የፍትሀ ብሄር ህግ ቁጥር 2143/2 ዓላማ ለካሳ ጥያቄው መነሻ የሆነው ድርጊት በወንጀል የሚያስቀጣና የይርጋ ጊዜውም ረዘም ያለ ከሆነ ካሳ ጠያቂው ረዘም ያለውን የወንጅል ህግ የይርጋ ጊዜ በመጠቀም ክሱን ማቅረብ እንዱችል ለማስቻል በመሆኑ የወንጀል ሕግ ይርጋ ጊዜ ከ2 ዓመት ያነሰ በሆነ ጊዜ ተፈፃሚ የሚሆነው የይርጋ ጊዜ በፍ/ብ/ሕግ ቄጥር 2143/1 ላይ የተደነገገው ስለመሆኑ ኢንሹራንስ ኩባንያዎች በደንበኛቸው በመዲረግ ጉዲት አድራሹ ላይ ለሚያቀርቡት ክስ የይርጋ ጊዜ መቆጠር ያለበት ካሳ ከከፈለበት ቀን ጀምሮ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት እና ፈይሰል አህመድ
No summary available.
የሰ/መ/ የካቲት 25 ቀን 2013 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ ተሾመ ሽፈራዉ ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግሥቱ ነጻነት ተገኝ አመልካች፡- የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ተጠሪ፡- ፈይሰል አህመድ መህዱን መዝገቡ ተመርምሮ ከዚህ የሚከተለዉ የፍርድ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የኢንሹራንስ ሰጪ በኢንሹራንስ ገቢዉ ምትክ ሆኖ በሚያቀርበዉ ክስ ላይ ተፈጻሚነት የሚኖረዉን ይርጋ ድንጋጌ የሚመለከት ነዉ። አመልካች በፈደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ድሬዲዋ ምድብ በአሁን ተጠሪ(በስር 3ኛ ተከሳሽ) እና በሥር 1ኛ ተከሳሽ ኒያላ ኢንሹራንስ አ.ማ እና በስር 2ኛ ተከሳሽ ፈቲ መሐመድ አህመድ ላይ በመሰረተዉ ክስ ንብረትነቱ የድሬዲዋ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በሆነ በሰላዲ ቁጥር 4-00325ድሬ ለሚታወቅ ተሽከርካሪ አጠቃላይ የመድን ዋስትና ሽፊን ሰጥቷል።በስር 2ኛ ተከሳሽ ሲሽከረከር የነበረ በተጠሪ ስም የተመዘገበ የሰላዲ ቁጥሩ 3-03059ድሬ የሆነ ተሽከርካሪ በድሬዲዋ ከተማ እየተሽከረከረ ላለዉ ለደንበኛዉ ተሽከርካሪ ቅድሚያ ባለመስጠት የደንበኛዉን ተሽከርካሪ ገጭቶ ጉዲት አድርሷል።ጥፊቱ የተጠሪ ተሽከርካሪ መሆኑ በትራፉክ ፖሉስ ተረጋግጧል።በደንበኛዉ መኪና ላይ የደረሰዉን ጉዲት ለማስጠገን በጨረታ በማወዲደር ዝቅተኛ ዋጋ ላቀረበዉ ጋራዥ የአደጋ መነሻ እና የዕርጅና መዋጮ ቀንሶ ብር 140,038.90(አንድ መቶ አርባ ሺህ ሰላሳ ስምንት ብር ከዘጠና ሳንቲም) መክፈለን በመግለጽ ተጠሪና የስር ተከሳሾች ይህንን ገንዘብ በአንድነትና በነጠላ ኃላፉነት እንዱከፍለ እንዱወሰን ዲኝነት ጠይቋል።
ተጠሪ ለክሱ በሰጡት መልስ ላይ ባቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አመልካች በደንበኛዉ ተሽከርካሪ ላይ ጉዲት የደረሰዉ በቀን 10/09/2007ዓ/ም ሆኖ ክሱን ያቀረበዉ በቀን 08/05/2010ዓ/ም ከ2 ዓመት ከ7 ወር በኋላ በመሆኑ የተጠሪ ክስ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2143/1 መሰረት በ2 ዓመት ይርጋ ቀሪ ሆኗል በማለት ፍርድ ቤቱ መዝገቡን ዘግቶ እንዱያሰናብታቸዉ በመጠየቅ ተከራክሯል።
ፍርድ ቤቱ ተጠሪ ባቀረቡት የይርጋ መቃወሚያ ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ በመ/ ላይ በቀን 12/02/2011 ዓ/ም በሰጠዉ ብይን በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2143/2 መሰረት ድርጊቱ በወንጀል የሚስቀጣ ከሆነ በወንጀል ሕጉ የተቀመጠዉ የይርጋ ጊዜ ተግባራዊ እንደሚሆን በተደነገገዉ መሰረት በአመልካች ደንበኛ ተሽከርካሪ ላይ ጉዲት ያደረሰዉ አሽከርካሪ የነበሩት የስር 2ኛ ተከሳሽ ራሳቸዉ አምነዉ በሰጡት መልስ በወንጀል ጥፊተኛ መባላቸዉ ስለተረጋገጠ ይርጋዉ በወንጀል ሕጉ መሰረት የሚታይ ነዉ።የወንጀል ይርጋ ደግሞ ከሁለት ዓመት ጊዜ በላይ በመሆኑ የይርጋ አቆጣጠሩን በተመለከተ በሰ/መ/ ላይ በሰጠዉ የሕግ ትርጉም መሰረት ክሱን ይርጋ አያግደዉም በማለት መቃወሚያዉን ዉድቅ በማድረግ ብይን ሰጥቶ ፍሬ ነገሩን በተመለከተ ግራ ቀኙን አከራክሮ ክስ የቀረበበትን ገንዘብ ተጠሪዎች ለአመልካች እንዱተኩለት ወስኗል።
