የብድር ውል የአራጣ ውል ነው ለማለት መሟላት የሚገባቸው እነ ወ/ሮ ገነት በላቸው (2 ሰዎች) እና አቶ ዮሴፍ አከበረኝ --- ይህ ውሳኔ በቅጽ 24፤ ገጽ 252 ላይ የታተመ ሲሆን በዚህ ቅጽ ጭብጡ ብቻ ተስተካክል ወጥቷል። አንድ ባንክ ለደንበኛው ክፍያ የፈጸመዉ በዋናነት ተከፊዩ ሰዉ ብቻ ያዉቀዋል ተብል የሚገመተዉን ፍሬ ነገር ማለትም ገንዘቡን የላከዉ ሰዉ ማንነት፤የተላከዉ ገንዘብ መጠን፤የሚስጥር ቁጥር እና የተላከለት ሰዉ ስም እና ተከፊዩ ሰዉ የሰጠዉ መረጃ ተዛማጅና ትክክል መሆናቸዉ በተለመደዉ አሰራር መሰረት በማረጋገጥ እስከሆነ ድረስ ክፍያዉን የተቀበለዉ ሰው ሀሰተኛ የቀበላ መታወቂያ ይዞ ስለቀረበ ክፍያው ለማይገባው ሰዉ ነዉ በሚል ምክንያት ባንኩ በድጋሚ ገንዘቡን እንዱከፍል የሚገደድበት የህግ ምክንያት የላለ አባይ ባንክ አ.ማ እና አቶ ማርቆስ ጋትሮ ---- አዋጅ ቁጥር 592/2000 አንቀጽ 2/2/መ/፣ 53
No summary available.
የሰ/መ/ ጥር 27 ቀን 2013 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ ተሾመ ሽፈራዉ ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግሥቱ ነጻነት ተገኝ አመልካች፡- አቶ ቶፉቅ መለሰ- ቀረቡ ተጠሪዎች፡-
ጉዲዩ አክሲዮን በሐራጅ ለመሸጥ በወጣ ማስታወቂያ ላይ ያልተገለጸ የባለአክሲዮን ዕዲ የመክፈል ኃላፉነት የማን እንደሆነና በሐራጅ ሽያጩ ላይ የሚኖረዉን ሕጋዊ ዉጤት የሚመለከት ነዉ። ፍርደን በሚያስፈጽመዉ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ተጠሪ የፍርድ ባለመብት፣ 2ኛ ተጠሪ ደግሞ የፍርድ ባለእዲ በመሆን የተከራከሩ ሲሆን የአሁን አመልካች ደግሞ በፍርድ አፈጻጸም ምክንያት በተደረገ የአክሲዮን ሐራጅ ሽያጭ አክሲዮኑን የገዙ ናቸዉ። ከክርክሩ እንደተረዲነዉ 1ኛ ተጠሪ በ2ኛ ተጠሪ ላይ ያስፈረደትን ገንዘብ ለማስከፈል 2ኛ ተጠሪ በሲነመር ትሬዱንግ አክሲዮን ማኅበር ያላቸዉን አክሲዮን ተሽጦ የፍርድ እዲዉ እንዱከፈል የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሰጠዉ ትእዛዝ መነሻ የፋዳራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዲይሬክቶሬት በቀን 12/03/2010 ዓ/ም በታተመ አዱስ ዘመን ጋዜጣ እንዱወጣ ባደረገዉ የሐራጅ ማስታወቂያ አመልካች በጨረታዉ ተሳትፈዉ ባቀረቡት ከፍተኛ ዋጋ በብር 490,000.00 የጨረታዉ አሸናፉ መሆናቸዉ ተረጋግጧል። በዚህም መሰረት አክሲዮኑ በስማቸዉ እንዱዞር(ለመረከብ) በሚጠይቁበት ጊዜ አክሲዮን ማኅበሩ የፍርድ ባለእዲዉ(ባለአክሲዮኑ) ያልከፈለት የግንባታ መዋጮ ብር 532,272.72 እና የሥራ ማስኬጃና ቅጣት ብር 83,549.07 በድምሩ ብር 615,522.69 እዲ እንዲለባቸዉ በመግለጽ እዲዉ ካልተከፈለ አክሲዮኑን በስማቸዉ እንደማያዛዉር በመግለጽ ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል።
