የቅጣት ውሳኔ እንዲይገደብ በወንጀል ህግ አንቀፅ 194 ስር የተቀመጠው ክልከላ ባልተሟላበት ሁኔታ ተከሳሽ ክሱን ክድ ከመከራከሩም በላይ ከተበዲይ ጋር ታርቆ ለመካስ እና የፍርድ ቤትን ወጪ ለመሸፈን የሰጠው ማረጋገጫ የለም በሚል በመልካም ጠባይ የሚመራ ለመሆኑ በፍርድ ቤት እንዱያቀርብ የሚጠየቅ የዋስትና ማረጋገጫ ትዕዛዝ ቅጣትን ለመገደብ ቅድመ ሁኔታ ተደርጎ የሚወሰድ የፋዳራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ እና አቶ ቢዝነስ ለማ
No summary available.
የሰ.መ.
ታሕሳስ 27 ቀን 2013 ዓ.ም ዳኞች፡- መዓዛ አሸናፉ እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሣዬ አመልካች፡- አቶ ብርሃኑ ምላው ተጠሪ፡- የትግራይ ክልል ዓቃቤ ሕግ መዝገቡ ለምርመራ የተቀጠረ ነው። በመሆኑም መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
የሰበር አቤቱታው ላቀርብ የቻለው አመልካች በቀን 22/03/2011 ዓ.ም ጽፍ ባቀረበው የሰበር አቤቱታ በትግራይ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ሽራሮ ከተማ ወረዲ ፍ/ቤት በመ. በቀን 24/10/2011 ዓ.ም አመልካችን በወንጀል ሕግ አንቀጽ 670 ድንጋጌ ጥፊተኛ በማለት የሰጠው የጥፊተኝነት ውሳኔ እና በቀን 02/11/2011 ዓ.ም አመልካች ከዚህ በፉት በተደጋጋሚ ተቀጥቶ ትምሕርት ስላላገኘ በአስራ ስምንት ዓመት ጽኑ እሥራት እንዱቀጣ ሲል የሰጠው የቅጣት ውሳኔ፤ ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት በየደረጃው ያለ የክልለ ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት አቤቱታ በማቅረቡ ነው።
ጉዲዩ ወንጀልን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በትግራይ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ሽራሮ ከተማ ወረዲ ፍ/ቤት ነው።
የአሁን ተጠሪ በስር 1ኛ ተከሳሽ እና በአሁን አመልካች ላይ በስር ፍርድ ቤት ያቀረበው ክስ ይዘት በአጭሩ፡- ተከሳሾች የወንጀል ሕጉን አንቀጽ 32/1/ሀ እና 670 ድንጋጌን በመተላለፍ የማይገባቸውን ጥቅም ለማግኘት በማሰብ በቀን 03/07/2011 ዓ.ም በግምት 5፡30 ሰዓት ሲሆን በሽራሮ ከተማ ቀበላ ሙሴ ልዩ መጠሪያው ሰላም ፕላኔት ሆቴል አካባቢ የግል ተበዲይን 1ኛ ተከሳሽ ከኋላው በመምጣት በእጁ አንገቱን አንቆ ሲይዘው አመልካች ደግሞ ከፉት እጁን አንቆ በመያዝ ወደ ኮብል ስቶን በአፈ በመድፊት እንዱወድቅ በማድረግ በሱሪው ኪስ ውስጥ የነበረውን ብር 400 ገንዘብ እና ብር 2200 የሚገመት ሞባይል ወስደዋል የሚል ነው።
አመልካች እና የስር 1ኛ ተከሳሽ ክሱ ተነቦላቸው እንዱረደት ከተደረገ በኋላ ድርጊቱን አልፈጸምንም ብለው ክደው በመከራከራቸው ፍርድ ቤቱ የዓቃቤ ሕግን ምስክሮች ከሰማ በኋላ ተከሳሾች ክሱን እንዱከላከለ ሲል ብይን ሰጥቷል።
አመልካች እና የስር 1ኛ ተከሳሽም ክሱን ለመከላከል ያስችለናል ያለትን የመከላከያ ማስረጃ አቅርበው አሰምተዋል። ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ መርምሮ ተከሳሾች ባቀረቡት የመከላከያ ማስረጃ የቀረበባቸውን ክስ አልተከላከለም በማለት በወንጀል ሕግ አንቀጽ 31/1/ሀ እና 670 ድንጋጌ መሰረት ጥፊተኛ ብሎቸዋል። ቅጣቱንም በቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 02/2006 መሰረት በማስላት የስር 1ኛ ተከሳሽን በሶስት ዓመት ጽኑ እሥራት እንዱቀጣ የወሰነ ሲሆን አመልካችን በሚመለከት ደግሞ አመልካች ከዚህ በፉት በሶስት የተለያዩ መዝገቦች የተቀጣ መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ ቀርቧል፤ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 188/1/2 ቅጣቱ የአዱሱ ወንጀል መጨረሻ ሉያርፍ እንደሚገባ የሚደነግግ በመሆኑ እና አመልካች በተደጋጋሚ ተቀጥቶ ትምሕርት ስላላገኘበት እና አሁን ጥፊተኛ የተባለበት የሕግ አንቀጽ እስከ 15 ዓመት ሉደርስ በሚችል ቅጣት እንደሚቀጣ ስለሚደነግግ የዚህ እጥፍ 30 ዓመት ነው፤ በቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 02/2006 የ 30 ዓመት እስራት ስለላለ ወደ 25 ዓመት ወርዶል፤ ይህም እርከን 37 ላይ ያርፊል፤ ወንጀለ በሕብረት የተፈጸመ በመሆኑ አንድ ማክበጃ ቢኖርም ከእርከን 37 በላይ የእስራት እርከን የለም፤ አመልካች የቤተሰብ አስተዲዲሪ በመሆኑ አንድ የቅጣት ማቅለያ አለው በማለት ቅጣቱን አቅል በእርከን 36 ላይ በማሳረፍ በዚሁ እርከን ባለው ፍቅድ ስልጣን በ 18 ዓመት ጽኑ እስራት እንዱቀጣ ሲል ወስኗል። ይህ ውሳኔ በየደረጃው ባለ የክልለ ፍርድ ቤቶች ጸንቷል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት ተፈጽሞበታል በሚል ሲሆን ይዘቱም፡- የዓቃቤ ሕግ ምስክሮች አመልካች ወንጀል እንደፈጸምኩ ባላስረደበት ሁኔታ አመልካች ክሱን እንድከላከል ብይን መሰጠቱ አግባብ አይደለም፤ አመልካች ባቀረብኳቸው መከላከያ ምስክሮች ወንጀለ ተፈጸመ በተባለበት ቦታ ላይ እንዲልነበርኩ አስረድቼ ሳለሁ መከላከያ ምስክሮቼ የሰጡት የምስክርነት ቃል በአግባቡ ሳይመዘን ጥፊተኛ መባላ አግባብ አይደለም፤ አመልካች ከዚህ በፉት ተደጋጋሚ የወንጀል ሪርድ አለበት በማለት የቀረበው የቅጣት ማክበጃ የወንጀል ሕጉን ቁጥር 84 እና 188(1)(2) ድንጋጌን መሰረት ያላደረገ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤቶች ልማደኛ ደጋጋሚ ነው በማለት ቅጣቱን አክብደው የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ ከቅጣት አንጻር አግባብነቱን ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ በዚህ ችልት እንዱታይ ተደርጓል። ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎም ግራ ቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
