የአሰሪና ሰራተኛ ሕግ ያስቀመጠው አስገዲጅ የክርክር መፍቻ መንገድ ሳይጣስ በሕጉ ከተጠቀሱት ዘዳዎች በተሻለ ሁኔታ የጊዜ፣ የሰው እና የገንዘብ ሀብት የሚቆጥብ እና በአሰሪና ሰራተኛ መካክል የሚከሰት አለመግባባት ፍትሀዊ በሆነ አኳኋን የሚፈታበትን ዘዳ ወይም የስራ ክርክር እልባት የሚያገኝበትን ስርዓት በኀብረት ስምምነት መዘርጋትን ህጉ የማይከለክል ስለመሆኑ አሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 136፣142፣144 እና 145 ለስራ ክርክር ችልት ክስ ማቅረብ የሚቻለው በኀብረት ስምምነት በተመለከተው መሰረት ቅሬታ ለቅሬታ ሰሚ አካል ከቀረበ በኋላ በሆነ ጊዜ የይርጋ ጊዜ መቆጠር ያለበት ቅሬታ ሰሚ አካል ውሳኔ ከሰጠበት ቀን ቀጥል ካለው ቀን ጀምሮ ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 164/1
No summary available.
ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ ተሾመ ሽፈራዉ ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግሥቱ ነጻነት ተገኝ አመልካች፡- አቶ አስራኤል ለላ ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መዝገቡ ተመርምሮ ከዚህ የሚከተለዉ የፍርድ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የግል የሥራ ክርክርን የሚመለከት የይርጋ ጊዜ አፈጻጸም የሚመለከት ነዉ። አመልካች በፋደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በተጠሪ ላይ በቀን 01/07/2012 ዓ/ም ጽፈዉ ባቀረቡት ክስ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከቀን 09/03/2006 ዓ/ም ጀምሮ ተቀጥረዉ እየሰሩ በቀን 12/01/2012ዓ/ም በተፃፈ ደብዲቤ ከሕግ አግባብ ዉጭ እንዲሰናበታቸዉ በመግለጽ ዉዝፍ ደመወዛቸዉን ከፍል ተጠሪ ወደ ሥራ እንዱመልሳቸዉ እንዱወሰን አሉያም የሕገ-ወጥ ስንብት ተከትል የሚከፈለ ክፍያዎች ተጠሪ እንዱከፍላቸዉ ዲኝነት ጠይቀዋል።
ተጠሪ ለክሱ በሰጠዉ መልስ ባቀረበዉ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ የአመልካች የሥራ ውል የተቋረጠው ከቀን 20/01/2012 ዓ/ም ጀምሮ ነው። አመልካች ክስ ያቀረቡት ደግሞ በቀን 01/07/2012 ዓ/ም ማለትም የአመልካች የሥራ ውል ከተቋረጠ ከአምስት ወራት በኋላ ነው። አንድ ሰራተኛ ወደ ሥራ ለመመለስ የሚያቀርበው ክስ የሥራ ውለ በተቋረጠ በ3 ወር ጊዜ ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ የሚታገድ በመሆኑ አመልካች ክስ ያቀረቡት በይርጋ ከታገደ በኋላ በመሆኑ የቀረበው ክስ ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክሯል።
ፍርድ ቤቱ በመ/ ላይ የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃዎችን መርምሮ በቀን 08/01/2013 ዓ/ም በሰጠው ውሳኔ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀፅ 163/2 መሰረት ሰራተኛው የሥራ ውለ ከሕግ ውጪ ተቋርጦብኛል በማለት ወደ ሥራው ለመመለስ የሚያቀርበው ክስ ውለ በተቋረጠ በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ ይታገዲል