የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ሸሪዓ ፍ/ቤት ጋብቻ በፍቺ ዉሳኔ እንዱፈርስ በወሰነበት ሁኔታ የፍቺ ዉጤቱንም ሰምቶ ለመወሰን የሥረ ነገር የዲኝነት ስልጣን ያለዉ ይኼዉ የሸሪዓ ፍ/ቤት እንጂ የፍደራል ፍ/ቤቶች የፍቺ ዉጤት የሆነዉን የንብረት ክፍፍል ለማየት የሥረ ነገር የዲኝነት ስልጣን የላላቸው ስለመሆኑ የኢ.ፋ.ዱ.ሪ. ሕገ መንግስት አንቀጽ 34 (5) እና አንቀጽ 78 (5)፣ የፍደራል ሸሪዓ ፍ/ቤቶችን አቋም ለማጠናከር የወጣ አዋጅ ቁጥር 188/1992 አንቀጽ 5 (4)፤የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.244 (2፣ሀ) እና 245 (2)
No summary available.
ጥቅምት 21 ቀን 2013 ዓ.ም ዳኞች፡-
ይህ የባልና ሚስት የንብረት ክርክር የተጀመረዉ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካች የሥር ከሳሽ፣ የአሁን ተጠሪ የሥር ተከሳሽ ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዲዩ ለዚህ ችልት ላቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.223910 በ10/8/2011 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱታረምልኝ በማለት በማመልከታቸዉ ነዉ።
የአሁን አመልካች በሥር ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ በአመልካች እና በተጠሪ መካከል የነበረዉ ጋብቻ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ሸሪዓ ፍ/ቤት በሰጠዉ ዉሳኔ ጋብቻችን በፍቺ እንዱፈርስ ወስኗል።
ስለሆነም አመልካች እና ተጠሪ በጋራ ያፈራነዉ በሱለልታ ከተማ ልዩ ስሙ ድሬ ጀርባ የሚገኘዉ የቤት ቁጥር 632 SUL 2.1 የሆነዉ በተጠሪ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ የመኖሪያ ቤት እንድንካፈል እንዱወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቋል።
የአሁን ተጠሪ በዚህ ክስ ላይ ባቀረቡት መልስ ይህን ቤት ተጠሪ ከአመልካች ጋር የነበረን ጋብቻ ከተቋረጠ በኋላ ተጠሪ ከግለሰብ ገንዘብ ተበድሬ የተሰራ ስለሆነ የጋራ ንብረት ሳይሆን የግል ንብረቴ በመሆኑ ክሱ ተቀባይነት የለዉም በማለት ተከራክሯል።
ከዚህ በኋላ የሥር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ግራ ቀኙን በማከራከር የሰዉ ምስክሮች በመስማትና የሰነድ ማስረጃ በመመርመር በሰጠዉ ዉሳኔ አመልካች እና ተጠሪ ጋብቻቸዉ ባለመግባባት ያለ ስምምነት ከተቋረጠ በኋላ የአሁን ተጠሪ በግላቸዉ ያፈሩት የግል ንብረት እንጂ የግራ ቀኙ የጋራ ሀብት አይደለም፤ የብድር ገንዘብ በተመለከተ የአሁን አመልካችን አይመለከትም በማለት ወስኗል።
የአሁን አመልካች በዚህ ዉሳኔ ቅር ተሰኝተዉ ይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረቡ ሲሆን ፍ/ቤቱ ግራ ቀኙን በማከራከር የሥር ፍ/ቤት ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል። የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ ይህን ዉሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነዉ።
