አንድ የንግድ ምልክት በባለቤትነት ያስመዘገበ ሰው ላስመዘገበበት የዓለም አቀፍ ምድብ የንግድ ምልክቱን በብቸኝነት የመጠቀም መብት (Exclusive Right) ያለው ስለመሆኑ፤ በንግድ ምልክትነት እና በንግድ ስምነት ተመዝግቦ ጥቅም ላይ እንደራስ ናሽናል ኃላ/የ/የግ/ማህበር እና እንደራስ የንብረት ያለ በልላ ሰው ባለቤትነት በንግድ ስምነት ሉመዘገብ አይገባም ወይም የተመዘገበው ሉሰረዝ ይገባል የሚል ክርክር ሲቀርብ ተቃውሞ የቀረበበት አንድ አይነት ስለመሆኑ ወይም የሚመሳሰልና ህዝብን የሚያሳስት እንዱሁም የአስመዘጋቢውን መብት የሚጎዲ ስለመሆን አለመሆኑ በማስረጃ ሉረጋገጥ የሚገባ እንጂ የህግ ማዕቀፍ የለም ተብል የሚታለፍ ስላለመሆኑ፤ ዓለም አቀፍ እቃዎች እና አገልግልቶች ምድብ ለመወሰን የወጣ ናይስ ስምምነት (Nice Agreement Concerning the International Classification of Goods and Services for the purposes of the Registration of Marks)፣ አዋጅ ቁጥር 813/2006፣ ከንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 980/2008፣ በንግድ ምልክት ምዝገባና ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 501/1998 እና የእነዚሁ አዋጆች ማስፈፀሚያ ደንቦች አስተዲደር ኃላ/የተ/የግ/ማህበር
No summary available.
የሰ/መ/ ሚያዚያ 26 ቀን 2013 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ ተሾመ ሽፈራዉ ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግሥቱ ነጻነት ተገኝ አመልካች፡- ብሓራዊ የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኩባንያ አክሲዮን ማኅበር ተጠሪ፡- አቶ ዲዊት ገ/ሀና መዝገቡ ተመርምሮ ከዚህ የሚከተለዉ የፍርድ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ በኢንሹራንስ ዉል ፖሉሲ ላይ ኢንሹራንስ ገቢ እንዱሸፍን የሚደረገዉ ክፍያ ወይም የራስ ኪሳራ ወይም በተለምድ የአደጋ መነሻ ዋጋ (Excess) በሚል የሚገለጸዉን አፈጻጸምና ሕጋዊ ዉጤት የሚመለከት ነዉ። ተጠሪ በደቡብ ክልል ሀድያ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአመልካች ላይ በመሰረቱት ክስ በግራ ቀኙ መካከል በውል ቁጥር MTC/1356/17H5 በተደረገ ስምምነት በአመልካች ስም በተመዘገበዉና የሰላዲ ቁጥር 03-90046 ኢት በሆነው ሲኖትራክ ተሽከራከሪ ላይ ለሚደርስ ጉዲት ብር 1,900,000.00(አንድ ሚሉዮን ዘጠኝ መቶ ሺህ ብር) ካሳ ለመክፈል ተስማምቷል።ተሽከርካሪዉ በቀን 29/09/2010 ዓ/ም በሆሳዕና ከተማ ባቴና ወንዝ ድልድይ ላይ ከሰላዲ ቁጥር 3-92155 ኢት ከሆነ ላላ ሲኖትራክ ተሽከርካሪ ጋር የተጋጨ ሲሆን በተጠሪ ተሽከርካሪ ላይ ለደረሰው ጉዲት ጥፊተኛዉ የሰላዲ ቁጥር 3-92155ኢት መሆኑ በላሞ ወረዲ ትራፉክ ፖሉስ ተረጋግጧል።