የምርጫ ክልልችን አከላለል በሚመለከት የሕዝብ እና ቤት ቆጠራን መሰረት በማድረግ እና ተገቢውን ጥናት በማካሄድ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ለፋደሬሽን ምክር ቤት በሚያቀርበው የምርጫ ክልል ረቂቅ መሰረት የፋደሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ የሚሰጥበት እንጂ አዱስ የሕዝብ ቆጠራ ተደርጎ የምርጫ ቦርድ የምርጫ ክልልች አከላለልን በተመለከተ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 103(5) እና በአዋጅ ቁጥር 1133/2011 አንቀጽ 7/6 መሰረት ለፋደሬሽን ምክር ቤት ረቂቅ አቅርቦ የተሰጠ ውሳኔ በላለበት ሁኔታ ለምርጫ ማስፈጸሚያ ዓላማ በምርጫ አካባቢ በተደራጀ የአገሪቱ ግዛት ላይ ለውጥ የማይደረግ ስለመሆኑ የኢትዮጲያ የምርጫ፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ-ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 13/1(ሀ) (ለ)
No summary available.
ሰኔ 11 ቀን 2013 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) እትመት አሰፊ ደጀኔ አያንሳ ብርቅነሽ እሱባለው አመልካች፡- የኢትዮጲያ ብሓራዊ ምርጫ ቦርድ-ተወካይ አውድሮ ታደስ ቀረቡ ተጠሪ፡- ሞቻ ዱሞክራሲያዊ ፓርቲ -ተወካይ አለማየሁ ሻረው ቀረቡ መዝገቡ ለምርመራ የተቀጠረ ነው። በመሆኑም መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
የሰበር አቤቱታው ላቀርብ የቻለው አመልካች ሰኔ 03 ቀን 2013 ዓ.ም ጽፍ ባቀረበው የሰበር አቤቱታ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በይ.መ. ግንቦት 11 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለው ችልት የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ ከካፊ ዞን ሳይለም ወረዲ ቀበላ ምርጫ ጣቢያዎች እና ከቤንች ሸካ ዞን ጉራፈርዲ ወረዲ ቀበላ ምርጫ ጣቢያዎች ወደ ሸካ ዞን ማሻ አካባቢ እና ቴፒ ምርጫ ጣቢያዎች የተጨመሩ የምርጫ ጣቢያዎች ሙለ በሙለ እንዱነሱ እና በራሳቸው ዞን ድምጻቸውን እንዱሰጡ ይወሰንለት ዘንድ ያቀረበውን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ የሰጠውን ውሳኔ ሽሮ ከካፊ ዞን ሳይለም ቀበላ ምርጫ ጣቢያዎች ወደ ሸካ ዞን ማሻ አካባቢ ምርጫ ክልል የተጨመሩ ምርጫ ጣቢያዎች ከማሻ አካባቢ ምርጫ ክልል ተቀንሰው ምርጫ ጣቢያዎቹ በሚገኙበት የካፊ ዞን ወረዲ አካባቢ በሚገኝ የምርጫ ክልል ስር እንዱጠቃለለ፤ ከቤንች ሸካ ዞን ቀበላ ምርጫ ጣቢያዎች ወደ ሸካ ዞን ቴፒ ምርጫ ክልል የተጨመሩ ምርጫ ጣቢያዎች ከቴፒ ምርጫ ክልል ተቀንሰው ምርጫ ጣቢያዎቹ ወደ ሚገኙበት የቤንች ሸካ ዞን ወረዲ አካባቢ በሚገኝ የምርጫ ክልል ስር እንዱጠቃለለ በማለት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት አቤቱታ በማቅረቡ ነው።
ከመዝገቡ ይዘት መረዲት እንደተቻለው የአሁን ተጠሪ ለአሁን አመልካች ባቀረበው አቤቱታ ከካፊ ዞን ሳይለም ቀበላ ውስጥ የሚገኙ ምርጫ ጣቢያዎች ወደ ሸካ ዞን ማሻ ምርጫ ክልል የተጨመሩ የምርጫ ጣቢያዎች፤ እንዱሁም በቤንች ሸካ ዞን ጉራፈርዲ ቀበላ ውስጥ የሚገኙ ምርጫ ጣቢያዎች ወደ ሸካ ዞን ቴፒ ምርጫ ክልል በሕገ ወጥ መንገድ የተጨመሩ የምርጫ ጣቢያዎች በመሆናቸው ሙለ በሙለ እንዱነሱ እና በራሳቸው ዞን ድምጻቸውን እንዱሰጡ እንዱደረግ ይወሰንልኝ በሚል አቤቱታ አቅርቧል።
የአሁን አመልካች ተጠሪ ያቀረበለትን አቤቱታ መርምሮ በቀን 08/07/2013 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ ተጠሪ ያቀረባቸው ጥያቄዎች ተገቢነት ያላቸው መሆናቸው ቢታመንም አንዲንድ የምርጫ ክልልች ተመሳሳይ ጥያቄዎች እያቀረቡ በመሆናቸው የሕዝብ እና የቤት ቆጠራ ሳይከናወን የምርጫ ክልል ማስተካከል ስለማይቻል ወጥ የሆነ አሰራር መከተል ስለሚኖርብን እንዱሁም በጉራፈርዲ ወረዲ ውስጥ ከሸካ ብሓረሰብ ውጪ የሚኖሩ መራጮች ድምጽ የሚሰጡት በቴፒ የምርጫ ክልል በመሆኑ እና የሳይለም ምርጫ ጣቢያዎችም የ2013 ዓ.ም ምርጫ የሚካሄደው በ2007 ዓ.ም በተካሄደው የምርጫ ክልልች እንዱሆን ተወስኗል የሚል ውሳኔ ሰጥቷል።
ተጠሪ ይህን ውሳኔ በመቃወም ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባቀረበው አቤቱታ ወደ ሻካ ዞን እንዱጨመሩ የተደረጉ የምርጫ ጣቢያዎች ድምጽ ለመስረቅ ሆን ተብለው የተፈጠሩ የምርጫ ጣቢያዎች ከመሆናቸው በተጨማሪ ዕጩዎች ላይ ዛቻ እና ማስፈራሪያ ደርሷል፤ በጉራፈርዲ እንኳንስ የምረጡኝ ቅስቀሳ ለማድረግ ቀርቶ ዜጎች በጅምላ የሚገደለበት እና ለሕይወት አስጊ ቦታዎች ናቸው፤
