የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 435 በጠባቡ መተርጎም ስላለበት በአክሲዮን ሽያጭ ማስታወቂያ ላይ መገለጽ የሚገባዉ ነገር ባለመገለጹ ወይም የሽያጩ ሥነ ሥርዓት በትክክል ባለመፈጸሙ ምክንያት በተፈጠረ ጉድለት ሐራጁ ሉፈርስ የሚችልበትን ልዩ ሁኔታ ድንጋጌዉ ባለማመላከቱ ጉዲት የደረሰበት ማንኛዉም ሰዉ የሐራጅ ሽያጩ ሳይፈርስ ለጉዲቱ አላፉ በሆነዉ ሰዉ ላይ ክስ አቅርቦ ተገቢውን ካሳ የሚካስ አቶ ቶፉቅ መለሰ እና እነ አቶ እንድሪስ ሳቢር (2 ሰዎች)
No summary available.
የካቲት 30/2013 ዓ.ም ዳኞች፡ እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሳዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡- የፋዳራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ተጠሪ፡- አቶ ቢዝነስ ለማ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ ለዚህ ችልት የቀረበው የወንጀል ቅጣት ሉገደብ ስለሚቻልበት ሁኔታ በወንጀል ህጉ ውስጥ ስለ ወንጀል ቅጣት አገዲደብ ከተቀመጠው መመዘኛ እና በዚሁ ችልት ቀደም ሲል በመ/ቁ/17211 ላይ ከተሰጠው የህግ ትርጉም አኳያ መርምሮ ለመወሰን ነው።
ክርክሩ የተጀመረው የአሁን አመልካች የአሁን ተጠሪን ጨምሮ በሁለት ተከሳሾች ላይ የኢ.ፋ.ዳ.ሪ.
የወንጀል ህግ አንቀፅ 32(1(ሀ)) እና 670 ድንጋጌን ጠቅሶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረበው የወንጀል ክስ ነው። ተጠሪ የቀረበበትን ክስ ድርጊቱን እና ጥፊተኝነቱን ክድ በመከራከሩ የግራ ቀኙ ምስክሮች ተሰምተው ተጠሪ በተከሰሰበት ወንጀል ጥፊተኛ ተብል በ1(አንድ) ዓመት ከ6(ስድስት) ወር ፅኑ እስራት እንዱቀጣ ተወስኖ የቅጣት ውሳኔው አፈፃፀም በ2(ሁለት) ዓመት የፈተና ጊዜ እንዱቆይ ታዟል። አመልካች የቅጣት ውሳኔው ሉገደብ አይገባም በማለት ለፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ያቀረበው ይግባኝ ውድቅ ተደርጓል።
የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ነው። አመልካች ህዲር 08/2012 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ተጠሪ የቀረበበትን ክስ ክድ በተከራከረበት፤ ከተበዲይ ጋር ታርቆ ባልካሰበት እና የፍርድ ቤቱን ወጪ ለመክፈል ማረጋገጫ ባላቀረበበት የቅጣት ውሳኔው መገደቡ የወንጀል ህጉ አንቀፅ 192 እና 197 መመዘኛን ያላማከለ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ሉታረም ይገባል በማለት ጠይቋል።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ከላይ በመግቢያው ላይ የተጠቀሰውን ነጥብ ግራ ቀኙ በተገኙበት ለማጣራት ጉዲዩ ለዚህ ችልት እንዱቀርብ በመታዘዙ ግራ ቀኙ የፅሁፍ ክርክር እንዱለዋወጡ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ጭብጥ በአጭሩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ችልቱም ጉዲዩን አግባብነት ካለው ህግ ጋር በማገናዘብ መርምሯል። እንግዱህ የወንጀል ቅጣት ዋና ዓላማው አጥፉውን ማስተማር ነው። በወንጀል ጥፊተኛ የተባለን ሰው ለማስተማር ደግሞ ሁላም ወደ ማረሚያ ቤት መላክ አስፈላጊ ላይሆን ይችላል። ይልቁንም ለጥፊተኛው አንድ የፈተና ጊዜ ከፅኑ ማስጠንቀቂያ ጋር ሰጥቶ አመለ ቢፈተሸ መልካም ይሆናል ተብል ሲታመን የእስራት ቅጣቱን አፈፃፀም ለጊዜው አግድ ማቆየት እንደሚቻል ከወንጀል ህጉ አንቀፅ 192 እና ተከታዮቹ መገንዘብ ይቻላል። ፍርድ ቤት በአንድ የወንጀል ተከሣሽ ላይ የጥፊተኛነትና የቅጣት ውሣኔ ከተሰጠ በኋላ የተወሰነው የእሥራት ቅጣት ሳይፈፀም በገደብ እንዱቆይ ሉያዝ የሚችልበት መሰረታዊ መርሆዎችም በወንጀል ህጉ አንቀፅ 192 ስር ተደንግጓል።