አመልካችም ይህንን በማረጋገጥ በቁጥር CL/MTC/0552/18/H5 ላይ በቀን 22/03/2011 ዓ/ም ከተሽከርካሪው የገበያ ዋጋ ላይ የአደጋ መነሻ ብር 360,000.00(ሦስት መቶ ስልሳ ሺህ ብር) ተቀናሽ በማድረግ ብር 1,440,000.00(አንድ ሚሉዮን አራት መቶ አርባ ሺህ ብር) ለተጠሪ ክፍሎል። ሆኖም አመልካች በተጠሪ ተሽከርካሪ ላይ ለደረሰው አደጋ በኢንሹራንስ ዉለ መሰረት የመድን ሽፊን ብር 1,900,000.00 በውላችን መሰረት መክፈል ሲገባው የአደጋ መነሻ ዋጋ በሚል ብር 360,000.00 ከመቀነሱም በተጨማሪ መክፈል ከነበረበት ክፍያ ላይ ብር 100,000.00(አንድ መቶ ሺህ ብር) ያለምክንያት ተቀናሽ አድርጓል። ስለሆነም አመልካች ያላግባብ ተቀናሽ ያደረገውን 360,000.00 እና ብር 100,000.00 በድምሩ ብር 460,000.00(አራት መቶ ስልሳ ሺህ ብር) ከሕጋዊ ወለድ ጋር እንዱከፍለኝ ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል።
አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስ በግራ ቀኙ መካከል እ.ኤ.አ ማርች 18 ቀን 2019ዓ/ም በተደረገ ስምምነት ተጠሪ ከተከፈላቸዉ ካሳ በተጨማሪ ምንም ዓይነት የጉዲት ካሳ ላለመጠየቅ ስለተስማሙ ይሕም ስምምነት በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1731 መሰረት ለግራ ቀኙ ሕግ ሆኖ የሚያገለግልና ጸንቶ የሚገኝ በመሆኑ ክሱ ዉድቅ ይደረግልኝ። በተጠሪ ተሽከርካሪ ላይ ለደረሰው ጉዲት የንግድ ሕጉ አንቀፅ 678 በሚፈቅደው መሰረት ተጠሪ መካስ ያለባቸው ተሽከርካሪው አደጋው በደረሰበት ወቅት በሚኖረው የገበያ ዋጋ በመሆኑ ይህንኑ ለማረጋገጥ በኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ የተጎደ ንብረቶችን ለመገመት ፈቃድ በተሰጠዉ የንብረት ገለልተኛ ገማች ጉዲት የደረሰበትን ተሽከርካሪ በሚገመትበት ወቅት የተሽከርካሪዉ የገበያ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ(ተ.እ.ታ) ጨምሮ እስከ ብር 1,800,000.00(አንድ ሚሉዮን ስምንት መቶ ሺህ ብር) መሆኑ ተረጋግጧል። በዚሁ ስላት በውለ መሰረት የአደጋ መነሻ ብር 360,000.00 ተቀናሽ በማድረግ ብር 1,440,000,00(አንድ ሚሉዮን አራት መቶ አርባ ሺህ ብር) ካሳ ክፍያ ለተጠሪ ተፈፅሟል።ስለዚህ አመልካች ለተጠሪ ካሳ የከፈለዉ በሕጉ አግባብ በተሽከርካሪዉ ላይ ጉዲት በደረሰበት ጊዜ የነበረዉን የገበያ ዋጋ መሰረት በማድረግ በመሆኑ ተጠሪ ያቀረቡት የብር 100,000.00 ተጨማሪ ካሳ ጥያቄ የሕግ መሰረት የለዉም። በተጨማሪም በግራ ቀኝ መካከል በተደረገ የኢንሹራንስ ዉል ፖሉሲ ላይ የተጠሪ ጥፊት ባልሆነበት ሁኔታ የአደጋ መነሻ አይቀነስም የሚል ቅድመ ሁኔታ በማድረግ የተፈጸመ የውል ስምምነት ባለመኖሩ ከዚህ ጋር ተያይዞ ተጠሪ ጉዲቱ የደረሰዉ በልላ ተሽከርካሪ ጥፊት ነዉ በማለት ያቀረቡት ክርክር የሕግና የማስረጃ ድጋፍ የላለዉ ነዉ በማለት ተከራክሯል።
