የደላላነት ስራ ለመስራት የሚያስችል የንግድ ፈቃድ ሳይኖር የደላላነት ስራ ሰርቻለሁ ብል ክፍያ ለማስከፈል የሚቀርብ ክስ የህግ ጥበቃ በላለው መብት ላይ ተመስርቶ የሚቀርብ ስለሆነ ውድቅ ላደረግ የሚገባ ስለመሆኑ የንግድ ህግ አንቀጽ 5/19፣ 56 እና ተከታዮቹ አቶ ዲዊት በላይ እና አቶ ፀጋዬ ሰኚ
No summary available.
የሰ/መ/ቁ/ 178414 ሚያዚያ 26 ቀን 2012 ዓ.ም ዳኞች፡- ሰለሞን አረዲ ብርሀኑ አመነዉ ተሾመ ሽፈራዉ ብርሀኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካቾች፡-
ለዚህ መዝገብ መቅረብ ምክንያት የሆነዉ አመልካቾች በግንቦት 30 ቀን 2011 ዓ.ም ፅፈዉ ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ሲሆን ለአቤቱታቸዉ ምክንያት የሆነዉ ደግሞ የፋ/ከ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ. 219536 በቀን 2/7/2011 ዓ.ም የስር የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት በፍ/ብ/መ/ቁ. 170021 በሰኔ 25 ቀን 2010 ዓ.ም በሰጠዉ ዉሳኔ ላይ አመልካቾች ያቀረቡትን የይግባኝ ቅሬታ ተቀብል ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 348(1) መሰረት በማጽናት የሰጠዉ ዉሳኔ ነዉ።
የጉዲዩ አመጣጥ ባጭሩ ሲታይ አመልካቾች (የስር ከሳሾች) በስር የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት ጥር 16 ቀን 2010 ዓ.ም በአጭር ሥ/ሥርዓት ባቀረቡት የተሻሻለ የክስ ማመልከቻ ከተጠሪ ጋር ያለንን ጉርብትናና መልካም ግንኙነት መሰረት በማድረግ መኪና እገዛላቸዋለሁ፣ መኪናዉን እስካስመጣ ድረስ ገንዘብ ስጡኝ ብሎቸዉ የተለያዩ ጥሬ ገንዘቦችን ባጠቃላይ ብር 215,000 (ሁለት መቶ አስራ አምስት ሺህ) ከሰጡት በኋላ ለመተማመኛ በሚል ለ1ኛና 2ኛ አመልካቾች የዚህን ያህል ብር ዋጋ ያላቸውን በተለያየ ጊዜ የሚመነዘሩ ሦስት ቼኮችን ሰጥቷቸዉ በኋላ ላይ ግን በቃለ ባለመገኘቱ ምክንያት ገንዘባቸዉን ለመዉሰድ ወደ ከፊዩ ባንክ በሚሄደበት ጊዜ የተጠሪ ሂሳቦች እንደተዘጉ ከማረጋገጫ ጋር እንደተሰጣቸዉ ገልፀዉ ተጠሪ በቼኮቹ ላይ የተመለከተዉን ዋናዉን ገንዘብ ከነወለደ እንዱከፍል እንዱሁም ወጪና ኪሳራ እንዱተካላቸዉ እንዱወሰንላቸዉ ዲኝነት ጠይቀዋል።
ተጠሪም በቀን 27/06/10 ዓ.ም ፅፍ ባቀረበዉ መልስ የተባለትን ቼኮች መስጠቱን አምኖ ነገር ግን የተሰጡበትን ምክንያት ክድ ተከራክሯል። በተለይም የተሰማራበት ንግድ የመጠጥና ግሮሰሪ ሥራ እንጂ መኪና ማስመጣት እንዲልሆነ፤ መኪና ለማስመጣትም ምንም ፈቃድ እንደላለዉና መኪና አስመጥቶም ሆነ ሸጦ እንደማያዉቅ ገልፆ 1ኛ አመልካች የቤት እመቤትና 2ኛ አመልካች ደግሞ የመንግስት ሰራተኛ ስለሆኑ ቼክ ለመቁረጥ የሚያበቃ የንግድ ግንኙነት እንደላላቸዉ፤ መኪና ለመገበያየት በፅሁፍ የተደረገ ዉል ስለሚያስፈልግ ከአመልካቾች ጋር በዚህ መልኩ ያደረገዉ ዉል እንደላለ ማስረጃም እንዲላቀረቡ ተከራክሯል። ቼኮቹ የሰጡት በተለያዩ ጊዜያት ስለሆኑ አመልካቾች ለመተማመኛ በአንድ ጊዜ ተሰጠን ካለት ጋር የሚጣረስ እንደሆነና ሙለ ገንዘቡን ባንዳ ወስድ ቢሆን