ለሶስተኛ ወገኖች የካሳ ክፍያ የፈፀመ የኢንሹራንስ ኩባንያ በደንበኛው ላይ የሚያቀርበውን ክስ ማቅረብ ያለበት ለሶስተኛ ወገን የካሳ ክፍያ ከፈፀመበት ቀን ጀምሮ ባለው ሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ እንጂ በሶስተኛ ወገኖች ላይ አደጋው ከደረሰበት ቀን ጀምሮ ስላለመሆኑ የንግድ ህግ አንቀጽ 674/1፣ አዋጅ ቄጥር 799/2005 አንቀጽ 6/2 እና የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1846
No summary available.
የሰ/መ/ ጥር 26 ቀን 2013 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ ተሾመ ሽፈራዉ ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግሥቱ ነጻነት ተገኝ አመልካች፡- እንደራስ ናሽናል ኃላ/የ/የግ/ማኅበር ተጠሪ፡- እንደራስ የንብረት አስተዲደር ኃላ/የተ/የግ/ማኅበር መዝገቡ ተመርምሮ ከዚህ የሚከተለዉ የፍርድ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የንግድ ምልክት እና የንግድ ስም ሸማቹን ወይም ተጠቃሚዉን ኅብረተሰብ አሳሳች ነዉ ልባል የሚችልበትን የሕግ አግባብ የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በመጀመሪያ በታየበት በፋደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል። አመልካች በተጠሪ ላይ በመሰረተው ክስ አመልካች እንደራስ ናሽናል ኃላ/የተ/የግ/ማኅበር በሚል የንግድ ስም በቀን 17/02/1998 ዓ/ም ተቋቁሞ ሪል እስቴትና ላልች ንብረቶችን በማስተዲደር፣የንግድ እንደራሴነት ሥራ፣የሪል እስቴት ልማት ሥራዎች፣የንብረት አቻ ግምት ሥራዎች እንደሚሰራ ገልጾ የሚሰጣቸዉ አገልግልቶች ከላልች አገልግልት ሰጪዎች ለመለየት እንደራስ ናሽናልስ እሴት ማኔጅመነት የሚል ቃል እና ምስል ያለበት የንግድ ምልክት በአለም አቀፍ ምድብ 36 እንዱመዘገብለት ለኢትዮጵያ አእምሮአዊ ንብረት ጽ/ቤት አመልክቶ ተጠሪ የንግድ ምልክቱ እንዲይመዘገብ ተቃዉሞ አቅርቦ የነበረ ቢሆንም የተጠሪን ተቃዉሞ ዉድቅ አድርጓል። ይህንን ተከትልም ጽ/ቤቱ የንግድ ምልክቱን በምዝገባ ቁጥር LTM/3042/2009 መዝግቦ የንግድ ምልክት የምስክር ወረቀት ለአመልካች ሰጥቶታል።በመሆኑም ተጠሪ ከአመልካች ጋር አንድ አይነት የሆነ አሳሳች የንግድ ስም እና የንግድ ምልክት የሚጠቀም በመሆኑ በንግድ ስም ስያሜነት እና በንግድ ምልክትነት መጠቀሙን እንዱያቆም እንዱወሰንለት፣ የጉዲት ካሳ ብር 400,000.00 እና የሞራል ካሳ እንዱከፈለዉ እንዱሁም ወጪና ኪሳራ እንዱተካለት ዲኝነት ጠይቋል።