በማለት ደንግጓል። የአመልካች የሥራ ውል በቀን 12/01/2012 ዓ/ም በተፃፈ ደብዲቤ ከመስከረም 20 ቀን 2012 ዓ/ም ጀምሮ የተቋረጠ መሆኑን ግራ ቀኙ ተከራካሪዎች ካቀረቡት ማስረጃ መረዲት ተችሎል። አመልካች ክስ ያቀረቡትና በሬጅስትራር በኩል ያስመሩት ደግሞ በቀን 01/07/2012 ዓ/ም ነው። አመልካች የሥራ ውለ ከተቋረጠበት ጊዜ ጀምሮ ስንብቱ ከሕግ ውጪ ስለሆነ ወደ ሥራዬ ልመለስ ብለው ክስ እስካቀረቡበት ጊዜ ድረስ ያለው ጊዜ ሲቆጠር ደግሞ አምስት ወር ከ9 ቀን ካለፈው በኋላ ክሱ እንደቀረበ የሚያረጋግጥ ነው። ስለሆነም አመልካች የስራ ውለ በተቋረጠ በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ ክሱን ሳያቀርቡ የቆዩት ጉዲዩ በዱሲፕሉን ኮሚቴ እየታየ በመቆየቱ ምክንያት ነዉ በማለት ያቀረቡትም ክርክር ቢሆን በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 138 እና 145 መሰረት የዱስፕሉን ኮሚቴ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ለመወሰን ሥልጣን የተሰጠዉ አካል ባለመሆኑ በአዋጁ አንቀጽ 165(1 እና 2) መሰረት የይርጋውን ጊዜ መቆጠር የሚያቋርጥ ምክንያት ባለመሆኑ አመልካች የሥራ ዉላ ከሕግ ዉጭ ስለተቋረጠ ወደ ሥራዬ እንድመለስ ይወሰንልኝ በማለት ያቀረቡት ክስ በአዋጁ አንቀጽ 163/2 መሰረት በይርጋ የታገደ ስለሆነ ክሱ ተቀባይነት የለውም በማለት ዉድቅ በማድረግ ወስኗል።
አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ችልቱ በመ/ ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ በቀን 17/02/2014 ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ የስር ፍርድ ቤትን ዉሳኔ በማፅናት ወስኗል።
አመልካች በቀን 16/05/2014 ዓ/ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረቡትም ከላይ በተመለከተዉ መሰረት በተሰጠ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን የአቤቱታቸዉ ይዘት በአጭሩ፡- የስር ፍርድ ቤቶች በሥራ ክርክር ጉዲይ ላይ ውሳኔ የመስጠት መብት ያላቸው የመንግስት አካላት የሆኑት የሥራ ክርክር ችልትና ቦርድ ብቻ ናቸው በማለት የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 2/5 ስር የተደነገገዉን የተከተለ አይደለም።የህብረት ስምምነት በአዋጁ አንቀጽ 135/2 ስር በተደነገገዉ መሰረት በሕግ ላይ ከተደነገገዉ የተሻለ ጥቅም የሚሰጥ ከሆነ ተፈጻሚነት አንዲለዉ የተደነገገ ሆኖ እያለ በሕብረት ስምምነት መሰረት የተቋቋመዉ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይን የመወሰን ሥልጣን የለዉም በማለት የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ዉሳኔ ይህንን ያገናዘበ አይደለም።በተጠሪና በሰራተኞች መካከል በተቋቋመዉ በ12ኛዉ የሕብረት ስምምነት አንቀጽ 38 ተራ ቁጥር 7.2 እና 7.61 እና አንቀጽ 37 ስር ሰራተኛዉ በተወሰደበት የሥንብት ዉሳኔ ላይ ለቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ይግባኝ ማቅረብ እንደሚችል ተደንግጓል።