ኖሮ ለመተማመኛም የሚሰጠዉም አንዳ ወዱያዉ መሆን ይኖርበት ነበር ብሎል። ከአመልካቾች ጋር የነበረዉም ግንኙነት የአራጣ ብድር እንደሆነ፣ አመልካቾችና ተጠሪ በሚኖሩበት በጉለላ ክ/ከ ቀጨኔ በሚባለዉ መኖሪያ ሥፍራ የአራጣ ብድር ግንኙነት የተለመደ ስለመሆኑ፣ ግንኙነቱም ህገ-ወጥ ስለሆነና ስለሚያስቀጣ በቃልም በፅሐፍም እንደማይደረግ፣ አራጣ አበዲሪዎች ላበደሩት ገንዘብ መመለሻ ዋስትና ቼክ፣ ሉብሬና ካርታ የመሳሰለትን እንደሚይዙ ገልጿል። በዚሁ መሰረት በመጀመሪያ ብር 65,000 (ስላሳ አምስት ሺህ ብር) በልላ ጊዜ ደግሞ ብር 20,000 (ሀያ ሺህ ብር) እና ብር 135,000 (እንድ መቶ ሰላሳ አምስት ሺህ ብር) ተበድሮ እንደ ነበር፣ ዋናዉን ገንዘብም እስከሚመልስ ድረስም በወር 10 በመቶ ሲከፍል እንደ ነበርና እንደተበደረዉ ገንዘብ መጠን እና ጊዜ ለዋስትና ወደፉት በመፃፍ ቼኮችን እንደ ሰጠ፣ በየወሩም አራጣ ሲከፍል እንደቆየና ባጠቃላይ ወለድ ብቻ ብር 65,000 (ስልሳ አምስት ሺህ ብር) ከፍል እንደ ነበር ገልጿል። ይህ ስምምነታቸዉም በዉል ህጉ ከተደነገገዉ የ12 በመቶ ወለድ በላይ ስለሆነና በወንጀል ህጉ አንቀጽ 712 የሚያስቀጣ ስለሆነ ሉፀና የሚችል የብድር ዉል እንዲልሆነ ተከራክሯል።
ጠቅሶ ቼክ ለመጻፈ መነሻ ከሆነዉ ዉል ጋር ተገናዝቦ ላታይ ስለሚገባ በመካከላቸዉ የተደረገዉ ዉል ደግሞ ሉፀና የሚችል ስላልሆነ ለዉለ ዋስትና የተሰጡት ቼኮችም አስገዲጅ ዉጤት ስለላላቸዉ በቼኮቹ የተመለከተዉን ገንዘብ ለመክፈል እንደማይገደድም ተከራክሯል።
በቃል ክርክር ወቅት አመልካቾች ከተጠሪ ጋር ምንም አይነት የዉል ግንኙነት እንደላላቸዉ፣ ቼኮቹን የያዙት በቅን ልቦና እንደሆነ፣ አመልካቾችና ተጠሪ አብሮ አደግ እንደሆኑ፣ መኪና አስመጣለሁ ስላለ ባላቸዉ ጉርብትና ገንዘቡን እንደ ሰጡትና ቼኮቹን ለመተማመኛ ብል እንደሰጣቸዉ፣ ከ10 በመቶ በላይ ለማስከፍልም እንዲልተስማሙ፣ ግንኙነታቸዉ በቅን ልቦና የተደረገ ስምምነት ስለሆነ በህግ ፉት ተቀባይነት እንዲለዉ፤ ተጠሪ ግን አለ ስላለት የአራጣ ዉልም ሆነ ከፍያለሁ ስላለት ክፍያ ምንም ያቀረቡት ማስረጃ የለም፤ የቼኮቹን ቀናት አራርቆ የፃፈዉ ራሱ ተጠሪ ነዉ፤ ቼኮቹን እንዲታስመቱብኝ ብል ራሱን መደበቅ ጀመረ በማለት ተከራክረዋል። ተጠሪም በበኩለ ቼኮቹ ሦስት የተለያየ የብድር ግንኙነት እንደ ነበር የሚያስረደ ናቸዉ በማለት አፅኖት ሰጥቶ ተከራክሯል።
የስር ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከሰማ በኋላ አመልካቾች እንዱፈፀምላቸዉ እየጠየቁት ስላለዉ ክፍያ ከመኪና ሽያጭ ዉል በመነጨ ግዳታ ቼኩን እንደተቀበለ ማስረዲት ቢኖርባቸዉም የቀረቡት የሰነድ ማስረጃ ቼክና የባንክ ማረጋገጫ ብቻ ስለሆነ እነዚህ ደግሞ ቼክ ስለመፃፈ መነሻ የሆነዉን ግንኙነት በተመለከተ ምንም ያስረደት ነገር አለመኖሩን እና ያቀረቡትም የምስክሮች ቃልም እርስ በርስ የሚጣረሱ፣ ወጥነት የላላቸዉ፣ ሉታመኑ የማይችለ፣ በቦታዉ ነበርን ብለም ቃላቸዉ የተለያየ ስለሆነ ፍፁም እዉነትነት የለላዉ፣ የስጋና ጋብቻ ዝምድና ስላላቸዉ በመደጋገፍ የሰጡት ቃል መሆኑን ያሳያል በማለት ሳይቀበል አልፎል። በልላ በኩል ተጠሪ የብድር ዉል ስለመኖሩና ብሩ ተከፍል እስከሚያልቅ ድረስ 10 በመቶ ለመክፈል ስለመስማማታቸዉ በባርማንነት