ይህንን ተከትል አመልካች አቤቱታቸዉን ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበዉ ፍርድ ቤቱ የፍርድ አፈጻጸም ዲይሬክቶሬት ማብራሪያ እንዱሰጥ አድርጎ በመ/ ላይ በቀን 02/07/2011ዓ/ም በሰጠዉ ትእዛዝ በዲይሬክቶሬቱ የተለመደ አሰራር አክሲዮን ሲሸጥ እዲ መኖሩ በማስታወቂያ ላይ ለተጫራቾች እንደማይገልጽ ጠቅሶ አሰራሩ ይሕ ከሆነ ተጫራች በራሱ ጥረት አድርጎ ሉመጣበት የሚችለዉን ጉዲት መቀነስ እንደሚኖርበት መረዲቱን ገልጾ አመልካች በፈቃዲቸዉ ሳያጣሩ የገዙትን አክሲዮን ሉረከቡ ይገባል በማለት የአመልካችን ጥያቄ እንዲልተቀበለ በመግለጽ መዝገቡን ዘግቷል።
አመልካች ከላይ ይዘቱ በተመለከተዉ ትእዛዝ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበዉ ፍርድ ቤቱ በመ/ ላይ ተጠሪዎች ቀርበዉ እንዱከራከሩ ጥሪ አድርጎላቸዉ ተጠሪዎች ባለመቅረባቸዉ የአመልካችን ይግባኝ ማመልከቻ መርምሮ በቀን 04/06/2012 ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፍርድ አፈጻጸም ዲይሬክቶሬት የአክሲዮን ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ ላይ አክሲዮኑ ያለበት እዲ ባለዉ አሰራር አይገለጽም ያለዉን መቀበለ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 423/2 ስር የተደነገገዉን የሚቃረን በመሆኑ ሉታረም የሚገባዉ ነዉ ካለ በኋላ ጸንቶ በሚገኘዉ ዉል የሚተላለፈዉ መብቱ ብቻ ሳይሆን ግዳታዉም ጭምር በመሆኑ ይግባኝ ባይ እዲዉ አይመለከተኝም በሚል ያቀረቡትን ጥያቄ የስር ፍርድ ቤት ዉድቅ ማድረጉ ከዉጤት አንጻር የሕግ መሰረት ያለዉ ነዉ በማለት በማፅናት ወስኗል። አመልካች ለዚህ ችልት በቀን 03/09/2011 ዓ/ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረቡትም በዚህ መሰረት በተሰጠው ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን የአቤቱታቸው ይዘት በአጭሩ የሚከተለዉ ነዉ።
የከፍተኛው ፍርድ ቤት በሰጠው ትዕዛዝ የፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 423/2 ድንጋጌን አለመከተለ አግባብ አይደለም በማለት ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ነቅፍ ሳለ ተመልሶ መብትና ግዳታ አይነጣጠለም በማለት የሰጠው ውሳኔ እርስ በእርሱ የሚጋጭ ነዉ። ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በመጨረሻ የሰጠው የፍርድ ሀተታ ሲታይ በሽያጭ ውል መብትና ግዳታ እኩል መታየት አለባቸው በሚለው አቅጣጫ ቢታይ እንኳ ሻጩ ፍርድ አፈፃፀም ዲይሬክቶሬት ባወጣው የሐራጅ ሽያጭ ላይ እዲ መኖሩን እስካልገለፀ ድረስ አመልካች በሚገዛው ንብረት ላይ እዲ መኖሩን ሳያውቅና ሳይገለፅለት ከገዛ እዲውንም አብሮ ተቀብሎል የሚያሰኝ የሕግ ድንጋጌም ሆነ የሕግ ግምት የለም።በሽያጭ ውል መብትና ግዳታ በተመለከተ በስር ፍርድ ቤትም ሆነ በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ክርክር አልተነሳም።እንዱሁም ይህ ጉዲይ የንብረት ሽያጭ ጉዲይ ቢሆንም አፈፃፀሙ የሚመራው በሐራጅ ሽያጭ ስርዓት መሰረት እንጂ እንደ ውል ጉዲይ ተቆጥሮ የመብትና ግዳታ ነጥብ የሚነሳበት አይደለም።ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በውጤት ደረጃ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ፀንቷል ካለ በፍርደ መግቢያ ላይ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 423/2 መሰረት ያላደረገ ነው በማለት የያዘዉን ድምዲሜ መልሶ እንደመሰረዝ ስለሚሆን የይግባኝ ሰሚዉ ፍርድ ቤት መሰረታዊ ውሳኔ የትኛው ነው የሚል ጥያቄ የሚያስነሳ ከመሆኑም በተጨማሪ በአንድ ጉዲይ ላይ ሁለት አይነት ፍርድ መሰጠቱ በራሱ በአንድ ጉዲይ ሁለት አይነት ፍርድ እንደመስጠት ሰለሚሆን በራሱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ።የሕግ ስህተት በመፈጸም ጉዲዩ እንዲይፈጸም ያደረገዉ የፍርድ አፈጻጸም ዲይሬክቶሬት በመሆኑ ይግባኙ እየተሰማ ባለበት ወቅት የፍርድ አፈፃፀም ዲይሬክቶሬቱ ጣልቃ እንዱገባ ያቀረብኩትን አቤቱታው ፍርድ ቤቱ አለመቀበለ መሰረታዊ የሕግ ስህተት በመሆኑ ይታረምልኝ በማለት አቤቱታቸዉን አቅርበዋል።
የሰበር አጣሪ ችልት አቤቱታዉን መርምሮ ከአክሲዮን ሽያጭ ጋር በተያያዘ የተሰጠውን ውሳኔ አግባብነት ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 423 አኳያ ለመመርመር ጉዲዩ ለሰበር ችልት ቀርቦ እንዱመረመር የሰጠዉን ትእዛዝ ተከትል ለተጠሪዎች መጥሪያ ደርሷቸዉ በአቤቱታዉ ላይ መልስ እንዱሰጡ ትእዛዝ ሰጥቷል።ሆኖም ተጠሪዎች በአድራሻቸዉ ሉገኙ እንዲልቻለ አመልካች በመሐላ ቃል በማረጋገጣቸዉ ተጠሪዎች አገራዊ ሽፊን ባለዉ አዱስ ዘመን ጋዜጣ ላይ በሚወጣ ማስታወቂያ ጥሪ እንዱደረግላቸዉ ታዞ በቀን 11/03/2013 ዓ/ም በታተመ አዱስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ መጥሪያ ጥሪ እንደተደረገላቸዉ የሚገልጽ ጋዜጣ በማስረጃነት የቀረበ ቢሆንም ተጠሪዎች ባለመቅረባቸው መልስ የማቅረብ መብታቸው ታልፎል።
