ክስ ወደ ላላ ሥፍራ ይዛወርልኝ አቤቱታን ጨምሮ ተከራካሪ ወገኖች ዳኞች እና የፍርድ ቤት አመራሮች በነፃነት እና ያለ አድል የመዲኘት ግዳታቸውን አልተወጡም በማለት የሚያቀርቡት ማናቸውም አቤቱታ ሕጋዊ መሰረት ያለው እና በተጨባጭ ማስረጃ ተረጋግጦ ላቀርብ የሚገባ ስለመሆኑ የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 78 እና 79፣ የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 106፣ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ሥነ ሥርዓትን እና የፍትሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግን ለማሻሻል የወጣ አዋጅ ቁጥር 84/1968
No summary available.
ሰኔ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሣዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡- አቶ አሸብር አውዳ ተጠሪ፡- በደቡብ ብሓሮች ብሓረሰቦች እና ሕዝቦች ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት የወላይታ ምድብ ዓቃቤ ሕግ መዝገቡ ለምርመራ የተቀጠረ ነው። በመሆኑም መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
የሰበር አቤቱታው ላቀርብ የቻለው አመልካች ጥር 18 ቀን 2012 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ በደቡብ ብሓሮች ብሓረሰቦች እና ሕዝቦች ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ. መስከረም 06 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለው ችልት አመልካች ያቀረበውን የክስ ወደ ላላ ሥፍራ ይዛወርልኝ ጥያቄን ውድቅ በማድረግ የሰጠው ውሳኔ፤ ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ. ታሕሳስ 01 ቀን 2012 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት አቤቱታ በማቅረባቸው ነው።
ጉዲዩ የክስ ወደ ላላ ሥፍራ ይዛወርልኝ ጥያቄን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በደቡብ ብሓሮች ብሓረሰቦች እና ሕዝቦች ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት ነው። የአሁን አመልካች ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረቡት የክስ ይዛወርልኝ አቤቱታ ይዘት በአጭሩ፡- የከፍተኛው ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት በፍርድ ቤት አስተያየት መስጫ መዝገብ ላይ የፍርድ ቤቱን ስም እና ዝናን የሚያጎድፍ እና ዛቻ መሰል አስተያየት እንደተጻፈ እና የእጅ ጽሐፈ ከአመልካች ጋር እንደሚመሳሰል በመግለጽ በቀን 06/11/2010 ዓ.ም በተጻፈ ደብዲቤ ቢሮ ቀርቤ ምላሽ እንድሰጥ ትዕዛዝ ሰጥቶኛል፤
ይህንኑ መሰረት በማድረግ በፍርድ ቤቱ ፕሬዝደንት ላይ በክልለ ዳኞች አስተዲደር ጉባኤ የዱስፕሉን ክስ አቅርቤአለሁ፤ በዚህም ምክንያት የፍርድ ቤቱ ፕሬዝደንት ዳኞች እና ሰራተኞችም በማሰባሰብ በአስተያየት መስጫ መዝገቡ ላይ እኔ እንደጻፍኩ ገልጸዋል፤ ስማቸው በአቤቱታው ላይ የተጠቀሰው የከፍተኛው ፍርድ ቤት ሁለት ዳኞች ተከሳሽ በሆንኩበት የፍ.መ. በሆነው መዝገብ ተከሳሿን ለመጥቀም ከስነ-ስርዓት ውጪ ክርክሩን በመምራታቸው ምክንያት በዞኑ ዳኞች አስተዲደር ጉባኤ ክስ አቅርቤባቸዋለሁ፤ የመ. በሆኑት መዛግብት የተፈጸመብኝን በደል ይግባኝ ጠይቄ ፍትሕ አግኝቻለሁ፤ በመ. ለቀረበብኝ የቼክ ወንጀል መቃወሚያ ያቀረብኩ ቢሆንም የዱስፕሉን ክስ ያቀረብኩበት የፍርድ ቤቱ ፕሬዝደንት ተሰይሞ ሕግን ባልተከተለ ሁኔታ መቃወሚያዬን ውድቅ አድርጓል፤ አመልካች በቂም እና በጥላቻ በተደጋጋሚ የፍትሕ መዛባት የደረሰብኝ እና በተጠቀሱት ምክንያቶች ፍርድ ቤቱ ያለአድል የቀረበውን ክስ ሉሰማ የማይችል በመሆኑ ክሱ ወደ ላላ ፍርድ ቤት ተዛውሮ ይታይልኝ የሚል ነው።