በተጠሪ ግሮሴሪ ዉስጥ ተቀጥሮ የሚሰራዉን ሰራተኛ እና ራሱ ተከሳሹ ወይም ተጠሪ የሰጡት ምስክርነት ግንኙነቱ ስለጀመረበት ቀንና ስለ ከፈለት የገንዘብ መጠን በተመለከተ ልዩነት ባለዉ መልኩ ወይም በማይጣጣም መልኩ የመሰከሩ ቢሆንም ተጠሪ በወር ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) ለመክፈል ስምምነት ስለመፈጸማቸዉ የሰጡት የምስክርነት ቃል 1ኛ ምስክር 1ኛ አመልካች በተደጋጋሚ ተጠሪ ጋር ይመጡ ነበር በማለት ከሰጠዉ የምስክርነት ቃል ጋር ሲገናዘብ አመልካቾች ከተጠሪ ጋር የነበራቸዉ የብድር ግንኙነት በወር ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) ለመክፈል ስምምነት የተደረገበት እንደሆነ የሚያስገነዝብ እንደሆነና የተጠሪ የምስክርነት ቃል በመሒላ ስር ሆኖ እስከመሰከረ ድረስ የተናገረዉ እዉነት ነዉ ተብል ግምት የሚወሰድበትና ግምቱንም የሚያፈርስ ማስረጃ በአመልካቾች በኩል አለመቅረቡን፤ ተጠሪ በወር ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) ለመክፈል ግራ ቀኙ ባደረጉት ስምምነት ከተረጋገጠ አመልካቾች የሚጠይቁት ዓመታዊ ወለድ መጠን ሲሰላ 120 በመቶ ስለሚሆን ይህ ደግሞ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2479(1) ያስቀመጠዉን የ12 በመቶ ገደብ የሚጥስና
ላይ በወር የ10 በመቶ ወለድ መጠየቅ ከህግ ዉጪ ስለመሆኑ የሰጠዉን የህግ ትርጉም የሚቃረን እንደሆነና በወንጀል ህግ አንቀጽ 712 መሰረት የሚያስቀጣ በመሆኑ በግራ ቀኝ መካከል የተደረገ ዉል ህግን የተከተለ ስላልሆነ ይህን መሰረት በማድረግ የተሰጡትም ቼኮች ተጠሪን ሉያስገድደ ስለማይችለ ተጠሪ በክሱ ላይ የተመለከተዉን ገንዘብ ለአመልካቾች ሉከፍል አይገባም፤ ተጠሪ ለክርክሩ ያወጡትን የጠበቃ አበል ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) በአመልካቾች ይተካለት በማለት ዉሳኔ ሰጥቷል። የስር የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤትም በዉሳኔዉ ላይ የቀረበለትን የይግባኝ ቅሬታ ተቀብል ካከራከረ በኋላ በስር ፍ/ቤት በግራ ቀኝ መካከል ያለዉ ግንኙነት የአራጣ ብድር ዉል ነዉ በማለት የሰጠዉ ዉሳኔ የሚነቀፍ አይደለም በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ ቁ. 348(1) መሰረት አፅንቷል።
የአመልካቾች የሰበር አቤቱታም እነዚህን ዉሳኔዎች ለማሳረም የቀረበ ነዉ። በዚሁ መሰረት አመልካቾች የስር ፍ/ቤቱ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈፅሞበታል በማለት ያቀረቡት ምክንያቶችም ባጭሩ ከተጠሪ ጋር ባለን ጉርብትናና መቀራረብ ምክንያት እምነት በመጣል መኪና እገዛላችኋለሁ ስላለን ገንዘባችንን ከመስጠት ዉጪ ምንም የዉል ግንኙነት በመካከላችን እንደላለ፣ ለዚህም መተማመኛ ይሆን ዘንድ ከተጠሪ ቼክ እንደተሰጠንና ይህንም ተጠሪ ራሱ አምኖ እያለ የስር ፍ/ቤቱ ምንም ማስረጃ የላችሁም በማለት ማለፈና በመካከላችን ያለዉ የብድር ዉል እንደሆነ አድርጎ ዉሳኔ መስጠቱ ተገቢ አይደለም። ዉሳኔዉም በ
