በወንጀል ህግ አንቀጽ 670፣ 672ና 240፣ የተደነገጉት ውንብድና፣ ዘረፊ እና ሽፍታነት የሚለት ቃላት ቴክኒካዊ ልዩነት በመካከላቸው ያለና በተናጠል የወንጀል ኃላፉነትን የሚያስከትለ በመሆኑ የአንድ ተከሳሽ የወንጀል ድርጊት “ውንብድና ነው” ወይም “ዘረፊ ነው” ወይም “ሽፍታነት ነው” ለማለት ከመነሻው አጠቃላይ የተፈፀመው ድርጊት ዲኜ ደጀኔ እና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የሸካ ጥር 27/2014 ዓ.ም 445 የተከሳሹ ተሳትፍ በተገቢው መንገድ ተለይቶ ሉታወቅ እና ሉረጋገጥ፤ በእምነት ቃል መሰረት ውሳኔ ለመስጠትም የተሰጠው ቃል ተከሳሹ ከተከሰሰበት ወንጀል ዝርዝር ጋር አንድ ላሆን፤ ዝርዝር ቃለም ተከሳሹ ወንጀለን ለመፈፀሙ የማያጠራጥርና ሙለ እምነት ሉጣልበት የሚገባ ስለመሆኑ የኢ.ፋ.ዱ.ሪ. ህገ መንግስት አንቀፅ 20፣ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 134 (1) እና 141 ዞን ዐቃቤ ህግ 63. በወንጀል ህግ አንቀጽ 693(1) መሰረት የሚያዝበት በቂ ገንዘብ ሳይኖር ቼክ ማውጣት ወንጀል የተከሰሰ ቼክ አውጪ ቼኩን ለመመንዘር ሳይሆን በግለሰቦች መካከል በነበረው የንግድ ግንኙነት መነሻነት ለመተማመኛ የሰጠ በመሆኑ ከወንጀል ኃላፉነት ነፃ ሉወጣ የሚችለው ቼኩን ለዋስትና ወይም ለመያዥያነት የሰጠ ለመሆኑ እና የዋስትና ወይም የመያዥያ ውለም በንግድ ህግ እና በፍትሐ ብሕር ህግ በተመለከተው መመዘኛ መሰረት ስለመፈፀሙ በማስረዲት ከመሆኑ በቀር በሰው ምስክር የሚሰጥ ማረጋገጫ ተቀባይነት የላለው ስለመሆኑ የንግድ ህግ አንቀፅ 952 እና የፍ/ብ/ህ/ቁጥር 2864-2866 (በፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1234/2013 መሰረት በፋ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ቀደም ሲል በ #### የሰ/መ/ቁ የነበረው የህግ ትርጉም ተሻሽሎል)
No summary available.
ሐምል 29 ቀን 2013 ዓ.ም ዳኞች፡- መዓዛ አሸናፉ ሰለሞን አረዲ እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሳዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡- የፋዳራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ተጠሪ፡- የሺመቤት ጥላሁን **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የሚያዝበት በቂ ገንዘብ ሳይኖር ቼክ ማውጣት ወንጀልን የሚመለከት ነው። የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአሁን አመልካች የወንጀል ህጉ አንቀፅ 693(1) ተጠቅሶ በተጠሪ ላይ ባቀረበው ስድስት የወንጀል ክስ ላይ የግራ ቀኙ ክርክር እና ማስረጃ ከሰማ በኋላ በአራተኛ ክስ ውስጥ ከተጠቀሰው ቼክ ውጭ ላልቹ የተሰጡት በተጠሪ እና ተበዲይ ተብለው