ከማስታወቂያ ስርጭት ጋር በተያያዘ የአሰራጩ ሃላፉነት። የማስታወቂያ አዋጅ ቁጥር 759/2004
No summary available.
የሰ/መ/ ሐምል 30 ቀን 2013 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሀኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሀኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካቾች፡ 1ኛ. ኢቢኤስ ቴላቪዥን-ጠበቃ ጥላሁን ሰቦቃ 2ኛ. የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን- ነ/ፈጅ ተስፊዬ አይናለም ተጠሪዎች፡ 1ኛ. አቶ አምሳለ ሲሳይ ደምሴ 2ኛ. አቶ ቢራራ ካሳሁን 3ኛ. አቶ ሲሳይ አረጋ ስዩም 4ኛ. አቶ ቃለአብ ብርሃን መኮንን 5ኛ. አቶ ኑረዱን አብደለጢፍ አብደ 6ኛ. አቶ መርሃ አድሰው ታፈሰ 7ኛ. አቶ ሑርጳሳ ዲንጌ አንጌሳ 8ኛ. አቶ አድማው ጎበና ፈታ 9ኛ. ወ/ሮ ራሄል ዮሴፍ ሙላት 10ኛ. አቶ ቃሲም እርጋ አብድ 11ኛ. አቶ ብርሀነ ታምራት ገ/ስላሴ 12ኛ. አቶ ዲንኤል ሀይላ ወልደየስ 13ኛ. ዜድ ዋይ ኮንስትራክሽን 14ኛ. አቶ ዮናስ ያይንሸት ወ/ሩፊኤል 15ኛ. አቶ ቆጭቶ ሙቹላ ማሞ 16ኛ. አቶ ተስፊዬ ሙንዬ ገረመው 17ኛ. አቶ ተወልደ ግደይ ገ/እግዜአብሓር 18ኛ. አቶ ጠና ተፈራ ምስክር 19ኛ. አቶ መገርሳ ጫላ ጉልማ 20ኛ. አቶ ብስራት ጉታ ዲባ 21ኛ. አቶ ግርማ ጉዱሳ ደበላ 22ኛ. አቶ ሓኖክ ወርቁ 23ኛ. አቶ ተስፊዬ ብርሀኑ አምሳለ 24ኛ. አቶ ግርማይ አሰፊ 25ኛ. አቶ ዮሐንስ መንገሻ ወጀቡ 26ኛ. አቶ ኢሳያስ ወለደ ክፍላ 27ኛ. አቶ ፍትዊ ፀሀዬ ገ/ሕይወት 28ኛ. አቶ ፔትሪኦት በረከት ስብስብ 29ኛ. አቶ አመኑ ለሚ ስዩም 30ኛ. አቶ ተቀባ ገ/ወልድ ላልሾ 31ኛ. አቶ ያሲን ካሳ ፊሪስ 32ኛ. ወ/ሮ ታሪካ ወተንጎ አደሬ 33ኛ. አቶ ገብረህይወት ሙላው 34ኛ. አቶ አዱስ ጥላሁን ተፈራ 35ኛ. አቶ አክሉለ ሰርጡ ጀማነህ 36ኛ. አቶ ዮሴፍ ደበበ 37ኛ. አቶ ተካበ ተሰማ ታንቶ 38ኛ. አቶ አበባ አስራት 39ኛ. ሁአብ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር 40ኛ. ዙና ትሬዱንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር 41ኛ. አቤኔዘር ገበየው (አቤኔዘር ገበየው የማስታወቂያ ስራ ድርጅት) 42ኛ. አቶ ሰለሞን ክንፈ ገ/እግዚአብሓር 43ኛ. አቶ ፀጋው ወዲጅነው አብተው 44ኛ. አቶ በለጠ ንጉሴ ደስታ 45ኛ. አቶ አለማየው አበበ አንዲቦ 46ኛ. አቶ አብደ መሐመድ አደም 47ኛ. አቶ ኢብራሂም ይማም ሰይድ 48ኛ. አቶ አበራ ለታ ደላ 49ኛ. አቶ ጎሳዬ አለማየው ግርኬ 50ኛ. አቶ ከተማ መንግስቱ ጉርሙ 51ኛ. አቶ አበባየው ሙሳ ረቡ 52ኛ. ወ/ሪት ስምሃር ጁሀር ሙሀባ 53ኛ. አቶ ኑረደን ዱታሞ አብደላ 54ኛ. አቶ ሳምሶን በላይ ዘውዳ 55ኛ. አቶ ኤርሚያስ ተሾመ ዘለላ 56ኛ. አቶ ጌዱዮን አሰፊ ተስፊማርያም 57ኛ. መ/አ ፀጋዬ ብርሀኑ ገ/ሚካኤል 58ኛ. አቶ ወልደጊዮርጊስ ለሜሳ ተሉላ 59ኛ. ወ/ሮ የሺ አጥላ ተክላ 60ኛ. አቶ ጌቱ ኡርጋ ደበላ 61ኛ. ወ/ሮ መሰረት ንብረት ገበየው 62ኛ. ዶ/ር ዘበናይ ቢተው ዘለቀ 63ኛ. አቶ በልዩ ጥላሁን ተፈራ 64ኛ. ወ/ሪት መሰረት ተክላ ወርቁ 65ኛ. የገሱባ ኮ/ኃ/የተ/የግ/ማህበር 66ኛ. አቶ ካላዩ መሐሪ ካህሳይ 67ኛ. አቶ የማነ ተስፊይ ረዲ 68ኛ. ዱሻ የህንፃ ስራ ተቋራጭ 69ኛ. አቶ ዲንኤል ገ/መድን ተስፊዬ እና ገ/የ/ሸ/ማ 70ኛ. አቶ ጥላሁን ታደሰ ሸንቁጥ 71ኛ. አቶ ጌታቸው ጀንበር 72ኛ. አቶ መስፍን ፈይሳ ወልቀባ 73ኛ. አቶ ከተማ ሙለታ ታደሰ 1ኛ አመልካች እና ስማቸው ከተራ ቁጥር 1 እስከ 41 የተጠቀሱት ተጠሪዎች እንደየ ቅደም ተከተላቸው በሰ/መ/ አመልካች እና ተጠሪዎች ሲሆኑ 2ኛ አመልካች እና ስማቸው በተራ ቁጥር 1-4፣ 42፣ 43፣ 5-7፣ 44፣ 45፣ 8፣ 46-50፣ 9፣ 51፣52፣ 11፣ 12፣ 53፣ 13፣ 54፣ 55፣ 14፣ 56፣ 15- 17፣ 58-59፣ 18-20፣ 6፣ 21፣ 22፣ 61፣ 62፣ 23፣24፣ 63፣ 25፣ 64፣ 26፣ 27፣ 65፣ 28-31፣ 66- 68፣ 32-35፣ 69፣ 36፣37፣ 70፣ 38፣ 71፣ 39፣ 73 ላይ የተጠቀሱት ተጠሪዎች በዚህ ቅደም ተከተል በሰ/መ/ አመልካች እና ተጠሪዎች ናቸው። የሰበር አቤቱታው ተመሳሳይ የፍሬ ነገር እና የሕግ ክርክር የተደረገበት እና በስር ፍ/ቤት ጉዲያቸው በአንድ መዝገብ በታየ ተመሳሳይ ተከራካሪዎች መካከል የቀረበ ስለሆነ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 11 መሰረት በሰ/መ/ አጣምረን በመመርመር ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ክርክሩ ውልና ከውል ውጪ ግንኙነትን የሚመለከት ሲሆን ጉዲዩ በተጀመረበት የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአሁን ተጠሪዎችን ጨምሮ 98 ሰዎች ከሳሾች፣ 40ኛ ተጠሪ 1ኛ ተከሳሽ፤ 1ኛ አመልካች 3ኛ ተከሳሽ፣ 2ኛ አመልካች 2ኛ ተከሳሽ እንዱሁም 1ኛ አመልካች የአሁን 41ኛ ተጠሪ ጣልቃ እንዱገባለት ባመለከተው መሰረት ጣልቃ ገብ በመሆን ተከራክረዋል። የስር ከሳሾች በከፍተኛ ፍ/ቤቱ በተለያዩ ሶስት መዝገቦች የስር ተከሳሾች ላይ ያቀረቡት ክስም በኮ/መ/ ተጣምሮ እልባት አግኝቷል።
