በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 27/3 ስር የተደነገገው ይርጋ ክስ የማቅረብ መብትን ቀሪ የሚያደርግ ባለመሆኑ ሰራተኛው የተሰናበተበትን ምክንያት፣ ምክንያቱ የተከሰተበትን ቀን እና ምክንያቱ የተከሰሰበትን አቶ ተስፊልኡል ቱፊ እና የኢትዮጵያ የኢንደስትሪ አሰሪው መቼ እንዲወቀ በግልጽ በማሰናበቻ ጽሁፍ ላይ ሳይገልጽለት አሰናብቶት ከሆነ ወይም በልላ ምክንያት ለማወቅ ያልተቻለ እንደሆነና እነዚህን ፍሬ ነገሮች ያወቀው አሰሪው ተከሶ በሰጠው መከላከያ መልስ ላይ ከተገለፀው ፍሬ ነገርና ከቀረበው ማስረጃ መነሻ የሆነ እንደሆነ ክሱን ለማሻሻል የግድ ከሆነ የአዋጁን አንቀጽ 27/3 ይዘት ባገናዘበ መልኩ ክሱን በማሻሻል አሉያም ክስ በሚሰማበት ጊዜ በቃል አንስቶ መከራከር የሚችል ስለመሆኑ ግብዓቶች ልማት ድርጅት
No summary available.
የሰ/መ/ ግንቦት 02 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ ተሾመ ሽፈራዉ ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግሥቱ ነጻነት ተገኝ አመልካች፡- አቶ ተስፊልዐል ቱፊ ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ የኢንደስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት መዝገቡ ተመርምሮ ከዚህ የሚከተለዉ የፍርድ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የግል ሥራ ክርክርን የሚመለከት ነው። አመልካች በፋደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በተጠሪ ላይ በመሰረቱት ክስ ከቀን 15/07/2006 ዓ/ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ የሚቆይ የቅጥር ውል ፈፅመን በድርጅቱ ውስጥ በሰው ሀብት ሥራ አመራር ዲይሬክቶሬት የሰው ሀብት ማሟላት ኬዝ ቲም ቡድን መሪ የሥራ መደብ በወር ጠቅላላ ደመወዝ ብር 16,628.00 እየተከፈላቸዉ ሲሰሩ ቆይተዉ አመልካች ድርጅት ከቀን 21/01/2013 ዓ/ም ጀምሮ የሥራ ውላቸዉን ከሕግ-ውጪ ማቋረጡን ገልጸዉ አመልካች ከሥራ ውል ማቋረጥ ጋር በተያያዘ ሉከፈል የሚገባውን ካሳ፣የሥራ ስንብት ክፍያ፣የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ፣ ያልተወሰደ የአምስት ቀናት ደመወዝ፣ የ137 ቀን የዓመት እረፍት በገንዘብ ተቀይሮ፣ ክፍያ ለዘገየበት የሶስት ወር ደመወዝ እንዱከፍላቸዉ እና የሥራ ልምድ ማስረጃ እንዱሰጣቸው ዲኝነት ጠይቀዋል።
ተጠሪ ለክሱ በሰጠው መልስ አመልካች በፈጸሙት ጥፊት በሕጋዊ መንገድ የተሰናበቱ ናቸዉ።
