ብርብራ የሚደረግበት የህግ ስርዓት ዝርዝር ሁኔታዎች የተመላከቱ ቢሆንም በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ.32(2) የተመለከቱት ቀሪ ሁኔታዎች (Exceptions) በላለበት ብርበራ ያለ ብርበራ ትዕዛዝ ቢከናወን ወይም በብርበራ ትዕዛዙ ከተመለከተው ጊዜና ቦታ ውጪ ብርበራ ቢደረግ አልያም በብርበራ ትዕዛዙ ላይ ከተመለከተው እቃ ውጪ በሆነ ሁኔታ ፖሉስ በብርበራ የመያዙ አግባብነት ተጨማሪ የብርበራ ትዕዛዝ ለማግኘት በቂ እና ምክንያታዊ ጊዜ ነበር የሚለው የብርበራውን ህጋዊነት ለመመዘን ከግምት ውስጥ ሉገባ የሚገባ መሰረታዊ መስፈርት ተደርጎ የሚወሰድ እነ መንሱር ጁሃር (2 ሰዎች) እና የፍደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ህገ መንግስታዊ ጥበቃ ከተሰጠው የግል ህይወት የመከበርና የመጠበቅ መብት አንፃር በፍርድ ቤት በብርበራ ትዕዛዝ ላይ ከተመለከተው ውጪ በሆነ ሁኔታ ፖሉስ የመያዙ አግባብነትን በተመለከተ ቅድሚያ ሉከበር የሚገባ የግል ህይወት የመከበርና የመጠበቅ መብት ያለ መሆኑ የሚታይና የሚመዘን ስለመሆኑ የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 26 (1)፣ የወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ.32(2)(ለ) እና 33 (1) የምርጫ ጉዲዮች 521
No summary available.
መጋቢት 08 ቀን 2014 ዓ.ም ዳኞች፡ እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሣዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካቾች፡- 1ኛ መንሱር ጁሃር መሀመድ 2ኛ ፈአድ ጁሃር መሀመድ ተጠሪ፡- የፍደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን በዚሁ አግባብ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ለዚህ የሰበር ክርክር መነሻው አመልካቾች ሐምል 19 ቀን 2013 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ የፍደራል መጀመሪያ ደረጀ ፍርድ ቤት የሰጠው የጥፊተኝነት ፍርድ እና የቅጣት ውሳኔ እንዱሁም የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት ስለሆነ ይኸው ይታረምልን በማለት ስለጠየቁ ነው።
የነገሩ አመጣጥ የኮንትሮባንድ ወንጀል ጉዲይ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ጉዲዩ የተጀመረው በፋደራል መጀመሪያ ደረጀ ፍርድ ቤት ነው።
የአሁን ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት በአመልካቾች ላይ ባቀረበው ክስ የአሁን አመልካቾች የምግብና መድሀኒት አስተዲደር አዋጅ ቁጥር 1112/2011 አንቀጽ 46 እና የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 በአዋጅ ቁጥር 1160/2011 እንደተሻሻለው/አንቀጽ 168/2/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ የአሁን አመልካቾች ስልጣን ባለው አካል ፈቃድ ካልሆነ በስተቀር ወደ ሀገር እንዲይገባ ገደብ የተደረገበት ዕቃ መሆኑ እያወቁ ወይም ማወቅ ሲገባቸው በቀን 19/01/2013 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 10፡30 ሰዓት ላይ በሚሆንበት ጊዜ በአዱስ አበባ ከተማ አሰተዲደር አራዲ ክ/ከተማ ወረዲ 