በተጠቀሱት ግለሰቦች መካከል በነበረው የንግድ ግንኙነት መነሻነት ለካፒታል መዋጮ መተማመኛነት እንጂ ለምንዛሪ አለመሆኑን አረጋግጫለሁ በማለት ክስ የቀረበበትን አንቀፅ ወደ አንቀፅ 693(2) በመቀየር የሰጠው ውሳኔ በይግባኝ ሰሚው የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ተቀባይነት ማግኘቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው በሚል ለማስለወጥ ነው።
የጉዲዩ አመጣጥ እንዱህ ነው። አመልካች በፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአሁን ተጠሪ ላይ የወንጀል ህጉን አንቀፅ 693(1) ድንጋጌን ጠቅሶ የሚያዙበት በቂ ገንዘብ ሳይኖራቸው ለተለያዩ አራት ሰዎች የተለያየ የገንዘብ መጠን የተፃፈባቸውን በጠቅላላው ስድስት ቼኮችን ሰጥተዋል በሚል ስድስት የወንጀል ክስ አቅርቧል።
በዚሁ ክስ ላይ መልስ እንዱሰጥ በታዘዘው መሰረት ተጠሪ ቀርበው ቼኮቹ ለተበዲዮች የተሰጡት ለሚያቋቁሙት የጠጠር ማምረቻ አክሲዮን ማህበር የአባላትን ድርሻ ለማረጋገጥ ለመተማመኛ እንዱሆን እንጂ ለመመንዘር እንዲልሆነ በመግለፃቸው ፍርድ ቤቱ የተከሳሽነት ቃለን በክህደት መዝግቦ የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ ሰምቷል። በመጨረሻም በአራተኛ ክስ ውስጥ ከተጠቀሰው ቼክ ውጭ ቀሪዎቹ ለካፒታል መዋጮ መተማመኛነት እንጂ ለምንዛሪ ያልተሰጡ መሆናቸውን በሰው እና በሰነድ ማስረጃ ማረጋገጡን ጠቅሶ ከአራተኛ ክስ ውጭ ያለትን አምስቱን ክሶች በተመለከተ ክስ የቀረበበት አንቀፅ በወንጀል ህግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 113(2) መሰረት ወደ አንቀፅ 693(2) በመለወጥ አራተኛ ክስን በተመለከለተ ደግሞ ክስ በቀረበበት አንቀፅ ስር ጥፊተኛ በማለት ለአራተኛ ክስ የእስራት ቅጣትን፤ ለተቀሩት ደግሞ የገንዘብ መቀጮ ቅጣትን መርጦ በጠቅላላው በ1(አንድ) ዓመት ከ8(ስምንት) ወር ፅኑ እስራት እና ብር 3,500(ሶስት ሺህ አምስት መቶ) እንዱቀጡ ከወሰነ በኋላ የእስራት ቅጣቱን አፈፃፀም በሁለት ዓመት የፈተና ጊዜ እንዱቆይ አዟል።
በዚሁ ውሳኔ ላይ በአሁን አመልካች አቤቱታ አቅራቢነት ጉዲዩ የቀረበለት የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በወ/ይ/መ/ቁ/156522 ላይ ሚያዝያ 29/2010 ዓ.ም በዋለው ችልት ተጠሪን መጥራት ሳያስፈልገው በወንጀል ህግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 195(1) መሰረት አቤቱታው በአብላጫ ድምፅ ሰርዟል።
የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔን በመቃወም ነው። አመልካች ሐምል 18/2010 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ በስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ላይ ተፈፅሟል ያለውን መሰረታዊ የህግ ስህተት ጠቅሶ በዚህ ችልት እንዱታረምለት ጠይቋል። ፍሬ ቃለም ክስ የቀረበበት የወንጀል ህጉ አንቀፅ መሰረታዊ ዓላማ ቼክ አውጪው ቼክ ከማውጣቱ በፉት በባንክ ሂሳቡ ውስጥ በቂ ገንዘብ መኖሩን እንዱያረጋግጥ በማድረግ ለገንዘብ እንቅስቃሴ ጥበቃ ማድረግ ሆኖ እያለ ከድንጋጌው ዓላማ ውጭ በዋስትና የተሰጠ ነው ተብል ድርጊቱ ወደ ቸልተኝነት መቀየሩ ከህግ አግባብ ውጭ ነው፤ የተወሰነው ቅጣትም ከተፈፀመው የወንጀል ድርጊት ጋር የማይመጣጠን ከመሆኑም በላይ ተጠሪ ከግል ተበዲዮች ጋር ታርቀው ገንዘቡንም ባልከፈለበት የእስራት ቅጣት ውሳኔውን አፈፃፀም መገደቡ አግባብ አይደለም የሚል ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ከተመረመረ በኋላ የግራ ቀኙ የንግድ ግንኙነት መሰረት ተደርጎ ክስ የቀረበበት አንቀፅ ወደ አንቀፅ 693(2) የተቀየረበት እና ቅጣቱም የተገደበበት የህግ አግባብ ለዚህ ችልት ቀርቦ እንዱመረመር በአጣሪ ችልት በመታዘዙ ተጠሪ የፅሁፍ መልስ እንዱሰጡበት ተደርጓል።
በዚሁ አግባብ ተጠሪ ጥር 03/2011 ዓ.ም በተፃፈ መልስ ክስ ከቀረበባቸው ስድስት ቼኮች ውስጥ በአራተኛ ክስ ውስጥ ከተጠቀሰው ቼክ ውጭ ቀሪዎቹ የተሰጡት ከተበዲዮች ጋር በጋራ ላቋቋምነው ኩባንያ በተበዲዮቹ በኩል ለተደረገው የካፒታል መዋጮ ማረጋገጫነት እንጂ ለምንዛሪ አይደለም፤
ቼክን ጨምሮ የገንዘብ መጠየቂያ ሰነድች በዋስትና ሉሰጡ የሚችለ ስለመሆናቸው የፍ/ብ/ህ/ቁጥር 2863 የሚደነግግ በመሆኑ ድርጊቱ ወንጀል አይደለም፤ ለንግድ ድርጅት ማቋቋሚያ ተብል የሚዋጣው መዋጮ የውል ግዳታን ከማቋቋም አልፍ የወንጀልም ሆነ ከውል ውጭ ኃላፉነትን የማያስከትል ስለመሆኑ በፍ/ብ/ህ/ቁጥር 2037 ላይ ተመልክቷል፤ የስር ፍርድ ቤትም ቼኮቹ በንግድ ግንኙነት ውስጥ ለካፒታል መዋጮ እንጂ ለምንዛሪ አለመሰጠታቸውን አረጋግጦ የወሰነ በመሆኑ በውሳኔው ላይ የተፈፀመ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም፤ ቅጣቱም ቢሆን የወንጀል ህጉን እና የቅጣት መሰረታዊ ዓላማን ያገናዘበ ነው ከሚባል በቀር የሚነቀፍ ባለመሆኑ የአመልካች የሰበር አቤቱታ ውድቅ ላደረግ ይገባል የሚል ነው። አመልካችም የሰበር ቅሬታውን የሚያጠናክር የመልስ መልስ በማቅረብ ሞግቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ችልቱም የግራ ቀኙን ክርክር ጉዲዩ ለዚህ ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ነጥብ አኳያ አግባብነት ካለው ህግ ጋር በማገናዘብ መርምሯል።