ተጠሪ ለክሱ በሰጠው መልስ የአመልካችን የንግድ ምልክትም ሆነ የንግድ ስም ተጠሪ አልተጠቀመም።እንደራስ ከሚለዉ ቃል በስተቀር የግራ ቀኝ የንግድ ስም አይመሳሰልም።ተጠሪ የሚሰጣቸዉ አገልግልት አመልካች ከሚሰጣቸዉ አገልግልቶች የተለዩ ናቸዉ።የተጠሪ የንግድ ምልክት እንደራስ የንብረት አስተዲደር አገልግልት ኃላ/የተ/የግ ማኅበር በሚለዉ የንግድ ስም እና የጣት አሻራ ምስል በቅንጅት የተፈጠረ ነዉ።የኢትዮጵያ አእምሮዊ ንብረት ጽ/ቤት ተጠሪ የአመልካች የንግድ ምልክት እንዲይመዘገብ ያቀረበዉን ተቃዉሞ ዉድቅ አድርጎ የአመልካችን የንግድ ምልክት መመዝገቡ የግራ ቀኙ የንግድ ምልክቶች ተመሳሳይ ናቸዉ የሚል መደምደሚያ ላይ የሚያደርስ አይደለም።አመልካች የደረሰበትን ጉዲት ያላስረዲ በመሆኑ እንዱከፈለዉ የጠየቀዉ ካሳ ከደረሰበት ጉዲት ጋር ተመጣጣኝ ላሆን የሚገባ መሆኑን እንዱሁም የሮያሉቲ ክፍያ ለጉዲዩ አግባብነት የላለዉ ነዉ በማለት መልሱን በመስጠት ተከራክሯል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ ሥልጣን የዲኘዉ የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ የግራ ቀኙን ክርክር በመስማትና የሰነድ ማስረጃዎችን እንዱሁም የንግድ ምልክት ምዝገባና ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 501/1998 እና በንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 980/2008 ስር ስለንግድ ምልክት እና ስለንግድ ስም ጥበቃና አሰጣጥ የተደነገጉትን ድንጋጌዎች በመመርመርና በዋቢነት በመጥቀስ በቀን 26/06/2011 ዓ/ም በሰጠዉ ውሳኔ የንግድ ስምንና የንግድ ምልክት ግጭት በተፈጠረ ጊዜ ወይም ተመሳሳይ በሆኑ ጊዜ እንዳት እንደሚፈታ የሚገልጽ ሕግ ባይኖርም አመልካች የንግድ ስሙን ተጠሪ የተጠቀመ ስለመሆኑ በማስረጃ ያላረጋገጠ በመሆኑ፤ተጠሪ የሚጠቀመዉ የንግድ ምልክት ከአመልካች የንግድ ምልክት ጋር ተመሳሳይነት የላለዉ በመሆኑ፤ ተጠሪ የሚጠቀመዉ የንግድ ምልክት አማካይ የሆነ ተጠቃሚን ሉያሳስት የሚችል ባለመሆኑ፤ግራ ቀኝ ከሚሰጡት አገልግልት አንጻር ተጠሪ የሚጠቅመዉ የንግድ ምልክት ህብረተሰቡን የማያሳክር በመሆኑ፤አመልካች የንግድ ምልክቱን ያስመዘገበዉ ለንብረት ግምት አቻ ሥራዎች ስለሆነ በንግድ ምልክቱ ላይ ያለዉም የብቸኝነት መብት ከዚህ አገልግልት ጋር በተያያዘ በመሆኑ፤አመልካች እንደራስ የሚለዉን ቃል በብቸኝነት ሉጠቀም የሚችለዉ የንግድ ምልክቱን ካስመዘገበበት የንብረት ግምት አቻ ሥራዎች ጋር በተያያዘ ብቻ በመሆኑ እንዱሁም አንደራስ የሚለዉን ቃል ላልች ሰዎች ላልች አገልግልቶች መጠቀም እንዲይችለ ለመከልከል የሚያስችል መብት በሕግ ስላልተጠበቀለት ተጠሪ በአመልካች የንግድ ስምም ሆነ የንግድ ምልክት ላይ ጥሰት አልፈጸመም በማለት ክሱን ዉድቅ በማድረግ ፍርድ ሰጥቷል።
አመልካች ከላይ በተመለከተዉ መሰረት በተሰጠ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቦ ፍርድ ቤቱም በመ/ ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ በቀን 23/04/2012 ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ የስር ፍርድ ቤት የሰጠዉን ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል።አመልካች ከላይ በተገለጸዉ መሰረት በተሰጡ ውሳኔዎች መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በማለት በቀን 09/07/2012 ዓ/ም ጽፍ ያቀረበዉ የሰበር አቤቱታ ይዘት በአጭሩ የሚከተለው ነው።