ከዚህ በላይ የተመለከተዉ የአመልካች አቤቱታና መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ የተባለዉ ትእዛዝና ዉሳኔ ይዘት ሲሆን እኛም በሐራጅ ማስታወቂያዉ ላይ ያልተመለከተዉን አክሲዮን ማኅበሩ የጠየቀዉን እዲ ጭምር አመልካች ሲከፍለ ነዉ የአክሲዮኑ ስመ-ሀብት በስማቸዉ ዞሮ የሚመዘገበዉ ተብል በመወሰኑ የተፈፀመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን አግባብነት ካለዉ የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ መርምረናል።
እንደመረመርነውም አመልካች በፋዳራል ፍርድ ቤቶች ፍርድ አፈጻጸም ዲይሬክቶሬት አማካኝነት በወጣዉ የሐራጅ ሽያጭ በመሳተፍ በጨረታዉ አሸናፉ በመሆን የገዙት በ2ኛ ተጠሪ ስም ተመዝግቦ በሲነመር ትሬዱንግ አክሲዮን ማኅበር የሚገኝ አክሲዮን ነዉ። ዲይሬክቶሬቱ የአክሲዮን ሐራጅ ሽያጭ ለማከናወን ለሕዝብ ይፊ ባደረገዉ ማስታወቂያ ላይ ከአክሲዮኑ ጋር በተያያዘ ከባለአክሲዮኑ የሚፈለገዉን እዲ አለመግለጹ ተረጋግጧል።ዲይሬክቶሬቱ በዚህ አግባብ እዲ መኖር አለመኖሩን በማስታወቂያዉ ላይ ሳይገልጽ ማስታወቂያ ያወጣበትን ምክንያት እንዱያብራር በከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠይቆ በሰጠዉ አስተያየት አክሲዮን ለመሸጥ በሚወጣ ማስታወቂያ ላይ የእዲ መኖር አለመኖር መግለጽ የተለመደ አሰራር እንዲልሆነ ገልጿል።
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 423(2/ለ እና ሰ) ስር በፍርድ አፈጻጸም ምክንያት ንብረት ለመሸጥ ለሕዝብ ይፊ በሚደረግ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ ላይ ከሚሸጠው ንብረት ላይ የሚጠየቅ መብት ወይም ማንኛውንም ተጫራች ሉያውቀው የሚገባ ዝርዝር መገለጽ እንዲለበት ተደንግጓል።በሐራጅ ማስታወቂያዉ ላይ በዚህ መልኩ እንዱገለጽ ሕጉ የሚያስገድደዉ ተንቀሳቃሽ(ግዙፍነት ያለዉም ሆነ ግዙፍነት የላለዉ) ንብረትም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት ለመሸጥ በሚወጣዉ ማስታወቂያ ላይ ሁለ እንደሆነ የድንጋጌዉ ይዘት ያሳያል። ይህ እንዱሆን ያስፈለገበት ዓላማ ገዥ ስለንበረቱ ባህርያትና ንብረቱን ከገዛ በኋላ ስለሚመጣበት ኃላፉነት እንዱሁም የሚያስከትልበትን ወጪ አዉቆና አመዛዝኖ ለንብረቱ ተገቢ ነዉ ብል ያመነዉን ዋጋ በመወሰን መጫረት እንዱችል ነዉ። በፍርድ ባለእዲዉ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ አክሲዮን በሐራጅ ለመሸጥ ማስታወቂያዉ ያወጣዉ የፍርድ አፈጻጸም ዲይሬክቶሬት አክሲዮን ለመሸጥ በሚወጣ ማስታወቂያ ላይ ከአክሲዮኑ የሚፈለግ እዲ ስለመኖሩ የሚገለጽበት የተለመደ አሰራር የለም ሲል የገለጸዉ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 423(2/ለ እና ሰ) ላይ በአስገዲጅነት የተደነገገዉን ያላገናዘበ ነዉ ።