በኢንሹራንስ ውል ፓሉሲ ላይ የተመለከተው አደጋ ደርሶ ከሚከፈለው ካሳ ወይም ጉዲቱን በማስጠገን ከሚወጣው ወጪ ላይ ኢንሹራንስ ገቢው በውለ በተወሰነው ልክ የራስ ኪሳራ/Own Damage (የአደጋ መነሻ ወይም Excess) ኢንሹራንስ ሰጪው ቀንሶ እንዱያስቀር የሚደረግ ስምምነት ህጋዊ ውጤት ሉሰጠው የሚገባ ስለመሆኑ የንግድ ህግ አንቀጽ 663/2፣ 654/1 እና 658፣ 678 አና የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1731/1
No summary available.
የሰ/መ/ ጥር 23 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ ተሾመ ሽፈራዉ ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግሥቱ ነጻነት ተገኝ አመልካች፡- አቶ ዳዊት በላይ ተጠሪ፡- አቶ ፀጋዬ ሰኚ መዝገቡ ተመርምሮ ከዚህ የሚከተለዉ የፍርድ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የደላላነት ሥራ ክፍያ የሚመለከት ነዉ።ተጠሪ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በአመልካች ላይ በመሰረቱት ክስ የንግድ ፈቃድ አዉጥቼ የደላላነት ሥራ እየሰራሁ አመልካች በአራዲ ክፍለ ከተማ ወረዲ 07 ክልል ዉስጥ ያላቸዉን የቤት ቁጥሩ 146 የሆነ ቤታቸዉን ተከራይ ፈልጌ እንዲከራይላቸዉ ጠይቀዉኛል።የፓኪስታን ኤምባሲ የአምባሳደሩ ፀኃፉ ለኤምባሲዉ ለቢሮና ለመኖሪያ የሚሆን የሚከራይ ቤት ሲፈልጉ እንደነበር ባለኝ መረጃ ለአምባሳደሩና ለቤተሰባቸዉ ቤቱን ለሶስት ጊዜ በማስገብኘት ቤቱን ኤምባሲዉ በቀን 22/03/2009ዓ/ም በወር በ8000 ድላር እንዱከራይ አድርጌያለሁ።በዚህ መሰረት ኤምባሲዉ ለአመልካች የስድስት ወር ኪራይ ከፍሎቸዋል።ኤምባሲዉ የሚጠበቅበትን ኮሚሽን 4800 ድላር የከፈለኝ ቢሆንም አመልካችን ወክለዉ ስምምነት ያደረጉት የአመልካች ወኪል ኮሚሽንና ቦነስ እንደሚከፍለኝ ቃል ገብተዉልኝ የነበረ ቢሆንም አመልካች ለመክፈል ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።በመሆኑም አመልካች ለፈጸምኩት የደላልነት ሥራ 4800.00 ድላር ወይም የዚህን ምንዛሬ ከቀን 22/03/2009ዓ/ም ጀምሮ ከሚታሰብ ሕጋዊ ወለድ ጋር እና ክሱ ካስከተለብኝ ወጪዎች ጋር እንዱከፍለኝ ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል።
አመልካች ለክሱ በሰጡት መልስ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ባነሱት መከራከሪያ ተጠሪ በንግድ ሕጉ አንቀጽ 58 መሰረት የሙያ ተግባራቸዉ አድርገዉ ጥቅም ለማግኘት በንግድ ማኅበርነት ስላልተቋቋሙ ክሱን የማቅረብ መብት የላቸዉም።አመልካች ከተጠሪ ጋር ያደረግሁት ስምምነት የለም እንጂ ከዛሬ ሶስት ዓመት በፉትም ሆነ የኪራይ ዉለ በተፈጸመበት ጊዜ ተጠሪ የድለላ የንግድ ሥራ ፈቃድ አዉጥተዉ ይሰሩ እንደነበር ለማስረዲት ያቀረቡት ማስረጃ የለም።