02 ልዪ ቦታው በግ ተራ ተብል በሚጠራው አካባቢ የቤት ቁጥር 668 በሆነ መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ በተደረገው ፍተሻ በአጠቃላይ ታክስና ቀረጥ መጠናቸው ብር 76,982.92 የሆነ ብዛቱ በቁጥር 80 ስቴክ ሻምላ የተባለ የስሪት ሀገሩ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና 79 ስቴክ ብለስ የተባለ የስሪት ሀገሩ እንግሉዝ የሆነ ሲጋራዎችን በካርቶን አሰቀምጠው የተገኙ በመሆናቸው የኮንትሮባንድ ወንጀል ፈጽመዋል በማለት ከሷል።
አመልካቾች ክሱ ደርሷቸው በችልት ተነቦላቸው እንዱረደት ከተደረገ በኋላ የወንጀል ድርጊቱን አልፈጸምንም ጥፊተኛ አይደለንም በማለት የተከራከሩ በመሆኑ ሁለት የአቃቤ ህግ ምስክሮች ቀርበው እንዱሰሙ ተደርጓል።የአቃቤ ሕግ 1ኛ ምስክርም በህብረተሰቡ ጥቆማ መሰረት በቀን 19/01/2013 ዓ.ም ከቀኑ 10፡30 ሰዓት አካባቢ በብርበራ ትዕዛዝ እና ታዛቢዎች ባለበት የአሁን አመልካቾች ቤት እንደተበረበረ እና የተለያዪ የውጭ ሀገር ብሮች እና ሲጋራዎች መገኘታቸውን፣ የተገኙት ሲጋራዎች የስሪት ሀገራቸው ኢንግላድ እና የአረብ ኤምሬትስ እንደነበር በሰዓቱ ደረሰኝ ተጠይቀው እንዲልነበራቸው፤ የአሁን 2ኛ አመልካች ዕቃው የእኛ ነው ብል እንዲላቸው ከዛም ዕቃዎቹን እና አመልካቾችን በመኪና ይዘናቸው ወደ አዱስ ከተማ ክ/ከተማ ወስደናቸዋል በማለት መስክሯል:: 2ኛ የዐቃቤ ሕግ ምስክር በሰጡት የምስክርነት ቃልም በተሰጠን ጥቆማ መሰረት በቀን 19/01/2013 ዓ.ም ከቀኑ 10፡30 ሰዓት አካባቢ አራዲ ክ/ከተማ ወረዲ 02 የቤት ቁጥር 668 የሆነ አመልካቾች የሚያከራዪት አልጋ ቤት ውስጥ የብርበራ ትዕዛዝ ወጥቶ እንደተበረበረ እና በክሱ ላይ የተገለፁትን የውጭ ሲጋራዎች አግኝተናል የአሁን 2ኛ አመልካች ለ1ኛ አመልካች ደውልለት መጣ፣ ደረሰኝ እናመጣለን ብለው የነበረ ቢሆንም አላመጡም በማለት መስክራለች።ዐቃቤ ሕግ የሰነድ ማስረጃዎችንም ከክሱ ጋር አያይዞ አቅርቧል።
በዚሁ መሰረት ቀርበው የተሰሙት የአቃቤ ሕግ ምስክሮች የአሁን አመልካቾች የወንጀል ድርጊቱን መፈፀማቸውን ስላስረደ የአሁን አመልካቾች ዐቃቤ ሕግ ክስ በመሰረተበት ድንጋጌዎች ስር በወ/መ/ስ/ስ/ሕ/ቁ.142 መሰረት እንዱከለከለ በማለት ብይን ሰጥቷል የአሁን አመልካቾች ሶስት የመከላከያ ምስክሮችን አሰምተዋል።1ኛ የመ/ምስክር የወንጀል ድርጊቱ ተፈፀመ በተባለ ቀን 10፡00 ሰዓት አካባቢ እዝያው ቤት ውስጥ እንደነበሩ በዛን ሰዓት ሰፈሩ በፖሉሶች ተከቦ እየተፈተሸ እንደነበር እና የአሁን አመልካቾች አልጋ ቤት ድላር ይመነዘራል ብለው እንደመጡ የአሁን አመልካቾች የለም ይመጣለ እንዲሎቸው፤ቤት ውስጥ ትንሽ ካዝና እንዲገኙ እና ቁልፍ ሲጠይቋቸው ቁልፍ የለም ሲለ ሰብረው እንደከፈቱት እና ውስጡ ምንም እንዲልነበር፣ከዛም በመቀጠል የተከራዮችን ቤት እንደፈተሹ እና ከአንደኛው ቤት ውስጥ ሶስት ካርቶን ሲጋራ ይዘው እንደወጡ፣ ከዛም የአሁን 2ኛ አመልካች እንደመጣ እና ደረሰኝ አለህ ወይ ብለው ሲጠይቁት ቆይ ለወንድሜ ልደውል ብል ለአሁን 1ኛ አመልካች እንደደወለለት እና እሱ እስኪመጣ ድረስ ብለው ዕቃውን እና የአሁን 2ኛ አመልካችን ይዘው መሄዲቸውን፤ የተገኘው ሲጋራ ቤት ሰው የሙስሉም ኮፍያ እና ሽርጥ የለበሰ ሰውዬ እንደነበር እና ሰላም ብልት እንደሄደ መስክሯል።2ኛ መ/ምስክር መስከረም 19/2013 ዓ.ም ቁጭ ብዬ ጫት እየቃሙ እያለ ሰፈሩ ውስጥ የጦር መሳሪያ ፍተሻ እንደነበር እና ከዚያም ወደ አሁን አመልካቾች አልጋ ቤት እንደገቡ እና ፍተሻ እንደጀመሩ ከዛም የተቆለፈ ካዝና እንዲገኙ እና ቁልፍ ብለው ሲጠይቁ የለም ጠፍቷል ሲባለ እንደተሰበረ ፣ የተከራዮች ቤት እየተፈተሸ እንደነበር እና አንደኛው ቤት ቁልፈ ተሰብሮ በሚፈተሽበት ወቅት ሁለት ካርቶን የተበታተነ ሲጋራ እንደተገኘ፣ ሲጋራው የተገኘው ቤት ሰውዬ ሰላም ብሎቸው እንደወጣ፣ የአሁን 2ኛ አመልካች እንደመጣ እና ለ1ኛ አመልካች እንደደወለለት እና ሲመጣ ፖሉሶች ይዘዋቸው እንደሄደ መስክሯል።
