በቸልተኝነት የሚፈፀሙ ድርጊቶች እንደ ሙከራ ሉቆጠሩ ይችላለ የሚል አስተያየት ቢኖርም አንድን የወንጀል ድርጊት ሙከራ ነው ለማለት ድርጊቱ በእውቀትና በፍላጎት የተፈፀመ መሆኑን ማረጋገጥ መሰረታዊ መስፈርት ስለሆነ በቸልተኝነት የሚፈፀሙ ድርጊቶችን እንደ ሙከራ መቁጠር በአሁኑ ጊዜ ብዙም ተቀባይነት የላለው ስለመሆኑ የወንጀል ህግ አንቀፅ 27(1)፣ 23(2) እና 58(1) (ለ)
No summary available.
ጥር 27/2014 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሳዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡- ዲኜ ደጀኔ ተጠሪ፡- በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የሸካ ዞን ዐቃቤ ህግ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበው ጉዲይ የወንጀል ክርክርን የሚመለከት ሲሆን የተጀመረውም የአሁን ተጠሪ የኢ.ፋ.ዳ.ሪ. የወንጀል ህግ አንቀፅ 671(2) ድንጋጌን ጠቅሶ በአሁን አመልካች ላይ በቀድሞ የደቡብ ብሕሮች ብሕረሰቦች እና ህዝቦች ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ሸካ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባቀረበው የወንጀል ክስ ነው። የክሱም ይዘት አመልካች የተጠቀሰውን የወንጀል ህጉን ድንጋጌ በመተላለፍ በሸካ ዞን በየኪ ወረዲና ቴፒ ከተማ ውስጥ ከነሓሴ ወር 2010 ዓ.ም ጀምሮ በቡድን በመደራጀትና ህገ ወጥ የጦር መሣሪያ በመያዝ በጫካ ውስጥ በመደበቅ በሰው ግድያ፣ በዘረፊና ጥይት በመተኮስ የዜጎችን ሰላም በማወክ ላይ ከተሰማሩት 1ኛ/አይሳነው ሲሳይ፣ 2ኛ/ ኡመር ሰይድ፣ 3ኛ/ አላዱ ኤሉያስ፣ 4ኛ/ ጮቤ/ሙክታር ከድር/፣ 5ኛ/ አቢቲ/ዲግም ታደሰ/ ከሚባለት የወንበዳ ቡድኖች ጋር በመሆን በክሱ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት ሲፈፅም ከቆየ በኋላ ታህሳስ 21/2013 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 9፡00 ሰዓት በሚሆንበት ጊዜ የመንግስት የፀጥታ ኃይል በሰላም በር ቀበላ ልዩ ስፍራው ታችኛው አዋሽ ተብል በሚጠራው ስፍራ የአሰሳ ሥራ እያደረጉ ባለበት የአሁን አመልካች እና ለጊዜው ያልተያዙት ከላይ በስም የተዘረዘሩት ሽፍቶች ተሰባስበው ጫት እየቃሙ ባለበት የፀጥታ ኃይልች በስፍራው ሲደርሱ በፀጥታ ኃይልቹ ላይ ጥይት በመተኮስ ሁለት የፀጥታ ኃይልች ላይ ጉዲት ካደረሱ በኋላ ሁለት ሞባይልችን ጥለው ወደተለያየ አቅጣጫዎች ሩጠው ያመለጡ ሲሆን የአሁን አመልካች በዚያው አካባቢ በሚገኝ የግለሰብ ቤት ተደብቆ በነጋታው በፀጥታ ኃይልች በአካባቢው ላይ በተደረገ ፍተሻ የተያዘ በመሆኑ በፈፀመው የውንብድና ወንጀል ተከሷል የሚል ነው።