ተጠሪዎች ባቀረቡት ክስ 40ኛ ተጠሪ የኮንስትራክሽን መሳሪያዎችን፣ መለዋወጫዎችን እና መገልገያዎችን ከላላ ሀገር ወደ ኢትዮጵያ ማስገባት የሚያስችለው ቁጥሩ 14/673/212364/2007 የሆነን የንግድ ስራ ፈቃድ መስከረም 21 ቀን 2007 ዓ.ም ከንግድ ሚኒስቴር ማግኘቱን ተከትል ፈቃድ ያገኘበትን የንግድ ስራ መስክ የሚመለከት በቴሉቪዥን ጣቢያዎች የሚተላለፍ የኦዱዮቪዥዋል ማስታወቂያ 41ኛ ተጠሪ እንዱሰራለት ተዋውል ማስታወቂያው የተነገረላቸውን ተሽከርካሪዎች እና መሳሪያዎችን የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስልችን የያዘ ማስታወቂያ ተሰርቷል። ይህንንም ማስታወቂያ በአመልካቾች የቴላቪዥን ጣቢያ ለማስተላለፍ 1ኛ አመልካች በወኪሉ ኢንኮም ትሬዱንግ አማካኝነት ማስታወቂያውን ካዘጋጀው እና የማስታወቂያ ወኪል ከሆነው 41ኛ ተጠሪ ጋር በመዋዋል ከጥቅምት 20 እስከ ጥር 30 ቀን 2008 ዓ.ም እንዱሁም 2ኛ አመልካች ከ40ኛ ተጠሪ ጋር በተደረገ ውል ከነሐሴ 10 ቀን 2007 እስከ የካቲት 26 ቀን 2008 ዓ.ም ማስታወቂያው በቴላቪዥን ጣቢያዎቹ ተላልፎል። የስር ከሳሾችም በቴላቪዥን ጣቢያዎቹ የተነገረውን ማስታወቂያ በማመን ከ40ኛ ተጠሪ ጋር በተናጠል በተደረገ የውል ስምምነት 336 የፈረስ ጉልበት ያላቸውን ሲኖ ትራክ ገልባጭ መኪና እና የተለያዩ ማሽነሪዎችን ውለ በተደረገ ከ75 እስከ 90 ቀናት ባለው ግዜ ውስጥ ሉያስረክበን፣ ተጠሪዎች (የስር ከሳሾች) የጉምሩክ ፍርማሉቲዎችን ለማጠናቀቅ ይቻል ዘንድ በኢንቨስትመንት አዋጁ መሰረት የግብር ምህረት ወይም ላልች ማበረታቻ የሚያስገኙልንን ሰነድች ውለ ሲፈረም ለማስረከብ፤ ድርጅቱም 50% የሚሆነውን ብድር ከመንግስት ወይም ከግል ባንኮች የምናገኝበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ተስማምቶ ከ25 እስከ 50% የሚደርስ ቅድሚያ ክፍያ የፈጸምን ቢሆንም ድርጅቱ (የስር 1ኛ ተከሳሽ) የውል ግዳታውን አልተወጣም። 40ኛ ተጠሪ ማስታወቂያውን ያስነገረው እንዱሁም ከስር ከሳሾች ጋር ውል በመፈረም ገንዘብ የሰበሰበው ተሽከርካሪዎቹን ወደ ሀገር ውስጥ ሳያስገባ እና የንግድ ፈቃደ የተሰጠበት የበጀት አመት ካለፈ በኋላ ሳያሳድስ የማታለል ተግባር ለመፈፀም አስቦ ሲሆን ከሳሾችም ውለን የተዋዋለት በአመልካቾች ቴላቪዥን የተነገረውን ማስታወቂያ በማመን ነው። አመልካቾች ማስታወቂያውን ከማሰራጨታቸው በፉት ድርጅቱ የታደሰ ንግድ ፍቃድና ለሚያስተዋውቃቸው ምርቶች የብቃት ማረጋገጫ ያለው መሆኑን፤ ማስታወቂያው የድርጅቱን ትክክለኛ የንግድ እንቅስቃሴ የሚያሳይ፣ እውነተኛ፣ የማያሳስት፣ በማስታወቂያው የታዩት ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ፣ ቀረጥ የተከፈለባቸው መሆኑን የማረጋገጥ ግዳታቸውን ባለመወጣት ከሳሾች እንዱሳሳቱ አድርገዋል። በመሆኑም የከፈልነውን የቅድመ ክፍያ ውለ ሉፈፀም ከሚገባው ቀን አንስቶ ከሚታሰብ ወለድ እንዱሁም ውለ ቢፈፀም ተሽከርካሪዎቹን በማከራየት እናገኝ የነበረው የቀን ገቢ በቀን ብር 2,666.66 ታስቦ እንዱከፍለ ይወሰንልን በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል።
የስር 1ኛ ተከሳሽ በሰጠው መልስ ለማታለል በማሰብ የፈጸምኩት ተግባር የለም፤ እንደ ውለ ያልፈጸምኩት በውጭ ምንዛሬ እጥረት ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ነው፤ ከሳሾች ግማሽ ክፍያ ብቻ የከፈለ ስለሆነ የታጣ ገቢ ሉጠይቁ አይችለም፤ ወለድም ልከፍል አይገባም በማለት ተከራክሯል።
1ኛ አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እና የፍሬ ነገር ክርክር አቅርቧል።
በፍሬ ጉዲይ ላይ በሰጠው መልስ ከሳሾች ውለን የተዋዋለት መኪኖቹ በ40ኛ ተጠሪ እጅ እንደላለና ወደ ፉት ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ መሆናቸውን በግልፅ አውቀው እና ተረድተው ውለ ከተፈረመበት ጊዜ አንስቶ ከ75 እስከ 90 ቀናት ውስጥ ለመረከብ ተስማምተው ነው፤ ውለን በተዋዋለበት ጊዜ ተሽከርካሪዎቹ በስር 1ኛ ተከሳሽ እጅ የሚገኙ መሆኑን ማረጋገጥ ስለነበረባቸው ለክሱ ኃላፉነት የለብኝም።
ማስታወቂያው አሳሳች ወይም ተገቢ ያልሆነ ይዘት የለውም፤ በሀሰት የተነገረ ነው ከተባለም በ41ኛ ተጠሪ የተዘጋጀ በመሆኑ እና 1ኛ አመልካች በማስታወቂያው የተነገረውን ለመጠራጠር የሚያበቃው ተጨባጭ ሁኔታ ስለላለ ኃላፉ ልሆን አይገባም። ማስታወቂያው በተነገረበት ጊዜም ተከሳሽ የፀና የንግድ ፍቃድ ነበረው፤ አብዛኞቹ ከሳሾች ተከሳሽ የፀና የንግድ ፍቃድ አልነበረውም በሚለበት ጊዜ ውስጥ ውል ፈፅመዋል፤ የስር 1ኛ ተከሳሽ ለሚያስተዋውቃቸው ምርቶች የብቃት ማረጋገጫ ያለው መሆኑን የማረጋገጥ ኃላፉነት የለብኝም፤ በውለ መሰረት ከሳሾች ለስር 1ኛ ተከሳሽ የኢንቨስትመንት ፍቃዲቸውን የማቅረብ ግዳታን አልተወጡም፤ ወለድ እንዱከፈላቸው ያቀረቡት ጥያቄም ተገቢ አይደለም። በከሳሾች ላይ ለደረሰው ጉዲት 1ኛ አመልካች ኃላፉነት አለበት የሚባል ከሆነ በማስታወቂያ አዋጅ ቁጥር 759/2004 አንቀፅ 34(1)(ለ) መሰረት መረጃን የማረጋገጥ ግዳታን መተላለፍ የሚያስከትለው ቅጣት ከብር 10,000 እስከ ብር 100,000 በመሆኑ ከዚሁ ጋር ተገናዝቦ ሉወሰን ይገባል በማለት ተከራክሯል።
