No summary available.
የሰ.መ.
ጥር 27 ቀን 2013 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሣዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካቾች፡-
የሰበር አቤቱታው ላቀርብ የቻለው አመልካቾች ሐምል 18 ቀን 2011 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ሰበር ሰሚ ፍርድ ቤት በመ. ሰኔ 28 ቀን 2011 ዓ.ም በስሩ ያለ ፍርድ ቤቶች የሰጡትን ውሳኔ በመሻር አመልካቾች አከራካሪውን ቤት እንዱለቁ በአባታቸው ስም የተሰጠው ማስጠንቀቂያ የሁከት ተግባር አይደለም በማለት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት አቤቱታ በማቅረባቸው ነው።
ጉዲዩ የሁከት ይወገድልኝ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የአዱስ አበባ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ነው። በሥር ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን አመልካቾች ከሳሾች፤ የአሁን ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል። የአሁን አመልካቾች በሥር ፍ/ቤት ያቀረቡት ክስ ይዘት በአጭሩ፡- ወላጅ አባታቸው አቶ ኪዲኔ ዘውገ በጉለላ ክፍለ ከተማ ወረዲ 09 ቤ.ቁ 680 የሆነው ቤት ሕጋዊ ተከራይ መሆናቸውን፤ አመልካቾች በዚሁ ቤት ውስጥ ተወልደው አድገው እስካሁን ድረስ በቤቱ በመኖር ላይ የሚገኙ መሆኑን፤ አባታቸው በከፍተኛ ሕመም ምክንያት እናታቸውን /ወ/ሮ ፍቅርተ ተረፈ/ ይዘው ከኢትዮጲያ ውጪ የወጡ መሆኑን፤ አባታቸው ባደረባቸው ከፍተኛ ሕመም ምክንያት ወደ ሐገር ቤት ተመልሰው የኪራይ ውለን ለመዋዋል ያልቻለ መሆኑን እና እናታቸው የቤቱን ኪራይ እየተመላለሱ የከፈለ መሆኑን በመግለጽ በአባታቸው ስም የቤቱን ኪራይ ተዋውለው ኪራይ በመክፈል በቤቱ መኖር እንዱቀጥለ ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
የአሁን ተጠሪ በሰጠው መልስ፡- የቤቱ ተከራይ የሆኑት አባታቸው አቶ ኪዲኔ ዘውገ ለሕክምና እንግሉዝ አገር እንደሚገኙ እና እንደሚመለሱ የቀረበ ማስረጃ የላለ መሆኑን፤ አመልካቾች በወላጆቻቸው ስም ኪራይ ለመዋዋል የሚያስችላቸው ደንብም ሆነ መመሪያ የላለ መሆኑን፤ የአመልካቾች ወላጆች ዜግነታቸው እንግሉዛዊ ስለሆነ እና ከአምስት ዓመት በላይ በቤቱ ስላልኖሩ በመመሪያ ቁጥር 4/2009 አንቀጽ 43/ሀ፤ 44/3 እና 44/13 እና 45/2 መሰረት ቤቱን እንዱያስረክቡ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ተገቢነት ያለው አሰራር መሆኑን በመግለጽ የአመልካቾች ክስ ወድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክሯል።
