በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.184 መሰረት የትዕዛዝ ይግባኝ የላለ ስለመሆኑ የተደነገገ ቢሆንም የተሰጠው ትዕዛዝ ወደፉት በዋናው ጉዲይ ላይ ከሚቀርበው ይግባኝ ጋር ተጠቃል ላቀርብ የማይችልና ውጤቱም የሚቀለበስ ካልሆነ በጊዜያዊ ትዕዛዝ ላይ የተሰጠ ይግባኝ ነው በሚል ተቃውሞ የማይቀርብበትና በይግባኝ የሚታይ ስለመሆኑ ለእስረኞች የሕክምና አገልግልት የሚሰጠው በማረሚያ ቤት ውስጥ በተዘጋጀ የጤና ተቋም ቢሆንም በሕግ ጥላ ስር የሚገኝ ተጠርጣሪ በጤና ተቋሙ ለመታከም እምነት የላለው በመሆኑ በመረጠው የግል የሕክምና ተቋም አገልግልት እንዱያገኝ በጠየቅ ጊዜ ይህንን ለማከናወን የፀጥታ ስጋት ቢኖርም መንግስት ጸጥታ እና ደሕንነትን በማስጠበቅ ተጠርጣሪው ህክምናውን እንዱያገኝ ሉያመቻች የሚገባ ስለመሆኑ የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግሰት አንቀጽ 22/1፣ አዋጅ ቁጥር 1174/2012 እነ አቶ ጀዋር ሲራጅ መሐመድ (4 ሰዎች) እና የፋዳራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ
No summary available.
የሰ.መ.
የካቲት 22 ቀን 2013 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሣዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካቾች፡-
የሰበር አቤቱታው ላቀርብ የቻለው አመልካቾች በጠበቆቻቸው አማካኝነት የካቲት 18 ቀን 2011 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ.
በቀን 16/06/2013 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት አቤቱታ በማቅረባቸው ነው።
ጉዲዩ በሕግ ጥላ ስር የሚገኝን እስረኛ ሕክምና ጉዲይ የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው። አመልካቾች በጠበቆቻቸው አማካኝነት ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የካቲት ባቀረቡት አቤቱታ የግል ሐኪሞቻቸው በአስቸኳይ ሆስፒታል ሄደው መታከም እንዲለባቸው ያሳወቁ ቢሆንም ማረሚያ ቤቱ አመልካቾች የግል ሐኪም ቤት ሄደው እንዲይታከሙ በመከልከለ ምክንያት ሕክምናቸው የተቋረጠ እና ለከፍተኛ አደጋ የተጋለጡ መሆኑን በመግለጽ ማረሚያ ቤቱ አመልካቾች በመረጡት የግል የጤና ባለሙያ እና የሕክምና ተቋም የሕክምና አገልግልት እንዱያገኙ ትዕዛዝ ይሰጥላቸው ዘንድ ዲኝነት ጠይቀዋል።
ጉዲዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት የአመልካቾችን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ጠበቆቻቸውን በችልት አስቀርቦ ከጠየቀ በኋላ ማረሚያ ቤቱ የካቲት 02 ቀን 2013 ዓ.ም ባመለከተው መሰረት አመልካቾች ለመታከም ፈቃደኛ ካልሆኑ እና የሚጠቅሱት ሆስፒታል ለሕዝብ እና ለደህንነት ስጋት የሚፈጥር ከሆነ ጦር ሀይልች ሆስፒታል እንዱያሳክማቸው ያዘዘ ሲሆን በዛሬው እለት አመልካቾች የግል ሐኪም ቤት በመግለጽ ሕክምና እንዱደረግላቸው የጠየቁ እና የሕክምና ማዕከለ የታወቀ በመሆኑ ማረሚያ ቤቱ አመልካቾችን አዱስ አበባ ከተማ ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው ላንድ ማርክ ጄነራል ሆስፒታል በአጃቢ አስፈላጊውን ጥበቃ ተደርጎ ሕክምና እንዱደረግላቸው እንዱወስዲቸው ሲል ትዕዛዝ ሰጥቷል።