ተጠሪ ከፍ ሲል በተገለጸዉ መሰረት በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዉ ላይ እና በፍሬ ነገሩ ላይ በተሰጠ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርበዉ ፍርድ ቤቱም በመ/ ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ በቀን 29/08/2011ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ ጉዲት አደረሰ የተባለዉ አሽከርካሪ ፈቲ መሀመድ በድሬ ዲዋ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ላይ በወንጀል ሕግ ቁጥር 854 መሰረት ክስ ቀርቦባቸዉ ጥፊተኛ ተብለዉ ተወስኖባቸዋል።በወንጀል ሕግ አንቀጽ 736/2 ስር አንድ ሰዉ ሉቀጣ የሚችለዉ በደንብ መተላለፍ ወይም በወንጀል ሕግ መሰረት ብቻ እንጂ በሁለቱም ላሆን እንደማይችል ተደንግጓል።አሽከርካሪዉ በደንብ መተላለፍ የተቀጣ ሰዉ በወንጀል ሕጉ ሉቀጣ የሚችልበት ላላ እድል ስለማይኖር ለደንብ መተላፍ የተቀመጠዉ የይርጋ ደንብ ተፈጻሚነት ስለሚኖረዉ በደንብ መተላለፍ ከተከሰሰና ከተቀጣ ተፈጻሚነት የሚኖረዉ በወንጀል ሕግ ቁጥር 773 ላይ ያለዉ አንድ ዓመት ይርጋ እንጂ በወንጀል ሕግ ቁጥር 214-219 ያለት የይርጋ ደንቦች አይሆኑም።በሰ/መ/ ላይ የተሰጠዉ ትርጉም አሽከርካሪዉ በደንብ መተላለፍ የተቀጡ ስለሆነ በድጋሚ በወንጀል ሕጉ ሉቀጡ የሚችለበት ሁኔታ ስለማይኖር አስገዲጅ የህግ ትርጉም ለተያዘዉ ጉዲይ ተፈጻሚነት የለዉም።ስለሆነም ጉዲቱ ከደረሰበት ከቀን 10/09/2007ዓ/ም በኋላ ክስ በቀን 08/05/2010ዓ/ም የቀረበ በመሆኑ ሁለት ዓመት ጊዜዉ ስላለፈ ፍርድ ቤቱ ክስ በይርጋ ቀሪ ሆኖ እያለ የሥር ፍርድ ቤት በተጠሪ የቀረበዉን የይርጋ መቃወሚያ ዉድቅ ማድረጉና በፍሬ ነገሩ ላይ ዉሳኔ መስጠቱ ተገቢ አይደለም ሲል የሥር ፍርድ ቤትን ብይንና በፍሬ ነገሩ ላይ የሰጠዉን ዉሳኔ በመሻር ወስኗል።
በመቀጠል አመልካች ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርቦ ችልቱም በመ/ ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ በቀን 26/09/2012 ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠዉን ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል።አመልካች በቀን 25/12/2012ዓ/ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረበዉም በፋዳራል ከፍተኛ እና ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች በተሰጠ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን ይዘቱ በአጭሩ የሚከተለዉ ነዉ።
አንድ የጥፊት ድርጊት በአንድ ጊዜ ከአንድ በላይ በሆኑ የወንጀል ሕጉ ድንጋጌዎች ስር የሚያርፍበት ሁኔታ ሉኖር ይችላል።በዚህ ጉዲይም የአሽከርካሪዉ ድርጊት በወንጀል ሕጉ ልዩ ክፍል አንቀጽ 572ም ሆነ በሕጉ በደንብ መተላለፍ ክፍል ሉያስቀጣ ይችላል።በወንጀል ሕግ አንቀጽ 736/2 የተደነገገዉ በአንደኛዉ ድንጋጌ ተከሶ የተቀጣ በልላኛዉ ሉያስቀጣዉ በሚችል ድንጋጌ ሉቀጣ አይችልም የሚል አይደለም።በአሽከርካሪዉ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 572 መሰረት ክስ ሉመሰረትባቸዉ የሚችልበት አግባብ ነበረ።በመሆኑም ጥፊት አድራጊዉ በደንብ መተላለፍ ተከሶ ባይቀጣ ኖሮ ድርጊቱ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 572 መሰረት በቸልተኝነት የትራፉክ ደንቦችን በመተላለፍ ንብረት አደጋ ላይ በመጣል እስከ 3 ዓመት ድረስ የሚያስቀጣዉ ድርጊት እንደነበር እርግጥ ነዉ።በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2143/2 ጥፊተኛዉ በወንጀል መቀጣት አለመቀጣቱ ወይም የተቀጣበት ምክንያት ግምት ዉስጥ እንደሚገባ አይደነግግም።