ለፍርድ ቤቶች የተሰጠው የዲኝነት ሥልጣን ህግን መሰረት ያደረገ የዲኝነት አገልግልት መሰጠት በመሆኑ ይህ ማለት በፍርድ ቤት ለሚሰጠው ማንኛውም ውሳኔ፤ በተለይም መብትን የሚያሳጣ በሆነ ጊዜ ግልፅ የህግ መሰረት ሳይጠቀስ ውሳኔ ከተሰጠ ተቀባይነት የላለው ስለመሆኑ የኢ.ፋ.ዱ.ሪ. ህገ መንግስት አንቀፅ 78 እና 79
No summary available.
የሰ.መ/ ጥቅምት 26/2013 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሳዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡ አቶ ሀፍቱ ኪሮስ ተጠሪ፡ የሀውልቲ ክፍለ ከተማ ማዘጋጃ ቤት **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ ለዚህ ሰበር ችልት ላቀርብ የቻለው በከተማ መስፊፊት ምክንያት የገጠር ይዞታን ይዞ ወደ ከተማ የገባ ሰው በይዞታው ምትክ ሉሰጠው ከሚገባው ይዞታ መጠን በታች በመሰጠቱ ምክንያት የተሰጠውን ይዞታ ተቀብል ከቆየ በኋላ ተቀነሰብኝ በሚለው የይዞታ መጠን ላይ ክስ ለማቅረብ መብት እና ጥቅም የለውም ተብል የተወሰነበትን ህጋዊ አግባብነት መርምሮ ለመወሰን ነው።
ክርክሩ የተጀመረው የአሁን አመልካች በትግራይ ብ/ራዊ ክልላዊ መንግስት በሐውልቲ ወረዲ ፍ/ቤት በአሁን ተጠሪ ላይ ባቀረቡት ክስ ነው። የክሱ ይዘትም በከተማ መስፊፊት ምክንያት ቀደም ሲል ለጎጆ መውጫ ተብል በህጋዊ መንገድ የተሰጣቸውን 400 ካሬ ሜትር ይዞታ ይዘው ወደ ከተማ መካለላቸውን፤ ይህ ቦታ ለመሰረተ ልማት ይፈለጋል በሚል እንዱነሱ ተደርጎ በምትኩ 400 ካ.ሜ ሉሰጣቸው ሲገባ 140 ካ.ሜ ብቻ የተሰጣቸው መሆኑን በመግለፅ ያለአግባብ የተቀነሰባቸው 260 ካሬ ሜትር እንዱሰጣቸው ዲኝነት የሚጠይቅ ነው።
የአሁን ተጠሪ ለዚሁ ክስ በሰጠው መልስ አመልካች በምትክነት የተሰጣቸው 140 ካሬ ሜትር ይዞታ ተቀብለው አቶ ኪሮስ ገ/መስቀል ለተባለት ግለሰብ የሸጡ በመሆኑ እና በተጠሪ ጽ/ቤትም ምንም ዓይነት ማህደር የላላቸው በመሆኑ ክስ ለማቅረብ የሚያስችላችው መብት እና ጥቅም የላቸውም የሚል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያን በማቅረብ ተከራክሯል።
ክሱ የቀረበለት ፍርድ ቤትም በመቃወሚያው ላይ የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ አመልካች በምትክነት የተሰጣቸውን ይዞታ ሸጠው ይዞታውን የሚመለከቱ ሰነድችንም ለላላ ሰው ካስተላለፈ በኋላ ቀረኝ ባለት ቦታ ላይ ክስ ለማቅረብ የሚያስችላቸው መብት እና ጥቅም የላላቸው በመሆኑ ክሱ የክስ ምክንያት የለውም በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 33(2) መሰረት በብይን ዘግቷል።