በልላ በኩል የወንጀል ቅጣት ውሳኔ ሉገደብ የማይቻልባቸው ልዩ ሁኔታዎች ደግሞ በወንጀል ህጉ አንቀፅ 194 ስር በዝርዝር ተቀምጠዋል። በዚህ አንቀፅ ስር ቅጣት እንዲይገደብ የተቀመጠው ክልከላ 1ኛ/ጥፊተኛው ከዚህ በፉት የፅኑ እስራት ቅጣት ወይም ከ3(ሶስት) ዓመት በሚበልጥ ቀላል እስራት ቅጣት ተፈርድበት ከሆነ እና አሁን ጥፊተኛ በተባለበት ወንጀልም ከእነዚሁ ቅጣቶች አንደ የሚወሰንበት ከሆነ፤ 2ኛ/ ከዚህ በፉት ያልተቀጣ ሆኖ አሁን በተከሰሰበት ወንጀል ከአምስት ዓመት የበለጠ ፅኑ እስራት የሚፈረድበት ከሆነ፤ 3ኛ/ የቅጣት አፈፃፀሙ ከመታገደ በፉት ጥፊተኛው በተራ ቁጥር 1 እና 2 ስር ከተመለከቱት ቅጣቶች ውስጥ በአንደ ሉያስቀጣው የሚችል ላላ ወንጀል ስለመፈፀሙ የተደረሰበት ከሆነ፤ 4ኛ/ ወንጀለኛው ቅጣቱ ታግድለት ለፈተና በተለቀቀበት ጊዜ ውስጥ በወንጀል ህጉ አንቀፅ 200 ስር በተመለከተው አኳኋን አስቦ አንድን ወንጀል የፈፀመ ከሆነ ወይም 5ኛ/ የቅጣት አፈፃፀሙ በታገደለት ጉዲይ የተሰጠው የፈተና ጊዜ መልካም ፍሬ የሚያስገኝ አለመሆኑን ፍርድ ቤቱ ሲረዲው የሚለት ናቸው። እናም ፍርድ ቤት አንድን የወንጀል ቅጣት ከመገደቡ በፉት የቅጣት ውሳኔው እንዲይገደብ ከእነዚህ መመዘኛዎች ውስጥ በአንደ ክልከላ ያልተደረገበት መሆኑን በቅድሚያ ሉያረጋግጥ ይገባል።
አሁን በቀረበው ጉዲይ የከፍተኛው ፍርድ ቤት በተጠሪ ላይ ተገቢ ነው ያለውን የወንጀል ቅጣት ከወሰነ በኋለ የቅጣት ውሳኔን አፈፃፀም በፈተና ጊዜ እንዱቆይ አዟል። በተጠሪ ላይ የተወሰነው የቅጣት ውሳኔ እንዲይገደብ በወንጀል ህጉ አንቀፅ 194 ስር የተቀመጠ ክልከላ የለም። አመልካችም የቅጣት ውሳኔው ሉገደብ አይገባም የሚለው በወንጀል ህግ አንቀፅ 194 ክልከላ ተደርጎበታል በሚል ሳይሆን ተጠሪ ክሱን ክድ ከመከራከሩም በላይ ከተበዲይ ጋር ታርቆ ለመካስ እና የፍርድ ቤቱን ወጪ ለመሸፈን የሰጠው ማረጋገጫ የለም በሚል ነው። በመሰረቱ እነዚህ መመዘኛዎች በወንጀል ህጉ አንቀፅ 197 መሰረት ጥፊተኛው በተሰጠው የፈተና ጊዜ ውስጥ በመልካም ጠባይ እንዱመራ እና የፈተና ጊዜው ተገቢውን ፍሬ እንዱያፈራ በሚል ለመልካም ጠባይ አመራር ዋስትና የሚሰጡ ትዕዛዛት እንጂ ቅጣትን ለመገደብ ቅድመ ሁኔታዎች አይደለም። በሰ/መ/ቁ/172111 ላይ የተሰጠው ውሳኔም በመዝገቡ ላይ በወንጀል ጥፊተኛ ከተባለት ግለሰብ የግል ሁኔታ አንፃር የፈተና ጊዜ ቢሰጣቸው በመልካም ጠባይ የሚመሩ ለመሆኑ አሳይተዋል የሚያስብል ነገር አልተገኘም በሚል አቋም የተያዘበት ጉዲይ እንጂ ሁላም ቢሆን የወንጀል ክስ ክድ የተከራከረ ወይም ከተበዲዩ ጋር ታርቆ ተገቢውን ካሳ ላልከፈለ የወንጀል አጥፉ ቅጣት ሉገደብ አይገባም የሚል ግልፅ ትርጉም አይደለም። ከመነሻውም ቢሆን የወንጀል ክስን ክድ መከራከር በራስ ላይ ማስረጃ ካለመሆን እና የወንጀል ጥፊተኝነቱ በማስረጃ እስኪረጋገጥ ድረስ ንፁህ ሆኖ ከመገመት ህገ መንግስታዊ መብት ጋር የተያያዘ በመሆኑ የወንጀል ክስ ያላመነ ሰው የቅጣት ውሳኔ ሉገደብለት አይገባም በሚል ትርጉም ላሰጥበት የሚቻል ጉዲይም አይደለም። ከላይ እንደተመለከው የወንጀል ክስን ማመን፤
ከተበዲዩ ጋር ታርቆ በእውነት መፀፀትን ማሳየት እና ላልች ተያያዥ ጉዲዮች የወንጀል ቅጣት ውሳኔን ለመገደብ በቅድመ ሁኔታነት የተቀመጡ መመዘኛዎች ሳይሆኑ የወንጀል አጥፉው በመልካም ጠባይ የሚመራ ለመሆኑ እንዱያቀርብ የሚጠየቅ የዋስትና ማረጋገጫ በመሆኑ በህግ በግልፅ ያልተቀመጠ ክልከላ መሰረት ተደርጎ ቅጣቱ ሉገደብ አይገባም የሚባልበት የህግ አግባብ የለም።
በመሆኑም የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ ላይ የወሰነውን የቅጣት ውሳኔ ማገደ እና ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም ይህንኑ በመቀበለ የፈፀሙት መሰረታዊ የህግ ስህተት ባለመኖሩ ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ በመ/ቁ/181393 ላይ ጥቅምት 26/2012 ዓ.ም በዋለው ችልት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ ያፀናበት ውሳኔ በወንጀል ህግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 195(2(ሀ)) መሰረት ፀንቷል።
መዝገቡ ተዘግቷል። ይመለስ።
No topics extracted.