በማስረጃነት ያቀረቡት የንግድ ፈቃድ የኪራይ ዉለ ከተደረገ በኋላ የወጣ በመሆኑ ሕጋዊ ደላላ ስላልሆኑ ክስ ለማቅረብ የሚያስችል መብት ስለላላቸዉ ክሱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 33/1 መሰረት ዉድቅ ላሆን ይገባል።ክስ የቀረበበት ክፍያ ከ2 ዓመት በኋላ የተጠየቀ በመሆኑ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2024 መሰረት በይርጋ የታገደ ነዉ የሚለ መከራከሪያዎችን አቅርበዋል።እንዱሁም ፍሬ ነገሩን በሚመለከት በሚል ባቀረቡት መልስ - በንግድ ሕጉ መሰረት አበል የሚከፈለዉ የድለላ ሥራዉን እንዱሰራ የጠየቀዉ ወገን እንደሆነ ይደነግጋል።ተጠሪ ቤት እንዱያከራዩልኝ ባልጠየቅሁበት እና የድለላ ዉልም ባላደረግንበት ይህን ክስ ማቅረቡ ተገቢ አይደለም።አመልካች ቤቱን እንዱያከራዩልኝ የጠየቅኳቸዉ አቶ ወንድወሰን አንጋሳ እና አብርሃም ስንታየሁ የተባለ ሰዎችን ሲሆን ለእነዚህም ተገቢዉን የደላልነት ኮሚሽን ከፍያለሁ።በመሆኑም ተጠሪ ቤቱን እንዱያከራዩልኝና የደላልነት ክፍያ እንደሚከፍላቸዉ ያደረግነዉ ስምምነት ስለላለና የገንዘብ መጠኑም የሕግና የማስረጃ ድጋፍ የላለዉ ስለሆነ ክሱ ዉድቅ ይደረግልኝ በማለት ተከራክረዋል።
ፍርድ ቤቱ በመ/ ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ አስቀድሞ በቀን 19/06/2011ዓ/ም በሰጠዉ ብይን አንድ ሰዉ የድለላ ሥራ በንግድ ሕጉ አንቀጽ 56 እና ተከታዮቹ መሰረት ሰርቷል የሚያሰኝ ዝርዝር ተግባር እስከፈጸመ ድረስ ይህን ሥራ በግለሰብ ደረጃ ወይም በማኅበር በመሆን መስራት ሥለሚችልና የንግድ ፈቃድ አለመኖሩ ብቻዉን ክስ እንዲያቀርብ የሚያደርግ ስላልሆነ ከዚህ አንጻር የቀረበዉ መቃወሚያ ተቀባይነት የለዉም።እንዱሁም በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2024 የተደነገገዉ የ2 ዓመት የሕግ ግምት የደላልነት ክፍያን የሚያጠቃልል አይደለም በማለት ከዚህ አኳያ የቀረበዉን መከራከሪያ ዉድቅ በማድረግ ወስኗል።ፍሬ ነገሩን በተመለከተ የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃዎች መርምሮ በቀን 09/03/2012ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ ተጠሪ ለኤምባሲዉ ቤት በግላቸዉ ሲያፈላልጉ እንደነበር እና የአመልካችን ቤት ለኤምባሲዉ አሳይተዉ አምባሳደሩ ከእነ ቤተሰቡ እና የኤምባሲዉ ሰራተኞች ከአንድ ጊዜ በላይ እንዱጎበኙ በማድረግ ምርጫቸዉ መሆኑን ሲወስኑ አብረዉ እንደነበሩ፤የአመልካች ወኪል የሆኑት አቶ ጫኔ በላይን ከአምባሳደሩ ጋር ያገናኘዉ አመልካች እንጂ አመልካች የገለጻቸዉ ላልች ደላልች አለመሆናቸዉ በሚገባ ተረጋግጧል። ኤምባሲዉ በጻፈዉ ደብዲቤ አምባሳደሩን ወስደዉ የሚከራየዉን ቤት ያስጎበኙት ተጠሪ እንደሆኑ መገለጹ ተደምሮ ሲታይ በግራ ቀኙ መካከል የድለላ ስምምነት ማድረጋቸዉን ያሳያል።