2ኛ አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስ ማስታወቂያውን ያስተላለፍኩት 40ኛ ተጠሪ መስከረም 21 ቀን 2007 ዓ.ም ከንግድ ሚኒስቴር የተሰጠው ቁጥሩ 4/673/212364/2007 የሆነ የንግድ ፈቃድ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችን፣መለዋወጫዎችንና መገልገያዎችን ከላላ ሀገር አስመጥቶ ኢትዮጵያ ውስጥ ለመሸጥ የሚያስችለው መሆኑን አረጋግጬ ነው፤ ማስታወቂያው መተላለፍ በጀመረበት ነሐሴ 10 ቀን 2007 ዓ.ም የፀና ንግድ ፍቃድ ነበረው፤ ተሽከርካሪዎቹ ከቀረጥ ነፃ የገቡ እንዱሁም ለሚያስተዋውቀው እቃ የብቃት ማረጋገጫ ያለው መሆኑን የማረጋግጥ ግዳታ የለብኝም፤ ማስታወቂያውም የስር 1ኛ ተከሳሽ በፍ/ሕ/ቁጥር 1687 መሰረት የኮንስትራክሽን መሳሪያዎችን ከውጪ አስመጥቶ ለመሸጥ ያለውን ፍላጎት ያሳወቀበት በመሆኑ አስገዲጅ አይደለም፤ ከሳሾችም ውለን ሉፈፅምላቸው የሚችል መሆኑን ማረጋገጥ ነበረባቸው፤ ማስታወቂያው በአመልካች ቴላቪዥን መተላለፍ ከመጀመሩ በፉት ድርጅቱ ጋር ውል የገቡ ከሳሾች አመልካች ላይ ክስ ሉያቀርቡ አይችለም በማለት ተከራክሯል።
41ኛ ተጠሪ በበኩለ የተነገረው ማስታወቂያ 40ኛ ተጠሪ በውለ መሰረት ባለመፈጸሙ ከሳሾች ደርሶብናል ከሚለት ጉዲት ጋር የምክንያት እና የውጤት ግንኙነት የለውም። ማስታወቂያው የተዘጋጀው ማስታወቂያ የሚነገርላቸውን የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች፤ መለዋወጫዎች፤ መገልገያዎች እና አቅርቦቶች ከላላ ሀገር ወደ ሀገር ውስጥ አስመጥቶ ለመሸጥ የፀና ፍቃድ ባለው ጊዜ ሲሆን ማስታወቂያው በተነገረበት ጊዜም ፍቃደ አልተሰረዘም። ከሳሾችም ውለን ሲዋዋለ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎቹ በ1ኛ ተከሳሽ እጅ የሚገኙ መሆናቸውን ማረጋገጥ ነበረባቸው። የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎቹን ያልተረከቧቸው ስለሆኑ ጉዲት ስለመድረሱ አልተረጋገጠም። የከፈለትንም ገንዘብ ሉጠይቁ የሚችለት ከከፈለት ሰው ነው በማለት ተከራክሯል።
ፍርድ ቤቱም 40ኛ ተጠሪ ከሳሾች ለቅድመ ክፍያ የሰጡትን ገንዘብ እንዱመልስላቸው ያቀረቡትን ክስ ስላመነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 242 መሰረት ሐምል 28 ቀን 2009 ዓ.ም በዋለው ችልት ከከሳሾች የተቀበለውን ቅድመ ክፍያ እንዱመልስ ከፉል ፍርድ ሰጥቷል። በላልች ጉዲዮች ግራ ቀኙን አከራክሮ በ1ኛ አመልካች የቀረበውን መቃወሚያ ውድቅ ያደረገ ሲሆን 40ኛ ተጠሪ ከከሳሾች ጋር በተናጠል ባደረገው ውል 336 የፈረስ ጉልበት ያላቸውን ሲኖ ትራክ ተሽከርካሪዎች ውለ በተደረገ ከ75 እስከ 90 ቀናት ውስጥ ለማስረከብ ተስማምቶ ከ25 እስከ 50 በመቶ የሚሆን ክፍያ የተቀበለ ቢሆንም በዚህ አግባብ አልፈፀመም። ተጠሪዎች ማሽኖቹን ስራ ላይ አሰማርተው የሚያገኙትን የተጣራ ትርፍ ማወቅ የሚቻለው ማሽኖቹን በእጃቸው አስገብተው ገቢ በሚያስገኙላቸው ስራዎች ላይ ካሰማሩ በኋላ በመሆኑ እንደ ውለ ባለመፈጸሙ አጥተነዋል የሚለትን ገቢ 40ኛ ተጠሪ የመክፈል ኃላፉነት የለበትም። የውጭ ምንዛሬ እጥረት በፍ/ሕ/ቁጥር 1792(1) መሰረት አስቀድሞ ላታይ እና ሉገመት የማይችል አይነት ክስተት ስላልሆነ የውል ግዳታውን ላለመወጣቱ ተቀባይነት ያለው ምክንያት አይደለም። ከሳሾች ክፍያውን የፈፀሙት መኪኖቹን እና ማሽነሪዎቹን በስራ ላይ በማሰማራት ገቢ ለማግኘት በመሆኑ እና ባንክ ቢያስቀምጡት ኖሮ ጥቅም ስለሚያገኙበት 40ኛ ተጠሪ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 242 ባመነው መሰረት ሐምል 28 ቀን 2009 ዓ.ም በዋለው ችልት በተሰጠው ፍርድ ላይ ለከሳሾች እንዱከፍል በተወሰነው የገንዘብ መጠን ላይ ውልቹ ሉፈፀሙ ከሚገባበት ቀን ጀምሮ ወለድ ሉከፍል ይገባል።
40ኛ ተጠሪ የኮንስትራክሽን መሳሪያዎችን፣ መለዋወጫዎችን፣ መገልገያዎችንና አቅርቦቶችን ከላላ ሀገር አስገብቶ ኢትዮጵያ ውስጥ ለመሸጥ የሚያስችለው ቁጥሩ 14/673/21236/2007 የሆነ የንግድ ስራ ፈቃድ መስከረም 21 ቀን 2007 ዓ.ም በንግድ ሚኒስቴር ተሰጥቶታል። ንግድ ፍቃደ በወቅቱ በስራ ላይ በነበረው የንግድ ስራ አዋጅ ቁጥር 686/2002(እንደተሸሻለ) አንቀፅ 2(10)(24) መሰረት እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2008 ዓ.ም ሉያገለገል ይችላል። ማስታወቂያውን በቴላቪዥን ለማስተላለፍ ውል በተፈረመበትና በቴላቪዥን ጣቢያዎቹ የኦዱዮቪዥዋል ማስታወቂያ መተላለፍ በጀመረበት ጊዜ ንግድ ፍቃደ የፀና በመሆኑ የንግድ ፍቃደ መታደስ አለመታደሱ ማረጋገጥ ሳይጠበቅባቸው በውለ ለተመላከተው ጊዜ ማስታወቂያውን የማስተላለፍ ግዳታ ስላለባቸው የንግድ ፍቃድን በሚመለከት የማስታወቂያ አዋጅ ቁጥር 759/2004 ድንጋጌን ጥሰዋል ለማለት አይቻልም። 40ኛ ተጠሪ ለሚያስተዋውቀው መኪና እና ማሽነሪዎች በማስታወቂያ አዋጅ ቁጥር 759/2004 አንቀፅ 9(1)(2) መሰረት የጥራት ደረጃ ማረጋገጫ ሉኖረው እንደሚገባ እንዱሁም በምን መንገድ ለውለ አለመፈጸም ምክንያት እንደሆነም ከሳሾች አላስረደም።