አመልካች የንግድ ምልክቱን ሲያስመዘግብ ተጠሪ አመልካች እንዱመዘገብለት የጠየቀዉ የንግድ ምልክት ከራሱ የንግድ ምልክት ጋር ተመሳሳይ እንደሆነ በመግለጽ/በማመን/ ተቃዉሞዉን ለኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት አቅርቦ ጽ/ቤቱ አመልካች የንግድ ምልክቱን አስቀድሞ ሲጠቀምበት የቆየ በመሆኑ የቀደምትነት መብት እንዲለዉ በማረጋገጥ የተጠሪን መቃወሚያ ዉድቅ በማድረግ በመወሰኑ ተጠሪ እንደራስ የንብረት አስተዲደር በሚለዉ ስም እና ምልክት ለመጠቀም መብት የለዉም።ተጠሪ በቀዲሚነት መብት ቢኖረዉ ኖሮ አመልካች ላላ የንግድ ምልክት እንዱቀይር ይገደድ ነበር።ይህ የአእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት ዉሳኔ በሕግ አግባብ ሥልጣን ባለዉ ፍርድ ቤት በተሰጠ ዉሳኔ አልተሻረም።የሥር ፍርድ ቤቶች የንግድ ስምንና የንግድ ምልክት ግጭት በተፈጠረ ጊዜ ወይም ተመሳሳይ በሆኑ ጊዜ እንዳት እንደሚፈታ የሚገልጽ የሕግ ማእቀፍ የለም በሚል የደረሱበት ድምዲሜ በሰ.መ. ላይ የንግድ ምልክትና የንግድ ስም ህብረተሰቡን በሚያሳስት ደረጃ ተመሳሳይነት ሲኖራቸዉ ተያያዥነት ያላቸዉ የሕግ ማእቀፍች ተጣጥመዉ እንዱታዩ በማድረግ እንደቅድሚያ ምዝገባቸዉ አንደ ላላዉን ቀሪ እንዱያደርግ ተደርጎ ሉወሰን እንደሚገባ የተሰጠዉን አስገዲጅ ትርጉም የሚቃረን ነዉ።ለአመልካች የተመዘገበለት የንግድ ምልክት የአእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት የተጠሪን ተቃዉሞ ዉድቅ በማድረግ የመዘገበዉ ሆኖ እያለ የንግድ ምልክቱ ለአመልካች የተመዘገበዉ ምድብ 36 ላይ ለንብረት አቻ ግምት ብቻ ነዉ በማለት ተጠሪ መጠቀም ይችላል ብለዉ የሥር ፍርድ ቤቶች መወሰናቸዉ በአዋጅ ቁጥር 501/2006 አንቀጽ 13/1 እና በደንብ ቁጥር 273/2012 አንቀጽ 21፣26/1 እና 27/1 ላይ የንግድ ምልክት ምዝገባ የሚከናወንበትንና ተቃዉሞ ዉድቅ የሚደረግበትን ሂደትና ዉጤቱን ያላገናዘበ ነዉ።
እንዱሁም ለአመልካች የተመዘገበለት የንግድ ምልክት በአለም አቀፍ ምድብ 36 ስለመሆኑ የተረጋገጠ በመሆኑ በአዋጁ አንቀጽ 2/7 እና በናይስ ዱፕልማቲክ ኮንፈረንስ በወጣዉ ምድብ መሰረት ምድብ 36 ስር ያለት የንግድ ምልክቶች የንብረት አስተዲደር፣የንብረት አቻ ግምት እና ላልች አገልግልቶችን ያቀፈ እንደመሆኑ አእምሯዊ ጸ/ቤት የአመልካችን እና የተጠሪን የመመስረቻ ጽሁፍ፣ መተዲደሪያ ደንብ በመመልከት ከቀረበዉ ክርክር እና ከሚሰጡት አገልግልት አንጻር ተመልክቶ ምልክቱ ቢመዘገብ ተጠቃሚዉን ያሳስታል የሚል መደምደሚያ ላይ በመድረሱ ምክንያት ማን ነዉ ቀዲሚ የሚለዉን መለያ ነጥብ (ጭብጥ) በመያዝ አመልካች ቀዲሚ ነዉ በማለት ምልክቱ ለአመልካች መዝግቧል። በዚህ መሰረት ምልክቱ እንዱመዘገብ የአእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት የሰጠዉ ዉሳኔ ጸንቶ ባለበት የሥር ፍርድ ቤቶች በአእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት መልስ የተሰጠባቸዉን ጉዲዮች በይግባኝ መልክ ጉዲዩ ሳይቀርብላቸዉ በመጀመሪያ ደረጃ ዲኝነት ሥልጣን እንደገና በመመርመር መወሰናቸዉ ስህተት ነዉ።