ተጠሪ የሰጠው መልስ ይዘት በአጭሩ፡- ፕሬዝደንቱ ጉዲዩን ለማጣራት አስተዲደራዊ ስራ ሰርቷል፤
ፕሬዝደንቱን በሚመለከት ለክልለ ዳኞች አስተዲደር ጉባኤ የደረሰ ክስ የለም፤ ሁለቱ ዳኞች የዱስፕሉን ክስ ቢቀርብባቸውም የመጨረሻ ውሳኔ አልተሰጠም፤ አንደኛው ዲኛ ከችልት እንዱነሱ አቤቱታ ቀርቦ እንዱነሱ ተደርጓል፤ ላላኛዋ ዲኛ ደግሞ የፍትሐብሕር ዲኛ በመሆን ዓመቱን ሙለ የጨረሱ እና አሁንም እዚያው ያለ ናቸው፤ ጉዲዮችን በይግባኝ ማሻር ለክስ ይዛወር ምክንያት አይሆንም፤ ፍርድ ቤቱ ከአስራ ሁለት በላይ ዳኞች ያለበት እና በአሁኑ ጊዜ ጉዲዩን እያዩ ያለት ዳኞች ከተጠቀሱት ዳኞች ውጪ በመሆናቸው አመልካች ያቀረቡት የክስ ወደ ላላ ሥፍራ ይዛወርልኝ አቤቱታ ውድቅ ላደረግ ይገባል የሚል ነው።
ጉዲዩ የቀረበለት ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ ፕሬዝደንቱ በሕግ በተሰጠው ስልጣን አስተዲደራዊ ተግባር መፈጸሙ ለክስ ይዛወርልኝ ምክንያትነት አይሆንም፤ ለክልለ ዳኞች አስተዲደር ጉባኤ ክስ አቅርቤአለሁ በማለት ቀሪ ደብዲቤ መቅረቡ በእርግጥም አቤቱታው መድረሱን የሚያሳይ አይደለም፤ ደርሷል ቢባል እንኳን ክሱ ተቀባይነት አግኝቶ መልስ እንዱሰጡ የተደረገበት ሁኔታ የለም፤
በተቋሙ ባልደረቦችም በኩል በክፈ ዓይን እየታየሁ ነው በማለት የቀረበውም የራስ ጥርጣሬ ከሚሆን በቀር በምክንያትነት ሉወሰድ አይችልም፤ በዲኞቹ ላይ ለዞኑ ዳኞች አስተዲደር ጉባኤ ክስ የቀረበባቸው ቢሆንም ጉዲዩ የመጨረሻ ዕልባት ስለማግኘቱ የቀረበ ማስረጃ የለም፤ አንደኛው ዲኛ ክስ የቀረበባቸው በመሆኑ ምክንያት ጉዲዩን እንዲያዩ መደረጉ በችልቱ ሂደት ተመዝግቦ እያለ ጉዲዩን በማያዩ ዲኛ የክስ ይዛወርልኝ ጥያቄ መቅረቡ እንዱሁም በስም ተጠቃሿ ላላኛዋ ዲኛም ጉዲዩን እያዩ ባለመሆኑ ጥያቄው ሕግን የተከተለ አይደለም፤ በይግባኝ ሥርዓት ጉዲዮች እንዱሻሩ፤ እንዱሻሻለ ወይም እንዱጸኑ ማድረግ ሕጋዊ ሥርዓት ሲሆን ክርክሩ ደረጃውን ጠብቆ በይግባኝ ወይም በሰበር ስርዓት የሚቀጥል እና ተሻረ የተባለውም ጉዲይ የሕግ ትርጉም ተሰጥቶት የሚሻርበት ወይም የሚሻሻልበት ሥርዓቶች በመሆናቸው ለክስ ይዛወርልኝ ምክንያት መሆን አይችለም በማለት አመልካች ያቀረቡትን የክስ ወደ ላላ ሥፍራ ይዛወርልኝ አቤቱታ ውድቅ በማድረግ ወስኗል። ይህም ውሳኔ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልትም ጸንቷል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም መሰረታዊ የሕግ ስሕተት ተፈጽሞበታል በሚል ሲሆን ይዘቱም፡- አመልካች ከፍርድ ቤቱ ፕሬዝደንት ዛቻ እና ማስፈራራት እንደደረሰብኝ እና ከፍተኛ ጥላቻ እንዱያድርብኝ ማስደረጉን፤ ለክልለ የሕዝብ ምክር ቤት እና ለዞኑ ምክር ቤት አቤቱታ ማቅረቤን እና በክልለ የዳኞች አስተዲደር ጉባኤ ክስ ማቅረቤን የሚያሳይ ማስረጃ አቅርቤአለሁ፤ በተለያዩ መዝገቦች ከሙግት ስነ ስርዓት ውጪ ክርክር በመምራታቸው በአምስት የፍርድ ቤቱ ዳኞች ላይ የዱስፕሉን ክስ አቅርቤአለሁ፤ በተከሰስኩበት የቼክ ወንጀል ፕሬዝደንቱ ሆን ብል የመሃል ዲኛ ሆኖ በመሰየም በዱስፕሉን ከከሰስዄቸው ዳኞች ጋር በመሆን መቃወሚያዬን ከሕግ ውጪ ውድቅ ማድረጉን፤ ክሱ የሚታይበት ፕሬዝደንት ዘመድ በሆነች ግለሰብ ላይ ያቀረብኩባትን የጉዲት ካሣና ኪሣራ ክስ አመልካች የጎፊ ብሓር ተወላጅ በመሆኔ ምክንያት ክሱን ውድቅ ማድረጋቸው፤ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ አቅርቤ በሰ.