3ኛ መ/ምስክር በበኩላቸው ወንጀለ ተፈፀመ በተባለ ቀን ከአሁን 2ኛ አመልካች ጋር ማኪያቶ ጠጥተው እየተመለሱ እንደነበር እና ቤቱም እየተፈተሸ እንደነበር፣ አልጋ ቤቱ የእናታቸው እንደሆነ እና ፖሉሶቹ ካዝናውን እየሰበሩ እንደነበር እና ቤቶቹን እየፈተሹ እንደነበር፣ ከዛም ሲጋራው እንደተገኘ እና የአሁን 2ኛ አመልካች ለ1ኛ አመልካች እንደደወለለት እና የተከራየው ሰውዬ ደረሰኝ አለው ወይ ብል እንደጠየቀው እና አላየሁም እንዲለው፣ አልጋ የተከራየውንም ሰውዬ እየዞሩ እንደፈለጉት እና እንዲላገኙት እና አመልካቾችን ፖሉሶች ይዘዋቸው እንደሄደ መስክሯል።
የፍደራል መጀመሪያ ደረጀ ፍርድ ቤት ይህንን ተከትል በሰጠው ውሳኔም በክሱ ላይ የተመለከተው የውጪ ሀገር ሲጋራ ከህብረተሰቡ በደረሳቸው ጥቆማ መሰረት ፍተሻ ተደርጎ እንደተገኘ 2ኛ አመልካችም እቃው የኛ ነው እንዲላቸው እና 1ኛ አመልካች ደረሰኝ አመጣለሁ ያለ ቢሆንም አለማምጣቱን አቃቤ ህግ በምስክሮቹ ማስረዲቱን አመልካቾች በምስክሮቻቸው ቤቱን ላላ ግለሰብ መከራየቱን በክርክራቸው አግባብ ያላስረደ መሆኑን፤ቤቱን ላላ ሰው ለመከራየቱ መታወቂያና ላላ አግባብነት ያለው ማስረጃ አለመቅረቡን፤የመከላከያ ምስክሮቹ አመልካቾች እቃው የኛ ነው ብለው በገለፁበት ምስክሮቹ የላላ ሰው ነው ማለታቸው የሚያሳምን አለመሆኑን በመጥቀስ አመልካቾችን በቀረበባቸው ክስ ጥፊተኛ በማለት አመልካቾችን ያርማል ላላውንም ያስጠነቅቃል ባለው በአንድ ዓመት ከስምንት ወር ፅኑ እስራት እና ብር 15,000.00/አስራ አምስት ሺህ/ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዱቀጡ ወስኗል።ይህ ውሳኔ ጉዲዩን በይግባኝ በተመለከተው የፋ/ከ/ፍርድ ቤት ፀንቷል።
አመልካቾች ባቀረቡት የሰበር አቤቱታም የወ/መ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 32 መግቢያ የብርበራ ስራ ስለሚከናወንበት ሂደት ይደነግጋል።በዚሁ መሰረት ማንኛውም መርማሪ ፖሉስ ወይም የፖሉስ ሰራዊት ባልደረባ በፍርድ ቤት በተሰጠ የብርበራ ማዘዣ መሰረት ካልሆነ በቀር ቤትን መበርበር እንደማይቻል በግልጽ ይደነግጋል።ይህንን ተከትል አንቀጽ 32(2) በፍርድ ቤት የሚሰጥ የብርበራ ትዕዛዝ የሚበረበረውን ቦታና የሚያዘውን ዕቃ ማመልከት እንዲለበት ይደነግጋል።ከዚህም ባለፈ ብርበራው የሚያከናውነው የፖሉስ ባልደረባ በመያዣው ትዕዛዝ ከተመለከተው ዕቃ ውጭ መያዝ እንደማይችል በግልጽ ይደነግጋል።ምንም እንኳን አመልካቾች የብርበራውን ትዕዛዝ ይዘት ብርበራው በተከናወነበት ወቅት በውል ባንረዲውም የተከበረው ፍ/ቤት ከመዝገቡ እንደሚረዲው በክሱም ሆነ በፍርደ በግልጽ እንደተመለከተው ፖሉስ ከፍርድ ቤት ያወጣው የብርበራ ትዕዛዝ የቤት ቁጥር 668 ን የሚመለከት ነው።በዚህም ቤት ውስጥ እንዱያዝ ትዕዛዝ የተሰጠበት ዕቃ የጦር መሳሪያ እና የውጭ አገር ገንዘብ ነው።
