ከህገ መንግስት ነክ ክርክሮች አወሳሰንና የህገ መንግስት ትርጉም አስፈላጊነትን መወሰንን በተመለከተ የህገ መንግስት ትርጉምን በማይጠይቁ ግልጽ የሆኑ የህገ መንግስት ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ በህገ መንግስት ክርክሮች ላይ ውሳኔ መስጠት እንዱሁም ትርጉም የማያሻቸው መሆኑን በፍርድ መወሰን የፍርድ ቤቶች ስልጣን ስለመሆኑ የፋዳራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 3(2) እና የህገ መንግስት ጉዲዮች አጣሪ ጉባኤ አዋጅ ቁጥር 798/2005 አንቀጽ 4(2) የክልል ህገ መንግስት ድንጋጌ ህገ መንግስታዊ መሆን አለመሆኑ ሥልጣን ባለው አካል ተጣርቶ ውሳኔ እስካልተሰጠበት ድረስ ህገ መንግስታዊ ነው ተብል የሚገመት የኢትዮጵያ ብሓራዊ ምርጫ ቦርድ እና በሐረሪ ህዝብ ክልል መንግስት የሐረሪ ብሓራዊ ጉባኤ የፋዳሬሽን ምክር ቤትን ለማጠናከር እና ሥልጣንና ተግባሩን ለመዘርዘር የወጣው አዋጅ ቁጥር 251/1993 አንቀጽ 9 የኢትዮጵያ ብሓራዊ ምርጫ ቦርድ የኢትዮጵያ ሽግግር መንግስት ተወካዮች ምክር ቤት መጋቢት 6/1987 ባካሄደው 102ኛ መደበኛ ስብሰባ በጉባኤው የተደረሰበት ውሳኔ እና የክልልች ሕገ መንግስት እንዱሁም እነዚህን ሰነድች መሰረት በማድረግ የሚከናወን የምርጫ ሂደት ሕገ መንግስታዊ አይደለም የሚል ከሆነ ይህንን ለማስለወጥ ጉዲዩን ወደ ፋደሬሽን ምክር ቤት አቅርቦ ከሚታይለት በቀር ቦርደ በራሱ ውሳኔ የማይሰጥ ስለመሆኑ የፋደሬሽን ምክር ቤትን ለማጠናከር እና ሥልጣንና ተግባሩን ለመዘርዘር የወጣ አዋጅ ቁጥር 251/1993 አንቀጽ 4(1) እና የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 62(1)
No summary available.
ግንቦት 19 ቀን 2013 ዓ.ም.
ዳኞች- ብርሃኑ አመነው ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) እትመት አሰፊ ደጀኔ አያንሳ ብርቅነሽ እሱባለው አመልካች፡
ተጠሪ፡
መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው አመልካች ግንቦት 2 ቀን 2013 ዓ.ም በተጻፈ አቤቱታ የፍደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ በቀን 19/08/2013 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልኝ በማለት ስለጠየቀ ነው። ጉዲዩ የምርጫ ሂደትን መሰረት ያደረገ ሲሆን የአሁን ተጠሪን ጨምሮ በሀረሪ ክልል የሚገኙ የተለያዩ አካላት ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ባቀረቡት አቤቱታ የተጀመረ ነው።
ከመዝገቡ መረዲት እንደሚቻለው የሀረሪ ህዝብ ክልል ምክር ቤት የሐረሪ ብሓራዊ ጉባኤ በቁጥር ሐጉ/183/4/13 በ27/7/2013፤ የሐረሪ ሕዝብ ክልል ም/ቤት ጽ/ቤት በቁጥር ሐም/350/አጉ/2/13 በ27/07/13፤ የሐረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዲንት ጽ/ቤት በቁጥር 1/9/15/2013 በ28/07/2013 እና የሐረሪ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት በቁጥር PP/14/H/111/2013 በ22/7/2013 በተፃፈ ደብዲቤዎች አቤቱታቸውን ለኢትዮጵያ ብሓራዊ ምርጫ ቦርድ አቅርበዋል።
ባቀረቡት አቤቱታ ከክልለ ውጭ የሚኖር የሐረሪ ሕዝብ የክልለ ምክር ቤት አካል ለሆነው ለሐረሪ ብሓራዊ ጉባኤ የመምረጥ መብት የሽግግር መንግስት ተወካዮች ምክር ቤት መጋቢት 6/1987 ባካሓደው 102ኛ መደበኛ ስብሰባ ውሳኔ ሰጥቷል፤ በዚህ መሰረትም አምስቱንም አገራዊ ምርጫዎች ከክልለ ውጭ ያለ የብሓረሰቡ አባላት መርጠዋል፤ በመሆኑም የኢትዮጵያ ብሓራዊ ምርጫ ቦርድ በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በዚሁ መሰረት ሉፈጽም ይገባዋል በማለት ጥያቄያቸውን አቅርበዋል።
የስራ አመራር ቦርደ ጉዲዩንና የቀረቡትን ሰነድች እንዱሁም ቀደም ሲል ተፈፀሙ የተባለትን ምርጫዎች ከሕገ መንግስቱ አንፃር መርምሬያለሁ በማለት ሚያዚያ 1 ቀን 2013 ዓ.ም ውሳኔ ሰጥቷል። በሰጠው ውሳኔ፡-
ከዚህ ውጪ ሕገ መንግስቱ አንድ ቁጥሩ አነስተኛ የሆነ ብሓረሰብ ለክልል ምክር ቤቶች አባላት ሲያስመርጥ ከክልለ ውጭ ያለ የብሓረሰቡ አባላት እንዱመርጡ የደነገገው፤
እንዱሁም ለዚህ ብሓረሰብ አባላት ለብቻው የተለየ አሰራር መተግበር የሚያስችል ሕገ መንግስታዊ ድንጋጌ የለም።
የኢትዮጵያ ሽግግር መንግስት ተወካዮች ምክር ቤት መጋቢት 6/1987 ባካሄደው 102ኛ መደበኛ ስብሰባ የሐረሪ ብሓራዊ ጉባኤ ከክልለ ውጭ ነዋሪ በሆኑ የብሓረሰቡ አባላት ይመረጣል የሚለውን ውሳኔ የሚደግፍ የህገ መንግስት አንቀጽ ጠቅሶ መወሰኑም በውሳኔው ላይ እንደማይታይ ቦርደ ተረድቷል።
በተጨማሪም ይህ መጋቢት 6/1987 የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 102ኛ መደበኛ ስብሰባ ሰጠ የተባለው ውሳኔ አግባብ ያለመሆኑን ከሚያሳዩት ሁኔታዎች አንደ በላዩ ላይ የም/ቤቱ ማህተም ያረፈበት አይደለም።
በልላም በኩል በዚህ በመጋቢት 6/1987 የተወካዮች ም/ቤት ውሳኔ መሰረት ቦርደ ዝርዝር መመሪያ አውጥቶ እንደ ውሳኔው ያለፈትን አምስት ምርጫዎች ሲያስፈጽም እንደነበር ያሳያል የተባለውም የቦርደ መመሪያ ከቦርደ ጽ/ቤት ማግኘት አልተቻለም።
ላለፈት 5 ምርጫዎች ለሐረሪ ብሓራዊ ጉባኤ የሚመረጡ ተወካዮች ከክልለ ውጭ ባለ የብሓረሰቡ አባላት የብሓራዊ ምርጫ ቦርድ ሲያስመርጥ ቆይቶ ቢሆንም፤ ቦርደ ሲያከናውን በቆየው የምርጫ ማሻሻያ ወይም ሪፍርም እንደዚህ አይነት የሕገ መንግስትና የምርጫ ሕጉ መሰረት የላላቸውን ልምድችና አሰራሮች እንዲይቀጥለ ማድረግን ዓላማው ያደረገ ነው።