ፍርድ ቤቱም በመ/ ላይ የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃዎች መርምሮ በቀን 10/07/2012 ዓ/ም በሰጠው ውሳኔ አመልካች ተጠሪን ምንም አይነት ተጨማሪ የጉዲት ካሳ ጥያቄ ላለማቅረብ ተስማምቷል በማለት ቢከራከርም በዚህ መሰረት የተደረገ የዉል ስምምነት በማስረጃነት ለፍርድ ቤቱ ስላላቀረበ ከዚህ አንጻር አመልካች ያቀረበዉ ክርክር ተቀባይነት የለዉም ሲል ዉድቅ አድርጓል።
የተሽከርካሪዉ የገበያ ዋጋ በኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ የተጎደ ንብረቶችን ለመገመት ፈቃድ በተሰጠዉ ባለሙያ ኤልያስ ራጋሳ ተገምቶ ብር 1,800,000.00(አንድ ሚሉዮን ስምንት መቶ ሺህ ብር) መሆኑ ተረጋግጧል። አመልካች ከተጠሪ ጋር ባደረገው የመድን ዋስትና ውል(ፖሉሲ) ከጠቅላላ የመድን ሽፊን ገንዘብ አደጋ መነሻ ተቀንሶ እንደሚከፈል በመድን ዋስትና ውል ላይ በግልፅ አልተደነገገም። ስለዚህ አመልካች ከሕግ ወይም ከውል የመነጨ ግዳታ ሳይኖር ተሽከርካሪ አደጋው በደረሰበት ወቅት ከነበረው የገበያ ዋጋና በባለሙያ ተገምቶ ከቀረበው ገንዘብ ብር 360,000.00 ቆርጦ አመልካች ማስቀረቱ ተገቢ ሆኖ አልተገኘም።ስለሆነም አመልካች ተቀናሽ ያደረገውን ብር 360,000.00 (ሶስት መቶ ስልሳ ሺህ ብር) ለተጠሪ ሉከፍል አይገባም ሲል ወስኗል።በልላ በኩል ለንብረት የሚሰጥ የኢንሹራንስ ሽፊን አደጋው በደረሰበት ጊዜ ንብረቱ የነበረውን ዋጋ ለመካስና ንብረቱ በመጎዲቱ ምክንያት በባለንብረቱ ላይ የደረሰውን ኪሳራ በኢንሹራንስ ውለ ላይ ከተመለከተው ገንዘብ ሳይበልጥ መከፈል እንዲለበት በንግድ ሕግ ቁጥር 665(1 እና 2)፣678(1 እና 2) እና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ ላይ አስገዲጅ ትርጉም ተሰጥቶበታል።በመሆኑም ተጠሪ ብር 100,000.00 ተቀነሰብኝ ብለዉ ያቀረቡት ዲኝነት ጥያቄ ተቀባይነት የለዉም ሲል ወስኗል።
በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት አመልካች ለደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ቢያቀርብም ፍርድ ቤቱ በመ/ ላይ በቀን 28/12/2012 ዓ/ም በሰጠዉ ትእዛዝ ይግባኙን በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞበታል። አመልካች በቀን 07/03/2013 ዓ/ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረበዉ በተገለጸዉ መሰረት በተሰጡ ዉሳኔዎች መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን የአቤቱታዉ ይዘት በአጭሩ የሚከተለዉ ነዉ።
ለተጠሪ በተሽከርካሪዉ ላይ ጠቅላላ ዉድመት ስለደረሰበት ካሳ ከተከፈለ በኋላ ተጨማሪ ክፍያ አልጠይቅም ብለዉ የተስማሙበትን ስምምነት በመጥቀስ ክሱ ዉድቅ እንዱሆን አመልካች ያቀረበዉን መከራከሪያ የሥር ፍርድ ቤት በዝምታ ማለፈ ሉታረም የሚገባዉ ስህተት ነዉ።በግራ ቀኙ መካከል በተደረገዉ የመድን ዋስትና ሽፊን ዉል ሰንጠረዥ እና ፖሉሲዉ መሰረት በተሽከራካሪዉ ላይ ለሚደርስ ጠቅላላ ዉድመት ከሚከፈለዉ የካሳ ክፍያ ላይ በዉለ ላይ ኢንሹራንስ ገቢዉ የአደጋ መነሻ (Excess)10% የመተካት ኃላፉነት የተጠሪ ነዉ። ተጠሪ ለዚህ በሰጡት መልስ ያሰሙት ክርክር የዉለን የአደጋ መነሻ ተጠሪ ለመክፈል የምገደደዉ አደጋዉ በእኔ ጥፊት የደረሰ ከሆነ ነዉ የሚል እንጂ በዉለ ላይ የአደጋ መነሻ ለመክፈል አልተስማማሁም የሚል አይደለም።