በሰ/መ/ ላይ የተሰጠዉ አስገዲጅ ትርጉም ላይ ጥፊቱ እስካልተካደ ድረስ እና ድርጊቱ በመደበኛዉ የወንጀል ድንጋጌ ዉስጥ የተካተተ እስከሆነ ድረስ አልተከሰስኩበትም ወይንም አልተቀጣሁበትም የሚል ክርክር የሕግ መሰረት የለዉም። ስለሆነም የሥር ፍርድ ቤቶች የቀረበዉን የይርጋ መቃወሚያ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2143/2 መሰረት በማየት ዉድቅ አለማድረጋቸዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስለሆነ ይታረምልን በማለት አቤቱታዉን አቅርቧል።
የሰበር አጠሪ ችልት አቤቱታዉን መርምሮ የአመልካች የይርጋ ክርክር በተመለከተ ተፈጻሚነት ያለዉ ሕግ ከፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2143 ትርጉምና ዓላማ አንጻር ጉዲዩ ለሰበር ችልት ቀርቦ እንዱመረመር ተጠሪ መልስ እንዱሰጡ ትእዛዝ በመስጠቱ ተጠሪ በቀን 21/03/2013ዓ/ም የተጻፈ መልስ ያቀረቡ ሲሆን ይዘቱ በአጭሩ፡-ጥፊት አድራጊዉ ሹፋር የተቀጡት በደንብ መተላለፍ ትራፉክ ጽ/ቤት ሳይሆን በዐቃቤ ሕግ ክስ ቀርቦባቸዉ በመደበኛ ፍርድ ቤት ጉዲዩ ታይቶ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 856 መሰረት በሁለት ወር ቀላል እስራት ወይም በብር 1000.00 የገንዘብ መቀጮ እንዱቀጡ መደረጉ የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነዉ።አንድ ሰዉ በአንድ የወንጀል ድርጊት ሁለት ጊዜ እንደማይቀጣ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 6 እና 732 ላይ ተመልክቷል።ስለሆነም አሽከርካሪዉ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 856 ስለተቀጡ አመልካች እንዲለዉ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 572 መሰረት ተጠያቂ የሚሆንበት የሕግ መሰረት የለም።ለወንጀል ሕግ አንቀጽ ተፈታሚነት ያለዉ የይርጋ ጊዜ አንድ አመት ነዉ።ስለሆነም ይርጋዉ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2143/1 ስር ያለዉ የ2 ዓመት ጊዜ እንጂ ለወንጀል ሕግ አንቀጽ 572 የተቀመጠዉ የ5 ዓመት ይርጋ ጊዜ አይደለም ተብል በመወሰኑ የተፈጸመ ስህተት የለም በማለት ተከራክረዋል።አመልካችም በቀን 13/04/2013ዓ/ም የተጻፈ የመልስ መልስ በማቅረብ ተከራክሯል።
ከዚህ በላይ የተመዘገበዉ የግራ ቀኝ ክርክርና በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ዉሳኔዎችን ይዘት የሚመለከት ሲሆን እኛም የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩ ለሰበር ችልት ያስቀርባል ሲል ከያዘዉ ጭብጥ አንጻር የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ መርምረናል።
እንደመረመርነዉም አመልካች ጠቅላላ የመድን ሽፈን የሰጠዉ ንብረትነቱ የድሬዲዋ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ለሆነዉ በሰላዲ ቁጥር 4-00325 ድሬ ለሚታወቅ ተሽከርካሪ ነዉ።ይህ በአመልካች የመድን ሽፊን የተሰጠዉ ተሽከርካሪ ንብረትነቱ የተጠሪ በሆነና በስር 2ኛ ተከሳሽ ሲሽከረከር በነበረ በሰላዲ ቁጥር 3-03059 ድሬ በሆነ ተሽከርካሪ በቀን 10/09/2007ዓ/ም በመገጨቱ ጉዲት ስለደረሰበት አመልካች የደንበኛዉን ተሽከርካሪ ለማስጠገን ብር 140,038.90 ወጪ ማድረጉን ገልጾ በመድን ገቢዉ ምትክ ሆኖ ይህ ገንዘብ እንዱተካለት በተጠሪና በስር 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች ላይ በቀን 08/05/2010ዓ/ም ክስ አቅርቧል።