እንዱሁም በምድብ 36 የሚመዘገብ የንግድ ምልክት ሲታይ ግራ ቀኝ የምንሰጣቸዉን አገልግልቶች ያቀፈ በመሆኑ የሥር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ዉሳኔ በአዋጅ ቁጥር 501/2006 አንቀጽ 2/7 የተደነገገዉን እና በናይስ ዱፕልማቲክ ኮንፈረንስ የወጣዉን ምድብ ሕግ ያላገናዘበ ነዉ። በተጨማሪም የሥር የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በቀን 15/02/2011 ዓ/ም ትእዛዝ የሰጠዉ የግራ ቀኝ የንግድ ምልክት እንድናቀርብ እንጂ ግራ ቀኝ የንግድ ስም ያስመዘገብንበትን ማስረጃ እንድናቀርብ ባልታዘዝንበት ከትእዛዙ ዉጭ ተጠሪ ያቀረበዉን የንግድ ስም ያስመዘገበበትን ማስረጃ የሥር ፍርድ ቤት የማስረጃ አቀራረብ ስርዓት ባልተከተለ ሁኔታ ተቀብልና ይህንን ማስረጃ መሰረት አድርጎ መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስለሆነ ይታረምልኝ የሚል ነዉ።
የሰበር አጣሪ ችልት አቤቱታውን መርምሮ የተጠሪ የንግድ ምልክትና የንግድ ስም ከአመልካች የንግድ ምልክትና ስም ጋር የሚመሳሰልና ተገልጋይ ህብረተሰቡን የሚያሣስት መሆን አለመሆኑን ከአዋጅ ቁጥር 501/2006፣ ከአዋጅ ቁጥር 980/2008፣ከአዋጅ ቁጥር 813/2006 እና በሰ/መ/ ላይ ከተሰጠዉ ትርጉም ጋር በማገናዘብ የስር ፍርድ ቤቶችን ዉሳኔ ለማጣራት ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልት ቀርቦ እንዱታይ ትዕዛዝ በመስጠቱ ተጠሪ በቀን 13/02/2013 ዓ/ም የተፃፈ በአጭሩ የሚከተለውን መልስ አቅርቧል።
ለአመልካች የተሰጠዉ የንግድ ምልክት የተመዘገበዉና የሕግ ጥበቃ የተሰጠዉ በአለም አቀፍ ምደባ 36 ለንብረት አቻ ግምት ሥራዎች በመሆኑ አመልካች የንግድ ምልክቱን በመመስረቻ ጽሁፈ ለተዘረዘሩት ላልች የንግድ አላማዎች ሉጠቀምበት አይችልም፤ወይም በዚህ ረገድ የሕግ ጥበቃ አልተሰጠዉም።ተጠሪ የሚሰጠዉ አገልግልት የንብረት አስተዲደር አገልግልት ነዉ።ቀደም ሲል ለኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት የአመልካቹ የንግድ ምልክት እንዲይመዘገብ መቃወሚያ ያቀረበዉ ምልክቱን ለንብረት አስተዲደር አገልግልት ይጠቀምበታል በሚል ግምት ነበር።ነገር ግን የንግድ ምልክቱ የሚያገለግለዉ ለንብረት አቻ ግምት(Asset valuation Services) ሥራዎች መሆኑን ተጠሪ ስለተረዲ ያቀረበዉ መቃወሚያ ዉድቅ ሲሆን ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፍርድ ቤት በማቅረብ ማሻር አላስፈለገዉም።