በብርበራ ትዕዛዙ የተጠቀሰው ቤትም ሆነ እንዱያዝ ትዕዛዝ የተሰጠበት ዕቃ ከአመልካቾች ምንም ግንኙነት ያለው አይደለም፤ በፍርድ ቤትም አልተረጋገጠም፤ይልቁንም በዐቃቤ ሕግ 2ኛ ምስክርና በአመልካቾች መ/ምስክር እንደተመሰከረው ዕቃዎቹ የተያዙት የተቆለፈ ክፍል ቤት በሩ ተሰብሮ ነው።ይህ የተሰበረው ቤት ደግሞ እናታችን የሚያከራዪት ቤት ስለመሆኑ የተመሰከረ ሲሆን ይህ ቤት በዐቃቤ ሕግ ክስ እንደተመለከተው የአመልካቾች መኖሪያ ቤት አይደለም።ይህ በብርበራ ትዕዛዝ የተመለከተው የቤት ቁጥር 668 ተበርብሮ እንዲበቃ እንዱሁ መደዲውን ያለት ቤቶች ናቸው የተበረበሩት።በዚህም ሂደት የእናታችን ቤት የቤት ቁጥር 664(ለ) ሲሆን ብርበራውም የተከናወነው መጨረሻ ላይ ነው። ሲጋራዎቹም የተያዙት በቤት ቁጥር 668 ሳይሆን በዚህ ቤት ቁጥር 664(ለ) ውስጥ ሲሆን ብርበራው የተከናወነው በፍርድ ቤት ከተፈቀደው ቦታ ውጭ መሆኑ ግልጽ ነው።
ከዚህ ባለፈ ፍርድ ቤት ሰጠ የተባለው የብርበራ ትዕዛዝ የውጭ ምንዛሪን እና የጦር መሳሪያ ፍለጋ ነው።በብርበራው የተያዘው ግን በብርበራ ትዕዛዙ እንዱያዝ ፈቃድ ከተሰጠበት የጦር መሳሪያ እና የውጭ ምንዛሪ ውጭ ሲጋራ ነው።ስለዚህ የተከበረው ፍርድ ቤት ፖሉስ በፍርድ ቤት ከተሰጠው ስልጣን በማለፍ ባልተፈቀደበት የቤት ቁጥር ቤቱን ሰብሮ በመግባት እንዱያዝ ከተፈቀደው ውጭ ያለን ዕቃ ነው የያዘው።በሕግ ከተሰጠው ስልጣን ውጭ የሚከናውን የባለስልጣን ተግባር ደግሞ እንዲልተከናወነ የሚቆጠር እና የሕግ ውጤት የማይሰጠው መሆኑ እየታወቀ አፈፃፀሙ የሕግ ስሕተት የለበትም መባለ ሉታረም የሚገባው መሰረታዊ የሕግ ስሕተት ነው።ስለሆነም ፖሉስ ብርበራ ያከናወነው በብርበራ ትዕዛዝ ከተጠቀሰው የቤት ቁጥር 668 ላላ በቤት ቁጥር 664(ለ) በመሆኑ ያለስልጣኑ ነው የሰራው እንዱባልልን፤
አመልካቾች የዐቃቤ ሕግን ምስክሮች ቃል በተገቢው ሁኔታ ያስተባበልን ሆኖ ሳለና የስር ፍርድ ቤት ጥፊተኛ ያለን የማስረጃ ምዘናን መርህ በመጣስ ሆኖ ሳለ በማስረጃ ምዘና ረገድ የተፈፀመ ስሕተት የለም መባለ ሉታረም የሚገባው መሰረታዊ የሕግ ስሕተት ነው፤ የአመልካቾች የእስራት ቅጣት ላለመገደብ በቂ ምክንያት ስለላለው ሉገደብ የሚገባው ሆኖ እያለ አመልካቾች የእድሜያችን ለጋነት፤አዛውንትና በሽተኛ ወላጆቻችንን የምንረዲ እና የምንደግፍ መሆናችን ከግምት ውስጥ ገብቶ ቅጣቱ ሉገደብ ሲገባ መታለፈ አግባብ አይደለም፤ ብርበራው የተደረገው የቤት ቁጥር 664(ለ) በሆነው የእናታችን ቤት ላይ መሆኑን ለማስረዲት በተጨማሪ ማስረጃነት ያቀረብነውን የንግድ ፈቃድ እና የኪራይ ውል ይቀበለን ጥያቄ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ውድቅ ማድረጉ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው፤ስለሆነም ክሱን በአግባቡ ተከላክለዋል ተብል ከክሱ በነፃ እንድንሰናበት ይወሰንልን፤ይህ የሚታለፍ ቢሆን የአመልካቾችን የእስራት ገደብ ጥያቄ ውድቅ ለማድረግ በቂ ምክንያት ባለመኖሩ የእስራት ቅጣቱ እንዱገደብልን በማለት አመልክተዋል።
ለክርክሩ ምክንያት የሆነው የኮንትሮባንድ ዕቃ የተያዘው አመልካቾች ባከራዪት አልቤርጎ ክፍል ውስጥ ስለመሆኑ አመልካቾች በስር ፍርድ ቤት ባስረደበት ሁኔታ በአዋጅ ቁጥር 859/2006 እንደተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 1160/2011 አንቀጽ 168/2/ ስር ጥፊተኛ የተባለበትን አግባብነት ከወንጀል ሕግ አንቀጽ 23/2/ ጋር በማገናዘብ ለመመርመር የሰበር አቤቱታው ለሰበር ችልት ያስቀርባል ከተባለ በኋላ ተጠሪ 25/02/2014 ዓ.ም በተፃፈ በሰጠው መልስ ሲጋራው የተገኘበት ቤት የአመልካቾች በመሆኑ እና ቤቱ ለላላ ሰው የተከራየ ስለመሆኑ ያልተረጋገጠ በመሆኑ አመልካቾች በቀረበባቸው ወንጀል ጥፊተኞች ናቸው በሚል እንዱቀጡ በስር ፍርድ ቤቶች የተወሰነው ውሳኔ የሕግም ሆነ የማስረጃ ምዘና ስሕተት ያልተፈፀመበት ስለሆነ አመልካቾች ያቀረቡት አቤቱታ ውድቅ እንዱደረግልን በማለት ተከራክሯል።