የአሁን ተጠሪ የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2143/1ን ጠቅሰዉ ክሱ በይርጋ ታግዶል በሚል ያቀረቡትን መቃወሚያ የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዉድቅ አድርጓል። ሆኖም ጉዲዩን በይግባኝ ያዩት የፋዳራል ከፍተኛ እና ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ጉዲት አድራሹን ተሽከርካሪ ሲያሽከረክሩ የነበሩት የሥር 2ኛ ተከሳሽ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 856 መሰረት ጥፊተኛ ተብለዉ ስለተቀጡ የዚህ የወንጀል ሕግ ድንጋጌ የይርጋ ጊዜ አንድ አመት በመሆኑ ለጉዲዩ ተፈጻሚነት ያለዉ የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2143/1 ነዉ በማለት የተጠሪን የይርጋ መቃወሚያ በመቀበል የአመልካች ክስ ዉድቅ ላሆን ይገባል በማለት ወስነዋል። የዚህን ችልት ምላሽ የሚሹ ነጥቦች መድን ሰጪ መድን በተገባለት ንብረት ላይ የደረሰዉን ጉዲት በማስጠገን ያወጣዉን ወጪ (ለመድን ገቢዉ የከፈለዉን) በመድን ገቢዉ ምትክ ሆኖ ለማስመለስ በጉዲት አድራሹ ተሸከርካሪ ባለቤትና አሽከርካሪዉ ላይ ለሚያቀርበዉ ክስ ተፈጻሚነት የሚኖረዉ የይርጋ ሕግ ድንጋጌ የትኛዉ ነዉ የይርጋ ጊዜዉስ ከመቼ ጀምሮ ሉቆጠር ይገባል የሚለ ጭብጦች ናቸዉ።
ከላይ እንደተመለከተዉ የሥር የፋዳራል ከፍተኛ እና ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ለጉዲዩ ተፈጻሚነት ያለዉ የይርጋ ድንጋጌ የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2143/2 ሳይሆን የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2143/1 ነዉ ብለዉ ሲወስኑ መሰረት ያደረጉት ምክንያት ድርጊቱ ጉዲት አድራሹን ተሽከርካሪ ሲያሽከረክሩ የነበሩት የሥር 2ኛ ተከሳሽ በወንጀል የተከሰሱትና ጥፊተኛ ተብለዉ የተቀጡት በወንጀል ሕግ ስር ባለ የደንብ መተላለፍ ድንጋጌ አንቀጽ 856 ስለሆነና የዚህ የወንጀል ሕግ ድንጋጌ የይርጋ ጊዜ አንድ አመት ነዉ በሚል ነዉ።አመልካች አጥብቆ የሚከራከረዉ ደግሞ አሽከርካሪዉ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 856 መሰረት ተከሰዉ ቢቀጡም ድርጊታቸዉ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 572/1 ጭምር ሉያስቀጣቸዉ ስለሚችል፣የዚህ ድንጋጌ የይርጋ ጊዜ ደግሞ ከሁለት ዓመት በላይ በመሆኑ እና በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2143/2 ስር ‛…ጉዲቱ በወንጀል የሚያስቀጣ“ የሚለዉ አገላለጽ ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ ላይ በሰጠዉ አስገዲጅ ትርጉም መሰረት ድርጊቱ በወንጀል የሚያስቀጣ መሆኑን የሚጠይቅ እንጂ የድርጊቱ ፈጻሚ ተከሶ መቀጣት እንዲለበት ከግምት ዉስጥ የሚያስገባ ባለመሆኑ ተፈጻሚ ላሆን የሚገባዉ የይርጋ ድንጋጌ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2143/2 ስር የተደነገገዉ ነዉ በሚል ነዉ።ተጠሪ ደግሞ አሽከርካሪዉ አንድ ጊዜ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 856 ስለተቀጡ በድጋሚ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 572/1 መሰረት እንዱጠየቁ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 6 እና 736/2 ስለማይፈቅደ በስር ፍርድ ቤቶች የተወሰነዉ በአግባቡ ነዉ በማለት ተከራክረዋል።
አመልካች ድርጊቱ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 572 ስር ወንጀል ሆኖ የተደነገገ በመሆኑ አሽከርካሪዉ በዚህ ድንጋጌ ሉከሰሱ የሚችለበት ሁኔታ አለ በሚል የተከራከረ ቢሆንም በዚህ ድንጋጌ ወንጀል ተደርጎ የተደነገገዉና አጥፉዉ በድንጋጌዉ በተመለከተዉ ቅጣት የሚቀጣዉ የተፈጸመዉ ድርጊት "ማንም አሽከርካሪ ወይም እግረኛ በቸልተኛነት የትራፉክ ደንብን በመጣስ የላላዉን ሰዉ ሕይወት፣አካል፣ጤና ወይም ንብረት ለአደጋ ያጋለጠ እንደሆነ ነዉ" ተብል የተደነገገዉን ድርጊቱን ወንጀል የሚያደርገዉን የድንጋጌዉን አነጋገር አሟልቶ ሲገኝ ነዉ።