መ. ጥቅምት 27 ቅ 2012 ዓ.ም በዋለው ችልት ፍርድ ቤቱ በክርክር አመራር ረገድ የሕግ ስሕተት መፈጸሙን እና የአመልካችን ፍትሕ የማግኘት መብት የሚጋፊ መሆኑን በመግለጽ ውሳኔውን ያረመ መሆኑን፤ የክስ ይዛወርልኝ በቀረበበት ጉዲይ ላይ የግል ተበዲይ የተባለው የዞኑ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ መምሪያ ሃላፉ አጎቱ በመሆኑ እና በአካባቢው በሀብቱ እና በዘመድቹ ብዛት ስሜን በማጥፊት መጠቋቆሚያ ያደረገኝ መሆኑን የሚያሳዩ ማስረጃዎች ባቀረብኩበት ሁኔታ አመልካች ያቀረብኩት አቤቱታ ውድቅ በማድረግ በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ አመልካች የስር ጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት ባደረሰብኝ በደል በዳኞች አስተዲደር ጉባኤ የዱስፕሉን ክስ ያቀረብኩ በመሆኑ በገለልተኝነት ጉዲዩን ፍርድ ቤቱ ሉመለከት አይችልም በማለት ያቀረበውን የክስ ወደ ላላ ሥፍራ ይዛወርልኝ አቤቱታ ውድቅ የመደረጉን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ በዚህ ችልት እንዱታይ ተደርጓል። ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎም ግራ ቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የተጠሪ መልስ ይዘት በአጭሩ፡- አመልካች ያቀረበው የክስ ይዛወርልኝ አቤቱታ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ውድቅ ተደርጎበታል፤ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 106/2 መሰረት በግልጽ እንደተደነገገው እንዱዚህ ዓይነት ትዕዛዞች ይግባኝ የማይባልባቸው በመሆኑ አመልካች ለዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ያቀረበው አቤቱታ የወንጀል ሥነ ሥርዓቱን ያልተከተለ ነው፤ በጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስተያየት መስጫ መዝገብ ላይ በተጻፈው የዛቻና የማስፈራሪያ ቃል አንጻር የፍርድ ቤቱ ፕሬዝደንት ይህን ጽሁፍ ጽፈዋል ተብለው ከተጠቆሙ ሰዎች ውስጥ አመልካችን ቢሮአቸው ጠርተው በማወያየታቸው እና የአስተዲደር ስራ በመስራታቸው ብቻ ለምን ተጠራሁ በሚል በሀሰት አቤቱታ ከማቅረባቸው በቀር አመልካች እንደሚለት በፕሬዝደንቱ ላይ የቀረበ የዱስፕሉን ክስ የለም፤ ስለሆነም የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ ሉጸና ይገባል የሚል ነው።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው። ይህ ችልትም በሰበር አጣሪው ችልት ሉጣራ ይገባዋል ተብል የተያዘውን ነጥብ ከግራ ቀኙ ክርክር፤ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምሮታል።
የብላክስ ልው መዝገበ ቃላት የክስ ወደ ላላ ሥፍራ ማዛወር /change of venue/ ትርጉም እንደሚከተለው አስቀምጦታል።
Change of venue is the removal of a suit began in one country or district to another country or district for trial, though the term is also sometimes applied to the removal of a suit from one court to another court of the same country or district.