አመልካቾችም የመልስ መልስ በማቅረብ የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል።
የነገሩ አመጣጥና የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ እንደተመለከተው ሲሆን እኛም ጉዲዩን አጣሪው በማሰቀረቢያነት ከያዘው ጭብጥ አንጻር መርምረናል።ማንኛውም ሰው የግል ህይወቱ፤ግላዊነቱ የመከበር መብት ያለው መሆኑ፤ይህ መብቱም መኖሪያ ቤቱ፤ሰውነቱና ንብረቱ ከመመርመር እንዱሁም በግል ይዞታው ያለ ንብረት ከመያዝ የመጠበቅ መብትን አንደሚያካትት በኢፋዱሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 26(1) የተመለከተ ሲሆን ይህ መብት ያለ ገደብ የተሰጠ ሳይሆን በተወሰኑ በህጉ በተመለከቱት ሁኔታዎች ሉገደብ እንደሚችል በአንቀፅ 26(3) የተመለከተ ሲሆን በዚህ አግባብም አስገዲጅ ሁኔታዎች ሲፈጠሩና ብሄራዊ ደህንነትን፤የህዝብን ሰላም፤ወንጀልን በመከላከል፤ጤናንና የህዝብ የሞራል ሁኔታ በመጠበቅ ወይም የላልችን መብትና ነፃነት በማስከበር አላማዎች ላይ በተመሰረቱ ዝርዝር ህጎች መሰረት የመብቱ አጠቃቀም ሉገደብ እንደሚችል ይደነግጋል።
በዚህ አግባብ ሉመረመርና ተገቢው የህግ ትርጉም ሉሰጣቸው የሚገባው የወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ.32 እና 33 ድንጋጌዎች አንድ መርማሪ ፖሉስ ወይም የፖሉስ ሰራዊት ባልደረባ የወንጀል ድርጊት ተፈፅሟል ብል ሲያምንና ከወንጀል ምርምራው ሂደት ጋር በተያያዘ ማስረጃዎችን ለማሰባሰብ እንዱረዲው ብርበራ በማድረግ ማስረጃዎቸን መሰብሰብ አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው በመርህ ደረጃ በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ.33(1) የብርበራ ማዘዣ ከማንኛውም ፍርድ ቤት ሉያገኝ እንደሚችል የተደነገገ ሲሆን ለፍትህ አላማ እንዱረዲ ምርመራውን ለማገዝ እንዱችል ይህ ሲከወንም የተጠርጣሪውን ግለሰባዊ መብት ባከበረ መልኩ መፈፀሙ አስፈላጊ መሆኑ በፍርድ ቤቱ ታምኖበት የተሰጠው የብርበራ ማዘዣ የሚበረበረውንና የሚያዘውን እቃ በግልፅ ማመልከት ያለበት መሆኑን፤በብርበራ ትዕዛዙ ላይ ከተመለከተው እቃ ውጪ ፖሉስ ሉይዝ የማይችል መሆኑን አንቀፅ 33(2) የሚደነግግ ሲሆን፤ብርበራው የሚደረግበትን ሰአት አስመልክቶም በተለየ ሁኔታ ካልታዘዘ በስተቀር ብርበራው የሚደረገው ከጠዋቱ አስራ ሁለት ሰአት ጀምሮ እስከ ማታው አስራ ሁለት ሰአት ድረስ ብቻ መሆኑን በአንቀፅ 33(5) የተመለከተ መሆኑን መነሻ በማድረግ የተዘጋጀው በህጉ የተመለከተው ፍርም የብርበራው ቀንና ሰአት በግልፅ መመልከት ያለበት መሆኑን ያሳያል።
ከላይ የተመለከቱት ዝርዝር ሁኔታዎች ብርብራ የሚደረግበትን የህግ ስርዓት በዝርዝር የሚያመለክቱ ቢሆኑም በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ.32(2) የተመለከቱት ቀሪ ሁኔታዎች (Exceptions) በላለበት ብርበራ ያለ ብርበራ ትዕዛዝ ቢከናወን ወይም በብርበራ ትዕዛዙ ከተመለከተው ጊዜና ቦታ ውጪ ብርበራ ቢደረግ አልያም በብርበራ ትዕዛዙ ላይ ከተመለከተው እቃ ውጪ በብርበራ ቢያዝ በሂደቱ የተገኘው ማስረጃ አግባብነቱ ምን ላሆን እንደሚገባ በህጉ በግልፅ አልተመለከተም።