በተደጋጋሚ ወንጅል ፈጽሞ የተቀጣ ተከሳሽ አዱስ ወንጀል ፈጽሞ በተገኘ ጊዜ ፍርድ ቤት ቅጣቱን ለማክበድ በወንጀል ሕግ ልዩ ክፍል አቶ ብርሃኑ ምላው እና ጣራ ቅጣት በማለፍ የዚህን መጠን እጥፍ በመያዝ መወሰን የሚችል ቢሆንም ይህ የሚቻለው ወንጀለ የተደጋገመ መሆኑን ብቻ በማየት ሳይሆን ጥፊተኛው የፈጸማቸው ወንጀልች ዓይነት፣ ክብደት እና ብዛት እንዱሁም ወንጀል ለመፈጸም የነበረው የአደገኝነት መጠን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ስለመሆኑ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 188 (1) እና (2)፣ የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 02/2006 አንቀጽ 22/2 የትግራይ ክልል ዓቃቤ ሕግ
No summary available.
መስከረም 27 ቀን 2013 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሣዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡- አቶ ሐይለ(አብይ) ሲሳይ ተጠሪ፡- የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን በዚሁ አግባብ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
የሰበር አቤቱታው ላቀርብ የቻለው አመልካች ሀምላ 11 ቀን 2011 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ የስር ፍ/ቤቶች የመግደል ሙከራ ሳልፈፅም እንደፈፀምኩ ተደርጎ የተሰጠው የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት አቤቱታ በማቅረባቸው ነው።
አመልካች በስር የፉንፉኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተከሳሽ የነበሩ ሲሆን ተጠሪ በአመልካች ላይ ባቀረቡት ክስም ተከሳሽ የወንጀል ህግ አንቀፅ 27(1) እና 540 በመተላለፍ ሰው ለመግደል አስቦ በሰንዲፊ በኬ 02 ቀበላ ውስጥ አለማየሁ ሙላቱ የተባለውን የግል ተበዲይ በሽጉጥ ተኩሶበት ሆደ ላይ በመምታት ጉዲት አድርሶቦት ህክምና በማግኘቱ ምክንያት ህይወቱ ሉተርፍ ችሎል በዚህም የመግደል ሙከራ ወንጀል ፈፅሟል በማለት ከሷል።
አመልካች ድርጊቱን አልፈፀምኩም በማለት ስለተከራከሩ የአቃቤ ህግ ምስክሮች ቀርበው የተሰሙ ሲሆን 1ኛ ምስክር አመልካች ወደ ሱቃቸው መጥተው ሲጋራ እንዱሸጡላቸው አዘዋቸው ዞር ሲለ ሽጉጥ ያልያዙ ቢሆንም ሲጋራውን ይዘው ዞር ሲለ የተኩስ ድምፅ የሰሙ መሆኑን ሆዲቸውን በግራ በኩል ተመትተው ሲወድቁ አመልካች መታሁክ ብለው ጥለዋቸው የሄደ መሆኑን ያስረደ ሲሆን 2ኛ ምስክርም ድምጽ ሰምተው ጎሚስታ ቤታቸው ፉት ለፉት ስላለ የጎማ ድምፅ መስሎቸው ሲወጡ አመልካች ሲሮጡ የተመለከቱ መሆኑን የግል ተበዲይ ውጪ ወጥተው የነበሩ ቢሆንም መሮጥ ያልቻለ መሆኑን ምን ሆንክ ሲለት አመልካች በሽጉጥ መታኝ ብለው የሆዲቸውን ግራ ጎን አሳይተዋቸው መቆም አቅቷቸው የወደቁ መሆኑን ስላስረደ አመልካች እንዱከላከለ ብይን ተሰጥቷል።
