የምርጫ ውጤት ከድምጽ መስጫ ወረቀት ጋር በተያያዘ ግድፈት የተፈፀመበት ነው ተብል የምርጫ ውጤት ተሰርዞ ድጋሚ ምርጫ እንዱደረግ የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ ከሰጠ በኋላ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እንደ ፍርደ ድጋሚ ምርጫ ለማድረግ መሰረት የሆነው የውሳኔ ሁኔታ የተቀየረና ዲግም ምርጫውን ማከናወን የማይቻለው በመሆኑ የቀደመውን የምርጫ ውጤት ተግባራዊ ማድረጉን የደ/ብ/ብ/ክ/መንግስት ብልጽግና ፓርቲ (ብልጽግና ፓርቲ) እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ፣ የሚሰጠው ውሳኔ የምርጫ ሂደትን የሚመለከት የመጨረሻ ውሳኔ ሆኖ ይግባኝ ለፋደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የሚቀርብበት እንጂ አስተዲደራዊ ውሳኔ ነው በሚል ለፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሚቀርብ ስላለመሆኑ የኢትዮጵያ ፍደራላዊ ዱሞክራሲያዊ ሪፐብላክ ብሓራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1133/2011 አንቀጽ 17(1) እና የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 155(4) የቁጫ ህዝብ ዱሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቁህዳፓ)
No summary available.
የሰ/መ/ ሀምላ 6 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) እትመት አሰፊ ደጀኔ አያንሳ ብርቅነሽ እሱባለው አመልካች፡- የደ/ብ/ብ/ክ/መንግስት ብልጽግና ፓርቲ (ብልጽግና ፓርቲ)፡- ጠበቃ ካላብ ተስፊዬ ቀረቡ ተጠሪዎች፡- 1ኛ. የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ፡- ተወካይ ወንጌል አባተ ቀረቡ 2ኛ. የቁጫ ህዝብ ዱሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቁህዳፓ)፡- ጠበቃ ጳውልስ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች በቀን 06/10/2014 ዓ.ም በተጻፈ አቤቱታ የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በ19/09/2014 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልኝ በማለት ስለጠየቀ ነው። ጉዲዩ ከዲግም ምርጫ ጋር የተያያዘ ሲሆን ክርክሩ የጀመረው የአሁን አመልካች 1ኛ ተጠሪ በሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለከፍተኛው ፍ/ቤት ቅሬታ በማቅረቡ ነው።
ከመዝገቡ መረዲት እንደሚቻለው በኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) እና በኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ መካከል በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በተካሄደ ክርክር የቁጫ ምርጫ ክልል ምርጫ ውጤት ከድምጽ መስጫ ወረቀት ጋር በተያያዘ ግድፈት የተፈፀመበት ነው ተብል የምርጫ ውጤቱ ተሰርዞ ድጋሚ ምርጫ እንዱደረግ በመ/ ነሐሴ 21 ቀን 2013 ዓ.ም ውሳኔ ተሰጥቷል።
ቦርደ እንደ ውሳኔው ለመፈፀም በእንቅስቃሴ ላይ እያለሁ አዱስ ሁኔታ ተከስቷል በማለት ጥቅምት 26 ቀን 2014 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ውሳኔ አሳልፍ ውሳኔውን በቁጥር አ116211/434 ህዲር 1 ቀን 2014 ዓ.ም ለአሁን 2ኛ ተጠሪ አሳውቋል። ቦርደ በሰጠው ውሳኔ የኢዜማ ፓርቲ ዕጩ የሆኑት ዶ/ር እንድሪያስ ሄባና እና ሻዛ ጋላላ ጋኔቦ ከምርጫ ውድድሩ ራሳቸውን በፈቃዲቸው ማግለላቸውን፤ እንዱሁም ላላዋ ዕጩ ወ/ሮ ብርቱካን ጦቃ ሀብቴ ፓርቲውን ወክለው እንዲይወዲደሩ የፓርቲው ወረዲ ጽ/ቤት እንዲገዲቸው ተገልጾልኛል። ይህ አዱስ ሁኔታ እንደተከሰተ ቦርደ ፓርቲውን ጠይቆ ፓርቲው ዕጩዎች ራሳቸውን ማግለል እንደማይችለ ከመግለጽ ውጪ ላላ ምላሽ አልሰጠም። በዚህ ምክንያት ቦርደ በፍርድ ቤቱ ውሳኔ መሰረት ለመፈፀም መቸገሩን በመግለጽ ስለፍርደ አፈፃፀም መመሪያ እንዱሰጥ ጠይቆ ፍርድ ቤቱ በተፈጠረው አዱስ ክስተት ምክንያት ውሳኔው የማይሻሻል (ማይለወጥ) መሆኑን በመግለጽ በመ/ ጥቅምት 5/2014 ዓ.ም ትዕዛዝ ሰጥቷል። ይህን የፓርቲውን መልስ እና የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ መሰረት በማድረግ ቦርደ ጉዲዩን እንደገና መርምሮ ፓርቲው ዕጩዎችን ወዱያውኑ ከመተካት ውጪ ያለፈቃዲቸው ዕጩ ማድረግ የማይችል በመሆኑና በወቅቱም ላለመወዲደር የወሰኑትን ዕጩዎቹን የሚተኩ ዕጩዎች ባለማቅረቡ እንዱሁም አንደኛዋ ዕጩ በፓርቲው ከውድድሩ እንዱወጡ የተወሰነ በመሆኑ እንደፍርደ ድጋሚ ምርጫ ለማድረግ መሰረት የሆነው የውሳኔ ሁኔታ የተቀየረ በመሆኑ ድጋሚ ምርጫ ለማድረግ የማይቻለው መሆኑን ቦርደ ተገንዝቧል። በመሆኑም በቁጫ ምርጭ ክልል ድጋሚ ምርጫ ይደረግባቸው በማለት ፍርድ ቤቱ በሰጠው ውሳኔ እና ትዕዛዝ መሰረት ዲግም ምርጫውን ማከናወን የማይቻለው መሆኑን ቦርደ ወስኗል። በዚህ ውሳኔ ምክንያት በምርጫ ክልለ የሚገኘው ህዝብ ያለ ተወካይ እንዲይቀር ለክልል ምክር ቤት አሸናፉ ናቸው ተብለው አስቀድሞ በቦርደ ማረጋገጫ የተሰጣቸው ዕጩ ተወዲዲሪዎች (የአሁን 2ኛ ተጠሪ ዕጮዎች) በምክር ቤቱ ተገኝተው የክልላቸው ህዝብ ህጋዊ ወኪል ሆነው እንዱያገለግለ በማለት ወስኗል።
የአሁን አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለከፍተኛው ፍ/ቤት በቀን 13/04/2014 ዓ.ም ባቀረበው ይግባኝ ቦርደ የምርጫ አዋጁን እና አዋጁን ለማስፈፀም የወጡ ደንብና መመሪያዎችን ሳይከተል በቁጫ ምርጫ ክልል የአንድ ዕጩ ፍቶ በምርጫ ወረቀት ላይ ባለማስቀመጡ የምርጫ ሥርዓት ግድፈት ፈጽሟል ተብል ቅሬታ ለፋ/ጠ/ፍ/ቤት ቀርቦ በመ/ በቀን 21/12/2013 ዓ.ም በተሰጠ ውሳኔ የምርጫ ክልለ ውጤት እንዱሰረዝና ድጋሚ ምርጫ እንዱደረግ ተወስኗል። በውሳኔው መሰረት 1ኛ ተጠሪ በቁጫ ምርጫ ክልል መስከረም 20/2014 ዓ.ም ድጋሚ ምርጫ ለማድረግ ቀጠሮ ይዞ ምርጫውን ለማስፈጸም ዝግጅት ተጀምሮ የነበረ ቢሆንም በላልች ምርጫ ክልልች ምርጫ ተደርጎ በቁጫ ምርጫ ክልል ምርጫ ሳያደርግ ቀርቷል። 1ኛ ተጠሪ ጥቅምት 26/2014 ዓ.