አመልካች ክሱን ሳይቃወም ወንጀለን ፈፅምያለሁ፤ ጥፊተኛም ነኝ ብሎል። ዝርዝር ቃለን ሲያስመዘግብም ከጥር ወር 2012 ዓ.ም ጀምሮ ስማቸው በክሱ ዝርዝር ውስጥ “የወንበዳ ቡድን” ተብል ከተጠቀሱት ግለሰቦች ጋር የቡድኑ አባል ሆኖ አብሮ መኖር የጀመረ መሆኑን፤ ግለሰቦቹ እሱን ወደ ከተማ የማያስወጡት መሆኑን፤ በራሳቸው ግን ተቦዲድነው ማታ ማታ ወደ ቴፒ ከተማ በመሄድ ጥይት ተኩሰው የሚመለሱ መሆኑን፤ በተጨማሪም ከሃብታሞች ገንዘብ በመጠየቅ የሚቀበለ መሆኑን፤ መኪናም እያስቆሙ ከአንድ ኤፍ ኤስ አር ላይ ብር 1000፤ አይሱዙ ከሆነ ደግሞ ብር 500 ተመን አውጥተው የሚቀበለ መሆኑን፤ ከዚያን በፉት ጮላ/ሙክታር አባድር/ የተባለው የሚቀበለውን ገንዘብ በጋራ ሲጠቀም የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ እየተጠቀመ እንዲልሆነ፤
ታህሳስ 21/2013 ዓ.ም ከእነዚሁ ግሰለቦች ጋር ሆነው በክሱ ዝርዝር በተጠቀሰው ቦታ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት አካባቢ ቡና ዛፍ ስር ተቀምጠው ጫት በመቃም ላይ እንዲለ የፀጥታ ኃይልች ሲመጡባቸው ኡመር ሰይድ እና አይሳነው ሲሳይ የተባለት በፀጥታ ኃይልቹ ላይ ተኩስ ከፍተዉባቸው ከእነክላሺንኮቭ መሳሪያቸው ሲያመልጡ እርሱም ሮጦ አምልጦ በነጋታው የተያዘ መሆኑን፤
የግለሰቦቹ ስራ ህገ ወጥ መሆኑን እያወቀ የሽፍታ አባል በመሆን ከእነርሱ ጋር ማበሩ ጥፊት መሆኑን መናገሩን ያሳያል።
ክሱ የቀረበለት ፍርድ ቤትም አመልካች ድርጊቱን እና ጥፊተኝነቱን ሙለ በሙለ አምኗል በሚል በወንጀል ህግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 134 መሰረት ክስ በቀረበበት አንቀጽ ስር ጥፊተኛ በማለት በ21 ዓመት ፅኑ እስራት እንዱቀጣ ወስኗል። ይኸው ውሳኔ እስከ ክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ድረስ ፀንቷል።
የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ነው። አመልካች ግንቦት 16/2013 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ በስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ ተፈፅሟል ያለውን መሰረታዊ የህግ ስህተት ጠቅሶ በዚህ ችልት እንዱታረምለት ጠይቋል። ፍሬ ቃለም አመልካች በዝርዝር የእምነት ክህደት ቃለ በክሱ የተገለፀውን ወንጀል ስለመፈፀሙ ሳይሆን ያልተያዙ ላልች ግለሰቦችን በመላላክና በመርዲት መሳተፈን እንጂ በውንብድና ወንጀል ስለመሳተፈ ቃለን ያልሰጠ በመሆኑ ቃለ በክህደት መመዝገብ ሲገባው ክሱን ሙለ በሙለ አምኗል በማለት የዐቃቤ ህግ ምስክሮች ሳይሰሙ ጥፊተኛ መባለ አግባብ አለመሆኑን፤ በድርጊቱም ተበዲይ ነኝ የሚል አካል ቀርቦ ባልተሰማበት ጥፊተኛ ተብል መቀጣቱ አግባብ አለመሆኑን ጠቅሶ ውሳኔው እንዱሻር የሚጠይቅ ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ አመልካች የውንብድና ወንጀል መፈፀሙን አምኗል በሚል የግራ ቀኝ ማስረጃ ሳይሰማ በወንጀል ህግ አንቀፅ 671(2) ስር ጥፊተኛ ተብል በ21 ዓመት ጽኑ እስራት እንዱቀጣ የተወሰነበት አግባብ ከወንጀል ህግ አንቀፅ 24 እና ከመሰረታዊ የክርክር አመራርና ማስረጃ ምዘና መርሆዎች አንጻር በዚህ ችልት እንዱጣራ በመታዘዙ ግራ ቀኙ በፅሁፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት በአጭሩ ይህንን ሲመስል ችልቱም የግራ ቀኙን ክርክር ጉዲዩ ለዚህ ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ማስቀረቢያ ነጥብ አኳያ አግባብነት ካለው ህግ ጋር በማገናዘብ መርምሯል።
ከክርክሩ አመጣጥ በግልፅ መገንዘብ እንደሚቻለው የስር ፍርድ ቤት የጥፊተኝነት ውሳኔ የሰጠው የአሁን አመልካችን የእምነት ቃል መሰረት አድርጎ ነው። በእርግጥ በወንጀል የተከሰሰ ሰው በክሱ ማመልከቻው ላይ የተዘረዘረውን ወንጀል ለመስራቱ በሙለ ያመነ እንደሆነ ይኸው በመዝገብ ላይ ከተፃፈ በኋላ በተከሳሹ ላይ የጥፊተኝነት ውሳኔ ላሰጥ የሚችል ስለመሆኑ የወንጀል ህግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 134(1) ይደነግጋል። በዚህ መልኩ ውሳኔ ለመስጠት በቅድሚያ ተከሳሹ ቃለን በዝርዝር ላሰጥ የሚገባ መሆኑን፤ በዝርዝር የተሰጠው ቃል ተከሳሹ ከተከሰሰበት ወንጀል ዝርዝር ጋር አንድ ላሆን እንደሚገባ እና ዝርዝር ቃለ ተከሳሹ ወንጀለን ለመፈፀሙ የማያጠራጥር እና ቃለም ሙለ እምነት የሚጣልበት ላሆን እንደሚገባው ከድንጋጌው ይዘት መገንዘብ ይቻላል።
በተከሳሽ ቃል መሰረት የጥፊተኝነት ውሳኔ ለመስጠት እንዱህ አይነት ጥብቅ መመዘኛ ያስፈለገበት መሰረታው ዓላማ ማንኛውም ተከሳሽ በራሱ ላይ ማስረጃ ያለመሆን ህገ መንግስታዊ መብት ያለው በመሆኑና በወንጀል የተከሰሰን ሰው አጥፉነት በተገቢው የማስረዲት ደረጃ የማስረዲት ግዳታ የዐቃቤ ህግ በመሆኑ እንደሆነ በኢ.ፋ.ዳ.ሪ. ህገ መንግስት አንቀፅ 20 ስር በወንጀል ለተከሰሱ ሰዎች ከተደረገው ጥበቃ፣ ከወንጀል ህግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 134 እና 141 ድንጋጌዎች አጠቃላይ ይዘት እና መንፈስ መረዲት ይቻላል። ለዚህም አንደ ማሳያ ላሆን የሚችለው ተከሳሹ የቀረበበትን የወንጀል ክስ በዝርዝር ያመነ ቢሆንም እንኳን ፍርድ ቤቱ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ዐቃቤ ህግ ለክሱ የሚደግፈውን ማስረጃ እንዱያቀርብ እና እንደ ነገሩ ሁኔታ ተከሳሹም የመከላከያ ማስረጃ እንዱያቀርብ ሉታዘዝ የሚችል ስለመሆኑ በወንጀል ህግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 134(2) ስር መደንገጉ ነው።