አመልካች በሰጡት የተከሳሽነት ቃልም ከግል ተበዲይ ጋር ፀብ የላላቸው መሆኑን በተለመደ ሁኔታ ወደ ሱቃቸው በመሄድ ሲጋራ፤ውሃ የመሳሰለትን ገዝተው የሚያልፈና የግል ተበዲይም የሚሸኟቸው መሆኑን በእለቱም በተመሳሳይ ሉገዙ ሄደው ሽጉጣቸው በካቦርት የውጭ ኪሳቸው ስለነበረ አውጥተው ወደ ግራ ጎናቸው ሉያዛውሩ ሲለ መሳርያው ባርቆባቸው የግል ተበዲይን የመታ መሆኑን ተመታህ ብለው ሆደን ይዘውልት የነበሩ ቢሆንም ቤተሰቦቹ ስለነበሩ ይገለኛል ብለው በመፍራት ሸሽተው የሄደ መሆኑን አስረድተዋል።
የአመልካች ምሰክርም በእለቱ ውሃ ለመግዛት ሄደው ከአመልካች ጎን ቆመው የነበረ መሆኑን አመልካች ሽጉጡን ከካፖርቱ ቀኝ ኪስ ወደ ግራ ኪስ ለማዛወር ሲል መሳርያው ተተኩሶ ጥይቱ በኮንቴነር ውስጥ አልፍ የግል ተበዲይን የመታው መሆኑን በዚህ ጊዜ አመልካች” መታሁክ ” ያለ መሆኑን ነገር ግን ወደ ውስጥ ገብተው የግል ተበዲይን ያልያዙ መሆኑን አመልካች የግል ተበዲይን አስበውበት ያልመቱ መሆኑን አስረድተዋል።
ከዚህ በኋላ ፍርድ ቤቱ በሰጠው ውሳኔም አቃቤ ህግ በምስክሩ አመልካች የግል ተበዲይን በሽጉጥ ሆዲቸውን የመቱ መሆኑን ያስረዲ መሆኑን የህክምና ማስረጃውም የግል ተበዲይ በተተኮሰባቸው ጥይት በደረሰባቸው ጉዲት ትንሹ አንጀት የተለያየ ቦታ ተበሳስቶ ፤ትልቁ አንጀት የላይኛው ክፍል ትንሹን አንጀት ሸፍኖ የሚገኘው በሆደና በጉበት ሽፊን ላይ ሰንበር መኖሩን የሚገልፅ ሆኖ ነገር ግን አመልካችና የመከላከያ ምስክራቸው ያስመዘገቡት ሽጉጡን ያዛወሩበትን ቦታ እና ከድርጊቱ በኋላ አመልካች የግል ተበዲይን መያዝ አለመያዛቸውን አስመልክቶ እርስ በእርሱ የሚጋጭ የምስክርነት ቃል ስለሰጡ አመልካች በቀረበባቸው ክስ ጥፊተኛ ናቸው በማለት የጥፊተኝነት ውሳኔ ሰጥቶ በስድስት አመት እስራት እንዱቀጡ ወስኗል።አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር ተሰኝተው ይግባኛቸውን ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረቡ ቢሆንም ተጠሪን መጥራት ሳያስፈልገው ይግባኙን የሰረዘው ሲሆን የክልለ ሰበር ሰሚ ችልትም በስር ፍርድ ቤት የተፈፀመ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም በማለት የሰበር አቤቱታውን ውድቅ አድርጎታል።