ም በሰጠው አስተዲደራዊ ውሳኔ የፋ/ጠ/ፍ/ቤት በቂ በሆኑ ህጋዊ ምክንያቶች ተሰርዟል ያለው ውሳኔ እያለ በተሰረዘው ውጤት ምርጫውን አሸንፈው የነበሩ የፓርቲ እጩዎች ህዝብን ወክለው ምክር ቤት ይግቡ በማለት የፍ/ቤቱን ውሳኔ የሚቃረን አስተዲደራዊ ውሳኔ ሰጥቷል። የ1ኛ ተጠሪ ውሳኔ የህግ የበላይነትና የፍ/ቤቶችን የዲኝነት ስልጣን ያላከበረ ነው። ማንኛውም ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ በህግ አግባብ እስካልተለወጠ ድረስ የጸና ነው የሚለውን መርህ ያልተከተለ ከመሆኑ በተጨማሪ የህዝብ ለአላዊነትን ያላከበረ ነው። ቦርደ የፍ/ቤቱን ውሳኔ ለማስፈጸም አለመቻለን የገለጸበት ምክንያት በጠቅላይ ፍ/ቤት ውሳኔ ረቺ የነበረው ኢዜማ ፓርቲ ሁለት እጩዎች ራሳቸውን ከምርጫ በማግለላቸው እና አንድ እጩ ፓርቲውን ወክለው እንዲይወዲደሩ የወረዲ ጽ/ቤት ያገዲቸው መሆኑን ተከትል ነው። ምንም እንኳ የምርጫ ውጤት እንዱሰረዝ ጥያቄ ያቀረበው ፓርቲ ኢዜማ ቢሆንም የተፈጠረው ስህተት በምርጫ ክልለ የሚወዲደሩ ተፍካካሪ ፓርቲዎችን በቀጥታ የሚመለከት በመሆኑ ኢዜማ ራሱን ከውድድሩ ማግለለ ምርጫ ቦርድ በፍ/ቤት ውሳኔ መሰረት ከመፈጸም አያግደውም። በመሆኑም ምርጫው ተሰርዞ ዲግም ምርጫ እንዱደረግ የጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ በመሻር 1ኛ ተጠሪ (ቦርደ) የሰጠው አስተዲደራዊ ውሳኔ ቀሪ እንዱሆን ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቋል።
1ኛ ተጠሪ በ20/04/2014 ዓ.ም በሰጠው መልስ ባቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲ ተብል የተመዘገበው ብልጽግና ፓርቲ እንጂ የደ/ብ/ብ/ሕ/ክልል ብልጽግና ፓርቲ ባለመሆኑ ክስ የማቅረብ መብት ያለው ዋናው ብልጽግና ፓርቲ ነው እንጂ ይግባኝ ባይ አይደለም፤ በዋናው ጉዲይ በፋ/ጠ/ፍ/ቤት ተከራካሪ የነበረው ኢዜማ እንጂ ይ/ባይ ባለመሆኑ የፍርደ ተጠቃሚ ያልተደረገው ይ/ባይ ለላላ አካል የተሰጠውን ውሳኔ መነሻ በማድረግ ተጠቃሚ የሚሆንበት አግባብ ባለመኖሩ ቅሬታ ለማስቀረብ የሚያስችል መብት የለውም፤ የቦርደ የመጨረሻ አስተዲደራዊ ውሳኔ የምርጫ ውጤትን የሚመለከት ሲሆን የምርጫ ውጤትን በተመለከተ የሚቀርብን ክርክር አይቶ ለመወሰን የሚያስችል ስልጣን ያለው የፋ/ጠ/ፍ/ቤት ነው እንጂ የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ባለመሆኑ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን ለማየት የሚያስችል የስረ ነገር ስልጣን የለውም፤ የምርጫ ውጤትን በተመለከተ ቦርደ በሰጠው የመጨረሻ አስተዲደራዊ ውሳኔ ላይ ለፋደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የሚቀርብ ይግባኝ ውሳኔ በተሰጠ 10 ቀን ውስጥ መቅረብ ያለበት በመሆኑ ይግባኝ ባይ ያቀረበው ይግባኝ በይርጋ ቀሪ ሆኗል በማለት ተከራክረዋል።
የአሁን 2ኛ ተጠሪ ወደ ክርክሩ ጣልቃ ገብቶ በ28/08/2014 ዓ.ም በተጻፈ አቤቱታ ድጋሚ ምርጫ ይደረግ ተብል በፋደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት፣ ኢዜማ እና ምርጫ ቦርድ ተከራካሪ ሆነው ውሳኔ የተሰጠ በመሆኑ አስቀድሞ በፍርድ ባለቀ ጉዲይ ላይ በድጋሚ ክስ ላቀርብ አይገባም የሚል እና ላልች በ1ኛ ተጠሪ የቀረቡ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎችን እንዱሁም በፍሬ ነገሩ ዝርዝር መከራከሪያውን አቅርቧል።