እና በን/ህ/ቁ. 827(ሀ) እና 854 መሰረት ቼክ እንደቀረበ የሚከፈልበት እንጂ ዉል መኖሩን የሚያሳይ ሰነድ አይደለም በማለት ከተሰጠዉ ዉሳኔ ጋር የሚቃረን ነዉ። ተጠሪ የ10 በመቶ ወለድ ለመክፈል ነዉ ቼኮቹን የፃፈዉ የሚለዉ እዉነት አይደለም፤
ከተባለዉም ገንዘብ በላይ ከፍያለሁ ስላለዉም ክፍያ ያቀረበዉ ማስረጃ የለም፤ ግንኙነቱ ህጋዊ ስላልሆነ ከቼኩ የሚመነጨዉ ግዳታ አስገዲጅነት የለዉም መባለ ስህተት ነዉ፤ ተጠሪ የብር 215,000 (ሁለት መቶ አስራ አምስት ሺህ ብር) ወለድ ብር 65,000 (ስልሳ አምስት ሺህ ብር) ከፍያለሁ ስላለዉም ያስረደት ነገር ሳይኖርና በችልትም ፉት የሰጡት የምስክርነት ቃል የተዛባ ሆኖ ሳለ ዉለ ህገ-ወጥና የማይፀና ነዉ ብል መወሰኑ ተገቢነት የለዉም በማለት ተከራክረዉ የስር ፍ/ቤቶች ዉሳኔዎች እንዱሻርላቸዉ ጠይቀዋል። የሰበር ማመልከቻዉና የተሰጠዉ ብይን ከፍ/ቤቱ መጥሪያ ጋር ለተጠሪ የፍ/ቤቱ መጥሪያ ከቀረበዉ የሰበር አቤቱታ ጋር ተልኮለት ችልት ላይ ከቀረበ በኋላ መልሱን እንዱያቀርብ በተለያዩ የቀጠሮ ቀናት ቢጠበቅም (ከማረሚያ ቤት መቅረቡን ከግምት ዉስጥ በማስገባት) በታዘዘዉ መሰረት መልሱን ስላላቀረበ ችልቱ የተጠሪን መልስ የማቅረብ መብት ህዲር 24 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለዉ ችልት ብይን ሰጥቶበት አልፍታል።
የጉዲዩ አመጣጥ፣ በስር ፍ/ቤቶች የተደረገዉ ክርክርና የተሰጡት ዉሳኔዎች እንዱሁም የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተመለከቱት ሲሆን የሰበር አጣሪ ችልትም በቀን 15/11/2011 በዋለዉ ችልት ‛የስር ፍ/ቤቶች አመልካቾች ቼክን መሰረት አድርጎ እንዱከፈላቸዉ የጠየቁትን ዲኝነት ያደረጉት ዉል ህጉን የሚጥስ የወንጀል ተግባር ነዉ በማለት የን/ህ/ቁ. 717/1/ እና /3/ ጠቅሶ የዘጋበትን ከን/ህ/ቁ. 827 እና 854 እንዱሁም የሰበር ችልት በመ/ቁ. 123984 ላይ ከሰጠዉ አስገዲጅ ዉሳኔ ጋር ለማጣራት ሰበር ያስቀርባል“ በማለት ግራ ቀኙ በፅሐፍ እንዱከራከሩበት ብይን ሰጥቷል። ይህ ችልትም የአመልካቾችን ክርክርና ጉዲዩ ያስቀርባል የተባለበትን ጭብጥ አግባብነት ካለዉ ህግ እና የሰበር ዉሳኔዎች አንፃር መርምሮታል።
ከመዝገቡ ዉስጥ እንደሚታየዉ በግራ ቀኙ መካከል ገንዘብ መቀባበል እንደነበረና ስለገንዘቡም መጠን፣ አብሮ አደጎችና መልካም ግንኙነት የነበራቸዉ ጎሮቤታሞች እንደሆኑ ግራ ቀኙ በግልፅ ቋንቋ ተናግሯል። ግራ ቀኙ የተካከደት ገንዘቡን ለመቀባበላቸዉ ምክንያት ስለሆነዉ ጉዲይ ነዉ። አመልካቾች ከጉርብትናዉና መልካም ግንኙነት የተነሳ መኪና እገዛላችዋለሁ (አስመጣላችዋለሁ) ስላለን ገንዘባችንን በእምነት ሰጠነዉ እንጂ ምንም የዉል ግንኙነት በመካከላችን የለም፤ ለመተማመኛ ብቻ በሚል ቼክ ተቀብለናል ሲለ ተጠሪ ደግሞ ገንዘቡን የተቀበልኳቸዉ በአራጣ ብድር ሆኖ በወር 10 በመቶ እንድከፍላቸዉ ስለተስማማን ነዉ በማለት ተከራክረዋል (እዚህ ላይ አንዲንዳ ብር 10 ሺህ፣ አንዲዳ ደግሞ 10 በመቶ ተብል ስለተፃፈ ትክከለኛዉ የቱ እንደሆነ ከስር ፍ/ቤት መዝገብ በትክክል መለየት አስቸግሯል፤ የብር 215 ሺህ 10 በመቶ ብር 10 ሺህ አለመሆኑን ግን ግንዛቤ ሉወሰድ ይገባል)። ከላይ እንደተገለጸዉ የስር የፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤት የግራ ቀኙ ግንኙነት በህግ ፉት የማይጸና የአራጣ ሰምምነት ስለሆነ ተጠሪ ከአመልካቾች የተቀበለዉን ገንዘብ መልሶ ሉከፍል አይገባም የሚል ዉሳኔ እንደሰጠ እና በዚህ ዉሳኔ ላይ ሉደርስ የቻለበትም ምክንያት በተጠሪ በኩል ለቀረቡት ምስክሮች ከፍ ያለ ዋጋ (high probative value) በመስጠት መሆኑን መዝገቡ ያሳያል። ስለዚህ የስር ፍ/ቤቶቹ የሰጡትን ዉሳኔ አግባብነት ለመመዘን እና ለቀረበዉ ክርክር እልባት ለመስጠት በመጀመሪያ በሀገራችን ህጎች ዉስጥ ያለዉን የአራጣ ብድር ትርጉም ማየት ያስፈልጋል።
በፍትሐ ብሓር ህጋችን ዉስጥ ስለ አራጣ ብድር የተሰጠ ትርጉም የለም። ስለዚህ አራጣን በተመለከተ ክርክር በሚነሳበት ጊዜ በወንጀል ህጋችን ዉስጥ በተሰጠዉ ድንጋጌና ትርጉም መመራት አማራጭ የላለዉ ጉዲይ ነዉ። በ1996ቱ የወንጀል ህጋችን የአራጣ ወንጅል ድርጊት በአንቀጽ 712 በሚከተለዉ መሰረት ተደንግጓል፡አንቀጽ 712 አራጣ 1/ ማንም ሰዉ የተበዲዩን ችግረኛነት፣ የበታችነቱን፣ ወይም የገንዘብ ችግሩን፣ ወይም መንፈሰ ደካማነቱን፣ ወይም ልምድ ወይም ችልታ የላለዉ መሆኑን መሰረት በማድረግ፡ሀ/ በህግ ከተፈቀደዉ ወለድ በላይ ገንዘብ ያበደረዉ እንደሆነ፤ ወይም ለ/ ካበደረዉ ገንዘብ ጋራ በግልፅ ተመጣጣኝነት የላለዉን ንብረት በምትኩ እንዱሰጠዉ ያደረገዉ ወይም ቃል ያስገባዉ እንደሆነ፤
በቀላል እሥራት፣ ወይም እንደነገሩ ሁኔታ ከአምስት ዓመት በማይበልጥ ፅኑ እሥራትና በመቀጮ ይቀጣል።
ስለዚህ በወንጀል ህጉ ድንጋጌ መሰረት አንድ የብድር ግንኙነት የአራጣ ብድር ነዉ ለማለት ከላይ በተጠቀሰዉ አንቀጽ ስር የተመለከቱት የህጉ ወሳኝ ፍሬ ነገሮች (basic elements) ተሟልቶ መገኘት አለበት። የፍሬ ነገሮቹ መኖር በማስረጃ ሲረጋገጥ ግን ይህ ጉዲይ የፍትሐ ብሓር ጉዲይ ስለሆነ በፍትሐ ብሓር ጉዲይ ጥቅም ላይ በሚዉለዉ ሚዛን በሚደፍ ማስረጃ የማስረዲት ሥርዓት (preponderance of evidence) መሰረት መረጋገጥ ይኖርበታል ።
ከላይ ይዘቱ በተጠቀሰዉ አንቀጽ 712 ንዐስ አንቀጽ 1 የመግቢያ ዐረፍተ ነገር (chappeue) ላይ በግልፅ እንደተመለከተዉ አንድ አበዲሪ የአራጣ ድርጊት በመፈጸም አበድሯል ለማለት በድንጋጌዉ ከተጠቀሱት አማራጭ ሁኔታዎች መካከል ቢያንስ አንደን ተጠቅሞ በንዐስ አንቀፅ (ሀ) ወይም (ለ) የተመለከተዉን ተግባር (ድርጊት) መፈፀሙ መረጋገጥ አለበት። በልላ አነጋገር በአንቀጹ መግቢያ ዐረፍተ ነገር የተገለጸዉ ሁኔታ ከላለ በንዐስ አንቀፅ (ሀ) ወይም (ለ) ወስጥ የተቀመጠዉን ድርጊት ፈፅሞ መገኘቱ ብቻዉን አንድን ሰዉ አራጣ አበዲሪ ሉያሰኘዉ አይችልም ማለት ነዉ። በመሆኑም የአራጣ ብድር አለ ብል የሚከራከር ወገን ድርጊቱ መኖሩን በተለይ ከላይ በተጠቀሰዉ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ 1 የመግቢያ ዐረፍተ ነገር ላይ የተገለጸዉ ሁኔታ የገጠመዉ መሆኑን የማስረዲት ሸክም አለበት።