አመልካች በድርጅቱ ያለ ክፍት የሥራ መደቦችን በቅጥር ማስያዝ ሲያስፈልግ የትምህርት ደረጃ እና የሥራ ልምድ ያላቸዉን እጩ ተወዲዲሪዎች እንዱቀጠሩ እና ክፍት የሥራ መደቦች ሲፈጠሩ የዉስጥ ማስታወቂያ እያወጡ ብቁ ሰራተኞች ተወዲድረዉ በሥራ መደቡ ላይ እንዱያድጉ የማድረግ ኃላፉነት የተሰጣቸዉ ቢሆንም በቀረበባቸዉ ተደጋጋሚ ቅሬታ መሰረት በተጠሪ በተቋቋመው ገለልተኛ አጣሪ ኮሚቴ በሰውና በሰነድ ማስረጃ ተመርምሮ በተገኘው ግኝት በሥራቸዉ ላይ የማታለል ተግባር በመፈፀም የተጠሪን አገልግልት በማቃወስ ለግል ጥቅማቸው በማሰብ የተዛባና የተሳሳተ መረጃ በመስጠት የተለያዩ የሥራ ቅጥሮችና ዝውውሮች መፈጸማቸዉ ተረጋግጧል።ስለዚህ የአመልካች የሥራ ውል የተቋረጠው ከተሰጣቸው ኃላፉነት ውጪ እና ተጠሪ ድርጅት የሚመራበትን የቅጥር፣ የዝውውርና የእድገት መመሪያ በሚቃረን አኳኋን የተለያዩ ቅጥርና ዝውውር በመፈፀማቸው በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ አንቀጽ 27 እና በሕብረት ስምምነት አንቀጽ 47 በተደነገገዉ እና በሰ/መ/ ላይ በተሰጠዉ ትርጉም መሰረት በሕጋዊ መንገድ የተፈጸመ ስንብት ነው በማለት ክሱ ውድቅ እንዱደረግ በመጠየቅ ተከራክሯል።
ፍርድ ቤቱ በመ/ ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮና ማስረጃዎችን መርምሮ በቀን 11/09/2013 ዓ/ም በሰጠው ውሳኔ ተጠሪ የሥራ ዉል ለማቋረጥ የሚያስችል በቂ እና ሕጋዊ ምክንያት ሳይኖር እንዱሁም ከቅጥር እና ከምደባ እድገት ጋር በተያያዘ አመልካች ፈጽመዋል የተባለዉ ግድፈቶችን ተጠሪ በጥናት እንደደረሰበት እና እርምጃ እንደወሰደ ገልጾ የተከራከረ ቢሆንም እነዚህ ጥፊቶች ተፈጽመዋል ቢባል እንኳን ከሰራተኛ ቅጥር እና እድገት ጋር በተያያዘ የተፈጸሙ ጥፊቶች በቅጥር ኮሚቴ፣ ቀጥልም ለመጽደቅ ወደ ኃላፉ ሲሄድ በዝርዝር እና በግልጽ ታይቶ ሉታረም ወይም ጥፊት አጥፍተዉ ከሆነም ሉቀጡበት የሚችል ባህሪ ያለዉ ነዉ።በግራ ቀኙ የቀረቡት የሰው ምስክሮችም የሰጡት ቃል እንዱሁም ከህብረት ስምምነት አንቀፅ 14 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መረዲት የሚቻለው እድገትም ሆነ ቅጥር በኮሚቴ እንደሚሰራ እና በተቋሙ የበላይ ኃላፉ የሚፀድቅ መሆኑን ነው። እንዱሁም አመልካች በኮሚቴው በፀሀፉነት የሚሰሩና ድምፅ አልባ መሆናቸው ተመስክሯል። ከዚህ አኳያ ቅጥሮቹ እና እድገቶቹ ከተሰጡ ከአመታት በኋላ የሥራ ዉለን ማቋረጥ በአዋጁ አንቀጽ 27/3 መሰረት በአንድ ወር ጊዜ ዉስጥ እርምጃ ያልወሰደ ስለሆነ በይርጋ ስለሚታገድ እና ባልጸደቀ የሥራ መዘርዝር ምክንያት የአመልካችን የሥራ ዉል ማቋረጡ ከሕግ-ዉጭ ነዉ በማለት ተጠሪ ለአመልካች ልዩ ልዩ ክፍያዎችን እንዱከፍል ወስኗል።
