ከገጠር መሬት ይዞታ ክርክር ጋር በተያያዘ ሁለት ዲኝነቶች በአንድ ላይ ተጣምረው ሲቀርቡ የፍርድ ቤት ስልጣንን በሚመለከት የስነ ስርዓት ህግ ይዘት ያላቸው ድንጋጌዎች በገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም አዋጅ፣ በሥነ-ሥርዓት ሕግና በክልል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ላይ የተመለከቱ ቢሆንም የክልል የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም አዋጅ ልዩ ሕግ ስለሆነ በሕግ አተረጓጎም መርሕ መሰረት ልዩ ሕጉ በቀዲሚነት የሚተገበር ስለመሆኑ የኦሮሚያ ክልል የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 130/1999 አንቀጽ 16(1)(ረ)፣ የኦሮሚያ ክልል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 216/2011 አንቀጽ 30(3) የገጠር መሬት ውርስን መሰረት አድርጎ ለቀረበ ክስ ከገጠር መሬት ጋር በተያያዘ ተፈፃሚነት ያለዉ የይርጋ ድንጋጌ ስለመኖሩ የክልል አቶ ዋኬኔ ዱንቃ እና እነ አቶ ኤብሳ እጅጉ (4 ሰዎች) መሬት አስተዲደር እና አጠቃቀም አዋጅ የተለየ ድንጋጌ በላለው ጊዜ ተፈጻሚ የሚሆነው የይርጋ ደንብ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.1677(1) እና 1845 የተመለከተው የ10 ዓመት ጊዜ ስለመሆኑ
No summary available.
ቀን፡- ሚያዚያ 28 ቀን 2013 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- አቶ ዋኬኔ ዱንቃ ተጠሪዎች፡-
የሰበር አቤቱታው የቀረበው የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው። የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዲነው አመልካች በሥር ፍርድ ቤት ከሳሽ ሲሆኑ ተጠሪዎች ተከሳሾች ሆነው ተከራክረዋል። አመልካች ጥቅምት 01 ቀን 2011 ዓ/ም በተጻፈ የክስ ማመልከቻ በጉደሩ ወረዲ ጉደኔ ጫላ ሲበሬ ቀበላ የሚገኝ 15.5 ሄክታር መሬት ወላጅ እናቴ ንጉሴ ኦብሴ ግንቦት 17 ቀን 2002 ዓ/ም ሕይወቷ ከማለፈ በፉት ስትጠቀምበት የነበረውን መሬት ስለያዙ እንዱለቁልኝ እና መሬቱን በማረስ የተጠቀሙበት የዓላባ ግምት በድምሩ ብር 3,607,212.00 እንዱከፍለኝ በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል።
ተጠሪዎች ባቀረቡት መልስ ይዞታውን ከ1971 ዓ/ም ጀምሮ የምንጠቀምበት ስለሆነ ክሱ በይርጋ የታገደ ነው በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርበዋል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የሆሮ ጉደሩ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግራ ቀኙን አከራክሮ በኦሮሚያ ክልል የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 130/1999 አንቀጽ 16 መሰረት የገጠር መሬት ይዞታ ጋር የሚፈጠር አለመግባባት በሽምግልና ለመፍታት ጥረት መደረግ እንዲለበትና አለመግባባቱ ካልተፈታም ክሱ ለወረዲ ፍርድ ቤት እንደሚቀርብ የተመለከተ ስለሆነ አመልካች የገጠር መሬት ይዞታ ክርክሩን የሰብል ምርትና ዓላባን ምክንያት በማድረግ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ መመስረት የለበትም