አመልካች ባቀረቡት የሰበር አቤቱታም ከግል ተበዲይ ጋር ከትውውቅ የዘለለ ፀብ ወይም ጥላቻ ሳይኖረኝ ምስክሮቹም በክሱ አግባብ ሳያስረደ የግል ተበዲይን ልገድል የምሞክርበት ምክንያት ሳይኖር አቃቤ ህግ የወ/ህ/ቁ.540ን ጠቅሶ ከፈፀምኩት ድርጊት ጋር የማይመሳሰል ክስ ማቅረቡ አላግባብ ነው፤እንደ ድርጊቱ እና እንደ ማሰረጃው ቅርበት በእንዝላልነት ወይም በግዳለሽነት ጥፊተኛ ተብዬ ልቀጣ ሲገባ በመግደል ሙከራ መቀጣቴ የወንጀል ህጉን አላማ የሳተ ነው፤የአመልካች ሽጉጥ ወንጀል የተፈፀመበት ስለሆነ ለመንግስት ገቢ ይሁን ተብል የታዘዘውም አግባብ ባለመሆኑ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ተሸሮ በእንዝላልነት ወይም በግዳለሽነት የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ ይሰጥልኝ እንዱሁም ሽጉጡ ለመንግስት ገቢ እንዱሆን የተሰጠው ትዕዛዝ ተነስቶ ሽጉጤ እንዱሰጠኝ ይወሰንልኝ በማለት አመልክተዋል፡፤
በአመልካች ላይ የተሰጠውን የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ ከድርጊቱ አፈፃፀምና ከወንጀል ህግ አንቀፅ 23(2) አንፃር ለማጣራት የሰበር አቤቱታው ያስቀርባል ከተባለ በኋላ ተጠሪ በሰጠው መልስም የአቃቤ ህግ የሰውና የሰነድ ማስረጃ የግል ተበዲይ ሆደ ላይ ተመትቶ ጉዲት የደረሰበት በአመልካች ሽጉጥ መሆኑን ያረጋገጡ በመሆናቸውና ይህ ፍሬ ነገር በአመልካች ያልተካደ በመሆኑ በአመልካች ላይ የተሰጠው የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ በዚሁ አግባብ የተሰጠ በመሆኑ ሉፀና ይገባል፤አመልካች ሽጉጡን አቀባብልት ከቦታ ቦታ ሲዘዋወር እንደነበረ በአመልካች ያልተካደ ፍሬ ጉዲይ በመሆኑ የተቀባበለ ሽጉጥ ጉዲት ቢያደርስ ውጤቱን እቀበለዋለሁ በማለት ሲንቀሳቀስ ወንጀለ በግል ተበዲይ ላይ ስለተፈፀመ የወንጀል ህጉ አንቀፅ 58(2)(ለ) በዚህ አይነት የሚፈፀም የወንጀል ድርጊት ሆነ ተብል እንደተፈፀመ የሚደነግግ በመሆኑ የመከላከያ ምስክሩም ወንጀለ በእንዝላልነት መፈፀሙን በማስረዲት የአቃቤ ህግን ማስረጃ ያላስተባበለ በመሆኑ ወንጀለ የተፈፀመበት ሽጉጥ ይመለስልኝ ማለቱ አግባብነት የላለው በመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያልተፈፀመበት የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ሉፀና ይገባል በማለት ተከራክሯል።
አመልካች የመልስ መልሳቸውን በማቅረብ ክርክራቸውን አጠናክረዋል።
በአጠቃላይ የግራ ቀኙ ክርክር ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም የሰበር ክርክሩን ያስቀርባል ከተባለበት ነጥብ፤ከተገቢው ህግና፤ከስር ፍርድ ቤት ክርክር አንፃር እንደሚከተለው መርምረነዋል።አንድ የወንጀል ድርጊት ተፈፀመ የሚባለው ህጋዊ ፤ግዙፊዊ እና ሞራላዊ ፍሬ ነገሮች በአንድነት ተሟልተው ሲገኙ መሆኑ በወ/ህ/አንቀፅ 23(2) የተመለከተ በመሆኑና አሁን በያዝነው ጉዲይ ተጠሪ ክሱን ያቀረበው የወ/ህ/አ.540ን ተላልፈው የመግደል ሙከራ ወንጀል መፈፀማቸውን መሰረት በማድረግ በመሆኑ ከአመልካች በተተኮሰ ጥይት የግል ተበዲይ በግራ ጎን ሆዲቸው ላይ መመታታቸውን ግራ ቀኙ የተማመኑበት ነጥብ በመሆኑ ይህም የህጉ መሰረታዊ ነጥብ ማለትም ግዙፊዊ ፍሬ ነገር የተሟላ መሆኑን የሚያሳይ በመሆኑ በአመልካች ላይ በአንቀፅ 27(1) እና 540 መሰረት የጥፊተኝነት ውሳኔ ላሰጥ የሚችለው አመልካች ድርጊቱን አስበው የፈፀሙ መሆናቸው በአቃቤ ህግ ማስረጃ ሲረጋገጥ ላሆን ይገባል።