ተጠሪ ይህን ውሳኔ በመቃወም ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የይግባኝ አቤቱታ አቅርቧል። ይግባኙ የቀረበለት ፍ/ቤት ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ ኢትዮጲያ የተቀበለቻቸውን አለም አቀፍ ስምምነቶች እና ሕገ መንግስቱን መሰረት በማድረግ በጉዲዩ ላይ ሰፉ ትችት ከሰጠ በኋላ አዋጅ ቁጥር 1174/2012 እስረኞች ወደ ግል ሆስፒታል እንዲይሄደ ገደብ ያልጣለ እና ገደቡ ከመንግስት አቅም እና የማሟላት ግዳታ አኳያ ብቻ እንጂ ከእስረኞች የግል አቅም አኳያ የማይገደብ መሆኑን በመግለጽ ተጠሪ አመልካቾች በግል ሕክምና ተቋም አገልግልት እንዲያገኙ የሚያቀርበው ክርክር ተቀባይነት የለውም፤ በልላ በኩል ተጠሪ ከጸጥታ ችግር አኳያ የሚያቀርበው ክርክር ዝቅተኛ ግምት ሉሰጠው አይገባም፤ አመልካቾች ከተከሰሱበት የእርስ በእርስ ግጭት ማስነሳት አኳያ እና ዓቃቤ ሕግ በይግባኙ ላይ ካቀረበው ለሕብረተሰብ እና ለአመልካቾች የደህንነት እና የጸጥታ ስጋት እንዱሁም ከነባራዊው ሁኔታ አኳያ ለአመልካቾች እና ለሕብረተሰቡ ደህንነት ሲባል በላንድ ማርክ ሆስፒታል የሕክምና አገልግልት እንዱያገኙ የተሰጠው ትዕዛዝ አማራጭ የለውም፤ የሕክምና አገልግልት በታካሚው ዘንድ ተቀባይነት ያለው እና የሚፈለገውን ውጤት የሚያመጣ መሆን አለበት፤ በመረጡት ሐኪም ሕክምና ማግኘት የታካሚው መብት ከመሆኑ አኳያ ያለፍላጎታቸው ይልቁንም ከፍተኛ ስጋት ያላቸው በመሆኑ በመንግስት የሕክምና ተቋም አገልግልት እንዱያገኙ ማድረግ ተመራጭ አይደለም፤
ስለሆነም ከግራ ቀኙ ከተነሳው ክርክር አኳያ አመልካቾች የመረጡት የላንድ ማርክ ሆስፒታል ፈቃደኝነት እና ፍላጎት መሰረት ባደረገ መልኩ የህክምና ሙያው በሚፈቅደው ደንብ መሰረት የሀኪሞች ቡድን በማደራጀት አመልካቾች ባለበት በቃሉቲ ማረሚያ ቤት ውስጥ ሙለ የሕክምና አገልግልት እንዱሰጣቸው በማለት ወስኗል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም መሰረታዊ የሕግ ስሕተት ተፈጽሞበታል በሚል ሲሆን ይዘቱም፡- ዓቃቤ ሕግ ለስር ይግባኝ ሰሚው ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረበው ይግባኝ በጊዜያዊ ትዕዛዝ ላይ የቀረበ በመሆኑ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 184 መሰረት ተቀባይነት የለውም፤ ተጠሪ የመጀመሪያው ትዕዛዝ ከተሰጠ በኋላ በ15 ቀን ውስጥ ይግባኝ እንደሚል ያላሳወቀ በመሆኑ ያቀረበው ይግባኝ በጊዜ ገደብ የሚታገድ ነው፤ የስር ይግባኝ ሰሚው ጠቅላይ ፍርድ ቤት የደህንነት ችግር መኖሩን በማስረጃ ሳያረጋግጥ በላንድ ማርክ ሆስፒታል የህክምና አገልግልት ቢሰጣቸው በአመልካቾች ላይ የጸጥታ ስጋት ይፈጠራል ማለቱ አግባብ አይደለም፤ አመልካቾች በመረጡት የግል ሐኪም የመታከም ሕገ-መንግስታዊ መብት አላቸው፤ የላንድ ማርክ ሆስፒታል ለንግድ የተቋቋመ እና በአንድ ቦታ የቆመ ድርጅት ሆኖ ሳለ ሆስፒታለ ተነቅል ቃሉቲ ማረሚያ ቤት እንዱገባ የተሰጠው ትእዛዘ አግባብ አይደለም፤ አመልካቾች በሚገኙበት ማረሚያ ቤት ሕክምናውን እንዱያገኙ ቢደረግ የተለያዩ የሕክምና መሳሪያዎች የሚያስፈልጉ ሲሆን እነዚህ መሳሪያዎች ደግሞ ለሕክምና በሚያመች መልኩ በሕክምና ተቋሙ ውስጥ የሚገኙ እንጂ እየተነቀለ የሚሄደ አይደለም፤ ላንድ ማርክ ሆስፒታል ማረሚያ ቤት ድረስ በመሄድ ለአመልካቾች ሕክምና መስጠት