በዚሁ ጉዲይ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የክልለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአመልካችን ይግባኝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 337 መሰረት ዘግቷል። የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በበኩለ በመ/ቁ/114270 ላይ የግራ ቀኙን የሰበር ክርክር ሰምቶ ግንቦት 09/2011 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ በከተማ መስፊፊት ምክንያት አመልካች 400 ካሬ ሜትር ይዞታ ይዘው ወደ ከተማ መጠቃለላቸው በአሁን ተጠሪም ያልተካደ መሆኑን፤ ይህ ይዞታ በልማት ምክንያት ከአመልካች በመወሰደ ምክንያት በ2005 ዓ.ም ለአመልካች 140 ካሬ ሜትር ምትክ ቦታ የተሰጣቸው መሆኑን፤
ለአመልካች ምትክ ቦታ በተሰጠበት ጊዜ ለጉዲዩ አግባብነት ያለው በ2003 ዓ.ም የወጣው መመሪያ መሆኑን፤ በዚህ መመሪያ መሰረት በልማት ምክንያት ይዞታው ለተወሰደበት ሰው ከከፍተኛው የከተማ ይዞታ መጠን እስካልበለጠ ድረስ በተወሰደው ይዞታ መጠን ምትክ ቦታ የሚሰጠው መሆኑን፤ በእለቱ ለአመልካች 400 ካሬ ሜትር ምትክ ቦታ ሉሰጣቸው ሲገባ 140 ካሬ ሜትር ሲሰጣቸው አመልካች የተሰጣቸውን ተቀብለው ለላላ ሰው አሳልፈው የሸጡ መሆኑን፤ አመልካች በዚህ መልኩ ተቀንሶ የተሰጣቸውን ይዞታ ተቀብለው ከ5 ዓመት በኋላ የተቀነሰብኝ ይዞታ ይሰጠኝ በሚል ያቀረቡት ክስ ቀድሞውኑ ቢሆን ቀረኝ ያለት ይዞታ የማይገባቸው መሆኑን መቀበላቸውን የሚያሳይ በመሆኑ ከዚህ ያክል ቆይታ በኋላ ተቀነሰብኝ በሚለው ምትክ ቦታ ላይ ክስ ለማቅረብ የሚያስችላቸው መብት እና ጥቅም የላቸውም በማለት የስር ፍርድ ቤቶችን ብይን እና ትዕዛዝ በምክንያት በማጠናከር አፅንቷል።
የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ነው። አመልካች ሰኔ 15/2011 ዓ.ም ፅፈው ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ በስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ላይ ተፈፅሟል ያለትን መሰረታዊ የህግ ስህተት ጠቅሰው በዚህ ችልት እንዱታረምላቸው ጠይቀዋል። ፍሬ ቃለም አመልካች የነበራቸው ነባር ይዞታ 400 ካ.ሜ መሆኑን በምትክ የተሰጣቸው ደግሞ 140 ካሬ ሜትር ብቻ ስለመሆኑ በተጠሪም ጭምር ያልተካደ መሆኑን፤ ቀድሞ የተሰጣቸውን 140 ካ.ሜ ለላላ ሰው በማስተላለፊቸው ምክንያት ቀሪውን ሉጠይቁ አይገባም መባለ ንብረታቸውን መሸጥ ህገ-መንግስታዊ መብታቸውን የሚፃረር በመሆኑ አግባብ እንዲልሆነ፤ ክስ ያቀረቡትም ያላግባብ የቀረባቸውን 260 ካ.ሜ በሚመለከት እንጂ በሽያጭ ባስተላለፈት ንብረት ላይ ባለመሆኑ የተሸጠውን ንብረት የሚመለከተው ሰነድ ለላላ ሰው በመተላለፈ ምክንያት ማህደር የላችውም ልባል እንደማይገባ፤ ለአቶ ኪሮስ ገ/መስቀል ከተላለፈው ሰነድ ላይ አመልካች 400 ካ.