ተጠሪ ቀድሞ የቤቱን አድራሻ እና ይከራያል ስለመባለ የማያዉቁትን ቤት ለማስጎብኘት አምባሳደሩን ይዘዉ ይሄዲለ ተብል አይታሰብም። በመሆኑም ተጠሪ ከአመልካች ጋር ቤት ለማከራየት የድለላ ስምምነት እንደነበረዉ እና በዚያዉ መሰረት ቤቱን ለፓኪስታን ኤምባሲ ማከራየታቸዉ ተረጋግጧል።ስለሆነም ምስክሮች በመሰከሩት ልማድ መሰረት ለደላልነት ሥራዉ መከፈል ያለበት የአንድ ወር ኪራይ ግማሽ በመሆኑ አመልካች 4000.00 ድላር ወይም በቀን 22/03/2009 ዓ/ም በነበረዉ ምንዛሪ መሰረት ተለዉጦ እንዱሁም ክሱ ላስከተለዉ ወጪ ብር 24,830.00 ዉሳኔ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ከሚታሰብ 9% ሕጋዊ ወለድ ጋር አመልካች ለተጠሪ እንዱከፍለ ወስኗል።
አመልካች በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ፍርድ ቤቱ በመ/ ላይ በቀን 08/04/2013ዓ/ም በሰጠዉ ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞባቸዋል።
አመልካች በቀን 08/07/2013ዓ/ም የተጻፈ አቤቱታ ያቀረቡት ከላይ በተመለከተዉ መሰረት በተሰጠ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን የአቤቱታቸዉ ይዘት በአጭሩ፡- ተጠሪ የደላልነት ሥራ ሙያ ተግባራቸዉ አድርገዉ ለመሥራት የንግድ ፈቃድ ያወጡት ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ የቤት ኪራይ ዉል ከተደረገ በኋላ እንደሆነ በማስረጃነት ያቀረቡት የንግድ ፈቃድ ማስረጃ ያሳያል።በመሆኑም ተጠሪ የኪራይ ዉለ ሲደረግ በደላላነት ሥራ ላይ ያልነበሩና የንግድ ፈቃድ ስለላላቸዉ ክስ የማቅረብ መብት የላቸዉም ብል መወሰን ሲገባዉ አመልካች ያቀረብኩትን መቃወሚያ ዉድቅ በማድረግ የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ።አመልካችና ተጠሪ መካከል የድለላ ሥራ ዉል መኖሩንና ቤቱን እንዱያከራዩልኝ አመልካች የጠየቅኳቸዉ ስለመሆኑ ተጠሪ በአግባቡ በማስረጃ ሳያስረደና ማስረጃ በአግባቡ ሳይመዘን በአንጻሩ አመልካች ባቀረብኳቸዉ ምስክሮች ቤቱን እንዱያከራዩልኝ የጠየቅኳቸዉ ላልች ደላልችን እንደሆነና አገልግልቱን ለሰጡኝ ደላልች ክፍያ እንደከፈልኩኝ አስረድቼቻለሁ። ከኤምባሲዉ የመጣዉ ማስረጃም ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሆኖ ሳለ አለአግባብ የተሰጠ ዉሳኔ በመሆኑ ዉሳኔዉ የንግድ ሕጉን አንቀጽ 59ን ያላገናዘበ በመሆኑ ስህተት ነዉ።እንዱሁም 4000.00 ድላር አመልካች ለተጠሪ እንዱከፍል የተሰጠዉም ዉሳኔ የሕግና የማስረጃ ድጋፍ የለዉም በማለት አቤቱታቸዉን አቅርበዋል።