በተጨማሪም አመልካቾች ተሽከርካሪዎቹና ማሽነሪዎቹ ቀረጥ የተከፈለባቸው መሆን አለመሆኑን ለማረጋገጥ በአዋጁ የተጣለባቸው ግዳታ የለም። ነገር ግን በአመልካቾች የቴላቪዥን ጣቢያ የተላለፈው ማስታወቂያ የተነገረላቸው መኪኖችና ማሽነሪዎችን 40ኛ ተጠሪ ከውጪ ሀገር አስመጥቶ ሀገር ውስጥ የገቡ መሆኑን ጭምር መልእክት የሚያስተላልፈ እንደነበር ፍ/ቤቱ የተገነዘበ ቢሆንም ማስታወቂያው በተዘጋጀበት ጊዜም ሆነ በተነገረበት ጊዜ በ40ኛ ተጠሪ እጅ ምንም አይነት መኪናም ሆነ ማሽነሪ አልነበረም። አመልካቾች ይህንንም አልካደም። 41ኛ ተጠሪ ማስታወቂያውን ሲያዘጋጅ፣ አመልካቾችም ማስታወቂያውን ከማስተላለፊቸው በፉት መኪኖቹን እና ማሽነሪዎቹን 40ኛ ተጠሪ ከውጪ ሀገር አስመጥቶ ሀገር ውስጥ እንዲለ አለማረጋገጣቸው ተገቢ አይደለም። ማስታወቂያው መኪናዎቹ እና ማሽነሪዎቹ ሀገር ውስጥ ገብተው በድርጅቱ እጅ ይገኛለ የሚል የተሳሳተ ግንዛቤን በተመልካቾች ዘንድ ሉያሳድር የሚችል አሳሳች ወይም ተገቢ ያልሆነ ይዘት ወይም አቀራረብ ያለው ማስታወቂያ ነው።
አመልካቾችም የተነገረው ማስታወቂያ ይህን እምነት አይፈጥርም፤ ከሳሾችም ማስታወቂያው በቴላቪዥን ሲተላለፍ አልተመለከቱም በማለት ያቀረቡት መከራከሪያ የለም። በመሆኑም በአዋጁ የተጣለባቸውን ማስታወቂያው አሳሳች ወይም ተገቢ ያልሆነ ይዘት ወይም ትክክለኛ አቀራረብ ያለው አለመሆኑን እንዱሁም በማስታወቂያው የተነገረው ነገር ትክክል መሆኑን የማረጋገጥ ግዳታቸውን አልተወጡም።
የአዋጁን ድንጋጌዎች በመተላለፍ ለተሰራጨ ማስታወቂያ ማስታወቂያ አስነጋሪው፣ የማስታወቂያ ወኪለ እና ማስታወቂያ አሰራጩ ሃለፉነት ያለባቸው ስለመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 759/2004 አንቀፅ 30 ላይ የተገለፀ ሲሆን በህግ በትክክል የተገለፀ ድንጋጌን መተላለፍም ጥፊት መሆኑ በፍ/ሕ/ቁጥር 2055(1) ላይ ተመላክቷል። ስለሆነም 41ኛ ተጠሪ እና አመልካቾች ማስታወቂያው ሉያሳድር በሚችለው የተሳሳተ እምነት ለደረሰ ጉዲት ከውል ውጪ 1ኛ አመልካች ከ1ኛ- 3ኛ ላለት ተጠሪዎች ብቻ፤ 2ኛ አመልካች ተጠሪ ከ1ኛ- 39ኛ እና 42ኛ-73ኛ ላለት ተጠሪዎች ከ40ኛ እና 41ኛ ተጠሪዎች ጋር በአንድነት እና በነጠላ ኃላፉነት አለባቸው።
በማስታወቂያ አዋጅ ቁጥር 759/2004 አንቀፅ 34(1)(ለ) ከብር 10,000 እስከ 100,000 በሚል የተገለፀው መቀጮ መረጃን የማረጋገጥ ግዳታን ያልተወጣ ማንኛውም ሰው ሉከተለው የሚገባን የቅጣት ወሰን የሚያመላክት እንጂ በማስታወቂያ የተነሳ ለደረሰ ጉዲት ከውል ውጪ የፍትሐብሕር ኃላፉነት ያለበት ሰው ለጉዲቱ ሉከፍል የሚገባውን የካሳ መጠን ለመወሰን የተደነገገ አይደለም። ነገር ግን ከሳሾቹ ማስታወቂያውን ከተመለከቱ በኋላ መልእክቱን ብቻ በማመን እንዲለ ተቀብል ከመዋዋል መኪኖቹ እና ማሽኖቹ ሀገር ውስጥ ገብተው በ40ኛ ተጠሪ እጅ የሚገኙ መሆኑን በራሳቸው በኩል ለማጣራት ሙከራ ቢያደርጉ ውለን ከመዋዋል በመቆጠብ የደረሰባቸውን ጉዲት የማስቀረት እድል የነበራቸው በመሆኑ ለደረሰው ጉዲት አስተዋፅኦ አድርገዋል። በመሆኑም በፍ/ሕ/ቁጥር 2098(2) መሰረት አመልካቾችና 41ኛ ተጠሪ 40ኛ ተጠሪ ከከሳሾች ላይ ከወሰደው ቅድመ ክፍያ ገንዘብ ውስጥ 1/4ኛውን ብቻ ውልቹ ሉፈጸሙ ይገባ ከነበረበት ቀን አንስቶ የሚታሰብ ወለድን ጨምሮ ከ40ኛ ተጠሪ ጋር የመክፈል የአንድነት እና የነጠላ ኃላፉነት አለባቸው በማለት ወስኗል።
አመልካቾች ውሳኔውን በመቃወም በየግላቸው ይግባኛቸውን ለፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ያቀረበ ቢሆንም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት የከፍተኛ ፍ/ቤቱን ውሳኔ አፅንቶታል።
አመልካቾች ሐምል 27 ቀን 2012 ዓ.ም የተፃፈ የሰበር አቤቱታቸውን ያቀረቡት ይህን የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የ1ኛ አመልካች የሰበር አቤቱታ ባጭሩ ለክሱ መነሻ የሆነው ማስታወቂያ ይዘት እና አቀራረብ አሳሳች ወይም ተገቢ ያልሆነ ልባል የሚችል ስለመሆኑ በማስታወቂያና ሚድያ ልዩ ባለሙያዎች እንዱጣራ ለይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤቱ ባቀረብነው አቤቱታ መሰረት አለመጣራቱ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 327(3)፣ 345(1)(ለ)፣ 136 እና 182 ድንጋጌን ይቃረናል። ተጠሪዎች ውለን ከተዋዋለ በኋላ የባንክ ሑደቶችን ተከታትለው ማሟላታቸው፣ ተሽከርካሪዎቹ ከ75 እስከ 90 ቀናት ውስጥ ከውጪ ሀገር ግዢ የሚፈጸምባቸው እና ውለ በርካታ ቅድመ ሁኔታዎች ያለት መሆኑ ተጠሪዎች ተሽከርካሪዎቹ ሀገር ውስጥ እንደላለ እያወቁ የተዋዋለ መሆኑን የሚያረጋግጥ በመሆኑ ማስታወቂያው በፍ/ሕ/ቁ 1697 እና 1698 በተገለፀው አግባብ ውለን ለመቀበል የሚያደርስ ስህተትን የማያስከትል ስለመሆኑ ሉመረመር ይገባ ነበር። በ1ኛ አመልካች የተሰራጨው ማስታወቂያ የማስታወቂያ አዋጁን ድንጋጌ በመተላለፍ የተሰራጨ ነው ቢባል እንኳ የማስታወቂያ አስነጋሪው፣ የማስታወቂያው ወኪል እና የማስታወቂያው አሰራጭ ተሳትፍ ተለይቶ በአዋጀ ቁጥር 759/2005 አንቀፅ 30 በተገለፀው አግባብ በአንድነት ወይም በነጠላ ያለብን ኃላፉነት ሳይለይ በአንድነት እና በነጠላ ኃላፉነት አለባችሁ ተብል መወሰኑ ተገቢ አይለም። ተጠሪዎች በ1ኛ አመልካች በተነገረው ማስታወቂያ ተሳስተን የሽያጭ ውለን ተዋውለናል በማለት የሚያነሱትን መከራከሪያ የውለን ይዘት መሰረት በማድረግ ከተሸከርካሪዎች ግብይት ጋር በተያያዘ በሀገሪቱ ያለውን የንግድ ልምድ (Trade Custom) እና በንግደ መስክ የዲበረውን የንግድ አፈፃፀም ስርዓት (Usage) ጋር በፍ/ሕ/ቁጥር 1713 እና 1732 መሰረት ተገናዝቦ ሳይመረመር የተሰጠው ውሳኔ ተገቢ አይደለም።