ጉዲዩ የቀረበለት ፍ/ቤት የአመልካቾች አባት እንግሉዝ አገር የሚገኙት ለሕክምና ዓላማ ብቻ? ወይንስ ለዘለቄታው ለመኖር? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ የአመልካቾች አባት እንግሉዘ አገር በሕክምና ላይ መሆናቸውን እና መቼ መመለስ እንደሚችለ የሚያስረዲ ማስረጃ አመልካቾች እንዱያቀርቡ ትዕዛዝ ሰጥቷል፤ በዚሁ መሰረት አመልካቾች አባታቸው በእንግሉዝ አገር በመደበኛ ታካሚነት እስከ 15/05/2010 በመታከም ላይ ያለ እና ዋንድ የሕክምና ማዕከል የሚገኙ መሆናቸውን የሚያስረዲ ማስረጃ ቀርቧል። ተጠሪ በሰጠው አስተያየት የቀረበው ማስረጃ ለአባታቸው የታዘዘላቸውን መድሀኒት የሚያመለክት እንጂ በሕክምና ላይ መሆናቸውን እና በቀጣይ ወደ ኢትዮጲያ እንዱሚመጡ የሚያሳይ አይደለም፤ ይልቁንም በ1993 ዓ.ም በእንግሉዝ አገር በስደተኝነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያሳይ ነው በማለት አስተያየት የሰጠ መሆኑን ከመዝገቡ ጋር ተያይዞ የቀረበልን የውሳኔ ግልባጭ ያመለክታል።
ፍርድ ቤቱም በመቀጠልም ጉዲዩን መርምሮ የቤቱ ተከራይ የሆኑት የአመልካቾች አባት ወደ እንግሉዝ አገር የሄደት ለሕክምና መሆኑን እና የአመልካቾች ወላጅ እናት ባለቤታቸውን ለማስታመም አብረው መሄዲቸውን እና ወደ ኢትዮጲያ ተመልሰው የቤቱን ኪራይ ውል ለማደስ ተጠሪን ቢጠይቁም ፈቃደኛ አለመሆኑን እና አመልካቾችም በዚሁ ቤት ውስጥ ተወልደው ኪራዩን እየከፈለ በመኖር ላይ ስለመሆናቸው በተጠሪ በኩል ማስተባበያ አልቀረበበትም፤ የተጠሪ ክርክር የአመልካቾች ወላጆች የእንግሉዝ አገር ዜግነት ያገኙ ስለሆነ በመመሪያው ቁጥር 43/ሀ መሰረት ቤቱን ሉያስረክቡ ይገባል የሚል ነው፤ የመመሪያው ቁጥር 45/2 ተከራይ ከሀገር ውጪ የወጣ እና እንደማይመጣ ሲረጋገጥ እና ላልች የውል ግዳታዎችን አለመወጣት ሲያጋጥም አከራይ የ30 ቀናት ቅድሚያ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ውለ ይፈርሳል ቤቱን ይረከባል በማለት ይደነግጋል፤ የአመልካቾች አባት እና እናት ለሕክምና ከሄደበት አገር እንደማይመጡ በተከሳሽ በኩል የቀረበ ማስረጃ ካለመኖሩም በላይ የአመልካቾች ወላጅ እናት በ2010 ዓ.ም አጋማሽ ወር ላይ ወደ ኢትዮጲያ በመምጣት የኪራይ ውለን ለማደስ ተጠሪን ጠይቀው እንግሉዛዊ ስለሆንሽ አናዋውልም ማለቱ ተረጋግጧል፤ የአመልካቾች ወላጆች ላልች የውል ግዳታቸውን ያልተወጡ ስለመሆናቸው የቀረበ ማስረጃ የለም፤ ከዚህም ላላ የአመልካቾች ወላጅ አባት ለ1ኛው አመልካች ውክልና ሰጥተውት የሄደ ስለሆነ የመመሪያው ቁጥር 45/3 አመልካቾችን የሚደግፍ ነው፤ ስለሆነም ከመመሪያው አንጻር ተጠሪ የቤቱ ተከራይ ልጆች ቤቱን ለቀው እንዱያስረክቡት በአባታቸው ስም ማስጠንቀቂያ መስጠቱ የሁከት ተግባር ስለሆነ ሁከቱ ሉወገድ ይገባል ሲል ወስኗል።
ተጠሪ ይህን ውሳኔ በመቃወም ለአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት የይግባኝ አቤቱታ ያቀረበ ቢሆንም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 337 መሰረት አቤቱታው ውድቅ ተደርጓል።
ተጠሪ በመቀጠል ለአዱስ አበባ ከተማ ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ አቅርቧል። አቤቱታው የቀረበለት ፍርድ ቤት ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ የቤቱ ሕጋዊ ተከራይ የሆኑት የአመልካቾች አባት አቶ ኪዲኔ ዘውገ ከሐገር መውጣታቸው እና ዜግነታቸው እንግሉዛዊ ስለመሆኑ አልተካደም፤ የስር ፍርድ ቤት ለውሳኔ መሰረት ያደረገው አቶ ኪዲኔ ዘውገ ወደ ሐገር እንደማይመለሱ ተጠሪ አላረጋገጠም በሚል ነው፤ በመንግሰት ቤቶች መመሪያ ቁጥር 4/2009 አንቀጽ 44/13 የመንግስት መኖሪያ ቤት የሚከራየው በከተማ ውስጥ ነዋሪ የሆነ ኢትዮጲያዊ ዜግነት ያለው እና/ ወይም በከተማው ውስጥ ነዋሪ ሲሆን የጸና /የታደሰ የኢትዮጲያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ላለው የውጪ ዜጋ ብቻ መሆኑ ተደንግጓል፤