ብለናል። ክሱ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት የሚቀርብ አይደለም እንጂ የሕግ ድጋፍ አለው ቢባል እንኳን ተጠሪዎች ይዞታውን ለ19 ዓመት የያዙት በመሆኑ ክሱ በይርጋ ቀሪ ነው በማለት ወስኗል። የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የአመልካችን ይግባኝ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 337 መሰረት ባለመቀበል ሰርዟል። የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ግራ ቀኙን አከራክሮ ክሱ የገጠር መሬት ይዞታ ክርክር ሳይሆን የውርስ ሀብት ጥያቄ በመሆኑ በሀብቱ ግምት መሰረት ለከፍተኛ ፍርድ ቤት መቅረቡ ተገቢ ነው። ክስ የቀረበበትን ይዞታ ተጠሪዎች ለ18 ዓመት የያዙ ስለመሆኑ አመልካችም ያመኑ በመሆኑ ክሱ በፍ/ሕ/ቁ. 1845 መሰረት በ10 ዓመት ይርጋ ቀሪ ነው ተብል መወሰኑ ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለም በማለት ወስኗል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘትም የሥር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሥልጣን የለኝም ካለ ክሱን ተቀብል ማስተናገድ አልነበረበትም። ክርክሩ የውርስ ሀብትን የሚመለከት በመሆኑና ይርጋው መቆጠር ያለበት አውራሼ ከሞቱበት ጊዜ ጀምሮ ስለሆነ ክሱ በይርጋ ሉታገድ አይገባም። ተጠሪዎች ይዞታውን ለ19 ዓመት መያዛቸው በማስረጃ አልተረጋገጠም የሚል ሲሆን የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩን ተመልክቶ ከገጠር መሬት ጋር የተያያዘ የውርስ ክርክርም ቢሆን የወረዲ ፍርድ ቤት ሥልጣን ሆኖ እያለ ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ክሱን ተቀብል በማስተናገድ ውሳኔ መስጠቱ ሕጋዊነቱን ለመመርመር ለሰበር ሰሚ ችልቱ ያስቀርባል በማለት ተጠሪዎች መልስ እንዱያቀርቡ ያዘዘ ሲሆን ከ1ኛ-3ኛ ያለት ተጠሪዎች ያቀረቡት መልስ የእርሻ መሬት ላይ የሚገኝ ሰብል ግምቱ በብር 3,607,212.00 ገንዘብ ላይ የቀረበው ክስ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ሥልጣን ነው። ይዞታውም ከ39 ዓመት በላይ በእጃችን የቆየ ስለሆነ ውሳኔው ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለም ብለዋል። አመልካች የመልስ መልስ በማቅረብ የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል። 4ኛ ተጠሪ መጥሪያ ደርሷቸው ባለመቅረባቸው ጉዲዩ በላለበት ታይቷል።
የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም የሥር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረበውን ክስ ለመመልከት የሥረ-ነገር ሥልጣን አለው ወይስ የለውም? ክሱ በይርጋ ቀሪ ነው መባለ ሕጋዊ መሆን አለመሆኑን? የሚለውን በጭብጥነት በመያዝ መዝገቡን እንደሚከተለው መርምረናል።