ተጠሪ መጋቢት 18 ቀን 2012 ዓ.ም የሰጠው መልስ ይዘት በአጭሩ፡- አመልካች ጥፊተኛ ከተባለበት ወንጀል በፉት በሶስት የተለያዩ ወንጀልች ጥፊተኛ ተብል ተቀጥቷል፤ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 188(2) እና (3) እና በቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 አንቀጽ 22/2 መሰረት ልማደኛ ደጋጋሚ በሚሆንበት ጊዜ በልዩ ሕግ ከተቀመጠው ቅጣት ከብድ እጥፍ ተደርጎ ሉቀጣ እንደሚችል እና በሕጉ ጠቅላላ ክፍል ከተቀመጠው ማለፍ እንደማይቻል ተደንግጓል፤ አመልካች ካንድም ሁለቴ ተቀጥቶ ከጥፊቱ ሉማር ስላልቻለ ይህንኑ መሰረት በማድረግ ቅጣቱ ከብድ መወሰኑ ተገቢ ስለሆነ ሉጸና ይገባል የሚል ነው። አመልካችም የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው። ይህ ችልትም በሰበር አጣሪው ችልት ሉጣራ ይገባዋል ተብል የተያዘውን ነጥብ ከግራ ቀኙ ክርክር፤ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምሮታል።
ከሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ ይዘት መገንዘብ የቻልነው በአመልካች ላይ ቅጣቱ ከብድ ሉወሰን የቻለው አመልካች ከዚህ በፉት በሶስት የተለያዩ መዝገቦች የተቀጣ ቢሆንም ከጥፊቱ መማር ስላልቻለ ቅጣቱ ሉሰላ የሚገባው የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 188(1)እና(2) በሚደነግጉት አግባብ ነው በሚል ነው። የስር ፍርድ ቤት ይህንኑ መሰረት በማድረግ ቅጣቱን ሲያሰላ አመልካች በአዱሱ ወንጀል የሚቀጣበትን ጣሪያ ቅጣት በመውሰድ የዚሁን መጠን እጥፍ በመያዝ ስለመሆኑ በውሳኔው ላይ በግልጽ ተመልክቷል።
ስለሆነም በዚህ ችልት ምላሽ ሉያገኝ የሚገባው የክርክሩ መሰረታዊ ነጥብ የስር ፍርድ ቤት አመልካች ደጋጋሚ ወንጀለኛ ነው በማለት ቅጣቱን አክብድ ለመወሰን አመልካች በአዱሱ ወንጀል ሉቀጣ የሚችልበትን ጣሪያ ቅጣት መያዙ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ነው።
በመሰረቱ የወንጀል ሕጉ መሰረታዊ ዓላማ እና ግብ ለጠቅላላው ጥቅም ሲባል የአገሪቱን መንግስት፤
የሕዝቦቹን፤ የነዋሪዎቹን፤ ሰላም፤ ደህንነት፤ ሥርዓት፤ መብት እና ጥቅም መጠበቅ እና ማረጋገጥ፤
ስለወንጀልች እና ስለቅጣታቸው በቅድሚያ ማስጠንቀቂያ በመስጠት፤ ማስጠንቀቂያነቱ በቂ ባልሆነበት ጊዜ ወንጀል አድራጊዎች ተቀጥተው ላላ ወንጀል ከመፈጸም እንዱቆጠቡ እና ለላልች ማስተማሪያ እንዱሆኑ ወይም እንዱታረሙ በማድረግ ወይም ተጨማሪ ወንጀልች እንዲይፈጽሙ እርምጃዎች እንዱወሰደባቸው ማድረግ ስለመሆኑ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 1 ላይ በግልጽ ተመልክቷል። ይህንኑ ዓላማ በሚያሳካ ሁኔታም ቅጣት ስለሚሰላበት፤ ስለሚከብድበት እና ስለሚቀልበት ሁኔታ በዚሁ ሕግ ላይ ስለወንጀል ቅጣት እና አፈጻጸሙ በሚደነግገው ሁለተኛ መጽሐፍ ከአንቀጽ 87 ጀምሮ በዝርዝር ተቀምጧል።