የአመልካቾች በቤቱ የመኖር መብት የሚመነጨው አባታቸው በተከራዩት ቤት ነው፤ ተጠሪ በመመሪያው መሰረት የቤቱ ተከራይ የሆኑት ግለሰቦች የውጪ ዜግነት ያላቸው እና በቤቱም የማይኖሩ መሆኑን አረጋግጦ የቤቱን የኪራይ ውል ማቋረጡ እና ቤቱን ለመረከብ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ አግባብ ሆኖ ሳለ ይህ ታልፍ በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ ተገቢ አይደለም በማለት ሽሮ ተጠሪ ቤቱን እንዱለቁ የሰጠው ማስጠንቀቂያ የሁከት ተግባር አይደለም ሲል ወስኗል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም መሰረታዊ የሕግ ስሕተት ተፈጽሞበታል በሚል ሲሆን ይዘቱም፡- አመልካቾች ወላጆቻችን እንግሉዝ አገር የሄደት አባታችን በመታመሙ ምክንያት ሕይወቱን ለማትረፍ መሆኑን አስረድተናል፤ ተጠሪውም ለረጅም ዓመታት በውክልና ሲያዋውለን ቆይቷል፤ ወላጆቻችን ዜግነት የተሰጣቸው ለሕክምና ወጪ እንዱቀንስ እና እንዱረደ ነው፤ ወላጆቻችን ተመልሰው ወደ ቤታቸው እንደሚመጡ አረጋግጠን ሳለ ተጠሪ ተወልደን ካደግንበት ቤት ለማስወጣት የጀመረው እንቅስቃሴ የሁከት ተግባር አይደለም በማለት የተሰጠው ውሳኔ ተገቢ አይደለም፤ ስለሆነም አመልካቾች በቤቱ የመኖር መብት እንዲለን የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የመንግስት ቤቶች አስተዲደር መመሪያ ቁጥር 4/2009 የሚደግፈን በመሆኑ በቤቱ የመኖር መብታችን ሉከበርልን ይገባል የሚል ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ የአመልካቾች ወላጆች ከሄደበት ውጪ ሐገር ወደ ኢትዮጲያ እንደማይመለሱ በተጠሪ በኩል የቀረበ ማረጋገጫ በላለበት ሁኔታ የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ሰበር ሰሚ ችልት በስሩ ያለት ፍርድ ቤቶች የሰጡትን ውሳኔ ሽሮ ሁከት የለም በማለት የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ በዚህ ችልት እንዱታይ ተደርጓል። ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎም ግራ ቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የተጠሪ መልስ ይዘት በአጭሩ፡- የአመልካቾች ወላጅ አባት ከ1987 ዓ.ም ጀምሮ እንግሉዝ አገር በስደተኝነት ተመዝግበው እንደሚኖሩ እና ዜግነታቸውም እንግሉዛዊ በመሆናቸው በመመሪያ ቁጥር 4/2009 አንቀጽ 44/13 በተቀመጠው መስፈርት ስለማይሸፈኑ ውል እንዱቋረጥ ተደርጓል፤
የአመልካቾች የዲኝነት ጥያቄም ወላጆቻቸው የላላቸውን መብት በውክልና ይዘን እንቀጥል የሚል ነው፤
ተከራይ በውክልና ቤቱን አስተላልፍ በውጪ ሐገር ሉኖር የሚችለው ከመነሻው ኢትዮጲያዊ ዜግነት ያለው ከሆነ እንጂ እንደ አመልካቾች ወላጆች ኢትዮጲያዊ ዜግነት የላላቸውን ሰዎች የሚመለከት አይደለም፤ ክርክሩ የወላጆቻቸው ወደ ሐገር መመለስ እና አለመመለስ ሳይሆን የዜግነት ጉዲይ ነው፤