የመጀመሪያውን ጭብጥ እንደመረመርነው አመልካች ጥቅምት 01 ቀን 2011 ዓ/ም በተጻፈ የክስ ማመልከቻ በጉደሩ ወረዲ ጉደኔ ጫላ ሲበሬ ቀበላ የሚገኝ 15.5 ሄክታር መሬት ወላጅ እናቴ ንጉሴ ኦብሴ ግንቦት 17 ቀን 2002 ዓ/ም ሕይወቷ ከማለፈ በፉት ስትጠቀምበት የነበረውን መሬት ስለያዙ እንዱለቁልኝ እና መሬቱን በማረስ የተጠቀሙበት የዓላባ ግምት በድምሩ ብር 3,607,212.00 እንዱከፍለኝ በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል። ክርክሩን በፍትሐ ብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕጉ መሰረት መምራት እና መቆጣጠር የፍርድ ቤቱ ኃላፉነት ሲሆን በዚህ ሂደት ከሚመረምራቸው ጉዲዮች መካከል ጉዲዩ ላይ ለመወሰን ሥልጣን ያለው መሆን አለመሆኑ ዋነኛው ነው። የፍርድ ቤት ሥልጣን ብሓራዊ የመዲኘት ሥልጣን (judicial jurisdiction)፣ የሥረ-ነገር ሥልጣን (material jurisdiction) እና የግዛት ወይም ከበባዊ ሥልጣን (local or territorial jurisdiction) በሚል የተከፊፈለ ነው። በያዝነው ጉዲይ አከራካሪ ሆኖ የሚመረመረው የሥር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሥረነ-ገር ሥልጣን ያለው መሆን አለመሆኑ ነው። የሥረ-ነገር ሥልጣን በአንድ ሀገር ጉዲዩን ለመዲኘት ሥልጣን ባላቸው ፍርድ ቤቶች መካከል በዋነኛነት ፣ታሳቢ የሚያደርገው የፍርድ ቤቱን አቅም ወይም ችልታ (competence of the court) ፍትሐዊነትን፣ ኢኮኖሚንና የሥራና ሀብት ክፍፍልን መሰረት አድርጎ በገንዘብ ግምት (pecuniary jurisdiction) ወይም በጉዲዩ ዓይነት (subject matter jurisdiction) ወይም ጉዲዩን በመጀመሪያ ሆነ በይግባኝ ደረጃ (original and appellate jurisdiction) የሚያዩት ሥለመሆኑ በፍርድ ቤቶች መካከል የሚመለከቱት ጉዲዩችን የሥልጣን ድልድል የሚደረግበት ነው።
አመልካች ለሥር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክስ ሁለት ዲኝነቶች በአንድ ላይ ተጣምረው የቀረቡበት ነው። የመጀመሪያ የገጠር መሬት ይዞታ እንዱለቀቅላቸው ሲሆን ይሕም በኦሮሚያ ክልል የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 130/1999 አንቀጽ 16(1)(ረ) ላይ በወረዲ ፍርድ ቤት ሥልጣን ሥር የሚወድቅ ጉዲይ ስለመሆኑ ተመልክቷል። ሁለተኛው ዲኝነት የዓላባ ግምትና በይዞታው ላይ ያለ ንብረት ግምት በድምሩ ብር 3,607,212.00 እንዱከፈላቸው ያቀረቡት የገንዘብ ግምትን መሰረት ያደረገው ነው። ክሱ ጥቅምት 01 ቀን 2011 ዓ/ም ሲቀርብ የሥረ-ነገር ሥልጣን እንደገና ያደላደለው የኦሮሚያ ክልል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 216/2011 ዓ/ም በክልለ ምክር ቤት ጸድቆ ሥራ ላይ የዋለና ስድስት ወር የመሸጋገሪያ ጊዜ ያለው ሲሆን በአዋጁ አንቀጽ 30(3) ሆነ በቀድሞው አዋጅ ቁጥር 141/2000 አንቀጽ 27(3) መሰረት ብር 3,607,212.00 የከፍተኛ ፍርድ ቤት ሥልጣን ነው።
የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 130/1999 በዋነኛነት ስለገጠር መሬት ባለይዞታዎች ስላላቸው መብትና አስተዲደር ጋር የተያያዙ መሰረታዊ መብቶችን የሚመለከት ቢሆንም ስለፍርድ ቤት ሥልጣን የተመለከተው ድንጋጌ የሥነ-ሥርዓት ሕግ ይዘት ያለው ነው። በአዋጁ ላይ የተመለከተው ከመሬት ይዞታ ጋር የተያያዘ ክርክር የወረዲ ፍርድ ቤት ሥልጣን ስለመሆኑ ያመለከተው ክፍል ከሥነ-ሥርዓት ሕጉ ሆነ ከፍርድ ቤቶች አዋጅ ላይ የተመለከቱ ጉዲዮች ቢኖሩም ከገጠር መሬት ጋር ለተያያዘ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 130/1999 ልዩ ሕግ ስለሆነ በሕግ አተረጓጎም መርሕ መሰረት ልዩ ሕጉ በቀዲሚነት መተግበር አለበት። ስለሆነም ከገጠር መሬት ጋር የተያያዘ ክርክር፤ ክርክሩ ይዞታ መብትን ለማስከበርም ሆነ የውርስ መብትን ወይንም ከገጠር መሬት ጋር የተያያዘ ላላ መብትን ለማስከበር፤ ክሱ መቅረብ ያለበት ለወረዲ ፍርድ ቤት ነው። በዚህ ረገድ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ከገጠር መሬት ውርስ መብት ጋር በተያያዘ ለሚቀርብ ክስ በአዋጅ ቁጥር 130/1999 የተመለከተው የወረዲ ፍርድ ቤት ሥልጣን ተፈጻሚነት የለውም ማለቱ ሥህተት ያለበትና ሉታረም የሚገባው ነው።
በልላ በኩል የገጠር መሬት አዋጁ ሙለ የሥነ-ሥርዓት ሕግን የሚሸፍን ድንጋጌዎች የላለት በመሆኑ ላልች የሥነ-ሥርዓት ጉዲዮች ሲኖሩ የፍትሐ ብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕጉ ሆነ የኦሮሚያ ፍርድ ቤቶች አዋጅ ተፈጻሚነት ይኖራቸዋል። በገጠር መሬት አዋጅ ቁጥር 130/1999 ላይ ከገጠር መሬት ጋር በተያያዘ ከሚቀርብ ክስ ጋር ተጣምረው በአንድ ላይ ሉቀርቡ ስለሚችለ ጉዲዮች ሆነ በአንድ ላይ ተጣምረው የሚቀርቡ የተለያዩ ዲኝነቶች ሲኖሩ የፍርድ ቤቱ ሥልጣን እንዳት ይወሰናል በሚለና በላልች ከክርክር አመራር ጋር በተያያዙ ጉዲዮች የሚመለከት ዝርዝር ድንጋጌ የለውም። ሕጉ በዋነኛነት ስለገጠር መሬት ባለይዞታዎች መብትና መሬት አስተዲደር ጋር የተያያዙ ጉዲዮች ለመወሰን የወጣ በመሆኑ ዝርዝር የሥነ-ሥርዓት ሕጎችን እንዱሸፍንም አይጠበቅበትም። የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመዝገብ (በቅጽ 21 እንደታተመ) በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 218 እና 216 የተመለከተውን ከመሬት ሕጉ ጋር በማገናዘብ የይዞታ መብትን ለማስከበር የሚቀርብ ክስ እና ዓላባውን መሰረት ያደረገ ክስ ተነጣጥል በቀረበ ጊዜ ስለሚኖረው ወጤት ዋና ጭብጥ አድርጎ ክሶቹ ተነጣጥለው መቅረባቸው የሥነ-ሥርዓት ሕጉን ያልተከተለ ነው ተብል ውድቅ ላደረግ አይገባም በማለት ትርጉም የሰጠበት ቢሆንም ሁለቱም ዲኝነቶች አብረው ሲቀርቡ እና የፍርድ ቤት ሥልጣን አከራካሪ ሲሆን የሚያስከትለው የሕግ ውጤት ምን እንደሚሆን በጭብጥነት ይዞ ያልመረመረ በመሆኑ ጉዲዩን መመልከቱ ተገቢ ሆኖ ተገኝቷል።
በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.17(2) ላይ በአንድ ክስ ውስጥ የተለያዩ ዲኝነቶች ተጣምረው ሲቀርቡ የፍርድ ቤቱ ሥልጣን የሚወሰነው ከፍተኛ ግምት ያለውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ስለመሆኑ ተመልክቷል።
አመልካች ሁለት ዲኝነቶች ያቀረቡ ሲሆን የመጀመሪያ ግምት የላለው የገጠር መሬትን ለመረከብ የቀረበ ሲሆን ይሕም ወረዲ ፍርድ ቤት ሥልጣን ነው። ሁለተኛው የዓላባ ጥቅም መሰረት ያደረገ ብር 3,607,212.00 ለማስከፈል የቀረበ ክስ ሲሆን ጉዲዩም የከፍተኛ ፍርድ ቤት ሥልጣን ነው። ከቀረቡት ሁለት ዲኝነቶች ከፍተኛ ግምት ያለው ሁለተኛው ዲኝነት በመሆኑ ክሱ ተጠቃል መቅረብ ያለበት ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ስለሆነ የሥረ-ነገር ሥልጣኑ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ላሆን ይገባል ብለናል።
ስለሆነም አመልካች ክሱን ለሥር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ማቅረባቸው ተገቢነት ያለው ሆኖ አግኝተነዋል።
በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 231(1)(ለ) መሰረት ክሱ የቀረበለት ፍርድ ቤት ጉዲዩን ለመመልከት የሥረ-ነገር ሥልጣን ያለው መሆን አለመሆኑን ወደ ክርክር ሂደት ከመግባቱ በፉት አስቀድሞ የመመርመር ኃላፉነት አለበት። የሥር ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ክሱ እንደቀረበለት ሥልጣን ያለው መሆን አለመሆኑን ሳይመረምር ውሳኔ በሰጠ ጊዜ ክሱ የወረዲ ፍርድ ቤት ሥልጣን ነው ማለቱ ተገቢነት የለውም።
ሥልጣን የለኝም ካለም ክሱን ለመመልከት ሥልጣን ላለው ፍርድ ቤት መመለስ ሲገባው በሥረ-ነገሩ ተመልክቶ ክሱ በይርጋ ቀሪ ነው ማለቱ የክርክር አመራር ግድፈት ያለበት ነው። ፍርድ ቤቱም ጉዲዩን ለማየት ሥልጣን ያለው ሆኖ እያለ ሥልጣን የለኝም ማለቱ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ነው።
ነገር ግን ክሱን ለመመልከት ሥልጣን ያለው በመሆኑ ክሱን ተቀብል የይርጋ ክርክሩን መመርመሩ በውጤት ደረጃ ተቀብለነዋል።
ወደ ሁለተኛው ጭብጥ ስንመለስ አመልካች ላቀረቡት የውርስ ገጠር መሬት ይዞታና ገንዘብ ይከፈለኝ ክስ ተጠሪዎች ክሱ በይርጋ ቀሪ ነው በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርበዋል። የይርጋ ክርክሩ የቀረበው አመልካች ክሱን ለማቅረብ የክስ የማቅረቢያ ጊዜው (limitation of action) አልፎል በሚል ነው። ይርጋ መብትን (extinctive prescription) እና/ወይም መብትን ለማስከበር የሚቀርብ ክስን ቀሪ የሚያደርግ ነው። እንደ ክሱ መሰረት ዓይነት ተፈጻሚ የሚሆነው የይርጋ ደንብና ሕግ የተለያየ ነው። የቀረበዉ ክስ በይርጋ ቀሪ ላሆን የሚገባ መሆን አለመሆኑን በመወሰን ረገድ ፍርድ ቤቶች መሰረት እንዱያደርጉ የሚጠበቅባቸዉ በከሳሽ ክስ ላይ የተመለከተዉን የክስ ምክንያት ነው።
ሁለም የገጠር የእርሻ መሬት ጋር የተያያዘ የክስ ዓይነት ላይ ተመሳሳይ የይርጋ ደንብ ተፈጻሚ ላሆን አይችልም። ክሱ ይዞታ እንዱለቀቅ የሚቀርብ የይዞታ መብትን ለማስከበር የሚቀርብ ክስ ወይም የገጠር መሬት ውርስ ይገባናል በሚል የቀረበ ክስ ወይም ከገጠር መሬት ጋር የተያያዘ ውልን መሰረት ያደረገ ክስ መሆኑ እየታየ እንደ ክሱ የዲኝነት መሰረት ክሱ በይርጋ ቀሪ የሚሆንበት ጊዜና ለጉዲዩ ተፈጻሚ የሚሆነው የይርጋ ደንብ ወይም ድንጋጌ የተለያየ ነው። ስለሆነም የክሱን መሰረት መለየት የይርጋ ክርክሩንም ሆነ ቀጣይ ያለ ሂደቶችን ለመመራት አስፈላጊ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል።
የአመልካች የክስ መሰረት የሆነው የገጠር መሬት ውርስን መሰረት ያደረገ በመሆኑ ከገጠር መሬት ጋር በተያያዘ ተፈፃሚነት ያለዉ የይርጋ ድንጋጌ ስለመኖሩ የክልለ ገጠር መሬት አስተዲደር እና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 130/99 የተለየ ድንጋጌ የለዉም። ይህ ማለት ግን ከገጠር መሬት ውርስ መብት ጋር የተያያዘ በሚቀርብ ክስ ላይ የይርጋ ደንቦች ተፈፃሚ አይሆኑም ማለት አይደለም።
ስለሆነም በዚህ ረገድ በሚቀርብ ክስ ላይ ተፈጻሚ የሚሆነው የይርጋ ደንብ በፍ/ሕ/ቁ. 1677(1) እና 1845 የተመለከተው የ10 ዓመት ጊዜ ነው። አመልካች በሥር ፍርድ ቤት በተደረገ የቃል ክርክር መሬቱ በተጠሪዎች ከተያዘ ከ18 ዓመት በላይ መሆኑን አምነው የተከራከሩ ስለመሆኑ ከውሳኔው ግልባጭ ተረድተናል። ስለሆነም ክስ የቀረበው ከ10 ዓመት በኋላ በመሆኑ ክሱን በ10 ዓመት ይርጋ ቀሪ መደረጉ ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አላገኘንበትም።
የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመዝገብ ጥር 19 ቀን 2012 ዓ/ም፣ የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ ሰኔ 12 ቀን 2011 ዓ/ም፣ የሆሮ ጉደሩ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ታህሳስ 24 ቀን 2011 ዓ/ም የሰጡት ውሳኔ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት በውጤት ደረጃ ፀንቷል።
በዚህ ችልት ለወጣ ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ።
መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
ማ/አ የልዩነት ሃሳብ እኛ ስማችን በ2ኛ እና 5ኛ ተራ ቁጥር ላይ የተሰየምነዉ ዳኞች የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዲዩን በቀጥታ ክስ ተቀብል የማየት ስልጣን የለዉም የሚል ሃሳብ ስላለን የልዩነት ሃሳባችንን እንደሚከተለዉ አስፍረናል።
ለክርክሩ ምክንያት የሆነዉ ጉዲይ የገጠር መሬትን የሚመለከት ነዉ። ከእርሻ መሬት ይዞታ መብት ጋር በተያያዘ የሚነሳ ክርክር ጉዲዩ በሚመለከታቸዉ ተከራካሪዎች በዉይይትና በስምምነት እንዱፈታ ጥረት የሚደረግ ስለመሆኑ እና በስምምነት ሉፈታ ካልቻለ በተከራካሪ ወገኖች በተመረጠ ሽምግልና ወይንም በክልለ የገጠር መሬት አስተዲደር በተደነገገዉ መሰረት የሚወሰን ስለመሆኑ በፋዳራል መንግስት በወጣዉ የገጠር መሬት አስተዲደር እና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 456/97 አንቀጽ 12 ስር ተመላክቷል።
ከገጠር መሬት ጋር በተያያዘ የሚነሳ የይዞታ ይገባኛል ክርክር እልባት የሚያገኝበትን አግባብ የኦሮሚያ የገጠር መሬት አስተዲደር እና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 130/99 ይደነግጋል። በዚህም መሰረት ክርክሮቹ በወረዲዉ ፍርድ ቤት ቀርበዉ ከመታየታቸዉ በፉት በግራ ቀኝ ስምምነት እና ቀጥልም በሽምግልና መታየት የሚገባቸዉ ስለመሆኑ ከአዋጁ አንቀጽ 16 እንዱሁም አዋጁን ለማስፈጸም በወጣዉ ደንብ ቁጥር 151/2005 አንቀጽ 18 ላይ ተመልክቷል። ከገጠር መሬት ይዞታ መብት ጋር በተያያዘ የሚነሱ ክርክሮች በተቻለ መጠን በአካባቢዉ ሽማግላ ካልሆነ ደግሞ ለወረዲዉ ፍርድ ቤት ቀርበዉ በመጀመሪያ መታየት እንዲለባቸዉ ከላይ በተመለከቱት የፋዳራል እና የኦሮሚያ ክልል የገጠር መሬት አስተዲደር እና አጠቃቀም አዋጆች የተደነገገበት መሰረታዊ ዓላማም በአርሶ አደሮች መካከል በእርሻ መሬት ይዞታ ምክንያት የሚነሱ አለመግባባት ጉዲዮች በቅርብ ታይተዉ በተቻለ መጠን ወደ ሙግት ሳይገባ እልባት እንዱሰጠዉ በማድረግ ወደ ሙግት የሚገባ ከሆነም ሙግቱ ቅርብ በሆነዉ በወረዲ ፍርድ ቤት እንዱታይ በማድረግ አርሶ አደሮች ከመሬት ይዞታ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ለምርት ስራ የሚያዉለት ጊዜ እንዱሁም ገንዘብ ያላግባብ እንዲይባክን ጥበቃ ለማድረግ ነዉ ተብል ይታመናል። ከገጠር መሬት ጋር በተያያዘ ከሚቀርብ ዲኝነት ጋር በተያያዘ የሚነሳን የስልጣን ጥያቄ በመወሰን ረገድም ይህንኑ የአዋጁን ዓላማ ከግምት ዉስጥ በማስገባት ትርጓሜ መስጠት ያስፈልጋል የሚል እምነት አለን።