ሜ እንደነበራቸው የሚያስረዲ መሆኑን በመግለፅ የስር ፍ/ቤቶች እነዚህን ሁኔታዎች አልፈው ክሳቸውን ውድቅ ማድረጋቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት በመሆኑ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ አመልካች ከገጠር ወደ ከተማ ይዘው የገቡት የይዞታ መጠን 400 ካ.ሜ መሆኑና በዚሁ ይዞታ ምትክ ተለዋጭ 140 ካ.ሜ ይዞታ የተሰጣቸው በ2005 ዓ.ም መሆኑ ያልተካደ ሆኖ እያለ፣ ለጉዲዩ አግባብነት ያለው መመሪያ ቁጥር 2003 ስለመሆኑ የክልለ ሰበር ችልት በተቀበለበት ሁኔታ እና መመሪያ ቁጥር 2003 ምትክ የሚሰጠው የነበረው ይዞታ መጠን የሚል ስለመሆኑ ተጠሪው በክልለ ሰበር ችልት ባቀረበው መልስ በገለፀበት ሁኔታ አመልካች የተሰጣቸውን 140 ካ.ሜ ይዞታ ለላላ ወገን ስላስተላለፈ ቀሪ ይዞታ አለኝ በሚል ክስ ለማቅረብ የሚያስችል መብትና ጥቅም የላቸውም በሚል የተሰጠውን ውሳኔ አግባብነት መጣራት ያለበት መሆኑ ስለታመበት ለዚህ ሰበር ችልት ቀርቦ እንዱታይ በመታዘዙ ግራ ቀኙ የፅሁፍ ክርክር እንዱለዋወጡ ተደርጓል።
ተጠሪ በቀን ታህሳስ 21/2012 ዓ.ም ፅፈው ባቀረቡት መልስ አመልካች ከገጠር ወደ ከተማ ሲገቡ ይዘውት የገቡት የመሬት ስፊት 400 ካ.ሜ መሆኑን፤ በዛን ወቅት በነበረው የልማት ተነሽነት መመሪያ ቁጥር 2002 በአንቀፅ 5 ንዐስ አንቀፅ 5.5 መሰረት ከቦታቸው የሚነሱ ሰዎች የሚሰጣቸው የይዞታ ስፊት 250 ካ.ሜ ያለ ካሳ፤ 140 ካ.ሜ ደግሞ ከካሳ ጋር እንደሆነ የሚደነግግ በመሆኑ ለአመልካች 140 ካ.ሜ ከካሳ ጋር የተሰጣቸው መሆኑንና አመልካች በዚህ ጉዲይ በጊዜው ያቀረቡት ቅሬታ ያልነበር መሆኑን፤ በቦታው አምነውበት ካርታና ሳይት ፕላን ተሰጥቷቸው በ2006 ዓ.ም ለአቶ ኪሮስ ገ/መስቀል የሸጡላቸው መሆኑን፤ በዚህ ምክንያት በአንድ ይዞታ ሁለት ሰነድ እንደማይሰጥ ህጉ የደነገገ በመሆኑ የአመልካች አቤቱታ ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክሯል።
አመልካች በበኩላቸው ጥር 23/2012 ዓ.ም በሰጡት የመልስ መልስ በወቅቱ የነበረው መመሪያ ከገጠር ወደ ከተማ የገባ ቦታ እንደ ስፊቱ መጠን ከ140 እስከ 500 ካ.ሜ መስጠት እንደሚፈቅድ የደነገገ መሆኑን፤ 400 ካ.ሜ ይዞ ወደ ከተማ የገባ ሰው 400 ካ.ሜ እንዱሰጠው ህጉ የደነገገ መሆኑን፤ መመሪያ 2002 የሉዝ መመሪያ ሆኖ የሚያገለግለው ከተማ ውስጥ ለቆየ ቦታ እንጂ ከገጠር ወደ ከተማ ለገባ ቦታ አለመሆኑን፤ የአመልካች ጉዲይ የሚዲኘው በመመሪያ 2003 መሰረት መሆኑን፤ ተጠሪ በመሰረተ ልማት ምክንያት የሚነሱ ከካሳ ጋር ከሆነ 140 ካ.ሜ ያለካሳ ከሆነ 250 ካ.ሜ ነው የሚሰጣቸው በማለት ያቀረበው መልስ ህግን መሰረት ያላደረገ መሆኑንና ህጉ በተወሰደው ቦታ መጠን አስፈላጊም ከሆነ ካሳ ተጨምሮለት ምትክ ቦታ እንዱሰጥ የሚደነገግ መሆኑን፤ የተሰጣቸው ካሳ ካለመኖሩም በላይ ክርክሩ በስር ፈርድ ቤት ያልቀረበ መሆኑን፤