የአሁን አመልካች በ15/8/2011 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ፡- አመልካች እና ተጠሪ በመካከላችን የነበረዉ ጋብቻ የፋ/መ/ደ/ሸሪዓ ፍ/ቤት በ8/5/2006 ዓ.ም በፍቺ ዉሳኔ ያፈረሰ ሲሆን ለክርክር ምክንያት የሆነዉ ቤት ጋብቻችን በፍቺ ዉሳኔ ከመፍረሱ በፉት በጋብቻዉ ዉስጥ እያለን የተገዛና የጋራ ንብረታችን ሆኖ ሳለ፣ አመልካች ባቀረበዉ ማስረጃም አረጋግጦ እያለ፣ የሥር ፍ/ቤቶች ቤቱ የተጠሪ የግል ሀብት እንጂ የጋራ ንብረት አይደለም በማለት የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ ዉድቅ ሆኖ እንዱታረምልኝ ፣ቤቱ የጋራ ንብረታችን መሆኑ ተረጋግጦ ግማሽ ድርሻዬ እንዱወሰንልኝ በማለት በዝርዝር አመልክቷል።
ይህ ችልት የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል በማለት ተጠሪ መልስ እንዱሰጡ ባዘዘዉ መሰረት ሐምል 8 ቀን 2011 ዓ.ም በተጻፈ መልስ፡ የሥር ፍ/ቤቶች የቀረበዉን የሰዉ ምስክሮች ቃልና የሰነድ ማስረጃ መርምረዉ ለክርክር ምክንያት የሆነዉ የመኖሪያ ቤት የተጠሪ የግል ሀብት እንጂ የግራ ቀኙ የጋራ ንብረት አይደለም በማለት የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የላለዉ በመሆኑ እንዱጸናልኝ በማለት በዝርዝር ክርክራቸዉን አቅርበዋል። የአሁን አመልካች የሰበር አቤቱታዉን በማጠናከር የመልስ መልስ አቅርበዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከፍ ሲል የተጠቀሰዉ ሲሆን ይህ ችልት የግራ ቀኙን ክርክር፣ ለዚህ ቅሬታ መነሻ የሆኑትን የሥር ፍ/ቤቶች ዉሳኔዎች እና አግባብነት ካላቸዉ የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ መርምሮታል። እንደመረመርነዉ በዚህ ጉዲይ ምላሽ ማግኘት ያለብት ፣የግራ ቀኙ ጋብቻ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ሸሪዓ ፍ/ቤት በፍቺ ዉሳኔ ፈርሶ እያለ፣ የፍቺ ዉጤት የሆነዉን የንብረት ክፍፍል ጥያቄ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ለማየት የሥረ ነገር የዲኝነት ስልጣን አለዉ ወይስ የለዉም? የሚለዉ ነጥብ መሆኑን ተገንዝበናል። አመልካች በሥር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በግልጽ ጽፍ ካቀረቡት ክስ፣ ከግራ ቀኙ ክርክር እና ከሥር ፍ/ቤቶች የዉሳኔ ግልባጭ መገንዘብ እንደሚቻለዉ በአመልካች እና በተጠሪ መካከል የነበረዉ ጋብቻ በመካከላቸዉ በተፈጠረዉ አለመግባባት፣ ጉዲዩ ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ሸሪዓ ፍ/ቤት ቀርቦ ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን አከራከሮ በመ.ቁ.209/06 በ8/5/2006 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የግራ ቀኙን ጋብቻ በፍቺ ዉሳኔ እንዱፈርስ ወስኗል። ከዚህ ዉሳኔ በኋላ የአሁን አመልካች የፍቺ ዉሳኔ ዉጤት የሆነዉን የንብረት ክፍፍል ክስ ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አቅርበዉ ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን አከራክሮ ተገቢ ነዉ ያለዉን ዉሳኔ የሰጠ ሲሆን ፣የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ጉዲዩ በይግባኝ ቀርቦለት የሥር ፍ/ቤት ዉሳኔን በማጽናት መወሰኑን የሥር ፍ/ቤቶች የዉሳኔ ግልባጭ ያመለክታል።