ይህ የዲኝነት ሥልጣን በመሆኑ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴዉ በአዋጁ አንቀጽ 165/1 መሰረት የሥራ ክርክር የሚወስን አካል በመሆኑ በቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ እየታየ የቆየበት ጊዜ የይርጋዉን ጊዜ የሚያቋርጥ ምክንያት ሆኖ እያለ የሥር ፍርድ ቤቶች የአመልካች ክስ የማቅረብ መብት በይርጋ ቀሪ ሆኗል በማለት የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ ይታረምልኝ በማለት አቤቱታቸዉን አቅርበዋል።
የሰበር አጣሪ ችልት አቤቱታውን መርምሮ በተጠሪ ዘንድ በተቋቋመ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ የአመልካች ቅሬታ ሲታይ ቆይቶ የተወሰነ መሆኑ ባልተካደበት ሁኔታ የስር ፍርድ ቤት የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲዮችን ለማስፈፀም የተቋቋመ አካል አይደለም በማለት ክሱን በይርጋ ውድቅ ያደረገበት አግባብ ተጠሪ ባለበት እንዱመረመር ትእዛዝ በመስጠቱ ተጠሪ በቀን 05/09/2014 ዓ/ም የተፃፈ መልስ ያቀረበ ሲሆን ይዘቱም በአጭሩ፡በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀፅ 165(1 እና 2) የተመለከተው የይርጋ ማቋረጫ ምክንያት የሥራ ክርክርን ለሚወስን ባለስልጣን ክስ ቀርቦ የመጨረሻ ውሳኔ እስከሚሰጥበት ቀን ድረስ ወይም የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ በሥራ ላይ ለማዋልና ለማስፈፀም ኃላፉነት ለተሰጠው ባለስልጣን አቤቱታ ቀርቦ የመጨረሻ ውሳኔ በፅሁፍ እስከሚሰጥበት ቀን ድረስ ነው።አመልካች ቅሬታ ያቀረቡት ለድርጅቱ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ እንጂ የዲኝነት ሥልጣን ለተሰጠዉ አካል አይደለም። በአዋጁ አንቀፅ 165(1 እና 2) እንዱሁም የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ በቀን 20/04/1998 ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ የሥራ ክርክርን ለሚወስን ሥልጣን ያላቸዉ ባለስልጣን ፍርድ ቤቶችና የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ወሳኝ ቦርድ ናቸዉ ሲል አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል። የድርጅቱ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ እንደ ዲኝነት አካል በሁለት ተከራካሪ ወገኖች መካከል በሚደረገው ክርክር ውሳኔ ላሰጥ የሚችል አካል አይደለም። በመሆኑም አመልካች በሕጉ የተደነገገዉ ክስ ማቅረቢያ የይርጋ ጊዜ ካለፈ በኋላ ክሱን ማቅረባቸዉ ተረጋግጦ የአመልካች ክስ በይርጋ ታግዶል ተብል በስር ፍርድ ቤቶች ዉሳኔ በመሰጠቱ የተፈጸመ ስህተት የለም በማለት ተከራክሯል። አመልካችም በቀን 19/09/2014 ዓ/ም የተጻፈ የመልስ መልስ በማቅረብ ተከራክረዋል።
ከዚህ በላይ አጠር ባለመልኩ የተመለከተዉ የግራ ቀኙ ክርክርና በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ዉሳኔዎች ይዘት ሲሆን እኛም የሰበር አጣሪ ችልት የያዘዉን ማስቀረቢያ ጭብጥ ከግምት በማስገባት በስር ፍርድ ቤቶች በተሰጠ ዉሳኔ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ መርምረናል።