ለትራንስፖርትም ምቹ አይደለም፤ በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ሸካ ዞን በተጨመሩ ወረዲና የምርጫ ጣቢያዎች በሚገኙበት አካባቢ የተጠሪ ዕጩዎች አለመኖራቸው ተጠሪን በነጻነት እኩል የፖለቲካ ምሕዲሩ ሰፍቶ ፕሮግራሙን ለመግለጽ የሚያስቸግረው እና ለመራጭ እና ለተመራጩ በሕገ መንግስት የተሰጣቸውን መብት የሚጋፊ ነው፤ ተጠሪ ለማይወክላቸው መራጮች ወደፉት ቢመረጥ የልማት ሥራዎችን እሰራለሁ ብል በምርጫ ቅስቀሳ ቃል ለመግባትም ሆነ ሲመረጥም ተግባራዊ ለማድረግ አይችልም፤ የተጠሪ ጥያቄ ከምርጫ ክልልች አደረጃጀት ጋር መያያዙ አግባብ ካለመሆኑም በላይ በአዋጁ የምርጫ ጣቢያዎች ለመለወጥ ከተሰጠው ሥልጣን ጋርም የሚጋጭ ነው፤ ስለሆነም ከከፊ ዞን ሳይለም ወረዲ ቀበላ ምርጫ ጣቢያዎች እና ከቤንች ሸካ ዞን ጉራፈርዲ ወረዲ ቀበላ ምርጫ ጣቢያዎች በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ሸካ ዞን ቴፒ ወረዲ የተጨመሩት የምርጫ ጣቢያዎች ሙለ በሙለ እንዱነሱ እና በራሳቸው ዞን ድምጻቸውን እንዱሰጡ እንዱደረግ ይወሰንልን በማለት አቤቱታ አቅርቧል።
የአሁን አመልካች በሰጠው መልስ የምርጫ ክልል የተካለለው በሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 54/3 መሰረት ነው፤ ሕገ-መንግስቱ እስካልተቀየረ ድረስ ቀደም ሲል ምርጫ ሲካሄድባቸው የነበሩት የውክልና የምርጫ ክልልች በተጠሪ ስልጣን ሉቀየሩ አይችለም፤ የምርጫ ክልል ሉቀየር የሚችለው የሕዝብ ቆጠራ ውጤት መሰረት ተደርጎ ሲሆን በውጤቱ መሰረት አመልካች ረቂቅ የውሳኔ ሀሳብ ለፋዳሬሽን ምክር ቤት አቅርቦ ወሳኔ የሚሰጥበት በመሆኑ አመልካች በአሁን ወቅት የምርጫ ክልል ማካለል አይችልም፤
አመልካች የ2013 ዓ.ም ምርጫ በ2007 ዓ.ም በተካሄደው ምርጫ መሰረት የሚፈጸም መሆኑን ለመላው የሐገሪቱ ሕዝብ አሳውቋል፤ የምርጫ ጣቢያ ሉጨመር ወይም ሉለወጥ የሚችለው በአዋጁ ቁጥር 15(6) መሰረት ቀድሞ የነበረው የምርጫ ጣቢያ ላይ የመራጩ ሕዝብ ቁጥር ከ 1500 በላይ ከሆነ እና በአርብቶ አደር አካባቢ የሕዝቡን የአኗኗር ሁኔታ መነሻ በማድረግ የሕዝብ መጨናነቅ ለመቀነስ ላይ የምርጫ ጣቢያ እንዱቋቋም ሲወሰን ነው፤ የምርጫ ጣቢያዎቹ አስቀድመው የነበሩ በመሆኑ የአመልካች ክርክር አግባብነት የለውም፤ የጸጥታ ችግር ተነስቷል ቢባል እንኳን ችግሩ ሉቀረፍ የሚገባው በሕገ-መንግስት እና በምርጫ ሕጎች ነው፤ ይቀየሩ የተባለት የምርጫ ጣቢያዎች በልላ የምርጫ ክልል ውስጥ የሚገኙ በመሆኑ እነኚህን የምርጫ ጣቢያዎች ወደ ላላ የምርጫ ክልል መለወጥ ሕገ-መንግስትን መጣስ ይሆናል፤ ስለሆነም ክሱ ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክሯል።
ጉዲዩ የቀረበለት ፍርድ ቤትም የተጠሪ ጥያቄ የምርጫ ክልልን የሚመለከት ነው? ወይስ የምርጫ ጣቢያን የሚመለከት? ተጠሪ በአመልካች ለይ ክስ ማቅረብ ይችላል? ወይስ አይችልም? የምርጫ ጣቢያን ለመቀነስ የግድ የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ ላደረግ ይገባል? ወይስ አይገባም? ከሳይለም እና ጉራፈርዲ ወረዲ ወደ ማሻና ቴፒ የምርጫ ክልልች ውስጥ የተካተቱ የምርጫ ጣቢያዎች ሉነሱ ይገባል?
ወይስ አይገባም? የሚለትን ጭብጦች በመያዝ ጉዲዩን መርምሮ የተጠሪ የዲኝነት ጥያቄ ያላግባብ የተጨመሩት የምርጫ ጣቢያዎቸ ይቀነሱልን የሚል እንጂ የምርጫ ክልል ይቀነስ ወይም ይጨመር የሚል አይደለም፤ ተጠሪ ሕጋዊ የሆነ የፖለቲካ ፓርቲ በመሆኑ እና ክሱም በምርጫ ክልለ ውስጥ ያለትን የምርጫ ጣቢያዎች የሚመለከት በመሆኑ በአመልካች ላይ ክስ የማቅረብ መብት አለው፤
ምርጫ ክልል የሚቋቋመው በአንድ የምርጫ ክልል ውስጥ ያለውን ሕዝብ ብዛት መሰረት በማድረግ ነው፤ እያንዲንደ ምርጫ ጣቢያ ሉመርጥ የሚችለውን ሕዝብ ብዛት ለማወቅ በቅርቡ የተደረገ የህዝብ እና ቤት ቆጠራ የለም፤ የሕዝብ ቁጥር ባልታወቀበት ደረጃ ደግሞ ተገቢውን ቁጥር የያዘ መራጭ ሕዝብ እንዲለ ተቆጥሮ የምርጫ ጣቢያ ሉቀነስ አይችልም፤ በቂ ቁጥር ያለው መራጭ ሕብረተሰብ መኖሩ ሳይረጋገጥ በሸካ ዞን ማሻ እና ቴፒ ምርጫ ክልልች የተጨመሩ የምርጫ ጣቢያዎች እንዱነሱ ቢደረግ የምርጫ ክልለ በተገቢ ተደራጅቷል የሚያሰኝ አይሆንም፤ ስለሆነም በሁለቱም ወረዲዎች ያለው ሕዝብ ብዛት በተጨባጭ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ የምርጫ ጣቢያዎች ይነሱልኝ ሲል ተጠሪ ያቀረበው የዲኝነት ጥያቄ ተቀባይነት የለውም በማለት ውድቅ አድርጎታል።
