ከመጋረጃ ጀርባ እና በዝግ ችልት ምስክር ሉሰማ አይገባም በሚል የተሰጠ ውሳኔ ራሱን ችል ይግባኝ የሚቀርብበት እንጂ ከዋናው ጉዲይ ጋር ተጠቃል በይግባኝ የማይታይ ስለመሆኑ የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 184/መ፣ የወንጀል ምስክሮች እና ጠቋሚዎች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 699/2003 አንቀጽ 6/1/ለ እና 4/1/ የፋዳራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ እና እነ እስክንድር ነጋ /5 ሰዎች/
No summary available.
የሰ.መ.
የካቲት 10 ቀን 2013 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሣዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡- የፋዳራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ - ዐ.ህግ አብይ መርዕድ ቀረቡ ተጠሪዎች፡-
የሰበር አቤቱታው ላቀርብ የቻለው አመልካች ታሕሳስ 22 ቀን 2013 ዓ.ም ጽፍ ባቀረበው የሰበር አቤቱታ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ. ታሕሳስ 13 ቀን 2013 ዓ.ም የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 184/መ መሰረት ማስረጃ መቀበል ወይም አለመቀበል ላይ በሚሰጥ ትዕዛዝ ላይ ይግባኝ የማይባልበት በመሆኑ እና ይግባኝ የተባለበት ጉዲይ የማስረጃ አሰማም ሂደት ላይ የተሰጠውን ብይን በመቃወም የቀረበ ቅሬታ በመሆኑ ይግባኝ የሚባልበት አይደለም በማለት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት አቤቱታ በማቅረባቸው ነው።
የአሁን አመልካች በአሁን ተጠሪዎች ላይ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረበውን ክስ ለማስረዲት የቆጠራቸው ምስክሮች ስለ ወንጀል ምስክሮች እና ጠቋሚዎች ጥበቃ የወጣ አዋጅ ቁጥር 699/2003 አንቀጽ 6/1/ለ መሰረት ጥበቃ የተደረገላቸው መሆኑን በመግለጽ አስራ ስድስቱ ምስክሮች በአዋጁ አንቀጽ 4/1/ቀ መሰረት ምስክርነታቸው በዝግ ችልት እንዱሰማ፤ አምስቱ ምስክሮች ደግሞ በአዋጁ አንቀጽ 4/1/በ መሰረት በአካል ሳይታዩ ከመጋረጃ ጀርባ ሆነው እንዱመሰክሩ ይታዘዝለት ዘንድ ዲኝነት ጠይቋል።
ተጠሪዎች በሰጡት አስተያየት ኢትዮጲያ በፈረመቻቸው የተለያዩ ዓለም ዓቀፍ ሕጎችም ሆነ ሀይማኖትን መሰረት አድርገው አንድን ማሕበረሰብ በጅምላ በማጥቃት የሚፈጸሙ ወንጀልች ወይም ዘር ማጥፊት ተፈጽሞባቸዋል በተባለ የተለያዩ ዓለም አገራት ላይ እንኳን ዓቃቤ ሕግ በጠየቀው አግባብ በዝግ ችልት ወይም ከመጋረጃ ጀርባ ምስክር እንዱሰማ አልተደረገም፤ የምስክሮች ጥበቃ አዋጅ ጥበቃ ተጠቃሚውን ብቻ ሳይሆን የተከሳሾችንም መብት ከግምት ያስገባ ነው፤ ከመጋረጃ ጀርባ ምስክር ቢሰማ የተጠሪዎችን የመከላከል መብት የሚያጣብብ በመሆኑ ሉፈቀድ አይገባም፤ ፍርድ ቤቱ የሙግት ሂደቱ ሙለ ለሙለ በግልጽ ችልት እንዱታይ በማድረግ የማናቸውም ወገን ጥርጣሬ እና መላ ምት ተቀባይነት እንዲይኖረው የማድረግ ሃላፉነት ያለበት በመሆኑ ዓቃቤ ሕግ ምስክሮች በዝግ ችልት እና ከመጋረጃ ጀርባ ሆነው እንዱሰሙ ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
ጉዲዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት ግራ ቀኙ በምስክሮች አሰማም ሂደት ላይ ያቀረቡትን ክርክር ከመረመረ በኋላ ዓቃቤ ሕግ ምስከሮች በዝግ ችልት እና ከመጋረጃ ጀርባ እንዱሰሙለት ያቀረበው ምክንያት ምስክሮች ከተከሳሾች ጋር የቅርብ ትውውቅ እንዲላቸው እና ከዚህ በፉትም ማስፈራሪያ ደርሶባቸው ነበር በማለት ነው፤ ይህ ደግሞ የምስክሮችን ማንነት ቀድሞ መታወቁን የሚያረጋግጥ ነው፤ የምስክሮች ማንነት ከታወቀ ደግሞ የጥበቃውን አስፈላጊነት ወይም የዓቃቤ ሕግን ጥያቄ ዋጋ ያሳጣዋል፤ በልላ በኩል ዓቃቤ ሕግ ምስክሮች ከተከሳሾች ጋር የቅርብ ትውውቅ እንዲላቸው እና ከዚህ በፉትም ማስፈራሪያ ደርሶባቸው እንደነበር ከመግለጽ ውጪ በተጨባጭ ሉደርስባቸው የሚችል ከባድ አደጋ/ ስጋት እንዲለ በበቂ ሁኔታ አልተረጋገጠም፤ ስለሆነም የተጠሪዎችን ሕገ መንግስታዊ መብት በሚጥስ መልኩ ምስክሮች በዝግ ችልት እና ከመጋረጃ ጀርባ ይሰሙልኝ በማለት የቀረበው አቤቱታ በሕግ አግባብነት የላለው እና ትክክለኛ ፍትህ ለመስጠት የማያስችል በመሆኑ ተቀባይነት የለውም በማለት ውድቅ አደርጎታል።
አመልካች ይህን ብይን በመቃወም ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የይግባኝ አቤቱታ አቅርቧል። ይግባኙ የቀረበለት ፍ/ቤት የአመልካችን የይግባኝ አቤቱታ ከመረመረ በኋላ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 184/መ መሰረት ማስረጃ መቀበል ወይም አለመቀበል ላይ በሚሰጥ ትዕዛዝ ላይ ይግባኝ የማይባልበት በመሆኑ እና ይግባኝ የተባለበት ጉዲይ የማስረጃ አሰማም ሂደት ላይ የተሰጠውን ብይን በመቃወም የቀረበ ቅሬታ በመሆኑ ይግባኝ የሚባልበት አይደለም በማለት የአመልካችን የይግባኝ አቤቱታ ውድቅ አድርጎታል።
አመልካች ታሕሳስ 22 ቀን 2013 ዓ.ም ያቀረበው የሰበር አቤቱታ ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም መሰረታዊ የሕግ ስሕተት ተፈጽሞበታል በሚል ሲሆን ይዘቱም፡- የስር ከፍተኛው ፍርድ ቤት ምሰክሮች በዝግ ችልት እና ከመጋረጃ ጀርባ ሉሰሙ ይገባል በማለት ባቀረብነው አቤቱታ ላይ የሰጠው ብይን የመጨረሻ ልባል የሚችል እንጂ ጊዜያዊ ትዕዛዝ /interelocutory/ አይደለም፤ በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ የክርክሩን መቀጠል እና አለመቀጠል መወሰን በሚችል እና ተጠሪዎችን ማስረጃ ከመሰማቱ በፉት ነጸ ሉያስብል የሚችል በመሆኑ ስሕተት ነው፤ አመልካች ምስክሮች ከመጋረጃ ጀርባ ይሰሙልኘ በማለት ያቀረበው አቤቱታ ውድቅ በመደረጉ በምስክሮች አሰማም ቀጣይ ሂደት ላይ ይህን አቤቱታ በድጋሚ ለማቅረብ የሚችልበት እድል የለም፤ ክርክሩ ሲጠናቀቅም አጠቃል ሉያቀርበው የሚችለው ጉዲይ አይደለም፤ የምስክሮች ጥበቃ ጉዲይ ላይ የተሰጠ ብይን ይግባኝ የተከለከለባቸው ጉዲዮች ስር አይሸፈንም፤ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ.መ. ጊዜያዊ አገልግልት ስላላቸው እና የመጨረሻ ውጤት ስላላቸው ጉዲዮች አስገዲጅ የህግ ትርጉም ሰጥቶበታል፤
ይህ ውሳኔ በክስ ላሻሽል ጥያቄ ላይ የተሰጠ ቢሆንም የሕግ ትርጉሙን ለመስጠት መነሻ የሆነው ምክንያት ግን የትዕዛዝ ይግባኝ የተከለከለ መሆኑን አስመልክቶ የተደነገገውን የስነ ስርዓት ሕጉ መርህ ሉተረጎም ስለሚገባበት አግባብ በመሆኑ ለተያዘው ጉዲይ ተፈጻሚነት አለው፤ ስለሆነም የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አመልካች ይግባኝ የጠየቀበት ውሳኔ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 184/መ መሰረት ይግባኝ የሚባልበት አይደለም በማለት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ የምስክሮች አሰማም ከመጋረጃ ጀርባ እንዱሆን እና በዝግ ችልት እንዱታይ በዓቃቤ ሕግ የቀረበው ጥያቄ ውድቅ ተደርጎ የተሰጠው ትዕዛዝ ጊዜያዊ ስለሆነ ይግባኝ ልባልበት አይገባም ተብል በስር ፍርድ ቤት የመወሰኑን አግባብነት የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ.መ. ከሰጠው የሕግ ትርጉም እና ከአዋጅ ቁጥር 699/2003 እና ከወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 184 ጋር በማገናዘብ ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ በዚህ ችልት እንዱታይ ተደርጓል።
ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርጎም ግራ ቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
ከ1ኛ እስከ 4ኛ ያለት ተጠሪዎች በጠበቆቻቸው አማካኝነት የካቲት 04 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጡት የጽሐፍ መልስ ይዘት በአጭሩ፡- ሕገ መንግስቱ ካስቀመጠው ሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌዎች አንጻር እና ስለ ወንጀል ምስክሮች እና ጠቋሚዎች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 699/2003 ከወጣበት ዓላማ አንጻር ሲታይ ዓቃቤ ሕግ ምስክሮች በዝግ ችልት እና ከመጋረጃ ጀርባ እንዱሰሙለት ያቀረበውን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ ተገቢ ነው፤ በምስክሮች አሰማም አቤቱታ ላይ የተሰጠው ብይን በመዝገቡ ላይ የመጨረሻ ልባል የማይችል እና ጊዜያዊ ትዕዝዝ ነው፤ የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 184 በትዕዛዝ ላይ ይግባኝ ላቀርብ እንደማይችል ይደነግጋል፤ ዋናው ጉዲይ ሲጠናቀቅ ይግባኙን አጠቃል ለማቅረብ የሚያስችል ስርዓት በመኖሩ እንጭፍጫፉ በሆኑ ጉዲዮች ላይ ይግባኝ ማቅረብ ክርክሮች እንዱጓተቱ እና መጠናቀቅ በሚገባቸው ጊዜ እንዲይጠናቀቁ የማድረግ ውጤት ያለው በመሆኑ ተቀባይነት ሉኖረው አይገባም፤ ዓቃቤ ሕግ ምስክሮች በዝግም ችልት ሆነ ከመጋረጃ ጀርባ ባይሰሙ ማስረጃ ከመቅረቡ በፉት ተጠሪዎችን ነጻ ሉያስብል የሚችል ነው በማለት የሚከራከር ቢሆንም ማስረጃ ሳይቀርብ ቢቀር ወደፉት የማንቀሳቀስ መብት ተጠብቆ መዝገብ ይቋረጣል እንጂ ተጠሪዎችን ነጻ የሚያስብል አይደለም፤ በሰ.መ. የተሰጠው ውሳኔ በክስ ላሻሽል አቤቱታ ላይ የተሰጠ በመሆኑ ከጉዲዩ ጋር አግባብነት የለውም የሚል ነው።
5ኛ ተጠሪም በጠበቃው አማካኝነት የካቲት 09 ቀን 2013 ዓ.ም በሰጠው መልስ አላስመሰክርም ማለት የዓቃቤ ሕግ መብት ነው፤ ዓቃቤ ሕግ ምስክሮች የማቅረብ ግዳታውን መወጣት አለመፈለጉ ይግባኝ በማይባልበት ነጥብ ላይ ይግባኝ ለማለት ዕድል ሉፈጥርለት አይገባም በማለት የተከራከረ ሲሆን በላልች ነጥቦች ላይ ደግሞ ከ1ኛ እስከ 4ኛ ያለት ተጠሪዎች ከሰጡት መልስ ጋር ተመሳሳይ ይዘት ያለው መልስ ሰጥቷል።
አመልካችም የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው። ይህ ችልትም በሰበር አጣሪው ችልት ሉጣራ ይገባዋል ተብል የተያዘውን ነጥብ ከግራ ቀኙ ክርክር፤ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምሮታል።