ከዚህ አንፃር በዚህ መዝገብ የተያዘዉን ጉዲይ ስንመለከት ግራ ቀኙ የነበራቸዉን ጉርብትናና መልካም ግንኙነት ለጊዜዉ ወደ ጎን ትተን ከተሰማሩበት የስራ መስክ አንፃር እንኳን ብንመለከት አመልካቾች (ባልና ሚስት የሆኑና 1ኛ አመልካች የቤት እመቤት፣ 2ኛ አመልካች የመንግስት ሰራተኛ የሆኑ) የተጠሪን ‛ ችግረኛነት፣ የበታችነቱን፣ ወይም የገንዘብ ችግሩን፣ ወይም መንፈሰ ደካማነቱን፣ ወይም ልምድ ወይም ችልታ የላለዉ መሆኑን መሰረት“ አድርገዉ ገንዘብ ያበደሩ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ አልቀረበም። ተጠሪም አመልካቾች ገንዘቡን ያበደሩት ችግረኛነቱን፣ የበታችነቱን ወይም የገንዘብ ችግሩን መሰረት አድርገዉ መሆኑን በመግለጽ ያቀረበዉ ክርክር የለም። ከላይ እንደተመለከትነዉ የስር ፍ/ቤት በግራ ቀኙ መካከል ያለዉ የአራጣ ብድር ግንኙነት ነዉ ብል ለመደምደም የቻለዉ ተጠሪ ራሱ በወር ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) ትከፍለኛለህ ብለዉኝ ለመክፈል ስምምነት አድርገናል በማለት የሰጠዉን የምስክርነት ቃል እና በተጠሪ ግሮሴሪ ዉስጥ በባርማንነት ተቀጥሮ ይሰራ የነበረዉ የተጠሪ 1ኛ ምስክር በሰጠዉ የምስክርነት ቃል ዉስጥ አመልካች ‛አልፍ አልፍ እየመጡ እንደሚጠይቁ“ የሚለዉን መሰረት በማድረግ ነዉ። ነገር ግን የራሱ የተጠሪ ቃልም ሆነ የላላኛዉ ምስክር ቃል የወንጀል ህጉ አንቀጽ 712 ንዐስ አንቀጽ 1 የመግቢያ ዐረፍተ ነገር እንዱኖሩ የሚጠይቃቸዉ ፍሬ ነገሮች (ሁኔታዎች) በተጠሪ ዘንድ ስለመኖራቸዉና አመልካቾችም ከእነዚህ አንደን መሰረት አድርገዉ አራጣ ስለማበደራቸዉ አያመለክቱም። የአንድ ሰዉ ወይም አበዲሪ አልፍ አልፍ ወደ ተበዲሪዉ የስራ ቦታ መሄድ ህጉ ከሚደነግገዉ የአራጣ ግንኙነት ጋር በቀጥታ የሚያገናኘዉ ምንም ነገር የለም። እንዱሁም ‛አልፍ አልፍ እየመጡ እንደሚጠይቁ“ የሚለዉ አገላለጽ በራሱ ምን እንደሚጠይቁ በግለፅ አላመለከቱም። በተጨማሪም የተጠሪ 1ኛ ምስክር በግራ ቀኙ መካከል የብድር ወይም የአራጣ ብድር ግንኙነት ስለመኖሩ እንደሚያዉቅ የሰጠዉ የምስክርነት ቃል በመዝገቡ ዉስጥ ተፅፍ አይገኝም።
ይልቁንም ‛ግንኙነቱን በተመለከተ ያስረዶቸዉ እንደላለ“ በግልፅ ቃለን ሰጥቷል። ስለዚህ ከራሱ ከተጠሪ ቃል ዉጪ ከላይ የተጠቀሰዉ የወንጀል ህግ አንድን ድርጊት አራጣ ከሚያደርገዉ ሁኔታ አንፃር የአራጣ ብድር መኖሩን የሚያሳይ ምንም ማስረጃ በመዝገቡ ዉስጥ የለም። በማስረጃ ህግ መርህ አንፃር ደግሞ አንድ ተከራካሪ ስለራሱ የሚሰጠዉ የምስክርነት ቃል በላልች ማስረጃዎች ካልተደገፈ የተቀባይነቱ ደረጃ እጅጉን ደካማ እንደሚሆን የሚታወቅ ነዉ። የተጠሪ 1ኛ ምስክር በሰጠዉ የምስክርነት ዉስጥ የግራ ቀኙን ‛ግንኙነቱን በተመለከተ ያስረዶቸዉ እንደላለ“ ተናግሮ እያለና ላልችም ከተጠሪ ቃል ጋር በቀጥታ የሚጣረስ የምስክርነት ቃል ሰጥቶ ባለበት ሁኔታ (ራሱ የስር የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤቱ በግልፅ በፍርድ ሐተታ ክፍለ ዉስጥ እንዲመለከተዉ ማለት ነዉ) ተጠሪ በመሒላ ሥር ሆኖ ስለመሰከረ ብቻ እዉነት ነዉ ብል መዉሰድ በየትኛዉም መልኩ ከህጉ ዓላማ ጋርም ሆነ ከማስረጃ ምዘና መርህ ጋር የሚሄድ አይደለም።