ተጠሪ በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቦ ፍርድ ቤቱ በመ/ ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ በቀን 27/05/2014 ዓ/ም በሰጠው ውሳኔ አመልካች በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 27/3 ስር የተደነገገዉን የይርጋ መቃወሚያ በግልጽ በማንሳት እልተከራከሩም።
የስር ፍርድ ቤት የይርጋ መቃወሚያዉን በራሱ አነሳሽነት በማንሳት ባልቀረበ ክርክር ላይ ተመስርቶ የሰጠዉ ዉሳኔ ክፍል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 182/2 ስር የተደነገገዉን የሚቃረን ነዉ። እንዱሁም የስር ፍርድ ቤት ስንብቱ ሕገ-ወጥ ነው ሲል የወሰነውን የውሳኔ ክፍል በማሻሻል የአመልካች ምስክሮች ከሰጡት ቃል መረዲት እንደሚቻለው የተጠሪ ምስክሮች ቃል በሚያጠናክር መልኩ ቅጥርና ምልመላን በሚመለከት ለዲይሬክቶሬቱ የሚያቀርቡት አመልካች እንደሆኑ እንዱሁም ለጉባኤው ቃለ ጉባኤ እንደሚያቀርቡ የተወዲዲሪዎችን ፕሮፊይል ለኮሚቴው የሚያቀርቡትና ቅጥሩን የሚያሟለ ሰዎችን አጣርተው ለኮሚቴ የሚያቀርቡት አመልካች መሆናቸውን፤ በቅጥር ኮሚቴ ላይ የተመዘገቡ ሰራተኞችን የትምህርት ደረጃና የሥራ ልምድ ከወጣው ማስታወቂያ ጋር አነፃፅሮ በተገቢው ሁኔታ አረጋግጠው የሚያቀርቡት አመልካች መሆናቸው ተረጋግጧል።በመሆኑም አመልካች በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀፅ 13/2 ላይ የተመለከተውን ግዳታ ካለመወጣታቸዉም በተጨማሪ በአንቀፅ 27(1/ሐ) በተደነገገው መሰረት በሥራቸው ላይ የማታለል ተግባር መፈፀማቸውን የሚያሳይ በመሆኑ ስንብቱ ሕጋዊ ነዉ በማለት የስር ፍርድ ቤትን ዉሳኔ በማሻሻል የ137 ቀናት የአመት እረፍት ብቻ ወደ ገንዘብ ተለዉጦ ሉከፈላቸዉ ይገባል ወስኗል።
አመልካች በቀን 28/06/2014 ዓ/ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረበዉ ከላይ በተመለከተዉ መሰረት በተሰጠ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን የአቤቱታቸዉ ይዘት በአጭሩ፡አመልካች የይርጋ ክርክር ቀድሜ በክስ አቤቱታዬ ላይ ለማንሳት እድል አልነበረኝም ነበር።ነገር ግን ተጠሪ መልስ ሲያቀርብ ስንብቱን የፈጸመዉ ከ4 ዓመት በላይ ባስቆጠረና የእኔ የሥራ ድርሻ ባልሆነ ድርጊት መሆኑን ምክንያት በማድረግ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 27/3ን ጠቅሼ ተከራክሬያለሁ።ይግባኝ ሰሚዉ ፍርድ ቤት በዚህ መልኩ ክርክር አቅርቤ እያለሁ የስር ፍርድ ቤት ባልተነሳ ክርክር ላይ ተመስርቶ እንደወሰነ በመቁጠር የስር ፍርድ ቤት መዝገብ አስቀርቦ ሳይመለከት እና ሳይመዝን የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ።እንዱሁም አመልካች በተጠሪ ድርጅት ዉስጥ በሚገኘዉ የቅጥር፣የምደባ እና የዝዉዉር ኮሚቴ ዉስጥ ዉሳኔ ለመስጠት የሚያስችል ድምጽ ሳይኖረኝ በጸሃፉነት የማገለግል ነኝ።