ተጠሪ ይህን ውሳኔ በመቃወም ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የይግባኝ አቤቱታ አቅርቧል። ይግባኙ የቀረበለት ፍርድ ቤትም አመልካች በጉዲዩ ላይ መልስ እንዱሰጥበት ካደረገ በኋላ ለክርክሩ መነሻ የሆኑት ምርጫ ጣቢያዎች ከሚገኙበት የምርጫ ክልልች ተቀንሰው በእነዚህ ጣቢያዎቸ የሚመረጡ መራጮች በሚኖሩበት ወረዲዎች አካባቢ ወደሚገኙ የምርጫ ክልልች እንዲይጠቃለለ የሚያደርግ ሕጋዊ ምክንያት አለ? ወይስ የለም? ለክርክሩ መነሻ የሆኑት ምርጫ ጣቢያዎች ባለበት ምርጫ ክልልች እንዱቀጥለ ቢደረግ በሸካ ዞን በሚገኝ ሕዝብ ራስን በራስ የማስተዲደር መብት ላይ የሚኖረው አለታዊ ውጤት ምንድነው? በመራጩ ሕዝብ የመምረጥ መብት እና በተጠሪ የመመረጥ መብት ላይ ወይም በምርጫው ዱሞክራሲያዊነት እና ፍትሐዊነት ላይ የሚያስከትለው ውጤትስ ምንድነው? የሚለ ጭብጦችን በመያዝ ጉዲዩን መርምሮ ለጉዲዩ አወሳሰን አግባብነት አላቸው ያላቸውን ዓለም ዓቀፊዊ እና አሕጉራዊ ስምምነቶቸ እንዱሁም ሐገራዊ ሕጎች ድንጋጌዎችን በዝርዝር ካስቀመጠ በኋላ ለክርከሩ መነሻ የሆኑት የምርጫ ጣቢያዎች በሸካ ዞን አስተዲደር ክልል ውስጥ የማይገኙ መሆኑ የታመነ ነው፤ እንዱሁም በሽግግር መንግስት ጊዜ በተቋቋሙ የምርጫ ክልልች እና በኋላም በሕገመንግስቱ አንቀጽ 54/3 ከተመለከተው 550 የምርጫ ክልልች ውስጥ በሸካ ዞን አስተዲደር ውስጥ ለሚገኝ የሸካቾ ብሓረሰብ በሁለት የምርጫ ክልልች የሚወከል ለሕዝብ ተወካዮቸ ምክር ቤት ሁለት መቀመጫ እንዲለው እና ለክልለ ምክር ቤት ደግሞ በሁለቱ የምክር ቤት ክልልች ስድስት የክልል ምክር ቤት አባላት መቀመጫ እንዲለው አመልካች ያመነው ጉዲይ ነው፤ የተጠሪ ክርክር ይህ የብሓረሰቡ ውክልና ሳይሸራረፍ ተግባራዊ እንዱደረግ የሚጠይቅ የምርጫ ጣቢያን የሚመለከት እንጂ ተጨማሪ የምርጫ ክልል ይደራጅልኝ የሚል አይደለም፤ የተጠሪ ጥያቄ በቀጥታ የምርጫ ክልል ይደራጅልኝ የሚል ቢሆን የምርጫ ክልል የሚደራጀው የሕዝብ ቆጠራ ተደርጎ ውጤቱ ከታወቀ በኋላ በመሆኑ እና ላለፈት 10 ዓመታታ በላይ የሕዝብ ቆጠራ ያልተደረገ በመሆኑ ጥያቄው ተቀባይነት ሉኖረው አይችልም ነበር፤ አመልካች በአዋጅ ቁጥር 1133/2011 አንቀጽ 7(13) እና በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 15(1) መሰረት የምርጫ ጣቢያዎች ቁጥር የመወሰን እና ለምርጫው አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው የተለያዩ ታሳቢዎች ግምት ውስጥ በማስገባት በሚወሰነው ስፍራ የምርጫ ጣቢያ እንዱያቋቁም እና ቦታዎች እንዱለውጥ ሥልጣን የተሰጠው ሆኖ ሳለ ላልች ተመሳሳይ ጥያቄዎች ስለሚነሱ ባለበት ይቀጥለ ማለቱ አግባብ አይደለም፤ ምርጫ ጣቢያዎች የሚቀነሱበትም ሆነ የሚጨመሩበት የምርጫ ክልልች በሽግግር መንግስት ጊዜ በነበረው የሕዝብ ቁጥር የተደራጁ ናቸው፤
የአገራችን የሕዝብ ቁጥር እድገት ምጣኔ እየጨመረ እንጂ እየቀነሰ እንዲልሆነ ከዲኝነት አስተውልት የምንገነዘበው በመሆኑ የሸካ ዞን የሕዝብ ቁጥር በዞኑ ለሚገኙ የምርጫ ክልልች ከሚፈለገው ቁጥር ያንሳል የሚያስብል አሳማኝ ምክንያት የለም፤ በተመሳሳይ የምርጫ ጣቢያዎቹ የሚጨመሩበት የምርጫ ክልልችም የሕዝብ ቁጥራቸው እንደጨመረ መገመት ይቻላል፤ ፍርድ ቤቱ ከዲኝነት አስተውልት እንደሚገነዘበው በቀድሞም ሆነ በአሁኑ የምርጫ ሕግ የምርጫ ክልልች የሚቋቋሙት የክልል መንግስታትን ድንበር በጠበቀ መልኩ የአገሪቱን የወረዲ አስተዲደርን መሰረት በማድረግ ነው፤ በደቡብ ክልል የዞኖች አደረጃጀት ልዩ ባሕርይ አንጻር አከራካሪዎቹ ምርጫ ጣቢያዎች በላልች ዞኖችና ወረዲዎች አስተዲደር ክልል ውስጥ የሚገኙ በመሆኑ በሸካ ዞን አስተዲደር ውስጥ የሚገኙ የምርጫ ክልልች አካል ሆነው የሚደራጁበት የሕግ መሰረት የለም፤ ስለሆነም አከራካሪዎቹ ምርጫ ጣቢያዎች ሉደረጁ የሚገባው በእነዚህ የምርጫ ጣቢያዎች የተመዘገቡ መራጮች ድምጻቸውን ሉሰጡ የሚገባው ምርጫ ጣቢያዎቹ በሚገኙበት ዞን ወረዲ አስተዲደር አካባቢ በሚገኝ የምርጫ ክልል ላሆን በመሆኑ ከሚገኙበት ምርጫ ክልልች ተቀንሰው መራጩ ሕዝብ በሚኖርበት ወረዲዎች አካባቢ ወደሚገኙ የምርጫ ክልልች እንዱጠቃለለ በተጠሪ የቀረበው ጥያቄ ሕግን መሰረት ያደረገ ነው። በአስተዲደር ዞኖች በሸካ ዞን ውስጥ የማይኖሩ ሰዎች በአከራካሪዎቹ ምርጫ ጣቢያዎች ተመዝግበው ድምጽ የመስጠት ዕድል ስለሚያገኙ የዞኑ ሕዝብ ራሱን በራሱ በማስተዲደር ጉዲይ ራሱን ችል የመወሰን መብቱ እንዱሸራረፍ የማያደርግ አለታዊ ውጤት ያስከትላል።
ከደቡብ ክልል አደረጃጀት አንጻር የክልለ ዞኖች እና ልዩ ወረዲዎች የብሓረሰብ ዞኖች እና ልዩ ወረዲዎች ሆነው የየራሳቸው ምክር ቤት ሕግ አስፈጻሚ እና የዲኝነት አካል ኖሯቸው የተደራጁ በመሆናቸው በክልል ደረጃ በወጣ ቀመር መሰረት የየራሳቸውን በጀት ይዘው ራሳቸውን በራሳቸው የሚያስተዲድሩ ናቸው፤ ተጠሪ በዚሁ ዞን ውስጥ ላለ ሕዝብ ፖለቲካል እንቅስቃሴ ለማድረግ የተደራጀ በመሆኑ ዕጩዎችን የሚመለምለውም ሆነ የሚመርጠው በዚሁ ዞን አስተዲደር ወሰን ክልል ውስጥ በመሆኑ የአከራካሪዎቹ ምርጫ ጣቢያዎች መጨመር ከክልለ አደረጃጀት ጋር ይጣረሳል።