ክርክሩ በዚህ መልኩ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዲዩን ለማየት የዲኝነት ስልጣን ያለው መሆን አለመሆኑን መርምሮ ውሳኔ ሰጥቷል። በሰጠው ውሳኔ በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 10(1)(ሀ) መሰረት ድጋሚ ምርጫ እንዱደረግ ውሳኔ መስጠት የሚችለው የፍደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት መሆኑ ተመልክቷል። በዚህ መሰረት ቦርደ የሰጠው አስተዲደራዊ ውሳኔ ተገቢ ባለመሆኑ ድጋሚ ምርጫ ይደረግ ወይም ቦርደ ድጋሚ ምርጫ አላደርግም ማለቱ ተገቢ ነው የሚለው ክርክር ታይቶ ውሳኔ ላሰጥበት የሚገባው በፋደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት እንጂ በፋደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አይደለም። አስቀድሞም የምርጫ ክልለን በተመለከተ ድጋሚ ምርጫ ይደረግ የሚል ውሳኔ የሰጠው የፋ/ጠ/ፍ/ቤት ሆኖ እያለ በዛው ምርጫ ክልል ላይ የተነሳውን ተመሳሳይ ጥያቄ የከፍተኛው ፍርድ ቤት አይቶ ለመወሰን የሚያስችል ስልጣን ያልተሰጠው በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን ለማየት የሚያስችል የስረ ነገር ዲኝነት ስልጣን የለውም በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 244(2) እና 245(2) መሰረት በአብላጫ ድምጽ ውሳኔ ሰጥቷል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ነው። አመልካች በ06/10/2014 ዓ/ም ባቀረበው ማመልከቻ በአዋጅ ቁጥር 1133/2011 አንቀጽ 17(1) መሰረት ቦርደ በሚሰጠው የመጨረሻ አስተዲደራዊ ውሳኔዎች ላይ በፋደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በይግባኝ እንደሚታይ በግልጽ ተደንግጓል። ከዚሁ ድንጋጌ ጋር በተጣጣመ መልኩ በፋዳራል የአስተዲደር ሥነ ሥርዓት አዋጅ 1183/2012 አንቀጽ 49(1) መሰረት የአስተዲደር ውሳኔ እንዱከለስ አቤቱታ የሚቀርበው ለፋደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ሆኖ ፍ/ቤቱም የመጨረሻ ውሳኔ እንደሚሰጥ በግልጽ ተደንግጓል። አመልካች በስር ፍ/ቤት ያቀረብነው ይግባኝ የቁጫ ምርጫ ክልልን አስመልክቶ የፋ/ጠ/ፍ/ቤት በመ/ የሰጠውን ውሳኔ የኢትዮጵያ ብሓራዊ ምርጫ ቦርድ በአስተዲደራዊ ውሳኔ በመሻሩ ይኸው ውሳኔ እንዱከለስ የቀረበ ይግባኝ ነው። በመሆኑም በይግባኙ የተጠየቀው ዲኝነት 1ኛ ተጠሪ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በራሱ በመሻር የሰጠው አስተዲደራዊ ውሳኔ ይከለስ የሚል በመሆኑ ላሰጥ የሚችለው ውሳኔ ከተጠየቀው ዲኝነት አንጻር ብቻ በመሆኑ የስር ፍ/ቤት በውሳኔው እንደገለጸው ምርጫው ዲግመኛ ይደረግ ወይም አይደረግ ብል ውሳኔ ላሰጥበት የሚያስችለው የህግ አግባብ የለም። አመልካች እንደ ስር ፍ/ቤት አገላለጽ የአፈጻጸም ወይም ያንን መሰል