የመንግስት መኖሪያ ቤት የሚከራየው በከተማ ውስጥ ነዋሪ ኢትዮጲያዊ ዜግነት ላለው እና/ወይም በከተማው ውስጥ ነዋሪ ለሆነ የጸና/የታደሰ የኢትዮጲያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ላለው የውጭ ዜጋ ብቻ ነው ተብል የተደነገገው ከከተማው አስተዲደር ቤትን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚከራዩ ሰዎችን የሚመለከትና ውል በሚታደስበት ጊዜም በድንጋጌው ላይ የተቀመጡት ቅድመ ሁኔታዎች ሉሟለ ይገባል የሚባል ከሆነ ተከራይ ይህን ለማድረግ በሚያስችል ሁኔታ ውስጥ የሚገኝ መሆኑ እነ አቶ ዱክሳ ኪዲኔ (3 ሰዎች) እና የጉለላ ክፍለ ከተማ ወረዲ 9 ቤቶች ልማት ጽ/ቤት ሉረጋገጥ የሚገባ ስለመሆኑ የአዱስ አበባ ከተማ ቤቶች አስተዲደር መመሪያ ቁጥር 4/2009 አንቀጽ 43/ሀ፤ 44/3፤ 44/13 እና 45/2 79. የክልል መንግስት የገጠር መሬት አስተዲደር እና አጠቃቀም አዋጅ ከገጠር መሬት ይዞታ ውርስ ጋር በተያያዘ መመዘኛዎችን ከማስቀመጥ ባለፈ ወራሽነትን ቀድሞ ያረጋገጠ ብቻውን የሚወርስ ስለመሆኑ ባልደነገገበት ሁኔታ በወራሾች መካከል በተነሳ የገጠር መሬት ይዞታ ውርስ ይገባኛል ጥያቄ ወራሽነትን ቀድሞ አረጋግጦ የውርስ ሀብት በመያዝና ቀድሞ ወራሽነትን በማረጋገጥ ብቻ ልዩ የመውረስ መብት የሚገኝ ስላለመሆኑ የአማራ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት የገጠር መሬት አስተዲደር እና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 252/2009 አንቀፅ 17 እና ወ/ት እንኳአየሁሽ ነጋሽ እና አቶ ካሳሁን ነጋሽ ህዲር 29/2013 ዓ.ም 596
No summary available.
ህዲር 29/2013 ዓ.ም ዳኞች፡ መዓዛ አሸናፉ እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሳዬ አመልካች፡- ወ/ት እንኳአየሁሽ ነጋሽ ተጠሪ፡- አቶ ካሳሁን ነጋሽ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል
**
በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበው ጉዲይ የገጠር መሬትና መኖሪያ ቤት የውርስ ክርክርን የሚመለከት ነው። የሰበር አቤቱታው የቀረበው የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ ላይ ሐምል 08/2011 ዓ.ም በዋለው ችልት የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ ያደረገበትን የመጨረሻ ትዕዛዝ በመቃወም ነው።
ክርክሩ የተጀመረው የአሁን አመልካች በደቡብ አቼፈር ወረዲ ፍ/ቤት በአሁን ተጠሪ ላይ ባቀረቡት ክስ ነው። የክሱም ጭብጥ ቦታ እና አዋሳኙ በክሱ ዝርዝር የተጠቀሰውን 13 ቃዲ የገጠር መሬት እና 42 ዚንጎ ቆርቆሮ መኖሪያ ቤት የሟች እናታቸው ወ/ሮ ታገኝ አስማረ የውርስ ሀብት መሆኑን፤
የሟች ወራሾች ስድስት ልጆች ሲሆኑ አመልካች በመ/ ላይ ግንቦት 25/2007 ዓ.ም ወራሽነታቸውን አረጋግጠው የውርስ ሀብቱን በሽማግላ ከተካፈለ በኋላ ተጠሪ ድርሻቸውን ሉሰጧቸው ፈቃደኛ አለመሆናቸውን በመግለፅ በፍርድ ኃይል ተገደው እንዱያስረክቧቸው ዲኝነት የሚጠይቅ ነው።