በተለያዩ የህግ ስርዓቶች በብርበራ የተገኘ ማስረጃን አስመልክቶ ማስረጃው የተገኘበት አግባብ ህጋዊ አለመሆኑ ማስረጃውን ህገ ወጥ አያሰኘውም (Admissibility of evidence is not affected by the illegality of the means through which the party has been enabled to obtain the evidence) የሚለው በመጀመሪያ የነበረው መርህ የግል ህይወት የመከበርና የመጠበቅ መብትን (Right to privacy) ጥበቃ መስጠትን ግቡ በማድረግ በሂደት እየዲበረ ሄድ የብርበራው ምክንያታዊ መሆን ከብርበራው ለተገኘው ማስረጃ ተቀባይነት የሚያስገኝለት ሆኖ ምክንያታዊ ካልሆነ በብርበራ የተገኘን ማስረጃ ዋጋ ማሳጣት እየተለመደ የመጣ ሲሆን የብርበራው ምክንያታዊ መሆንና አለመሆን የሚለካውም ብርበራው ሲካሄድ የነበሩትን አጠቃላይ (Total atmosphere of the case) ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ በማስገባት ላሆን እንደሚገባ የተለያዩ የዘርፈ ፀሀፍት ያስረዲለ።
በዚህ አግባብም ተጨማሪ የብርበራ ትዕዛዝ ለማግኘት በቂ እና ምክንያታዊ ጊዜ ነበርን? የሚለው የብርበራውን ህጋዊነት ለመመዘን ከግምት ውስጥ ሉገባ የሚገባ መሰረታዊ መስፈርት ተደርጎ የሚወሰድ ይሆናል።ከሶስት አመት በላይ ሉያስቀጣ የሚችል ክስ ወይም አቤቱታ የቀረበበት ወንጀል ለማስረጃ የሚሆን ወንጀለ የተፈፀመበት ነገር በአንድ ቦታ የተደበቀ ወይም የተቀመጠ መሆኑ ለመርማሪው ፖሉስ ወይም ለፖሉስ ሰራዊት ባልደረባ የተነገረው ከሆነና መበርበሪያ ትዕዛዝ እስኪቀበል ድረስ ወንጀል የተሰራበት ነገር ካለበት ቦታ ይወሰዲል ተብል በበቂ ምክንያት የታመነ ከሆነ ብርበራው ያለብርበራ ማዘዣ ሉከናወን እንደሚችል በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ.32(2)(ለ) መመልከቱ ከላይ የተመለከተው ቀሪ ሁኔታ በስነ ስርዓት ህጋችንም ተገቢው አውቅና የተሰጠው መሆኑን ያሳያል።
አሁን በያዝነው ጉዲይም በብርበራ የተገኙት ሲጋራዎች ተቀባይነትና ማስረጃዊ ፊይዲ ህገ መንግስታዊ ጥበቃ ከተሰጠው የግል ህይወት የመከበርና የመጠበቅ መብት አንፃር እየታየና እየተመዘነ የህግ ትርጉም ሉሰጠው ይገባል ብለን እናምናለን።አመልካቾች ብርበራው የተከናወነው ብርበራው እንዱከናወን ከተፈቀደለት ቤት ውጪ እናታቸው የንግድ ፈቃድ በማውጣት እያከራዩ በሚጠቀሙበት የቤት ቁጥር 664(ለ) ውስጥ መሆኑን በብርበራ የተገኘው እቃም የብርበራ ፈቃድ ከተሰጠበት የጦር መሳሪያና የውጪ ምንዛሪ ውጪ ሲጋራ መሆኑን በመግለፅ በብርበራው የተገኘው በውጪ ሀገር የተመረተው ሲጋራ ማስረጃ ሆኖ ላቀርብባቸው እንደማይገባ ገልጸው የተከራከሩ ቢሆንም በአመልካቾች ጭምር እንደታመነው ቤቱ እናታቸው አከራይተው የሚጠቀሙበት ሆኖ እያለ የመከላከያ ምስክሮቹ እንዲስረደትም ቤቶቹ ለአልጋ ተከራዮች የሚከራዩ ሆኖ እያለ ይህም በቤቱ ላይ የግል ህይወት የመከበርና የመጠበቅ መብት አላቸው ሉባለ የሚችለት በወቅቱ የተከራዩ ግለሰቦች የነበሩ መሆኑን አመልካቾች በምስክሮቻቸው ያላስረደ መሆኑ በስር ፍርድ ቤት ከመረጋገጡ አንፃር የግል ህይወት የመከበርና የመጠበቅ መብቱ እጅግ ቢበዛ የእናታቸው መሆኑን ያሳያል።