የተጠሪ ክርክር ይህ ሆኖ እያለ የሥር ፍርድ ቤት የአደጋ መነሻ መቀነስ እንዲለበት የተደረገዉ የዉል ስምምነት ግልጽ አይደለም በማለት የሰጠዉ ዉሳኔ ከጭብጥ ዉጭ ነዉ።እንዱሁም አመልካች ለተጠሪ ከከፈለዉ ካሳ ላይ ቀንሶ ያስቀረዉ ብር 360,000.00 በዉለ በግልጽ የተመለከተና በተጠሪም ያልተካደ ሆኖ እያለ የሥር ፍርድ ቤት የሕግ መሰረት የለዉም ሲል ዉድቅ ማድረጉ መሰረታዊ ስህተት ነዉ።በአመልካች የአደጋ መነሻ በዉለ የተመለከተዉ 10% እጥፍ ተደርጎ መቀነሱ ከዉል ዉጭ ነዉ የሚል ክርክር በተጠሪ ተነስቶ ስለነበር አመልካች እጥፍ ተደርጎ የተቀነሰዉ በተሽከርካሪዉ ላይ አደጋዉ የደረሰዉ በምሽት ሲሽከረከር ወይም አዱስ መንጃ ፈቃድ በያዘ ግለሰብ ሲሽከረከር ከሆነ የአደጋ መነሻዉ ሉቀነስ የሚገባዉ በእጥፍ ይሆናል የሚል የዋናዉ የዉል አካል የሆነ ተጨማሪ ዉል(Endorsement) አመልካች በማስረጃነት ማቅረብ ባለመቻለ እንደተጠሪ ክርክር በእጥፍ ብር 360,000.00 መቀነስ የለበትም ቢባል እንኳን የሥር ፍርድ ቤት መቀነስ ያለበት በዋናዉ ዉል መሰረት ከአጠቃላይ ካሳ ከብር 1,800,000.00 ላይ 10% ብር 180,000.00 ነዉ ብል ክስ ከቀረበበት ገንዘብ ላይ አመልካች ለተጠሪ ብር 180,000.00 ብር ብቻ እንዱመልስ መወሰን ሲገባዉ አመልካች ለተጠሪ ብር 360,000.00 ይክፈል ብል ዉሳኔ መስጠቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስለሆነ ሉሻሻል ይገባል በማለት በመጠየቅ ተከራክሯል።
ሰበር አጣሪ ችልት አቤቱታዉንና የሥር ፍርድ ቤትን ዉሳኔ በመመርመር ግራ ቀኙ በኢንሹራንስ ዉለ ሰንጠረዥ ላይ የአደጋ መነሻ በተመለከተና መቀነስ ያለበት ገንዘብ ምን ያህል እንደሆነ ስምምነት ስለማድረጋቸዉ ተመልክቶ እያለ የሥር ፍርድ ቤት ይህንን አልፍ የወሰነበትን አግባብነት ከኢንሹራንስ ዉለ አኳያ ተጠሪ ባለበት ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልት ቀርቦ እንዱመረመር ትእዛዝ በመስጠቱ ተጠሪ በቀን 24/05/2013 ዓ/ም የተጻፈ መልስ አቅርበዋል።የመልሳቸዉ ይዘት በአጭሩ፡- አመልካች መክፈል የሚገባዉ ካሳ በንግድ ሕጉ አንቀጽ 678 መሰረት እና በሰ/መ/ መሰረት የተሽከርካሪዉን የወቅቱን ዋጋ ነዉ።ሆኖም የተሽከርካሪዉ የወቅቱ ዋጋ ከብር 2,000,000 በላይ ሆኖ ሳለ የተጎዲዉን ተሽከርካሪ ግምት ብር 1,800,000.00 አድርጎ 10% ቀንሶ ብር 1,440,000.00 ብቻ መክፈለ ሕግን መሰረት ያደረገ አይደለም።አመልካች እጥፍ የአደጋ መነሻ የሚያስቀነስ ተጨማሪ ዉል አለ ብል ቢከራከርም ዉለን በማስረጃነት ባለማቅረቡ ከዚህ አንጻር በስር ፍርድ ቤት በተሰጠዉ ዉሳኔ የተፈጸመ ስህተት የለም።ከተጠሪ በኩል ምንም አይነት ጥፊት ከላለ የአደጋ መነሻ በምንም ሁኔታ ከተጠሪ የማይቆረጥ መሆኑን በግልጽ በዉለ ላይ ተጠቅሶ ተስማምተናል። ለደረሰዉ ጉዲት ተጠሪ ጥፊት እንደላለበት ተረጋግጧል።ስለዚህ ተጠሪ ለአደጋዉ መነሻ ሳልሆንና በእኔ ጥፊት የደረሰ ጉዲት ባልሆነበት በአመልካች የአደጋ መነሻ በሚል መቀነሱ ተገቢ ስላልሆነ የሥር ፍርድ ቤት አመልካች ቀንሶ ያስቀረዉን ብር 360,000.00 ለተጠሪ እንዱከፍል በመወሰኑ የተፈጸመ ስህተት የለም በማለት ተከራክሯል።አመልካችም በቀን 08/06/2013ዓ/ም የተጻፈ የመልስ መልስ በማቅረብ ተከራክሯል።