ክሱ የቀረበለት ፍርድ ቤትም የአሁን ተጠሪን መልስ ከሰማ በኋላ ክስ ከቀረበበት ይዞታ ውስጥ 10 ቃዲ መሬት ተጠሪ በውርስ ያገኙት በመሆኑ ሉያካፍለ አይገባም በማለት ሶስት ቃዲ መሬቱን ብቻ እንዱያካፍለ የወሰነ መሆኑን፤ በዚሁ ውሳኔ ላይ በአሁን አመልካች ይግባኝ ባይነት ጉዲዩ የቀረበለት የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የወረዲ ፍርድ ቤትን ውሳኔ በመሻር በጉዲዩ ላይ የግራ ቀኙን ማስረጃ ሰምቶ እንዱወስን ለስር ፍርድ ቤት ጉዲዩን የመለሰ መሆኑን፤ በዚሁ አግባብ ክርክሩ ቀጥል እያለ ላልች ወራሾች የጣልቃ ገብነት ጥያቄ አቅርበው የክርክር አካል ተደርገው ክስ ለመስማት በተቀጠረ ቀን የአሁን ተጠሪ ባለመቅረባቸው ጉዲዩ በላለበት እንዱሰማ ተደርጎ የአመልካች እና የጣልቃ ገቦች ማስረጃ የተሰማ መሆኑን፤ በኋላም የቀረቡት የሰው ምስክሮች የአሁን ተጠሪ ወደው እና ፈቅደው ክስ የቀረበበትን ይዞታ በስምምነት ማካፈላቸውም አላስረደም፤ ተጠሪም ይዞታውን የያዙት ወራሽነታቸውን አረጋግጠው በመሆኑ ሉያካፍለ አይገባም በማለት ይዞታውን በተመለከተ የቀረበውን ክስ እና የጣልቃ ገብነት አቤቱታ ውድቅ በማድረግ ቤቱን በተመለከተ ብቻ ተጠሪ የአመልካችን ድርሻ ግምት እንዱያካፍላቸው በማለት ወስኖ ይኸው ውሳኔ እስከ ክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የፀና መሆኑን የስር ፍርድ ቤቶች የመዝገብ ግልባጭ ያሳያል።
የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንን ውሳኔ በመቃወም ነው። አመልካች ሀምላ 25/2011 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ በስር ፍ/ቤቶች ውሳኔና ትዕዛዝ ላይ ተፈፅሟል ያለትን መሰረታዊ የህግ ስህተት ጠቅሰው በዚህ ችልት እንዱታረምላቸው ጠይቀዋል። ፍሬ ቃለም ክስ የቀረበበት ይዞታ የወላጅ እናታችን መሆኑን እና ከተጠሪ ውጭ ላልች ወራሾች መኖራቸው ተረጋግጦ እያለ ተጠሪ ከመሬት አስተዲዲር ጋር በመመሳጠር በወሰደው የይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት መነሻነት የውርስ ሃብቱን ሉያካፍል አይገባም መባለ አግባብ አይደለም፤ ይዞታውም በወራሾች መካከል በሽማግላችዎ ተከፊፍል እያለ ፍርድ ቤቱ በራሱ ተነሳሽነት አልተከፊፈለም ማለቱ አግባብ አይደለም፤ የወረዲው መሬት አስተዲደር ይዞታው በሟች እናታችን ስም ተመዝግቦ እንደሚገኝ ከገለፀ በኋላ ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ በተጠሪ ስም ተመዝግቧል በሚል መግለጫ መስጠቱ እርስ በራሱ የሚጣረስ ሆኖ እያለ የስር ፍርድ ቤቶች ይህንን በተገቢ መንገድ ሳያጣሩ ውሳኔ መስጠታቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት በመሆኑ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ክርክር የቀረበበት ይዞታ የውርስ ሀብት ስለመሆኑ ተረጋግጦ እያለ ተጠሪ ወራሽነቱን አረጋግጦ በስሙ በማስመዝገቡ ብቻ ላልች ወራሾች መውረስ እንደማይችለ የተወሰነበት አግባብነት ለዚህ ችልት ቀርቦ እንዱመረመር በመደረጉ ተጠሪ መልስ እንዱሰጡበት ታዟል። ሆኖም ተጠሪ የፍርድ ቤቱ መጥሪያ ደረሷቸው ባለመቅረባቸው መልስ የመስጠት መብታቸው ታልፎል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ችልቱም የቀረበውን ክርክር ጉዲዩ ለዚህ ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ነጥብ አኳያ ለጉዲዩ አግባብነት ካለው ህግ ጋር በማገናዘብ ተመርምሯል።