እንግዱህ ከክርክሩ ይዘት መረዲት እንደሚቻለው የግራ ቀኙ ክርክር የሚያጠነጥነው ቼክ በዋስትና ላሰጥ የሚችል መሆን አለመሆኑ እና ከወንጀል አኳያ በሚኖረው ውጤት ላይ ነው። ይህንን ነጥብ አስመልክቶ ይኸው ችልት ቀደም ሲል በሰ/መ/ቁ/67947 ላይ ሰኔ 15/2003 ዓ.ም በዋለው ችልት “የሚያዝበት ገንዘብ ሳይኖር ቼክ ማውጣት በሚል በወንጀል ህጉ አንቀፅ 693(1) ውስጥ የተመለከተውን የወንጀል ድርጊት ለማቋቋም ቼኩ ለክፍያ ባንክ በቀረበበት ጊዜ በቂ ስንቅ የላለው መሆኑን/ያለመኖሩን/ ማረጋገጥ ብቻ በቂ ነው” የሚል የህግ ትርጉም ሰጥቷል። እናም ከወንጀል ተጠያቂነት አኳያ ቼክን ለዋስትና አልያም ከምንዛሪ ውጭ ለሆነ ላላ ዓላማ ሰጥቻለሁ የሚለው የወንጀል ክስ መከላከያ ላሆን አይችልም ማለት ነው።
ሆኖም ይኸው ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ቁ/166392 ላይ ሚያዝያ 26/2012 ዓ.ም በዋለው ችልት ቼክ እንደማንኛውም ሉተላለፍ እንደሚችል የንግድ ሰነድ በመያዥያነት ወይም በዋስትና ላሰጥ የሚችል መሆኑን፤ ይህ ሲሆንም በንግድ ህጉ አንቀፅ 952 እና በፍ/ብ/ህ/ቁጥር 2864-2866 ላይ በተመለከቱት ጥብቅ መመዘኛዎች አግባብ መመራት እንዲለበት አስገዲጅ የህግ ትርጉም ሰጥቷል።
በእርግጥ ይህ የህግ ትርጉም የተሰጠው በፍትሓ ብሕር ጉዲይ ላይ ነው። ቢሆንም ከዚህ ሰበር ሰሚ ችልት የሚሰጠው የህግ ትርጉም በማናቸውም ደረጃ ላይ በሚገኙ ፍርድ ቤቶች ላይ የአስገዲጅነት ባህሪ ያለው በመሆኑ በወንጀልም ሆነ በፍትሓ ብሄር ጉዲይ ላይ የሚሰጠው የህግ ትርጉም አንደ ላላውን እንዲያፊልስ እና ውጤትም እንዲያሳጣ ወጥነት ሉኖረው ይገባል። ከዚህ አንፃር ቀደም ሲል በሰ/መ/ቁ/67947 ላይ የተሰጠው የህግ ትርጉም ባለበት በኋላ ላይ የተሰጠው ትርጉም በወንጀል ጉዲይ ተፈፃሚ ላሆን አይችልም። በውጤት ደረጃም ሲታይ አንድ ቼክ አውጪ በፍትሓ ብሕር ክስ ቼኩን ለዋስትና አልያም ለመያዥያነት የሰጠ ስለመሆኑ አረጋግጦ ከክሱ ነፃ ቢባል እንኳን በወንጀል ጉዲይ በቼክ ማጭበርበር ወንጀል ጥፊተኛ ተብል ይቀጣል ማለት ነው። ይህ ደግሞ ከወንጀል እና ፍትሐ ብሕር ጉዲዮች ተፈጥሮዓዊ ባህሪ እና ከሚያስከትለት ውጤት አኳያ ተቀባይነት ያለው አይደለም።
እናም ቀደም ሲል የወንጀል ህጉ አንቀፅ 693(1) አተረጓጎምን አስመልክቶ በሰ/መ/ ላይ ተሰጥቶ የነበረው የህግ ትርጉም ትርጉሙ የተሰጠበትን ድንጋጌ መሰረት አድርገው የሚቀርቡትን የወንጀል ክሶችን ተግባራዊ አፈፃፀም መሰረት በማድረግ የድንጋጌው አተረጓጎም እና አተገባበር አጠቃላይ ከወንጀል ህግ መሰረተ ሀሳብ እንዱሁም በዚሁ ችልት በሰ/መ/ቁ/166392 ላይ ከተሰጠው ትርጉም አኳያ ማስተካከያ ላደረግበት የሚገባው ሆኖ ተገኝቷል። በዚሁ አግባብ ቀድሞ የተሰጠው የህግ ትርጉም “በወንጀል የተከሰሰ ቼክ አውጪ ቼኩን ለዋስትና ወይም ለመያዥያነት የሰጠ ለመሆኑ እና የዋስትና ወይም የመያዥያ ውለም በንግድ ህግ ቁጥር 952 እና በፍ/ብ/ህግ ቁጥር 2864-2866 በተመለከተው አግባብ የተፈፀመ ስለመሆኑ ማስረዲት ከቻለ በወንጀል ጥፊተኛ ሆኖ ሉቀጣ አይገባም” በሚል በተሻሻለ ትርጉም ተተክቷል።
በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበው ጉዲይም ከዚሁ ከተሻሻለው የህግ ትርጉም አንፃር ተቃኝቷል። ተጠሪ አጥብቀው የሚከራከሩት ክስ ከቀረበባቸው ስድስት ቼኮች ውስጥ አምስቱ ለምንዛሪ ሳይሆን ለካፒታል መዋጮ የተሰጡ በመሆኑ በወንጀል ልጠየቅ አይገባም በሚል ነው። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ክስ የቀረበበትን አንቀፅ ወደ ቸልተኝነት አንቀፅ የለወጠው አምስቱ ቼኮች በተጠሪ እና የግል ተበዲዮች መካከል በነበረ የንግድ ግንኙነት ለካፒታል መዋጮ የተሰጡ ስለመሆናቸው አረጋግጫለሁ በሚል ምክንያት ነው። በእርግጥ ፍርድ ቤቱ በዚህ መልኩ ሲወስን ከላይ የተመለከተው የህግ ትርጉም ያልተሰጠ በመሆኑ ተፈፃሚነት ያለው በሰ/መ/ቁ/67947 ላይ ተሰጥቶ የነበረው ነው። በዚህ ትርጓሜ መሰረት ደግሞ ቼክን ለዋስትናም ሆነ ለላላ ከምንዛሪ ውጭ ለሆነ ዓላማ ሰጥቻለሁ የሚለው ጉዲይ ለወንጀል ክስ መከላከያነት ሉውል የሚችል አይደለም። እናም የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይህንን ምክንያት ጠቅሶ ድርጊቱን ወደ ቸልተኝነት አንቀፅ መቀሩ ከድንጋጌው አፈፃፀም እና አተረጓጎም አኳያ የተሰጠውን አስገዲጅ የህግ ትርጉም የተላለፈ ነው። ከፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የተሰጠን አስገዲጅ የህግ ትርጉም የተላለፈ ውሳኔ ደግሞ መሰረታዊ የህግ ስህተት ስለመሆኑ የፋዳራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀፅ 2(4(ሸ)) የሚደነግግ በመሆኑ ውሳኔው በእርግጥም ሉነቀፍ የሚገባው ነው።
ሆኖም ጉዲዩ በክርክር ላይ እያለ ቀድሞ ከተሰጠው የህግ ትርጉም የተለየ ትርጉም የተሰጠ በመሆኑ የተጠሪ መከራከሪያ ተሻሽል ከተሰጠው የህግ ትርጉም አኳያ ስለሚኖረው ውጤት ማየቱ ተገቢ ይሆናል። እንግዱህ ተሻሽል በተሰጠው የህግ ትርጉም መሰረት በቂ ስንቅ የላለው ቼክ ሰጥቷል ተብል በወንጀል የተከሰሰ ሰው ከወንጀል ኃላፉነት ነፃ ሉወጣ የሚችለው ቼኩ የተሰጠው በዋስትና ወይም በመያዥያነት መሆኑን እና የዋስትናው አልያም የመያዥያ ውለም በተቀመጠው መመዘኛ መሰረት የተፈፀመ ስለመሆኑ ማስረዲት ከቻለ ነው። አሁን በቀረበው ጉዲይ ተጠሪ ቼኩን ለካፒታል መዋጮ ማረጋገጫነት ስለመስጠታቸው ያረጋገጡት በሰው ምስክር ነው። ከዚህ ውጭ በተሰጠው የህግ ትርጉም መሰረት ቼኮቹ ስለመሰጠታቸው የተረጋገጠ ነገር ባለመኖሩ የተሻሻለው ትርጉም በተጠሪ የወንጀል ኃላፉነት ላይ የሚያመጣው ለውጥ የለም።
በመሆኑም የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ቁ/187459 ላይ ጥር 22/2010 ዓ.ም የሰጠው የጥፊተኝነት ፍርድ እና ይህንኑ ፍርድ በማፅናት የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ቁ/156522 ላይ ሚያዝያ 29/2010 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በወንጀል ህግ ቁጥር 195(2(ለ(2))) መሰረት ተሻሽል ተጠሪ በ1ኛ፣ 2ኛ፣ 3ኛ፣ 5ኛ እና 6ኛ ክሶች በወንጀል ህግ አንቀፅ 693(1) ስር ጥፊተኛ ናቸው ተብሎል።