ከመዝገቡ ይዘት መገንዘብ የቻልነው አመልካች ስለ ወንጀል ምስክሮች እና ጠቋሚዎች ጥበቃ የወጣ አዋጅ ቁጥር 699/2003 አንቀጽ 6/1/ለ እና 4/1/ቀ ድንጋጌን መሰረት በማድረግ በተጠሪዎች ላይ ያቀረበውን ክስ ለማስረዲት ከተቆጠሩት ምስክሮች ውስጥ ከፉልቹ በዝግ ችልት፤ ከፉልቹ ደግሞ ከመጋረጃ ጀርባ ሆነው እንዱመሰክሩ ይታዘዝልኝ በማለት ላቀረበው አቤቱታ የሰጠው ምክንያት ተጠሪዎች የተከሰሱበት ክስ በባሕሪው በሕብረተሰቡ እና በአገር ሰላም እና ደህንነት ላይ አደጋ የሚጥል እና ከባድ ወንጀል ነው፤ የምስክሮች ጥበቃ አዋጅም የዚህ ዓይነት ወንጀልች ላይ በምስክርነት የሚቀርቡ ሰዎች በልዩ ሁኔታ ጥበቃ እንደሚደረግላቸው ይደነግጋል፤ ምስክሮቹ ከተጠሪዎች ጋር የቅርብ ግንኙነት ያላቸው በመሆኑ ለጥቃት ይጋለጡብኛል፤ እንዱሁም ጉዲዩን ለመለከታተል በሚመጡ ባልደረቦቻቸው፤
ጓደኞቻቸው እና ዘመድ ቤተሰቦቻቸው ታይተው ለአደጋ የሚጋለጡበት ሁኔታ ይኖራል፤ ቀዲሚ ምርመራ በሚካሄድበት ጊዜም የግድያ ዛቻ የደረሰባቸው ምስክሮች አለ በሚል ነው።
ጉዲዩ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች ምስክሮች በዝግ ችልት እና ከመጋረጃ ጀርባ ሆነው እንዱሰሙ በማለት ያቀረበውን አቤቱታ ውድቅ ያደረገ ሲሆን ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ደግሞ የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 184/መ መሰረት በማድረግ አመልካች ያቀረበው የይግባኝ አቤቱታ ይግባኝ በሚባልበት ጉዲይ ላይ የቀረበ አይደለም በማለት ተጠሪዎችን ሳያስቀርብ ከወዱሁ ውድቅ አድርጎታል። ስለሆነም በዚህ ችልት ምላሽ ሉያገኝ የሚገባው የክርክሩ መሰረታዊ ነጥብ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች ምስክሮች በዝግ ችልት እና ከመጋረጃ ጀርባ ሉሰሙልኝ ይገባል በማለት ያቀረበውን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ የሰጠው ውሳኔ ይግባኝ የሚባልበት ነው? ወይስ አይደለም? የሚለው ነው።
የወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ሕግ በ1954 ዓ.ም የወጣ ሲሆን የትዕዛዝ ይግባኝ ስላለመኖሩ አስመልክቶ የተደነገገው የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 184 ድንጋጌ ፍርድ ቤቱ በቁጥር 94 መሰረት ቀጠሮ መስጠት ወይም አለመስጠትን፤ በቁጥር 131 መሰረት ስለሚቀርብ መቃወሚያ ወይም በቁጥር 146 መሰረት ማስረጃን ስለመቀበል ወይም ስላለመቀበል አስመልክቶ በሚሰጠው ትዕዛዝ ላይ ይግባኝ የተከለከለ መሆኑን፤ ነገር ግን የጥፊተኝነት ውሳኔ በተሰጠበት፤ ለጊዜው በመልቀቅ ወይም ነጻ በመልቀቅ ፍርድ ተሰጥቶ ይግባኝ በተባለበት ጊዜ እነዚህ የተሰጡት ትዕዛዞች ይግባኝ ለማለት ምክንያቶች ለመሆን ይችላለ በማለት ይደነግጋል።
የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 184 በዋናው የስረ ነገር ክርክሩ ላይ ከሚሰጠው ፍርድ በፉት የትዕዛዝ ይግባኝ ክልከላ የተጣለባቸውን ጉዲዮች የሚዘረዝር ሲሆን ስለ ወንጀል ምስክሮች እና ጠቋሚዎች ጥበቃ የወጣ አዋጅ ቁጥር 699/2003 የወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ሕጉ ከወጣ አራት አሰርት ዓመታት ካለፈ በኋላ የወጣ እንደ መሆኑ መጠን በአዋጁ የተካተቱትን መብቶች አስመልክቶ ፍርድ ቤቶች በሚሰጧቸው ትዕዛዞች ላይ ስለሚኖረው የይግባኝ ስርዓት በመደበኛው የወንጀል ስነ ስርዓት ሕጉ ድንጋጌዎች ላይ ተካተው አናገኛቸውም። ስለሆነም በዝግ ችልት ወይም ከመጋረጃ ጀርባ ምስክር ሉሰማ አይገባም ተብል የተሰጠው ብይን በእርግጥም ይግባኝ የማይባልበት ጊዜያዊ ትዕዛዝ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ለመለየት የስነ ስርዓት ሕጉ በጊዜያዊ ትዕዛዝ ላይ ይግባኝ ከከለከለበት ምክንያት እና ዓላማ ጋር ተገናዝቦ ምላሽ ሉሰጠው ይገባል።
በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 184 ላይ የትዕዛዝ ይግባኝ የተከለከለበት ምክንያት የተሰጠው ትእዛዝ ከዋናው ጉዲይ ጋር ተጠቃል ላቀርብ የሚችል እና አቤት ባዩም ወደፉት አጠቃል በሚያቀርበው ጉዲይ ላይ መፍትሄ ሉያገኝበት የሚችል ሲሆን እንደሆነ ከድንጋጌው ይዘት መገንዘብ ይቻላል። ይህም የድንጋጌው ዓላማ ፍርድ ቤቶች በሚሰጧቸው ጊዜያዊ ትዕዛዞች በሙለ ይግባኝ እየጠየቁ የፍትሕ ስርዓቱን እንዱጓተት ከማድረግ ይልቅ አቤት ባዩ ዋናውን ጉዲይ በሚመለከት ከሚያቀርበው ጉዲይ ጋር ተጠቃለው መፍትሓ ሉያገኙ የሚችለ ጉዲዮች በዚያው ተጠቃለው እንዱቀርቡ በማድረግ የተቀላጠፈ የፍትህ ስርዐት እንዱኖር ማድረግ መሆኑን የሚያሳይ ነው።
በያዝነው ጉዲይ አመልካች ምስክሮች በዝግ ችልት ወይም ከመጋረጃ ጀርባ እንዱሰሙ በማለት ያቀረበውን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ በስር ከፍተኛው ፍርድ ቤት የተሰጠው ብይን አመልካች ጥበቃ ያስፈልጋቸዋል፤ ዛቻ እና ማስፈራሪያ ደርሶባቸዋል በማለት ከመጋረጃ ጀርባ እና በዝግ ችልት እንዱሰሙ ጥያቄ ያቀረበባቸው ምስክሮች በግልጽ ችልት እንዱሰሙ የማድረግ ውጤት ያለው በመሆኑ ምስክሮች ከተሰሙ በኋላ ይግባኝ የሚጠየቅበት እና ለክርክር የሚቀርብ ጉዲይ አይለም። ስለሆነም የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች ምስክሮች በዝግ ችልት እና ከመጋረጃ ጀርባ እንዱሰሙ ያቀረበውን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ የሰጠው ትዕዛዝ መታየት ያለበት ትዕዛዝ ነው ከሚል መነሻ ብቻ ሳይሆን ከውጤቱም አኳያ ላሆን ይገባል።
በመሆኑም የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 184/መ መሰረት ማስረጃ መቀበል ወይም አለመቀበል ላይ በሚሰጥ ትዕዛዝ ላይ ይግባኝ የማይባልበት በመሆኑ እና ይግባኝ የተባለበት ጉዲይ የማስረጃ አሰማም ሂደት ላይ የተሰጠውን ብይን በመቃወም የቀረበ ቅሬታ በመሆኑ ይግባኝ የሚባልበት አይደለም በማለት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ. ታሕሳስ 13 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ተሽሯል።
አመልካች ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ያቀረበው ጉዲይ በጊዜያዊ ትዕዛዝ ላይ የቀረበ ሳይሆን የመጨረሻ ውጤት ባለው ብይን ላይ የቀረበ በመሆኑ ይግባኝ የሚባልበት ነው በማለት ወስነናል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በውሳኔ የዘጋውን መዝገብ በማንቀሳቀስ አመልካች ያቀረበውን የይግባኝ ክርክር መርምሮ ተገቢውን እንዱወስን በማለት ጉዲዩ ተመልሶለታል።
በዚህ መዝገብ ጥር 25 ቀን 2013 ዓ.ም በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ. ምስክር ለመስማት የተጀመረው ሂደት እንዲይቀጥል በማለት የተሰጠው የእግድ ትዕዛዝ ተነስቷል፤ ይጻፍ
No topics extracted.