የወንጀል ሕግ አንቀጽ 188/1 በዚሁ ሕግ አንቀጽ 67 /ስለደጋጋሚነት/ በተገለጹት ሁኔታዎች አንድ አዱስ ወንጀል በተፈጸመ ጊዜ፤ ፍርድ ቤቱ ቅጣቱን ማክበድ ያለበት ሲሆን ለአዱሱ ወንጀል በሕጉ ልዩ ክፍል ከተደነገገው ጣራ ቅጣት በማለፍ መወሰን ይችላል። ፍርድ ቤቱ በሕጉ ልዩ ክፍል ለአዱሱ ወንጀል ወይም ከአዱሶቹ ተደራራቢ ወንጀልቸ ከባድ ስለሆነው ወንጀል የተደነገገውን ጣራ ቅጣት እጥፍ እስኪሆን ቅጣቱን ሉያከብድ ይችላል በማለት ይደነግጋል። የዚሁ ሕግ ንዐስ ቁጥር 2 በተደጋገሙት የወንጀልች ዓይነት እና ብዛት እንዱሁም በወንጀለኛው ጥፊተኝነት እና በድርጊቱ አደገኛነት መጠን ፍርድ ቤቱ በዚሁ አንቀጽ በንዐስ አንቀጽ 1 የተመለከተውን ከፍተኛ ቅጣት ሳይከተል ለቅጣቱ ዓይነት በሕጉ ጠቅላላ ክፍል እስከተደነገገው ከፍተኛ ቅጣት ሉያሳድግ ይችላል በማለት ይደነግጋል። በልላ በኩል የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 02/2006 አንቀጽ 22/2 ጥፊተኛው ደጋጋሚ ወንጀለኛ በሆነ ጊዜ ፍርድ ቤቱ ለአዱሱ ወንጀል የመነሻ ቅጣቱ የሚያርፍበትን እርከን በመመሪያው መሰረት ከለየ በኋላ ቅጣቱን በወንጀል ሕግ አንቀጽ 188 በተመለከተው መሰረት ከአንድ እርከን ጀምሮ ቅጣቱን ሉያሳድግ ይችላል፤ በመቀጠልም ጠቅላላ የቅጣት ማክበጃ ምክንያቶችን መሰረት በማድረግ ቅጣቱን ያከብዲል፤
ነገር ግን በወንጀል ሕጉ ጠቅላላ ክፍል ለቅጣቱ ዓይነት ከተቀመጠው ጣሪያ ሉበልጥ አይችልም በማለት ይደነግጋል።
ከላይ በዝርዝር ከተመለከቱት ከድንጋጌዎች ይዘት መገንዘብ የሚቻለው በድንጋጌው በተጠቀሰው አግባብ የአዱሱን ወንጀል የቅጣት ጣሪያ በመውሰድ ቅጣትን እጥፍ ድረስ ማክበድ የሚቻለው ወንጀለ የተደጋገመ መሆኑን ብቻ በማየት ሳይሆን ጥፊተኛው የፈጸማቸው ወንጀልች ዓይነት፤ ክብደት እና ብዛት እንዱሁም ጥፊተኛው ወንጀል ለመፈጸም የነበረው የአደገኝነት መጠን ግንዛቤ ውስጥ ማስገባት አስፈላጊ መሆኑን እና ይኸው ሲፈጸምም ፍርድ ቤቱ እንደ ሁኔታው ከአንድ እርከን ጀምሮ ቅጣቱን ሉያሳድግ የሚችል መሆኑን ነው። ስለሆነም ፍርድ ቤቶች ይህንኑ አንቀጽ መሰረት በማድረግ ቅጣትን ሲወስኑ እነኚህን ሁኔታዎች በጥንቃቄ ሉፈትሹ ይገባል።
በያዝነው ጉዲይ የስር ፍርድ ቤት አመልካች ከዚህ በፉት የመዝገብ ቁጥራቸው 4977 በሆኑ የተለያዩ ሶስት መዝገቦች በገደብ፤ በ4 ዓመት ጽኑ እሥራት እና በአንድ ዓመት ከ7 ወር እስራት ተቀጥቶ ሉታረም አልቻለም በማለት የአዱሱን ወንጀል ጣሪያ ቅጣት በመወሰድ እጥፈን ወስድ ቅጣቱን ያሰላ ቢሆንም አመልካች ጥፊተኛ የተባለባቸው ወንጀልች ዓይነት እና ክብደት እንዱሁም ጥፊተኛው ወንጀል ለመፈጸም የነበረው የአደገኝነት መጠን ምን እንደሚመስል በውሳኔው ላይ አላመላከተም። ስለሆነም ይህ ባልተሟላበት ሁኔታ የስር ፍርድ ቤት