በስር ፍርድ ቤት የቀረበው ማስረጃ ከሐገር የወጡት በሕክምና ምክንያት መሆኑን አያስረዲም፤
ይልቁንም በስደት ከሐገር የወጡ ስለመሆኑ እና እንደማንኛውም ሰው የታከሙ መሆኑን የሚሳይ በመሆኑ የወላጆቻቸው ተመልሶ ወደ ሐገር የመምጣት ጉዲይ በተጠሪ በኩል የተወሰነውን ውሳኔ የሚያስለውጥ አይደለም፤ ተጠሪ የአመልካቾች ወላጆች ወደ ሐገር አለመመለሳቸውን ማረጋገጥ አይጠበቅበትም፤ ቢመለሱም ዜግነታቸው ኢትዮጲያዊ እስካልሆነ ድረስ ተጠሪ ሉያስተናግዲቸው የሚችልበት የሕግ አግባብ ስለላለ ውሳኔው ሉጸና ይገባል የሚል ነው።
አመልካቾችም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው። ይህ ችልትም በሰበር አጣሪው ችልት ሉጣራ ይገባዋል ተብል የተያዘውን ነጥብ ከግራ ቀኙ ክርክር፤ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምሮታል።
አመልካቾች በስር ፍርድ ቤት ባቀረቡት ክስ በአባታቸው አቶ ኪዲኔ ዘውገ ስም የቤቱን ኪራይ ውል ተዋውለው ኪራዩን እየከፈለ በቤቱ መኖር እንዱቀጥለ እንዱወሰንላቸው ዲኝነት ሉጠይቁ የቻለት ተጠሪ የአዱስ አበባ ከተማ ቤቶች አስተዲደር መመሪያ ቁጥር 4/2009 አንቀጽ 43/ሀ፤ 44/3፤ 44/13 እና 45/2 ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ የቤቱ ተከራይ የሆኑት የአመልካቾች አባት ለሕክምና እንግሉዝ አገር የሚገኙ እና እንደሚመለሱ የቀረበ ማስረጃ የላለ መሆኑን፤ ዜግነታቸውም እንግሉዛዊ ሆኖ ከአምስት ዓመት በላይ በቤቱ ያልኖሩ መሆኑን ጠቅሶ የኪራይ ውለን አቋርጦ ቤቱን እንዱያስረክቡ ማስጠንቀቂያ በመስጠቱ ምክንያት እንደሆነ ግራ ቀኙ በስር ፍርድ ቤት ካደረጉት ክርክር ይዘት መገንዘብ ችለናል።
ተጠሪ በዚህ አግባብ የሚከራከር ከሆነ ይህንኑ በማስረጃ ማረጋገጥ ይጠበቅበታል። በአንጻሩ በስር ፍርድ ቤቶች ከተረጋገጠው ፍሬ ነገር መገንዘብ የተቻለው የአመልካቾች አባት አቶ ኪዲኔ ዘውገ የቤቱ ሕጋዊ ተከራይ መሆናቸውን እና ባደረባቸው ሕመም ምክንያት ለ1ኛው አመልካች /ለልጃቸው/ ውክልና ሰጥተው ወደ እንግሉዝ አገር ሄደው በዚያው አገር በሚገኝ የሕክምና ማዕከል በመደበኛ ታካሚነት በመታከም ላይ የሚገኙ መሆኑን፤ የአመልካቾች ወላጅ እናትም ባለቤታቸውን ለማስታመም አብረው የሄደ መሆኑን እና በመሀልም ወደ ኢትዮጲያ ተመልሰው የቤቱን ኪራይ ውል ለማደስ ተጠሪን የጠየቁ ቢሆንም ተጠሪ ፈቃደኛ አለመሆኑን እና በቤቱ ውስጥ የሚኖሩት የቤቱ ሕጋዊ ተከራይ ልጆች የሆኑት አመልካቾች መሆናቸውን ነው። ስለሆነም በስር ፍርድ ቤቶች ከተረጋገጠው ፍሬ ነገር አኳያ በየደረጃው ያለ የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ አግባብ መሆን አለመሆኑን እንደሚከተለው መርምረናል።
የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የቤቶች ልማት እና አስተዲደር ቢሮ የመንግስት ቤቶች አስተዲደር መመሪያ ቁጥር 4/2009 አንቀጽ 45 የኪራይ ውል የሚቋረጥባቸውን ምክንያቶች የሚደነግግ ሲሆን የዚሁ አንቀጽ ንዐስ ቁጥር 2 ተከራይ ከሐገር ውጪ ከወጣ እና እንደማይመጣ ሲረጋገጥ እና ላልች የውል ግዳታዎችን አለመወጣት ሲያጋጥም አከራዩ የሰላሳ ቀናት ቅድሚያ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ውለን እንደሚያፈርስ ይደነግጋል። የዚሁ አንቀጽ ንዐስ ቁጥር 3 ደግሞ ተከራይ ከባል፤ ከሚስት፤