በእኛም ሐገር ይህ ጽንስ ሐሳብ በአንድ ሥፍራ የተጀመረን ክስ ወደ ላላ ስፍራ ሄድ እንዱታይ ማድረግ ወይም በአንድ ፍርድ ቤት የተጀመረን ክስ በዚያው ሥፍራ ላይ ወደሚገኝ ላላ ፍርድ ቤት ተዛውሮ እንዱታይ ማድረግ ማለት እንደሆነ ግንዛቤ ተወስድበታል።
በወንጀል ጉዲይ የክስ ይዛወርልኝ አቤቱታ የሚቀርብበት ሥርዓት በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 106 ላይ ተደንግጓል። ሆኖም ይህ ድንጋጌ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ሥነ ሥርዓትን እና የፍትሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግን ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር 84/1968 ተሻሽሎል። በዚሁ በተሻሻለው አዋጅ መሰረት በወንጀል ጉዲይ ክስ ወደ ላላ ሥፍራ እንዱዛወር መጠየቅ የሚቻለው ማስረጃ ከመሰማቱ በፉት ዓቃቤ ሕጉ ወይም ተከሳሹ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዲዩን መሥማት የጀመረው የበታች ፍርድ ቤት በማመልከቻ የቀረበለትን ጉዲይ ያለአድል በትክክል ለመስማት የማይችል መሆኑን ወይም ጉዲዩ ዘወትር የማያጋጥም አስቸጋሪ የሕግ ክርክር የሚያስነሳ መስል መታየቱን ወይም በድንጋጌው አግባብ ትዕዛዝ ቢሰጥ ለሁለቱም ተከራካሪ ወገኖች ወይም ለምስክሮች ምቹ መሆኑን ወይም ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ቢሰጥ በአጭር ጊዜ ትክክለኛ ፍርድ ለማስገኘት የሚያስችል ወይም ትዕዛዝ እንዱሰጥ የዚህ ሕግ ድንጋጌ የሚጠይቅ መሆኑን ሲያመለክት ነው።
ከክስ ወደ ላላ ሥፍራ ይዛወርልኝ ጽንስ ሐሳብ እና ከላይ ከተመለከተው ድንጋጌ ይዘት መገንዘብ የሚቻለው ክሱ ወደ ላላ ሥፍራ እንዱዛወር የቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት አግኝቶ ክሱ ወደ ላላ ሥፍራ ወይም በዚያው ሥፍራ ላይ ወደሚገኝ ላላ ፍርድ ቤት ሉዛወር የሚችለው ክሱ እየታየ ባለበት ሥፍራ ወይም ፍርድ ቤት ውስጥ ጉዲዩን ለማየት የሚችል ሥልጣን ያለው ላላ ችልት የላለ በሆነ ጊዜ ነው።
በያዝነው ጉዲይ አመልካች ክሱ ወደ ላላ ሥፍራ እንዱዛወር ሲጠይቁ ያቀረቧቸው ምክንያቶች በሙለ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን ያለአድል ሉያይልኝ አይችልም በሚል የቀረቡ በመሆኑ የአመልካች ዋነኛ የክርክር አውድ የሚያጠነጥነው ከፍርድ ቤቱ ገለልተኝነት ላይ ነው። ስለሆነም በእርግጥም አመልካች ያቀረቧቸው ምክንያቶች ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን ያለአድል እንዲያይ የሚያደርጉ እና ክስ ወደ ላላ ሥፍራ እንዱዛወር የሚያስችለ ተቀባይነት ያላቸው ምክንያቶች ናቸው? ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምረናል።