ይህንንም ለስር ፍርድ ቤት በማስረጃ አስረድቼ የስር ፍርድ ቤት ተጠሪ ተፈጠረ ባለዉ ችግር አመልካች አንድም አስተዋጽኦ እንደላለኝ አስረድቼ የስር ፍርድ ቤት ስንብቱ ሕገ-ወጥ ነዉ ሲል የሰጠዉ ዉሳኔ ተገቢ ሆኖ እያለ በይግባኝ ሰሚዉ ፍርድ ቤት መሻሩ ስህተት ስለሆነ ይታረምልኝ በማለት አቤቱታቸዉን አቅርበዋል።
የሰበር አጣሪ ችልት አቤቱታውን መርምሮ የስር ፍርድ ቤት ተጠሪ አመልካችን በሕግ አግባብ አሰናብቷል ሲል የወሰነበትን አግባብ ከአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀፅ 27/3 አንጻር ተጠሪ ባለበት እንዱመረመር ትእዛዝ በመስጠቱ ተጠሪ በቀን 22/07/2014 ዓ/ም የተፃፈ መልሱን በማቅረብ፡-አመልካች በስር ፍርድ ቤት ለስንብት ምክንያት የሆኑት ጥፊቶች በይርጋ ቀሪ መሆናቸውን ጠቅሰዉ በፅሁፍም ሆነ በቃል ያቀረቡት ክርክር የለም። በፅሁፍ ያልተነሳ ክርክር በቃል ክርክር ወቅት ሉነሳ አይችልም።ተጠሪ ዉለን ሉያቋርጥ የሚችል ምክንያት መከሰቱን ባወቀ በ1 ወር ጊዜ ዉስጥ በመሆኑ የአመልካች የሥራ ውል የተቋረጠው የይርጋ ጊዜው ከማለፈ በፉት ነው። ስለሆነም የሥር ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሰጠዉ ዉሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 82፣234(1/ሐ) እና 243/3 ስር የተደነገገዉን መሰረት ያደረገ በመሆኑ የተፈጸመ ስህተት ስለላለ የአመልካች አቤቱታ ዉድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክሯል። አመልካችም የመልስ መልስ አቤቱታቸውን አጠናክረው ተከራክረዋል።
ከዚህ በላይ አጠር ባለመልኩ የተገለጸዉ የግራ ቀኙን ክርክርና በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ዉሳኔዎችን ይዘት የሚመለከት ሲሆን እኛም የሰበር አጣሪ ችልት የያዘዉን ጭብጥ መሰረት በማድረግ በስር ፍርድ ቤቶች በተሰጠ ዉሳኔ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ መርምረናል።
እንደመረመርነዉም አመልካች በተጠሪ ላይ ክስ የመሰረቱት ተጠሪ ከእኔ ሥራ ጋር ባልተገናኘ ምክንያት ከሕግ-ዉጭ ከሥራ አሰናብቶኛል በማለት ነዉ።ተጠሪ ደግሞ ለክሱ በሰጠዉ መልስ የአመልካች የሥራ ዉል የተቋረጠዉ በድርጅቱ በሚገኙ ክፍት የሥራ መደቦች ሰራተኛ በቅጥር፣በዝዉዉር እና በምደባ ሲያሟለ አመልካች ከድርጅቱ መመሪያ ዉጭ በሆነ አኳኋን ለግል ጥቅማቸው በማሰብ በሥራቸዉ ላይ የማታለል ተግባር በመፈፀም የተጠሪን አገልግልት በሚያቃዉስ አኳኋን የተዛባና የተሳሳተ መረጃ በመስጠት የተለያዩ የሥራ ቅጥሮችና ዝውውሮች በመፈጸም በፈጠሩት ጥፊት ምክንያት ስለሆነ ስንብቱ ‛ሕጋዊ ነዉ ሲል