ዲኝነት ፈጽሞ አልተጠየቀም። በመሆኑም የስር ፍ/ቤት በዚህ ረገድ የደረሰበት መደምደሚያ ተቀባይነት የላለው ነው። አመልካች ለስር ፍ/ቤት ካቀረበው ጉዲይ አንፃር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 10 ተገቢነት የላለው እና ይኸው ድንጋጌም ከአዋጁ አንቀጽ 155(1-4) እና አዋጅ ቁጥር 1133/2011 አንቀጽ 17(1) ጋር ተዲምሮ መተርጎም ያለበት ነው። የምርጫ ሂደትና ውጤትን አስመልክቶ የነበሩ ቅሬታዎች በጠቅላይ ፍ/ቤት ታይተው ውሳኔ ተሰጥቶባቸዋል፤ለይግባኝ መንስኤ የሆነው የምርጫ ውጤት ተገልጾ በሂደቱ ላይ ቅሬታ ቀርቦ፣ ምርጫው በፍ/ቤት ከተሰረዘ በኋላ በተሰጠ አስተዲደራዊ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ነው። ስለሆነም የስር ፍርድ ቤት ስልጣን የለኝም በማለት የሰጠው ውሳኔ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ይሻርልን በማለት ቅሬታውን አቅርቧል።
ቅሬታው በሰበር አጣሪ ችልት ተመርምሮ አመልካች ለፋደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረበው አቤቱታ የፍደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ድጋሚ ምርጫ እንዱካሄድ ወስኖ እያለ 1ኛ ተጠሪ ይህን ውሳኔ ወደ ጎን በማድረግ ቀደም ሲል በፍ/ቤት በተሻረው ምርጫ ያሸነፈት እጩዎች ወደ ምክር ቤት እንዱገቡ አስተዲደራዊ በሆነ መልኩ ወስኗል የሚል ሆኖ እያለ አቤቱታው የቀረበለት ፍ/ቤት ጉዲዩን የማየት የስረ ነገር ስልጣን የለኝም በሚል የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ ያደረገበት አግባብ ከምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1133 አንቀጽ 17(1) እና ከፋደራል ፍ/ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 13(2) አኳያ ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለዚህ ሰበር ችልት እንዱቀርብ እና ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡበት ተደርጓል።
1ኛ ተጠሪ በቀን 17/10/2014 ዓ.ም ባቀረበው መልስ በድምጽ መስጫ ወረቀት ላይ የኢዜማ አንድ እጩ ካለመውጣቷ ውጭ ነጻና ፍትሀዊ በነበረው ምርጫ ተሳትፈው በተወካዮቻቸው አማካኝነት በመንግስት አስተዲደር የመሳተፍ መብታቸውን ያረጋገጡ ዜጎችን መብት ለመጠበቅ ተገቢ ነው የሚለውን መፍትሓ ተጠሪ ሰጠ እንጂ የሻረው ምንም አይነት የፍ/ቤት ውሳኔ የለም። የፋ/ጠ/ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ የሻረ አስተዲደራዊ ውሳኔ በ1ኛ ተጠሪ ባልተሰጠበት ሁኔታና የተሰጠ ውሳኔ ስለመኖሩም ማረጋገጫ ሳይቀርብ የፍ/ቤትን ውሳኔ የሻረ አስተዲደራዊ ውሳኔ በ1ኛ ተጠሪ ተሰጥቷል በሚልና ላልችም ተያያዥ ምክንያቶች በማንሳት በአመልካች በስር ፍርድ ቤት የቀረበውን ክርክር ተመልክቶ ፍርድ ቤቱ የሚሰጠው ውሳኔ የምርጫ ሂደትና ውጤት ብልም ድጋሚ ምርጫ ማድረግ አለማድረግን የሚመለከት እንደመሆኑ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ስልጣኑ የእኔ ሳይሆን የፋ/ጠ/ፍ/ቤት ነው በማለት የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ ማድረጉ ምንም አይነት የህግ ስህተት የለውም። በመሆኑም ወደ ፍሬ ጉዲዩ ቢገባ የሚሰጠው ውሳኔ በውጤት ደረጃ የምርጫ ሂደትንና ውጤትን ብልም ድጋሚ ምርጫ ማድረግን የሚመለከት እንደሆነ ፍርድ ቤቱ አረጋግጦ ጉዲዩን የማየት የስረ ነገር ስልጣን የለኝም በሚል በአመልካች ከህግ አግባብ ውጭ የቀረበውን ይግባኝ የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ውድቅ በማድረግ የሰጠው ውሳኔ የሚነቀፍበት ምክንያት ባለመኖሩ የአመልካች አቤቱታ ውድቅ ተደርጎ ውሳኔው እንዱጸና በማለት ተከራክሯል። 2ኛ ተጠሪ በበኩለ በቀን 17/10/2014 ዓ.ም ባቀረበው መልስ የከፍተኛው ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ ጉድለት ስለላለበት ውሳኔው እንዱጸና በማለት ጠይቋል።
አመልካችም አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልስ አቅርቧል።
ይህን ከዲኝነት ስልጣን ጋር የተያያዘ ክርክር ለመወሰን በምርጫ ነክ አዋጆች በብሓራዊ ምርጫ ቦርድ ውሳኔዎች ላይ ለፍርድ ቤቶች ይግባኝ የሚቀርብበትን አግባብ በተመለከተ የተደነገጉትን ድንጋጌዎች በቅድሚያ መመልከቱ ተገቢ ነው።
የምርጫ ቦርድ የመጨረሻ ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ ተከራካሪዎቹ ጉዲያቸውን ወደ ፍርድ ቤት በመውሰድ ይግባኝ የሚለበትና ውሳኔው እንዱሻር ማመልከቻ የሚቀርብበት ሂደት በህጉ ተመልክቷል። የብሓራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1133/2011 አንቀጽ 17 ስለ ይግባኝ ስልጣን የሚደነግግ ሲሆን በንዐስ ቁጥር 1 ስር እንደተመለከተው የስራ አመራር ቦርደ የሚሰጣቸው የመጨረሻ አስተዲደራዊ ውሳኔዎች በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንዱሁም የምርጫ ሂደትና ውጤትን በተመለከተ የሚሰጣቸው የመጨረሻ ውሳኔዎች በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በይግባኝ ሉታዩ ይችላለ።
የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 በተመሳሳይ ቦርደ በስነ ምግባር ጥሰቶች በሚሰጠው አስተዲደራዊ ውሳኔ ላይ እንዱሁም በድምጽ ቆጠራና ውጤት በሚነሱ ክርክሮች ላይ በሚሰጠው ውሳኔ ላይ ስለሚቀርበው ይግባኝ በመለያየት ይደነግጋል። በአንቀጽ 149 ስር እንደተመለከተው ቦርደ የምርጫ ስነ ምግባር ጥሰቶችን ተከትል በሚሰጠው ውሳኔ ላይ ቅር የተሰኘ ወገን አቤቱታውን ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ማቅረብ የሚችል ሲሆን፤ በልላ በኩል በአንቀጽ 155(4) ስር እንደተመለከተው ቦርደ በድምፅ ቆጠራ እና ውጤት ላይ ለሚነሱ ክርክሮች በሚሰጠው ውሳኔ ላይ ቅር የተሰኘ ወገን ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቤቱታ ማቅረብ ይችላል።