ሕገ መንግስታዊ ድጋፍ ባይኖረውም ላለፈት 5 ምርጫዎች ይህ የሐረሪ ጉባኤ ከክልለ ውጭ ባለ የብሓረሰቡ አባላት ሲመረጥ ቆይቷል የሚለውን (practice) ይዞ ለመቀጠል ቦርደ ቢወስን፤ ላልች አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ብሓረሰቦች ከክልላቸው ውጭ ያለት አባልቻቸው በምርጫው እንዱሳተፈ ቢጠይቁ፤ ቦርደ ልፈጽም አልችልም ቢል የቦርደን በፍትሐዊነት እና በገለልተኝነት ምርጫን የማስተዲደሩ ጉዲይ አደጋ ላይ እንዱወድቅ ያደርጋል።
በሕገ መንግስቱ ድጋፍ ያላቸውን አስቀድሞ ያለ ልምድችና አሰራሮች (practice) ብቻ ለመውሰድ ቦርደ ይገደዲል።
በመሆኑም ከሕገ መንግስቱና ከሚተገብራቸው የምርጫ ህግና መመሪያዎች አንፃር ይህን ጥያቄ ተቀብል ለማስተናገድ አይቻልም በማለት አቤቱታውን ውድቅ በማድረግ ወስኗል።
አመልካቹም መልስ እንዱሰጥ ተደርጎ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን ለማየት ስልጣን አይኖረውም የሚል መቃወሚያን ጨምሮ በፍሬ ጉዲዩም የሰጠው ውሳኔ እንዱፀና ክርክሩን አቅርቧል። ይግባኝ ሰሚው ችልት የግራ ቀኙን ክርክር ተመልክቶ፡- 1ኛ. የሐረሪ ክልል ሕገ መንግስት አንቀጽ 50(2) ድንጋጌ ከኢፋዱሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 50(3) ድንጋጌ ጋር የሚቃረን በመሆኑ ምክንያት ጉዲዩ የሕገ መንግስት ጥያቄ የሚያስነሳ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን ለማየት የሚያስችል ሥልጣን የለውም በሚል መልስ ሰጪው (የአሁን አመልካች) ያቀረበው የመቃወሚያ ክርክር ተቀባይነት ያለው ነው ወይስ አይደለም? 2ኛ. አይደለም ከተባለ ፍሬ ጉዲዩን በተመለከተ የይግባኝ ባዩን (የአሁን ተጠሪ) ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ቦርደ የሰጠው ውሳኔ ተቀባይነት ያለው ነው ወይስ አይደለም? የሚለ ጭብጦችን በመያዝ ጉዲዩን መርምሮ ውሳኔ ሰጥቷል።
ይህ አጠቃላይ መርህ ልዩ ሁኔታዎች ሉኖሩት ይችላለ ወይስ አይችልም የሚለው ሲታይ የምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 ልዩ ሁኔታዎችን በአንቀጽ 17 ይደነግጋል። በተለይም አንቀጽ 17(3) በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዬጵያውያን በአገሪቱ ውስጥ በሚደረግ ምርጫ ድምጽ መስጠትን የሚፈቅድ ነው፤ ይህም የሕገ መንግስቱ አንቀጽ 50(3) ድንጋጌ ልዩ ሁኔታዎች ሉኖሩት እንደሚችለ መገንዘብ የሚያስችል ሲሆን የክልለ ሕገ መንግስት አንቀጽ 50(2) ድንጋጌም በክልለ ጉዲይ የዚህ አይነቱን ልዩ ሁኔታ የሚደነግግ ነው ከሚባል በቀር ይቃረናል የሚባልበት ሕጋዊ ምክንያት የለም። ቦርደ ልዩ ሁኔታን የሚደነግገውን የአዋጅ ቁጥር 1162/2011 በአንቀጽ 17(3) ድንጋጌዎች አስመልክቶ የሕገ መንግስት ተቃርኖ ጥያቄ ያላነሳ ሆኖ ሳለ በተመሳሳይ አግባብ ልዩ ሁኔታን የሚደነግገውን የክልለን ሕገ መንግስት አንቀጽ 50(2) ድንጋጌ አስመልክቶ የሕገነመንግስት ተቃርኖ ጥያቄ ማንሳቱ ምክንያታዊ ልባል የሚችል አይደለም። በእነዚህ ሁለ ምክንያቶች የክልለ ሕገ መንግስት አንቀጽ 50(2) ድንጋጌ ከኢፋዱሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 50(3) ድንጋጌ ጋር የሚቃረን በመሆኑ ምክንያት ጉዲዩ የሕገ መንግስት ጥያቄ የሚያስነሳ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን ለማየት የሚያስችል ስልጣን የለውም በሚል ቦርደ ያቀረበው የመቃወሚያ ክርክር ተቀባይነት የለውም በማለት ወስኗል።
በእነዚህ ጊዜያት ሁለ በሽግግር መንግስት ተወካዮች ምክር ቤት ውሳኔም ሆነ በክልለ ሕገ መንግስት የሕገ መንግስት ተቃርኖ ጉዲይ ከየትኛውም አካል የተነሳ ተቃውሞም ሆነ የተላለፈ ተቃራኒ ውሳኔ የለም። ቦርደ የኢትዮጵያ ሽግግር መንግስት ተወካዮች ምክር ቤት ውሳኔ እና የክልለ ሕገ መንግስት እንዱሁም እነዚህን ሰነድች መሰረት በማድረግ የሚከናወን የምርጫ ሂደት ሕገ መንግስታዊ አይደለም የሚል ከሆነ ይህንን ማስለወጥ የሚገባው ጉዲዩን ለሚመለከተው አካል አቅርቦ በሚያሰጠው ውሳኔ መሰረት ከሚሆን በቀር በራሱ በሚሰጠው ውሳኔ ላሆን ስለማይገባ ቦርደ የሰጠው ውሳኔ ጉድለት ያለበትና ሉታረም የሚገባው ነው ብሎል። ይህን ተከትልም ቦርደ ያሳለፈውን ውሳኔ በመሻር የኢትዮጵያ የሽግግር መንግስት ተወካዮች ምክር ቤት በ06/07/1987 ባደረገው 102ኛ መደበኛ ስብሰባ ባስተላለፈው ውሳኔ እና በክልለ ሕገ መንግስት በተመለከተው መሰረት ቦርደ ተገቢውን ሉፈጽም ይገባል በማለት ወስኗል።
የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 51(15) ምርጫን የሚመለከቱ ህጎች የማውጣት ስልጣን የፍደራል መንግስት ብቻ መሆኑን አንቀጽ 55(1) (መ) ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ምርጫን በተመለከተ ህግ የማውጣት ስልጣን መስጠቱን፣ ከክልል ም/ቤት በግልጽ ከምርጫ ጋር የተያያዘ ሕግ የማውጣት ስልጣን በአዋጅ 1162/2011 አንቀጽ 13(2) ከአካባቢ ምርጫ ጋር በተያያዘ ስልጣን በመስጠቱ የክልለ ሕገ መንግስት ከተሰጠው ስልጣን ውጭ ወጥቶ በፋ/መ/ተወካዮች ም/ቤት ስልጣን ውስጥ በመግባት የደነገገው ድንጋጌ ከፍተኛ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው።
በአጠቃላይ የፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ይህን ጉዲይ ለማየት ስልጣን የለውም በሚል በአዋጅ ቁጥር 1133/2011 አንቀጽ 17(1) አንፃር ያቀረብነውን ክርክር፤ እንዱሁም የክልለ ሕገ መንግስት አንቀጽ 50(2) የኢፋዱሪ ሕገ መንግስትን አንቀጽ 50(3) የሚቃረን በመሆኑ በክልለ ሕ ገመንግስት ላይ ባለ ድንጋጌዎች ለመፈፀም የሕገ መንግስት አጣሪ ጉባኤ መርምሮ በሚሰጠውና የፋዳሬሽን ምክር ቤት በሚሰጠው ውሳኔ መሆኑን በማንሳት የፋ/ጠ/ፍ/ቤት ይህን ጉዲይ ለማየት ሥልጣን የለውም በሚል ያቀረብነው የህግ ክርክር ውድቅ መደረጉ አላግባብ በመሆኑ ውሳኔው የህግ ስህተት ያለበት ነው ተብል እንዱሻርልን። የኢፋዱሪ ሕገ መንግስት አነስተኛ ቁጥር ላላቸው ብሓረሰቦች የሚያደርገው ጥበቃ ‘territorial’ በሆነ መርህ እንጂ በ‘non territorial’ ያለመሆኑን በዝርዝር አስረድተን ፍ/ቤቱ ያቀረብነውን ክርክር ምንም ሳይል አልፍታል ስለሆነም የሰበር ችልቱ ጉዲዩን እንዱመረምርና ከዚህ አንፃር ውሳኔው እንዱሻርልን።