ከዚህ በላይ የተመዘገበዉ የግራ ቀኝ ክርክርና በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ዉሳኔዎች ይዘት ሲሆን እኛም የሰበር አጣሪ ችልት ከያዘዉ ማስቀረቢያ ነጥብ አንጻር በስር ፍርድ ቤት በተሰጠ ዉሳኔ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ መርምረናል።
እንደመረመርነዉም በግራ ቀኙ መካከል በተደረገ የኢንሹራንስ ዉል ፖሉሲ አመልካች በተጠሪ ስም በተመዘገበዉ የሰላዲ ቁጥር 03-90046 ኢት በሆነው ሲኖትራክ ተሽከራከሪ ላይ ለሚደርስበት ጉዲት ለተጠሪ እስከ ብር 1,900,000.00(አንድ ሚሉዮን ዘጠኝ መቶ ሺህ ብር) ካሳ ለመክፈል መስማማቱን ግራ ቀኙ ካለመካካዲቸዉም በተጨማሪ በስር ፍርድ ቤት በዉለ ማስረጃነት የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነዉ።
እንዱሁም ይህ ኢንሹራንስ የተገባለት ተሽከርካሪ በቀን 29/09/2010 ዓ/ም ከላላ የሰላዲ ቁጥር 3- 92155 ኢት ከሆነ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ጠቅላላ ጉዲት (total damage) የደረሰበት መሆኑም የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነዉ። ጉዲቱ በደረሰበት ጊዜ ኢንሹራንስ የተገባለት ተጠቃሹ ተሽከርካሪ የገበያ ዋጋ በብሓራዊ ባንክ ፈቃድ ባለዉ ገለልተኛ ባለሙያ ተጣርቶ ብር 1,800,000.00(አንድ ሚሉዮን ስምንት መቶ ሺህ ብር) እንደነበርም በማስረጃ ተረጋግጧል።ግራ ቀኙን ያከራከረዉ በኢንሹራንስ ዉል ፖሉሲ ላይ ተጠሪ (ኢንሹራንስ ገቢዉ) እንዱሸፍን የሚደረገዉ ክፍያ/የራስ ኪሳራ (Excess) ወይም በተለምድ የአደጋ መነሻ ዋጋ በሚል የሚታወቀዉን ለተጠሪ ከሚከፈለዉ ካሳ ላይ አመልካች ቀንሶ የማስቀረቱ ሕጋዊነትና በዚህ አግባብ ሉቀነስ የሚገባዉ ገንዘብ መጠን በተመለከተ ነዉ።
እንደሚታወቀዉ የኢንሹራንስ ዓይነተኛ ባህሪይ ኪሳራን በሂደቱ ተሳታፉ የሚሆኑ ሰዎች እንዱጋሩት ማድረግ (risk-distribution among a substantial number of members) ነዉ።ይህም የሚሆነዉ ኢንሹራንስ ሰጪዉ በኢንሹራንስ ዉለ ሽፊን የተሰጠዉ ነገር ላይ አደጋ በደረሰ ጊዜ በዉል ወይም በሕግ የተመለከተዉን ካሳ እንዱከፍል በማድረግ እና በዚህ መልኩ በካሳ መልክ የሚከፍለዉን ገንዘብ የሚያገኘዉ ኢንሹራንስ ከገቡ በርካታ ሰዎች ከሚሰበስበዉ አርቦን (premium) ሲሆን ኢንሹራንስ ገቢዎችም አደጋዉ ከመድረሱ በፉት ለኢንሹራንስ ሰጪዉ አርቦን እየከፈለ ኪሳራዉን እንዱጋሩት በማድረግ ነዉ። ይህም ተግባራዊ የሚሆነዉ በአንጻራዊነት ኢንሹራንስ ሰጪዎች ከፍተኛ የገንዘብ መጠን ያለዉን አርቦን ኢንሹራንስ ገቢዉን በማስከፈል ነዉ። በተጨማሪም ኢንሹራንስ በተገባለት ነገር ላይ ጉዲት ያደረሰዉ ሰዉ የደረሰዉን ጉዲት እንዱተካ በማድረግ ኪሳራዉ እንዱተላለፍ ይደረጋል።በዚህ መልኩ የተገለጸዉ ኪሳራ የመጋራት አሰራር በኢንሹራንስ ንግድ ሥራ ዘርፍ በሰፉዉ የሚታወቅ ነዉ።