ቅጣትን በተመለከተ የጥፊተኝነት ፍርድ ለተሰጠበት የወንጀል ህጉ ድንጋጌ በቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 ደረጃ እና እርከን የወጣለት ነው። ተጠሪ በአምስቱ ክሶች ውስጥ በቂ ስንቅ ሳይኖራቸው ሰጥተዋል በተባለት ቼኮች ላይ ያለው የገንዘብ መጠን እንደ ቅደም ተከተላቸው ብር 5,000,000(አምስት ሚሉዮን ብር)፣ ብር 1,000,000(አንድ ሚሉዮን ብር)፣ ብር 240,000(ሁለት መቶ አርባ ሺህ ብር)፣ 100,000 ዩሮ(አንድ መቶ ሺህ ዩሮ) ወይም ብር 2,205,000(ሁለት ሚሉዮን ሁለት መቶ አምስት ሺህ ብር) እና ብር 500,000(አምስት መቶ ሺህ ብር) ነው። በዚሁ አግባብ በቅጣት አወሳሰን መመሪያው መሰረት 1ኛ ክስ ደረጃ 10፣ የእስራት ቅጣት እርከን 23 እና መቀጮ እርከን 6፤ 2ኛ ክሰ ደረጃ 8 የእስራት ቅጣት እርከን 19 እና መቀጮ እርከን 6፤ 3ኛ ክስ ደረጃ 6 የእስራት ቅጣት እርከን 15 እና መቀጮ እርከን 4፤ 5ኛ ክስ ደረጃ 10 የእስራት ቅጣት እርከን 23 እና መቀጮ እርከን 6፤ 6ኛ ክስ ደረጃ 7 የእስራት ቅጣት እርከን 17 እና መቀጮ እርከን 5 ይሆናል።
የእስራት ቅጣትን በተመለከተ በቅጣት እርከኖች ስር በተቀመጠው ፍቅደ ስልጣን ውስጥ መነሻ ቅጣታቸው ብቻ ተወስድ ሲደመሩ 22 ዓመት ፅኑ እስራት ይሆናል። የገንዘበ ቅጣትን በተመለከተ እርከን 4 እስከ ብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር)፤ እርከን 5 እስከ ብር 7,000 (ሰባት ሺህ ብር) እና እርከን 6 እስከ ብር 10,000(አስር ሺህ ብር) የሚደርስ ነው። በእነዚህ እርከኖች ስር አማካይ ቅጣት ተወስድ ሁለም ሲደመሩ በጠቅላላው እስከ ብር 35,500(ሰላሳ አምስት ሺህ አምስት መቶ ብር) የሚደርስ የገንዘብ ቅጣት ይሆናል። የእስራት እና የገንዘብ አማካይ ቅጣቱ ተጠሪ በ4ኛ ክስ ስር ጥፊተኛ ከተባለበት ጋር ሲደመር የእስራት ቅጣቱ 24 ዓመት ከ9 ወር ፅኑ እስራት እና እስከ ብር 39,500(ሰላሳ ዘጠኝ ሺህ አምስት መቶ ብር) የገንዘብ ቅጣት ይሆናል። ይህም በቅጣት አወሳሰን መመሪያው አባሪ አንድ በእስራት እርከን 37 እና መቀጮ እርከን 9 ስር የሚገኝ ነው።
በልላ በኩል በስር ፍርድ ቤት ተቀባይነት ያገኘ አንድ የቅጣት ማክበጃ ምክንያት እና አምስት የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች መኖራቸውን ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ይዘት ለመገንዘብ የተቻለ በመሆኑ እና በእነዚህ የቅጣት አስተያየቶች ላይ የቀረበ መከራከሪያ ባለመኖሩ ምክንያቶቹ በዚህ ችልትም ተወስደዋል። በዚሁ አግባብ በሚደረግ ስላት መጨረሻ ቅጣቱ የሚሰላው በእስራት እርከን 34 እና መቀጮ እርከን 6 ስር ይሆናል ማለት ነው። ለዚህ እርከን የተቀመጠው ቅጣት ደግሞ ከ15(አስራ አምስት) ዓመት እስከ 18 (አስራ ስምንት) ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እና እስከ ብር 10,000(አስር ሺህ ብር) የሚደርስ መቀጮ ነው። እናም በቅጣት አወሳሰን መመሪያ መሰረት በሚደረስ ስላት ተጠሪ በትንሹ 15 ዓመት ፅኑ እስራት ይቀጣለ ማለት ነው።