የሥር የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዲይሬክቶሬቱ የገለጸለትን እንዲለ በመቀበል እዲ መኖር አለመኖሩን ገዥ በራሱ አስቀድሞ ማረጋገጥ የሚገባዉ እንጂ በሐራጅ ማስታወቂያ ላይ ሉገለጽ የሚገባ ነገር እንዲልሆነ በመጥቀስ መወሰኑ ተጠቃሹን የሥነ ሥርዓት ሕጉን ድንጋጌ መሰረት ያደረገ ባለመሆኑ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ከዚህ አኳያ በስር ፍርድ ቤት የተፈጸመዉ ስህተት ታርሞ መወሰኑ ተገቢ ነዉ።በዚህ መልኩ የሥነ ሥርዓት ሕጉን ተከትል የሐራጅ ማስታወቂያ ሲወጣ ሽያጭ የተፈጸመበት አክሲዮን ሥመ-ሀብት ሲተላለፍ ለአክሲዮን ማኅበሩ የሚከፈል ዕዲ ስለመኖሩ ተገቢው ዝርዝር አለመግለጹ የሐራጅ ሽያጩ ጉልህ የሆነ የአሻሻጥ ጉድለት እንዲለበት በግልጽ የሚያሳይ ነው።
በልላ በኩል የሐራጅ ማስታወቂያ ሲወጣ ሽያጭ የተፈጸመበት አክሲዮን ሥመ-ሀብት ሲተላለፍ ለአክሲዮን ማኅበሩ የሚከፈል ዕዲ ስለመኖሩ ተገቢው ዝርዝር አለመገለጹ የሐራጅ ሽያጩ ጉልህ የሆነ የአሻሻጥ ጉድለት እንዲለበት የሚያሳይ መሆኑ በተረጋገጠበት የአክሲዮኑ ስመ-ሀብት ወደ አመልካች ስም ዞሮ የሚመዘገበዉ ወይም አመልካች ባለአክሲዮን እንደሆኑ የሚገልጽ ማስረጃ የሚሰጣቸዉ በምን አግባብ ነዉ የሚለዉ ነጥብ የዚህን ችልት ምላሽ የሚሻ ነዉ። የሐራጅ ሽያጩ እንዱፈጸም ያዘዘዉ የሥር ፍርድ ቤት በፍርድ አፈጻጸም ዲይሬክቶሬት በኩል እንዱሸጥ ያደረገዉን አክሲዮን የፍርድ ባለዕዲው በአክሲዮኖ ላይ በነበራቸዉ መብትና ግዳታ ልክ ለአመልካች(ለገዥ) የማስተላለፍ ኃላፉነት ስላለበት የአመልካችን ሥመ-ሀብት ዝውውር ይፈጸምልኝ አቤቱታ ማስተናገድ አለበት።
በልላ በኩል በሐራጅ የተሸጠዉ ንብረት አክሲዮን ስለሆነ እንደሚታወቀዉ አክሲዮን ደግሞ ግዙፍነት የላለዉ ተንቀሳቃሽ ንብረት ነዉ። በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 435 ስር የሚንቀሳቀስ ንብረት እንዱሸጥ በሚወጣዉ ማስታወቂያ ላይ ጉድለት በመገኘቱ ወይም የሽያጩ ሥነ ሥርዓት በትክክል ባለመፈጸሙ ምክንያት ማናቸዉም የሚንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ እንደማይፈርስ፤ይልቁንም በሥርዓቱ መጓደል ምክንያት ጉዲት የደረሰበት ማናቸዉም ሰዉ ለጉዲቱ ኃላፉ በሆነዉ ሰዉ ላይ ክስ አቅርቦ ተገቢ ካሳዉን ሉጠይቅ እንደሚችል፤ለጉድለቱ ኃላፉ የሆነዉ ገዥዉ ራሱ የሆነ እንደሆነ ግን የገዛዉን እቃ እንዱመልስ ወይም ካሳ እንዱከፍል ሉወሰን እንደሚገባ ተደንግጓል።ይህ ድንጋጌ የሚያስገነዝበዉ የሚንቀሳቀስ ንብረት ለመሸጥ የተደረገ የሐራጅ ሽያጭ በገዥ ጉድለት ካልሆነ በስተቀር በልላ ጉድለት ሉፈርስ እንደማይችልና የሚሸጠዉ አክሲዮን በሆነ ጊዜ በሐራጅ ማስታወቂያዉ ላይ በተፈጠረ ጉድለት ምክንያት ወይም የሽያጩ ሥነ ሥርዓት በትክክል አለመፈጸሙን መሰረት በማድረግ ሐራጁ ሉፈርስ የሚችልበትን ልዩ ሁኔታ ድንጋጌዉ አለማመላከቱን ነዉ።