እንግዱህ እንደሚታወቀዉ በኢ.ፋ.ዳ.ሪ. ሕግ መንግስት አንቀጽ 34 [5] ሥር እንደተመለከተዉ ‛ይህ ሕገ መንግስት የግል እና የቤተሰብ ሕግን በተመለከተ በተከራካሪዎች ፈቃድ በሀይማኖቶች ወይም በባህልች ሕጎች መሰረት መዲኘትን አይከለክልም፤ ዝርዝሩም በሕግ እንደሚወሰን“ ደንግጎ እናገኛለን።
እንዱሁም በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 78 [5] ሥር በተደነገገዉ አግባብ የሀይማኖት እና የባህል ፍ/ቤቶች ሉቋቋሙ ወይም እዉቅና ሉሰጣቸዉ እንደሚችል ተመልክቷል። ይህን የሕገ መንግስቱን ድንጋጌ ተከትል ከእስልምና ሀይማኖት አንጻር የፋዳራል ሸሪዓ ፍ/ቤቶችን አቋም ለማጠናከር የወጣ አዋጅ ቁጥር 188/1992 ወጥቶ እየተሰራበት ይገኛል። በዚህ አዋጅ አንቀጽ 4 መሰረት የፋዳራል ሸሪዓ ፍ/ቤቶች የወል የዲኝነት ስልጣን የሚኖራቸዉ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ 1 ሥር የተዘረዘሩ ጉዲዮችን የሚመለከት ሆኖ፣ ፍ/ቤቶቹ ይህን የዲኝነት ስልጣን ሉኖራቸዉ የሚችለዉ ተከራካሪ ወገኖች በእስልምና ሀይማኖት ሥርዓት ለመዲኘት ግልጽ በሆነ መንገድ በፈቃዲቸዉ መርጠዉ የቀረቡ ከሆነ ብቻ መሆኑን ይደነግጋል። ከእነዚህ ጉዲዮች መካከል በአዋጁ አንቀጽ 4 [1፣ ሀ] ሥር የተጠቀሱት ማናቸዉም የጋብቻ፣ የፍቺ፣ የቀለብ አወሳሰን፣ አካለ መጠን ያላደረሱ ሕጻናት ሞግዚትነት እና በቤተሰብ ተዛምድ ላይ የሚነሱ ጉዲዮች መሆናቸዉን ተመልክቷል። ተከራከሪ ወገኖች በፋዳራል ሸሪዓ ፍ/ቤቶች ለመዲኘት ፈቃደኝነታቸዉን እና ተቃዉሟቸዉን የሚገልጹትና የሚያረጋግጡት በአዋጁ አንቀጽ 5 ሥር በተመለከተዉ አግባብ ይሆናል። ከተከራካሪ ወገኖች አንደ በሸሪዓ ፍ/ቤት ለመዲኘት አቤቱታ ያቀረበ እንደሆነ በግልጽ ፈቃደኝነቱን እንደገለጸ እንደሚቆጠር ከዚህ ድንጋጌ መገንዘብ ይቻላል። ጉዲዩ የቀረበለበት የሸሪዓ ፍ/ቤት ደግሞ ላላ ተከራካሪ ወገን በፍ/ቤቱ ለመዲኘት ፈቃደኛ መሆን አለመሆኑን ከአዋጁ ጋር ተያይዞ በሚገኘዉ ቅጽ መሰረት ቀርቦ እንዱያረጋግጥ መጥሪያ እንደሚልክለት በአዋጁ አንቀጽ 5 [1] ሥር ተመልክቷል። ይህ ተከራካሪ ወገን ቀርቦ በሸሪዓ ፍ/ቤት ለመዲኘት ከአዋጁ ጋር በተያያዘ ቅጽ መሰረት ያረጋገጠ እንደሆነ በግልጽ ፈቃደኝነቱን መግለጹን ስለሚያረጋግጥ፣ ጉዲዩ የቀረበለት የሸሪዓ ፍ/ቤት ተከራካሪ ወገኖች ያቀረቡትን ዲኝነት ለማየት የሥረ ነገር ስልጣን ይኖረዋል ማለት ነዉ። ነገር ግን ተከራካሪ ወገኖች ጉዲዩ በቀረበለበት ሸሪዓ ፍ/ቤት ለመዲኘት ግልጽ በሆነ መንገድ ስምምነት በላለ ጊዜ ፍ/ቤቱ ጉዲዩን ለመዲኘት የሥረ ነገር የዲኝነት ስልጣን ስለማይኖረዉ ፣ተከራካሪ ወገኖች ጉዲያቸዉን በመደበኛ ፍ/ቤት እንዱያስወስኑ ጉዲዩን ሥልጣን ላለዉ የፋዳራል መደበኛ ፍ/ቤት ማስተላለፍ እንዲለበት በአዋጁ አንቀጽ 5 [3] ሥር ተደንግጓል። ተከራካሪ ወገኖች ፈቃድ ላይ ተመስርቶ በሸሪዓ ፍ/ቤት በመታየት ላይ የሚገኙ ጉዲዮችን በማናቸዉም ምክንያት ወደ መደበኛዉ ፍ/ቤት፤ ወይም በመደበኛዉ ፍ/ቤት በመታየት ላይ የሚገኙ ጉዲዮችን ወደ ሸሪዓ ፍ/ቤት ተዘዋዉረዉ እንዱታዩ ማድረግ እንደማይችለ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ 4 ሥር ተመልክቷል። ከዚህ ድንጋጌ የምንገነዘበዉ ተከራካሪ ወገኖች በፋዳራል ሸሪዓ ፍ/ቤቶች ለመዲኘት ግልጽ በሆነ መንገድ ፈቃዲቸዉን ሰጥተዉ ፍ/ቤቱ ጉዲዩን በማየት ላይ እያለ ተከራካሪ ወገኖቹ ወይም ከተከራካሪ ወገኖች አንደ ጉዲዩ ከሸሪዓ ፍ/ቤቶች ወደ የፋዳራል ፍ/ቤቶች እንዱተላለፍለት ጥያቄ ወይም አቤቱታ ማቅረብ እንደማይችለ ነዉ። ተከራካሪ ወገኖች በፋዳራል ሸሪዓ ፍ/ቤቶች ለመዲኘት በአዋጁ በተመለከተዉ አግባብ ግልጽ በሆነ መንገድ ፈቃደኝነታቸዉን ገለጸዉ ክርክር ከቀጠለ ፣ይህን ጉዲይ ሰምቶ ሕጋዊ ዉሳኔ ለመስጠት የሥረ ነገር የዲኝነት ስልጣን ያላቸዉ የፋዳራል ሸሪዓ ፍ/ቤቶች እንጂ የፋዳራል መደበኛ ፍ/ቤቶች አለመሆናቸዉን ያስገነዝባል።
በዚህ አግባብ አሁን ወደ ተያዘዉ ጉዲይ ስንመለስ የአሁን አመልካች ከተጠሪ ጋር የነበራቸዉ ጋብቻ በፍቺ ዉሳኔ እንዱፈርስላቸዉ ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ሸሪዓ ፍ/ቤት አቤቱታ አቅርበዉ፣ የአሁን ተጠሪም ቀርበዉ በጉዲዩ ላይ ተገቢ ነዉ ያለትን ክርክራቸዉን ማቅረባቸዉን ከግራ ቀኙ ክርክርና ከሥር ፍ/ቤቶች ዉሳኔና ከሸሪዓ ፍ/ቤት የዉሳኔ ግልባጭ መረዲት ይቻላል። ይህ ከሆነ ግራ ቀኙ በሃይማኖታቸዉ በእስልምና ሀይማኖት ሥርዓት በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ሸሪዓ ፍ/ቤት ለመዲኘት ፈቃደኝነታቸዉን ግልጽ በሆነ መንገድ ስምምነት መኖሩን በሚያሳይ ሁኔታ ክርክራቸዉን ማቅረባቸዉን ያመለክታል። በመሆኑም የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ሸሪዓ ፍ/ቤት የግራ ቀኙን የጋብቻ ፍቺ ጉዲይ እና የፍቺ ዉሳኔ ዉጤት የሆኑትን ጉዲዮችን ለማየት የሥረ ነገር የዲኝነት ስልጣን ይኖራቸዋል ማለት ነዉ። ይህ ማለት ግራ ቀኙ በፍቺ ጉዲይ በሸሪዓ ፍ/ቤት እየተከራከሩ እያለ አንደኛዉ ተከራካሪ ወገን ወይም ሁለቱም ይህ ክርክራቸዉ ወደ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ተዘዋዉሮ የፍቺ ዉሳኔ እንዱሰጥ አቤቱታ ለማቅረብም ሆነ የሸሪዓ ፍ/ቤቱ የፍቺ ዉሳኔ ከሰጠ በኋላ የፍቺ ዉጤት የሆነዉን የንብረት ክፍፍል በሸሪዓ ፍ/ቤት ሳይሆን በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ለማቅረብ አይችለም።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ሸሪዓ ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ጋብቻ በፍቺ ዉሳኔ እንዱፈርስ የወሰነ ስለሆነ፣ የፍቺ ዉጤቱንም ቢሆንም የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶ ለመወሰን የሥረ ነገር የዲኝነት ስልጣን ያለዉ የፋዳራል ሸሪዓ ፍ/ቤቶች እንጂ የፋዳራል ፍ/ቤቶች አይደለም። ስለሆነም የአሁን አመልካች ጋብቻቸዉን በተመለከተ የፍቺ ዉሳኔና ውጤቱ ላይ ውሳኔ እንዱሰጥላቸዉ ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ሸሪዓ ፍ/ቤት አቤቱታ አቅርበዉ፣ ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን አከራክሮ በመ.ቁ.209/06 በ8/5/2006 ዓ.