ተከራክሯል። አመልካች በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ባሰሙት የቃል ክርክር ተጠሪ ለስንብቱ ምክንያት ያደረጋቸዉ ቅጥሮች ከሁለትና ሦስት ዓመት በፉት የተፈጸሙ በመሆኑ አሁን ላይ የሥራ ዉለን ለማቋረጥ ምክንያት ሉሆኑ አይችለም በማለት መከራከራቸዉን የዉሳኔዉ ይዘት ያሳያል። የስር ፍርድ ቤት ይህንን የአመልካችን ክርክር መሰረት በማድረግ ተፈጸመ የተባለዉ ጥፊት በባህሪዉ ተደብቆ ሉቆይ የማይችል ሆኖ ሳለ ጥፊቱ ከታወቀ ወይም መታወቅ ካለበት ጊዜ አንስቶ በ30 ቀናት ዉስጥ አመልካች ላይ እርምጃ ሳይወስድ ቆይቶ የጊዜ ገደቡ ካለፈ በኋላ የአመልካችን የሥራ ቅጥር ዉል ማቋረጡ ስንብቱን ሕገ-ወጥ ያደርገዋል በማለት እንዱሁም ስንብቱ የተፈጻመዉ በቂና ሕጋዊ ምክንያት ሳይኖር ነዉ በማለት የወሰነ ሲሆን ይግባኝ ሰሚዉ ፍርድ ቤት ደግሞ በስር ፍርድ ቤት በዚህ መልኩ የተወሰነዉ አመልካች በግልጽ የይርጋ መከራከሪያ ባላነሱበት ነዉ በማለት ሽሮ ወስኗል።
አንድ አሰሪ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 27/3 መሰረት ሰራተኛዉ ያለማስጠንቀቂያ ከሥራ የሚያሰናብተዉን ድርጊት መፈጸሙን አዉቆ ይሄዉ ድርጊት መኖሩን ካወቀበት ቀን ጀምሮ በ30 የሥራ ቀናት ዉስጥ የሥራ ዉለን ለማቋረጥ ባለዉ መብት ካልሰራበት መብቱ በይርጋ እንደሚታገድ ተደንግጓል። በመሰረቱ ይርጋ(limitation) ከሚያስከትለዉ ዉጤት አንጻር ሁለት ገጽታዎች አለት።ይኸዉም አንደኛዉ መብት የሚሰጥ(የሚያስገኝ) ይርጋ (acquisitive prescription) ሲሆን ሁለተኛዉ ደግሞ መብት የሚያሳጣ (መብት ቀሪ የሚያደርግ) ይርጋ(extinctive prescription) በሚል የሚታወቁ ናቸዉ። የኋለኛዉ አይነት ይርጋ ባለመብቱ (ባለገንዘቡ) በሕግ በተመለከተዉ የጊዜ ገደብ ዉስጥ መብቱን(ጥቅሙን ወይም ገንዘቡን) ሳይጠይቅ ቆይቶ ጊዜዉ ካለፈበት በመብቱ መስራት እንዲይችል የሚያደርግ (right killer limitation) ነዉ። መብት ለማስከበር የሚቀርብ ክስ በሕጉ በተመለከተዉ የጊዜ ገደብ ዉስጥ ባለመቅረቡ ክስ የማቅረብ መብትን ቀሪ የሚያደርግ ይርጋም (limitation of action) በዚህ ማዕቀፍ ዉስጥ የሚታይ ነዉ። የዚህ ይርጋ ላላዉ ገጽታዉ ከላይ በተጠቀሰዉ የአዋጁ አንቀጽ 27/3 ስር እንደተመለከተዉ የአሰሪዉን ዉል የማቋረጥ መብት የሚያሳጣ ነዉ።
በዚህ ይርጋ መሰረት አሰሪዉ በሕጉ በተመለከተዉ ጊዜ የሰራተኛዉን ዉል የማቋረጥ እርምጃ ሳይወስድ ቆይቶ ጊዜዉ ካለፈ በኋላ ዉል ያቋረጠ እንደሆነ ሰራተኛዉ የጊዜ ገደቡ ባለፈበት ድርጊት ተጠያቂ እንዲይሆን መብት ስለሚሰጠዉ ሰራተኛዉ የክስ ምክንያት በማድረግ ስንብቱ ሕገ-ወጥ ነዉ እንዱባልለት መከራከር ይችላል። ሰራተኛዉ በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 27/3 ድንጋጌ ላይ ተመስርቶ በክስ አቤቱታዉ ላይ የክስ ምክንያት አድርጎ ለመግለጽ የሚገደደዉ የሥራ ዉል የማቋረጥ እርምጃ በአሰሪዉ የተወሰደዉ ድርጊቱ መፈጸሙን አሰሪዉ ከአወቀ ከ30 የሥራ ቀናት በኋላ መሆኑን ክሱን ሲያቀርብ እዉቀቱ ያለዉ እንደሆነ ነዉ።