አሁን በቀረበው ጉዲይ አመልካች የተከሰሰው ከላልች የጦር መሳሪያ ይዘው ጫካ በመግባት በሰው ግድያ፣ ዘረፊ እና ጥይት በመተኮስ የህብረተሰቡን ሰላምና ፀጥታ በማወክ ላይ የተሰማሩት የሽፍታ ቡድን አባል በመሆን ከባድ የወንብድና ወንጀል ፈፅሟል በሚል ነው። አመልካች በሰጠው ዝርዝር የተከሳሽነት ቃል ሽፍታ ተብለው ከተጠቀሱት ግለሰቦች ጋር አባል መሆኑን ከመግለፁ ውጭ በክሱ ዝርዝር ውስጥ በተገለፀው አግባብ በሰው ግድያ፤ ዘረፊ እና ጥይት በመተኮስ በህብረተሰቡ ሰላም እና ፀጥታ ስለማደፍረሱ በግልፅ የሰጠው ቃል የለም። እንዱያውም ላልች የአመልካች አባልች ናቸው የተባለት ማታ ማታ ወደከተማ እየወጡ ተሽከርካሪዎችን በማስቆም አስገድደው ገንዘብ ሲቀበለ እና ላልች ድርጊቶችን ሲፈፅሙ ለእርሱ ግን ወደከተማ መውጣት የተከለከለ መሆኑን ገልፅጿል።
እንግዱህ ውንብድና፣ ዘረፊ እና ሽፍታነት የሚለት ቃላት በተለምድ በህብረተሰቡ ዘንድ አንደ ላላውን ለመግለፅ ተፈራርቆ አግልግልት ላይ የሚውል ቢሆንም ቴክኒካዊ ልዩነት በመካከላቸው ያለ ስለመሆኑ መገንዘብ ያስፈልጋል። ውንብድና እና ዘረፊ በወንጀል ህጉም ቢሆን ከሞላ ጎደል ትርጉም የተሰጣቸው እና በራሳቸው በተናጠል የወንጀል ኃላፉነትን የሚያስከትለ ስለመሆኑ ከወንጀል ህጉ አንቀፅ 670 እና 672 ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል። የውንብድና ወንጀል ማለት ተገቢ ያልሆነ ብልፅግናን ለራስ አልያም ለላላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ የላላ ሰው የሆነውን ተንቀሳቃሽ ንብረት በኃይል ተግባር ወይም፣ ከባድ የሆነ ማንገላታት፣ ወይም ከባድ ዛቻን በመጠቀም ወይም ማናቸውንም ላላ ዘዳን በመጠቀም ተበዲዩን እንዲይከላከል በማድረግ ንብረቱን በኃይል መውሰድ ማለት እንደሆነ የወንጀል ህግ አንቀፅ 670 ድንጋጌ ያስገነዝባል። የዘረፊ ወንጀል ማለት ደግሞ በተፈጥሮ፣ በሰው ሰራሽ አልያም በማናቸውም ምክንያት በተፈጠረ አለመረጋጋት ወይም አደጋ ውስጥ የላላ ሰው የሆነን ንብረት መስረቅ ማለት እንደሆነ ከወንጀል ህግ አንቀፅ 672 ድንጋጌ መገንዘብ ይቻላል።
በልላ በኩል በወንጀል ህጉ ስለ ሽፍታነት በተወሰነ መልኩ የተገለፀው በአንቀፅ 240 ስር ነው።
ከዚህ ድንጋጌ ይዘት መገንዘብ እንደሚቻለው ሽፍታነት በዋናነት የጦር መሳሪያ በመያዝ በህግ በተቋቋመ መንግስት ላይ ታስቦ ከሚደረጉ አመፆች ውስጥ አንደ ነው። የጦር መሳሪያ ይዞ ማመፅ በራሱ ወንበዳ ወይም ዘራፉ የሚያስብል አይደለም። ድርጊቱ ውንብድና ወይም ዘረፊ የሚሆነው በአመፁ ሂደት ውስጥ በኃይል ተግባር የላላውን ሰው/አካል/ ንብረት መውሰድ ወይም መዝረፍ ሲረጋገጥ ነው። እናም የአንድ ተከሳሽ የወንጀል ድርጊት “ውንብድና ነው” ወይም “ዘረፊ ነው” ወይም “ሽፍታነት ነው” ለማለት ከመነሻው አጠቃላይ የተፈፀመው ድርጊት እና የተከሳሹ ተሳትፍ በተገቢው መንገድ ተለይቶ ሉታወቅ እና ሉረጋገጥ ይገባል።