ኢንሹራንስ ገቢዉ አርቦን በመክፈል ኪሳራ እንዱጋራ ከሚደረግበት አሰራር ባሻገር ኢንሹራንስ ገቢዉ ኪሳራ እንዱጋራ የሚደረግበት ላላዉ አሰራር ኢንሹራንስ ገቢዉ በዉለ ከኢንሹራንስ ሰጪዉ ጋር በሚያደርገዉ ስምምነት በሚወሰነዉ መጠን ልክ አደጋዉ ሲደርስ ኢንሹራንስ ሰጪዉ ከሚከፈለዉ ካሳ ላይ ጉዲቱን ለመካስ የሚያስችል ተጨማሪ ክፍያ ለመክፈል ወይም ካሳዉ ለኢንሹራንስ ገቢዉ የሚከፈል በሆነ ጊዜም ከሚከፈለዉ ካሳ ላይ ኢንሹራንስ ሰጪዉ በዉለ በተመለከተዉ መጠን ልክ ቀንሶ እንዱያስቀር በፈቃደኝነት በኢንሹራንስ ዉል ፖሉሲ ላይ የሚስማማበት ሲሆን ይህም በኢንሹራንስ ንግድ ሥራ ዘርፍ የራስ ኪሳራ(የአደጋ መነሻ) በእንግሉዝኛዉ Excess/Own Damage ተብል የሚታወቅ ነዉ። በዘርፈ ከተጻፈ ድርሳናት መገንዘብ እንደሚቻለዉ በእንዱህ አይነት ስምምነት በስተጀርባ ያለዉ የፖሉሲ ምክንያትና ዓላማ ኢንሹራንስ ገቢዎች የኢንሹራንስ ሽፊን የገቡለትን ነገር በግድየለሽነት በመጠቀም ጉዲት እንዲያደርሱበት ለማድረግ ወይም ተገቢዉን ጥበቃ እንዱያደርጉለት ለማስቻል ወይም በጥቅለ በተቻለ መጠን አደጋ ለመቀነስና ኢንሹራንስ ሽፊን የተሰጠዉ ነገር ለአደጋ እንዲይጋለጥ ለማድረግ የሚያስችል ኃላፉነት ኢንሹራንስ ገቢዎች እንዱወስደ በማድረግ ካሳ የሚጠየቅበት አደጋ በደረሰ ጊዜ በስምምነቱ መሰረት በማስፈጸም ኪሳራ የማጋራቱን መሰረታዊ ዓላማ ከግብ ማድረስ ነዉ።ይህም በአብዛኛዉ ተግባራዊ የሚሆነዉ በአንጻራዊነት አነስተኛ አርቦን በማስከፈል በምትኩ በዉለ የተመለከተዉ አደጋ በደረሰ ጊዜ መጠኑ አስቀድሞ የተወሰነ ገንዘብ ኢንሹራንስ ገቢዉ እንዱከፍል ወይም ከካሳዉ ላይ ኢንሹራንስ ሰጪዉ ቀንሶ ሉያስቀር የሚችልበትን የራስ ኪሳራ(የአደጋ መነሻ/Excess) ስምምነት በኢንሹራንስ ዉል ፖሉሲ ላይ በመዋዋል ነዉ።በዚህ መልኩ የሚደረገዉ ስምምነት በሁኔታ ላይ የተመሰረተ ወይም ሁኔታ የላለዉ ላሆን ይችላል።ሁኔታ ላይ የተመሰረተ የሚሆነዉ ኢንሹራንስ የተገባለት ባለሞተር ተሽከርካሪ ላይ ለሚደርስ አደጋ ቢሆንና ኢንሹራንስ ገቢዉ ልምድ ለላለዉ ወይም አዱስ መንጃ ፈቃድ ላወጣ አሽከርካሪ በመስጠት እንዱሽከረከር ቢያደርግ ወይም አደጋዉ የደረሰዉ ተሽከርካሪዉ በዉለ በምሽት ማሽከርከር አይቻለም ተብል ተለይቶ በተገለጸበት የምሽት ሰዓት በሚሽከረከርበት ጊዜ ሲሆን የሚለ ሁኔታዎችን በመጥቀስ አደጋዉ በደረሰ ጊዜ ከእነዚህ ሁኔታዎች አንደ ተከስቶ ሲገኝ የኢንሹራንስ ገቢዉን ስህተት መሰረት ተደርጎ (Fault based) የአደጋ መነሻ/Excess ተግባራዊ የሚደረግበት አሰራር ነዉ።