በመሆኑም የአእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት የሰጠዉ ዉሳኔ በይግባኝ አልተሻረም በሚል ያቀረበዉ መከራከሪያ ተቀባይነት ሉያገኝ አይገባም።አመልካች እንደራስ ናሽናል የንብረት አስተዲደር የሚል ስም በንግድ ምልክትነት ወይም በንግድ ስምነት ሳያስመዘግብ የንግድ ምልክቱን የምጠቀምበት እንደራስ ናሽናል የንብረት አስተዲደር ለሚለዉ አገልግልት ነዉ ማለቱ ሀሰት ነዉ።የንግድ ስሙ እንደራስ ናሽናል ኃላ.የተ.የግ.ማኅበር እንደሆነ የመመስረቻ ጽሁፈ ያሳያል።ተጠሪ ለአእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት ተቃዉሞዉን ያቀረበዉ ምልክቱን ለንብረት አቻ ግምት እየተጠቀምኩ ነዉ በሚል ሳይሆን አመልካቹ ምልክቱን ለንብረት አስተዲደር(Property Administration) ሉጠቀምበት ያለ መስልት ስለነበር ሲሆን ይህ አለመሆኑን ሲረዲ በተቃዉሞዉ አለገፊበትም።የአእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት የአስተዲደር ፍርድ ቤት በመሆኑ መደበኛ ፍርድ ቤቶች በአስተዲደር ዉሳኔ ስለማይገደደ እና ጽ/ቤቱ ሁለቱንም ምልክቶች ያሳስታል አያሳስትም የሚለዉን ሳያነጻጽር የወሰነዉ ዉሳኔ በመሆኑ አመልካች የስር ፍርድ ቤቶች የጽ/ቤቱን ዉሳኔ እንደገና አይተዋል በሚል ያቀረበዉ ቅሬታ ተቀባይነት ሉኖረዉ አይገባም።
በተጨማሪም ተጠሪ የሚጠቀምበት የንግድ ምልክትና ስም አመልካች ከሚጠቀምበት የንግድ ስምና ምልክት ጋር በቅርጽም ሆነ በይዘት ስለማይመሳሰል እና ግንኙነት የላላቸዉ እንደሆኑ በስር ፍርድ ቤቶች ተረጋግጦ የተወሰነ በመሆኑ አመልካች ተጠሪ የንግድ ምልክቴን ህብረተሰቡን በሚያሳስት መልኩ እየተጠቀመ ነዉ ያለዉ የሕግም ሆነ የፍሬ ነገር መሰረት የለዉም።አመልካቹ በተጠሪዉ የንግድ ስም የሚታየዉ የንግድ ምልክት ወይም ምስል ከእኔ የንግድ ምልክት ጋር አንድ አይነት ስለሆነ ሕዝብ ያሳስታል የሚል ክርክር አቅርቦ ስለነበር ይህንን ለማጣራት ፍርድ ቤቱ የአመልካች የንግድ ምልክት ምዝገባ የምስክር ወረቀትና የተጠሪ የንግድ ስም ምዝገባ ምስክር ወረቀት እንዱቀርብ የስር ፍርድ ቤት በራሱ አነሳሽነት ትእዛዝ ሰጥቶ እንዱያቀርብ የተደረገ በመሆኑና ፍርድ ቤቱ በማንኛዉም ጊዜ ማስረጃ እንዱቀርብ ትእዛዝ መስጠት የሚችል በመሆኑ ይህንን አመልካች እንደ ስህተት መቁጠሩ ተቀባይነት የለዉም ። ተጠሪ የንግድ ስም እንጂ የንግድ ምልክት የለዉም። እንዱሁም ተጠሪ በአመልካች የንግድ ምልክት ላይ የፈጸመዉ ጥሰትም ሆነ ያደረሰዉ ጉዲት ባለመኖሩ የስር ፍርድ ቤቶች በሰጡት ዉሳኔ የፈጸሙት ስህተት የለም በማለት መልስ በመስጠት ተከራክሯል። አመልካችም በቀን 16/03/2013 ዓ/ም የተጻፈ የመልስ መልስ በማቅረብ ተከራክሯል።
ከዚህ በላይ የተመዘገበዉ የግራ ቀኝ ክርክርና በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ዉሳኔዎች ይዘት ሲሆን እኛም የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩ ለሰበር ችልት ያስቀርባል ሲል ከያዘዉ ጭብጥ አንጻር በስር ፍርድ ቤቶች በተሰጡ ዉሳኔዎች የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ መርምረናል።