በመሰረቱ ነጻ የዲኝነት አካል የተቋቋመ ስለመሆኑ፤ በየትኛውም ደረጃ የሚገኝ የዲኝነት አካል ከማናቸውም የመንግስት አካል፤ ከማናቸውም ባለስልጣንም ሆነ ከማናቸውም ላላ ተጽዕኖ ነጻ መሆኑን፤ ዳኞች የዲኝነት ተግባራቸውን በሙለ ነጻነት ሉያከናውኑ እንደሚገባ እና ከሕግ በስተቀር በልላ ሁኔታ ሉመሩ እንደማይገባ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 78 እና 79 ድንጋጌዎች ላይ በግልጽ ተመልክቷል። ይህም የዲኝነት ሥርዓቱ መሰረታዊ መርህ በመሆኑ ዳኞች እና የፍርድ ቤት አመራሮች በላቀ ሥነ-ምግባር እና በጥብቅ ሉተገብሩት ይገባል። ይህን ተላልፈው በተገኙ ጊዜም አግባብነት ባላቸው ሕጎች መሰረት ተጠያቂነት ያለባቸው ስለመሆኑ ግንዛቤ ሉወሰድበት ይገባል።
በልላ በኩል በሕገ-መንግስቱ በተቋቋመው ነጻ የዲኝነት አካል ፉት በመቅረብ ፍትሕ የማግኘት መብታቸው የተረጋገጠላቸው ዜጎች ጉዲያቸው ውሳኔ ከማግኘቱ በፉትም ሆነ በኋላ ይህ መብታቸው በአግባቡ እንዱከበር ለማድረግ የሚያስችለ መፍትሓዎች በተለያዩ ሕጎች ላይ ተቀምጠውላቸዋል።
ከእነዚህም ውስጥ ገለልተኛ ያልሆነው ዲኛ ከችልት እንዱነሳ መጠየቅ፤ የክስ ወደ ላላ ስፍራ ይዛወርልኝ ጥያቄን ማቅረብ እና ዲኛው የሰጠው ፍርድ በይግባኝ እና በሰበር ስርዓት ማሳረም የሚለት ተጠቃሽ ናቸው። ስለሆነም በነጻነት እና ያለ አድል የመዲኘት ሕገ-መንግስታዊ ግዳታቸውን አክብረው ሥራቸውን ይከውናለ ተብል ግምት የሚወሰድባቸው ዳኞች እና የፍርድ ቤት አመራሮች ይህን ሕገመንግስታዊ ግዳታ አልተወጡም በማለት ተከራካሪ ወገኖች መብታቸውን ለማስከበር የሚያቀርቡት ማናቸውም አቤቱታ ሕጋዊ መሰረት ያለው እና በተጨባጭ ማስረጃ የተረጋገጠ ላሆን ይገባል።
በያዝነው ጉዲይ አመልካች ላቀረቡት የክሥ ወደ ላላ ሥፍራ ይዛወርልኝ ጥያቄ ያቀረቧቸው የመጀመሪያዎቹ ምክንያቶች የከፍተኛው ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት በፍርድ ቤት አስተያየት መስጫ መዝገብ ላይ የፍርድ ቤቱን ስም እና ዝናን የሚያጎድፍ እና ዛቻ መሰል አስተያየት እንደተጻፈ እና የእጅ ጽሐፈ ከአመልካች ጋር እንደሚመሳሰል በመግለጽ ቢሮ ቀርቤ ምላሽ እንድሰጥ ትዕዛዝ በመስጠቱ የዱስፕሉን ክስ አቅርቤአለሁ፤ ይህንኑ ተከትል የፍርድ ቤቱ ፕሬዝደንት ዳኞች እና ሰራተኞችም በማሰባሰብ በአስተያየት መስጫ መዝገቡ ላይ እኔ እንደጻፍኩ በመግለጽ በጥላቻ እንድታይ አድርገዋል፤
ስማቸው በአቤቱታው ላይ የተጠቀሱት ሁለት የከፍተኛው ፍርድ ቤት ዳኞች ተከሳሽ በሆንኩበት የፍ.መ. በሆነው መዝገብ ተከሳሿን ለመጥቀም ከስነ-ስርዓት ውጪ ክርክሩን በመምራታቸው በዞኑ ዳኞች አስተዲደር ጉባኤ ክስ አቅርቤባቸዋለሁ፤ በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተለያዩ መዝገቦች ባደረግኩት ክርክር አላግባብ የተሰጠብኝን ውሳኔ በይግባኝ አሳርሜያለሁ፤ በመ. ለቀረበብኝ የቼክ ወንጀል መቃወሚያ ያቀረብኩ ቢሆንም የዱስፕሉን ክስ ያቀረብኩበት የፍርድ ቤቱ ፕሬዝደንት ተሰይሞ ሕግን ባልተከተለ ሁኔታ መቃወሚያዬን ውድቅ አድርጓል፤ ተጠቃሾቹ ምክንያቶች ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን ያለአድል ሉያይ እንደማይችል ማሳያ ናቸው በሚል ነው።
