ከውል ውጪ በሆነ ኃላፉነት ለደረሰ ጉዲት እንዱከፈል የሚወሰን ካሳ በተቻለ መጠን ከደረሰው ጉዲት ጋር እኩል ሆኖ የሚመዛዘን መሆን ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2090/1 እና 2091 ኢንሹራንስ ሰጪዎች ቅሪት አካለ እንዱሰጣቸው ወይም የቅሪት አካለ ግምት ከካሳው ላይ እንዱቀነስ በሚል የሚያቀርቡት ክርክር ካሳው ከደረሰው ጉዲት ጋር እኩል መሆን አለበት በሚል መከራከሪያ ማእቀፍ ውስጥ ላታይ የሚገባ እንጂ ዲኝነት ተከፍል የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ መቅረብ አለበት የሚባል ክርክር ስላለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 234 (1/ረ)
No summary available.
የሰ/መ/ ጥር 23 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ ተሾመ ሽፈራዉ ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግሥቱ ነጻነት ተገኝ አመልካች፡- የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ተጠሪ፡- ሳምራዊት ጫኔ መዝገቡ ተመርምሮ ከዚህ የሚከተለዉ የፍርድ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ ከዉል ዉጭ የሆነ ኃላፉነት መነሻ ያደረገ ካሣ አወሳሰን የሚመለከት ነዉ።የአሁን ተጠሪ በስር ተከሳሽ አቶ በላይ ባህሩ ላይ በሰሜን ወል ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ የአሁን አመልካች በተከሳሽ ጠያቂነት ጣልቃ ገብቶ የተከራከረ ሲሆን የክሱም አጭር ይዘት ንብረትነቱ የስር ተከሳሽ የሆነ ተሽከርካሪ በተቃራኒ አቅጣጫ ሲጓዝ የነበረዉን የሰላዲ ቁጥር 3-88863 የሆነዉን የተጠሪን አይሱዙ ተሽከርካሪ ገጭቶ ጉዲት ስላደረሰ ጉዲት የደረሰበትን ተሽከርካሪ ለማስጠገን የወጣዉን ብር 495,000.00 ካሳ እንዱከፍለኝ ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል።
የስር ተከሳሽ ጉዲቱ የደረሰዉ በእኔ ተሽከርካሪ ጥፊት ባለመሆኑ ለደረሰዉ ጉዲት ኃላፉነት እንደላለባቸዉና የተጠየቀዉም ካሳ የተጋነነ እንደሆነ በመግለጽ ከመከራከራቸዉም በተጨማሪ የአሁን አመልካች ለተሽከርካሪያቸዉ የመድን ሽፊን እንደሰጠ በመግለጽ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 43 መሰረት በክርክሩ ጣልቃ ገብቶ እንዱከራከር እንዱወሰንላቸዉ በመጠየቅ ተከራክረዋል።የአሁን አመልካችም በክርክሩ ጣልቃ ገብቶ ባቀረበዉ ክርክር ለደረሰዉ ጉዲት ደንበኛዉ ኃላፉነት እንደላለባቸዉ፣ ኃላፉነት አለባቸዉ የሚባል ከሆነም በሁለት ተሽከርካሪዎች ግጭት ምክንያት የደረሰ ጉዲት በመሆኑ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2084 መሰረት ተጠሪ የራሳቸዉን ይችላለ እንጂ ደንበኛዉ ኃላፉነት እንደላለባቸዉ፤ደንበኛቸዉ ኃላፉ እንደሆኑ የሚወሰን ከሆነ ጉዲት የደረሰበት ተሽከርካሪ ቅሪት ለጣልቃ ገብ ሉመለስ ይገባል።የማይመለስበት ምክንያት ካለ የቅሪቱ ግምት ከካሳዉ ላይ ተቀናሽ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክሯል።