እነዚህ ከፍ ሲል የተመለከቱ ድንጋጌዎች ይዘታቸው ምን አይነት ጉዲዮች ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንደሚቀርብ ምን አይነት ጉዲዮች ደግሞ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እንደሚቀርብ የሚያሳዩ ናቸው። በተያዘው መዝገብ እያከራከረ ያለውና ቦርደ ውሳኔ የሰጠበት ጉዲይ የቁጫ ምርጫ ክልል ምርጫ ውጤት ከድምጽ መስጫ ወረቀት ጋር በተያያዘ ግድፈት የተፈፀመበት ነው ተብል የምርጫ ውጤቱ ተሰርዞ ድጋሚ ምርጫ እንዱደረግ በመ/ ነሐሴ 21 ቀን 2013 ዓ.ም በፋ/ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ የሥራ አመራር ቦርደ እንደ ውሳኔው ለመፈፀም በእንቅስቃሴ ላይ እያለሁ አዱስ ሁኔታ ተከስቷል በማለት ፍርድ ቤቱ በሰጠው ውሳኔ እና ትዕዛዝ መሰረት ዲግም ምርጫውን ማከናወን የማይቻለው መሆኑንና በዚህ ምክንያት በምርጫ ክልለ የሚገኘው ህዝብ ያለ ተወካይ እንዲይቀር አስቀድሞ አሸናፉ ናቸው ተብለው ማረጋገጫ የተሰጣቸው ዕጩ ተወዲዲሪዎች ወደ ምክር ቤት እንዱገቡ የሰጠውን ውሳኔ የሚመለከት ነው።ይህ የቦርደ ውሳኔ ከምርጫ ሂደትና ውጤት ውጪ የሆነ ላላ የአስተዲደራዊ ውሳኔ ተደርጎ የሚወሰድ አይደለም። ይግባኙ የቀረበው ከፍ ሲል በተጠቀሰው የቦርደ ውሳኔ ላይ በመሆኑ በፍርድ ቤቱ በጭብጥነት ተይዞ ውሳኔ የሚሰጠው ቦርደ በቁጫ ምርጭ ክልል ድጋሚ ምርጫ አላደርግም ማለቱ ተገቢ መሆን አለመሆኑን በተመለከተ ነው። መሰል ጉዲይ ደግሞ የምርጫ ሂደትን የሚመለከት ነው።
ስለሆነም ጉዲዩ በቦርደ የምርጫ ሂደትን አስመልክቶ በተሰጠ የመጨረሻ ውሳኔ (final decision with regard to electoral process) ላይ የቀረበ እና በአዋጅ ቁጥር 1133/2011 አንቀጽ 17(1) ስር የሚሸፈን ነው ብለናል። በዚህ ውሳኔ ላይ ደግሞ ይግባኙ ላቀርብ የሚችለው ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ነው።
ሥረ ነገሩን ለመስማትና ለመዲኘት ሥልጣን የላለው ፍርድ ቤት አቤቱታ የቀረበለት እንደሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 9(1) እና 231 በተደነገገው መሰረት አቤቱታው ተቀባይነት የለውም በማለት መመለስ የሚኖርበት ሲሆን ከዚህ አልፍ በተጠሪ በሚቀርብ የሥረ ነገር የዲኝነት ሥልጣን መቃወሚያ ላይ ክርክር ሰምቶ ሥልጣን የላለው መሆኑን በማረጋገጥ የሚሰጥ ውሳኔም የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 244(1)(ሀ) እና 245 ድንጋጌን የተከተለ ነው ከሚባል በቀር የሚነቀፍ አይሆንም።
ስለሆነም አመልካች የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ጉዲዩን ለማየት ስልጣን አለው በማለት ያቀረበው ክርክር ከፍ ሲል በዝርዝር ያመለከትነውን የመሰረታዊ እና የስነ ሥርዓት ህጉን ድንጋጌዎች ይዘት ያገናዘበ ባለመሆኑ ተቀባይነት የለውም ብለናል። ተከታዩም ተወስኗል።
ው ሣ ኔ
የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 19/09/2014 ዓ.ም በአብላጫ ድምጽ የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348(1) መሰረት ፀንቷል።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ይቻቻለ።
No topics extracted.