እንደመረመርነውም ‛እንደራስ ናሽናልስ እሴት ማኔጅመነት“ በእንግሉዝኛዉ ‛ENDERAS NATIONAL ASSET MANAGEMENT’’ የሚል ቃል እና ምስል ያለበት የንግድ ምልክት በኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት ተመዝግቦ የሚገኘዉ በአመልካች ባለቤትነት መሆኑ በስር ፍርድ ቤት ከግራ ቀኙ ክርክርና ማስረጃ የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነዉ።ለአመልካች ይህ የንግድ ምልክት በምዝገባ ቁጥር LTM/3042/2009 የተመዘገበላቸዉ በአለም አቀፍ ምድብ 36 ለንብረት አቻ ግመታ ሥራዎች እንደሆነም የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነዉ። እንዱሁም ተጠሪ ‛እንደራስ የንብረት አስተዲደር አገልግልት“ በእንግሉዝኛ ‛ENDERAS PROPERTY ADMINISTRATION SERVICE“ በሚል የሚታወቅ የንግድ ስም ያስመዘገበዉ በቀን 11/07/2004 ዓ/ም ሲሆን በንግድ ምልክትነት ግን እንዲላስመዘገበ ከሥር ፍርድ ቤት መዝገብ እና ከግራ ቀኝ ክርክር ተገንዝበናል። አመልካች ተጠሪ ላይ ክስ የመሰረተዉ የንግድ ምልክቱን በአለም አቀፍ ምድብ 36 አስመዝግቤ እያለሁ ተጠሪ ከአመልካች ጋር አንድ አይነት የሆነና አሳሳች የንግድ ስም እና የንግድ ምልክት የሚጠቀም በመሆኑ በንግድ ስያሜነት እና በንግድ ምልክትነት መጠቀሙን እንዱያቆምና ብር 400,000.00 ካሳ እንዱከፈለኝ ይወሰንልኝ በሚል ነዉ።ተጠሪ ደግሞ እየተጠቀምኩ ያለሁት የንግድ ስም ‛እንደራስ የንብረት አስተዲደር አገልግልት“ በእንግሉዝኛ ‛ENDERAS PROPERTY ADMINISTRATION SERVICE“ የሚል በመሆኑ ከአመልካች የንግድ ምልክት ጋር አይመሳሰልም፤አመልካች የንግድ ምልክቱን ያስመዘገበዉና የሕግ ጥበቃ ያገኘዉ ለንብረት አቻ ግምት ሲሆን ተጠሪ ደግሞ የንግድ ስሙን እየተጠቀመ ያለዉ ከንብረት አስተዲደር አገልግልት ጋር በተያያዘ በመሆኑና ‛እንደራስ“ ከሚለዉ ቃል በስተቀር ቃላቶቹ ስለማይመሳሰለ ህበረተሰቡን አያሳስትም በማለት ተከራክሯል።
እንዱሁም አመልካች በክሱ ላይ እንደገለጸዉ የንግድ ምልክቱ በምዝገባ ሂደት ላይ እያለ የንግድ ምልክቱ ለአመልካች መመዝገቡን የሚቃወም ካለ ተቃዉሞዉን እንዱያቀርብ በአእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት በማስታወቂያ በተደረገዉ ጥሪ መሰረት ተጠሪ ለአመልካች የንግድ ምልክቱ እንዲይመዘገብ ተቃዉሞ አቅርቦ የነበረ መሆኑ ተረጋግጧል። አእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት የተጠሪን ተቃዉሞ መርምሮ በቀን 09/10/2009ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ ተቃዉሞዉን ባለመቀበል የንግድ ምልክቱን ለአመልካች መመዝገቡን በስር ፍርድ ቤት መዝገብ ዉስጥ የሚገኘዉ የጽ/ቤቱ ዉሳኔ ይዘት ያሳያል። አመልካች ይህንን የአእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት ዉሳኔ እና አመልካች ለጽ/ቤቱ ጽፍ የነበረዉን መቃወሚያ በማስረጃነት በማቅረብ ካስመዘገብኩት የንግድ ምልክት ጋር አንድ አይነት የሆነ ሕብረተሰቡን በሚያሳስት መልኩ በንግድ ስምነት ወይም ምልክትነት ተጠሪ መጠቀሙን እንዱያቆም ሉወሰንልኝ ይገባል በማለት ተከራክሯል። ተጠሪ የንግድ ምልክቱ ለአመልካች እንዲይመዘገብ ተቃዉሞ እንደነበርና ተቃዉሞዉ ዉድቅ እንደተደረገ አምኖ በይግባኝና በልላ አኳኋን በተቃዉሞዉ ያልገፊዉ ተቃዉሞዉን አቅርቦ የነበረዉ አመልካች ምልክቱን ለንብረት አስተዲደር አገልግልት የሚያስመዘግብ መስልት እንደሆነና በኋላ ለተጠሪ የንግድ ምልክቱ የተመዘገበዉ ለንብረት አቻ ግምት(Asset valuation Services) አገልግልት መሆኑን በመረዲቱ እንደሆነ ገልጾ ተከራክሯል። በዚህ አግባብ የቀረበዉን የግራ ቀኙን ክርክር የሰሙት የሥር ፍርድ ቤቶች የግራ ቀኙን የሰነድ ማስረጃዎች መርምረዉ አመልካች የንግድ ምልክቱን ያስመዘገበዉ አለም አቀፍ ምድብ 36 ለንብረት አቻ ግመታ መሆኑንና ምልክቱም ከተጠሪ የንግድ ሥም ጋር ስለማይመሳሰል ኅብረተሰቡን ስለማያሳክር ተጠሪ የንግድ ስሙን መጠቀም ይችላል በማለት የአመልካችን መከራከሪያ ዉድቅ በማድረግ ወስነዋል።
በመሰረቱ በንግድ ምልክት ምዝገባና ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 501/1998 አንቀጽ 2/12 እና በንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 980/2008 አንቀጽ 2/10 ላይ እንደተመለከተዉ የንግድ ምልክት የአንድን ነጋዳ ወይም ኩባንያ እቃ(ምርት) ወይም አገልግልት ከላላዉ ነጋዳ/ኩባንያ እቃ(ምርት) ወይም አገልግልት ለመለየት የምልክቱ ባለቤት የሚጠቀምበት የአእምሮ ፈጠራ ዉጤት ሲሆን የንግድ ስም ደግሞ አንድ ነጋዳ/ኩባንያ በንግድ ሥራዉ በኅብረተሰቡ ዘንድ የሚታወቅበትና ኅብረተሰቡ ከላላ ነጋዳ/ኩባንያ ለይቶ እንዱያዉቀዉ ለማድረግ የሚገለገልበት መጠሪያዉ ነዉ። እንዱሁም በንግድ ምልክት ምዝገባና ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 501/1998 እና በንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 980/2008 እንደተመለከተዉ የንግድ ምልክት የሚመዘገበዉ በኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት ሲሆን የንግድ ስም የሚመዘገበዉ ደግሞ በንግድ ሚኒስቴር ነዉ።በዚህ አግባብ በተለያዩ መስሪያ ቤቶች የመመዝገብ አሰራር በላልች አገሮችም የተለመደ ቢሆንም ይህ አሰራር ኅብረተሰቡን በሚያመሳክር ሁኔታ አንድ አይነት ወይም በጣም የተቀራረበ የንግድ ምልክትና የንግድ ስም የተለያዩ ሰዎች እንዱያስመዘግቡ አለታዊ አጋጣሚ የሚፈጥር አሰራር ላሆን ይችላል።