አንድ ዞን ውስጥ ባለው ብሓረሰብ ስም የተደራጀ ፓርቲ በአደረጃጀት የማይወክለውን በልላ ዞን ውስጥ ያለውን ብሓረሰብ እወክልሃለሁ ብል የፖለቲካ እንቅስቃሴ የሚያደርግበት ሁኔታ በተግባር አይኖርም፤
ተጠሪ በልላ ዞን አስተዲደር ክልል ውስጥ በሚገኙ አከራካሪዎቹ ምርጫ ጣቢያዎች የተመዘገቡ መራጮችን እንዱህ አደርግላችኋለሁ እና ምረጡኝ ብል ለመቀስቀስም ሆነ የሚመረጥ ቢሆን ደግሞ የተመረጠበትን የሸካ ዞን በጀት በመጠቀም በካፊ ዞን እና በቤንች ሸኮ ዞን ለሚገኙት አከራካሪ ምርጫ ጣቢያዎች በተዋቀሩበት አካባቢ ለሚኖሩ መራጮች ቃል የገባላቸውን ነገር መስራት አይችልም፤ ይህም መራጮች ከተጠሪ ይልቅ ከአንድ ዞን በላይ እነሱ ያለበትን አካባቢ ጭምር ሉወክል የሚችል ላላ ፓርቲ ወደ መምረጡ ስለሚያዘነብለ የምርጫው ምሕዲር ፍትሐዊ እንዲይሆን የማድረግ ውጤት ይኖረዋል በማለት አመልካች እና የስር ከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጡትን ውሳኔ ሽሮ ከካፊ ዞን ሳይለም ቀበላ ምርጫ ጣቢያዎች ወደ ሸካ ዞን ማሻ አካባቢ ምርጫ ክልል የተጨመሩ ምርጫ ጣቢያዎች ከማሻ አካባቢ ምርጫ ክልል ተቀንሰው ምርጫ ጣቢያዎቹ በሚገኙበት የካፊ ዞን ወረዲ አካባቢ በሚገኝ የምርጫ ክልል ስር እንዱጠቃለለ፤ከቤንች ሸካ ዞን ቀበላ ምርጫ ጣቢያዎች ወደ ሸካ ዞን ቴፒ ምርጫ ክልል የተጨመሩ ምርጫ ጣቢያዎች ከቴፒ ምርጫ ክልል ተቀንሰው ምርጫ ጣቢያዎቹ ወደሚገኙበት የቤንች ሸካ ዞን ወረዲ አካባቢ በሚገኝ የምርጫ ክልል ስር እንዱጠቃለለ፤ የመራጮች ምዝገባ የተጠናቀቀ በመሆኑ በእነዚህ ምርጫ ጣቢያዎች የተመዘገቡ መራጮች ምርጫ ጣቢያዎቹ በሚገኙበት ወረዲ አካባቢ በሚገኝ የምርጫ ክልል የሚፍካከሩ ተወዲዲሪዎችን የሚመርጡበትን ሁኔታ አመልካች እንዱያመቻች ሲል በአብላጫ ድምጽ ወስኗል።
አመልካች በቀን 03/10/2013 ዓ.ም ጽፍ ያቀረበው የሰበር አቤቱታ ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት ተፈጽሞበታል በሚል የቀረበ ሲሆን ይዘቱም፡- የምርጫ ክልል በጽንስ ሐሳብ ደረጃ በአንድ አካባቢ የሚኖሩ እና ተመሳሳይ ፍላጎቶች የሚያንጸባርቁ ዜጎች ተወካዮቻቸውን እንዱመርጡ በአንድ አገር የተወሰነ የአገሪቱን የግዛት ክልል በመከፊፈል የሚደራጅ ነው፤ በሕግ መሰረት ለተለያዩ ምክር ቤቶች መቀመጫዎች የሚመረጡ ተወካዮች ቁጥር በሕግ የተቀመጠለት የምርጫ የጊዜ ሰላዲ ይፊ ከመደረጉ አስቀድሞ በምርጫ አስፈጻሚ ሳይሆን ስልጣን ባለው የመንግስት አካል የምርጫ ክልል ወሰን ሲወስን የተለያዩ መስፈርቶች በማስቀመጥ ሉወሰን የሚችል ሲሆን የሕዝብ ቁጥር አሰፊፈርን መሰረት በማድረግ የሚሰጠው ውሳኔ አንደ ነው፤ በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 13 እና በአዋጅ ቁጥር 1133/2011 አንቀጽ 7(6) መሰረት የምርጫ ክልል የሕዝብ እና ቤት ቆጠራን መሰረት በማድረግ እና ተገቢውን ጥናት በማካሄድ ቦርደ ለፋዳሬሽን ምክር ቤት በሚያቀርበው የምርጫ ክልል ረቂቅ መሰረት የፋዳሬሽን ምክር ቤቱ ውሳኔ እንደሚሰጥበት በግልጽ ተመልክቷል፤
የፋዳሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ ሳይሰጥ ለምርጫ ማስፈጸሚያ አላማ በምርጫ አካባቢ በተደራጀ የአገሪቱ ግዛት ላይ አመልካችን ጨምሮ ማንም አካል ለውጥ ማድረግ አይችልም።
በሽግግር ጊዜ የተቋቋመው ምክር ቤት የብሓራዊ ክልላዊ መስተዲድር ምርጫ ይካሄድ ዘንድ የተመቻቸ ሁኔታ ለመፍጠር አዋጅ ቁጥር 9/1984 በማውጣት ተግባራዊ አድርጓል፤ በመቀጠልም የምርጫ አስፈጻሚ ኮሚሽንን ያቋቋመው እና ስልጣን እና ተግባሩን የወሰነውን አዋጅ ቁጥር 11/1984 አውጥቶ ተግባራዊ አድርጓል፤ ይህ የምርጫ ኮሚሽን የሕገ-መንግስት አባላትን ለማስመረጥ ባወጣው የምርጫ አዋጅ መሰረት የአገሪቱን ወረዲዎች በሕዝብ ቁጥር ላይ ተመርኩዞ ፍትሐዊ የሆነ የምርጫ ክልል ለመመስረት ያስችል ዘንድ በ1976 ዓ.ም ተካሂድ የነበረውን የሕዝብ ቤቶች ቆጠራ ውጤትን ወደ 1985 ዓ.ም በመተንበይ የነበረውን የሕዝብ ቁጥር ባለው የሕዝብ ተወካዮቸ መቀመጫ ልክ እንዱደለደል ያቀረበው ውሳኔ ሀሳብ በሽግግር መንግስቱ ተቀባይነት አግኝቷል፤ በዚህ መሰረት አንድ የምርጫ ክልል 100,000 ሕዝብ እንዱወክል ተደርጓል፤ በዚሁ መሰረት በ1985 ዓ.ም በክልል ውስጥ የሚኖር የሕዝብ ብዛትን መሰረት ብቻ በማድረግ የምርጫ ክልል ተካሎል፤ በ1985 ዓ.