ከማስታወቂያው ቪዱዮ ዝግጅት ጋር በተያያዘ 1ኛ አመልካች ምንም አይነት አስተዋፅኦ እንደላለው ለማስረዲት የቆጠራቸው ምስክሮች አለመሰማታቸው፣ ማስታወቂያውንም ከ1ኛ አመልካች ቀድሞ ፊና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ሬድዮ አስተላልፍት የነበረ መሆኑን ገልጾ ጣልቃ እንዱገባለት በጠየቀው መሰረት አለመታዘዙ፣ ማስታወቂያው በሚነገርበት ጊዜ 40ኛ ተጠሪ የተወሰኑ ተሽከርካሪዎችን ወደ ሀገር ውስጥ እንዲስገባ ወይም በሂደት ላይ እንደነበር ከጉምሩክ እንዱጣራ ጠይቆ ሳይጣራ መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስለሆነ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
የ2ኛ አመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘት 1ኛ አመልካች ካቀረበው ቅሬታ ጋር የሚመሳሰል ሲሆን በተጨማሪም በፍ/ሕ/ቁጥር 2035(1) አንድ ተከሳሽ ኃላፉነት የሚኖርበት ግልፅ ህግን የጣሰ ሲሆን ነው።
አመልካች በማስታወቂያ አዋጅ ቁጥር 759/2004 አንቀፅ 8(1-17) ከተዘረዘሩት ጥፊቶች አንደን ስለመፈፀሙ ሳይረጋገጥ የአዋጁን አንቀፅ 8(18) በመጥቀስ መወሰኑ ተገቢ አይደለም፤ በአመልካች የተላለፈው ማስታወቂያ አሳሳች የሚያስብለው ሁኔታ የለም እንጂ አለ እንኳ ቢባል ቅጣቱ በአዋጁ አንቀፅ 30 እና 34(1)(ሐ) በተደነገገው አግባብ ላሆን ይገባ ነበር። ተጠሪዎች(የስር ከሳሾች) ውል ከመዋዋላቸው በፉት ተገቢውን ማጣራት ቢያደርጉ ኑሮ የደረሰባቸውን ጉዲት ማስቀረት ይችለ ነበር የሚል መደምደሚያ ላይ ደርሶ እያለ በፍ/ሕ/ቁጥር 2097(2) መሰረት 2ኛ አመልካችን ከኃላፉነት ነፃ ማድረግ ነበረበት።
ማስታወቂያው በፍ/ሕ/ቁጥር 1687 መሰረት 40ኛ ተጠሪ ውል ለመዋዋል ያለውን ፍላጎት ከሚያመላክት በቀር ውል ለመዋዋል ጥያቄ እንዲቀረበ ስለማያስቆጥር የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
ጉዲዩ በሰበር አጣሪ ችልቱ ተመርምሮ የስር ፍ/ቤት የያዟቸውን ጭብጦች በተጠቀሰው አዋጅ መሰረት ተገቢውን ማጣራት አድርገው መወሰን አለመወሰናቸውን ከፍ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 241 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች አንፃር ለመመርምር ያስቀርባል በመባለ ተጠሪዎች መልሳቸውን እንዱያቀርቡ ትዕዛዝ ተሰጥቷል።
40ኛ እና 41ኛ ተጠሪዎች በጋዜጣ ጥሪ ተደርጎላቸው ባለመቅረባቸው መልስ የማቅረብ መብታቸው የታለፈ ሲሆን ከ1ኛ እስከ 39 እንዱሁም ከ42ኛ እስከ 73ኛ ስማቸው የተጠቀሰው ተጠሪዎች በጠበቃቸው አማካይነት ጥቅምት 16 ቀን 2013 ዓ.ም የተፃፈ መልሳቸውን አቅርበዋል። የመልሱ ይዘት ባጭሩ የስር 1ኛ ተከሳሽ (40ኛ ተጠሪ) የማታለል ተግባሩን በከፍተኛ ሁኔታ ለማስፊፊት የተጠቀመው የቴላቪዥን ማስታወቂያን በማሰራጨት ሲሆን አንድም መኪና ወደ ሀገር ውስጥ ያላስገባ ቢሆንም በርካታ አዲዱስ መኪኖች ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው እየተጓዙ በማሳየት፤ መኪኖቹን ማስመጣታችንን ስንገልፅ ደስታ ይሰማናል ልዩነታችን 50% የባንክ ብድር ማመቻቸታችን ነው በሚል የላለውን ነገር እንዲለ በማስመሰል የተዘጋጀውን አሳሳች የሀሰት የቪዱዮ ምስልች አመልካቾች በሕግ የተጣለባቸውን የማስታወቂያውን ትክክለኛነት የማረጋገጥ ግዳታ ሳይወጡ በማሰራጨታቸው ተጠሪዎች በማስታወቂያው ምክንያት እምነት እንዱያድርብን እና ገንዘባችንን እንድንከፍል ሁነናል። ተከሳሹም ገንዘቡን ለግል ጥቅሙ በማዋለ ሉከፍለን ስላልቻለ የአንድነት እና የነጠላ ኃላፉነት አለባቸው ተብል የተሰጠው ውሳኔ ተገቢ ነው በማለት ተከራክረዋል።
የክርክሩ አመጣጥ ባጭሩ ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም 1ኛ. በአመልካቾች የቴላቪዥን ጣቢያ የተላለፈው ማስታወቂያ አሳሳች ወይም ያልተገባ አቀራረብ ያለው መሆን? አለመሆኑ? በልዩ አዋቂ ባለሞያዎች ያለመጣራቱ ተገቢ ነው? ወይስ አይደለም?
2ኛ. ማስታወቂያው አሳሳች ወይም ያልተገባ አቀራረብ አለው ከተባለ በአመልካቾች የቴላቪዥን ጣቢያ መተላለፈ የማስታወቂያ አዋጁን ድንጋጌዎች ይቃረናል? ወይስ አይቃረንም? አመልካቾች ላይ የሚያስከትለው ኃላፉነትስ ምንድነው?
3ኛ. ተጠሪዎች ከ40ኛ ተጠሪ ጋር ውለን ሲዋዋለ ተገቢ ማጣራት አለማድረጋቸው እንዱሁም የተዋዋለት ውል ይዘት በተሽከርካሪዎች ግብይት ከዲበረው የንግድ ልምድ (Trade Custom) እና የንግድ አፈፃፀም ስርዓት (Trade Usage) አንፃር የሚኖረው ውጤት ምንድነው?