እንደመረመርነዉም አመልካች በተጠሪ ላይ ክስ የመሰረቱት ተጠሪ በቀን 12/01/2012 ዓ/ም በተፃፈ ደብዲቤ ከሕግ አግባብ ዉጭ እንዲሰናበታቸዉ በመግለጽ ተጠሪ ወደ ሥራ ገበታቸዉ እንዱመልሳቸዉ፤ይህ የማይቻል ከሆነም ሕገ-ወጥ ስንብት ተከትለዉ የሚከፈለ ክፍያዎችን ተጠሪ እንዱከፍላቸዉ እንዱወሰን ዲኝነት በመጠየቅ ነዉ።ተጠሪ ክሱ የቀረበዉ የ3 ወር የይርጋ ጊዜ ካለፈ በኋላ በመሆኑ የአመልካች ክስ የማቅረብ መብት በይርጋ ቀሪ ስለሆነ ክሱ ዉድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተቃዉሟል።ተጠሪ አመልካችን ያሰናበተዉ ከቀን 20/01/2012 ዓ/ም ጀምሮ እንደሆነ፣አመልካች በተጠሪ የተወሰደባቸዉን የስንብት እርምጃ በመቃወም በተጠሪ ባንክ ኅብረት ስምምነት መሰረት ለተቋቋመ ቅሬታ ሰሚ አካል ቅሬታቸዉን ያቀረቡት በቀን 27/01/2012 ሆኖ ቅሬታ ሰሚዉ አካል በጉዲዩ ላይ ዉሳኔ ሰጥቶ ዉሳኔዉን ለአመልካች ያሳወቀዉ ደግሞ በቀን 07/04/2012ዓ/ም ለአመልካች በጻፈዉ ደብዲቤ ነዉ። በመቀጠል አመልካች በተጠሪ ላይ በስር ፍርድ ቤት ክስ የመሰረቱት ደግሞ በቀን 01/07/2012 ዓ/ም መሆኑ በግራ ቀኙ የታመነና በስር ፍርድ ቤትም የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነዉ።የስር ፍርድ ቤት የተጠሪን መቃወሚያ በመቀበል ክሱን ዉድቅ ያደረገዉ የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አስመልክቶ የሚነሱ ክርክሮችን ለመዲኘት በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሰረት ሥልጣን የተሰጠዉ አካል ባለመሆኑ በቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ እየታየ በነበረበት የባከነዉ ጊዜ የይርጋ ማቋረጫ ላሆን አይችልም በሚል ምክንያት ነዉ። የስር ፍርድ ቤት መሰረት ያደረገዉ ምክንያት ይህ ቢሆንም ተጠሪ በኅብረት ስምምነት የተቋቋመ የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ መኖሩንና ለዚሁ አካል አመልካች ቅሬታዉን አቅርቦ ሲታይ መቆየቱን አልካደም።
በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 163/2 መሰረት ሰራተኛዉ ከሕግ ዉጭ የሥራ ዉለ ተቋርጦብኛል በማለት ወደ ሥራ ለመመለስ የሚያቀርበዉን ክስ ዉለ በተቋረጠ በ3 ወር ጊዜ ዉስጥ ካላቀረበ በይርጋ እንደሚታገድ ደንግጓል።በልላ በኩል በዚሁ ሕግ አንቀጽ 163/4 ስር የሥራ ዉል በመቋረጡ ምክንያት በሰራተኛዉም ሆነ በአሰሪዉ የሚቀርብ ማንኛዉም የክፍያ ጥያቄ የሥራ ዉለ በተቋረጠ በ6 ወር ጊዜ ዉስጥ ካልቀረበ በይርጋ እንደሚታገድ ተደንግጓል።ከእነዚህ ድንጋጌዎች የምንገነዘበዉ የሥራ ዉል መቋረጥን መነሻ በማድረግ ወደ ሥራ ለመመለስ በሚቀርብ ክስ እና በዚሁ ምክንያት ክፍያ ለማስከፈል ዲኝነት ተጠይቆ በሚቀርብ ክስ ላይ ተፈጻሚ የሚደረጉ የይርጋ ጊዜያት የተለያዩ በመሆናቸዉ የይርጋ መቃወሚያ ሲቀርብም ሆነ ዉሳኔ ሲሰጥ የቀረበዉን የዲኝነት ጥያቄ መሰረት ማድረግ ይገባል።