አመልካቾች የቤቱ ባለቤት ባለመሆናቸው ብርበራው ከተከናወነበት ቤት ጋር በተያያዘ ሉከበር የሚገባ የግል ህይወት የመከበርና የመጠበቅ መብት ያላቸው መሆኑን ከመነሻውም ባላሳዩበት ብርበራው ኢ-ምክንያታዊ ሆኖ የግል ህይወት የመከበርና የመጠበቅ መብታችንን ጥሷል በዚህ ምክንያትም ማስረጃው አግባብነት የለውም ብለው መከራከራቸው የሚያሳምን ሆኖ አልተገኘም።ከዚህም በተጨማሪ በብርበራው ወቅት የነበሩትን አጠቃላይ ሁኔታዎች ስንመዝንም ለመርማሪው ተጨማሪ የብርበራ ትዕዛዝ ለማግኘት የሚያስችለ አለመሆናቸውን ምስክሮቹ ከሰጡት የምስክርነት ቃል የምንረዲው ነው።ይህም አመልካቾች በብርበራ የተገኘው ሲጋራ ለፖሉስ ከተፈቀደለት ስልጣኑ ውጪ የተገኘ በመሆኑ ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ያቀረቡት ለጉዲዩ አግባብነት ያላቸውን ድንጋጌዎችና መርህዎች መሰረት ያላደረገ መሆኑን ያሳያል።
አመልካቾች ከማስረጃ ምርመራና ምዘና አንጻር ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ በተመለከተ በመሰረቱ በኢፋዱሪ ህግ መንግስት አንቀፅ 80(3)(ሀ) እና በፋደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀፅ 10(1) እንደተመለከተው ለዚህ ሰበር ሰሚ ችልት የተሰጠው የዲኝነት ስልጣን በስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ውስጥ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈፅሞ ሲገኝ በሰበር አይቶ የማረም ነው።በዚህ አግባብም ይህ ሰበር ሰሚ ችልት የሰበር ሰሚነት ስልጣኑን ተግባራዊ ሲያደርግ ፍሬ ነገርን በተመለከተ በዋነኝነት መነሻ የሚያደርገው ስልጣን ባላቸው የበታች ፍርድ ቤቶች የተረጋገጡትን ፍሬ ነገሮች ነው።
አሁን በያዝነው ጉዲይ የስር ፍርድ ቤት በአመልካቾች ላይ የጥፊተኝነት ውሳኔ የሰጠው ውሳኔም በክሱ ላይ የተመለከተው የውጪ ሀገር ሲጋራ ከህብረተሰቡ በደረሳቸው ጥቆማ መሰረት ፍተሻ ተደርጎ እንደተገኘ 2ኛ አመልካችም እቃው የኛ ነው እንዲላቸው እና 1ኛ አመልካች ደረሰኝ አመጣለሁ ያለ ቢሆንም አለማምጣቱን አቃቤ ህግ በምስክሮቹ ማስረዲቱን አመልካቾች በምስክሮቻቸው ቤቱን ላላ ግለሰብ መከራየቱን በክርክራቸው አግባብ ያላስረደ መሆኑን፤ቤቱን ላላ ሰው ለመከራየቱ መታወቂያና ላላ አግባብነት ያለው ማስረጃ አለመቅረቡን፤የመከላከያ ምስክሮቹ አመልካቾች እቃው የኛ ነው ብለው በገለፁበት ምስክሮቹ የላላ ሰው ነው ማለታቸው የሚያሳምን አለመሆኑን በመጥቀስ ነው።ይህ የስር ፍርድ ቤቶች ማስረጃን የመስማት፤የመመርመርና የመመዘን ስልጣናቸውን ተጠቅመው የደረሱበት ድምዲሜ በዚህ ችልት ሉለወጥ የሚችለው የስር ፍርድ ቤቶች በማስረጃ ምዘና ረገድ የፈፀሙት ስህተት ከተገኘ ብቻ ሲሆን ይህ ችልት ባደረገው ምርመራ በስር ፍርድ ቤት የተፈፀመ የማስረጃ ምዘና መርህ ጥሰት ያልተገኘ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤቶች በአመልካቾች ላይ የጥፊተኝነት ውሳኔ መስጠታቸው የሚነቀፍ ሆኖ አልተገኘም።
ገደብን አስመልክቶም ከእስር በገደብ መለቀቅ ማለት ፍርድ ቤት አንድ ጥፊተኛ የተባለን ሰው ለጥፊቱ መነሻ የሆኑትን ምክንያቶች በጠቅላላው በመመልከት በጥፊተኛው ላይ የተወሰነውን ቅጣት ለጊዜው በገደብ እንዱታገድ በማድረግ የወንጀለኛውን ጠባይ ለማረምና ለማሻሻል እንዱሁም ወደ መደበኛ ማህበራዊ ኑሮው ለመመለስ ጠቃሚ መሆኑን አረጋግጦ ከእስር እንዱፈታ የሚደረግበት የህግ ስርዓት መሆኑን ከወ/ህ/አ.190 የምንገነዘበው ነው።የገደብ ውሳኔ በዘፈቀደ የሚሰጥ ወይም የሚከለከል ባለመሆኑ የገደብ አሰጣጥ ውሳኔዎችን ተግባራዊ ለማድረግ ወይም ጥያቄውን ውድቅ ለማድረግ ፍርድ ቤቶች በህግ የተመለከቱት ሁኔታዎች በዋነኝነትም በወ/ህ/አ.192፤194 እና 197 መሟላት አለመሟላታቸውን በጥንቃቄ ሉያረጋግጡ ይገባል።በዚህ አግባብ የገደብ ውሳኔ ካልተሰጠ የወንጀል ህጉን መሰረታዊ አላማ ለማሳካት የማይቻል መሆኑ ይታመናል።