ከላይ የተመለከትነዉን በኢንሹራንስ ሥራ ዘርፍ በተግባር ዲብሮ የሚሰራበትን አሰራር(ልማድ) በንግድ ሕጉ ስለ ኢንሹራንስ በአንቀጽ 654 እና ተከታዮች ድንጋጌዎች ከተመለከተዉ አንጻር መርምረናል።በዚህ ሕግ አንቀጽ 654/1 እና 658 ስር እንደተመለከተዉ በኢንሹራንስ ዉል ፖሉሲ ላይ ከሚገለጹ ነገሮች መካከል ኢንሹራንስ ገቢዉ ስለሚከፈለዉ አሮቦን ፣ኢንሹራንስ የተገባለት ንብረትና አደጋ አይነት፣የሚከፈለዉ ካሳ መጠን፣እና ከኢንሹራንስ ገቢዉ ኃላፉነት ጋር በተያያዘ የሚደረገዉ ስምምነት ወዘተ ይገኙበታል።እንዱሁም በዚሁ ሕግ አንቀጽ 663/2 ስር እንደተደነገገዉ በኢንሹራንስ ሰጪዉና ገቢዉ መካከል በሚደረግ ተቃራኒ ስምምነት በኢንሹራንስ ገቢዉ ቸልተኝነት ለሚደርሰዉ አደጋ ኢንሹራንስ ሰጪዉ በሙለም ሆነ በከፉል የጉዲት ካሳ ሉከፍል የማይችልበትን አግባብ መስማማት ይቻላል። ከዚህ መገንዘብ የሚቻለዉ በኢንሹራንስ ሰጪዉና ኢንሹራንስ ገቢዉ መካከል በኢንሹራንስ ዉል ፖሉሲ ላይ በሚደረግ ስምምነት በዉለ የተመለከተዉ አደጋ በደረሰ ጊዜ መጠኑ አስቀድሞ የተወሰነ ገንዘብ ኢንሹራንስ ገቢዉ እንዱከፍል ወይም ከካሳዉ ላይ ኢንሹራንስ ሰጪዉ ቀንሶ ሉያስቀር የሚችለዉን የአደጋ መነሻ/Excess በሁኔታ ላይ በመመስረት ወይም ያለሁኔታ በኢንሹራንስ ዉል ፖሉሲ ላይ መዋዋል እንዱቻል ፈቃጅ ሕግ መኖሩን ነዉ።
በያዝነዉ ጉዲይ በግራ ቀኙ መካከል ከተደረገዉ የኢንሹራንስ ዉል ፖሉሲ ላይ በግልጽ እንደተመለከተዉ ኢንሹራንስ በተገባለት ተሽከርካሪ ላይ ለሚደርስ ጠቅላላ ጉዲት ከሚከፈለዉ ካሳ ወይም ጉዲቱን ለመጠገን ከሚወጣዉ ወጪ ላይ አመልካች 10% የራስ ኪሳራ(የአደጋ መነሻ) ወይም Excess/Own Damage ቀንሶ እንዱያስቀር ተጠሪ መስማማታቸዉን አረጋግጠናል።በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1731/1 ስር እንደተደነገገዉ በሕጉ አግባብ የተቋቋሙ ዉልች ባቋቋሟቸዉ ሰዎች ላይ እንደሕግ ተፈጻሚ ይሆናለ።
በተያዘዉም ጉዲይ ግራ ቀኝ ከላይ በተጠቀሰዉ መልኩ ያደረጉት ስምምነት በንግድ ሕጉ ስለ ኢንሹራንስ ሥራ በአንቀጽ 654 እና ተከታዮች ድንጋጌዎች ከተደነገጉት ጠቅላላና ልዩ ድንጋጌዎች ጋር የሚጣረስ ካለመሆኑም በተጨማሪ ሕጉ እንዱህ አይነት ስምምነት ማድረግን የሚፈቅድ እንጂ በግልጽ የሚከለክል ባለመሆኑ ግራ ቀኝ በዚህ አግባብ ያደረጉት ስምምነት ሉፈጸም የሚገባዉ ነዉ።በመሆኑም በንግድ ሕጉ አንቀጽ 678 ስር በተደነገገዉ መሰረት ኢንሹራንስ የተገባለትና ጉዲት የደረሰበት ተሽከርካሪ ጉዲት በደረሰበት ጊዜ የነበረዉ የገበያ ዋጋ በባለሙያ ተገምቶ የተረጋገጠዉ ብር 1,800,000.00 በመሆኑ በዉለ መሰረት የዚህ ገንዘብ 10% ብር 180,000(አንድ መቶ ሰማን ሺህ ብር) እንደ የራስ ኪሳራ (የአደጋ መነሻ/ Excess)ለተጠሪ ከሚከፈለዉ ካሳ ላይ አመልካች ቀንሶ የማስቀረት መብት አለዉ።
ሆኖም አመልካች ከተጨማሪ ዉል ጋር በተያያዘ ለስር ፍርድ ቤት ያቀረበዉ ክርክር በዝምታ እንደታለፈበት በመግለጽ የሰበር አቤቱታ ያቀረበ ቢሆንም ተሸከርካሪዉ በምሽት ሲሽከረከር ወይም አዱስ መንጃ ፈቃድ በያዘ ግለሰብ ሲሽከረከር በተሽከርካሪዉ ላይ አደጋ ከደረሰበት ለተጠሪ ከሚከፈለዉ ካሳ ላይ ተጨማሪ 10% የአደጋ መነሻ(Excess) አመልካች ቀንሶ ያስቀራል የሚል የዋናዉ የዉል አካል የሆነ ተጨማሪ ዉል (Endorsement) አመልካች ከተጠሪ ጋር መዋዋለን የሚያሳይ ማስረጃ ለስር ፍርድ ቤት አቅርቦ አለማስረዲቱን ራሱ ለዚህ ችልት ባቀረበዉ የሰበር አቤቱታ ላይ ያመነ በመሆኑ የሥር ፍርድ ቤት ከዚህ አኳያ አመልካች ያቀረበዉን ክርክር በማስረጃ አልተደገፈም በሚል የሚነቀፍ አይደለም።