እንደማይችል ያሳወቀ በመሆኑ የስር ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሰጠው ሉፈጸም የማይችል ውሳኔ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የአመልካቾችን ሕክምና በተመለከተ የላንድ ማርክ ሆስፒታል የሀኪሞች ቡድን በማደራጀት ባለበት ማረሚያ ቤት ውስጥ የሕክምና አገልግልት እንዱሰጣቸው በማለት የመወሰኑን አግባብነት ከኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግሰት አንቀጽ 22/1 እና ከወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 184 ጋር በማገናዘብ ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ በዚህ ችልት እንዱታይ ተደርጓል። ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎም ግራ ቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የተጠሪ መልስ ይዘት በአጭሩ፡- አመልካቾች ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ የፍሬ ነገር ክርክር የሚመለከት በመሆኑ ይህ ችልት ጉዲዩን የማየት ስልጣን የለውም፤ በስር ፍርድ ቤት የተሰጠው ትዕዛዝ የአመልካቾችን የሕክምና ጉዲይ በሚመለከት የመጨረሻ ትዕዛዝ በመሆኑ በዋናው ጉዲይ ላይ ይግባኝ በሚቀርብ ጊዜ ተጠቃል የሚቀርብ አይደለም፤ በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 21/2 የታሰሩ ሰዎች ከሀኪሞቻቸው ጋር የመገናኘት መብት ያላቸው ቢሆንም በጥቅለ የተቀመጠ ነው፤ በፋዳራል ማረሚያ ቤት አዋጅ ቁጥር 1174/2012 አንቀጽ 37 መሰረት ለእስረኞች የሕክምና አገልግልት የሚሰጠው በማረሚያ ቤት ውስጥ የተዘጋጀ የጤና ተቋም ሲሆን በዚሁ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ 9 ላይ በማረሚያ ቤቱ የሚገኘው እስረኛ የጤና ሁኔታ በጤና ተቋሙ ከሚሰጠው የሕክምና አገልግልት አቅም በላይ የሆነ ሕክምና የሚጠይቅ ሲሆን በኮሚሽኑ በጤና ተቋሙ ባለሙያዎች በሚቀርብለት ሪፖርት መሰረት ወዱያውኑ ተገቢውን ጥበቃ በመመደብ እስረኛው ያስፈለገውን የሕክምና አገልግልት ላሰጥ ወደሚችል የመንግስት ሆስፒታል በመውሰድ አገልግልቱን እንዱያገኝ ያደርጋል ይላል፤ አመልካቾች በመንግስት ሕክምና እምነት የለንም በማለታቸው የግል ሐኪማቸው እንዱያክሟቸው ሲደረግ የቆየ ሲሆን በሕገ መንግስቱ የተሰጣቸው በግል ሐኪም የመጎብኘት መብት በማረሚያ ቤቱ ውስጥ ሆነው በግል ሐኪማቸው የመታየት መብትን የሚሰጥ ነው ከሚባል በቀር ያለባቸው የጤና ችግር በተቋሙ ከሚሰጠው የሕክምና አቅም በላይ መሆኑ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ በልላ የሕክምና ተቋም እንዱታከሙ የሚያደርግ አይደለም፤ ሕክምናውን የሚሰጠው የላንድ ማርክ ሆስፒታል ሕክምናውን ለመስጠት የተለያዩ መሳሪያዎችን ማጓጓዝ ይጠይቃል አላለም፤ ስለሆነም የስር ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ ሉጸና ይገባል የሚል ነው።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው። ይህ ችልትም በሰበር አጣሪው ችልት ሉጣራ ይገባዋል ተብል የተያዘውን ነጥብ ከግራ ቀኙ ክርክር፤ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምሮታል።