ም በሰጠዉ ዉሳኔ የግራ ቀኙ ጋብቻ እንዱፈርስ የፍቺ ዉሳኔ ከሰጠ በኋላ የፍቺ ዉጤት የሆነዉን የንብረት ክፍፍል ጥያቄ ለማየት የሥረ ነገር የዲኝነት ስልጣን ያለዉ ይኼዉ ፍ/ቤት ሆኖ ሳለ፣ አመልካች ከተጠሪ ጋር ያፈራነዉን የጋራ ሀብታችን የሆነዉን የመኖሪያ ቤት እንድካፈል እንዱወሰንልኝ በማለት ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ያቀረበዉ አቤቱታ በዚህ ክርክር ጉዲዩን ለማየት የሥረ ነገር የዲኝነት ስልጣን ለላለዉ ፍ/ቤት ያቀረበ ስለሆነ ተቀባይነት የለዉም። የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም በሸሪዓ ፍ/ቤት የፍቺ ዉሳኔ በመስጠቱ የፍቺ ዉጤት በተመለከተ ለማየት ስልጣን የለኝም ብል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.9 [2]፣ የፋዳራል ሸሪዓ ፍ/ቤቶችን አቋም ለማጠናከር የወጣ አዋጅ ቁጥር 188/1992 አንቀጽ 5 [4]፣ እና በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.244 [2፣ ሀ] እና 245 [2] መሰረት ዉድቅ ማድረግ ሲገባዉ፣ የንብረት ክፍፍል በተመለከተ ግራ ቀኙን በማከራከር ዉሳኔ መስጠቱ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ይህን ማረም ሲገባዉ የሥር ፍ/ቤት ዉሳኔ በማጽናት የሰጠዉ ዉሳኔ የህግ መሰረት የለዉም ብለናል።
ሲጠቃለል የሥር የፋዳራል ፍ/ቤቶች በፋዳራል ሸሪዓ ፍ/ቤት የፍቺ ዉሳኔ የተሰጠበትን ጉዲይ የፍቺ ዉጤት የንብረት ክፍፍል ጥያቄ በተመለከተ ግራ ቀኙን አከራከረዉ ዉሳኔ ለመስጠት የሥረ ነገር የዲኝነት ስልጣን ሳይኖራቸዉ መወሰናቸዉ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ የሚከተለዉ ተወስኗል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ.116454 በ16/2/2011 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.223910 በ10/8/2011 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 [1] መሰረት ተሽሯል።
በግራ ቀኙ መካከል የነበረዉን ጋብቻ በተመለከተ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ሸሪዓ ፍ/ቤት በሰጠዉ የፍቺ ዉሳኔ ጋብቻቸዉን በማፍረስ የወሰነ ስለሆነ፣ የፍቺዉ ዉጤቱንም ሰምቶ ለመወሰን የሥረ ነገር የዲኝነት ስልጣን ያለዉ ይኼዉ የሸሪዓ ፍ/ቤት በመሆኑ፣ የፋዳራል ፍ/ቤቶች በዚህ ጉዲይ የፍቺ ዉጤት የሆነዉን የንብረት ክፍፍል ለማየት የሥረነገር የዲኝነት ስልጣን የላቸዉም ብለናል።
የዚህ ዉሳኔ ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤቶች ይድረስ።
ግራ ቀኙ በዚህ ችልት የደረሰባቸዉን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን ይቻለ።
ይህ ችልት በ7/9/2011 ዓ.ም የሰጠዉ የእግድ ትዕዛዝ በዚህ ዉሳኔ ተነስቷል። ለሱለልታ ከተማ መሬት ልማትና ማናጅመንት ጽ/ቤት ይጻፍ።
የመ.ቁ.123631 የሆነዉ መዝገብ ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አረዲ ምድብ ችልት ይመለስ፤ እንዱሁም የመ.ቁ.209/06 የሆነዉ መዝገብ ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ሸሪዓ ፍ/ቤት ይመለስ ብለናል።
ይህ ዉሳኔዉ በ23/2/2013 ዓ.ም ተነቧል።
No topics extracted.