ከልጅ፤ ከሞግዚት ውጪ ለላላ ወገን በውክልና ስም አስተላልፍ አምስት ዓመት እና ከዚያ በላይ ውጭ አገር ከኖረ የቤት ኪራይ ውለ ተቋርጦ መንግስት ቤቱን ይረከባል በማለት ይደነግጋል።
ከላይ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች መሰረት በማድረግ የአመልካቾችን ጉዲይ ስንመለከተው የአመልካቾች አባት ከኢትዮጲያ የወጡ ቢሆንም ላልች የውል ግዳታዎችን አለመወጣታቸው እና ወደ ሐገር ተመልሰው እንደማይመጡ በተጠሪ በኩል የቀረበ ማረጋገጫ የለም። የአመልካቾች አባት ወደ እንግሉዝ ሐገር የሓደት ለሕክምና መሆኑ እና በዚያው ሐገር በሚገኝ የሕክምና ማዕከል ውስጥ መደበኛ ታካሚ መሆናቸው የተረጋገጠ ሲሆን ሕክምና በሚከታተለበት ሐገር በስደተኝነት መመዝገባቸው ብቻውን ወደ ሐገራቸው እንደማይመጡ የሚያሳይ አረጋጋጭ ነው ተብል ድምዲሜ የሚወሰድበት አይደለም። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ የአመልካቾች አባት ወደ ውጪ ሐገር ሲሄደ ውክልና የሰጡት ልጃቸው ለሆነው 1ኛ አመልካች በመሆኑ ውክልናው በመመሪያው አንቀጽ 45/3 በተደነገገው አግባብ የተሰጠ መሆኑን የሚያሳየን ነው። በቤቱ ውስጥ የሚኖሩትም አስቀድሞ ከአባታቸው ጋር ይኖሩ የነበሩ የቤቱ ተከራይ ልጆች እንጂ ላላ 3ኛ ወገን አይደለም። ስለሆነም ከመነሻውም ቢሆን ተጠሪ ውለ የተቋረጠ መሆኑን ገልጾ ቤቱን ለመረከብ የሰጠው ማስጠንቀቂያ በመመሪያው አንቀጽ 45 ላይ በተመለከተው መሰረት ውል ለማቋረጥ የሚያስችለ ሁኔታዎች መፈጠራቸውን ሳያረጋግጥ የተሰጠ መሆኑን የሚያሳይ ነው።
በመሆኑም ጉዲዩ የቀረበለት የመጀመሪያው ደረጃ ፍርድ ቤት ይህንኑ መሰረት በማድረግ ከመመሪያው አንጻር አመልካቾች ቤቱን ለቀው እንዱያስረክቡት ተጠሪ የሰጠው ማስጠንቀቂያ ተገቢ አይደለም ሲል የሰጠው ውሳኔ የሚነቀፍ አይደለም።
በልላ በኩል የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ሰበር ሰሚ ችልት በስሩ ያለት ፍርድ ቤቶች የሰጡትን ውሳኔ ለመሻር እንደ ምክንያት የወሰደው የቤቱ ተከራይ የውጪ ሐገር ዜግነት ያላቸው እና በቤቱ የማይኖሩ በመሆኑ ተጠሪ የቤቱን የኪራይ ውል ማቋረጡ እና ቤቱን ለመረከብ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ አግባብ ነው በሚል ነው። የቤቱ ሕጋዊ ተከራይ የሆኑት የአመልካቾች አባት ውለን በተዋዋለ ጊዜ ኢትዮጲያዊ የነበሩ እና ለሕክምና ወደ ውጪ ሐገር ከሄደ በኋላ ዜግነታቸውን የለወጡ ከመሆኑ አኳያ የስር ሰበር ሰሚ ችልት ዜግነታቸውን መሰረት በማድረግ የሰጠው ውሳኔ አግባብ መሆን አለመሆኑን ቀጥለን እንመልከት።
የአዱስ አበባ ከተማ የመንግስት ቤቶች አስተዲደር መመሪያ ቁጥር 04/2009 አንቀጽ 44/13 የመንግስት መኖሪያ ቤት የሚከራየው በከተማ ውስጥ ነዋሪ ኢትዮጲያዊ ዜግነት ላለው እና/ ወይም በከተማው ውስጥ ነዋሪ ለሆነ የጸና /የታደሰ የኢትዮጲያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ላለው የውጭ ዜጋ ብቻ ነው በማለት ይደነግጋል። በመሰረታዊነት የዚህ ድንጋጌ ተፈጻሚነት ከከተማው አስተዲደር ቤትን ለመጀመሪያ ጊዜ ለሚከራዩ ሰዎች እንደሆነ መገንዘብ የሚቻል ሲሆን አስቀድሞ የተፈጸመ የቤት ኪራይ ውል በሚታደስበት ጊዜም በድንጋጌው ላይ የተቀመጡት ቅድመ ሁኔታዎች ሉሟለ ይገባል የሚባል ከሆነ ውል ለማደስ የሚጠይቀው ወገን ይህንኑ ለማድረግ በሚያስችል ሁኔታ ውስጥ የሚገኝ መሆኑ በቅድሚያ ሉረጋገጥ ይገባል።