አሁን በያዝነው ጉዲይ አመልካቾች በስር ፍርድ ቤት የገደብ ጥያቄ አቅርበው የነበረ መሆኑን የግራ ቀኙን ክርክር ተከትል የተሰጠው ውሳኔ የሚያሳይ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ የገደብ ጥያቄውን ውድቅ ያደረገው በደፈናው ይገደብልን በማለት ያቀረቡትን ሀሳብ ፍርድ ቤቱ አልተቀበለውም በማለት ነው።የአመልካቾች የገደብ ጥያቄ ከወ/ህ/አ.192፤194 እና 197 መስፈርቶች አንፃር ተቀባይነት ያጣበትን ምክንያት በመዘርዘር በውሳኔው ላይ የገደብ ጥያቄውን ውድቅ ያደረገበትን ምክንያት በዝርዝር አላሰፈረም።ይህ በፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት የገደብ ጥያቄን በደፈናው ውድቅ የማድረግ ሂደት ጉዲዩን በይግባኝ በተመለከተው የፋ/ከ/ፍ/ቤት ሉታረም ሲገባው ፍርድ ቤቱ ይህንን መሰረታዊ የህግ ስህተት ሳያርም መቅረቱ አግባብነት ያለው ሆኖ አልተገኘም።
በአመልካቾች የተጣለው የእስራት ቅጣት ከአምስት ፅኑ እስራት ያልበለጠ መሆኑ በወ/ህ/አ.194(1)(ለ) የተመለከተው መሰረታዊ መስፈርት መሟላቱን የሚያሳይ ሲሆን በአመልካቾች ላይ የተያዘ የቀደም ሪከርድ አለመኖሩና የእድሜያቸውን ሁኔታ እንዱሁም ማህበራዊ ተሳትፍአቸውና ለቤተሰባቸው የሚያደርጉት ድጋፍ ሲታይ አመልካቾች ከስህተታቸው እንዱማሩና በተመሳሳይ የወንጀል ድርጊት እንዲይሰማሩ አንድ ፅኑ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ከዚህ በኋላ ባለው ህይወታቸው በመልካም ፀባይ እንዱመሩና ከተመሳሳይ ድርጊት እንዱታቀቡ ይረዲል፤ያግዛል ብለን ስላመንን በስር ፍርድ ቤት የተሰጠው የእስራት ቅጣት በሁለት አመት የፈተና ጊዜ ሉገደብ ይገባል በማለት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፍደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ በቀን 15/10/2013 ዓ.ም የሰጠው የጥፊተኝነትና በ21/10 2013 ዓም የሰጠው የቅጣት ውሳኔ (የገደብ አቤቱታውን ውድቅ በማድረግ የሰጠውን የውሳኔ ክፍል ሳይጨምር የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.272693 በቀን 14/11/2013 ዓ.ም ይህንን የውሳኔ ክፍል በማፅናት የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈፀመበት ሆኖ ስላልተገኘ በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ 195 (2) (ለ) (2) መሰረት ፀንቷል።
ገደብን አስመልክቶ የፍደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ቁ. 289523 በ21/10/2013 ዓ.ም የሰጠው የቅጣት ውሳኔ ክፍል እና ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ይህንን የውሳኔ ክፍል በማፅናት የሰጠው ትዕዛዝ ተሸሯል።
በአመልካቾች ላይ የተጣለው የእስራት ቅጣት አፈፃፀሙ በሁለት አመት የፈተና ጊዜ የተገደበ ስለሆነ አመልካቾች በዚህ የፈተና ጊዜ ውስጥ በወንጀል ድርጊት ላለመሰማራት ግዳታ ገብተው ፈርመው ለገደቡ አፈፃፀም ዋስትና እየአንዲንዲቸው ብር 25,000.00(ሀያ አምስት ሺህ ብር) ሲያሲዙ ወይም ተመጣጣኙን ዋስትና ሲያቀርቡ ከእስር እንዱለቀቁና በዚህ ችልት ለዋስትና ያስያዙት ገንዘብ እንዱመለስላቸው ታዟል።
No topics extracted.