ይዞታውን ለ3ኛ ወገን ሽጠዋል ለሚለውም የተሰጣቸውን 140 ካ.ሜ ሽጠው ቀሪ 260 ካ.ሜ ለመጠየቅ የሚከለክላቸው ህግ አለመኖሩን በመግለፅ በቀረበው ቅሬታ መሰረት ሉወሰንልኝ ይገባል ሲለ ሞግተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክር ይዘት ጠቅለል ባለ መልኩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ችልቱም ጉዲዩ ለዚህ ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ነጥብ አኳይ የግራ ቀኙን ክርክር አግባብነት ካለው ህግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምሯል።
ከክርክሩ ይዘት በግልፅ መረዲት እንደሚቻለው አመልካች ክስ ያቀረቡት በልማት ምክንያት በተወሰደባቸው 400 ካሬ ሜትር ይዞታ ምክት 400 ካሬ ሜትር ቦታ ሉሰጣቸው ሲገባ ከህግ አግባብ ውጭ ተቀንሶብኛል ባለት 260 ካሬ ሜትር ላይ ነው። በእርግጥ ከምትክ ቦታ አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ተፈፃሚነት ባለው መመሪያ ላይ በግራ ቀኙ መካከል ያለመግባባት እንዲለ ከሚያቀርቡት ክርክር መረዲት ይቻላል። ሆኖም የክልለ ሰበር ችልት ለጉዲዩ አግባብነት ያለው በ2003 ዓ.ም.
የወጣው መመሪያ መሆኑን እና በመመሪያው መሰረት ከከፍተኛው የከተማ ይዞታ መጠን እስካላለፈ ድረስ ምትክ ቦታ የሚሰጠው በተወሰደው ይዞታ መጠን ስለመሆኑ ገልጿል። ይህ የሰበር ችልቱ የህግ መረጣ እና አተረጓጎም አግባብ አይደለም በሚል በአሁን ተጠሪ በኩል ሥርዓቱን ጠብቆ የቀረበ የሰበር ቅሬታም ሆነ ግልፅ ክርክር የለም። ይህ በላለበት አሁን ላይ ለጉዲዩ አግባብነት ያለው ላላ የህግ ማዕቀፍ ነው በማለት ተጠሪ የሚያቀርበው መከራከሪያ ሥነ ሥርዓቱን የጠበቀ ባለመሆኑ ችልቱ አልተቀበለውም።
የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ለግራ ቀኙ ክርክር አግባብነት ያለው በ2003 ዓ.ም የወጣው መመሪያ መሆኑን ከለየ በኋላ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔን ያፀናው በመመሪያው መሰረት 400 ካሬ ሜትር ምትክ ቦታ የሚገባህ ቢሆንም መጠኑ ተቀንሶ 140 ካሬ ሜትር ቦታ ብቻ ሲሰጥ ተቀብለህ ከ5 ዓመት ቆይታ በኋላ ቀረኝ ያልከውን ይዞታ ለመጠየቅ መብት የለህም በሚል ነው።
እንግዱህ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ. ህገ መንግስት አንቀፅ 78 እና 79 መሰረት ለፍርድ ቤቶች የተሰጠው የዲኝነት ሥልጣን ህግን መሰረት ያደረገ የዲኝነት አገልግልት መሰጠት ነው። ህግን መሰረት ያደረገ የዲኝነት አገልግልት መስጠት ማለት ፍርድ ቤት ለሚሰጠው ማንኛውም ውሳኔ፤ በተለይም ውሳኔው መብትን የሚያሳጣ በሆነ ጊዜ ግልፅ የህግ መሰረት ሉኖር ይገባል ማለት ነው። ለውሳኔው መሰረት የሆነ ህግ ሳይጠቀስ በደፈናው መብትን የሚያሳጣ ውሳኔ የህግ መሰረት የላለው በመሆኑ ተቀባይነት የለውም።