ከክርክሩ አጀማመር መገንዘብ እንደሚቻለው ጉዲዩ በወራሾች መካከል የተነሳ የገጠር መሬት ይዞታ ውርስ ይገባኛል ጥያቄን የሚመለከት ነው። በመሰረቱ ጉዲዩ በሚመለከተው የክልል መሬት አስተዲደር ህግ አግባብ ከወራሾች መካከል የገጠር መሬት ይዞታን ለመውረስ የተለየ መስፈርት ወይም ልዩ ሁኔታ እስካልተደነገገ እና ይኸው ሁኔታ ስለመኖሩ እስካልተረጋገጠ ድረስ አንደ ወራሽ ከላላኛው ወራሽ የተለየ መብት የለውም። ወራሽነትን ቀድሞ አረጋግጦ የውርስ ሀብትን መያዝም ምናልባት ከይርጋ አኳያ የሚያጎናፅፈው መብት ካለ ተገቢ ክርክር ተደርጎበት ከሚወሰን በቀር ቀድሞ ወራሽነትን በማረጋገጥ ብቻ የሚገኝ ልዩ የመውረስ መብት አይኖርም።
አሁን በቀረበው ጉዲይ የአማራ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት የገጠር መሬት አስተዲደር እና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 252/2009 ከገጠር መሬት ይዞታ ውርስ ጋር በተያያዘ በአንቀፅ 17 እና ተከታዮቹ ወራሽ የሆነ/ች ሰው በግብርና ስራ የሚተዲደር አልያም ለመተዲደር ፍላጎት ያለው መሆን ያለበት ስለመሆኑ እና ላልች መሰል መመዘኛዎችን ከማስቀመጥ ባለፈ ወራሽነቱን ቀድሞ ያረጋገጠ ብቻውን የሚወርስ ስለመሆኑ የሚደነግገው ነገር የለም። የውርስ ጉዲይ በመርህ ደረጃ የሚገዛው በውርስ ህግ በመሆኑ በልዩ ህግ አጠቃላይ የውርስ ህግ መሰረተ ሀሳብን የሚቃረን ድንጋጌ ይወጣል ተብልም አይጠበቅም። በክልለ የገጠር መሬት አስተዲደር እና አጠቃቀም ህግ መሰረት አመልካች ክስ የቀረበበትን ይዞታ ለመካፈል አይችለም በሚል በአሁን ተጠሪ በኩል የቀረበ ክርክርም ሆነ የተረጋገጠ ነገር የለም። እናም ተጠሪ ቀድሞ ወራሽነቱን በማረጋገጥ ይዞታውን በመያዙ ብቻ ሉያካፍል አይገባም በሚል የተሰጠው ውሳኔ ህግን መሰረት ያላደረገ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም።
በልላ በኩል አመልካች ክስ ያቀረቡት የውርስ ሃብትን ለመካፈል እስከሆነ ድረስ ይዞታውን በተመለከተ ተደርጓል የተባለው ክፍፍል በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ አለመሆኑ መረጋገጡ በተጠየቀው ዲኝነት ላይ የሚያመጣው ለውጥ የለም። እናም በስምምነት የተደረገ ክፍፍል ስለመኖሩ ከተካደ የውርስ ሀብት የተባለው ይዞታ አግባብ ባለው የክልለ ገጠር መሬት አስተዲር እና አጠቃቀም ህግጋት መሰረት ወራሾች እንዱካፈለ ከሚደረግ በቀር በፈቃደኝነት የተደረገ የክፍፍል ስምምነት የለም በሚል ክሱ ውድቅ የሚደረግበት የህግ አግባብ የለም። ከዚህ አንፃር የክልለ ፍርድ ቤቶች የደረሱበት ድምዲሜ ህግን መሰረት ያላደረገ በመሆኑ በእርግጥም የሚነቀፍ ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
በአማራ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ደቡብ አቼፈር ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/22683 ላይ መጋቢት 12/2011 ዓ.ም ተሰጥቶ እስከ ክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ድረስ የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሻሽሎል።
ተጠሪ ክስ ከቀረበበት የውርስ ይዞታ ውስጥ ሁለት ቃዲ መሬት ለአመልካች ሉያካፍሎቸው ይገባል።
አመልካች በዚህ ሰበር ችልት ክርክር ምክንያት ያወጡትን ወጪ ዝርዝር ለወረዲው ፍርድ ቤት አቅርበው የመጠየቅ መብታቸው ተጠብቋል።
መዝገቡ ተዘግቷል። ይመለስ።
No topics extracted.