በመሆኑም አመልካች ለተጠሪ ከሚከፈለዉ ካሳ ላይ በዉለ መሰረት ብር 180,000.00 ብቻ ቀንሶ ማስቀረት ሲገባዉ ብር 360,000.00 አለአግባብ ቀንሶ ማስቀረቱን ተገንዝበናል።ስለሆነም የሥር ፍርድ ቤቶች ጉዲዩን ከዚህ በላይ በተመለከተዉ መሰረት መርምረዉ መወሰን ሲገባቸዉ በዋናዉ ኢንሹራንስ ዉል ፖሉሲዉ ላይ በግልጽ የተመለከተዉን ወደ ጎን በመተዉ አመልካች በዉለ መሰረት ቀንሶ ያስቀረዉን ጭምር ለተጠሪ እንዱመልስ መወሰናቸዉ ለግራ ቀኙ እንደሕግ የሚያገለግለዉን የኢንሹራንስ ዉል ፖሉሲዉን ያላገናዘበ በመሆኑ ሉታረም የሚገባዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ።
በልላ በኩል አንድን ፍሬ ነገር ማስረጃ አቅርቦ የማስረዲት ሸክምን ከሚመለከተዉ መሰረታዊዉ መርህ (Basic Principle of Burden of Proof) መረዲት እንደሚቻለዉ አንድ አከራካሪ ፍሬ ነገር አለ ወይም የለም ብል የሚከራከር ተከራካሪ ወገን ፍሬ ነገሩ መኖሩን ወይም አለመኖሩን ተገቢዉንና ሕጉ በተለየ ሁኔታ የሚጠይቀዉ ማስረጃ ካለም በሕግ ተቀባይነት ያለዉ ነዉ የተባለዉን ማስረጃ በማቅረብ የማስረዲት ሸክም(ግዳታ) አለበት (የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2001 ይመለከቷል)። አመልካች ተጠሪ ብር 1,440,000.00 ሲከፈላቸዉ ተጨማሪ ካሳ አልጠይቅም በማለት ስለተስማሙ ተጨማሪ ካሳ እንዱከፈላቸዉ ያቀረቡት ክስ ዉድቅ ላሆን ይገባል በማለት ቢከራከሩም ይህንን ዉል ለስር ፍርድ ቤት በማስረጃነት በማቅረብ ክርክሩን አላስረዲም።በመሆኑም የስር ፍርድ ቤት አመልካች ከዚህ አኳያ ያቀረበዉን መከራከሪያ ዉለን በማስረጃነት አቅርቦ አላስረዲም በማለት ዉድቅ በማድረጉ የተፈጸመ ስህተት የለም።በዚህ ሁለ ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
የሀድያ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 10/07/2012 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 28/12/2012 ዓ/ም የሰጠዉ ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348(1) መሰረት ተሻሽለዋል።
አመልካች ለተጠሪ ብር 360,000.00(ሦስት መቶ ስልሳ ሺህ ብር) እንዱከፍል የተወሰነዉን በማሻሻል ብር 180,000.00(አንድ መቶ ሰማንያ ሺህ ብር) ብቻ ይክፈል ብለናል።ላላዉ የስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ ክፍል አልተነካም
በዚህ ችልት የወጣ ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
በዉሳኔዉ መሰረት እንዱያስፈጽም የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ።ግልባጩ ለግራ ቀኙም ይሰጣቸዉ።
በመዝገቡ ላይ የተሰጠ የዕግድ ትእዛዝ ካለ ተነስቷል ይጻፍ።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።