በመሰረቱ የፍርድ ቤቱ ፕሬዝደንት ፍርድ ቤቱን በበላይነት የሚመራ በመሆኑ ራሡም ሆነ የፍርድ ቤቱ ዳኞች ከማናቸውም አካል ተጽእኖ ነጻ ሆነው ጉዲዮችን ያለአድል እንዱያዩ የማድረግ ሕገመንግስታዊ ግዳታ ያለበት ሲሆን የፍርድ ቤቱንም ስም እና ክብር የመጠበቅ እና የማስጠበቅ ሀላፉነት አለበት። ይህንኑ ሲያደርግም ሕግን እስካልተላለፈ ድረስ ተቋሙን በሚመለከት የሚቀርቡለትን ማናቸውንም መረጃዎች እና ማስረጃዎች እንደ አግባብነታቸው ሉጠቀምባቸው እና ጉዲዩ ይመለከታቸዋል ያላቸውን አካላት ሉያነጋግር እንደሚችል ይጠበቃል። የፍርድ ቤቱ ፕሬዝደንት በፍርድ ቤቱ አስተያየት መስጫ መዝገብ ላይ የፍርድ ቤቱን ስም እና ዝና የሚያጎድፍ ጽሐፍ በማየቱ ምክንያት አስተያየቱን ጽፎል ብል የገመተውን አመልካች ምላሽ እንዱሰጥበት ደብዲቤ መጻፈ ብቻውን አስተዲደራዊ ስራውን ሰርቷል ከሚያስብል በቀር የአመልካች ጉዲይ በነጻነት እና ያለአድል እንዲይታይ የማድረግ ውጤት አይኖረውም። ሆኖም የፍርድ ቤቱ ፕሬዝደንት ከዚህ አልፍ አመልካች የፍርድ ቤቱን ስም እና ዝና የሚያጎድፍ ጽሐፍ ጽፎል በሚል ምክንያት በፍርድ ቤቱ ዳኞች ላይ ተጽእኖ በመፍጠር የአመልካች ጉዲይ በገለልተኝነት እንዲይታይ የሚያደርግ ተግባር የፈጸመ ስለመሆኑ በተጨባጭ ማስረጃ የተረጋገጠ እንደሆነ ክስ ወደ ላላ ስፍራ ይዛወርልኝ ብል ለመጠየቅ የሚያስችል በቂ ምክንያት ይሆናል። ይህንኑ መሰረት በማድረግ ጉዲዩን እንደተመለከትነው አመልካች የፍርድ ቤቱ ፕሬዝደንት ፈጸሙት ያለውን ድርጊት ከማመላከት በቀር ፕሬዝደንቱ አቤቱታ ቀርቦባቸው መልስ ስለመስጠታቸውም ሆነ በቀረበው የዱስፕሉን ክስ መሰረት የተላለፈባቸው ውሳኔ ስለመኖሩ በመግለጽ ያቀረበው ክርክርም ሆነ ማስረጃ የለም።
አመልካች ስማቸው በአቤቱታው ላይ የተጠቀሱት የፍርድ ቤቱ ዳኞች ተከሳሽ በሆንኩበት የፍ.መ. በሆነው መዝገብ ተከሳሿን ለመጥቀም ከስነ-ስርዓት ውጪ ክርክሩን በመምራታቸው በዞኑ ዳኞች አስተዲደር ጉባኤ ክስ አቅርቤባቸዋለሁ በማለት የተከራከሩ ሲሆን በስም ተጠቃሾቹ ዳኞች ላይ ለዞኑ ዳኞች አስተዲደር ጉባኤ ክስ የቀረበባቸው ቢሆንም ጉዲዩ የመጨረሻ ዕልባት ማግኘቱን የሚያሳይ ማስረጃ ያልቀረበ መሆኑን፤ አንደኛው ዲኛ ክስ የቀረበባቸው በመሆኑ ምክንያት ጉዲዩን እንዲያዩ የተደረገ መሆኑ እና ላላኛዋም ዲኛ ጉዲዩን የማያዩ መሆኑ ተረጋግጧል፤ ስለሆነም ይህ በተረጋገጠበት ሁኔታ አመልካች ጉዲያቸውን በማየት ላይ የላለ ዳኞች ጉዲዬን በገለልተኝነት ሉያዩ አይችለም በሚል ያቀረቡት የክስ ይዛወርልኝ ጥያቄ ተቀባይነት ያለው አይደለም።
አመልካች በመ. ለቀረበብኝ የቼክ ወንጀል ክስ መቃወሚያ ያቀረብኩ ቢሆንም የዱስፕሉን ክስ ያቀረብኩበት የፍርድ ቤቱ ፕሬዝደንት ተሰይሞ ሕግን ባልተከተለ ሁኔታ መቃወሚያዬን ውድቅ አድርጓል በማለት ያቀረቡት ምክንያትም ፕሬዝደንቱ አመልካችን ለመጉዲት ብለው ከሕግ ውጪ መቃወሚያውን ውድቅ ስለማድረጋቸው በማስረጃ አለማረጋገጣቸው እንደተጠበቀ ሆኖ በመዝገቡ ላይ ተሰየሙ የተባለት ፕሬዝደንት ገለልተኛ ሆነው ጉዲዩን አያዩም የሚለ ከሆነ ፕሬዝደንቱ ከችልት እንዱነሱ አቤቱታ ለማቅረብ የሚያስችላቸው ከሚሆን በቀር ክስ ወደ ላላ ስፍራ እንዱዛወር ለመጠየቅ የሚያስችል በቂ ምክንያት አይደለም።
ከላይ የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ አመልካች ክሱ ወደ ላላ ሥፍራ እንዱዛወርላቸው ለመጠየቅ የሰጡት ላላው ምክንያት በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዘመድ ላይ ያቀረብኩት ክስ አላግባብ ውድቅ ተደርጎ በየደረጃው ባለ ፍርድ ቤቶች አቤቱታ አቅርቤ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ.መ. ጥቅምት 27 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለው ችልት ፍርድ ቤቱ በክርክር አመራር ረገድ የሕግ ስሕተት መፈጸሙን እና የአመልካችን ፍትሕ የማግኘት መብት የሚጋፊ መሆኑን በመግለጽ ውሳኔውን አርሟል፤ ይህም የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዲዬን በገለልተኝነት እንደማያይልኝ ማሳያ ነው የሚል ነው።
ስለይግባኝ ሥርዓት በተመለከተው የፍትሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት ሕጉ ስድስተኛ መጽሐፍ ቁጥር 320 እና ተከታይ ድንጋጌዎች በተለይም ከቁጥር 337፤ 341፤ 343 እና 348 ድንጋጌዎች ይዘት መገንዘብ የሚቻለው ይግባኝ የተጠየቀበት ፍርድ ሉጸና፤ ሉሻሻል፤ ሉለወጥ፤ ሉሻር ወይም ጭብጥ ተይዞ ጉዲዩ ተጣርቶ እንዱወሰን በማለት ፍርደን ለሰጠው ችልት ሉመለስለት እንደሚችል ነው።
አመልካች ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ. አቤቱታ አቅርበው ጥቅምት 27 ቀን 2012 ዓ.ም ተሰጠ የተባለው ውሳኔ ይዘት አመልካች የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ዘመድ ናቸው የሚሎቸው የመዝገቡ 1ኛ ተጠሪ ሽንት ቤቱን ማፍረሳቸው ተረጋግጦ የፈረሰውን ለመገንባት የሚያስከትለውን ወጪ እንዱከፍለ እና የተዘጋውን ሽንት ቤት እንዱያስከፍቱ ተወስኖ እያለና ውሳኔው ስለመሻሩ ክርክርም ሆነ ማስረጃ ሳይቀርብ አመልካች በዚህ ምክንያት የተቋረጠውን ገቢ ሲጠይቁ ሀላፉነትን የሚያሳይ የጸና ፍርድ ሕጋዊ ውጤት ምንድነው የሚለውን ሳይመለከቱ 1ኛ ተጠሪ ለክሱ ሀላፉ አይደለም ሲለ የስር ፍርድ ቤቶች የደረሱበት ድምዲሜ ተገቢ አይደለም፤ ስለሆነም የስር ፍርድ ቤቶች በክርክር አመራር ረገድ የፈጸሙት ስሕተት የአመልካች ፍትሕ የማግኘት መብት የሚጋፊ ሆኖ ስለተገኘ ሉታረም የሚገባው ነው በማለት የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአመልካች እና በመዝገቡ 1ኛ ተጠሪ መካከል ያለውን ክርክር በመቀጠል ጭብጥ መስርቶ አከራክሮ እንዱወስን በሚል የተሰጠ ውሳኔ ነው። ይህም በፍትሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት ሕጉ ላይ ስለ ይግባኝ ሥርዓት በተደነገጉት ድንጋጌዎች አግባብ በየደረጃው ባለ ፍርድ ቤቶች ክርክር ተደርጎ በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ የተሻሻለ መሆኑን የሚያሳይ እንጂ አመልካች እንደሚለት የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአመልካችን ጉዲይ ገለልተኛ ሆኖ ባለማየቱ ምክንያት የተሰጠ ውሳኔ ስለመሆኑ ተገልጾ ውሳኔው የተሻረ መሆኑን የሚያሳይ አይደለም። ስለሆነም አመልካች ይህንኑ መሰረት በማድረግ ያቀረቡት የክስ ወደ ላላ ሥፍራ ይዛወርልኝ ጥያቄ ተቀባይነት ያለው አይደለም።
በልላ በኩል ተጠሪ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰጠው መልስ ፍርድ ቤቱ ከአስራ ሁለት በላይ ዳኞች ያለበት እና በአሁኑ ጊዜ ጉዲዩን እያዩ ያለት ዳኞች ከተጠቀሱት ዳኞች ውጪ ናቸው በማለት ያቀረበው ክርክር በአመልካች በኩል ያልተካደ ከመሆኑ አኳያ አመልካች ጉዲዬ በገለልተኝት ላታይ አይችልም በማለት ያቀረቡት ምክንያት ተቀባይነት አለው ቢባል እንኳን ጉዲዩን የሚያዩት ዳኞች ከችልት እንዱነሱ በሚቀርብ አቤቱታ መነሻነት ክሱ በዚያው ፍርድ ቤት ውስጥ በሚገኝ ላላ ችልት ላይ በሚያስችለ ዳኞች እንዱታይ ከሚደረግ በቀር በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውስጥ ያለት ዳኞች በሙለ የአመልካችን ጉዲይ በገለልተኝነት እንደማያዩ ተቆጥሮ ክሱ ወደ ላላ ሥፍራ እንዱዛወር ማድረግ ፍርድ ቤቶች በሕገመንግስቱ የተጣለባቸውን ግዳታ አክብረው ነጻ እና ገለልተኛ ሆነው ጉዲዮችን ይዲኛለ በሚል በሕዝብ ዘንድ ያላቸውን አመኔታ በእጅጉ የሚሸረሽር በመሆኑ ተቀባይነት ሉኖረው አይገባም።
ሲጠቃለል አመልካች ክስ ወደ ላላ ሥፍራ ይዛወርልኝ በማለት ላቀረቡት አቤቱታ የጠቀሷቸው ምክንያቶች ሕጋዊ መሰረት የላላቸው እና በተጨባጭ ማስረጃ ያልተረጋገጡ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤቶች ይህንኑ መሰረት በማድረግ የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ የሰጡት ውሳኔ በአግባቡ ነው ከሚባል በቀር የተፈጸመ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት አላገኘንበትም። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ውሳኔ በአብላጫ ድምጽ ሰጥተናል።
በደቡብ ብሓሮች ብሓረሰቦች እና ሕዝቦች ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ. መስከረም 06 ቀን 2012 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፤ ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ. ታሕሳስ 01 ቀን 2012 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1 መሰረት ጸንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻለ።
ጥር 21 ቀን 2012 ዓ.ም በመዝገቡ የተሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል። ይጻፍ