በያዝነዉ ጉዲይ የአመልካች ቀዲሚ የዲኝነት ጥያቄ ወደ ሥራ እንዱመለሱ እንዱወሰንላቸዉ የጠየቁበት ቢሆንም በአማራጭ ደግሞ ወደ ሥራ እንዱመለሱ የማይወሰንበት ምክንያት ካለ በሕገ-ወጥ መንገድ የሥራ ዉላቸዉ በመቋረጡ በሕጉ መሰረት ሉከፈላቸዉ የሚገባ ልዩ ልዩ ክፍያ እንዱከፈላቸዉ ዲኝነት መጠየቃቸዉን የክሳቸዉ ይዘት ያሳያል። የስር ፍርድ ቤት በአዋጁ አንቀጽ 163/2 ስር የተደነገገዉን መሰረት በማድረግ ክሱ የቀረበዉ የ3 ወር የይርጋ ጊዜ ካለፈ በኋላ ነዉ በሚል ሲወስን አመልካች በአማራጭ የጠየቁትን ዲኝነት ጥያቄ መሰረት በማድረግ ከአዋጁ አንቀጽ 163/4 አንጻር ክስ የማቅረብ መብታቸዉ በይርጋ ቀሪ መሆን አለመሆኑን ሳይመረምር ክሱን ሙለ በሙለ ዉድቅ በማድረግ መዝገቡ እንዱዘጋ የሰጠዉ ዉሳኔ እና ይግባኝ ሰሚዉ ፍርድ ቤት ይህንን ሳያርም ያለፈበት አግባብ የክርክር አመራርና የሕግ አተገባበር ጉድለት ያለበት በመሆኑ ሉታረም የሚገባዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ።
በተጨማሪም በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 29 ስር የኅብረት ስምምነት ማናቸዉንም የሥራ ግንኙነቶችንና የሥራ ሁኔታዎችን የሚመለከቱ ጉዲዮች እንደሚሸፍን ተደንግጓል።እንዱሁም በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 130(3 እና 4) ላይ … ስለዱሲፕሉን አፈጻጸም፣ ስለሥራ ደንብና ስለቅሬታ አቀራረብ ሥነ ሥርዓት በኅብረት ስምምነት ላይ መሸፈን እንደሚቻል ተደንግጓል። ይህም የሚያሳየዉ የዱሲፕሉን ክስ አቀራረብና ዉሳኔ አሰጣጥ፣ ቅሬታ በማን፣ ለማን እና መቼ ላቀርብ እንደሚችልና ቅሬታ ስለሚሰማበት ሥነ ሥርዓት እና ስለዉሳኔ አሰጣጥ በኅብረት ስምምነት ላይ መወሰን እንደሚቻል ነዉ።በተጨማሪም በአዋጁ አንቀጽ 135/2 ስር እንደተመለከተዉ በተመሳሳይ ጉዲይ ላይ በሕግ ከተደነገገዉ ይልቅ የኅብረት ስምምነቱ ለሰራተኞች የበለጠ ጥቅም የሚያስገኝ ሆኖ ሲገኝ ስምምነቱ ተፈጻሚ እንደሚሆን ተደንግጓል።በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ መሰረት የሥራ ክርክር በስምምነት፣ በግልግል ዲኝነት አማራጭ የክርክር መፍቻ ዘዳዎች አሉያም በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ወሳኝ ቦርድ እና በፍርድ ቤት በሚደረግ የሙግት ሥርዓት(litigation) ታይቶ እልባት እንዱያገኝ ላደረግ እንደሚችል በአንቀጽ 136፣142፣144 እና 145 ተደንግጓል። ሕጉ ያስቀመጠዉ አስገዲጅ የክርክር መፍቻ መንገድ ሳይጣስ በሕጉ ከተጠቀሱት በተሻለ ሁኔታ የጊዜ፣ የሰዉ እና የገንዘብ ሀብት የሚቆጥብ እና በአሰሪና ሰራተኛ መካከል የሚከሰት አለመግባባት ፍትሐዊ በሆነ አኳኋን የሚፈታበትን ዘዳ ወይም የሥራ ክርክር እልባት የሚያገኝበትን ሥርዓት በኅብረት ስምምነት መዘርጋትን ሕጉ አይከለክልም። በመሆኑም አሰሪም ሆነ ሰራተኛዉ በአዋጁ የተዘረጉትን የሥራ ክርክር የሚታይባቸዉን ዘዳዎች ከመጠቀማቸዉ በፉት በቅድሚያ በኅብረት ስምምነቱ በተቋቋመዉ የዱስፕሉን ወይም የቅሬታ ሰሚ አካል ጉዲያቸዉ እንዱታይ የማድረግ መብትም ሆነ ከኅብረት ስምምነቱ የመነጭ ግዳታ ይኖርባቸዋል።
በያዝነዉም ጉዲይ በተጠሪ ባንክ በኅብረት ስምምነት የተቋቋመ የቅሬታ ሰሚ አካል መኖሩ በተጠሪ የታመነ ጉዲይ ነዉ።አመልካች ተጠሪ ከሕግ-ዉጭ የሥራ ዉላቸዉን አቋርጧል የሚለዉን የግል የሥራ ክርክር የሚመለከተዉን ክሳቸዉን ወደ ፍርድ ቤት ከማቅረባቸዉ በፉት በኅብረት ስምምነት በተቋቋመዉ ቅሬታ ሰሚ አካል እንዱታይላቸዉ ቅሬታቸዉን ማቅረባቸዉ ኅብረት ስምምነቱን መሰረት ያደረገ ነዉ።በዚህ መልኩ በኅብረት ስምምነቱ ቅሬታ የሚሰማበት ሥርዓት የተዘረጋዉ በአዋጁ ከተዘረጉት አለመግባባትና ክርክር መፍቻ መንገድች የተሻለ ጥቅም እንደሚያስገኝ በማሰብ ነዉ ተብል ይገመታል።