4ኛ. 1ኛ አመልካች ፊና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ሬድዮ ጣልቃ እንዱገባ፣ ከጉምሩክ ማስረጃ እንዱቀርብ እንዱሁም ምስክሮቹ እንዱሰሙለት ጠይቆ ከነበረ በዚህ አግባብ ያለመታዘዙን አግባብነት እንዱሁም 5ኛ. አመልካቾች ለተጠሪዎች ኃላፉነት አለባቸው ተብል ተጠሪዎች የከፈለትን ቅድመ ክፍያ 1/4ኛ ወለድና ወጪና ኪሳራን ጨምሮ እንዱከፍለ የመወሰኑን አግባብነት በስር ፍ/ቤቶች ከተደረጉ ክርክሮች፣ በማስረጃ ከተረጋገጡ ፍሬ ነገሮች እንዱሁም ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምረነዋል።
የመጀመሪያውን ነጥብ በሚመለከት፡- ጉዲዩን ይበልጥ ለማብራራት ወይም ለትክክለኛ ውሳኔ አሰጣጥ ጠቃሚ መስል በታየው ጊዜ ሁለ ፍርድ ቤቱ በራሱ አነሳሽነት ወይም በተከራካሪዎቹ ወይም ከተከራካሪዎቹ በአንደ አመልካችነት ጉዲዩ በልዩ አዋቂ እንዱመረመር ትዕዛዝ ላሰጥ እንደሚችል በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 136 ላይ ተመላክቷል። በተያዘው ጉዲይ በአመልካቾች የቴላቪዥን ጣቢያ የተላለፈው ማስታወቂያ አሳሳች ወይም ያልተገባ አቀራረብ ነበረው? ወይስ አልነበረውም? የሚለው በልዩ አዋቂ መመርመር ነበረበት ወይ? የሚለውን ለመወሰን የማስታወቂያውን ይዘት ማስታወቂያ ተደራሽ እንዱሆን ከተፈለገው የማህበረሰብ ክፍል አንፃር መመርመሩ ተገቢ ነው። ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት እንዱሁም ይግባኝ ሰሚው የፍደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የኦዱዮ ቪዥዋል ማስታወቂያው 40ኛ ተጠሪ የተለያዩ የኮንስትራክሽን ማሽኖችን፣ የቤት እና የመስክ መኪኖችን፣ ሲኖትራክ፣ ደረቅ ጭነት ገልባጭ መኪኖችን ስለማስመጣቱ እና ወደ ፉትም የሚያስመጣ እና 50% ብድር የሚያመቻች መሆኑን በመግለፅ ተሽከርካሪዎቹን በምስል በማሳየት የተላለፈ እንደነበር ነገር ግን ማስታወቂያው በተዘጋጀበት ጊዜም ሆነ በተነገረበት ጊዜ በ40ኛ ተጠሪ እጅ ምንም አይነት መኪናም ሆነ ማሽነሪ እንዲልነበረ አረጋግጠዋል። ማስታወቂያው የሚነገርበት ዋና አላማም ተሽከርካሪዎቹን እና ማሽነሪዎቹን የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት ከማስታወቂያ አስነጋሪው ጋር ግብይት ውስጥ እንዱገባ ማስቻል ነው። የማስታወቂያው ይዘትም ተሽከርካሪዎቹ እና ማሽነሪዎቹን በምስል የሚያሳይ፣ ሀገር ውስጥ እንደገቡ እና ወደ ፉት እንደሚገቡ የሚገልፅ እና ማንኛውንም ሰው ለግብይት የሚጋብዝ ነው ካልን የማስታወቂያው አሳሳች መሆን አለመሆን ወይም ያልተገባ አቀራረብ ያለው መሆኑ ልዩ አዋቂ የሚያስፈልገው ሳይሆን ይልቁንም አንድ ምክንያታዊ ሰው ማስታወቂያውን በመመልከት ከሚደርስበት መደምደሚያ (reasonable man standard) አንጻር የሚለካ ነው። ማስታወቂያውን የሚመለከት ማንኛውም ምክንያታዊ ሰውም በድምፅ የተነገረውን እና በምስል የታዩት ተሽከርካሪዎች በመመልከት ሀገር ውስጥ ገብተዋል ብል እንዱያምን የሚያደረግ ነው። ማስታወቂያው በተዘጋጀበት ጊዜም ሆነ ከዚያ በኋላ መኪኖቹ እና ማሽነሪዎቹም ሀገር ውስጥ እንዲልገቡ በስር ፍ/ቤቶች ስለተረጋገጠ ማስታወቂያው አሳሳች ነው? ወይስ አይደለም? አቀራረቡስ ያልተገባ ነው? የሚለውን ለመለየት የተለየ የልዩ አዋቂ ማስረጃነት የሚጠይቅ ባለመሆኑ በዚህ ረገድ የቀረበውን የአመልካቾች ቅሬታ አልተቀበልነውም።
ሁለተኛውን ነጥብ በሚመለከት፡- ማስታወቂያ ህብረተሰቡ በሚያከናውነው የምርት ግብይት ውስጥ ተፅእኖ የሚፈጥር፣ ገበያው ጤናማ በሆነ ውድድር እንዱመራ በማድረግ ጉልህ ሚና የሚጫወት፣ በስርዓት ካልተመራም የሕብረተሰቡን መብት እና ጥቅም እንዱሁም የሀገር ገጽታን የሚጎዲ መሆኑ፤ በዚህም ምክንያት የማስታወቂያ ወኪልች፣ የማስታወቂያ አስነጋሪዎች እና የማስታወቂያ አሰራጮችን መብት እና ግዳታ በግልፅ ለመወሰን እንዱቻል የማስታወቂያ አዋጅ ቁጥር 759/2004 መውጣቱን ከአዋጁ መግቢያ ላይ ተጠቅሷል። ይህንን አላማ ለማሳካት ማንኛውም ማስታወቂያ አሳሳች ወይም ተገቢ ካልሆነ አገላለጽ ነፃ መሆን ያለበት ስለመሆኑ፣ በገበያ ውስጥ የላለ ምርት ወይም አገልግልት እንዲለ አስመስል የሚያቀርብ ማስታወቂያ አሳሳች ወይም ተገቢ ያልሆነ ይዘት ወይም አቀራረብ እንዲለው ማስታወቂያ የሚቆጠር ስለመሆኑ፣ መሰል አሳሳች ወይም ተገቢ ያልሆነ ይዘት ወይም አቀራረብ ያለው ማንኛውም ላላ ማስታወቂያ በዚህ ምድብ ስር የሚወድቅ ስለመሆኑ በአዋጁ አንቀፅ 6(1)(ለ)፤ አንቀፅ 8(1)(10)፤
8(18) ላይ ተመላክቷል። በአዋጁ አንቀፅ 27(1)(ሀ) ላይም ማንኛውም የማስታወቂያ ወኪል ወይም አሰራጭ በማስታወቂያ አስነጋሪው የቀረበለትን ማስታወቂያ ትክክለኛነት የማረጋገጥ ግዳታ ያለበት ስለመሆኑ ተገልጿል። በተያዘው ጉዲይ ወደ ሀገር ውስጥ እንደገቡ ተደርጎ ምስላቸው እየታየ ማስታወቂያ የተነገራላቸው ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዲልገቡ በስር ፍ/ቤቶች ተረጋግጧል። ይህም ማስታወቂያውን የሚመለከቱ ሰዎች መኪኖቹ እና ማሽነሪዎቹ ሰዎች ወደ ሀገር ውስጥ ገብተዋል የሚል እምነት እንዱያድርባቸው የሚያደረግ በመሆኑ አሳሳች ወይም ያልተገባ አቀራረብ ያለው ነው።
አመልካቾችም መኪኖቹ እና ማሽኖቹ ወደ ሀገር ውስጥ እንደገቡ በማጣራት የማስታወቂያውን ትክክለኛነት የማረጋገጥ ኃላፉነታቸውን ስላልተወጡ የአዋጁን ድንጋጌዎች በመተላለፍ የተፈፀመ ተግባር ነው።