በወንጀል ሕግ አንቀጽ 572 አነጋገር መሰረት አንድ አሽከርካሪ ወይም እግረኛ በቸልተኛነት የትራፉክ ደንብ በመጣስ በፈጸመዉ ድርጊት ላላዉ አሽከርካሪ ወይም እግረኛ የላላዉን ሰዉ ሕይወት፣አካል፣ጤና ወይም ንብረት ለአደጋ ሲያጋልጥ (ሲጎዲ) የመጀመሪያዉ አሽከርካሪ ወይም እግረኛ የትራፉክ ደንብን በመጣስ ላላዉን ሰዉ ለአደጋ በማጋለጡ የሚጠየቅበት ድንጋጌ እንጂ በተያዘዉ ጉዲይ የተከሰተዉን በአንደኛዉ አሽከርካሪ የትራፉክ ደንብ በቸልተኛነት በመጣሱ ምክንያት በሁለት ተሽከርካሪዎች መካከል ግጭት በመፈጠሩ በሁለተኛዉ ተሽከርካሪ ላይ ለደረሰዉ ጉዲት ጉዲት አድራሹን አሽከርካሪ በወንጀል ተጠያቂ ለማድረግ የተደነገገ ድንጋጌ አይደለም።በመሆኑም በአመልካች ካሳ ለመጠየቅ መሰረት የተደረገዉ ድርጊት በወንጀል ሕግ አንቀጽ 572 የሚገዛ ባለመሆኑ ከዚህ አንጻር ታይቶ የይርጋ ጊዜዉ አለመወሰኑ ስህተት አይደለም።
በወንጀል ሕጋችን በአንቀጽ 677(1/ለ እና 2) ስር በተደነገገዉ መሰረት ማንም ሰዉ በመንግስት ወይም በሕዝብ ንብረት ላይ በቸልተኛነት በድንጋጌዎቹ በተገለጸዉ አነጋገር ጉዲት በማድረሱ ሉጠየቅ ከሚችል በስተቀር በንብረት መብቶች ላይ ስለሚፈጸሙ ወንጀልች ስድስተኛ መጽሐፍ ርእስ አንድ ስር በተደነገጉ ድንጋጌዎች መሰረት በመንግስት ወይም በሕዝብ ወይም በግለሰብ ንብረት ላይ በቸልተኛነት ጉዲት ማድረስ እንደ መደበኛ ወንጀል ተቆጥሮ የሚያስጠይቅ አይደለም። እንዱሁም ምንም እንኳን በወንጀል ሕግ አንቀጽ 559/2 መሰረት በቸልተኛነት የትራፉክ ደንብ በመጣስ በሰዉ አካል ላይ ጉዲት ማድረስ በወንጀል የሚያስጠይቅ ቢሆንም ከላይ እንደተመለከተዉ በተለይም አንድ አሽከርካሪ በቸልተኛነት የትራፉክ ደንብ በመጣስ በሚሽከረከረዉ ተሽከርካሪ ራሱ ላላ ተሽከርካሪ ወይም ንብረት በመግጨት በልላ ተሽከርካሪ ወይም በልላ ንብረት ላይ ጉዲት ቢያደርስ በወንጀል ተጠያቂ እንደሚሆን በወንጀል ሕጉ አልተደነገገም። ይህም የሆነበት ምክንያት በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 662 ስር በተደነገገዉ መርህ ላይ እንደተመለከተዉ በልላ ሰዉ ንብረትና የኢኮኖሚ መብት ወይም በገንዘብ ሉተመኑ በሚችለ መብቶች ላይ የሚደረግ ጣልቃ ገብነት ከፍተኛነት ደረጃ ታይቶ በሕጉ ስድስተኛ መጽሐፍ ስር እንደወንጀል ድርጊት ተቆጥሮ በግልጽ አስቀጪነታቸዉ ካልተደነገገ በስተቀር እንደአነስተኛ ድርጊት ተቆጥሮ አጥፉዎች በደንብ መተላለፍ እንዱቀጡ ማድረግ የሕግ አዉጭዉ ፍላጎት በመሆኑ ነዉ።
በተያዘዉ ጉዲይ እንደታየዉ በአመልካች ደንበኛ ተሽከርካሪ ላይ ጉዲት ያደረሰዉ አሽከርካሪ(የስር 2ኛ ተከሳሽ) የተከሰሱትና በፍርድ ቤት በተላለፈበት ዉሳኔ የተቀጡት በወንጀል ሕጉ ስለደንብ መተላለፍ ጥፊቶች በስምንተኛ መጽሐፍ ስር በሚገኘዉ አንቀጽ 856 ላይ የትራፉክ ደንብ በመጣስ ተሽከርካሪን በመጥፍ ሁኔታ በማሽከርከር ወይም በግዳለሽነት ወይም በቸልተኛነት በመጠቀም በልላ ሰዉ ንብረት ላይ ጉዲት በማድረስ የሚፈጸም ድርጊት …በሚል በተደነገገዉና በዚሁ ድንጋጌ ላይ በተመለከተዉ ቅጣት መሰረት እንደሚቀጣ በተደነገገዉ መሰረት ነዉ። እንዱሁም በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 773 ስር ማንኛዉም አይነት የደንብ መተላለፍ ድርጊት ቢሆን ክስ ሳይቀርብበት አንድ ዓመት ካለፈ፤የተፈረደዉም ቅጣት ተፈጻሚ ሳይሆን ሁለት ዓመት ካለፈ በይርጋ እንደሚታገድ ተደንግጓል።
በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2143/2 ስር ‛… ጉዲቱ በወንጀል የሚያስቀጣ ሆኖ…“ የሚለዉ አገላለጽ የተፈጸመዉ ድርጊት በወንጀል የሚያስቀጣ ከሆነ የድርጊቱ ፈጻሚ በወንጀል ቢከሰስም ፤ባይከሰስም፤ቢቀጣም፤
ባይቀጣም የይርጋ ጊዜዉ የሚወሰነዉ ድርጊቱን የወንጀል ድርጊት ለሚያደርገዉ የወንጀል ሕግ ድንጋጌ በተቀመጠዉ የይርጋ ጊዜ መሰረት ይሆናል ከሚል አላማ የተቀመጠ እንደሆነ የሚያስገነዝብ ነዉ።ከዚህ ጋር በተያያዘ በሰ/መ/ ላይ በቀን 22/06/2003 ዓ/ም (በቅጽ 11 ላይ እንደታተመዉ) የተመለከተዉ አስገዲጅ ትርጉም ላይ በግልጽ እንደተመለከተዉ ድርጊቱን የፈጸመዉ አሽከርካሪ በወንጀል አልተከሰስኩም፤ አልተቀጣሁምም የሚል ክርክር አቅርበዉ ድርጊቱ በወንጀል ሕጉ እንደ ወንጀል ድርጊት የተደነገገ እስከሆነ ድረስ አሽከርካሪዉ በወንጀል ባይከሰሱም በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2143/2 የተደነገገዉ የይርጋ ጊዜ ተፈጻሚ ይሆናል ተብል ትርጉም የተሰጠበት ነዉ።