አብላጫዉ ድምጽ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዲዩን ለማየት ስልጣን አለዉ በሚል ለደረሰበት ድምዲሜ የሰጠዉ መሰረታዊ ምክንያት የይዞታ ክርክር እና የአላባ ግምት አብረዉ በመቅረባቸዉ የተነሳ የፍርድ ቤት ስልጣን አከራካሪ የሆነ እንደሆነ የዲኝነት ስልጣን መወሰን የሚቻለዉ ከፍተኛ ግምት ያለዉን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 17(2) ላይ የተመለከተዉን ድንጋጌ መሰረት በማድረግ መሆኑን እና የኦሮሚያ ክልል የገጠር መሬት አስተዲደር እና አጠቃቀም አዋጅም ይህን አስመልክቶ የተለየ ድንጋጌ የላለዉ መሆኑን በመጥቀስ ነዉ። በእርግጥ ሁለት የተለያዩ ዲኝነቶች ተጣምረዉ በአንድ ላይ ሲቀርቡ የፍርድ ቤቱን ስልጣን ለመወሰን ከፍተኛ ግምት ያለዉን ዲኝነት መሰረት በማድረግ ነዉ የሚለዉን እኛም የምንስማማበት ነዉ። ይሁንና የሥ/ሥርዓት ህጉ በወጣበት ወቅት በነበረዉ የመንግስት አወቃቀር እና የፍርድ ቤቶች የስልጣን ድልድል መሰረት የማይንቀሳቀስ ንብረት (የማይንቀሳቀስ ንብረት መሬትን እንደሚያካትት በፍትሐ ብሓር ህጉ አንቀጽ 1130 ላይ ከተመለከተዉ መገንዘብ ይቻላል) እንደየአግባብነቱ ለወረዲ ፍርድ ቤት፣ ለአዉራጃ ፍርድ ቤት እና ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ላቀርብ እንደሚችል በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 13፣ 14 እና 15 ላይ ከተመለከቱት ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል። ስለሆነም በየደረጃዉ ካለት ፍርድ ቤቶች ጉዲዩን የማየት ስልጣን ያለዉ የትኛዉ ፍርድ ቤት እንደሆነ የሚወሰነዉ የንብረቱን ግምት ወይም ከንብረት ማስመለስ ጥያቄዉ ጋር አብሮ ተያይዞ የሚቀርብ የገንዘብ ጥያቄ (ለምሳላ የማይንቀሳቀስ ንብረትን ለማስመለስ ከሚቀርብ ክስ ጋር ከንብረቱ የሚገኝ ጥቅም ወይም ዉዝፍ ኪራይ ወይም ከንብረቱ የሚገኘዉን ገቢ አጠቃል ማቅረብ እንደሚቻል ሰለሚደነግገዉ የፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 218 /ሀ/ ማየት ይቻላል) መሰረት በማድረግ ነዉ። ከላይ የተመለከተዉ የፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 17 (2) ድንጋጌም ይህንኑ እዉነታ መሰረት በማድረግ የተቀረጸ እንደሆነ ይታመናል።
በልላ በኩል፣ ከፍ ሲል እንደተመለከተዉ፣ ከእርሻ መሬት ጋር በተያያዘ የሚፈጠር አለመግባባት ቢቻል ከሙግት ዉጪ በአማራጭ በአገር ሽማግላዎች እንዱታይ ካልሆነም ለወረዲ ፍርድ ቤት በመጀመሪያ መቅረብ እንዲለበት የክልለ የገጠር መሬት አስተዲደር እና አጠቃቀም አዋጅ አስገዲጅነት ባለዉ ኃይለ ቃል በግልጽ የሚደነግግ በመሆኑ ከዲኝነት ስልጣን ጋር በተያያዘ በጠቅላላዉ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ ላይ የተመለከቱት ድንጋጌዎች ለተያዘዉ ጉዲይ ተፈፃሚነት አይኖራቸዉም። ይህም ማለት የእርሻ መሬትን የሚመለከት የዲኝነት ጥያቄ ከመሬቱ ከሚገኘዉ የአላባ ግምት ጭምር መቅረቡ እና የአላባዉ ግምት ከወረዲዉ ፍርድ ቤት ስልጣን በላይ ሆኖ መገኘቱ ዲኝነቱ በከፍተኛ ፍርድ ቤት እንዱታይ ምክንያት ላሆን አይገባም ማለት ነዉ። ከአላባ ግምት ጋር ተጣምሮ በመቅረቡ ምክንያት ከገጠር መሬት ጋር ተያይዞ የሚቀርብ ክርክር ለዚህ ዓላማ በአዋጁ የተዘረጋዉን ሥርዓት ሳይከተል የቀረበዉን የገንዘብ ግምት ለማየት ስልጣን ላለዉ ለዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንዱቀርብ ማድረግ ከላይ የተመለከተዉን የአዋጁን ዓላማ የሚያፊልስ ዉጤት ይኖረዋል። በአዋጁ በተዘረጋዉ ስርዓት መሰረት ጉዲዩ እንዱታይ ካለመፈለግ በአላባ እያሳበቡ ጉዲዩ በቀጥታ በተለይም ለከፍተኛ ፍርድ ቤት እንዱቀርብ ለሚፈልጉ ሰዎችም በር የሚከፍት ሲሆን ይህም አዋጁ በዚህ ረገድ የዘረጋዉ ስርዓት ወጥነት ባለዉ መልኩ ተግባራዊ እንዲይሆን ምክንያት ይሆናል። ስለሆነም ምንም እንኳ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ ላይ ከስልጣን ጋር በተያያዘ የተመለከቱት መርሆዎች እንደየአግባብነታቸዉ ተፈፃሚ ሉሆኑ የሚችለበት ሁኔታ ቢኖርም፣ ከገጠር መሬት ጋር በተያያዘ የሚፈጠር አለመግባባት ለማየት ስልጣን ያላቸዉን አካላት አስመልክቶ አዋጁ በልዩ ሁኔታ የደነገገ በመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 17(2) ላይ የተመለከተዉ ድንጋጌ ተፈፃሚነት ሉኖረዉ አይገባም።
ይህ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልትም ይህን ሁለ ከግምት ዉስጥ በማስገባት እንዱሁም አጠቃላይ ከገጠር መሬት ጋር ተያይዞ የሚቀርብ የዲኝነት ጥያቄ የሚስተናገድበትን ሥርዓት አስመልክቶ በክልለ አዋጅ ቁጥር 130/99 አንቀጽ 16 ላይ ከተመለከተዉ ድንጋጌ አጠቃላይ ዓላማ አንፃር አገናዝቦ ከመረመረ በኋላ ያላግባብ የተያዘ ገጠር መሬት እንዱመለስለት ክስ የሚያቀርብ ወገን ከመሬቱ ከሚገኝ የአላባ ግምት ጋር አጣምሮ ማቅረብ እንደላለበት እና ፍርድ ቤትም ሉቀበለዉ እንደማይገባ በሰ/መ/ (ቅጽ 21 ላይ እንደታተመዉ) ላይ የህግ ትርጉም ሰጥቷል።
በሰ/መ/ ላይም ተመሳሳይ ይዘት ያለዉ ዉሳኔ ሰጥቷል። ይህም የሚያሳየዉ በአላባ ግምት ሰበብ ከገጠር መሬት ጋር በተያያዘ የሚቀርብ ክርክር ይህንኑ አስመልክቶ በአዋጁ አንቀጽ 16 ላይ ከተዘረጋዉ ሥርዓት ዉጪ ላሆን የማይገባዉ መሆኑን ነዉ።
በመሆኑም የአሁን አመልካች ለክርክሩ መነሻ ከሆነዉ መሬት ላይ መብት አለኝ የሚል ከሆነ በቅድሚያ ጥያቄዉን በክልለ የገጠር መሬት አዋጅ መሰረት በየደረጃዉ ባለት አካላት አቅርቦ መብቱን ካረጋገጠ በኋላ የአላባ ጥያቄዉን ማቅረብ ሲገባዉ ይህን ባለማድረግ ዲኝነቱን ከአላባ ግምት ጋር በማጣመር ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ ማቅረቡ ስህተት ሲሆን፣ የሆሮ ጉደሩ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ይህን የአመልካችን ክስ ዉድቅ ማድረግ ሲገባዉ በአንድ በኩል ፍርድ ቤቱ ስልጣን የለዉም እያለ በልላ በኩል ስልጣን ሲኖረዉ ብቻ የሚመረምረዉን የይርጋ ጉዲይ መሰረት በማድረግ ክሱ በይርጋ ይታገዲል የሚል እርስ በእርሱ የሚጋጭ ዉሳኔ መስጠቱ፤ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ እና ሰበር ሰሚ ችልቶችም ይህን ማረም ሲገባቸዉ ያላግባብ (ስልጣን ለላለዉ) ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረበዉን ክስ መሰረት በማድረግ ጉዲዩን በመመርመር የሰጡት ዉሳኔ ከገጠር መሬት ዲኝነት ጋር በተያያዘ በክልለ የገጠር መሬት አዋጅ ላይ የተመለከተዉን አጠቃላይ ዓላማ የሚያፊልስ ከመሆኑም በላይ ይህ ሰበር ሰሚ ችልት ከላይ በተመለከቱት መዛግብት ላይ የሰጠዉን አስገዲጅ የህግ ትርጉም ያላገናዘበ ሆኖ አግኝተነዋል። በዚህም ምክንያት በስር በየደረጃዉ ያለ የክልለ ፍርድ ቤቶች ዉሳኔ ሙለ በሙለ ሉሻር ይገባዋል በሚል ሃሳብ ከአብላጫዉ ድምጽ በሃሳብ ተለይተናል።
No topics extracted.