ም የምርጫ ክልል ድልድል ከተሰራ በኋላ እስካሁን ድረስ ቦርደ በሚያቀርበው ጥናት መሰረት በፋዳሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ የምርጫ ክልል አልተካለለም፤ አመልካች ጥናት እንዱካሄድ በማድረግ በውጤቱ ላይ ተመስርቶ የውሳኔ ሀሳብ ለፋዳሬሽን ምክር ቤት በማቅረብ የአከላለል ለውጥ ከሚያስወስን በቀር የምርጫ ክልልችን ወሰን ለመለወጥ ስልጣን የለውም፤ ለክርከሩ መነሻ የሆኑት የምርጫ ጣቢያዎች ተጠሪ እንደሚለው ከከፊ እና ቤንች ሸካ ዞን የምርጫ ክልልች የተጨመሩ ሳይሆኑ ላለፈት 5 ጠቅላላ ምርጫዎች በማሻና ቴፒ ምርጫ ክልል ሥር ተከልለው ሲተገበር የቆየ ነው፤ የሸካቾ ብሓረሰብ በፋዳራልም ሆነ በክልል ምክር ቤቶች የሚወከልበት ሁለት የምርጫ ክልልች ያለት በመሆኑ የምርጫ ጣቢያዎች በፋዳሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ ወደ ሸካ ዞን መካለላቸው ራስን በራስ የማስተዲደር መብቱን የሚሸራርፍ አይደለም፤ በአሁኑ ጊዜ የምርጫ ሂደቱ የተጠናቀቀ እና ድምጽ የሚሰጥበት ቀን ብቻ የቀረ በመሆኑ፤ ለምርጫ ክልለ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች በእያንዲንደ ክልል ስም ታትመው ተሰራጭተው በተጠናቀቀበት ወቅት የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ሕጉን በተሳሳተ መንገድ በመተርጎም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ በግራ ቀኙ መካከል ያለውን ክርክር በሚመለከት የካፊ ዞን ሳይለም ወረዲ እና ከቀድሞ ቤንች ማጂ ዞን በአሁኑ ቤንች ሸካ ዞን ጉራፈርዲ ወረዲ ወደ ሸካ ዞን ማሻና ቴፒ የተጨመሩ የምርጫ ጣቢያዎች እንዱቀነሱ ምክንያታቸውን በመጥቀስ ተጠሪ ለአመልካች ያቀረቡት ጥያቄ በኢትዮጲያ የምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 2(15) እና 2(16) መሰረት የምርጫ ክልል ነው? ወይም የምርጫ ጣቢያ ነው?
በዚህ ረገድ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ምርጫ ጣቢያ ነው ያለው በአዋጁ የተሰጠውን ትርጉም ያገናዘበ ነው? ወይስ አይደለም? አመልካች በኢትዮጲያ የምርጫ፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 2(15) መሰረት የምርጫ ክልል አከላለል በብሓራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1133/2011 አንቀጽ 7/6 መሰረት ጥናት ተደርጎ ለፋዳሬሽን ምክር ቤት የውሳኔ ሃሳብ ያቀረቡ መሆኑን በመጥቀስ ያቀረቡትን ክርክር ውድቅ በማድረግ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርደ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በአብላጫ ድምጽ የመሻሩን አግባብነት ከአዋጅ ቁጥር 1133/2011 አንቀጽ 7/6 ጋር በማገናዘብ ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ በዚህ ችልት እንዱታይ ተደርጓል። ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎም ግራ ቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
ተጠሪ በቀን 10/10/2013 ዓ.ም በሰጠው መልስ የተጠሪ ጥያቄ ከምርጫ ክልል ማሻሻያ ጋር በፍጹም የሚገናኝ አይደለም፤ ከሸካ ዞን ውጪ ከሚገኙ የራሳቸው ማንነት እና አደረጃጀት ካላቸው ዞኖች ሥር የሚገኙ የወረዲ ሕዝብ ለማይወክሎቸው ለሸካ ዞን ተመራጭ ድምጽ እንዱሰጡ የምርጫ ጣቢያዎች ማደራጀቱ የምርጫ ሂደቱን ነጻ ተአማኒ እና ፍትሐዊ እንዲይሆን የሚደርግ ነው፤ በኢትዮጲያ ውስጥ ካለ ክልልች ከየዞኖች በሚወከለ አባላት የብሓረሰቦች ምክር ቤት ያለው ብቸኛ ዞኖችና ልዩ ወረዲዎች በደቡብ የሚገኙ ሲሆኑ የየራሳቸውን በጀት ስለሚያስተዲድሩ ከሳይለም እና ከጉራፈርዲ ሕዝብ አንጻር የመልማት እና የመልካም አስተዲደር መብት ዙሪያ በቅስቀሳ ወቅት ብመረጥ አሟላለሁ ብል ቃል ቢገባ እንኳን ተግባራዊ ማድረግ አይቻልም፤ ያላግባብ ሁለት የራሳቸው ማንነት ካላቸው ዞን ወረዲዎች የራሱ ማንነት ወዲለው ሸካ ዞን ስር የተጨመሩ ምርጫ ጣቢዎች ተቀንሰው ወደ ራሳቸው ዞን ሥር በሚገኙ የምርጫ ክልልች ቢጨመሩ ባለት ላይ እንዱጨመሩ እንጂ ላላ የምርጫ ክልል ይፈጠራል ወይም የማሻ እና የቴፒ ምርጫ ክልልች ይቀነሳል የሚል አይደለም፤ በተጠሪ የቀረበው ጥያቄ የምርጫ ክልልችን የሚያፊልስ አይደለም፤ የአመልካች ክርክር ጥናት አድርገን አቅርበናል የሚል ሳይሆን ወደፉት የፋዳሬሽን ምክር ቤት የሕዝብ እና ቤቶች ቆጠራ ተካሂድ በሚወስነው ይሆናል የሚል ነው፤
ተጠሪ አዋጅ ቁጥር 9/1984፤ 11/1984 የጠቀሰ ቢሆንም በአዋጅ ቁጥር 532/2000 ዓ.ም በሕግ የተቋቋመ የምርጫ ክልል አደረጃጀት የለም፤ በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 ቢሆን የምርጫ ክልልች ወደፉት እንደሚቋቋሙ እና አደረጃጀቱ ምን መምሰል እንዲለበት የሚገልጽ እንጂ የምርጫ ክልል አላቋቋመም፤ ከፍተኛው ፍርድ ቤት የተጠሪ ጥያቄ የምርጫ ክልል ይቀነስ ወይም ይጨመር የሚል አይደለም በማለት የሰጠውን የውሳኔ ክፍል አመልካች በይግባኝ አላስለወጠም፤ አመልካች የመራጮች ምዝገባ እና የምርጫ ቁሳቁስ ማጓጓዝን አስመልክቶ ያቀረበው ክርክር አዱስ የክርክር ሐሳብ ነው፤