በያዝነዉ ጉዲይ ጉዲቱን አደረሱ የተባለት አሽከርከሪ(የስር 2ኛ ተከሳሽ) በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 856 መሰረት በዐቃቤ ሕግ ተከሰዉ በፍርድ ቤት በተሰጠ ዉሳኔ ጥፊተኛ ተብለዉ የተቀጡ መሆኑ የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነዉ። በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ተወስኖ የሚሰጥ አስገዲጅ ትርጉም በፋዳራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10/4 (በአዋጅ ቁጥር 454/1997 እንደተሻሻለዉ)መሰረት በየትኛውም ደረጃ ላይ በሚገኙ ፍርድ ቤቶች ዘንድ አስገዲጅነት ኖሯቸዉ ተፈጻሚ መሆን ያለባቸዉ ዉሳኔ ከሚፈልገዉና አከራካሪ በሆነዉ ተመሳሳይ ጉዲይ (ratio decidendi - the point in a case that determines the judgement) ላይ የተሰጠ የሕግ ትርጉም ሲሆን ነዉ። በመሆኑም በሰ/መ/ የሕግ ትርጉም የተሰጠበት አከራካሪ ፍሬ ነገር እና በተያዘዉ ጉዲይ ዉሳኔ የሚፈልገዉ አከራካሪ ጉዲይ ተመሳሳይ ( ratio decidendi ) ባለመሆኑ በሰ/መ/ ላይ የተሰጠዉ ትርጉም ለተያዘዉ ጉዲይ ተፈጻሚነት ያለዉ አይደለም።በመሆኑም ይግባኝ ሰሚዉ ችልት እና የሥር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከዚህ አኳያ የደረሱበት ድምዲሜ የሚነቀፍ አይደለም።
እንዱሁም አመልካች አሽከርካሪዉ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 572 ሉከሰሱ የሚችለበት ሁኔታ እንዲለ በመግለጽ የተከራከረ ቢሆንም ከላይ እንደተመለከተዉ አሽከርካሪዉ የፈጸሙት ድርጊት በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 572 የሚሸፈን ባለመሆኑ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 856 መሰረት ተከሰዉ ተቀጥተዋል።በወንጀል ሕግ አንቀጽ 60(ለ) ስር በተደነገገዉ መሰረት በአንድ ድርጊት በአንድ ጊዜ ሁለት ወይም ከሁለት በላይ የሆኑ የሕግ ድንጋጌዎችን በመጣስ …ወንጀልች ተፈጽመዉ ሲገኙ በሁለት የወንጀል ሕግ ድንጋጌዎች ተደራራቢ ወንጀልችን በመፈጸም ሉያስከስስ ይችላል።ሆኖም በተያዘዉ ጉዲይ አሽከርካሪዉ የፈጸሙት ድርጊት በወንጀል ሕጉ በመደበኛ የወንጀል ድንጋጌዎች የሚያስቀጣ አለመሆኑ የተረጋገጠና ከላይ እንደተመለከተዉ በወንጀል ሕጉ በደንብ መተላለፍ ድንጋጌ በአንቀጽ 856 መሰረት ተከሰዉ የተቀጡ ስለሆኑ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 2/5 ስር በተደነገገዉ የሕጋዊነት መርህ መሰረት እና በዚሁ ሕግ በአንቀጽ 736/2 መሰረት በወንጀል ሕጉ በመደበኛ የወንጀል ድንጋጌዎች የአሽከርካሪዉን ድርጊት የወንጀል ጥፊት የሚያደርግ ድንጋጌ የለም እንጂ ቢኖር እንኳን መጀመሪያ በተደራራቢነት እስካልተከሰሱ ድረስ በአንደኛዉ (በደንብ መተላለፍ)ከተቀጣ በኋላ በዚያዉ ድርጊት እንደገና የሚከሰስበትና የሚቀጣበት የወንጀል ሕግ አግባብ የለም።በመሆኑም በዚህ ረገድ አመልካች ያቀረበዉን ክርክር ይግባኝ ሰሚዉ ችልት እና የሥር የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አለመቀበላቸዉ ሕግን መሰረት ያደረገ ነዉ ብለናል።
በልላ በኩል የይርጋ ጊዜዉ መቆጠር ያለበት ከመቼ ጀምሮ ነዉ የሚለዉን ነጥብ መርምረናል።
