያ አላነሱም በማለት የሚከራከሩ ቢሆንም፣ ተጠሪዎች ክሱ በይርጋ እንደሚታገድ የመጀመሪያ መቃወሚያ ያነሱ ስለመሆኑ የወረዲዉ ፍርድ ቤት በቀን 22/06/2010 ዓ.ም በዋለዉ ችልት ከሰጠዉ ብይን ይዘት ለመገንዘብ የሚቻል ሲሆን፣ የወረዲዉ ፍርድ ቤት የይርጋ መቃወሚያን ዉድቅ ያደረገዉ ተጠሪዎች መሬቱን ከያዙት 10 ዓመት ያልሞላዉ መሆኑን ነዉ። በአንፃሩ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ክሱ በይርጋ ይታገዲል በሚል ድምዲሜ ላይ የደረሰዉ ለጉዲዩ ተፈፃሚነት ያለዉ ይርጋ በፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 1000(1) ላይ የተመለከተዉ የሦስት ዓመት ጊዜ መሆኑን በመጥቀስ ነዉ። በመሆኑም ከዉርስ ይርጋ ጋር በተያያዘ በፍትሐብሕር ህጉ ላይ የተመለከቱት ድንጋጌዎች ተፈፃሚነት አላቸዉ ወይ የሚለዉን ነጥብ በሰበር አጣሪ ችልት ከተያዘዉ ጭብጥ አንፃር መመርመሩ ተገቢ ሆኖ ተገኝቷል።
ምንም እንኳ አሁን በአገራችን በስራ ላይ ባለዉ የመሬት ስሪት መሰረት መሬት የህዝብ እና የመንግስት በመሆኑ እንዱሁም መሬት የእራሱ የሆነ የተለየ ባህርይ ያለዉ ቢሆንም፤ ከመሬት ጋር በተያያዘ የሚፈጠሩ መብቶች እና ግዳታዎች፣ ግንኙነቶች የሚመሩት በንብረት ህግ አጠቃላይ መርሆዎች በመሆኑ የከተማም ሆነ የገጠር መሬት አስተዲደር እና አጠቃቀምን አስመልክቶ የሚወጡ ህጎች/አዋጆች በንብረት ህግ ማዕቀፍ ዉስጥ የሚመደቡ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል። ስለሆነም ከንብረት ጋር በተገናኘ ያለ ጽንሰ ሃሳቦች፣ ህጎች እና መርሆዎች ከመሬት ጋር በተያያዘ ለሚቀርብ ክርክር እንደየአግባብነታቸዉ ተፈፃሚነት ይኖራቸዋል። በጽንሰ ሃሳብ ደረጃ የንብረት ህግ ማለት ለአንድ ንብረት ባለመብት ወይም ባለይዞታ የሆነ ሰዉ ከላልች ሰዎች ጋር የሚኖረዉን ግንኙነት የሚገዛ ነዉ።
የንብረት ህግ አንድ ሰዉ በአንድ ንብረት ላይ ባለቤትነት ወይም ባለይዞታ ላሆን የሚቻልበትን መንገድ፤
የመብቱ ዓይነት፣ ስፊት እና ማዕቀፍ፤ መብቱ ከአንደ ወደ ላላ ሉተላለፍ የሚችልበትን ሥርዓት የሚደነግግ የህግ ክፍል ነዉ። ንብረትን የመከታተል መብት፣ በመብቱ ማዕቀፍ ያለ ማንም ጣልቃ ገብነት የመጠቀም መብት እንዱሁም ክስ አቅርቦ መብትን የማስከበር መብት የንብረት ባለ ሀብት ወይም ባለይዞታ መሆን ከሚሰጣቸዉ መብቶች ዉስጥ ዋነኞቹ ናቸዉ።
አንድ ሰዉ የአንድ ንብረት ባለመብት ወይም ባለይዞታ መሆኑ የሚታወቀዉ እና የንብረት ባለ ሀብት ወይም ባለይዞታ መሆን በሚሰጣቸዉ መብቶች ተጠቃሚ ላሆን የሚችለዉ ንብረቱን በህግ አግባብ በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ በእጁ ካደረገበት ጊዜ ጀምሮ ስለመሆኑም ከአጠቃላይ የንብረት ህግ ጽንሰ ሃሳብ የምንገነዘበዉ ነዉ። ስለሆነም አንድን ንብረት አስመልክቶ የሚቀርበዉን ክስ ተከትል ንብረትን የሚመለከት የህግ ክፍል ተፈፃሚ የሚሆነዉ ከሳሽ ክሱን ያቀረበዉ ንብረቱን በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ በእጁ ካደረገ በኋላ በንብረቱ ላይ ያለዉ መብት እንዱከበርለት የቀረበ ክስ መሆኑ በክሱ የተረጋገጠ ሲሆን ነዉ። ይህም ማለት አንድ ከሳሽ ባቀረበዉ ክስ የጠየቀዉ ዲኝነት ንብረትን የሚመለከት መሆኑ ብቻዉን ጉዲዩን የንብረት ክርክር አያደርገዉም ማለት ነዉ። በአጠቃላይ ንብረትን የሚመለከት ለፍርድ ቤት የሚቀርብ ዲኝነት ሁለት ገጽታዎች ያለት ሲሆን አንደኛዉ የንብረት ባለሀብትነት ወይም ባለይዞታነትን ወይም ከንብረቱ ጋር በተያያዘ ያለዉን ማንኛዉንም መብት ለማስከበር የሚቀርብ ዲኝነት ሲሆን፤ ሁለተኛዉ የንብረት ባለቤትነት ወይም ባለይዞታነት መብት በፍርድ ኃይል እንዱተላለፍለት በዚህም የንብረቱ ባለሀብት ወይም ባለይዞታ ለመሆን የሚቀርብ ዲኝነት ነዉ። የመጀመሪያዉ በንብረት ህግ ማዕቀፍ የሚመራ ሲሆን፣ ሁለተኛዉ ዓይነት ለቀረበዉ የመብት ይተላለፍልኝ ጥያቄ መሰረት የሆነዉን ምክንያት መሰረት በማድረግ የሚወሰን ሲሆን እንደየጉዲዩ ባህርይ በተለያዩ የህግ ማዕቀፍች መሰረት የሚዲኝ ነዉ፤ ይህም ማለት ለቀረበዉ የመብት ይተላለፍልኝ ዲኝነት መሰረቱ ዉል ከሆነ የዉል ህግ ድንጋጌዎች፣ ዉርስ ከሆነ የዉርስ ህግ ድንጋጌዎች፣ ጋብቻ መፍረሱን ተከትል የቀረበ ከሆነ የቤተሰብ ህግን መሰረት በማድረግ ላታይ የሚችልበት ሁኔታ ይኖራል ማለት ነዉ። ይህ፣ ከፍ ሲል በተመለከተዉ ምክንያት፣ ከመሬት ጋር የተያያዘ ለሚቀርቡ የመብት ጥያቄዎችም እንደየአግባብነታቸዉ ተፈፃሚነት ይኖራቸዋል።
ከዚህ አንጻር የተያዘዉን ጉዲይ ስንመለከት አመልካቾች ያቀረቡት ክስ ይዞታችን ያላግባብ ተይዟል በሚል ሳይሆን ተጠሪዎች በዉርስ በእጃቸዉ ካስገቡት መሬት ዉስጥ የዉርስ ድርሻቸዉን እንዱለቁላቸዉ ነዉ። ይህም የአመልካቾች የባለይዞታነት መብት ይገባናል ጥያቄ ዉርስን መሰረት ያደረገ ሆኖ በፍርድ ኃይል በዉርስ በሚተላለፍላቸዉ ይዞታ ላይ ባለመብት ለመሆን ያቀረቡት ክስ መሆኑን የሚያሳይ ነዉ። የክልለ የገጠር መሬት አስተዲደር እና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 252/2009ም ሆነ ከእርሱ በፉት የነበረዉ አዋጅ ቁጥር 133/98 የገጠር መሬት በዉርስ የሚተላፍባቸዉን ሁኔታዎች በተመለከተ የተለየ ድንጋጌ ቢኖራቸዉም፣ የገጠር መሬት በዉርስ እንዱተላለፍ ዲኝነት የሚቀርብበትን የጊዜ ገደብ በተመለከተ የተለየ ድንጋጌ የላቸዉም። በአዋጅ ቁጥር 252/2009 አንቀጽ 55 ላይ የተመለከተዉ የይርጋ ደንብም ቢሆን ያላግባብ የተያዘን የገጠር መሬት ለማስለቀቅ ለሚቀርብ የዲኝነት ጥያቄ እንጂ (ይህ የይርጋ ደንብ ይዞታዬ ያላግባብ ተይዟል በሚል ለሚቀርቡ ለሁለም ጉዲዮች ተፈፃሚነት አለዉ ወይ? የሚለዉ ጥያቄ እንደተጠበቀ ሆኖ) የባለ ይዞታነት መብት ይተላለፍልኝ በሚል ዉርስን መሰረት በማድረግ ለሚቀርብ ክስ ተፈፃሚነት ያለዉ አይደለም። ስለሆነም አመልካች ያቀረቡት የዉርስ ድርሻ ይገባኛል ጥያቄን በተመለከተ ተፈፃሚነት ያለዉ ህግ በፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 1000 ላይ የተመለከተዉ የይርጋ ድንጋጌ እንጂ ከይዞታ ክርክር ጋር በተያያዘ ለሚቀርብ ክስ የተመለከተዉ የአዋጅ ቁጥር 252/2009 አንቀጽ 55 ላይ የተመለከተዉ ድንጋጌ ላሆን አይገባም። ከዚህ አንፃር ሲታይ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የፍትሐብሕር ህጉን አንቀጽ 1000(1) ላይ የተመለከተዉን ድንጋጌ በዋቢነት በመጥቀስ የአመልካች ክስ በይርጋ ቀሪ ነዉ በማለት የሰጠዉ ዉሳኔ በአግባቡ ነዉ ከሚባል በስተቀር መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አልተገኘም። ስለሆነም ተከታዩ ተወስኗል።
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁጥር 03-78188 በቀን 08/03/2012 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጡት ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 348(1) መሰረት ጸንቷል።
በዚህ ችልት የተደረገዉ ክርክር ያስከተለዉን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን ይቻለ።
No topics extracted.