እንዱሁም የምርጫ ሕግ የማውጣቱ ስልጣን የፋዳራል መንግስትና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ብቻ ሆኖ ሳለ የክልል ምክር ቤት የዞንና የወረዲ፣ የከተማ፣ የክፍለ ከተማ፣ የቀበላ ም/ቤቶች ቁጥር (ወይም ወንበር) ከመወሰን ውጭ ላላ ስልጣን እንደላላቸው ያቀረብነውን ክርክር ሳይታይ መታለፈ አግባብ ባለመሆኑ ሰበር ችልቱ ክርክራችንን ተቀብል የክልለ መንግስት ያወጣው ሕገ መንግስት የላላን የመንግስት አካል ስልጣን የሚጋፊ ያለስልጣኑ ሕግ ያወጣ መሆኑን በመገንዘብ የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በመሻር አመልካች የሰጠው (ያሳለፈው) ውሳኔ ህጋዊና በህገ መንግስቱ ትክክለኛ ትርጉም ላይ የተመረኮዘ መሆኑን በመረዲት ከዚህ በተቃራኒ የበታች ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ ፍ/ቤቱ ውድቅ እንዱያደርግልን በማለት ቅሬታውን አቅርቧል።
ቅሬታው በሰበር አጣሪ ችልት ተመርምሮ ለአሁን አመልካች ቀርቦ የነበረው ጥያቄ ከምርጫ ድምጽ አሰጣጥ እና ውጤት ቆጠራ ጋር የተያያዘ ሳይሆን ከዚህ ውጭ በሆነ ጉዲይ ላይ ሆኖ እያለ ቦርደ በሰጠው ውሳኔ ላይ ለፋ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ላቀርብ የቻለበት የህግ አግባብ ከአዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 155(4) አኳያ መመርመር ያለበት በመሆኑ፤ እንዱሁም የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ህገ መንግስት ከመታወጁ በፉት በሽግግር መንግስቱ የተወካዮች ምክር ቤት ተሰጥቷል የተባለው ውሳኔ ህገ መንግስቱ ስራ ላይ ከዋለ በኋላ ተፈፃሚ የተደረገበት የህግ አግባብ እና ተያያዥ የህጋዊነት ጉዲዮች ከህገ መንግስቱ አንቀጽ 9 እና 50 ድንጋጌ አኳያ ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብና ተጠሪ መልስ እንዱሰጥበት ተደርጓል።
ተጠሪ በቀን 09/09/2013 ዓ.ም ባቀረበው መልስ በአዋጅ ቁጥር 1133/2011 አንቀጽ 17(1) ድንጋጌ ለስር ፍ/ቤት ስልጣን የሚሰጥ ድንጋጌ ከመሆኑም በላይ ግራ ቀኙ የሚከራከሩበት ጉዲይ የዚሁ ድንጋጌውን መስፈርት ጭምር የሚያሟላ ነው። መራጮችን የመመዝገብና ካርድ የመስጠት ተግባራት የምርጫ ሂደቶች በመሆናቸው በእነዚህ ጉዲዮች ላይ ቦርደ የሚሰጣቸው የመጨረሻ ውሳኔዎችን አስመልክቶ በይግባኝ ደረጃ ለማየት ስልጣን የተሰጠው አካል የፋ/ጠ/ፍ/ቤት መሆኑን የአዋጁ ድንጋጌ በግልጽ የሚያመለክት በመሆኑ ጉዲዩ በስር ጠ/ፍ/ቤት ታይቶ መወሰኑ አግባብ ነው። አመልካች በክልለ የሚያካሂደውን ምርጫ በገለልተኝነት ማስፈጸም ሲገባው ላላ አዱስ ልዩ ምርጫ ጣቢያ እንዱያቋቁም የተጠየቀ በማስመሰል ጉዲዩ ላታይ የሚገባው በአዋጅ ቁጥር 1133/2011 አንቀጽ 17 መሰረት ሳይሆን በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 17 ነው በማለት ለተለያየ አላማ የሚያገለግለ አዋጆችን በማምታታትና በማዘባረቅ ያቀረበውን ክርክር ጉዲዩ ላይ ስልጣን ያለው ቦርደ እንጂ ፍ/ቤት አይደለም ከሚል በቀር ጉዲዩ የምርጫ ሂደትን የማይመለከት ስለመሆኑ በስር ፍ/ቤት ያቀረበው ክርክር ባለመኖሩ የፋ/ጠ/ፍ/ቤት የስረ ነገር ስልጣንን አስመልክቶ ጉዲዩ የምርጫ ሂደትን የሚመለከት አይደለም ሲል ያቀረበው ክርክር የለም በሚል መተቸቱ አግባብነት ያለው ነው። አመልካች የስረ ነገር ስልጣን ክርክር ነጥብ አቅርቦ ቢሆን እንኳን በአዋጅ ቁጥር 1133/2011 አንቀጽ 17(1) መሰረት በቦርደ ደረጃ የመጨረሻ ውሳኔ በተሰጠበት የምርጫ ሂደት ላይ ጠ/ፍ/ቤቱ ከማየት የሚከለክለው ላሆን አይችልም። በተጨማሪም አከራካሪው ጉዲይ ከክልለ ውጭ የሚገኙ የሐረሪ ብሓረሰብ አባላት የፍደራል ተወካዮቻቸውን ጨምሮ የሐረሪ ብሓራዊ ጉባኤ አባላትን በመራጭነት የመመዝገብና ካርድ የመውሰድ ተግባራት ከድምጽ አሰጣጥና ቆጠራ በፉት የሚገኝ የምርጫ ሂደት እንጂ በአዋጅ 1162/2011 አንቀጽ 155(4) ድንጋጌ የተመለከተውን የድምጽ አሰጣጥና ቆጠራ የሚመለከት ክርክር ባለመሆኑ ከጉዲዩ ጋር ተያያዥነት ያለው አይደለም። ስለሆነም አከራካሪ የሆነው ጉዲይ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት መጋቢት 6/1987 በተወሰነው እና በክልለ ህገ መንግስት አንቀጽ 49 እና 50(2) በተመለከቱት ድንጋጌዎች መሰረት በቦርደ በ6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ በተቋቋሙ ምርጫ ጣቢያዎች አግባብነት ባላቸው የኢትዮጵያ ከተሞች የሚገኙ ሐረሪዎች የፍደራል ተወካያቸውን ጨምሮ የሐረሪ ብሄራዊ ጉባኤ አባላትን በመራጭነት እንዱመርጡ የመመዝገብና የመራጭነት ካርድ መስጠት የምርጫ ሂደት እንጂ ይኸው ሀገራዊ ምርጫ በአሁን ደረጃ የሚገኝበት ሂደት ድምጽ አሰጣጥ ሂደት ገና ያልደረሰ በመሆኑ የድምጽ ቆጠራና ውጤት አግባብነት ያለው ባለመሆኑ የስር ፍ/ቤት ውሳኔ አግባብ ነው። በልላም በኩል ግልጽ የህገ መንግስት ድንጋጌዎች ትርጉም የማያሻቸው እና እነዚሁኑ ድንጋጌዎች ተፈጻሚ ማድረግ ህገ መንግስታዊ ግዳታ እንጂ የህገ መንግስት ትርጉም መስጠት አይደለም፤ የሐረሪ ክልል ሕገ መንግስት አንቀጽ 50(2) ድንጋጌ የሚመለከተው የክልለን ም/ቤት የሚያዋቅሩት ሁለት ጉባኤዎች መካከል አንደኛው ስለሆነው የሐረሪ ብሄራዊ ጉባኤ አባላት አመራረጥ ሲሆን የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 50(3) ደግሞ የሚያመለክተው የክልል ም/ቤቶች ተጠሪነትን ነው። ስለዚህ ድንጋጌዎቹ የሚያወሱት ሁለት ስለተለያዩ አካላት የሚመለከቱ እና የተለያዩ ርዕሰ ጉዲዮችን የሚሸፍኑ በመሆናቸው ግንኙነት የላላቸውና ግልጽ በመሆናቸው ሉቃረኑ የማይችለ፣ ግልጽ፣ የማያሻሙና ትርጉም የማያሻቸው በመሆኑ የአመልካች ተቃውሞ ውድቅ መደረጉ አግባብ ነው። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውሳኔ እና የክልለ ህገ መንግስት የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ህገ መንግስቱን መሰረት ያደረገ ነው፤ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ውሳኔ ከህገ መንግስቱ ጋር የሚጣጣምና የክልል ህገ መንግስት አካል ሆኖ መጽደቁ በፋደራለም ሆነ በክልል ህገ መንግስት ድጋፍ ያለው ስለመሆኑ አስረጅዎች ናቸው። አመልካች መጋቢት 6/1987 በተካሄደው 102ኛ መደበኛ ስብሰባ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የተሰጠው ውሳኔ ህገ መንግስቱ ኦፉሺያሉ ተፈጻሚ እንዱሆን ከታወጀበት ነሐሴ 15/1987 በፉት የሆነ በማስመሰል የውሳኔው ተፈጻሚነት አጠራጣሪ ለማድረግ የሚያቀርባቸው መከራከሪያዎች የህግ መሰረት የላላቸው ናቸው ምክንያቱም ም/ቤቱ ውሳኔውን ካስተላለፈበት በፉት ህዲር 29/1987 ተመክሮና ተዘክሮ በህገ መንግስታዊ ጉባኤ ፀድቆ ስለነበር ም/ቤቱ ከህገ መንግስቱ ድንጋጌዎች ጋር የተጣጣሙ ውሳኔ መስጠቱና በ1988 አዱስ ለሚመሰረተው ም/ቤት እስከሚያስረክብበት ጊዜ ድረስ ህገ መንግስቱም ፀድቆም ተፈጻሚ በሚሆንበት ጊዜያት ጭምር በህገ መንግስቱ መሰረት ስራዎችን ሲያከናውን እንደነበር አስረጅ ነው። ከክልለ ውጭ የሚገኙ የብሓሩ አባላት የፍደራል ተወካያቸውን ጨምሮ የሐረሪ ብሓራዊ ጉባኤ ላይ የሚሰጡት ድምጽ በህገ መንግስቱ የተረጋገጠ ራስን በራስ የማስተዲደር መብት በተጨባጭ ለማስከበር ከኢ.ፋ.ዱ.ሪ ህገ መንግስት ጋር በሚጣጣም መልኩ የተወሰነ አዎንታዊ እርምጃ ነው። የሐረሪን ክልል ም/ቤት አወቃቀር እና አወካከል የውስጥ ዱሞክራሲ አሰራር አስመልክቶ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አጥንቶ እንዱያቀርብ የተወከለው ኮሚቴ ተሞክሮ የተወሰደባቸው ሀገራት የአናሳ ቡድን እና ማህበረሰብ መብት መሰረት የሆኑ የአለም አቀፍ ኢትዮጵያ ተቀብላ ያጸደቀቻቸው ሰነድች የሀገሪቱ ህግ አካል ከመሆናቸውም በላይ የአናሳ መብቶችን የሚደግፈ መሆናቸው የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ውሳኔም የክልለን ህገ መንግስት አንቀጽ 49 እና 50(2) ከኢ.ፋ.ዱ.ሪ ህገ መንግስት ጋር በማጣጣም የተፈጸሙ ሆኖ ሳለ ቦርደ ይህን ሳያገናዝብ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ህገ መንግስት ድጋፍ እንደላለው አድርጎ መውሰደ መሰረታዊ ስህተት ነው። የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 50(3) ላይ የተመለከተውን ድንጋጌ ቦርደ የሚረዲው ‹‹የክልል ም/ቤት ሉመረጥ የሚችለው በክልል ውስጥ በሚኖሩ ህዝቦች ብቻ›› እንደሆነ ቦርደ አመላክቷል። በቦርደ የተጠቀሰው ይህ ድንጋጌ የማያሻማና ግልጽ ድንጋጌ በመሆኑ ትርጉም የማያሻው ሲሆን በትርጉም ሰበብ በድንጋጌው ባልተመለከተው አግባብ ስለ ክልል ም/ቤት ተጠሪነት የሚያወሳ ድንጋጌን የክልል ም/ቤት አመራረጥ ያወሳል ብል ህገ መንግስታዊ ላልሆነው የቦርደ የተሳሳተ አረዲድ ላይ የተመሰረተው አቋም ለጉዲዩ አግባብነት የላለውና ተያያዥ ያልሆነ ድንጋጌ ጠቅሶ ያቀረበው ክርክር ከፍተኛ የህግ ስህተት አለበት።
ቦርደ የክልል ም/ቤትን ተጠሪነትን የሚመለከተውን የህገ መንግስት ድንጋጌ የክልል ም/ቤት አመራረጥ እንደሆነ አድርጎ በመጥቀስ የኢትዮጵያ ምርጫ non territorial ሳይሆን territorial ነው የሚለው አተረጓጎም የተሳሳተ ነው። የክልል ም/ቤት አወቃቀርና አወካከል እንዱሁም የም/ቤት አባላት ቁጥር መወሰን የምርጫ ህግ ማውጣት ባለመሆኑ ቦርደ በዚህ ረገድ ከሃላፉነት ተግባሩ በመሸሽ ያቀረበው ክርክር ተቀባይነት የለውም። ቦርደ ከስልጣኑ በመተላለፍ የወሰነበት አግባብ ህግን ያልተከተለ በመሆኑ የስር ፍ/ቤት በቦርደ የተሰጠውን ውሳኔ መሻሩ በአግባቡ ነው። የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት በቀን 06 መጋቢት 1987 ባካሄደው 102ኛ መደበኛ ስብሰባ የተሰጠው ውሳኔ ተመሳሳይ ስልጣን ባለው አካል ወይም ላላ በህግ አግባብ ውሳኔው የተለወጠ ወይም የተሻረ አለመሆኑ እየታወቀ በበላይ አካል የተሰጠ ውሳኔ ለማረም ስልጣን ሳይኖረው ላለመፈጸም የያዘው አቋም የህግ የበላይነትን የሚጻረር ነው። የክልል መንግስትና የፍደራል መንግስታት መካከል መከባበር ግዳታ እንደመሆኑ የፍደራል አስፈጻሚ መስሪያ ቤት መካከል አንደ የሆነው ቦርደ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ አንቀጽ 50(8) መሰረት ለክልልች የተሰጠ ስልጣን በፋደራል መንግስት መከበር አለበት የሚለውን ድንጋጌ በሚጻረር መልኩ የምርጫ ሂደቱን በክልለ ህገ መንግስት መሰረት ያለመምራቱ የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ህገ መንግስቱን አንቀጽ 50(8) የተላለፈ በመሆኑ እና የተጠሪ ጥያቄ የህግ መሰረት ያላቸው መሰረታዊ መብቶች እንጂ በስመ ሪፍርም የሚጨፈለቁ ህገ መንግስታዊ መሰረት የላቸውም በሚል ተራ ውሳኔ የሚገደቡ ባለመሆናቸው የቦርደን ውሳኔ በመሻር የስር ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ አግባብ ነው። በተጨማሪም ከዚህ ቀደም በተካሄደ ተከታታይ አምስት አገራዊ ምርጫ ከክልለ ውጭ የሚገኙ የሐረሪ ብሄረሰብ አባላት የፍደራል ወኪላቸውን ጨምሮ የሐረሪ ጉባኤ አባላትን መምረጣቸው የህግ ድጋፍ ሳይኖረው እንዱሁ ሲፈጸም የነበረ ተግባር ሳይሆን በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት በተሰጠ ውሳኔ መሰረት ህገ መንግስቱን መሰረት በማድረግ ነው፤ ሆኖም ይህን ውሳኔ የሚቀይር ወይም የሚያስቀይር ተቃራኒ ውሳኔ ወይም ህግ ሳይኖር ምርጫ ቦርደ ስልጣኑን በማለፍ በራሱ አተረጓጎም የማይቃረኑትን ይቃረናለ ብል ትርጉም መስጠቱ በፋዳሬሽን ም/ቤት ስራ መግባት በመሆኑ የስር ፍ/ቤት ቦርደ ግዳታውን እንዱወጣ የሰጠው ውሳኔ አግባብ እና ፍትሀዊ ነው። በአጠቃላይ የአመልካች አቤቱታ ውድቅ ተደርጎ የፍደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ውሳኔ እንዱጸና በማለት ተከራክረዋል። አመልካችም ክርክሩን በማጠናከር ግንቦት 11/2013 ዓ.ም የተጻፈ የመልስ መልስ አቅርቧል።
የጉዲዩ አመጣጥና የግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ከላይ የተመለከተው ሲሆን ይህ ችልት ክርክራቸውን በቃል ሰምቷል። የቃል ክርክራቸው ከመቅረፀ ድምፅ ተገልብጦ የመዝገቡ አካል እንዱሆንም አድርጓል። ለጉዲዩ አወሳሰን ይረዲ ዘንድ የኢትዮጵያ ሽግግር መንግስት የተወካዮች ምክር ቤት 102ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ ከኢፋዱሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዱቀርብ በማድረግ፤ እንዱሁም የሐረሪ ብሓራዊ ጉባኤ ምርጫ አፈፃፀም መመሪያን በማስቀረብ ተመልክቷል። አጠቃላይ ጉዲዩንም የሰበር አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሯል።
እንደመረመርነው አመልካች ያቀረበው ቅሬታ እንዱሁም በሰበር አጣሪ ችልቱ እንዱታይ የተያዘው ጭብጥ ቀዲሚ ማጠንጠኛ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ጉዲዩን ተቀብል ለመወሰን ስልጣን የለውም በሚል የቀረበው ነው። ከዲኝነት ስልጣን ጋር ተያይዞ የቀረበው ይኸው ክርክር በሁለት መልክ የቀረበ ነው። አንደኛው የፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ይህን ጉዲይ ለማየት ስልጣን የለውም በሚል የአዋጅ ቁጥር 1133/2011 አንቀጽ 17(1) በዋቢነት ተጠቅሶ የቀረበው እና ከዚሁ ጋር በተያያዘ በአጣሪ ችልት የተጠቀሰው ለአሁን አመልካች ቀርቦ የነበረው ጥያቄ ከምርጫ ድምጽ አሰጣጥ እና ውጤት ቆጠራ ጋር የተያያዘ ሳይሆን ከዚህ ውጭ በሆነ ጉዲይ ላይ ስለሆነ ቦርደ በሰጠው ውሳኔ ላይ ለፋ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ላቀርብ የቻለበት የህግ አግባብ ከአዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 155(4) አኳያ ይመርመር መባለ ነው።
ሁለተኛው ከስልጣን ጋር የተያያዘ የክርክር ዘውግ የህገ መንግስት ትርጉም አሰጣጥን መሰረት ያደረገ ሲሆን የክልለ ሕገ መንግስት አንቀጽ 50(2) የኢፋዱሪ ሕገ መንግስትን አንቀጽ 50(3) የሚቃረን በመሆኑ ጉዲዩ በሕገ መንግስት አጣሪ ጉባኤ ተመርምሮ በፋዳሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ ላሰጥበት የሚገባ መሆኑን በማንሳት የፋ/ጠ/ፍ/ቤት ይህን ጉዲይ ለማየት ሥልጣን የለውም በሚል የቀረበ ክርክር ነው።
ከፍ ሲል የተጠቀሱትን ከዲኝነት ስልጣን ጋር የተያያዙ ክርክሮች ለመወሰን በምርጫ ነክ አዋጆች በብሓራዊ ምርጫ ቦርድ ውሳኔዎች ላይ ለፍርድ ቤቶች ይግባኝ የሚቀርብበትን አግባብ በተመለከተ የተደነገጉትን ድንጋጌዎች፤ ከህገ መንግስት ጋር በተያያዘ በሚነሱ ክርክሮች ላይ ፍርድ ቤቶች ስለሚኖራቸው ስልጣን፤ ስለ ህገ መንግስታዊነት ግምት፤ እንዱሁም በዲኝነት በተያዘ ጉዲይ ላይ የህገ መንግስት ትርጉም አስፈላጊነትን ስለመወሰን በሀገራችን የተዘረጋውን ስርዓትና የህጉን ማእቀፍ መመልከቱ ተገቢ ነው።
የምርጫ ቦርድ የመጨረሻ ውሳኔ ከሰጠ በኋላ ተከራካሪዎቹ ጉዲያቸውን ወደ ፍርድ ቤት በመውሰድ ይግባኝ የሚለበትና ውሳኔው እንዱሻር ማመልከቻ የሚቀርብበት ሂደት በህጉ ተመልክቷል። የብሓራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1133/2011 አንቀጽ 17 ስለ ይግባኝ ስልጣን የሚደነግግ ሲሆን በንዐስ ቁጥር 1 ስር እንደተመለከተው የስራ አመራር ቦርደ የሚሰጣቸው የመጨረሻ አስተዲደራዊ ውሳኔዎች በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንዱሁም የምርጫ ሂደትና ውጤትን በተመለከተ የሚሰጣቸው የመጨረሻ ውሳኔዎች በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በይግባኝ ሉታዩ ይችላለ። የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 በተመሳሳይ ቦርደ በስነ ምግባር ጥሰቶች በሚሰጠው አስተዲደራዊ ውሳኔ ላይ እንዱሁም በድምጽ ቆጠራና ውጤት በሚነሱ ክርክሮች ላይ በሚሰጠው ውሳኔ ላይ ስለሚቀርበው ይግባኝ በመለያየት ይደነግጋል። በአንቀጽ 149 ስር እንደተመለከተው ቦርደ የምርጫ ስነ ምግባር ጥሰቶችን ተከትል በሚሰጠው ውሳኔ ላይ ቅር የተሰኘ ወገን አቤቱታውን ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ማቅረብ የሚችል ሲሆን፤ በልላ በኩል በአንቀጽ 155(4) ስር እንደተመለከተው ቦርደ በድምፅ ቆጠራ እና ውጤት ላይ ለሚነሱ ክርክሮች በሚሰጠው ውሳኔ ላይ ቅር የተሰኘ ወገን ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቤቱታ ማቅረብ ይችላል። እነዚህ ድንጋጌዎች ፍርድ ቤቶች ቦርደ የተቋቋመበትን ዓላማ ማሳካቱና እና በህጉ አግባብ ጉዲዩን መወሰኑን እንዱያረጋግጡ የሚያስችለ ናቸው። በይዘታቸውም ምን አይነት ጉዲዮች ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንደሚቀርብ ምን አይነት ጉዲዮች ደግሞ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እንደሚቀርብ የሚያሳዩ ናቸው። በተያዘው መዝገብ እያከራከረ ያለውና ቦርደ ውሳኔ የሰጠበት ጉዲይ ከክልለ ውጭ የሚገኙ የሐረሪ ብሓረሰብ አባላት የሐረሪ ብሓራዊ ጉባኤ አባላትን ለመምረጥ እንዱችለ ተገቢው ምርጫ ነክ ሥራ ምርጫን በሚያስተዲድረው ቦርድ እንዱፈፀም የቀረበን ጥያቄ የሚመለከት ነው። ይህ ደግሞ የምርጫ ስነ ምግባርን በመጣስ የሚተላለፍ አስተዲደራዊ ውሳኔ አይደለም። እንዱሁም በአዋጅ 1162/2011 አንቀጽ 155(4) ድንጋጌ የተመለከተውን የድምጽ አሰጣጥና ቆጠራ የሚመለከት ክርክር አይደለም። ይልቁንም በቦርደ የምርጫ ሂደትን አስመልክቶ የተሰጠ የመጨረሻ ውሳኔ (final decision with regard to electoral process) ልባል የሚችልና በአዋጅ ቁጥር 1133/2011 አንቀጽ 17(1) ስር የሚያርፍ ነው። በዚህ ውሳኔ ላይ ደግሞ ይግባኙ ላቀርብ የሚችለው ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ነው።
በልላ በኩል ከህገ መንግስት ነክ ክርክሮች አወሳሰንና የህገ መንግስት ትርጉም አስፈላጊነትን መወሰንን በተመለከተ የህጉን ማእቀፍ እንመልከት። የፋዳራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/1988 ከጥር 12/2013 ዓ.ም ጀምሮ በፀናው በፋዳራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 ተተክቷል። በሁለቱም አዋጆች እንደተመለከተው የፋዳራል ፍርድ ቤቶች ሕገ መንግስቱን መሰረት በማድረግ በሚነሱ ጉዲዮች ላይ ለመወሰን የዲኝነት ስልጣን አላቸው። (እንደ ቅደም ተከተላቸው የአዋጆቹን አንቀጽ 3(1) እና 3(1)(ሀ) ይመለከቷል።) በተለይም አዱሱ የፋዳራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 3(2) የፋዳራል ፍርድ ቤቶች በሚሰጡት የዲኝነት አገልግልት በህገ መንግስቱ አንቀጽ 9(2) መሰረት የህገ መንግስቱን ድንጋጌዎች ተግባራዊ ማድረግ እንደሚኖርባቸው ተመልክቷል። ስለሆነም የህገ መንግስት ትርጉምን በማይጠይቁ ህገ መንግስቱን መሰረት አድርገው የሚነሱ ክርክሮችን ተመልክተው ፍርድ ቤቶች ዲኝነት ሉሰጡ አይገባም የሚባልበት የህግ ምክንያት አይኖርም።
በልላም በኩል በፍርድ ቤት በተያዙ ጉዲዮች የህገ መንግስት ትርጉም ጥያቄ የተነሳ እንደሆነ ጥያቄው ጉዲዩን በያዘው ፍርድ ቤት አማካኝነት ለህገ መንግስት ጉዲዮች አጣሪ ጉባኤ ላቀርብ እንደሚችል የህገ መንግስት ጉዲዮች አጣሪ ጉባኤ አዋጅ ቁጥር 798/2005 አንቀጽ 3(2)(ሀ) እና አንቀጽ 4(1) ይደነግጋል። ነገር ግን ጉዲዩን የያዘው ፍርድ ቤት የትርጉም ጥያቄ ለአጣሪ ጉባኤው የሚልከው ጉዲዩን ለመወሰን ሕገ መንግስቱን መተርጎም ያስፈልጋል ብል ሲያምን ስለመሆኑ በአንቀጽ 4(2) ስር በግልጽ ተመልክቷል (….When it believes that the interpretation of the constitution is necessary to decide the case)። በመሆኑም ግልጽ የሆኑ የህገ መንግስት ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ በህገ መንግስት ክርክሮች ላይ ውሳኔ መስጠት እንዱሁም ትርጉም የማያሻቸው መሆኑን በፍርድ መወሰን የፍርድ ቤቶች ተግባር ላሆን እንደሚገባ ከፍ ሲል ከተጠቀሱት ህጎች ይዘት መገንዘብ ይቻላል።
ስለሆነም አመልካች የፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ይህን ጉዲይ ለማየት ስልጣን የለውም በማለት የምርጫ አዋጆችን እንዱሁም የህገ መንግስት ትርጉም አስፈላጊነትን በማንሳት ያቀረበው ክርክር ከፍ ሲል በዝርዝር ያመለከትነውን የህጉን ይዘት ያገናዘበ ባለመሆኑ ተቀባይነት የለውም ብለናል።
ፍሬ ጉዲዩን በተመለከተ አመልካች በክርክሩ የኢፋዱሪ ሕገ መንግስት አነስተኛ ቁጥር ላላቸው ብሓረሰቦች የሚያደርገው ጥበቃ ‘territorial’ በሆነ መርህ እንጂ በ‘non territorial’ ያለመሆኑን፤
የምርጫ ሕግ የማውጣቱ ስልጣን የፋዳራል መንግስትና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ብቻ መሆኑን፤ የክልለ መንግስት ያወጣው ሕገ መንግስት የፋዳራለን ህግ አውጪ የመንግስት አካል ስልጣን የሚጋፊና ያለስልጣኑ መሆኑ ታይቶ የይግባኝ ሰሚው ችልት ውሳኔ ተሽሮ ቦርደ የሰጠው (ያሳለፈው) ውሳኔ እንዱፀና ተከራክሯል። ከዚህ ክርክሩ ላላ ቦርደ በጉዲዩ ላይ ባሳለፈው ውሳኔም የኢትዮጵያ ሽግግር መንግስት ተወካዮች ምክር ቤት መጋቢት 6/1987 ባካሄደው 102ኛ መደበኛ ስብሰባ የሐረሪ ብሓራዊ ጉባኤ ከክልለ ውጭ ነዋሪ በሆኑ የብሓረሰቡ አባላት ይመረጣል በማለት ያሳለፈው ውሳኔ ህገ መንግስቱን መሰረት ያደረገ ባለመሆኑ ተፈጻሚነት ሉኖረው እንደማይገባ መወሰኑን፤ ላለፈት 5 ምርጫዎች ለሐረሪ ብሓራዊ ጉባኤ የሚመረጡ ተወካዮች ከክልለ ውጭ ባለ የብሓረሰቡ አባላት የብሓራዊ ምርጫ ቦርድ መመሪያ አውጥቶ ሲያስመርጥ ቆይቶ ቢሆንም ቦርደ ሲያከናውን በቆየው የምርጫ ማሻሻያ ወይም ሪፍርም እንደዚህ አይነት ልምድችና አሰራሮች እንዲይቀጥለ ማድረግን ዓላማው ያደረገ መሆኑን መወሰኑን፤ እንዱሁም በምክር ቤቱ ውሳኔ እና በክልለ ህገ መንግስት መሰረት ላለፈት 5 ምርጫዎች የሐረሪ ጉባኤ ከክልለ ውጭ ባለ የብሓረሰቡ አባላት ሲመረጥ ቆይቷል የሚለውን (practice) ይዞ ለመቀጠል ቦርደ ሉገደድ እንደማይገባ መወሰኑን የሚያሳይ ስለመሆኑ ተገንዝበናል። የዚህን ክርክርና ውሳኔ ተገቢነት ግራ ቀኙ ከሚያቀርቡት ሙግት፤ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውሳኔ እና የክልል ህገ መንግስታት ሉኖራቸው ከሚገባው የህገመንግስታዊነት ግምት፤ እንዱሁም ህገ መንግስታዊ አይደለምና ተግባራዊ ሉሆኑ አይገባም ተብል ሉወሰን የሚችልበትን የህግ ስርዓት ጋር መመርመር ይገባል።