በልላ በኩል የወረዲው ፍርድ ቤት የአመልካችን ክስ ውድቅ ያደረገው ክሱ የክስ ምክንያት የለውም በሚል በመሆኑ በዚሁ ነጥብ ላይ አንድ ነገር ማለቱ ተገቢ ይሆናል። በእርግጥ የክስ ምክንያት የላለው የክስ አቤቱታ ተቀባይነት የላለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 231(1(ሀ)) ድንጋጌ ያስገነዝባል። አንድ በፍርድ ቤት የቀረበ የክስ አቤቱታ የክስ ምክንያት ያለው መሆን አለመሆኑን ለመለየት ፍርድ ቤቶች በክሱ ላይ የተገለፀው ነገር ቢረጋገጥ ክሱን ያቀረበው ወገን የጠየቀውን ዲኝነት ለማግኘት ህግ የሚፈቅድለት መሆን አለመሆኑን በጥያቄነት ይዘው ሉመረምሩ እና “የክስ ምክንያት አለው!” ለማለት ለተጠየቀው ጥያቄ አዎንታ መልስ ሉኖራቸው እንደሚገባ ይኸው ችልት በሰ/መ/ቁ/45247 ላይ አስገዲጅ የህግ ትርጉም የሰጠ በመሆኑ አመልካች ያቀረቡት ክስም በዚሁ ስላት መሰረት ሉቃኝ ይገባል።
በዚሁ አግባብ አመልካች ያቀረቡት ክስ ከህግ አግባብ ውጭ የተቀነሰብኝ 260 ካሬ ሜትር ምትክ ይዞታ ሉሰጠኝ ይገባል የሚል ነው። ይኽው ፍሬ ነገር ቢረጋገጥ አመልካች የጠየቁትን ዲኝነት እንዲያገኙ የተቀመጠ ግልፅ የህግ ክልከላ የለም። ጉዲዩ ይህ ከሆነ ደግሞ ዲኝነት የተጠየቀበት ጉዲይ ለአመልካች የሚገባቸው መሆን አለመሆኑ በክርክር ሂደት በማስረጃ የሚነጥር ከሚሆን በቀር የክስ አቤቱታው የክስ ምክንያት የለውም ተብል በመጀመሪያው የክርክር ምዕራፍ ውድቅ የሚደረግበት የህግ አግባብ የለም። እናም የወረዲው ፍርድ ቤት የአመልካች ክስ የክስ ምክንያት የለውም ማለቱ እና የክልለ ሰበር ሰሚ ችልትም ምክንያት ጨምሮ ይህንኑ ማፅናቱ ሉታረም የሚገባው መሰረታዊ የህግ አረዲድ እና አተገባበር ስህተት ሆኖ ተገኝቷል። ሲጠቃለል ይህንን ጉዲይ በተመለከተ ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
የትግራይ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ/114270 ላይ ግንቦት 09/2011 የሰጠው ውሳኔ፤ የመቀላ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/26177 ላይ የካቲት 05/2011 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ እና የሐውልቲ ክ/ከተማ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/010931 ላይ ታህሳስ 05/2011 ዓ.ም የሰጠው ብይን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽረዋል።
የሐውልቲ ክ/ከተማ ፍርድ ቤት በብይን የዘጋውን መዝገብ በማንቀሳቀስ በክሱ ሥረ ነገር ክርክር ላይ የግራ ቀኙን ክርክር እና የተጠቀሰ ማስረጃም ካለ በመስማት የመሰለውን እንዱወስን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 341(1) መሰረት ጉዲዩ ይመለስለት።
የዚህን ሰበር ሰሚ ችልት ክርክር ወጨ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
መዝገቡ ተዘግቷል። ይመለስ።
No topics extracted.