የሰበር አጣሪ ችልት አቤቱታዉን መርምሮ አመልካች ተጠሪ በደላላነት ቤቱን እንዱያከራዩላቸዉ ያቀረብኩት ጥያቄ የለም በሚል ያቀረቡት ክርክር ታልፍ በኤምባሲዉ በቀረበዉ ማስረጃ መነሻ ዉሳኔ የተሰጠበትን አግባብነት ከንግድ ሕጉ አንቀጽ 59 እና ከመሰረታዊ የማስረጃ ምዘና መርህ አኳያ ተጠሪ ባለበት እንዱመረመር ትእዛዝ በመሰጠቱ ተጠሪ በቀን 22/10/2013ዓ/ም የተጻፈ መልስ አቅርበዋል።የመልሳቸዉም ይዘት በአጭሩ፡- የተያዘዉ ጭብጥ የፍሬ ነገር ክርክርና የማስረጃ ምዘና ጉዲይ የሚመለከት በመሆኑ በተያዘዉ ጭብጥ ላይ ሰበር ሰሚ ችልት ዉሳኔ ለመስጠት የሚያስችል ሥልጣን የለዉም።የስር ፍርድ ቤት የቀረቡትን ማስረጃዎች መርምሮና መዝኖ ተጠሪ ከአንዳም አራት ጊዜ የቤቱን ቁልፍ በመዉሰድ የኤንባሲዉን ፀሃፉ ፣አምባሳደሩን፣ፀሃፉዉንና ሹፋራቸዉን እንዱሁም አምባሳደሩንና ቤተሰባቸዉን እንዱሁም ሰራተኞቻቸዉን በመዉሰድ ማሳየቴንና በዚህም መነሻነት ቤቱ ለኤንባሲዉ መከራየቱን በምስክሮች እና ከኤምባሲዉ በመጣዉ ማስረጃ አስረድቼ በአግባቡ ተጣርቶ የተወሰነ ነዉ።እንዱሁም ቤቱ ለረጅም ጊዜ አልተከራየልኝምና አከራይልኝ ኮሚሽን እከፍላለሁ በማለት በወኪላቸዉ አማካኝነት ጠይቀዉኝ በቃል ባደረግነዉ ስምምነት መሰረት በንግድ ሕጉ አንቀጽ 59/2 መሰረት በደላልነት ቤቱን እንዲከራየሁ ባቀረብኩት ምስክሮች አስረድቼ የተሰጠ ዉሳኔ በመሆኑ የተፈጸመ ስህተት የለም። 4000 ድላር እንዱከፈላቸዉ መወሰኑ ተገቢ አይደለም ሲለ ያቀረቡት ክርክር በምስክሮች ቃል ተረጋግጦ የተወሰነ ከመሆኑም በተጨማሪ ፍሬ ነገርንና ማስረጃ ምዘናን የሚመለከት በመሆኑ በዚህ ችልት ላታይ የሚገባ አይደለም በማለት የሰበር አቤቱታዉ ዉድቅ እንዱሆን በመጠየቅ ተከራክረዋል።አመልካችም የመልስ መልስ በማቅረብ ተከራክረዋል።
ከዚህ በላይ አጠር ባለ መልኩ የተገለጸዉ የግራ ቀኙን ክርክርና በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ዉሳኔዎች ይዘት የሚመለከት ሲሆን እኛም የሰበር አጣሪ ችልት የያዘዉን ጭብጥ በማሻሻል ተጠሪ ለአመልካች የደላላነት ሥራ ሰራሁኝ ባለበት ጊዜ የደላላነት ሥራ ንግድ ፈቃድ ባይኖራቸዉም ክስ የቀረበበት ገንዘብ እንዱከፈላቸዉ የመጠየቅ መብት አላቸዉ በሚል የአመልካች መከራከሪያ በስር ፍርድ ቤት ዉድቅ ተደርጎ በመወሰኑ በዚህ ችልት ደረጃ ሉታረም የሚችል የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ መርምረናል።
እንደመረመርነዉም ተጠሪ በአመልካች ላይ ክስ የመሰረቱት በአመልካች ጠያቂነት ቤታቸዉን በደላልነት አከራይቸላቸዉ የአበል ክፍያ አልፈጸሙልኝም በማለት 4000 ድላር እንዱከፈላቸዉ ወይም ይህ ገንዘብ በኢትዮጵያ ብር ተመንዝሮ እንዱከፈላቸዉ ነዉ። አመልካች ባቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ የኪራይ ዉለ በተደረገበት ጊዜ የደላልነት ሥራ ለመሥራት የሚያስችል የንግድ ፈቃድ ተጠሪ እንደላላቸዉ በመግለጽ ተጠሪ ክስ የማቅረብ መብት የላቸዉም በማለት ተቃዉመዋል።