እንደሚታወቀው የሐረሪ ክልል ከፍተኛ የህግ አውጪ አካል የሐረሪ ህዝብ ክልል ምክር ቤት ሲሆን ተጠሪነቱም ለወከለው ህዝብ መሆኑ በክልለ ሕገ መንግስት አንቀጽ 46(1) ተመልክቷል። ይህ የክልለ ምክር ቤት የህዝብ ተወካዮች ጉባኤ እና የሐረሪ ብሓራዊ ጉባኤ የሚባለ ሁለት ጉባኤዎች እንደሚኖሩት በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 49(1) ተመልክቷል። ይኸው አደረጃጀት የኢትዮጵያ ሽግግር መንግስት ተወካዮች ምክር ቤት መጋቢት 6/1987 ባካሄደው 102ኛ መደበኛ ስብሰባ ያሳለፈው ውሳኔ የክልለ ህገ መንግስት አካል ተደርጎ የተፈጠረ መሆኑንም መገንዘብ ይቻላል። የህዝብ ተወካዮች ጉባኤ አባላት ሐረሪዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ በክልለ ነዋሪዎች የሚመረጡ ሲሆን የሐረሪ ብሓራዊ ጉባኤ አባላት በሐረሪዎች ብቻ የሚመረጡ መሆኑን የሕገ መንግስቱ አንቀጽ 50 ያሳያል። በዚህ መልኩ የተዋቀረው የክልለ ምክር ቤት 36 አባላት ያለት ሲሆን 22ቱ የህዝብ ተወካዮች ጉባኤ አባላት እንዱሁም 14ቱ ደግሞ የሐረሪ ብሓራዊ ጉባኤ አባላት ናቸው። ከዚህም ላላ የሕዝብ ተወካዮች ጉባኤን እና የሐረሪ ብሓራዊ ጉባኤ ስልጣንና ተግባር በሕገ መንግስቱ ተዘርዝሯል። የሽግግር መንግስቱ የተወካዮች ምክር ቤት በ102ኛ ጉባኤው ካደረገው ውይይትና ከደረሰበት ውሳኔ እንዱሁም በክልለ ሕገ መንግስት አንቀጽ 59 ከተደነገገው መገንዘብ እንደሚቻለው የሐረሪ ብሓራዊ ጉባኤ ቀዲሚ ስልጣንና ተግባር የሐረሪዎችን እንደ ብሓረሰብ የመቀጠል ሁኔታ ማረጋገጥ የሚያስችለ የቋንቋ፣ ባህል፣ ቅርስ እና የማንነት ጥበቃ ጋር የተያያዘ ነው። ከክልለ ውጭ የሚኖሩ ሐረሪዎች በሐረሪ ብሓራዊ ጉባኤ 14 አባላት ምርጫ ውስጥ ብቻ እንዱሳተፈ የመወሰኑ መሰረታዊ ምክንያትም ከክልለ ውጭ የሚኖሩ ሐረሪዎች ከክልላቸው እና ብሓራዊ ማንነታቸው ጋር ያላቸውን ቁርኝት ለማጥበቅና ለማረጋገጥ እንዱያስችላቸው እንዱሁም ለሐረሪ ብሓራዊ ጉባኤ የተሰጠውን ህጋዊ ኃላፉነት ዲር ለማድረስ ስለመሆኑም መገንዘብ ይቻላል።
ከፍ ሲል በተጠቀሰው መልኩ በሽግግር መንግስቱ የተወካዮች ምክር ቤት በ102ኛ ጉባኤው የተደረሰበት ውሳኔ ህገ መንግስቱ ስራ ላይ ከዋለ በኋላም ተፈጻሚነት የሚኖረውና የህገ መንግስቱን መርሆች መሰረት በማድረግ መወሰኑን ምክር ቤቱ ከያዘው ቃለ ጉባኤ መገንዘብ ችለናል። ለዚህም ነው የፋዳራለን ህገ መንግስት ተከትል በወጣው የክልለ ህገ መንግስት ይኸው የተመለከተው። የኢፋዱሪ ህገ መንግስት በአፅዲቂ ጉባኤው ህዲር 29/1987 ዓ.ም ተቀባይነት አግኝቶ ከፀደቀ በኋላ የተሰጠው ይኸው የተወካዮች ምክር ቤት ውሳኔና በክልለ ሕገ መንግስት ግልጽ ድንጋጌዎች የተካተቱት መርሆች የፋዳራለ ህገ መንግስት መሰረታዊ መርሆዎችን መሰረት ያደረጉ ናቸው። የፋዳራለ ህገመንግስት አንቀፅ 5(1)፣3፣39 (2)፣ 91(1) እና (2) ብሓር ብሓረሰቦችና ህዝቦች ማንነታቸው ተጠብቆ መቀጠል የሚችለበትን ሁኔታ ማረጋገጥ ለሚያስችለ የቋንቋ፣ ባህል፣ ቅርስ እና የማንነት ጥበቃ ያደርጋል። በተለይ በሕዝብ ቁጥር አነስተኛነት ምክንያት ማንነታቸው የሚገለፅበት የቋንቋ፣ ባህልና ቅርስ እንዲይጠፊ የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት ጥበቃ የሚያደርግ መሆኑን መገንዘብ ይገባል። ሀገሪቱ የተቀበለቻቸው አለማቀፍ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ስምምነት እንዱሁም የማህበራዊ፣ ባህላዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶች ስምምነት ቀዲሚ(የመጀመሪያ) ድንጋጌዎች ይህን የሚቀበለ ናቸው። በተለይ የአለም አቀፍ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ስምምነት አንቀጽ 1 እና 27 እንዱሁም በተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ በብሓር፣ በጎሳ፣ በሐይማኖት ወይም በቋንቋ አናሳ የሆኑ ቡድኖች አባላትን መብቶች አጠባበቅ አስመልክቶ በውሳኔ ቁጥር 47/135 ዱሴምበር 18/1992 ዓ.ም ያሳለፈው ውሳኔ እንዱሁም በዳሞክራሲና ዕድገት የበለፀጉ ሃገራት ያላቸው የዲበረ ልምድ የሚያሳየው ለእነዚህ መብቶች ጥበቃ ላደረግላቸው እንደሚገባ ነው። የሐረሪ ብሓረሰብ የዚህ ጥበቃ ተጠቃሚ የሆነ ሲሆን ላልች አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ብሓረሰቦችም በተመሳሳይ የማንነታቸው መግለጫ የሆኑ የቋንቋ፣ ባህልና ቅርስ ጥበቃ እንዱኖራቸው ማድረግ ህገ መንግስታዊ ነው። የሐረሪ ክልል ምክር ቤት በህግ በልዩ ሁኔታ እንዱዋቀር መደረጉና የሐረሪ ብሓራዊ ጉባኤን ማቋቋም እንዱሁም በልዩ ሁኔታ አባላቱ እንደሚመረጡ መደረጉ ሁለ ይህን ጥበቃ ተግባራዊ ለማድረግ ነው።
ቦርደ በጉዲዩ ላይ ከሰጠው ውሳኔ እና እስከዚህ ፍርድ ቤት ካቀረበው ክርክር የኢትዮጵያ ሽግግር መንግስት ተወካዮች ምክር ቤት በ06/07/1987 ባደረገው 102ኛ መደበኛ ስብሰባ ያስተላለፈው ውሳኔ እና የክልለ ህገመንግስት ድንጋጌዎች የተጠሪን ክርክር የሚደግፈ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሓራዊ ምርጫ ቦርደ መገንዘቡን ተረድተናል። ነገር ግን ከፍ ሲል እንደተገለፀው የምክር ቤቱ ውሳኔ ህገ መንግስቱን መሰረት ያደረገ ባለመሆኑ ተፈጻሚነት ሉኖረው አይገባም፤ ላለፈት 5 ምርጫዎች ለሐረሪ ብሓራዊ ጉባኤ የሚመረጡ ተወካዮች ከክልለ ውጭ ባለ የብሓረሰቡ አባላት ሲያስመርጥ የቆየ ቢሆንም እንደዚህ አይነት ልምድችና አሰራሮች እንዲይቀጥለ ማድረግ ያስፈልጋል፤ መሰል ልምድችን (practice) ይዞ ለመቀጠል ቦርደ አይገደድም በማለት ወስኗል።