ይህ በአዋጁ አንቀጽ 27/3 ስር የተደነገገዉ ይርጋ ክስ የማቅረብ መብትን ቀሪ የሚያደርግ ባለመሆኑ ሰራተኛዉ የተሰናበተበትን ምክንያት፣ ምክንያቱ የተከሰተበትን ቀን እና ምክንያቱ የተከሰተበትን ቀን አሰሪዉ መቼ እንዲወቀ በግልጽ በማሰናበቻ ጽሁፍ ላይ ሳይገለጽለት በመሰናበቱ ምክንያት ወይም በልላ ምክንያት ለማወቅ ያልቻለ እንደሆነና እነዚህን ፍሬ ነገሮች ያወቀዉ አሰሪዉ ተከሶ በሰጠዉ መከላከያ መልስ ላይ ከተገለጸዉ ፍሬ ነገርና ከቀረበዉ ማስረጃ መነሻ የሆነ እንደሆነ ክሱን ማሻሻል የግድ ከሆነ ክሱን በማሻሻል የአዋጁን አንቀጽ 27/3 ይዘት ባገናዘበ መልኩ በማሻሻል አሉያም ክስ በሚሰማበት ጊዜ በቃል አንስቶ መከራከር ይችላል። በሁለቱም መንገድ በግልጽ የክርክር ነጥብ ሆኖ በሰራተኛዉ ሲነሳ አሰሪዉም በሥነ ሥርዓት ሕጉ አግባብ የበኩለን ክርክር እንዱያሰማ ከተደረገ በኋላ ዉሳኔ ላሰጥበት የሚገባ የክርክር አይነት ነዉ። እንደሚታወቀዉ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 234(1/ሐ) እና 244(2/ሰ እና 3) ስር በተደነገገዉ መሰረት የከሳሽን ክስ የማቅረብ መብት የሚያስቀር የይርጋ መቃወሚያ በተከሳሹ በመከላከያ መልስ ላይ ተጽፍና በመጀመሪያ ክስ የሚሰማበት ሥነ ሥርዓት ከመከናወኑ በፉት መቅረብ አለበት። እነዚህ ድንጋጌዎች ክስ የማቅረብ መብትን ቀሪ የሚያደርግ ይርጋን ጨምሮ ላልች የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎችን ተከሳሹ ስለሚያቀርብበት ሥርዓት ለመደንገግ የተቀረጹ በመሆናቸዉ ሰራተኛ በከሳሽነት ዘንግ ሆኖ የአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 27/3ን ጠቅሶ ለሚያቀርበዉ መከራከሪያ ተፈጻሚነት የላቸዉም።
በመሆኑም ከሳሽ አስቀድሞ እንዱህ አይነት መከራከሪያ በክሱ ላይ አልገለጸም በሚል ምክንያት መከራከሪያ አድርጎ እንዲያነሳ ሉከለከል አይገባም።ዋናዉ ሉረጋገጥ የሚገባዉ ነገር እንዱህ አይነት ክርክር በተቻለ ፍጥነት ሰራተኛዉ ስለጉዲዩ እወቀት እንዲገኘ የመጀመሪያዉ የክስ አሰማም ሥነ ሥርዓት ከመጠናቀቁ በፉት መቅረብ መቻለ ነዉ። እዚህ ላይ ማስተዋል የሚገባዉ ሰራተኛዉ የአዋጁን አንቀጽ 27/3ን በመጥቀስ ባይከራከርም አሰሪዉ የሥራ ዉለን የማቋረጥ እርምጃ የወሰደዉ ድርጊቱ መፈጸሙን ካወቀ ከ30 የሥራ ቀናት በኋላ መሆኑን ገልጾ ከተከራከረ ይህ አይነት ክርክር በአዋጁ አንቀጽ 27/3 ስር የተመለከተዉን ይርጋ የሚመለከት ነዉ ወይስ የፍሬ ነገር ክርክር የሚመለከት ነዉ?