የስር ፍርድ ቤት በአመልካች ላይ ከላይ በተመለከተው ድንጋጌ መሰረት የጥፊተኝነት ውሳኔ የሰጠ ቢሆንም አመልካች የወንጀል ሙከራ ድርጊቱን የፈፀሙት አስበው መሆኑን ያረጋገጠበትን የህግ አግባብ በውሳኔው ላይ አላመለከተም።ተጠሪ ለሰበር አቤቱታው ምላሽ ሲሰጥ የተቀባበለ ሽጉጥ ይዘው መንቀሳቀሳቸው የተቀባበለው ሽጉጥ ጉዲት ቢያደርስ ውጤቱን ተቀብለው መንቀሳቀሳቸውን ስለሚያሳይ የሃሳብ ክፍለ በወ/ህ/አ.58(2) አግባብ የተሟላ መሆኑን ገልፀው ተከራክረዋል።
በመሰረቱ አንድ የወንጀል ድርጊት ቀጥተኛ ባልሆነ አውቆ አጥፉነት ተፈፀመ የሚባለው ድርጊቱ ህገ ወጥና የሚያስቀጣ ውጤት ሉያስከትል እንደሚችል እያወቀ የሆነው ይሁን ብል ውጤቱን በመቀበል ድርጊቱን ያከናወነ መሆኑ ሲረጋገጥ ለመሆኑ በወ/ህ/አ.58(1)(ለ) ተመልክቷል።አሁን በያዝነው ጉዲይ አቃቤ ህግ በመልሱ ላይ አመልካች ሽጉጡ መቀባበለን የሚያውቁ መሆኑን ገልፆ የተከራከረ ቢሆንም የአመልካች ሽጉጥ ተቀባብል የተቀመጠው አመልካች መቀባበለን አውቀው ይሁን በእንዝላልነት አቀባብለው በመርሳታቸው መሆኑን ለይቶ ሉያስረዲ የሚገባ ቢሆንም ይህንን ስለማድረጉ የስር ፍርድ ቤት መዝገብ አያሳይም።
ሽጉጡን ከአንድ ጎናቸው ወደ ላላው ሲያዛውሩ ሽጉጡ የተቀባበለ መሆኑን ያውቁ የነበረ መሆኑንም አላስረዲም።አመልካች ሽጉጡ መቀባበለን እያወቁ እንዲይቀባበል በማድረግ ሉያዘዋውሩ ሲገባ ተቀባብል እያለ በጥንቃቄ ቢዘዋወር ጉዲት አያስከትልም ቢያስከትለም የመጣው ይምጣ በማለት ውጤቱን በመቀበል ሽጉጡን ሲያንቀሳቅሱ በግል ተበዲይ ላይ ጉዲቱን ያደረሱ መሆኑን አቃቤ ህግ ባላስረዲበት ወይም ወደዚህ አይነት መደምደሚያ የሚወስድ የምስክርነት ቃል ባልተሰጠበት ከመነሻውም አመልካች ወደ ግል ተበዲይ ሱቅ ሲሄደ የተቀባበለ ሽጉጥ የታጠቁ መሆኑን ያውቁ የነበረ መሆኑን ባላስረዲበት ድርጊቱን ቀጥተኛ ባልሆነ አውቆ አጥፉነት እንደተፈፀመ ተደርጎ በአመልካች ላይ በወ/ህ/አ.27(1) እና 540 መሰረት የጥፊተኝነት ውሳኔ መሰጠቱ የወንጀል ህግ አንቀፅ 23(2) እና 58(1)(ለ) ን መሰረት ያላደረገ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ብለናል።
ከዚህ ይልቅ አመልካች ሽጉጡን ከአንድ ጎናቸው ወደ ላላው ሲያዛውሩ መቀባበል አለመቀባበለን በማረጋገጥ ሉያዘዋውሩ ሲገባ ይህንን ሳያደርጉ ሽጉጡን ሲያንቀሳቅሱ በግል ተበዲይ ላይ ጉዲቱን ማድረሳቸው ጉዲት ያደረሰውን ድርጊት አስመልክቶ ምንም ጥንቃቄ ወይም በቂ ጥንቃቄ አለማድረጋቸው አመልካች ድርጊቱን በቸልተኝነት የፈፀሙ መሆኑን ያሳያል፡፤