ሲጠቃለል አመልካች ክሳቸዉን ለፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ማቅረብ የሚችለት በኅብረት ስምምነቱ ለተቋቋመዉ ቅሬታ ሰሚ አካል ያቀረቡት ቅሬታ እልባት ከተሰጠ በኋላ ነዉ።በዚህ መሰረት በተጠሪ በቀን 20/01/2012ዓ/ም የስንብት ዉሳኔ ተላልፍባቸዉ አመልካች ለቅሬታ ሰሚዉ አካል አቤቱቻዉን በቀን 27/01/2012 ያቀረቡ ሲሆን ቅሬታ ሰሚዉ አካል ስንብቱ ሕጋዊ ነዉ በማለት በቅሬታዉ ላይ የሰጠዉን ዉሳኔ ለአመልካች ያሳወቀዉ ደግሞ በቀን 07/04/2012ዓ/ም ነዉ። በመቀጠል አመልካች በተጠሪ የተፈጸመባቸዉ የስንብት እርምጃ ሕገ-ወጥ ነዉ ተብል ተጠሪ ወደ ሥራ እንዱመልሳቸዉ አሉያም የተለያዩ ክፍያዎችን እንዱከፍላቸዉ ዲኝነት በመጠየቅ ክስ የመሰረቱት በቀን 01/07/2012 ዓ/ም ነዉ። የይርጋ ጊዜዉ መቆጠር ያለበት ከቀን 08/04/2012 ዓ/ም (ቅሬታ ሰሚዉ አካል ዉሳኔ ከሰጠበት ቀን ቀጥል ካለዉ ቀን ጀምሮ - የአዋጁ አንቀጽ 164/1 ይመለከቷል) ጀምሮ በመሆኑ ከዚህ ቀን ጀምሮ ክሱ እስከ ቀረበበት ቀን 01/07/2012ዓ/ም ድረስ ያለዉ ጊዜ ሲቆጠር ገና ሦስት ወር አልሞላዉም።በመሆኑም በአዋጁ አንቀጽ 163/2 ስር የተደነገገዉ የ3 ወር የይርጋ ጊዜ ሳይደርስ የቀረበ ክስ በመሆኑ የአመልካች ክስ የማቅረብ መብት በይርጋ ቀሪ የሆነ አይደለም።እንዱሁም ተጠሪ ለክርክሩ መሰረት ያደረገዉ በሰ/መ/ ላይ የተሰጠዉ የሕግ ትርጉም በሰ/መ/ ላይ ሰባት ዳኞች በተሰየሙበት ችልት በተሰጠ ዉሳኔ የተለወጠ ከመሆኑም በተጨማሪ በእነኚህ መዛግብት ላይ የተሰጠዉ ትርጉም የይርጋ ጊዜ ማቋረጫ ምክንያት የሚመለከት ሲሆን የተያዘዉ ጉዲይ ደግሞ ከዚህ የተለየ በመሆኑ ለተያዘዉ ጉዲይ አግባብነት ያለዉ የሕግ ትርጉም ባለመሆኑ አልተቀበልንም። ስለሆነም የስር ፍርድ ቤት ጉዲዩን በኅብረት ስምምነት በተዘረጋዉ የቅሬታ አቀራረብ ሥርዓት መሰረት በመጀመሪያ መፍትሓ ለማግኘት ጥረት (exhausting internal remedy) ከማድረግ አኳያ ማየት ሲገባዉ ጉዲዩን ከይርጋ ማቋረጫ ምክንያት አንጻር በማየት የአመልካች ክስ የማቅረብ መብት በይርጋ ታግዶል ሲል የሰጠዉ ዉሳኔም ሆነ ይግባኝ ሰሚዉ ፍርድ ቤት የሥር ፍርድ ቤት የሰጠዉን ዉሳኔ በማጽናት የወሰነዉ መሰረታዊ የሆነ የክርክር አመራርና የሕግ አተገባበር ስህተት ያለበት በመሆኑ ተከታዩን ወስነናል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 06/05//2014ዓ/ም የሰጠዉ ዉሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ተሽረዋል።
የአመልካች ክስ የማቅረብ መብት በይርጋ አልታገደም ብለናል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መዝገቡን አንቀሳቅሶ በፍሬ ነገሩ ላይ ግራ ቀኙን በመስማት እንደነገሩ ሁኔታ ማስረጃዎቻቸዉን ሰምቶና መርምሮ ሕግን መሰረት ያደረገ ዉሳኔ እንዱሰጥ ጉዲዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 341/1 መሰረት መልሰንለታል።
ግራ ቀኝ በዚህ ችልት ያወጡትን ወጭ የየራሳቸዉን እንዱችለ ተወስኗል።
ት እ ዛ ዝ
የዉሳኔዉ ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤት ይተላለፍ። ግራ ቀኙ ሲጠይቁም ግልባጩ ይሰጣቸዉ።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.