አመልካች ክሱን ያቀረበው በኢንሹራንስ ገቢው መብት በመዲረግ ወይም በምትክነት ነው። አመልካች ለክሱ መሰረት ያደረገው የመድን ገቢው ጋር ያደረገው የዕቃዎች/ንብረት ኢንሹራንስ ሲሆን በንግድ ሕጉ አንቀጽ 683 መሰረት ኢንሹራንስ ሰጪው በከፈለው ካሣ መጠን ጉዲት እንዱደርስ ባደረጉ ሦስተኛ ወገኖች ላይ ክስ ለማቅረብ ኢንሹራንስ ለገባው ሰው በተከፈለው ገንዝብ መጠን፣ ባለት መብቶችና ክሶች ኢንሹራንስ ሰጪው ምትክ ሆኖ እንደሚገባ ተመልከቷል። ይሕም የመዲረግ መብቱ ከውል ሳይሆን ከሕግ የመነጨ መሆኑን ያስገነዝባል። የመዲረግ መብትን ተመስርቶ የሚቀርብ ክስ ይርጋ አቆጣጠርን ስንመለከት በአንድ በኩል የመዲረግ መብቱ ኢንሹራንስ ገቢው መብት ላይ ተመስርቶ የሚቀርብ መሆኑ እና በልላ በኩል መዲረግ በሕግ የተፈቀደበት ሕግ አውጪው ሉያሳካው የፈለገው ዓላማ ጋር ተገናዝቦ ላታይ የሚገባው ነው። መድን ገቢውና ተጠሪ ያላቸው ግንኙነት የተመሰረተው ከውል ውጭ በመሆኑ አመልካች በመድን ገቢው እግር ተተክቶ የሚያቀርበው ክስም ከውል ውጭ ማዕቀፍ የሚታይ ነው።
በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2143/1 መሰረት ከውል ውጭ ክስ የሚቀርበው ጉዲቱ ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ በሁለት ዓመት ጊዜ ስለመሆኑ ተደንግጓል። የሥር ፍርድ ቤቶችም የይርጋ ጊዜውን የቆጠሩት ጉዲቱ ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ ነው።
አመልካች በሕግ የመዲረግ መብት ያገኘው ለመድን ገቢው ካሣውን ሲከፍል ነው።ሕግ አውጪው የመዲረግ መብት ለኢንሹራንስ ሰጪው የደነገገበት በዋነኛነት ሁለት ዓላማዎችን ለማሳካት እንደሆነ መረዲት ይቻላል። የመጀመሪያው ማሕበራዊ ምክንያት ነው።ይኸዉም መድን ገቢው ካሣውን ከኢንሹራንስ ሰጪው ከተቀበለ ጥፊት የፈጸመው ሰው ላይ ክስ ለማቅረብ ፍላጎት ስለማይኖረውና ክስ ቢያቀርብ እንኳን ለደረሰው ጉዲት በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2090/1 እና 2091 መሰረት ከካሣ ተመዛዛኝነት መርሕ አኳያ ድጋሚ የሚካስበት ዕድል አይኖርም። ይሕም ጥፊቱን ያደረሰው ሰው ለጥፊቱ ተገቢው ተጠያቂነት ሳይከተልበት እንዱቀር ያደርጋል። ስለሆነም ኢንሹራንስ ሰጪው የመዲረግ መብት እንዱኖረው ማድረግ ለጉዲቱ ምክንያት የሆነው ጥፊት ፈጻሚው ሰው ለጥፊቱ ኃላፉነት እንዱወሰድና በሂደትም ጥፊት መፈጸምን በመቀነስ ወይም በመተው በሕብረተሰቡ ዘንድ አዎንታዊ የባሕሪ ለውጥ እንዱመጣ ማስቻል ዓላማ ያደረገ ነው። ሁለተኛው ኢኮኖሚያዊ ምክንያት ነው። የመዲረግ መብት መኖሩ ኢንሹራንስ ሰጪው ለመድን ገቢው የከፈለውን ገንዘብ እንዱተካለት ጉዲት አድራሹ ወይም የእሱ መድህን እንዱተካ በማድረግ የኢንሹራንስ ሥራ ትርፍ ማግኘት ከመሆኑ አኳያ ትርፊማ ድርጅት እንዱሆን ማድረግ ነዉ። ይሕም የአረቦን ክፍያ መጠን ላይ ቅናሽ እንዱደረግና ሕብረተሱቡ የኢንሹራንስ ኢንደስትሪውን በተሻለ እንዱጠቀም ሉያበረታታ የሚችል ነው። ኢንሹራንስ ሰጪ ድርጅቶች ጤናማ የሆነ የንግድ እንቅስቃሴ የሚኖራቸው ከሆነ በኢኮኖሚው ላይም አዎንታዊ ሚና የሚጫወት ይሆናል።
ስለሆነም ሕጉ ተግባራዊ በሚሆንበት ጊዜ በሕጉ ለማሳካት የተፈለገውን ዓላማ በማገናዘብ አመልካች በሕግ የተሰጠውን የመዲረግ መብቱን እንዱሰራበት በሚያስችል መልኩ ላሆን ይገባል። ከላይ እንደተመለከተዉ አመልካች በሕግ የመዲረግ መብት ማግኘት የሚችለዉ ለመድን ገቢው ካሣውን ሲከፍል እንደመሆኑ ክስ ሉያቀርብ የሚችለው ጉዲቱ ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ ሳይሆን የመዲረግ መብቱን ካገኘበት ጊዜ ጀምሮ ነው። ይህም በካሣው አከፊፈል ሂደት በሕጉ የተመለከተው የሁለት ዓመት ጊዜ ሉያልፍ የሚችልበት ዕድል እንዲለ ያስገነዝባል።በመሆኑም የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2143/1 የተመለከተው የይርጋ ጊዜና አቆጣጠር በፍትሐብሕር ሕጋችን ስለ ይርጋ በጠቅላለዉ በሚደነግገዉ ክፍል በአንቀጽ 1846 ‛የይርጋው መነሻ ጊዜ“ በሚል ርእስ ሥር ‛የይርጋው ቀን መቆጠር የሚጀምረው ግዳታዉን ለመጠየቅ ተገቢ ከሆነዉ ወይም ዉለ የሚሰጠዉ መብት ከተሰራበት ቀን ጀምሮ ነዉ“ በማለት ከተደነገገው ጋር ተገናዝቦ ሉመረመር ይገባል።
በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2143 እና በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1846 ድንጋጌዎች ስር የተደነገገዉን ይዘት፣ መንፈስና ዓላማ መሰረት በማድረግ በአመልካችና በተጠሪ መካከል ያለዉን ግንኙነትና የክሱን ምክንያት መሰረት አድርገን እንደመረመርነዉ አመልካች ለደንበኛዉ በሰጠዉ ጠቅላላ የመድን ሽፊን ዉል መሰረት ለደንበኛዉ የካሳ ክፍያ መክፈል ይጠበቅበታል። በዚህ መሰረት አመልካች ለደንበኛዉ ካሳ የከፈለዉ ወይም ጉዲት የደረሰበትን የደንበኛዉን ተሽከርካሪ በማስጠገን ለባለጋራዡ ክፍያ የፈጸመዉ መቼ እንደሆነ በስር ፍርድ ቤቶች አልተረጋገጠም። አመልካች በደንበኛዉ ምትክ በመሆን በተጠሪና በስር ተከሳሾች ላይ ክስ መመስረት የሚችለዉ የመድን ዉል ፖለሲዉንም መሰረት በማድረግ ለደንበኛዉ ካሳ ወይም የተሽከርካሪ ማስጠገኛ ክፍያ ሲፈጽም ነዉ። ይህንን ሳያደርግ ይተካልኝ በማለት በመድን ገቢዉ ምትክ ሆኖ ክስ ለመመስረት የሚያስችል የበሰለ መብት አይኖረዉም። በእንዱህ አይነት ጉዲይ በመድን ሰጪዉ ላይ ለክሱ ምክንያት የሆነ ጉዲት ደረሰበት ማለት የሚቻለዉ (the occurrence giving rise to the claim) እና በመብቱ መሥራት የሚችለዉ ለደንበኛዉ የካሳ ክፍያ ከፈጸመበት ቀን ጀምሮ ነዉ።
ሲጠቃለል የአመልካች ደንበኛ ተሽከርካሪን በመግጨት ጉዲት እንዱደርስበት ያደረጉት አሽከርካሪ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 856 ስር በተደነገገዉ መሰረት ተከሰዉ የተቀጡ ስለሆነ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 773 ስር የተደነገገዉ የ1 ዓመት የይርጋ ጊዜ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2143/1 ስር ከተደነገገዉ ከ2 ዓመት የይርጋ ጊዜ ያነሰ በመሆኑ ለተያዘዉ ጉዲይ ተፈጻሚነት ያለዉ የይርጋ ጊዜ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2143/1 ስር የተደነገገዉ የሁለት ዓመት የይርጋ ጊዜ ነዉ። የይርጋ ጊዜዉም መቆጠር የሚጀምረዉ አመልካች ለደንበኛዉ ካሳ ወይም የተሽከርካሪ ማስጠገኛ ክፍያ ከፈጸመበት ቀን ቀጥል ካለዉ ቀን ጀምሮ እንጂ በአመልካች ደንበኛ ተሽከርካሪ ላይ አደጋዉ ከደረሰበት ቀን ጀምሮ ባለመሆኑ የስር ፍርድ ቤቶች ለይርጋ ጊዜ አቆጣጠር በተሽከርካሪዉ ላይ ጉዲት የደረሰበትን ቀን መነሻ በማድረግ መወሰናቸዉ ሉታረም የሚገባዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ።በመሆኑም አመልካች ለደንበኛዉ ካሳ ወይም የተሽከርካሪ ማስጠገኛ ክፍያ የፈጸመበት ቀን የግራ ቀኝ ክርክርና ማስረጃ ተሰምቶ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 245/1 መሰረት ተጣርቶ ሉወሰን ይገባል። ስለሆነም ተከታዩ ተወስኗል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 12/02/2011 ዓ/ም የሰጠዉ ብይን እና በቀን 23/02/2011 ዓ/ም የሰጠዉ ዉሳኔ፣የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 29/08/2011ዓ/ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ ላይ በቀን 26/09/2012 ዓ/ም የሰጠዉ ዉሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ተሽረዋል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መዝገቡን አንቀሳቅሶ አመልካች ለደንበኛዉ ካሳ ወይም የተሽከርካሪ ማስጠገኛ ክፍያ የፈጸመበትን ቀን የግራ ቀኝ ክርክርና ማስረጃ ሰምቶና በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 245/1 መሰረት አጣርቶ የይርጋ ጊዜ ለመቁጠር መነሻ የሚሆነዉን ቀን ለይቶ በተጠሪ በቀረበዉ የይርጋ መቃወሚያ ላይ ተገቢዉን ዉሳኔ እንዱሰጥ ጉዲዩን መልሰንለታል።
ግራ ቀኝ በዚህ ችልት ያወጡትን ወጭ የየራሳቸዉን እንዱችለ ተወስኗል።
ት እ ዛ ዝ
የዉሳኔዉ ግልባጭ ለሥር ፍርድ ቤት ይተላለፍ። ግራ ቀኙ ሲጠይቁም ግልባጩ ይሰጣቸዉ።
በመዝገቡ ላይ የተሰጠ እግድ ካለ ተነስቷል።ይጻፍ።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።