ይኸው ውሳኔ ከህገ መንግስት ትርጉም ስርዓት ጋር ተያይዞ እንደሚከተለው ሉመረመር የሚገባ ነው።
ከህገ መንግስት ትርጉም ጋር በተያያዘም የፋዳሬሽን ምክር ቤትን ለማጠናከር እና ሥልጣንና ተግባሩን ለመዘርዘር በወጣው አዋጅ ቁጥር 251/1993 አንቀጽ 9 ስር በግልጽ እንደተመለከተው የአንድ ህግ ህገ መንግስታዊነት ተጣርቶ ግምቱን የሚያፈርስ ላላ ሁኔታ እስካልተፈጠረ ድረስ የወጣው ህግ ህገ መንግስታዊ ነው ተብል እንደሚገመት ይደነግጋል። የህጉን ህገመንግስታዊነት አጣርቶ ትርጉም ለመስጠት ሥልጣን የተሰጠው ደግሞ ምክር ቤቱ ስለመሆኑ በአዋጁ አንቀጽ 4(1) እና በፋዳራለ ህገ መንግስት አንቀጽ 62(1) ሥር ተደንግጓል። ስለሆነም በእጃችን ባለው ጉዲይ የብሓራዊ ምርጫ ቦርድ የኢትዮጵያ ሽግግር መንግስት ተወካዮች ምክር ቤት መጋቢት 6/1987 ባካሄደው 102ኛ መደበኛ ስብሰባ የሐረሪ ብሓራዊ ጉባኤ ከክልለ ውጭ ነዋሪ በሆኑ የብሓረሰቡ አባላት ይመረጣል በሚል ያሳለፈው ውሳኔ እንዱሁም የክልለ ህገ መንግስት ተያያዥ ድንጋጌዎች የፋዳራለን ህገ መንግስት መሰረት ያደረጉ አይደለም፤ ህገ መንግስታዊ ድጋፍም የላቸውም፤ እንዱህ አይነት አሰራር እንዲይቀጥል አደርጋለሁ በማለት በራሱ ውሳኔ ማሳለፈ ከፍ ሲል የተጠቀሱትን የህጉን ድንጋጌዎች መሰረት ያደረገ ባለመሆኑ ተቀባይነት የለውም። የምክር ቤቱ ውሳኔና የክልለ ህገ መንግስት ድንጋጌ ህገ መንግስታዊ አለመሆኑ ሥልጣን ባለው አካል ተጣርቶ ውሳኔ እስካልተሰጠበት ድረስ ህገ መንግስታዊ ነው ተብል ይገመታል።
ስለሆነም የአሁን አመልካች የኢትዮጵያ ሽግግር መንግስት ተወካዮች ምክር ቤት ውሳኔ እና የክልለ ሕገ መንግስት እንዱሁም እነዚህን ሰነድች መሰረት በማድረግ የሚከናወን የምርጫ ሂደት ሕገ መንግስታዊ አይደለም የሚል ከሆነ ይህንን ማስለወጥ የሚገባው ጉዲዩን ለሚመለከተው አካል አቅርቦ በሚያሰጠው ውሳኔ መሰረት ከሚሆን በቀር በራሱ በሚሰጠው ውሳኔ ላሆን ስለማይገባ ቦርደ የሰጠው ውሳኔ ጉድለት ያለበትና ሉታረም የሚገባው ነው ተብል በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ በአግባቡ ነው። ውሳኔው ህጉን መሰረት ያደረገ ነው ከሚባል በቀር የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው የሚያሰኝ ሆኖ አላገኘነውም።
በአጠቃላይ የሐረሪ ብሓራዊ ጉባኤ 14 የሐረሪ ብሓረሰብ አባላት እንደሚኖሩት እና አባላቱ በክልለ ውስጥና ከክልለ ውጪ በላልች የኢትዮጵያ ክልልች እና ከተሞች ከሚኖሩ የሐረሪ ብሓረሰብ አባላት የሚመረጡ ስለመሆኑ በክልለ ሕገ መንግስት አንቀጽ 49(3) እና 50(2) የተደነገገ በመሆኑ፤ ይኸው አሰራር በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውሳኔ የተደገፈ በመሆኑ፤
የክልለ ህገ መንግስትም ሆነ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውሳኔ ተግባራዊ መደረግና ሕገ መንግስታዊነት አስመልክቶ ህገ መንግስቱን ለመተርጎም ስልጣን ባለው አካል ፉት የቀረበ ተቃውሞ ባለመኖሩ፤ ከብሓሩ አባላት ቁጥር አናሳነት እና ላደረግለት ከሚገባው ጥበቃ አንፃር ታይቶ ከክልለ ውጪ የሚኖሩ የሐረሪ ብሓረሰብ አባላት የሐረሪ ብሓራዊ ጉባኤን እንዱመርጡ መደረጉ ፀንቶ የኖረ ህጋዊ አሰራር በመሆኑ የኢትዮጵያ ብሓራዊ ምርጫ ቦርድ የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ውሳኔ መስጠቱ ህጋዊ አይደለም ብለናል። ይኸው ውሳኔ በይግባኝ ሰሚው ችልት መታረሙም በአግባቡ ነው ብለናል። ተከታዩም ተወስኗል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ በቀን 19/08/2013 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ባለመሆኑ የአመልካች የሰበር ማመልከቻ ተቀባይነት የለውም በማለት ውሳኔው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348(1) መሰረት አጽንተናል።
ከሐረሪ ክልል ውጪ በላልች ክልልች እና ከተማ አስተዲደሮች ለሚኖሩ የሐረሪ ብሓረሰብ ተወላጆች ከክልለ ምክር ቤት ሁለት ጉባኤዎች መካከል አንደ ለሆነው እና የሐረሪ ብሓረሰብ አባላት ለሚካተቱበት የሐረሪ ብሓራዊ ጉባኤ አባላትን የመምረጥ መብት አስቀድሞ በህግ በተዘረጋው ስርዓት መሰረት ተግባራዊ እንዱደረግ ከክልለ የመንግስት አካላት የቀረበለትን ጥያቄ የኢትዮጵያ ብሓራዊ ምርጫ ቦርደ ውድቅ በማድረግ ያሳለፈው ውሳኔ በይግባኝ ሰሚው ችልት መሻሩ በአግባቡ ነው ብለናል።
በክልለ ሕገ መንግስት በተደነገገው እና የኢትዮጵያ የሽግግር መንግስት ተወካዮች ምክር ቤት መጋቢት 6/1987 ዓ.ም ባደረገው 102ኛ መደበኛ ጉባኤ ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሉፈጽም ይገባል በማለት ወስነናል። በዚሁ መሰረት ቦርደ ተገቢውን ይፈፅም።
የሰበር አጣሪ ችልቱ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ እንዲይፈፀም ታግድ እንዱቆይ በዚህ መዝገብ ግንቦት 4 ቀን 2013 ዓ.ም ያሳለፈው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል።
ይጻፍ።
የውሳኔው ግልባጭ ምርጫውን ለሚያስፈፅመው የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ እንዱሁም ከስር ጀምሮ አቤቱታ ላቀረቡ አካላት ሁለ ይተላለፍ።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ይቻቻለ።
ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የኢትዮጵያ ሽግግር መንግስት የተወካዮች ምክር ቤት 102ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ በመጣበት መልኩ ለምክር ቤቱ ይመለስ።
ውሳኔው ዛሬ ግንቦት 19 ቀን 2013 ዓ.ም በችልት ተነቧል።
No topics extracted.