የኢትዮጵያ ኦርቶድክስ ተዋህድ ቤተክርስቲያን ህጋዊ ሰውነት የሚመነጨው ከ1952ቱ የፍትሐ ብሓር ህግ አንቀፅ 398 በመሆኑ ቤተክርስቲያንዋ ተካፊይ የሆነችበት ክርክር እንደ ክርክሩ ዓይነት፣ መጠን እና ቦታ ጉዲዩ በቀረበበት ክልል የሚታይ ስለመሆኑ የኢ.ፋ.ዱ.ሪ. ህገ መንግሰት አንቀፅ 78(2)፣ 80(2) ፣ (4) እና (5)፣ የፍደራል ፍ/ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 5(6) እና 11(1)
No summary available.
መጋቢት 30 2013 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሳዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡ አስገዲጅ ደብረ መዊ ቅደስ ጊወርጊስ ቤ/ክርስቲያን ተጠሪ፡ ቄስ ሞላ ሰማው **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ በስራ ምክንያት የተረከቡት ንብረት ባለመገኘቱ ምክንያት የንብረቱ ግምት እንዱከፈል የቀረበ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን የተጀመረውም አመልካች በአማራ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ወል ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተጠሪ ላይ ባቀረቡት ክስ ነው። የክሱም ጭብጥ የአሁን ተጠሪ የአመልካች ቤተክርስቲያን ግምጃ ቤት ኃላፉ በነበሩበት ወቅት በስራ ምክንያት የተረከቡትን የቤተክርስቲያኒቷ ቅርስ የሆነ በውስጡ ሜርኩሪ ያለውን እና በራሱ ኃይል የሚሰራ የዋጋ ግምቱ ብር 20,000,000(ሃያ ሚሉዮን) የሆነ ማሾ አጉድለው የተገኙ እና በዚህም ምክንያት በወንጀል ተከሰው ጥፊተኛ የተባለ በመሆኑ የቅርሱን ዋጋ ሉከፍለ ይገባል የሚል ነው።
በዚሁ ክስ ላይ መልስ እንዱሰጥ በታዘዘው መሰረት የአሁን ተጠሪ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እና አማራጭ የስረ ነገር ክርክር አቅርበው ተከራክረዋል። የቀረበው መቃወሚያ ለክሱ ምክንያት የሆነው ንብረት ቅርስ አይደለም፤ ግምቱም ከብር 100/አንድ መቶ/ አይበልጥም የሚል ነው። የስረ ነገር ክርክሩ ይዘት ደግሞ የተጠቀሰው ማሾ ማዕድን ያለበት ቅርስ ሳይሆን እማሆይ አመተ ስላሴ የተባለ ምዕመን ገዝተው ለቤተክርስቲያኒቷ የሰጡት በጋዝ የሚሰራ ነው፤ በወንጀል የተቀጣሁትም በተገለፀው አግባብ ሳይሆን የማሾው ብርጭቆ ጠፍቷል በሚል በብር 300(ሶስት መቶ) መቆጮ በመሆኑ የተጠቀሰውን ግምት ልጠየቅ አይገባም የሚል ነው።
ጉዲዩ የቀረበለት ፍርድ ቤትም የተጠቀሰው ማሾ ዋጋ በክልለ ውሃ መስኖ እና ኢነርጂ ቢሮ በኩል ተገምቶ እንዱቀርብ ያደረገ መሆኑን፤ የታዘዘው አካልም ክስ የቀረበበት ንብረት ብርጭቆ ቢኖረው ኖሮ ብር 50/ሃምሳ ብር/ ያወጣል በሚል የገለፀለት መሆኑን፤ ፍርድ ቤቱም ይህንኑ መነሻ በማድረግ በቀረበው ግምት መሰረት ጉዲዩን ለማየት የስር ነገር ስልጣን የለኝም በሚል መዝገቡን የዘጋ መሆኑን፤ ይኸው ጉዲይ እስከ ክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ድረስ ታይቶ ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ስልጣን አለው ተብል አከራክሮ እንዱወስን የተመለሰለት መሆኑን፤ በዚሁ አግባብ ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃን ከሰማ በኋላ ክስ የቀረበበት ንብረት ማዕድን ያለበት ቅርስ ሳይሆን እማሆይ አመተ ስላሴ የተባለት በ1987 ዓ.ም ከመርካቶ በብር 150(አንድ መቶ ሃምሳ) ገዝተው ለቤተክርስቲያንዋ አገልግልት እንዱውል በስጦታ ያበረከቱ መሆኑን፤ ማሾው ጠፊ በተባለበት ጊዜም ብርጭቆ የላለው መሆኑን እና ተጠሪ በወንጀል ጥፊተኛ ተብለው በብር 300(ሶስት መቶ) መቀጮ የተቀጡት የማሾውን ብርጭቆ ጠፍቷል በሚል እንደሆነ በማስረጃ ማረጋጡን ጠቅሶ የአሁን ተጠሪ የንብረቱ ዋጋ የተባለውን ብር 50(ሃምሳ ብር) ለአመልካች እንዱከፍለ ወስኖ ይኸው ውሳኔ እስከ ክልለ ሰበር ሰሚ ችልት መፅናቱን ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ ይዘት ለመረዲት ተችሎል።
የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንን ውሳኔ በመቃወም ነው። የአመልካች ወኪል ጥቅምት 08/2012 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ በስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ላይ ተፈፅሟል ያለትን መሰረታዊ የህግ ስህተት ጠቅሰው በዚህ ችልት እንዱታረምላቸው ጠይቀዋል። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ክርክሩ ከቤተክርስቲያን ጋር በመሆኑ እና ለክርክሩ ምክንያት የሆነው የንዘብ መጠን ሃያ ሚሉዮን ከመሆኑ አንጻር በክልለ ከፍተኛ ፍ/ቤት የስረ ነገር የዲኝነት ስልጣን ስር የሚወድቅ መሆን አለመሆኑ ከህገ መንግሰቱ አንቀጽ 80(2) እንዱሁም ከፋዳራል ፍ/ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 5(6) እና 11(1) ድንጋጌ አንጻር ለዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ቀርቦ እንዱመረመር በመታዘዙ ግራ ቀኙ የፅሁፍ ክርክር እንዱለዋወጡ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክር ይዘት ጠቅለል ባለ መልኩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ችልቱም ጉዲዩ ለዚህ ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ነጥብ አኳያ የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካለው ህግ ጋር በማገናዘብ መርምሯል።
እንግዱህ የማስቀረቢያ ነጥቡ ከዲኝነት የስር ነገር ሥልጣን ጋር የተያያዘ ነው። መነሻውም አንደ ተከራካሪ ወገን ቤተክርሲትያን በመሆንዋ እና ጉዲዩ የፋዳራል ጉዲይ በመሆኑ ከክርክሩም መጠን አኳያ በክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንዳት ላታይ ቻለ የሚል ስለመሆኑ በማስቀረቢያ ነጥቡ ውስጥ ከተጠቀሱት ህግጋት አንፃር መረዲት ይቻላል።
የፋዳራል ፍርድ ቤቶች የዲኝነት የስረ ነገር ስልጣን ምንጭ አንደ በፋዳራል መንግስቱ በተመዘገቡ ህጋዊ ሰውነት በተሰጣቸው ድርጅቶች ላይ ስለመሆኑ የፋዳራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀፅ 5(6) ይደነግጋል። እናም የፋዳራል መንግስቱ ተመዝጋቢ ድርጅቶች ተካፊይ የሆኑብት ክርክር የፋዳራል ጉዲይ መሆኑ የሚያከራክር አይደለም። የፋዳራል ከፍተኛ እና የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ባልተቋቋመባቸው ክልልች በፋዳራል ፍርድ ቤቶች የስረ ነገር ስልጣን ስር የሚወድቁ ጉዲዮች እንደክርክሩ መጠን ከክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጀምሮ የሚታይ ስለመሆኑ የህገ መንግስት አንቀፅ 78(2) እና 80((4) እና (5)) ይደነግጋል።
አሁን በቀረበው ጉዲይ የክርክሩ አንደ አካል የኢትዮጵያ ኦርቶድክስ ተዋህድ ቤተክርስቲያን ነች።
የቤተክርስቲያንዋ ህጋዊ ሰውነት የሚመነጨው ከ1952ቱ የፍትሐ ብሕር ህግ አንቀፅ 398 እንጂ የፋዳራል መንግስቱ ተመዝጋቢ አካል አይደለችም። እናም ቤተክርስቲያንዋ ተካፊይ የሆነችበነት ክርክር የፋዳራል ጉዲይ የሚባል ሳይሆን እንደ ክርክሩ ዓይነት፣ መጠን እና ቦታ ጉዲዩ በቀረበበት ክልል የሚታይ ይሆናል። ከዚህ አንፃር የከልለ ክፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዲዩን አከራክሮ ለመወሰን የዲኝነት የስር ነገር ስልጣን ያለው በመሆኑ በየደረጃው ያለት የክልለ የበላይ ፍርድ ቤቶችም ይህንኑ በመቀበላቸው የፈፀሙት መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም። በመሆኑም ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
የአማራ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቀ/0326886 ላይ ሐምል 24/2011 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል።
የዚህን ሰበር ችልት ክርክር ወጪ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
መዝገቡ ተዘግቷል። ይመለስ።