አመልካች የግል ተበዲይን በሽጉጥ የመቱት በቸልተኝነት ከሆነ ደግሞ የአመልካች ድርጊት ሞትን ያላስከተለ በሙከራ ደረጃ የቀረ በመሆኑ የግራ ቀኙ ክርክር ከወ/ህ/አንቀፅ 27(1) ላታይና ሉመረመር ይገባል።በቸልተኝነት የሚፈፀሙ ድርጊቶች እንደ ሙከራ ሉቆጠሩ ይችላለ የሚል አስተያየት ቢኖርም አንድን የወንጀል ድርጊት ሙከራ ነው ለማለት ድርጊቱ በእውቀትና በፍላጎት የተፈፀመ መሆኑን ማረጋገጥ መሰረታዊ መስፈርት መሆኑ በተለያዩ ሀገራት ህጎች ውስጥ መካተቱ በቸልተኝነት የሚፈፀሙ ድርጊቶችን እንደ ሙከራ መቁጠሩ በአሁኑ ጊዜ ብዙም ተቀባይነት የላለው መሆኑን ያሳያል ።
የወንጀል ህጋችንም በአንቀፅ 27(1) “ማንም ሰው አስቦ…” የሚለውን ሃረግ በማካተት መቀረፁ ድርጊቱ በአውቆ አጥፉነት የተጀመረ መሆኑ መረጋገጡ መሰረታዊ መስፈርት መሆኑን የሚያሳይ በመሆኑ አመልካች የተከሰሱበት ድርጊት በቸልተኝነት የተፈፀመ የሙከራ ድርጊት መሆኑ ከላይ በተመለከተው አግባብ የተረጋገጠ ሆኖ እያለ የስር የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአመልካች ላይ የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ መስጠቱ እና በየደረጃው ያለ ፍርድ ቤቶች ይህንን መሰረታዊ የህግ ስህተት ሉያርሙ ሲገባ ሳያርሙ መቅረታቸው አግባብ ባለመሆኑ የስር ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ በመሻር አመልካች ከቀረበባቸው የመግደል ሙከራ የወንጀል ክስ በነፃ ሉሰናበቱ ይገባል በማለት ፍርድ ሰጥተናል።
የስር ፍርድ ቤት አመልካች የወንጀል ሙከራ ድርጊቱን የፈፀሙበትን ሽጉጥ እንዱወረስ የወሰነበትን የህግ አግባብ በውሳኔው ላይ ያላመለከተ በመሆኑና ተጠሪም የወንጀል ሙከራ ድርጊቱ የተፈፀመበት መሳርያ የሚወረስበትን አሳማኝና ህጋዊ ምክንያት ያላቀረበ በመሆኑ የሚከተለው ውሳኔ በአብላጫ ድምፅ ተሰጥቷል።
1.በፉንፉኔ ዙርያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.18862 ግንቦት 06 እና 08 ቀን 2011 ዓም ተሰጥቶ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.315181 በ04/10/2011 ዓም በተሰጠ ትዕዛዝ እና በክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ.311856 በ28/10/2011 ዓም በተሰጠ ትዕዛዝ የፀናው የጥፊተኝነትና የቅጣት እንዱሁም የሽጉጥ ውርስ ትዕዛዝ በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ.195 (2)(ለ)(1) መሰረት ተሽሯል።
2.አመልካች ከቀረበባቸው ክስ በነፃ የተሰናበቱ ስለሆነ ከእስር ሉለቀቁ ይገባል ብለናል።ለማረሚያ ቤቱ የመፈቻ ትዕዛዝ ይፃፍ።
3.መለያ ቁጥሩ EP1291212 የሆነው የቱርክ ሽጉጥ ለአመልካች እንዱመለስላቸው በአብላጫ ድምፅ ታዟል።መዝገቡ ተዘግቷል።
No topics extracted.