ስለሆነም የአመልካች የሰበር አቤቱታ ውድቅ ተደርጎ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠው ውሳኔ ሉጸና ይገባል የሚል ነው።
አመልካችም በቀን 10/10/2013 ዓ.ም በሰጠው የመልስ መልስ የምርጫ ክልል መሰረታዊ ገጽታ ከሆኑት መካከል አንደ እና ዋነኛው መልክአምድር ነው፤ ይህም በአንድ መልክአምድር ውስጥ የሚኖሩ ሕዝቦችን በመንግስት አስተዲደር ውስጥ የሚወከለበትን ሁኔታ ለማመቻቸት እና የተሳትፍ መብታቸውን እውን ለማድረግ የሚመሰረት ከመደበኛ የአስተዲደር ወሰን የተለየ የምርጫ አካባቢ ነው፤
ለአመልካች በሕግ የተሰጠው ስልጣን በልላ አካል ሥልጣን መሰረት በተወሰነ አንድ የምርጫ ክልል ስር የተለያዩ ምርጫ ጣቢያዎችን መመስረት እና እነዚህኑ የምርጫ ማስፈጸሚያ አደረጃጀቶች በዚያ ክልል ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች የመምረጥ መብት መረጋገጡን ተደራሽ ማድረግ ብቻ በማለት የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው።ይህ ችልትም በሰበር አጣሪው ችልት ሉጣራ ይገባዋል ተብል የተያዘውን ነጥብ ከግራ ቀኙ ክርክር፤ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምሮታል።
እንደመረመርነው አመልካች በዋነኝነት አጥብቆ የሚከራከረው ተጠሪ ከካፊ ዞን ሳይለም ወረዲ ቀበላ ምርጫ ጣቢያዎች እና ከቤንች ሸካ ዞን ጉራፈርዲ ወረዲ ቀበላ ምርጫ ጣቢያዎች ወደ ሸካ ዞን ማሻ አካባቢ እና ቴፒ ምርጫ ጣቢያዎች በሕገ ወጥ መንገድ የተጨመሩ የምርጫ ጣቢያዎች ሙለ በሙለ እንዱነሱ እና በራሳቸው ዞን ድምጻቸውን እንዱሰጡ ይወሰንልኝ በማለት ጥያቄ ያቀረበ ቢሆንም በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 13 እና በአዋጅ ቁጥር 1133/2011 አንቀጽ 7(6) መሰረት የምርጫ ክልል የሕዝብ እና ቤት ቆጠራን መሰረት በማድረግ እና ተገቢውን ጥናት በማካሄድ ቦርደ ለፋደሬሽን ምክር ቤት በሚያቀርበው የምርጫ ክልል ረቂቅ መሰረት የፋደሬሽን ምክር ቤቱ ውሳኔ እንደሚሰጥበት በግልጽ ተመልክቷል፤ የፋደሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ ሳይሰጥ ለምርጫ ማስፈጸሚያ ዓላማ በምርጫ አካባቢ በተደራጀ የአገሪቱ ግዛት ላይ አመልካችን ጨምሮ ማንም አካል ለውጥ ማድረግ አይችልም የሚል ነው።
ስለሆነም ለጉዲዩ አወሳሰን መሰረታዊ የሆነው ጭብጥ የተጠሪ ጥያቄ የምርጫ ክልልን የሚመለከት ነው? ወይስ የምርጫ ጣቢያን የሚመለከት? የሚለው ነው።
በኢትዮጲያ የምርጫ፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 2(15)እና(16) እና በብሓራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ አንቀጽ 2(6)እና(7) ላይ የምርጫ ክልል ማለት ለምርጫ አፈጻጸም እንዱያመች እና ሕዝቡ ወኪልቹን እንዱመርጥ በሕግ መሰረት የሐገሪቱ ግዛት ተከፊፍል የሚደራጅ የምርጫ አካባቢ ነው፤ የምርጫ ጣቢያ ማለት ደግሞ በየደረጃው የሚካሄደ ምርጫዎች የመራጭ ምዝገባ የሚካሄድበት፤ መራጮች ድምጽ የሚሰጡበት እና የድምጽ ቆጠራ የሚካሄድበት ቦታ ነው በማለት በግልጽ ተመልክቷል። የአዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 15(6)እና(7) በእያንዲንደ የምርጫ ጣቢያ የሚስተናገደው የመራጮች ብዛት ከ1500 መብለጥ እንደላለበት እና ለአንድ የምርጫ ጣቢያ በተከለለ አካባቢ ከአንድ የምርጫ ጣቢያ በላይ ማቋቋም እንደማይቻል ይደነግጋል። የመራጮች ብዛት በሕግ ተለይቶ በተቀመጠለት የምርጫ ጣቢያ ውስጥ በመራጮች የሚሰጠው ድምጽ ወደ ምርጫ ክልል የመራጮች ድምጽ መስጫ ቋት ውስጥ የሚገባ በመሆኑ የሕዝብ ብዛትን መሰረት በማድረግ የተከለለውን የምርጫ ክልል አደረጃጀት ላይ እና በምርጫ ውጤት ላይ ተጽዕኖ ይኖረዋል። ስለሆነም ተጠሪ ከካፊ ዞን ሳይለም ወረዲ ቀበላ ምርጫ ጣቢያዎች እና ከቤንች ሸካ ዞን ጉራፈርዲ ወረዲ ቀበላ ምርጫ ጣቢያዎች ወደ ሸካ ዞን ማሻ አካባቢ እና ቴፒ ምርጫ ጣቢያዎች በሕገ ወጥ መንገድ የተጨመሩ የምርጫ ጣቢያዎች ሙለ በሙለ እንዱነሱ እና በራሳቸው ዞን ድምጻቸውን እንዱሰጡ ይወሰንልኝ በማለት ያቀረበው ጥያቄ የምርጫ ክልልን የሚመለከት እንጂ የምርጫ ጣቢያን የሚመለከት አይደለም። የተጠሪ ጥያቄ የምርጫ ክልልን የሚመለከት ነው ከተባለ የምርጫ ቦርድ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ የሰጡት ውሳኔ ተገቢ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለውን ቀጥለን እንመልከት።
የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 103(5) የሕዝብ ቆጠራ በየአሥር ዓመቱ ይካሄዲል። በውጤቱም መሰረት የምርጫ ክልልችን አከላለል የምርጫ ቦርድ በሚያቀርበው ረቂቅ መሰረት የፋደሬሽን ምክር ቤት ይወስናል በማለት ይደነግጋል። የኢትዮጲያ ፍደራላዊ ዱሞክራሲያዊ ሪፐብላክ ብሓራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1133/2011 አንቀጽ 7/6 ለቦርደ ከተሰጠው ስልጣን እና ተግባር ውስጥ አንደ የምርጫ አከላለል በተመለከተ ጥናት አድርጎ ለፋደሬሽን ምክር ቤት የውሳኔ ሐሳብ ማቅረብ ነው።
የኢትዮጲያ የምርጫ፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ-ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 13/1(ሀ) (ለ) ለምርጫ አፈጻጸም ዓላማ የክልል መንግሥታት ድንበር እንደተጠበቀ ሆኖ አገሪቱ የወረዲ አስተዲደርን መሰረት በማድረግ የሚከፊፈለ በሕዝብ ቆጠራ ውጤት መሰረት ማስተካከያ ላደረግባቸው በሚችለ ቋሚ የምርጫ ክልልች ትከፊፈላለች፤ አገሪቱ እያንዲንዲቸው አንድ ተወካይ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚመረጥባቸው ከ550 የማይበልጡ የምርጫ ክልልች የሚኖሯት ሆኖ አከላለለ የሕዝብ ብዛትንና በልዩ ትኩረት ውክልና የሚሰጣቸው የሕዝብ ብዛታቸው አነስተኛ የሆነ ብሓረሰቦች እና ሕዝቦችን ቁጥር መሰረት በማድረግ ይወሰናል፤ አነስተኛ የሕዝብ ብዛት ያላቸው ብሓረሰቦች እና ሕዝቦች የሚወከለባቸው የምርጫ ክልልች ሳይጨምር ምርጫ ክልልቹ ተቀራራቢ የሕዝብ ቁጥር ያላቸው ሆነው በመካከላቸው ያለው ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ልዩነት ከ15 በመቶ መብለጥ የለበትም በማለት ይደነግጋል። ከእነዚህ ሁለ ድንጋጌዎች ይዘት መገንዘብ እንደሚቻለው የምርጫ ክልልች እና የምርጫ ጣቢያዎችን የማደራጀት እና የማካለል ሥራ አስተዲደራዊ ጉዲይ መሆኑን ነው።
እንደሚታወቀው ከ1987 ዓ.ም በኋላ በአገራችን አምስት ምርጫዎች የተከናወኑ ሲሆን እነዚህ ምርጫዎች የተከናወኑት የምርጫ ቦርድ ቀደም ሲል የነበረውን የሕዝብ ቆጠራ መነሻ በማድረግ የምርጫ ክልልችን አከላለል በተመለከተ ባቀረበው ረቂቅ መነሻነት የፋዳሬሽን ምክር ቤት ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት እንጂ አሁን ያለውን ነባራዊ ሁኔታ መሰረት በማድረግ አዱስ የሕዝብ ቆጠራ ተደርጎ የምርጫ ቦርድ የምርጫ ክልልች አከላለልን በተመለከተ በሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 103(5) እና በአዋጅ ቁጥር 1133/2011 አንቀጽ 7/6 መሰረት ለፋደሬሽን ምክር ቤት ረቂቅ አቅርቦ የተሰጠ ውሳኔ የለም።
ይህም በጉዲዩ ላይ ውሳኔ የመስጠት ስልጣን ባለው አካል የምርጫ ክልልችን አከላለል በተመለከተ የተሰጠ ውሳኔ እንደላለ የሚያሳይ ነው። ስለሆነም ስልጣን ያለው አካል የምርጫ ክልልችን አከላል በሚመለከት ያሳለፈው ውሳኔ ሳይኖር ተጠሪ ከካፊ ዞን ሳይለም ወረዲ ቀበላ ምርጫ ጣቢያዎች እና ከቤንች ሸካ ዞን ጉራፈርዲ ወረዲ ቀበላ ምርጫ ጣቢያዎች ወደ ሸካ ዞን ማሻ አካባቢ እና ቴፒ ምርጫ ጣቢያዎች በሕገ ወጥ መንገድ የተጨመሩ የምርጫ ጣቢያዎች ሙለ በሙለ እንዱነሱ እና በራሳቸው ዞን ድምጻቸውን እንዱሰጡ ይወሰንልኝ በማለት ያቀረበው ጥያቄ ከመነሻውም ቢሆን የሕግ ድጋፍ የላለው እና አላግባብ የቀረበ ጥያቄ ነው። ይህንኑ መሰረት በማድረግ የምርጫ ቦርድ እና የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተጠሪን አቤቱታ ውድቅ ማድረጋቸው አግባብ ሆኖ ሳለ ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የተጠሪ ጥያቄ የብሓረሰቡ ውክልና ሳይሸራረፍ ተግባራዊ እንዱደረግ የሚጠይቅ የምርጫ ጣቢያን የሚመለከት እንጂ ተጨማሪ የምርጫ ክልል ይደራጅልኝ የሚል አይደለም በማለት የደረሰበት መደምደሚያ ተገቢነት ያለው ሆኖ አላገኘነውም።
ስለሆነም በዚህ ረገድ የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ለውሳኔው መሰረት ያደረጋቸውን ምክንያቶች እና በመጨረሻም የሰጠው ውሳኔ አግባብ መሆን አለመሆኑ እንደሚከተለው ተመልክተናል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አከራካሪ የሆኑት የምርጫ ጣቢያዎች ተነስተው ምርጫ ጣቢያዎቹ በሚገኙበት ዞን ወረዲ አካባቢ በሚገኝ ምርጫ ጣቢያ ክልል ስር እንዱጠቃለለ ከሚል መደምደሚያ ላይ ሉደርስ የቻለበት ዋነኛ ምክንያት የአገራችን የሕዝብ ቁጥር እድገት ምጣኔ እየጨመረ እንጂ እየቀነሰ እንዲልሆነ ከዲኝነት አስተውልት የምንገነዘበው ነው በሚል ነው።