አሁን በቀረበው ጉዲይ አመልካች ለቀረበበት ክስ በሰጠው የተከሳሽነት ቃል/የእምነት ክህደት ቃል/ “የሽፍታ ቡድን” ተብል በክሱ ዝርዝር ውስጥ ስማቸው ከተገለፁት ሰዎች ጋር አባል በመሆን ጫካ ከመግባቱ ውጭ በቀረበው ክስ አግባብ በውንብድና ስራው ላይ የተሰማራ ስለመሆኑ የገለፀው ነገር የለም። የሽፍታ ቡድን የተባለት ሰዎችም በቁጥር በርከት ያለ ከመሆናቸው በዘለለ በእርግጥም “የወንበዳ ቡድን” በሚያሰኝ አኳኋን የቡድን አደረጃጀት የነበራቸው እና የውንብድና ስራ ላይ ተሰማርተው የነበረ ስለመሆኑም የሚታወቅ ነገር የለም። በእርግጥ የተጠቀሱት ግለሰቡች በጦር መሳሪያ የታገዘ የውንብድና ስራ ላይ ተሰማርተው የነበረ ስለመሆኑ አመልካች በዝርዝር የተከሳሽነት ቃለ ውስጥ ገልጿል። ሆኖም በወንጀል የተከሰሰ ሰው የሚሰጠው ቃል ውጤት የሚኖረው የራሱን ጉዲይ በተመለከተ ብቻ በመሆኑ በአመልካች ቃል መነሻነት ብቻ በዚያ ደረጃ ድምዲሜ ላይ ለመድረስ የሚያስችል የህግ አግባብ የለም።
ሲጠቃለል አመልካች የሰጠው ዝርዝር የተከሳሽነት ቃል ከተከሰሰበት ወንጀል ዝርዝር ጋር አንድ ባለመሆኑ አመልካቹ ወንጀለን ለመፈፀሙ በማያጠራጥር እና ሙለ እምነት በሚጣልበት አኳኋን ድርጊቱን እና ጥፊተኝነቱን አምኗል የሚያሰኝ አይደለም። ይህ ከሆነ ደግሞ የአመልካቹ የወንጀል አጥፉነት ሉረጋገጥ የሚገባው ተጠሪ በሚያቀርበው ማስረጃ እንጂ አመልካች በሰጠው ቃል ባለመሆኑ የክልለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክሱ ሙለ በሙለ ታምኗል በሚል መነሻነት በአመልካች ላይ የሰጠው የጥፊተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ ከህግ አግባብ ውጭ ነው። የክልለ የበላይ ፍርድ ቤቶችም ይህንኑ ስህተት ማረም ሲገባቸው ውሳኔውን ማዕናታቸው በእርግጥም ሉነቀፍ የሚገባው መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ቁ/08986 ላይ የካቲት 25/2013 ዓ.ም የተሰጠው ትዕዛዝ እንዱሁም የሸካ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/14782 ላይ የካቲት 02/2013 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው የጥፊተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ በወንጀል ህግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 195(2(ለ(2))) መሰረት ተሽረዋል።
አመልካች ከዋስትና መብት አንፃር የሚያነሳው ጥያቄ ካለ ክርክሩን ለሚሰማው ፍርድ ቤት ያቅርብ።
መዝገቡ ተዘግቷል። ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.