ፍርድ ቤቱም በመ/ ላይ የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃዎች ሰምቶና መርምሮ በቀን 18/07/2011ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ በተጠሪ ተሽከርካሪ ላይ ለደረሰዉ ጉዲት የስር ተከሳሽ (የአመልካች ደንበኛ) ኃላፉነት አለባቸዉ በማለት ተጠሪ ለተሽከርካሪያቸዉ ማስጠገኛ ያወጡትን ወጪ ብር 495,000.00 ለተጠሪ እንዱከፍለ ወስኗል።እንዱሁም ከዚህ ገንዘብ ላይ በመድን ዉለ መሰረት አመልካች ብር 100,000.00 ለተጠሪ እንዱከፍለ ወስኗል።አመልካች በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርቦ ፍርድ ቤቱ በመ/8 ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ በቀን 09/04/2013ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ አመልካች ቅሪት አካለ እንዱመለስለት ወይም ከጉዲት ገንዘቡ ላይ እንዱቀነስለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 234(1/ረ እና ሰ) እና 215/2 መሰረት ዲኝነት በመክፈል የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ በመመስረትና ዲኝነት በመክፈል ያቀረበዉ ክስ ባለመኖሩ የጠየቅሁት ዲኝነት በዝምታ ታልፍብኛል በማለት ያቀረበዉ ይግባኝ ተቀባይነት የለዉም በማለት የሥር ፍርድ ቤትን ዉሳኔ አጽንቷል።
አመልካች በቀን 08/07/2013ዓ/ም የተጻፈ አቤቱታ ያቀረበዉ ከላይ በተመለከተዉ መሰረት በተሰጠ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን የአቤቱታዉ ይዘት በአጭሩ፡- በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2090 እና 2091 እንደተደነገገዉ የሚከፈለዉ የጉዲት ካሳ ከደረሰዉ ጉዲት ጋር ተመጣጣኝ መሆን አለበት። ከተጠየቀዉ የጉዲት ካሳ ላይ የቅሪቱ ተቀናሽ የማይደረግ ከሆነ የሚከፈለዉ ካሳ ከደረሰዉ ጉዲት በላይ ይሆናል።አመልካች ቅሪቱ ሉመለስ ወይም ከሚከፈለዉ ካሳ ላይ ሉቀነስ ይገባል ብል ሲከራከር አዱስ ዲኝነት እየጠየቀ ሳይሆን ካሳዉ ተመጣጣኝ መሆን አለበት በማለት መከራከር በመሆኑ ዲኝነት ከፍል የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ እንዱያቀርብ ማቅረብ የሚገባዉ አይደለም።ስለሆነም የስር ፍርድ ቤት የቅሪት አካለ ግምት ብር 95,000-100,000.00 ድረስ እንደሆነ በባለሙያ አስገምቶ ካረጋገጠ በኋላ ይህንን ሳይቀንስ ካሳ መወሰኑ ተጠሪ ከሚገባቸዉ በላይ ካሳ እንዱከፈላቸዉና ከደረሰዉ ጉዲት እንዱያተርፈ የሚያደርግ በመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ።ስለሆነም ለተጠሪ ከተወሰነላቸዉ ካሳ ላይ ብር 95,000.00 ተቀናሽ እንዱደረግ ይወሰንልኝ በማለት አቤቱታዉን አቅርቧል።