አመልካች ደጋጋሚ ወንጀለኛ ነው በማለት በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 188(1)እና(2) መሰረት በአዱሱ ወንጀል የሚቀጣበትን የቅጣት ጣሪያ እጥፈን በመውሰድ ቅጣቱን አስልቶ በ 18 ዓመት ጽኑ እሥራት እንዱቀጣ ሲል የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል። በመሆኑም በቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 02/2006 መሰረት ቅጣቱን እንደሚከተለው አስልተናል።
አመልካች ጥፊተኛ የተባለበት የወንጀል ሕግ አንቀጽ 670 በቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 02/2006 ደረጃ እና እርከን የወጣለት ነው፤ አመልካች ድርጊቱን ለመፈጸም የተጠቀመው መሳሪያ የላለ እና የወሰደው ንብረት ግምት ብር 2400 በመሆኑ የወንጀል ደረጃው በደረጃ 2 የቅጣት መነሻ እርከን ደግሞ በእርከን 13 ላይ ያርፊል፤ አመልካች ደጋጋሚ ወንጀለኛ በመሆኑ በአምስት እርከን ቅጣቱ ሉከብድ የሚገባ ሆኖ አግኝተነዋል፤ በልላ በኩል በስር ፍርድ ቤት ተቀባይነት ያገኙ ሁለት የቅጣት ማክበጃ ምክንያቶች ስላለ በድምሩ በሰባት እርከን ቅጣቱ ሲከብድ በእርከን 20 ላይ ያርፊል፤ አመልካች በስር ፍርድ ቤት ተቀባይነት ያገኘ አንድ የቅጣት ማቅለያ ምክንያት ስላለው ቅጣቱ ሲቀል በእርከን 19 ላይ ያርፊል፤ በእርከን 19 ያለው ፍቅድ ስልጣን ከአራት ዓመት እስከ አራት ዓመት ከአስር ወር ነው፤
ስለሆነም በዚሁ ፍቅድ ስልጣን ስር አመልካችን ያርማል፤ ላልቹንም ያስጠነቅቃል ብለን ያመንበትን አመልካች በአራት ዓመት ከስድስት ወር ጽኑ እሥራት እንዱቀጣ በማለት ቅጣቱን አሻሽለን ወስነናል።
በዚህም ምክንያት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
በትግራይ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ሽራሮ ከተማ ፍ/ቤት በመ. በቀን 02/11/2011 ዓ.ም በአመልካች ላይ ያስተላለፈው የቅጣት ውሳኔ፤ ይህንኑ የቅጣት ውሳኔ በማጽናት የሰሜን ምዕራብ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ. በቀን 26/11/2011 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ፤ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ. በቀን 18/02/2012 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 195/2/ለ/2 መሰረት ተሻሽሎል።
ከላይ በፍርድ ሐተታው ላይ በተገለጸው ምክንያት በአመልካች ላይ ተላልፍ የነበረውን የቅጣት ውሳኔ በማሻሻል በአራት ዓመት ከስድስት ወር ጽኑ እሥራት እንዱቀጣ በማለት ወስነናል።
የሚመለከተው ማረሚያ ቤት በተሻሻለው የቅጣት ውሳኔ መሰረት እንዱያስፈጽም የዚህ ውሳኔ ግልባጭ ይተላለፍለት።
መዝገቡ ውሳኔ ስላገኘ ተዘግቷል። ይመለስ
No topics extracted.