ለእንዱህ አይነት ክርክር ተፈጻሚነት ያለዉ ድንጋጌስ የትኛዉ ነዉ የሚለዉን የመለየት ኃላፉት ክርክሩን የሚሰማዉ ፍርድ ቤት ኃላፉነት መሆኑን ነዉ።
በያዝነዉ ጉዲይ አመልካች በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ክሱ በተሰማበት እለት ባሰሙት የቃል ክርክር ተጠሪ ለስንብቱ ምክንያት ያደረጋቸዉና አመልካች ጥፊት ፈጽመዋል በማለት የገለጻቸዉ ቅጥሮች ከሁለትና ሦስት ዓመት በፉት የተፈጸሙ ስለሆኑ አሁን ላይ የሥራ ዉላን ለማቋረጥ ምክንያት ሉሆኑ ስለማይችለ ስንብቱ ሕገ-ወጥ ነዉ የሚል ይዘት ያለዉን ክርክር ማቅረባቸዉን የዉሳኔዉ ግልባጭ ያሳያል።አመልካች በዚህ መልኩ ክርክር ሲያቀርቡ በግልጽ የአዋጁን አንቀጽ 27/3ን ጠቅሰዉ ባይከራከሩም ፍርድ ቤቱ አመልካች በዚህ መልኩ ያቀረቡት ክርክር በአዋጁ አንቀጽ 27/3 ስር የተደነገገዉን ይርጋ የሚመለከት ነዉ በማለት ይህንን የአመልካችን ክርክር መሰረት በማድረግ ተፈጸመ የተባለዉ ጥፊት በባህሪዉ ተደብቆ ሉቆይ የማይችል ሆኖ ሳለ ተጠሪ ጥፊቱ ከታወቀ ወይም መታወቅ ካለበት ጊዜ አንስቶ በ30 ቀናት ዉስጥ አመልካች ላይ እርምጃ ሳይወስድ ቆይቶ የጊዜ ገደቡ ካለፈ በኋላ የአመልካችን የሥራ ቅጥር ዉል ማቋረጡ ስንብቱን ሕገ-ወጥ ያደርገዋል የሚል ድምዲሜ ላይ ደርሷል።በእኛም እምነት አመልካች በዚህ መልኩ ያቀረቡት መከራከሪያ ለስንብቱ ምክንያት የሆነዉን ድርጊትና ድርጊቱ የተፈጸመበትን ጊዜ መሰረት በማድረግ የቀረበ በመሆኑ በአዋጁ አንቀጽ 27/3 ስር የተደነገገዉን ይርጋ የሚመለከት ነዉ መባለ ተገቢ ነዉ። ሆኖም ፍርድ ቤቱ ወደእዚህ ድምዲሜ ከመድረሱ በፉት በዚህ መልኩ አመልካች ያቀረቡት ክርክር ተጠሪ ዉለን በማቋረጥ የወሰደዉን እርምጃ ሕገ-ወጥ የማድረግ አቅም ያለዉ መሰረታዊ መከራከሪያ ከመሆኑ እና አስቀድሞ በክሱ ላይ የክሱ ምክንያት ሆኖ ያልተገለጸ መከራከሪያ ከመሆኑ አንጻር አይቶ ላላኛዉ ወገን(ተጠሪ) የበኩልን ክርክር እንዱያሰማ እድል መስጠቱን ዉሳኔዉ አያሳይም።በዚህ መልኩ በአንደኛዉ ተከራካሪ የክርክር ነጥብ ሆኖ በተነሳና በክርክሩ ዉጤት ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተጽእኖ ባላቸዉ ክርክሮች ላይ የላላዉ ተከራካሪ ወገን ክርክር ሳይሰማ የሚሰጥ ዉሳኔ የእኩልነትና የፍትሀዊነት መርሆዎችን የሚጥስ ስለሚሆን መሰረታዊ የሆነ የክርክር አመራር ጉድለት ነዉ።