የሰበር አጣሪ ችልት አቤቱታዉን መርምሮ የስር ፍርድ ቤት አመልካች የቅሪት አካለ እንዱመለስ ወይም ግምቱ ከካሳዉ ላይ እንዱቀነስ ያቀረበዉን ክርክር የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ አላቀረበም በማለት ዉድቅ ማድረጉ ሕጋዊ መሆን አለመሆኑ ተጠሪ ባለበት እንዱመረመር ትእዛዝ በመስጠቱ ተጠሪ ቀርበዉ እንዱከራከሩ በቀን 01/11/2013ዓ/ም በታተመ አዱስ ዘመን ጋዜጣ ላይ በወጣ መጥሪያ ጥሪ ተደርጎላቸዉ ስላልቀረቡ መልስ የመስጠት መብታቸዉ ታልፍ በላለበት ተመርምሯል።
ከዚህ በላይ አጠር ባለመልኩ የተገለጸዉ በስር ፍርድ ቤቶች በግራ ቀኙ የቀረበዉን ክርክር፣ በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ዉሳኔዎች እና የሰበር አቤቱታ ይዘት የሚመለከት ሲሆን እኛም በአመልካች ክርክር መሰረት ጉዲት የደረሰበት ተሽከርካሪ ቅሪት አካላት የሚመለሱት ወይም ተጠሪ ከጠየቁት ካሳ ላይ ግምቱ ተቀናሽ የሚሆነዉ አመልካች ዲኝነት ከፍል የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ አቅርቦ ሲከራከር ነዉ በሚል ዉድቅ ተደርጎ በመወሰኑ በዚህ ችልት ደረጃ ሉታረም የሚችል መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ መርምረናል።
እንደመረመርነዉም ለክርክሩ መሰረት የሆነዉ ምክንያት የአመልካች ደንበኛ የሆኑት የስር ተከሳሽ ንብረት የሆነ ተሽከርካሪ የተጠሪን ተሽከርካሪ ገጭቶ ጉዲት አድርሷል የሚል በመሆኑ በተጠሪና በአመልካች ደንበኛ(በስር ተከሳሽ) መካከል የነበረዉ ግንኙነት ከዉል ዉጭ የሆነ ነዉ።አመልካችም በክርክሩ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 43 መሰረት ጣልቃ እንዱገባ የተደረገዉ በስር ተከሳሽ ተሽከርካሪ ለሚደርስ ጉዲት የመድን ሽፊን በመስጠተ ተጠሪ እንዱከፈላቸዉ ከጠየቁት ካሳ ላይ አመልካች በኢንሹራንስ ዉለ መሰረት መክፈል የሚገባዉ ድርሻ አለ በሚል ምክንያት ነዉ።
ተጠሪ ባቀረቡት ክስ የስር ተከሳሽ ተሽከርካሪ ተሽከርካሪያቸዉን ገጭቶ ያደረሰዉን ጉዲት ለማስጠገን ባወጡት ወጪ መነሻ ብር 495,000.00 ጉዲት እንደደረሰባቸዉ በመግለጽ ብር 495,000.0 ካሳ እንዱከፈላቸዉ ነዉ።የስር ፍርድ ቤትም የስር ተከሳሽንና የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ መርምሮ ተጠሪ ጉዲት የደረሰበትን ተሽከርካሪያቸዉን ለማስጠገን ላወጡት ወጪ የስር ተከሳሽ ብር 495,000.00 ካሳ እንዱከፍለ ወስኗል።በዚህ አጠቃላይ የካሳ መጠን ላይ የቀረበ ክርክር የለም። የስር ተከሳሽ ለተጠሪ እንዱከፍለ ከተወሰነዉ ከተጠቀሰዉ የካሳ ገንዘብ ላይ አመልካች በኢንሹራንስ ዉለ መሰረት ብር 100,000.00 እንዱከፍለ በመወሰኑም ከመድን ሽፊኑ በላይ ባለመሆኑ የቀረበ ክርክር የለም።ግራ ቀኙን ያከራከረዉ አመልካች ጉዲት የደረሰበት ተሽከርካሪ ቅሪት አካላት ተጠሪ ሉመልሱ ወይም ከሚከፈላቸዉ ካሳ ላይ ግምቱ ሉቀነስ ይገባል በማለት ያቀረበዉን ክርክር በተመለከተ የተሰጠዉን ዉሳኔ የሚመለከት ነዉ።ከዚህ አንጻር የቀረበዉን ክርክር በተመለከተ የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዝምታ ያለፈ ሲሆን ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተዉ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ደግሞ አመልካች ዲኝነት በመክፈል የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ባለማቅረቡ ከቅሪት አካል አንጻር አመልካች ያቀረበዉን ክርክር የስር ፍርድ ቤት በዝምታ ማለፈ ተገቢ ነዉ ሲል ይግባኙን ዉድቅ አድርጓል።