የስር ፍርድ ቤት ተጠሪ ለአመልካች የደላላነት ሥራ ሰራሁኝ ባለበት ጊዜ የደላላነት ሥራ ንግድ ፈቃድ ባይኖራቸዉም ክስ የቀረበበት ገንዘብ እንዱከፈላቸዉ የመጠየቅ መብት አላቸዉ ሲል በዚህ ረገድ አመልካች ያቀረቡትን መከራከሪያ ዉድቅ በማድረግ መወሰኑን መዝገቡን አስቀርበን ተመልክተናል።በዚህ መልኩ የስር ፍርድ ቤት የአመልካችን መቃወሚያ ዉድቅ በማድረጉ የተፈጸመ ስህተት መኖር አለመኖሩን እንደመረመርነዉም አንድ ሰዉ በልላ ሰዉ ላይ ክስ በማቅረብ በዲኝነት አካል ማስወሰን የሚችለዉ ክሱ በቀረበበት ሰዉ የተጣሰበት/ የተነካበት በሕግ ወይም በዉል እዉቅና እና/ወይም ጥበቃ ያገኘ መብት ወይም ጥቅም ሉኖረዉ ይገባል።(የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 33(2 እና 3) ይመለከቷል።) ይሕንንም ከሳሽ በፍሬ ነገር ደረጃ በክስ አቤቱታዉ ላይ ማሳየት(ማረጋገጥ) ይጠበቅበታል።በዚህ መሰረት በፍሬ ነገር ደረጃ በክሱ ላይ የተገለጸዉን በተመለከተ ላላኛዉ ወገን ክስ በተመሰረተበት ነገር ላይ ከሳሹ በሕግ እና/ወይም በዉል እዉቅና እና ጥበቃ ያገኘ መብት ወይም ጥቅም የለዉም እንዱሁም የሚያስከስሰኝን ተግባር አልፈጸምኩም ወይም በክሱ የተገለጸዉ ድርጊት የሚያስከስስ አይደለም በሚል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በማቅረብ መቃወሚያ አቅርቦ እንዱቃወም ሳይጠብቅ ክሱ የቀረበለት ፍርድ ቤት በእራሱ ጊዜ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 33(2 እና 3) እና 231(1/ሀ) መሰረት የክስ አቤቱታዉን መርምሮ ተገቢዉን የመወሰን ኃላፉነት አለበት።እንዱሁም ተከሳሹ ይህንን መከራከሪያ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 244/2 መሰረት በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ሲያቀርብ ፍርድ ቤቱ ሥረ ነገሩን የሚመለከት ጭብጥ ከመመስረቱና በጭብጡ ላይ ማስረጃ ከመስማቱ እና ከመመርመሩ በፉት እንደነገሩ ሁኔታ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 245/1 መሰረት እንደ አስፈላጊነቱ ዉሳኔ ለመስጠት ተገቢ ነዉ ያለዉን ማስረጃ አስቀርቦና መርመሮ ዉሳኔ መስጠት ይኖርበታል።
በያዝነዉ ጉዲይ ተጠሪ በአመልካች ላይ በመሰረቱት የክስ አቤቱታ ላይ የደላልነት ሥራ የሰሩት ባላቸዉ የንግድ ፈቃድ እንደሆነ ከመግለጻቸዉም በተጨማሪ ይህንን ያስረዲልኛል ያለትን ማስረጃ በማያያዝ አቅርበዋል።አመልካች ደግሞ ይህ ለክርክሩ መነሻ የሆነ የደላላነት አበል የተጠየቀበት የኪራይ ዉል በተፈጸመበት ጊዜ የደላላነት ሥራ ለመስራት የሚያስችል የንግድ ፈቃድ ተጠሪ አልነበራቸዉም በማለት ተከራክረዋል።