በመሰረቱ የዲኝነት አስተውልት /judicial notice/ የሚወሰደው ተቀባይነት ያገኘ የታወቀ እውነት ሲኖር እና በልላ ማስረጃ ማረጋገጥ የማያስፈልገው ሆኖ ሲገኝ ነው /Judicial notice of a fact means a court’s declaration of the existence of a fact normally decided by the trier of fact, without requiring proof of that fact / ፤ ሆኖም የተያዘው ጉዲይ የምርጫ ክልል እና ምርጫ ጣቢያ አከላለል ሆኖ መነሻ የሚያደርገው የመራጭ የሕዝብ ቁጥር ስለመሆኑ ከላይ ተመልክተናል። ይህም በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 103 መሰረት የሕዝብ ቆጠራ ይህንኑ ለማድረግ ስልጣን በተሰጠው የሕዝብ ቆጠራ ኮሚሽን የሚከወን እና በየአሥር ዓመቱ የሚካሄድ እና ውጤቱም ለሕዝብ የሚገለጽበት ነው። ምንም እንኳን የሕዝብ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እንደሚሄድ የሚገመት ቢሆንም ለዲኝነት ሰጪ አካል በበቂ ማስረጃ ሳይረጋገጥ ውሳኔ ለመስጠት የሚቻልበት አይደለም። ስለሆነም በልላ ስልጣን ባለው አካል ሉረጋገጥ የሚችለውን ውጤት የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የአገራችን የሕዝብ ቁጥር እድገት ምጣኔ እየጨመረ እንጂ እየቀነሰ እንዲልሆነ ከዲኝነት አስተውልት የምንገነዘበው ነው ማለቱ አግባብ ሆኖ አላገኘነውም።
በመጨረሻም የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርደ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አከራካሪ የሆኑት ምርጫ ጣቢያዎች ከሸካ ዞን ቴፒ እና ማሻ ክልል የተጨመሩ ምርጫ ጣቢያዎች ተነስተው ወደ ሚገኙበት ዞን ወረዲ አካባቢ በሚገኝ ምርጫ ጣቢያ ክልል ስር እንዱጠቃለለ ሲል የሰጠው ውሳኔ ፍርድ ቤቶች ፍርድን ሲሰጡ ካላቸው ስልጣን እና ገደብ ጋር በማገናዘብ ማየት አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።
ሕግ አውጪው፤ ሕግ አስፈጻሚ እና ሕግ ተርጓሚው ሶስቱም የመንግስት አካላት ሲሆኑ በሕግ ተለይቶ የተሰጣቸው የየራሳቸው የሆነ ስልጣን እና ተግባር አላቸው። ፍርድ ቤቶች በሕግ አግባብ የተጠበቀ መብት በተነፈገ ጊዜ ይህንኑ አረጋግጠው ውሳኔ የመስጠት ያልተገደበ ስልጣን ያላቸው ስለመሆኑ አከራካሪ አይደለም። ሆኖም በዚህ መዝገብ አከራካሪ የሆነው ተጠሪ ያቀረበው አከራካሪ የሆኑት የምርጫ ጣቢያዎች ተነስተው ወደ ነበሩበት ይዛወሩልኝ የሚለው ጥያቄ ከምርጫ ክልል አከላለል ጋር በቀጥታ ተያያዥነት ያለው ነው። ስለሆነም የምርጫ ጣቢያው ከአንድ ቦታ ተነስቶ ወደ ላላ ቦታ እንዱዛወር መወሰን የሚችለው በሕጉ ሥልጣን የተሰጠው አካል እንጂ ፍርድ ቤቶች አይደለም። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ተጠሪ ያቀረበው የምርጫ ጣቢያዎች ይነሱልኝ ጥያቄም ምላሽ ሉያገኝ የሚገባው ተጠሪ ባቀረበው ጥያቄ መነሻነት ብቻ ሳይሆን የሐገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ በማገናዘብ የምርጫ ቦርድ ለፋዳሬሽን ምክር ቤት በሚያቀርበው የአከላለል ረቂቅ ምክር ቤቱ በሚሰጠው ውሳኔ መሰረት ነው። ስለሆነም የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ተጠሪ ምርጫን መሰረት በማድረግ ያቀረበውን አቤቱታ መነሻ በማድረግ ላልች ተከታታይ ጥያቄዎችን ሉያስነሳ የሚችል ውሳኔ መስጠቱ አግባብ ሆኖ አላገኘነውም።
ሲጠቃለል ከላይ በዝርዝር በገለጽናቸው ምክንያቶች የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ከካፊ ዞን ሳይለም ቀበላ ምርጫ ጣቢያዎች ወደ ሸካ ዞን ማሻ አካባቢ ምርጫ ክልል የተጨመሩ ምርጫ ጣቢያዎች ከማሻ አካባቢ ምርጫ ክልል ተቀንሰው ምርጫ ጣቢያዎቹ በሚገኙበት የካፊ ዞን ወረዲ አካባቢ በሚገኝ የምርጫ ክልል ስር እንዱጠቃለለ፤ ከቤንች ሸካ ዞን ቀበላ ምርጫ ጣቢያዎች ወደ ሸካ ዞን ቴፒ ምርጫ ክልል የተጨመሩ ምርጫ ጣቢያዎች ከቴፒ ምርጫ ክልል ተቀንሰው ምርጫ ጣቢያዎቹ ወደ ሚገኙበት የቤንች ሸካ ዞን ወረዲ አካባቢ በሚገኝ የምርጫ ክልል ስር እንዱጠቃለለ ሲል የሰጠው ውሳኔ ስለምርጫ ክልልች በሕገ መንግስቱ እና በምርጫ አዋጅ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች ያላገናዘብ እና መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ. ግንቦት 11 ቀን 2013 ዓ.ም በአብላጫ ድምጽ የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1 መሰረት ተሽሯል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ. ሚያዝያ 08 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ጸንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻለ።
No topics extracted.