የአሁን ተጠሪ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የይግባኝ አቤቱታ ያቀረበው የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካቾች በመረጡት ላንድ ማርክ ሆስፒታል ሕክምና እንዱደረግላቸው በማለት የሰጠውን ትዕዝዝ በመቃወም ነው። በልላ በኩል ግራ ቀኙ በስር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤትም ሆነ በዚህ ችልት ካደረጉት ክርክር ይዘት መገንዘብ የቻልነው አመልካቾች በመረጥነው የግል ሐኪም ልንታከም ይገባል በማለት የሚከራከሩት በመንግስት የሕክምና ተቋም ብንታከም ከፍተኛ የሆነ ስጋት አለን በሚል ሲሆን ተጠሪ በበኩለ አመልካቾች በላንድ ማርክ ሆስፒታል /በግል የሕክምና ተቋም/ እንዱታከሙ ቢደረግ የጸጥታ ስጋት አለኝ የሚል መሆኑን ነው። ይህንኑ መሰረት በማድረግ ጉዲዩን እንደተመለከትነው በቅድሚያ ምላሽ ሉያገኝ የሚገባው ነጥብ አመልካቾች በላንድ ማርክ ሆስፒታል እንዱታከሙ ሲል የተሰጠው ትዕዛዝ ይግባኝ የሚባልበት ነው? ወይስ አይደለም? የሚለው ነው።
ዓቃቤ ሕግ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካቾች በላንድ ማርክ ሆስፒታል እንዱታከሙ ሲል የሰጠውን ትዕዝዝ በዋነኝነት የሚቃወመው የጸጥታ ችግር ሉፈጠር ይችላል በሚል በመሆኑ እንደ ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ትዕዝዝ ቢፈጸም እና ምናልባትም ዓቃቤ ሕግ ሉፈጠር ይችላል ብል የሰጋው የጸጥታ ችግር ቢከሰት ይህንኑ የተፈጠረውን የጸጥታ ችግር ወደፉት በዋናው ጉዲይ ላይ ከሚያቀርበው ይግባኝ ጋር አጠቃል ሉያቀርበው የሚችል ባለመሆኑ ውጤቱ የሚቀለበስ አይደለም። ስለሆነም ዓቃቤ ሕግ ይግባኝ የጠየቀበት ትዕዛዝ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 184 በተገለጸው አግባብ ይግባኝ የማይጠየቅበት ነው በማለት በአመልካቾች በኩል የቀረበው ክርክር ተቀባይነት ያለው አይደለም።
በልላ በኩል የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አመልካቾች በመረጡት ሐኪም ሕክምና ማግኘት የታካሚው መብት ከመሆኑ አኳያ ያለፍላጎታቸው ይልቁንም ከፍተኛ ስጋት ያላቸው በመሆኑ በመንግስት የሕክምና ተቋም አገልግልት እንዱያገኙ ማድረግ ተመራጭ አይደለም ከሚል መደምደሚያ ላይ ከደረሰ በኋላ ተጠሪ ከጸጥታ ችግር አኳያ የሚያቀርበው ክርክር ዝቅተኛ ግምት ሉሰጠው አይገባም በማለት አመልካቾች የመረጡት የላንድ ማርክ ሆስፒታል ፈቃደኝነት እና ፍላጎት መሰረት ባደረገ መልኩ የህክምና ሙያው በሚፈቅደው ደንብ መሰረት የሀኪሞች ቡድን በማደራጀት አመልካቾች ባለበት በቃሉት ማረሚያ ቤት ውስጥ ሙለ የሕክምና አገልግልት እንዱሰጣቸው በማለት የሰጠው ውሳኔ አግባብ መሆን አለመሆኑን ቀጥለን እንመልከት።
የዓቃቤ ሕግ ዋነኛ ስጋት አመልካቾች በመረጡት የላንድ ማርክ ሆስፒታል እንዱታከሙ ቢደረግ የጸጥታ ስጋት አለኝ የሚል መሆኑን በተለይም በስር ይግባኝ ሰሚው ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከተደረገው ክርክር ይዘት መገንዘብ ይቻላል። ይህ የዓቃቤ ሕግ ስጋት የመነጨው አንድም ዓቃቤ ሕግ ምናልባትም ሉፈጠር ይችላል በሚለው የጸጥታ ችግር ምክንያት ተጠሪጣሪዎቹ ቢያመልጡ ወይም በተጠርጣሪዎቹ ላይ አደጋ ቢደርስ በፍትሕ ስርዓቱ ላይ ሉያመጣ የሚችለውን አደጋ ከወዱሁ በመገመት መሆኑን ይህ ችልትም ይገነዘባል።
በመሰረቱ የመንግስት ዋነኛ ሚና የሕዝቦችን ሰላም እና ደህንነት ማረጋገጥ እና ማስጠበቅ ነው። በዚሁ መሰረት መንግስት በፍትሕ ስርዓቱ ውስጥ የሚያልፈ ተጠርጣሪዎች ሰላም እና ደህንነት የማስጠበቅ ግዳታ አለበት።ይህ ግዳታም ተጠሪጣሪዎቹ በማረሚያ ቤት በሚገኙበት ጊዜ፤ፍርድ ቤት በሚቀርቡበት እና ወደ ሕክምና ተቋማት በሚሄደበት ጊዜ ሁለ በጥብቅ ሉተገበር የሚገባው ነው። ይህን ካልን ዘንዲ በሕግ ጥላ ስር የሚገኝ ተጠርጣሪ ሕክምና ባስፈለገው ጊዜ ሁለ ሕክምና እንዱያገኝ መሟላት ያለባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች ሁለ ማሟላት ያለበት መንግስት እንደሆነ ከአዋጅ ቁጥር 1174/2012 ድንጋጌዎች ይዘት መገንዘብ ይቻላል።
በያዝነው ጉዲይ የስር ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት አመልካቾች በላንድ ማርክ ሆስፒታል ሉታከሙ ይገባል በማለት በሰጠው ውሳኔ ላይ ዓቃቤ ሕግ ለዚህ ችልት ያቀረበው ቅሬታ የለም። ይልቁንም ዓቃቤ ሕግ የአመልካቾች አቤቱታ ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት የሚከራከረው የጸጥታ ችግር ስጋት ሉኖር ይችላል በሚል ነው። በልላ በኩል ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ባስቀመጠው አማራጭ መሰረት ሕክምናውን እንዱያከናውን ትዕዛዝ የተላለፈለት የላንድ ማርክ ሆስፒታል ማረሚያ ቤት ድረስ ሄጄ አመልካቾችን አላክምም ብሎል በማለት በአመልካቾች በኩል የቀረበውን ክርክር በግልጽ በመካድ ከዓቃቤ ሕግ የተሰጠ ምላሽ የለም። ስለሆነም የስር ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የወሰደው አማራጭ ተፈጻሚ ላሆን የማይችል መሆኑን ይህ ችልት ግንዛቤ ወስዶል።
በልላ በኩል በአገራችን ባለው ነባራዊ ሁኔታ በማረሚያ ቤት የሚገኝ ተከሳሽ ወደ ሕክምና ተቋሙ ሄድ አገልግልቱን የሚያገኝበት አሰራር እንጂ የሕክምና ተቋሙ ራሱ በማረሚያ ቤት የሚገኝ ተከሳሽ ባለበት ማረሚያ ቤት ሕክምናውን ለመስጠት የሚያስችለ መሣሪያዎችን ይዞ በመሄድ ተንቀሳቃሽ ሕክምና ላሰጥ የሚችልበት አሰራር የላለ በመሆኑ እና በክርክሩ ተካፊይ ያልሆነን አካል በአማራጭ በተሰጠው ውሳኔ መሰረት በፈቃደኝነት ላይ ተመስርቶ የሕክምና ቡድኑን በመያዝ ሕክምናውን በማረሚያ ቤቱ ተቋም ሄድ ባይሰጥ ላላ አማራጭ ያልተቀመጠ በመሆኑ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ ሉፈጸም የማይችል እና መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ስለሆነም መንግስት ሉፈጠር ይችላል ያለውን የጸጥታ ስጋት ለማስወገድ ተገቢውን የጸጥታ እና ደሕንነት ማስጠበቅ ሃላፉነቱን በመወጣት አመልካቾች ቀድሞ በመረጡት የላንድ ማርክ ሆስፒታል ሕክምናውን እንዱያገኙ እንዱያደርግ በማለት ወስነናል። በዚህም ምክንያት ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ. በቀን 16/06/2013 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ተሻሽሎል።
መንግስት ሉፈጠር ይችላል ያለውን የጸጥታ ስጋት ለማስወገድ ተገቢውን የጸጥታ እና ደሕንነት ማስጠበቅ ሃላፉነቱን በመወጣት አመልካቾችን ቀድሞ በመረጡት የላንድ ማርክ ሆስፒታል ሕክምናውን እንዱያገኙ እንዱያደርግ በማለት ተወስኗል።
No topics extracted.