የስር ፍርድ ቤትም የአመልካችን መከራከሪያ ዉድቅ ያደረገዉ በወቅቱ ተጠሪ የደላላነት ሥራ ለመስራት የሚያስችል የንግድ ፈቃድ እንዲልነበራቸዉ አረጋግጦ የንግድ ፈቃድ ባይኖራቸዉም ክስ የማቅረብ መብት አላቸዉ በሚል ነዉ። እኛም የስር ፍርድ ቤትን መዝገብ አስቀርበን እንደተመለከትነዉ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉና ተጠሪ የደላላነት ሥራ ሰራሁኝ ያለት የአመልካች ቤት የተከራየበት ዉል በቀን 22/03/2009ዓ/ም እንደተደረገ እና ተጠሪ ያቀረቡት የንግድ ፈቃድ የተሰጠበት ቀን 10/05/2009ዓ/ም እንደሆነና የታደሰበት ቀን ደግሞ በቀን 10/05/2009ዓ/ም እንደሆነ ተገንዝበናል።
ስለሆነም ተጠሪ በክስ አቤቱታቸዉ ላይ የንግድ ፈቃድ እንዲላቸዉ የገለጹ ቢሆንም የአመልካችን ቤት አከራየሁኝ ባለበት ጊዜ ተጠሪ የደላልነት ሥራ ለመስራት የሚያስችል የንግድ ፈቃድ እንደላላቸዉ ተረጋግጧል። የደላላነት ሥራ በቀድሞዉ የንግድ ሕግ አንቀጽ 5/19፣ 56 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎችም ሆነ በአዱሱ የንግድ ሕግ አንቀጽ 5/34 መሰረት የሙያ ሥራ ተደርጎ ጥቅም ለማግኘት የሚሰራ የንግድ ሥራ ነዉ።ይህ ሥራም ሆነ ይህንን ሥራ የሚሰራዉ ሰዉ የሕግ ጥበቃ ሉያገኝ የሚችለዉ እንደማንኛዉም ሰዉ አግባብ ባለዉ ሕግ መሰረት በነጋዳነት ተመዝግቦና የንግድ ፈቃድ አዉጥቶ መሥራት ሲችል ነዉ።ከዚህ ጉዲይ ጋር በተያያዘ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ ላይ በቀን 25/01/2009ዓ/ም ዉሳኔ ሰጥቷል።
ስለሆነም ተጠሪ የደላላነት ሥራ ለመስራት የሚያስችል የንግድ ፈቃድ አዉጥተዉ የአመልካች ቤት በደላላነት ማከራየታቸዉን ባላረጋገጡበት የደላላነት ሥራ ስለሰራሁ የአበል ክፍያ አመልካች ሉከፍለኝ ይገባል በማለት ክስ ለማቅረብ የሚያስችል በሕግ ጥበቃ የተደረገ መብት የላቸዉም።በመሆኑም የስር ፍርድ ቤት በዚህ ረገድ የቀረበዉን የአመልካችን መከራከሪያ ዉድቅ በማድረግ የሰጠዉ ዉሳኔ የሕግ አተገባበርና የክርክር አመራር ጉድለት ያለበት ስለሆነ ሉታረም የሚገባዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ በማለት ተከታዩን ወስኗል።
1.የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 19/06/2011ዓ/ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 08/04/2013ዓ/ም የሰጠዉ ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ተሽረዋል።
2.ግራ ቀኝ በዚህ ችልት ደረጃ ያወጡትን ወጭ የየራሳቸዉን እንዱችለ ብለናል።
የዉሳኔዉ ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤት ይተላለፍ። ለግራ ቀኙም ግልባጩ ይሰጣቸዉ።
በመዝገቡ ላይ የተሰጠ የዕግድ ትእዛዝ ካለ ተነስቷል፤ይጻፍ።
የስር ፍርድ ቤት መዝገብ ይመለስ።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።