በእርግጥ የፍ/ብ/ህጉ አንቀጽ 2479(1) ላይ የብድር ወለድን በተመለከተ ተዋዋይ ወገኖች በዓመት ከ12 በመቶ በላይ የወለድ መጠን መስማማት እንደማይችለ በግልፅ ይደነግጋል። ነገር ግን ይህ አንቀጽ ከዚህ ከተቀመጠዉ ገደብ በላይ በሆነ የወለድ መጠን ተስማምቶ መገኘት የብድር ስምምነቱን የአራጣ ብድር ያሰኘዋል የሚል ትርጉምም ሆነ ስምምነቱ ከዚህ የተነሳ ዉጤት የለዉም የሚል ድንጋጌ በፍፁም አልሰጠም። በተቃራኒዉ አንቀጽ 2479(3) ስር ተዋዋዮች (ባንኮችንና አበዲሪ ተቋማትን አይጨምርም) ‛በወለድ የሚከፈለዉ ገንዘብ በመቶ ከአስራ ሁለት በላይ በዓመት እንዱሆን በጽሐፍ የተደረገ ዉል ቢኖር እንኳ ተበዲሪዉ በመቶ ዘጠኝ ብቻ በዓመት ወለድ መክፈል አለበት“ በማለት በግልጽ ይደነግጋል። ስለሆነም ከስር ፍ/ቤቶች ዉሳኔ በተቃራኒ የፍ/ብ/ህጉ አንድ የብድር ዉል ከተደነገገዉ የወለድ መጠን በላይ ለመክፈል ስምምነት የተደረገበት ዉል ስላደረጉ ብቻ ዉለ የአራጣ ብድር ዉል ነዉ ወይም ፈራሽ ነዉ (ዉጤት አይኖረዉም) የሚል አቋም የለዉም። ይልቁንም የህጉ አቋም የብድር ዉለ ፀንቶ እንዱቀጥልና ተበዲሪዉ በአመት ዘጠኝ በመቶ ብቻ ወለድ እንዱከፍል በማድረግ ዉለ ፍፃሜ እንዱያገኝ ማድረግ ነዉ።
ከላይ እንደተመለከተዉ በአመልካቾች እና በተጠሪ መካከል የአራጣ ብድር ግንኙነት ስለመኖሩ በተጠሪ በኩል በማስረጃ አልተረጋገጠም። የተባለትም ቼኮቹም ቢሆኑ ለአመልካቾች የሚከፈል ገንዘብ የመጠየቅ መብትን ከማመልከታቸዉ በስተቀር በመካከላቸዉ የአራጣ የብድር ግንኙነት ውል ስለመኖር የሚያስረደ ሰነድች (documentary evidence) አይደለም። የሰበር አጣሪ ችልቱም እንዱጣራ በማለት በያዘዉ ጭብጥ ዉስጥ የጠቀሰዉ
ላይ የተመለከተዉ ትርጉምም የሚያረጋግጠዉ በን/ህ/ቁ. 827(ሀ) እና 854 ድንጋጌዎች መሰረት ቼክ የክፍያ ሰነድ ወይም ክፍያ የሚፈጸምበት ሰነድ እንጂ የብድር ዉልን ተክቶ ብድር መኖሩን ለማስረዲት አግባብነት ያለዉ ሰነድ ነዉ ለማለት የሚያስችል የህግ መሰረት አለመኖሩን ነዉ። ከዚሁ ጋር ተያይዞ አመልካቾች የተባለትን ቼኮች ለመተማመኛ ብቻ ብለን የተቀበል ነዉ ቢለም በፍ/ብ/ህጉ እና በንግድ ህጉ ዉስጥ ስለ ዋስትና ወይም መያዣ ዉል የተደነገጉትን መስፈርቶች (ፍርሞች) ባገናዘበ መልኩ የተደረገ ዉል በመካከላቸዉ ስለመኖሩ ያቀረቡት ማስረጃ የለም። በተጨማሪም ተጠሪ በስር ፍ/ቤት
፣24435 በመጥቀስ በመካከላቸዉ ያለዉ ግንኙነት ህገ-ወጥ ስለሆነ በቼኮቹ ላይ የተመለከተዉን የብር መጠን ለመክፈል እንደማይገደድ ተከራክሮ እንደነበር መዝገቡ ያመለክታል። ነገር ግን
የሚመለከተዉ በማስገደድ (እስራትን ጨምሮ) ስለተፈረመዉ የቼክ ሰነድ ስለሆነ ለዚህ ጉዲይ አግባብነት የለዉም።
ከዚህ የተነሳ የስር ፍ/ቤትም ይህን የሰበር ዉሳኔ መሰረት በማድረግ የሰጠዉ ትንታኔና የደረሰበት መደምደሚያ ተቀባይነት የለዉም።
ደግሞ በቼክ አዉጪና አምጪዉ መካከል ያለዉን የግል ግንኙነት ወይም ከቼኩ በስተጀርባ ያለዉን ስምምነት መሰረት በማድረግ የቼክ አዉጪዉ የሆነዉ ባለዕዲ በን/ህ/ቁ. 717 በሚፈቅደዉ መሰረት ሉያነሳቸዉ ስለሚችላቸዉ መቃወሚያዎች በተመለከተ የተሰጡ ዉሳኔዎች ናቸዉ። ነገር ግን ከላይ ከተገለፁት ምክንያቶች የተነሳ በግራ ቀኙ መካከል በን/ህ/ቁ. 717 ድንጋጌና የተጠቀሱት የሰበር ዉሳኔዎች የሚጠይቁት አይነት የግል ግንኙነት (የአራጣ ብድር ግንኙነት) ስለመኖሩ የሚያመለክት ምንም ማስረጃ ስለላለ እነዚህ ዉሳኔዎች ለዚህ ጉዲይ አግባብነት የላቸዉም።