የአዋጁን ድንጋጌ በመተላለፍ የተሰራጨ ማስታወቂያ በማስታወቂያ አስነጋሪው፣ በማስታወቂያ ወኪለ እና በማስታወቂያ አሰራጩ ፈቃድ እንደተሰራጨ ተቆጥሮ እንደሃላፉነታቸው መጠን በአንድነት ወይም በነጠላ ተጠያቂ እንደሚሆኑ በአዋጁ አንቀፅ 30 ላይ የተገለፀ በመሆኑ ተጠሪዎች በማስታወቂያው ላይ እምነት በማሳደር ተዋውለው ለደረሰባቸው ጉዲት አመልካቾች ኃላፉነት አለባቸው መባለ ተገቢ ነው።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ 2ኛ አመልካች ማስታወቂው በፍ/ሕ/ቁጥር 1687 መሰረት 40ኛ ተጠሪ ውል ለመዋዋል ያለውን ፍላጎት ከሚያመላክት በቀር ውል ለመዋዋል ጥያቄ እንዲቀረበ የሚወሰድ አይደለም በማለት የሚያቀርበውን መከራከሪያ መመልከቱ አስፈላጊ ነው። በተጠቀሰው ድንጋጌ ንዐሰ አንቀፅ ለ ላይ አንድ የእቃ ዝርዝርን የሚያሳይ ፅኁፍ ለላላ ሰው የላከ ወይም በአደባባይ በሚታይ ማስታወቂያ የገለፀ ወይም የንግድ እቃዎች ለሕዝብ ስለመሸጥ ያሳየ የውል ግዳታ እንደገባ የማያስቆጥረው መሆኑ ተመላክቷል። ይህ ድንጋጌ ነጋዳው ባስነገረው ማስታወቂያ መሰረት ውል እንዱገባ ሉገደድ የማይችል መሆኑን የሚያመላክት እንጂ በማስታወቂያ አዋጁ በልዩ ሁኔታ ማስታወቂያ አስነጋሪውም ሆነ ማስታወቂያ አሰራጩ አሳሳች ወይም ትክክለኛ ያልሆነ አቀራረብ ያለውን ማስታወቂያ እንዱሰራጭ ከማድረግ እንዱቆጠቡ እንዱሁም የማስታወቂያ አስነጋሪው የማስታወቂያውን ትክክለኛነት የማረጋገጥ ግዳታውን እንዱወጣ፤ ካልተወጡም በኃላፉነት የሚያስጠይቃቸው መሆኑን የሚገልፅ የአዋጁን ድንጋጌ ተፈጻሚነት የሚያስቀር ስላልሆነ 2ኛ አመልካች በዚህ ረገድ ያቀረበውን ቅሬታ አልተቀበልነውም።
ላላው አመልካቾች በአዋጁ አንቀፅ 34(1) መሰረት ኃላፉነት አለባችሁ ቢባል እንኳ እንደየተሳትፎችን የአንድነት ወይም የነጠላ ኃላፉነት አለባችሁ ተብል መወሰን ሲገባው የአንድነት እና የነጠላ ኃላፉነት አለባችሁ ተብል የተሰጠው ውሳኔ ተገቢ አይደለም በማለት የሚያነሱት መከራከሪያ ነው። ይህ የአዋጁ ድንጋጌ የማስታወቂያ ወኪለ፣ ማስታወቂያ አስነጋሪው ወይም ማስታወቂያ አሰራጩ እንደየሁኔታው ሁለም ወይም አንደ ኃላፉነት አለባችሁ ተብል ሉወሰን የሚችል መሆኑን የሚያመላክት እንጂ ሁለም ኃላፉነት አለባቸው ከተባለ የኃላፉነት ሁኔታ በአንድነት እና በነጠላ እንዲይሆን ክልከላ የሚያደርግ ባለመሆኑ እና ሶስቱም የአዋጁን ድንጋጌ መተላለፊቸው ስለተረጋገጠ ቅሬታው ተገቢነት የለውም።
ሶስተኛውን ነጥብ በሚመለከት፡- ማንኛውም ጠንቃቃ ገዢ ስለሚዋዋልበት ጉዲይ እና ስለሚዋዋልበት ነገር ተገቢውን ማጣራት ማድረግ ያለበት ስለመሆኑ ግልጽ ነው። ተጠሪዎች ውለን ከመዋዋላቸው እና ክፍያ ከመፈፀማቸው በፉት በእርግጥም መኪኖቹ እና ማሽነሪዎቹ በ40ኛ ተጠሪ እጅ ይገኙ እንደነበር በራሳቸው መንገድ ማጣራት ነበረባቸው። የውለን ይዘት በሚመለከትም 40ኛ ተጠሪ ተሽከርካሪዎቹን ከ75 እስከ 90 ባለት ቀናት ውስጥ ሉያስረክባቸው፣ ተጠሪዎች የጉምሩክ ስርዓቱን ማስፈጸም የሚያስችለ ሰነድችን ለድርጀቱ ሉያቀርቡ፤ የክፍያውን 50 በመቶ ድርጅቱ ከባንኮች ጋር ብድር ሉያመቻች እና ተጠሪዎችም ከ25-50 በመቶ የሚሆነው ክፍያ የከፈለ መሆኑን እንደሚገልፅ ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ባላቸው የስር ፍ/ቤቶች ተረጋግጧል። ይህ የውለ ይዘት የሚኖረው ትርጉም በሀገራችን ከዲበረው የተሽከርካሪዎች ግብይት ልምድ (Trade Custom) ጋር ተገናዝቦ ላታይ ይገባዋል። ከዚህ አንፃር የመኪና ሻጮች በእጃቸው ያለ ተሽከርካሪዎችን ለመሸጥ በሚደርጉት ውል የተሽከርካሪው የሻንሲ ቁጥር፣ የሞተር ቁጥር፣ የምርት ዘመን፣ የተሽከርካሪው አይነት እና መሰል ጉዲዮች የሚጠቀሱበት ሲሆን ስም ተዛውሮ እስኪያልቅ ድረስ በገዢው እጅ እንዱቆይ ከሚደረገው መጠነኛ ገንዘብ ውጪ ከግማሽ በላይ የሚሆነው ክፍያ ወዱያው ይከፈላል። በአንፃሩ ተሽከርካሪዎቹ በእጃቸው የላለ ከሆነ የተሽከርካሪውን አይነት ከመጥቀስ በዘለለ ዝርዝር ሁኔታዎች የማይገለፁበት ሲሆን በአብዛኛው ከግማሽ በላይ የሆነው ክፍያ ለሻጭ አይከፈልም።
ይህን የዲበረ የንግድ ልውውጥ ልምድ በተጠሪዎች እና በዙና ትሬዱንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር መካከል የተደረገውን የውል ይዘት ጋር ስናገናዝበው ተጠሪዎች ተሽከርካሪዎቹ በ40ኛ ተጠሪ እጅ እንዲልነበሩ አያውቁም የሚያስብል ሆኖ አላገኘነውም። ይህ ከሆነ አመልካቾች ማስታወቂያ ማስነገራቸው ከ40ኛ እና 41ኛ ውጪ ባለት ተጠሪዎች ላይ ጉዲት እንዱደርስ ያደረገው አስተዋጽኦ ምንድነው? የሚለውን መመርመሩ ተገቢ ነው።
የስር ፍርድ ቤቶች አመልካቾች ያስተላለፈት ማስታወቂያ ይዘት 40ኛ ተጠሪ ተሽከርካሪዎችን እና ማሽነሪዎችን አስመጥቶ የሚሸጥ እና ወደፉትም የሚያስመጣ መሆኑን የሚገልጽ መሆኑን የማስታወቂያውን ቪዱዮ በመመልከት ያረጋገጡ ሲሆን በአመልካቾችም በማስታወቂያው ይዘት ላይ መካካድ የለም። አመልካቾች በሰበር ቅሬታቸው ላይ የሽያጭ ውል የተደረገው 40ኛ ተጠሪ በእጁ የነበሩትን ተሸከርካሪዎች ለመሸጥ ሳይሆን ገና የሚያስመጣቸውን ለመሸጥ የተደረገ ውል ስለሆነ ሃላፉነት የለብንም በማለት ተከራክረዋል። እንደሚታወቀው የንግድ ግንኙነት የማይዲሰሱ(intangible) ጉዲዮች፣ የንግድ መልካም ስም (good wil)፣ መተማመን (trust) እና የመሳሰለትን የሚያካትት ነው። እነዚህ ሁኔታዎች በንግድ ግንኙነት ውሳኔ ላይ ተጽኖ ያላቸው በመሆኑ 40ኛ ተጠሪ ወደ ሀገር ውስጥ ያስገባቸው ተሸከርካሪዎች ሳይኖሩ እንዲለ ተደርጎ አመልካቾች ባስተላለፈት ማስታወቂያ መነገሩ 40ኛ ተጠሪ ውለን ለመፈጸም መልካም ስም(good will) ያለውና ውለን መፈጸም የሚችል ስለመሆኑ እምነት እንዱጣልበት ያደርጋል። ይህም ማለት ተጠሪዎች ውል ከመፈጸማቸው በፉት ውል የተዋዋለባቸው ተሸከርካሪዎች እና የተለያዩ ማሽነሪዎች በ40ኛ ተጠሪ እጅ እንደነበሩ እና እንዲልነበሩ የማጣራት ግዳታቸውን አልተወጡም እንኳን ቢባል በአመልካቾች የተነገረው ማስታወቂያ በውሳኔያቸው ላይ ተጽኖ በማሳደር ወይም በማሳሳት በውል መሰረት ይፈጸምልናል በሚል