እንደሚታወቀዉ የጉዲት ካሳ የሚከፈልበት ዓላማ ጉዲት የደረሰበትን ተበዲይ (ነገር) ጉዲት ከመድረሱ በፉት ወደ ነበረበት ስፍራ ለመመለስ እንጂ ተጎጂዉ ከጉዲቱ እንዱያተርፍ ለማድረግ አይደለም። ወደዚህ አጠቃላይ ድምዲሜ ላይ ለመድረስ የሚያስችል ተቀባይነት ያለዉ የካሳ አከፊፈል መሰረታዊ መርህ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2090/1 እና 2091 ላይ ተደንግጓል።ይኸዉም በአንድ ጉዲት ምክንያት የሚከፈለዉ ካሳ ከደረሰዉ ጉዲት ጋር እኩል ሆኖ የሚመዛዘን መሆን እንዲለበት ወይም ደግሞ ለአንድ ጉዲት ኃላፉ የሆነዉ ሰዉ የሚከፍለዉ የጉዲት ካሳ ኃላፉነቱ ያመጣዉ ጉዲት በተበዲዩ ላይ ካደረሰዉ ጉዲት ጋር እኩል ሆኖ መመዛዘን እንዲለበት የሚያስገድድ ነዉ።ይህንን መርህ በአግባቡ ተግባራዊ ማድረግ የጉዲት ካሳ ጠያቂዉ ከጉዲቱ አትራፉ እንዲይሆን ያደርጋል። በዚህ መሰረት ጉዲት የደረሰበት ተሽከርካሪ አካላት በልላ አካላት ተተክቶ የሚጠገን ከሆነ ጉዲት የደረሰባቸዉ ቅሪቶች ዋጋ ሉያወጡ የሚችለ ስለሚሆኑ ሉገመቱና ግምታቸዉ ከሚከፈለዉ ካሳ ላይ ሉቀነስ ወይም ቅሪት አካላት በአይነት ለካሳ ከፊዩ ሉመለሱ ይገባል። ይሕ የማይሆን ከሆነና በንብረቱ ላይ ጉዲት የደረሰበት ሰዉ ቅሪቱን የማይመልስ ወይም ግምቱ ከሚከፈለዉ ካሳ ላይ የማይቀነስ ከሆነ ለተጎጂዉ የሚከፈለዉ ካሳ ከደረሰዉ ጉዲት ጋር እኩል ሆኖ የሚመዛዘን መሆን አለበት የሚለዉ መርህ እንዱጣስና ተጎጂዉ መካስ ከሚገባዉ በላይ ካሳ በማግኘት ከጉዲቱ እንዱያተርፍ የሚያደርግ ይሆናል።
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 242 መሰረት የታመነ ፍሬ ነገር ነዉ በሚል ዉሳኔ ካልተሰጠ በስተቀር በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 246 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሰረት ተከራካሪ ወገኖች ተካክደዉ የተከራከሩባቸዉ የፍሬ ነገር ወይም የሕግ ጭብጥ ሉለይ ይገባል።እንዱሁም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 182/3 ስር እንደተደነገገዉ ከክርክሩ ላይ ከቀረቡት ብዙ ጭብጦች አንደ ጭብጥ ብቻ ቢወሰን ላልችም ጭብጦች ላይ ተጠቃል ዉሳኔ እንደተሰጠ የሚያስቆጥር ሁኔታ ካልተፈጠረ በስተቀር አከራካሪ ሆነዉ የተያዙ ጭብጦችን ሁለ በተናጠል በመመርመር በማስረጃ ሉረጋገጥ የሚገባዉ በማስረጃ እንዱረጋገጥ ተደርጎ እንዱሁም የሕግ ጭብጥ ደግሞ በተገቢዉ ሕግ ላይ ተመስርቶ ተገቢዉ ምክንያት ተስጥቶባቸዉ ሉወሰኑ ይገባል።ከዚህ አንጻር የተያዘዉን ጉዲይ ስንመለከት የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአመልካች በግልጽ ክርክር በቀረበዉ ቅሪት አካለን በሚመለከተዉ ጉዲይ ላይ ከተጠሪ በኩል የቀረበዉን ክርክር መሰረት በማድረግ ተገቢዉን ጭብጥ በመያዝ አጣርቶ ግልጽ ዉሳኔ መስጠት ሲገባዉ በዝምታ ማለፈ የክርክር አመራርና የፍርድ አሰጣጥ ጉድለት በመሆኑ ሉታረም የሚገባዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ ብለናል።