ሲጠቃለል ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተዉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከላይ በተገለጸዉ አግባብ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ክርክር አመራር ላይ የታየዉን ጉድለት ማረም ሲገባዉ አመልካች በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 27/3 የተመለከተዉን ይርጋ የሚመለከት መከራከሪያ ከላይ በተመለከተዉ አግባብ በግልጽ አንስተዉ ተከራክረዉ እያለ አመልካች የአዋጁን አንቀጽ 27/3ን በመጥቀስ እና በክሳቸዉ ላይ የክስ ምክንያት አድርገዉ አለመግለጻቸዉን ምክንያት በማድረግ ወይም ደግሞ ክሱ ሲሰማ ከዚህ አኳያ ላቀረቡት ክርክር ተገቢዉን ትኩረት ባለመስጠትና ባለመቀበል አመልካች በመከራከሪያነት ያላነሱትን የስር ፍርድ ቤት በራሱ አነሳሽነት ማንሳቱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 182/2 ስር የተደነገገዉን የሚቃረን ነዉ በማለት ሽሮ ጉዲዩን በስረ ነገሩ አይቶ ዉሳኔ የሰጠበት መንገድ ሉታረም የሚገባ መሰረታዊ የሆነ የክርክር አመራር ጉድለት በመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ብለናል።ስለሆነም ተከታዩን ወስነናል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 11/09/2013ዓ/ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 27/05/2014ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ተሽረዋል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መዝገቡን አንቀሳቅሶ ተጠሪ ለስንብቱ ምክንያት ያደረጋቸዉና አመልካች ጥፊት ፈጽመዋል በማለት የገለጻቸዉ ቅጥሮች ከሁለትና ሦስት ዓመት በፉት የተፈጸሙ ስለሆኑ አሁን ላይ የሥራ ዉላን ለማቋረጥ ምክንያት ሉሆኑ ስለማይችለ ስንብቱ ሕገ-ወጥ ነዉ በማለት አመልካች ባቀረቡት ክርክር ላይ ተጠሪ የበኩለን ክርክር እንዱያሰማ በማድረግ ተጠሪ የአመልካችን የሥራ ዉል ያቋረጠዉ ለስንብቱ ምክንያት ያደረገዉ ድርጊት መፈጸሙን ከአወቀ 30 የሥራ ቀናት ሳያልፍ ነዉ ወይስ አይደለም? 30 የሥራ ቀናት ካለፈ በኋላ የተወሰደ የስንብት እርምጃ ከሆነም ይህ ላሆን የቻለበትንና ሕጋዊ ዉጤቱ እና እንደነገሩ ሁኔታ ላልች መከራከሪያዎችንም በተመለከተ ከተገቢዉ ሕግ አንጻር መርምሮ ዉሳኔ እንዱሰጥ ጉዲዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 343/1 መሰረት መልሰንለታል።
ግራ ቀኝ በዚህ ችልት ያወጡትን ወጭ የየራሳቸዉን እንዱችለ ተወስኗል።
ት እ ዛ ዝ
የዉሳኔዉ ግልባጭ ለሥር ፍርድ ቤት ይተላለፍ። ግራ ቀኙ ሲጠይቁም ግልባጩ ይሰጣቸዉ።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።