በያዝነው ጉዲይ የቤቱ ሕጋዊ ተከራይ የሆኑት የአመልካቾች አባት ባደረባቸው ሕመም ምክንያት ለሕክምና ወደ ውጪ ሐገር የሄደ እና በዚያው ሐገር በሚገኝ የሕክምና ማዕከል ውስጥ መደበኛ ታካሚ መሆናቸው የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነው። ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት ባደረገው ክርክር የአመልካቾች አባት የእንግሉዝ ዜግነት ያላቸው በመሆኑ ውለ ተቋርጦ አመልካቾች ቤቱን እንዱያስረክቡ ማስጠንቀቂያ መስጠታችን አግባብ ነው በማለት ከሚከራከር በቀር በእርግጥም የአመልካቾች አባት ወደ ኢትዮጲያ ተመልሰው በመምጣት በመመሪያው አንቀጽ 44/13 ላይ በተመለከተው መሰረት በከተማው ውስጥ ነዋሪ ሆነው የጸና/ የታደሰ የኢትዮጲያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ለማግኘት በሚችለበት የጤና ሁኔታ ላይ መሆናቸውንም ሆነ ከነጭራሹም ወደ ሐገራቸው የማይመለሱ መሆናቸውን በመግለጽ ያቀረበው ክርክርም ሆነ ማስረጃ የለም። ተጠሪ በዚህ አግባብ ያቀረበው ክርክር እና ማስረጃ እስከላለ ድረስ የአመልካቾች አባት የጤና ሁኔታቸው ሲስተካከል ወደ ሐገራቸው በመምጣት ኑሯቸውን ሉቀጥለ እንደሚችለ ግምት ይወሰዲል። የአመልካቾች አባት ጤናቸው ተስተካክል ወደ ሐገራቸው መጥተው መኖር የሚቀጥለ ከሆነም አስቀድሞ በሕግ አግባብ በተከራዩት ቤት ውስጥ የመኖር መብት አላቸው።
ስለሆነም የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ሰበር ሰሚ ችልት ጉዲዩን በዚህ አግባብ አይቶ መወሰን ሲገባው ተጠሪ የቤቱ ተከራይ የውጪ ዜግነት ያላቸው እና በቤቱም የማይኖሩ መሆኑን አረጋግጦ የቤቱን የኪራይ ውል ማቋረጡ እና ቤቱን ለመረከብ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ተገቢ ነው ሲል የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ሰበር ሰሚ ፍርድ ቤት በመ. ሰኔ 28 ቀን 2011 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1 መሰረት ተሽሯል።
በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የአዱስ አበባ ከተማ መጀመሪያ ደራጀ ፍርድ ቤት በመ. ሕዲር 07 ቀን 2011 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፤ ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የኢዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርደ ቤት በመ. ጥር 06 ቀን 2011 የሰጠው ትዕዛዝ ጸንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርከር የወጣውን ወጪ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻለ።
No topics extracted.