እንዱሁም ሽያጩን ከዉል ሕግ አንጻር የተመለከትን እንደሆነም የሐራጅ ማስታወቂያ ለሕዝብ ይፊ ተደርጎ አመልካች በሀራጅ ማስታወቂያዉ መነሻ በሐራጁ ተሳትፈዉ አሸናፉ የሚያደርጋቸዉን ዋጋ ሲያቀርቡ ዉል የማቅረብ ተግባር (Offer) እንዲደረጉ ስለሚቆጠርና የፍርድ አፈጻጸም ዲይሬክቶሬት አመልካች ያቀረቡትን ከፍተኛ ዋጋ በመቀበል የጨረታዉ አሸናፉ እንደሆኑ ሲገልጽ ዉል የመቀበል ተግባር (Acceptance) እንደፈጸመ ስለሚያሳይ የአክሲዮን ሽያጭ ዉል ተቋቁሟል።የአንድ ዉል ተዋዋይ ወገን እዉነቱን አዉቆ ቢሆን ኖሮ ዉለን ሉዋዋል እንደማይችል ማስረዲት ከቻለ እንዱህ አይነት ስህተት የዉል ማፍረሻ ላሆን የሚችል ዐይነተኛ ስህተት(fundamental mistake) ተደርጎ ሉወሰድ የሚችል በመሆኑ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1797 እና 1798 ስር እንደተደነገገዉ ዉለ እንዱፈርስ መጠየቅ ይችላል።ሆኖም አመልካች ከአክሲዮኑ ጋር በተያያዘ አክሲዮን ማኅበሩ የሚጠይቀዉ እዲ መጠን በሐራጅ ማስታወቂያ ላይ ተገልጾ ቢሆን ኖሮ በጨረታዉ በመሳተፍ አክሲዮኑን አልገዛም ነበር በማለት የሽያጭ ዉለ እንዱፈርስ ባለመጠየቃቸዉ የዉል ሕጉን መሰረት በማድረግ የሐራጅ ሽያጩ እንዱፈርስ ሉወሰን የሚችልበት አግባብ የለም።
በተጨማሪም ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ በሐራጅ ማስታወቂያዉ ላይ የተፈጠረ ጉድለት የሚመለከት በመሆኑ ይህንን እንደ ጉድለት የሚቆጥረዉ የፍትሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ በመሆኑ የዚህ ጉድለት ሕጋዊ ዉጤት ምን ላሆን ይገባል የሚለዉን ለመወሰን ተፈጻሚ ላደረግ የሚገባዉም ከዉል ሕግ ይልቅ ይኸዉ የሥነ ሥርዓት ሕግ ላሆን ይገባል። ከላይ እንደተገለጸዉ አመልካች የሐራጅ ሽያጩ እንዱፈርስ አለመጠየቃቸዉ እንደተጠበቀ ሆኖ ሐራጁ እንዱፈርስ ቢጠይቁ እንኳን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕጉ ቁጥር 435 ላይ የተደነገገዉ በጠባቡ መተርጎም ስላለበት በአክሲዮን ሽያጭ ማስታወቂያ ላይ መገለጽ የሚገባዉ ነገር ባለመገለጹ ምክንያት በተፈጠረ ጉድለት ምክንያት ሐራጁ ሉፈርስ አይችልም። ሕጉ በዚህ ድንጋጌ እንደ መፍትሓ ያስቀመጠዉ የሐራጅ ሽያጩን ማፍረስ ሳይሆን በተከሰተዉ ጉድለት ምክንያት ጉዲት የደረሰበት ማንኛዉም ሰዉ የሐራጅ ሽያጩ ሳይፈርስ ለጉዲቱ አላፉ በሆነዉ ሰዉ ላይ ክስ አቅርቦ ተገቢ ካሳ እንዱከፈለዉ ጠይቆ የሚካስበትን አግባብ ነዉ።ከዚህ ጋር በተያያዘ ይግባኝ እየተሰማ እያለ የፍርድ አፈጻጸም ዲይሬክቶሬት በክርክሩ ጣልቃ እንዱገባ አመልክቼ ይግባኝ ሰሚዉ ችልት አቤቱታዬን አለመቀበለ ስህተት ነዉ በማለት ያቀረቡትን አቤቱታ መርምረናል።አመልካች ይግባኝ ያቀረቡት በአፈጻጸም መዝገብ ላይ የስር ፍርድ ቤት ሰጥቶ የነበረዉን ትእዛዝ በመቃወም ነዉ።የፍርድ አፈጻጸም መዝገብ በዋናነት የሚከፈተዉ ፍርድ ለማስፈጸም በመሆኑ በዋናዉ ክርክር ጊዜ ያልነበረና ፍርደ የማይመለከተዉ ሰዉ በክርክሩ እንዱሳተፍ በማድረግ እየተሰማ ለደረሰዉ ጉዲት ኃላፉነት ያለበት ሰዉ ማነዉ ምን ያህል ካሳ መክፈል አለበት በሚለዉ ጭብጥ ላይ ክርክር ተሰምቶ ዉሳኔ የሚሰጥበት አይደለም።ለዚህም ነዉ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 435 ላይ ጉዲት የደረሰበት ሰዉ ካሳ መጠየቅ የሚችለዉ ኃላፉነት ባለበት ሰዉ ላይ ክስ በማቅረብ ነዉ ተብል የተደነገገዉ።ስለሆነም ይግባኝ ሰሚዉ ችልት አመልካች የፍርድ አፈጻጸም ዲይሬክቶሬት በፍርድ አፈጻጸም መዝገብ ላይ ጣልቃ እንዱገቡ በመጠየቅ ያቀረቡትን አቤቱታ አለመቀበለ የሥነ ሥርዓት ሕግ ድጋፍ ያለዉ ነዉ።
ሲጠቃለል አመልካች በሐራጅ ማስታወቂያዉ ጉድለት ምክንያት ከአክሲዮኑ ዋጋ በላይ ተጨማሪ እዲ እንዱከፍል ተጠይቀዉ እዲዉን በመክፈላቸዉ የሚደርስባቸዉን ኪሳራ (ጉዲት) አግባብ ባለዉ ሕግ መሰረት ኃላፉነት ባለበት ሰዉ ላይ ክስ በመመስረት እንዱተካላቸዉ ሉጠይቁ ከሚችለ በስተቀር እዲዉ አይመለከተኝም በሚል ያቀረቡት ክርክር ተቀባይነት ያለዉ አይደለም።በመሆኑም የአክሲዮኑ ሥመሀብት ወደ አመልካች ስም ዞሮ ሉመዘገብና አመልካች ባለአክሲዮን መሆናቸዉን የሚገልጽ ማስረጃ ከአክሲዮን ማኅበሩ እንዱሰጣቸዉ ፍርደን የሚያስፈጽመዉ ፍርድ ቤት ሉያዝ የሚችለዉ የፍርድ ባለዕዲው በአክሲዮኑ ላይ በነበራቸዉ መብትና ግዳታ ልክ በመሆኑ አመልካች እዲዉን መክፈል አለባቸዉ ተብል በስር ፍርድ ቤትና በይግባኝ ሰሚዉ ችልት በመወሰኑ የተፈጸመ ስህተት ባለመኖሩ ተከታዩን ወስነናል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 02/07/2011ዓ/ም የሰጠዉ ትዕዛዝ እና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ ላይ በቀን 04/06/2012 ዓ/ም የሰጠዉ ዉሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ጸንተዋል።
ግራ ቀኝ በዚህ ችልት ያወጡትን ወጪ የየራሳቸዉን እንዱችለ ተወስኗል።
ት እ ዛ ዝ
የዉሳኔዉ ግልባጭ ለሥር ፍርድ ቤት ይተላለፍ። ግራ ቀኙ ሲጠይቁም ግልባጩ ይሰጣቸዉ።
በመዝገቡ ላይ የተሰጠ እግድ ካለ ተነስቷል።ይጻፍ።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.