እምነት ውል እንዱዋዋለ የማድረግ አቅም ያለው መሆኑን መገንዘብ ይቻላል። የማስታወቂያ አዋጁ ዋነኛ አላማም እንደዚህ አይነት አሳሳች ማስታወቂያዎችን በመከላከል የንግድ ግንኙነቱን ጤናማ ማድረግ ነው። በተቃራኒው አመልካቾች በአዋጁ የተጣለባቸውን ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ ማስታወቂያ የማስተላለፍ ግዳታቸውን ባለመወጣት 40ኛ ተጠሪ ወደ ሀገር ውስጥ ያስገባቸው ተሸከርካሪዎች ሳይኖሩ ተሸከርካሪ አስገብቶ የመሸጥ ልምድ ያለው መሆኑ የሚያሳይ ማስታወቂያ በማስነገር በተጠሪዎች ላይ ጉዲት እንዱደርስ አስተዋጽኦ በማድረጋቸው ከ40ኛ እና 41ኛ ተጠሪዎችን ሳይጨምር በላልች ተጠሪዎች ላይ ለደረሰው ጉዲት ኃላፉነት አለባቸው መባለ የማስታወቂያ አዋጁን እና ከውል ውጪ ኃላፉነትን በሚመለከት በፍትህ ብሓር ህጉ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች ያገናዘበ ሆኖ አግኝተነዋል።
4ኛውን ነጥብ በሚመለከት፡- 1ኛ አመልካች በጉዲዩ ላይ እንዱሰሙ የቆጠርኳቸው ምስክሮቼ አልተሰሙም፤ ማስታወቂያውንም ከ1ኛ አመልካች ቀድሞ ፊና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ሬድዮ አስተላልፍት የነበረ መሆኑን ገልጬ ጣልቃ እንዱገባ በጠየኩት መሰረት ሉታዘዝ ይገባ ነበር፤
ማስታወቂያው በሚነገርበት ጊዜም 40ኛ ተጠሪ የተወሰኑ ተሽከርካሪዎችን ወደ ሀገር ውስጥ እንዲስገባ ወይም በሂደት ላይ እንደነበር ከጉምሩክ እንዱጣራ በጠየኩት አግባብ አለመጣራቱ ተገቢ አይደለም በማለት ተከራክሯል። በፍትሐ ብሄር ክርክር ማስረጃ የሚሰማው የክርክሩን ፍሬ ጉዲይ ለማጣራት የግድ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 136-138፣ 145፣ 256፣ 257 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መረዲት ይቻላል። ከግራ ቀኙ ክርክር አንፃር ሉጣሩ የሚገባቸው ጉዲዮች በአመልካቾች የቴላቪዥን ጣቢያ የተነገሩት ማስታወቂያዎች ይዘት አሳሳች መሆን አለመሆኑ፣ ተጠሪዎች በዚህ ማስታወቂያ መነሻነት እምነት አሳድረው አስነጋሪው ጋር መዋዋላቸው እና ክፍያ በመፈፀም ጉዲት የደረሰባቸው መሆኑ እና ይህ ደግሞ ከሕግ አንጻር የሚኖረው ውጤት ነው። የተጠቀሱትን ፍሬ ነገሮች ደግሞ ፍ/ቤቱ በቀረቡለት ማስረጃዎች አጣርቶ ድምዲሜ ላይ የደረሰባቸው በመሆኑ እና ማስታወቂያው በተነገረበት ጊዜም ሆነ ከዚያ በኋላ ተሽከርካሪዎቹ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲልገቡ ስለተረጋገጠ 1ኛ አመልካች ምስክሮቼ አልተሰሙም፤
ከጉምሩክ ተቋምም ተጨማሪ ማስረጃ እንዱቀርብ ጠይቄ ነበር በማለት ያቀረበው ቅሬታ ተቀባይነት የለውም። ከስር ፍ/ቤት መዝገብ መረዲት እንደሚቻለው አመልካች ጣልቃ እንዱገባ የጠየቀው የአሁን 41ኛ ተጠሪን ሲሆን በዚሁ አግባብ ጣልቃ እንዱገባ ተደርጓል። በመሆኑም ፊና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ሬድዮ ጣልቃ እንዱገባ ጠይቄ ነበር በማለት የሚያነሳው ቅሬታ ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም።
5ኛውን ነጥብ በሚመለከት፡- አመልካቾች ኃላፉነት አለባችሁ ከተባልን ኃላፉነታችን በአዋጁ አንቀፅ 34(1)(ለ) በተገለፀው አግባብ ኃላፉነታችን ከብር 10,000 እስከ ብር 100,000 ባለው ወሰን ውስጥ ሉሆነ ይገባል በማለት የሚከራከሩ ሲሆን ድንጋጌው ይህ ገንዘብ መቀጮ መሆኑን የሚገልፅ ሲሆን የአዋጁን ድንጋጌ በተላለፈ ላይ የሚጣል ቅጣትን የሚመለከት ነው። በአመልካቾች እና በተጠሪዎች መካከል የውል ግንኙነት ስለላለ እንዱሁም አዋጁን ድንጋጌዎች በመተላለፍ ኃላፉነት ያለባቸው መሆኑ በአንቀፅ 30 ላይ መገለፁን እና ግልጽ የሆነ ሕግን መተላለፍ ጥፊት መሆኑ በፍ/ሕ/ቁጥር 2035 ላይ ስለተመለከተ ለተጠሪዎች ያለባቸው የኃላፉነት መጠን ከውል ውጪ ድንጋጌዎች መሰረት በማድረግ መሰላቱ ተገቢ ነው። በጉዲት ምክንያት የሚከፈል ካሳም ከደረሰው ጉዲት ጋር ተመጣጣኝ መሆን ያለበት(Compensation shall be equal to damage) ስለመሆኑ በፍ/ሕ/ቁጥር 2090 እና 2091 ላይ ተመላክቷል። በአንፃሩ የደረሰው ጉዲት የተጎጂው አስተዋፅኦ ያለበት እንደሆነ ካሳ የመክፈል ኃላፉነት ያለበት ወገን ኃላፉነቱ በከፉል እንደሚሆን በፍ/ሕ/ቁጥር 2098(1) ላይ ተመላክቷል። በተያዘው ጉዲይ ተጠሪዎች እንደ አንድ ጠንቃቃ ገዢ ተገቢውን ማጣራት ያላደረጉ በመሆኑ የአመልካቾች ኃላፉነት በፍ/ሕ/ቁጥር 2098 መሰረት በከፉል ነው ተብል መወሰኑ እንዱሁም ተጠሪዎች ለ40ኛ ተጠሪ ክፍያ በመፈጸም ከደረሰባቸው ጉዲት አመልካቾች ሉክሱ የሚገባው 1/4ኛውን ብቻ ነው ተብል በተሰጠው ውሳኔ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስለላለ ተከታዩን ወስነናል።
የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በኮ/መ/ ሚያዝያ 9 ቀን 2011 ዓ.ም እንዱሁም የፍደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ሰኔ 30 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጡት ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ጸንቷል።
በዚህ ችልት የተደረገው ክርክር ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
ትእዛዝ በፋደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ የተጀመረው አፈጻፀም ታግድ እንዱቆይ በሰ/መ/ ነሀሴ 6 ቀን 2012 የተሰጠው የእግድ ትዕዛዝ ተነስቷል። ይፃፍ።
No topics extracted.