እንዱሁም ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተዉ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤት ከላይ በተመለከተዉ መሰረት የፈጸመዉን ስህተት ማረም ሲገባዉ እና የአመልካችን ክርክር በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2090/1 እና 2091 አንጻር በማየት ተገቢዉን መወሰን ይገባዉ ነበር።ሆኖም አመልካች በመከላከያ መልሱ ያቀረበዉ ክርክር ለተጠሪ የሚከፈለዉ ካሳ ከደረሰዉ ጉዲት ጋር እኩል ሆኖ የሚመዛዘን መሆን አለበት በሚል የሕግ መሰረት ባለዉ መርህ ማዕቀፍ ዉስጥ ሆኖ በመከላከያ ክርክር መልክ የሚታይ ሆኖ እያለ፤ በአመልካች የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ቀርቦ ተገቢዉ ዲኝነት ተከፍልበት የተጠሪ ክርክርም ከዚህ አንጻር ተሰምቶ ዉሳኔ ማግኘት እንደሚገባዉ አዱስ እና ራሱን እንደቻለ ክርክርና የዲኝነት ጥያቄ አድርጎ በመቁጠር ዉድቅ በማድረግ የሰጠዉ ዉሳኔ የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ላቀርብ የሚችልበትን አግባብ ያልተከተለና በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 234(1/ረ) ስለተከሳሽ ከሳሽነት ከስ የተደነገገዉን ያላገናዘበ በመሆኑ ሉታረም የሚገባዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ ብለናል።ስለሆነም ተከታዩን ወስነናል።
የሰሜን ወል ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 18/07/2011ዓ/ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/8 ላይ በቀን 09/04/2013ዓ/ም የሰጠዉ ዉሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ተሻሽለዋል።
ለተጠሪ ሉከፈል የሚገባዉ የካሳ ልክ የቅሪት አካለን ግምት ጨምሮ ከብር 495,000.00 ሉበልጥ አይገባም ብለናል።ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መዝገቡን በማንቀሳቀስ ከአጠቃላይ የካሳ መጠን ላይ ሉቀነስ የሚገባ የቅሪት አካላት ግምት መጠን ወይም ቅሪት አካላት በአይነት የሚመለሱ ከሆነም የሚመለሱ የቅሪት አካላት አይነት እና ብዛት ምንነት በተመለከተ እና ተያያዥ በሆኑ ነጥቦች ላይ ሕግን መሰረት ያደረገ ዉሳኔ እንዱሰጥ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 343/1 መሰረት ጉዲዩን መልስንለታል።
ግራ ቀኝ በዚህ ችልት ደረጃ ያወጡትን ወጭ የየራሳቸዉን እንዱችለ ብለናል።
የዉሳኔዉ ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤት ይተላለፍ። ለግራ ቀኙም ግልባጩ ይሰጣቸዉ።
በመዝገቡ ላይ የተሰጠ የዕግድ ትእዛዝ ካለ ተነስቷል፤ይጻፍ።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.