ይሁንና ከተፈፀመው የወንጀል ድርጊት እንዱሁም ከድርጊቱ አፈፃፀም ሁኔታ አኳያ የዚህ ቅጣት ተመጣጣኝነት እና አስተማሪነቱም መፈተሽ ያለበት ጉዲይ ሆኖ ተገኝቷል። እንግዱህ የወንጀል ቅጣት ቀዲሚ ዓላማው ወንጀል ፈፃሚዎችን በማረም በቀሪ ህይወታቸው ከመሰል ድርጊት ታቅበው መልካም ዜጋ እንዱሆኑ ማድረግ ነው። የቅጣት ውሳኔ የወንጀል አጥፉዎችን ለማረም ደግሞ አጥፉው ከፈፀመው የወንጀል ድርጊት ጋር ተመጣጣኝ ላሆን ይገባል። በልላ አገላለፅ የተፈፀመው የወንጀል ድርጊት ቀላል ወይም የአጥፉውን አደገኛነት የማያሳይ ሆኖ እያለ የተጋነነ ቅጣት የሚወሰንበት ከሆነ ወይም ድርጊቱ ከባድ ሆኖ አነስተኛ ቅጣት የሚወሰን ከሆነ አጥፉውንም ሆነ ላላውን ማህበረሰብ የማያስተምር በመሆኑ የወንጀል ቅጣት ውሳኔ መሰረታዊ ዓላማን የማያሳካ ነው ማለት ነው። ሥራ ላይ ያለው የቅጣት አወሳሰን መመሪያም በመርህ ደረጃ የትኛውም የወንጀል ቅጣት ውሳኔ በመመሪያው መሰረት እንዱወሰን ካዘዘ በኋላ ከመመሪያው ውጭ ቅጣት ሉወሰን የሚችልበትን ሁኔታ በአንቀፅ 27 ስር ያሰፈረውም በዚሁ መነሻነት እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል።
አሁን በቀረበው ጉዲይ ተጠሪ የተከሰሱትም ሆነ በወንጀል ጥፊተኛ የተባለት ስድስት የተለያየ የገንዘብ መጠን የተፃፈባቸውን ቼኮች ለአራት ግለሰቦች ሰጥተዋል በሚል ነው። በ4ኛ ክስ ውስጥ ከተጠቀሰው ቼክ ውጭ ቀሪዎቹ የተሰጡበት ሁኔታ የተጠሪን የወንጀል ኃላፉነት የሚያስቀር ባይሆንም በተጠሪ እና በቼክ ተቀባዮቹ መካከል በነበረው የጋራ የንግድ ስራ ውስጥ የተሰጡ ለመሆናቸው በፍሬ ነገር ደረጃ ተረጋግጧል። የዚህ ድርጊት አፈፃፀም ሁኔታ ሲታይ የተጠሪን ወንጀል የመፈፀም አደገኛነት የሚያሳይ አይደለም። ይህ ከሆነ ደግሞ በንግድ ግንኙነት ውስጥ በተሰጠ ቼክ መነሻነት ተጠሪ በቅጣት አወሳሰን መመሪያው በተለየው የእስራት ቅጣት እንዱቀጡ መወሰኑ ከተፈፀመው ድርጊት ጋር የማይጣጣም በመሆኑ ቅጣቱ የወንጀል ህጉን አላማና ግብ የማያሳካ ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም ቅጣቱ ከመመሪያው በመውጣት በወንጀል ህግ አንቀፅ 88(2) እና 179 መሰረት መወሰን እንደሚገባው ታምኗል።
በዚሁ አግባብ ተጠሪ ጥፊተኛ የተባለበት የወንጀል ድርጊት የተፈፀመበት ከባቢያዊ ሁኔታ እና የተጠሪን አደገኛነት መጠን ከግንዛቤ በማስገባት ለሁለም የወንጀል ድርጊቶች ተጠሪ ከዚህ በፉት በዚሁ ጉዲይ የታሰሩት ካለ ታስቦበት በ5(አምስት) ዓመት ፅኑ እስራት እና በብር 10,000(አስር ሺህ ብር) መቀጮ እንዱቀጡ ተወስኗል። በልላ በኩል በወንጀል ጥፊተኛ የተባለን ሰው ለማስተማር ሁላም ወደ ማረሚያ ቤት መላክ አስፈላጊ ላይሆን ይችላል። ይልቁንም ለጥፊተኛው አንድ የፈተና ጊዜ ከፅኑ ማስጠንቂያ ጋር ሰጥቶ አመለ ቢፈተሸ መልካም ይሆናል ተብል ሲታመን የእስራት ቅጣቱን አፈፃፀም ለጊዜው አግድ ማቆየት እንደሚቻል ከወንጀል ህጉ አንቀፅ 192 እና ተከታዮቹ መገንዘብ ይቻላል። የወንጀል ቅጣት ውሳኔ ሉገደብ የማይቻልባቸው ልዩ ሁኔታዎች ደግሞ በወንጀል ህጉ አንቀፅ 194 ስር በዝርዝር ተቀምጠዋል። በእነዚህ መመዘኛዎች መሰረት የአሁን ተጠሪ ላይ በዚህ ችልት የተላለፈው የእስራት ቅጣት ውሳኔ እንዲይገደብ የተቀመጠ ክልከላ ባለመኖሩ የቅጣቱ አፈፃፀም በፈተና ጊዜ እንዱቆይ ማድረጉ ተገቢ ሆኖ ተገኝቷል። ሲጠቃለል ይህንን ጉዲይ በተመለከተ ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
ከወንጀል ህግ አንቀፅ 693(1) አተረጓጎም ጋር ተያይዞ ቀደም ሲል በዚሁ ችልት በሰ/መ/ቁር67947 ላይ ተሰጥቶ የነበረው የህግ ትርጉም በፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀፅ 26 መሰረት ተሻሽሎል። በዚሁ አግባብ “በወንጀል የተከሰሰ ቼክ አውጪ ቼኩን ለዋስትና ወይም ለመያዥያነት የሰጠ ለመሆኑ እና የዋስትና ወይም የመያዥያ ውለም በንግድ ህጉ እና በፍትሐ ብሕር ህጉ በተመለከተው መመዘኛ መሰረት የተፈፀመ ስለመሆኑ ማስረዲት ከቻለ በወንጀል ጥፊተኛ ሆኖ ሉቀጣ አይገባም” ተብሎል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ቁ/187459 ላይ ጥር 22/2010 ዓ.ም የሰጠው የጥፊተኝነት ፍርድ እና ይህንኑ ፍርድ በማፅናት የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ቁ/156522 ላይ ሚያዝያ 29/2010 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በወንጀል ህግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 195(2(ለ(2)) መሰረት ተሻሽል ተጠሪ በ1ኛ፣ 2ኛ፣ 3ኛ፣ 5ኛ እና 6ኛ ክሶች በወንጀል ህግ አንቀፅ 693(1) ስር ጥፊተኛ ናቸው ተብሎል።
በውሳኔ ተራ ቁጥር 2 ስር በተገለፀው አግባብ ተጠሪ ጥፊተኛ በተባለበት ስድስቱም ክሶች በጠቅላለው በአምስት ዓመት ፅኑ እስራት እና በብር 10,000(አስር ሺህ ብር) የመቀጮ እንዱቀጡ ተወስኖ የእስራት ቅጣት ውሳኔው አፈፃፀም በ4(አራት) ዓመት የፈተና ጊዜ እንዱቆይ ተወስኗል።
ተጠሪ በወንጀል ሕጉ አንቀፅ 197(2) መሰረት ለመልካም ፀባይ አመራር ዋስትና ይሆን ዘንድ ብር 5,000(አምስት ሺህ) የአራት ዓመት ጊዜው እስኪጠናቀቅ ድረስ በዋስትና ያስይዙ።
የቅጣት ውሳኔው ከቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 ውጭ የተወሰነ መሆኑን እንዱያውቅ የዚህ ውሰኔ ግልባጭ ለፍርድ ቤቱ ለሚመለከተው የስራ ክፍል እንዱተላለፍ በመመሪያ አንቀፅ 27(3) መሰረት ታዟል።
መዝገቡ ተዘግቷል። ይመለስ።
No topics extracted.