ይልቁንም በአመልካቾችና በተጠሪ መካከል የነበረዉ ጉርብትና፣ አብሮ አደግነትና መልካም ግንኙነት በተወሰነ ደረጃ አንደ በልላዉ ላይ እምነት እንዱጥል እና ገንዘብ እንዱቀባበለም ምክንያት ሆኗል ብል መገመት አያዲግትም። በእርግጥ እንዱህ አይነቱ ግንኙነትና መተማመን ለማህብረሰባችን እንግዲ ነገር አይደለም። አብሮ አደጎችና መልካም ግንኙነት ያላቸዉ ጎረቤታሞች ከዚህም ለበለጠ ነገር ሉተማመኑ ይችላለ። በስር ፍ/ቤት ከቀረቡት ማስረጃዎች ማለትም ከግራ ቀኙ ከተማመኑት፣ በአመልካቾች በኩል ከቀረቡት የምስክሮች ቃል እና በቼኮቹ ከተረጋገጠዉ አንፃር ጎላ ብል በግልፅ የሚታየዉ እዉነት ተጠሪ ከአመልካቾች ላይ ብር 215,000 (ሁለት መቶ አስራ አምስት ሺህ ብር) ስለ መቀበለ ነዉ። ይህ ደግሞ የሚያሳየዉ አመልካቾች ባቀረቡት ክስ መሰረት ተጠሪ የተጠቀሰዉን ገንዘብ መኪና አስመጣላችዋለዉ ብል መቀበለን በተወሰነ መልኩ (prima facie) ስለማስረዲታቸዉ እና ተጠሪ ግን ይህን በአግባቡ እንዲልተስተባበለ ነዉ። ከዚህም የተነሳ ተጠሪ መቀበለን ያልካደዉን የገንዘብ መጠን ለአመልካቾች መልሶ ለመክፈል ይገደዲል ማለት ነዉ። ከመዝገቡ እንደተረዲነዉ ተጠሪ ከአመልካቾች ስለመቀበለ ከተረጋገጠዉ ብር 215,000 (ሁለት መቶ አስራ አምስት ሺህ ብር) ዉስጥ ብር 2,000 (ሁለት ሺህ ብር) በሆነ ቀን ከተጠሪ 1ኛ ምስክር እጅ 1ኛ አመልካች ተቀበብሎል (ለምን ምክንያት እንደሆነ ባይታወቅም) በማለት የመሰከረዉን ብንቀበል እንኳን ለአመልካቾች መከፈል ያለበት ብር 213,000 (ሁለት መቶ አስራ ሶስት ሺህ ብር) በተጠሪ እንጅ እንዲለ ነዉ። ከዚህ ዉጪ ተጠሪ ለአመልካቾች ገንዘብ ስለመክፈለ የሚያሰረዲ ምንም አሳማኝ የሆነ ማስረጃ አልቀረበም። ስለዚህ ተጠሪ ተቀብያለዉ ብል በራሱ ቃል ያመነዉን ይህን የገንዘብ መጠን ለአመልካቾች እንዲይመልስ የሚያስችለዉ ምንም ህጋዊ ምክንያት የለም።
በአጠቃላይ ከላይ ከተዘረዘሩት ምክንያቶች የተነሳ የስር ፍ/ቤቶች በግራ ቀኙ መካከል በህግ ፉት የማይፀና የአራጣ ብድር ግንኙነት ነዉ በማለት እና ተጠሪ ከአመልካቾች ላይ የተቀበለዉን ጥሬ ገንዘብ ለመክፈል አይገደድም በማለት የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈፀመባቸዉ ናቸዉ ብለናል። ስለሆነም የሚከተለዉን ዉሳኔ ሰጥተናል።
የፋ/ከ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ. 219536 በቀን 2/7/2011 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ዉሳኔ እና የስር የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት በፍ/ብ/መ/ቁ/ 170021 በሰኔ 25 ቀን 2010 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ዉሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 348(1) መሰረት ተሽረዋል።
ተጠሪ ከአመልካቾች እጅ የተቀበለዉን ቀሪ ገንዘብ ብር 213,000 (ሁለት መቶ አስራ ሶስት ሺህ ብር) ክስ ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ ከሚታሰብ 9% (ዘጠኝ ከመቶ) ወለድ ጋር ለአመልካቾች እንዱከፍል ተወስኗል።
ወጪና ክሳራ ግራና ቀኝ ራሳቸዉን ይቻለ።
የዚህ ዉሳኔ ግልባጭ ለስር ፍ/ቤቶች ይድረስ።
መዝገቡ ተዘግቷል።
No topics extracted.