በአዋጅ ቁጥር 501/1998 ከአንቀጽ 26 እስከ 28 ድረስ በተደነገገዉ መሰረት የንግድ ምልክት በማስመዝገብ ባለቤት የሆነ ሰዉ የንግድ ምልክቱን ካስመዘገበበት እቃ ወይም አገልግልት ጋር አያይዞ የመጠቀም ወይም ላላ ሰዉ እንዱጠቀምበት የመፍቀድ እንዱሁም ላላ ሰዉ ማንኛዉንም የንግድ ምልክቱን የሚመስል መለያ ምልክቱ ከተመዘገበባቸዉ ዕቃዎች ወይም አገልግልቶች ጋር በተያያዘ ወይም ሕዝብን ሉያሳስት በሚችል አኳኋን ከላልች እቃዎች ወይም አገልግልቶች ጋር በተያያዘ እንዲይጠቀሙ የማገድ መብት አለዉ። እንዱሁም የንግድ ምልክቱን ወይም የንግድ ምልክቱን የሚመስል መለያ ያለበቂ ምክንያቶች ጥቅሙን ሉጎዲ በሚችል አኳኋን ላላ ሰዉ እንዲይጠቀም እና መሰል ድርጊቶች እንዲይፈጸሙ ለማገድ/ለመከላከል የሚያስችል መብት አለዉ።ይህም የንግድ ምልክቱን በባለቤትነት ያስመዘገበዉ ሰዉ ላስመዘገበበት የዓለም አቀፍ ምድብ የንግድ ምልክቱን በብቸኝነት የመጠቀም መብት(Exclusive Right) እንዲለዉ የሚያስገነዝብ ነዉ።
አንድን በንግድ ምልክትነት የተመዘገበ ማንኛዉንም የንግድ ምልክቱን የሚመስል መለያ ምልክቱ ከተመዘገበባቸዉ ዕቃዎች ወይም አገልግልቶች ጋር በተያያዘ ወይም ሕዝብን ሉያሳስት በሚችል አኳኋን ከላልች እቃዎች ወይም አገልግልቶች ጋር በተያያዘ እንዱሁም የንግድ ምልክቱን ወይም የንግድ ምልክቱን የሚመስል መለያ በንግድ ምልክትነት ወይም በንግድ ስምነት ያለበቂ ምክንያቶች የንግድ ምልክቱን ባለቤት ጥቅም ሉጎዲ በሚችል አኳኋን እና በመሰል ድርጊቶች ላላ ሰዉ ተጠቅሟልና ፍርድ ቤቱ ያስቁምልኝ የሚል ክርክር ሲቀርብ ፍርድ ቤቶች የተባለት ድርጊቶች መፈጸም አለመፈጸማቸዉን በተከራካሪዎቹ ማስረጃዎች በማረጋገጥ እና አስፈላጊ ከሆነም የልዩ አዋቂ ሙያዊ ምስክርነት ቃል በመስማት የፍሬ ነገሩን መኖር አለመኖር አረጋግጠዉ አግባብነት ባለዉ ሕግ መሰረት መወሰን ይገባቸዋል።እንዱሁም ከዚህ ጋር ተያይዞ የንግድ ምልክቱ የተመዘገበበትን ምድብ እቃዎች ወይም አገልግልቶች ምንነት የሚመለከት ክርክር ቀርቦ ከሆነና የንግድ ምልክቱ የተመዘገበዉ የዓለም አቀፍ የንግድ ምልክት ምድብ ቁጥር ተጠቀሶ ከሆነ ጉዲዩ የንግድ ምልክት ምዝገባ የሚካሄድበትን ዓለም አቀፍ ዕቃዎች እና አገልግልቶች ምድብ ለመወሰን በፈረንሳይቱ ናይስ ከተማ ከወጣዉ ናይስ ስምምነት እና በስምምነቱ ለምድቦቹ ከተሰጠዉ ማብራሪያ (Nice Agreement Concerning the International Classification of Goods and Services for the Purposes of the Registration of Marks)ጋር አገናዝቦ መመርመር ያስፈልጋል።
በተጨማሪም የንግድ ምልክትም ሆነ የንግድ ስም ተመዝግቦ የሕግ ጥበቃ የሚደረገዉ ለነጻ ገበያ ዉድድር እንቅፊት ባልሆነ አኳኋን የአእምሯዊ ንብረት መብት እንዱጠበቅ በማድረግ ሰዎች ለፈጠራ እንዱነሳሱ ለማድረግ እና ኢኮኖሚያዊ ቀልጣፊነትንና ማኅበራዊ ደህንነትን በማስፈን የንግድና የኢንቨስትመንት አሰራር ለማቀላጠፍ ነዉ።በንግድ ምልክትና በንግድ ስም መካከል መመሳሰል ኖሮ ሕዝቡን ያሳስታል እንዱሁም የአንደ ባለቤት የላላዉን ጥቅም በሚጎዲ አኳኋን መለያዉን ጥቅም ላይ አዉሎል የሚል ክርክር ከቀረበም በዚህ አግባብ ተፈጸመ የተባለዉ ድርጊት የተፈጸመዉ በንግድ ሥራ ሂደት ዉስጥ ማንኛዉንም ሀቀኛ ያልሆነ፣አሳሳች ወይም አታላይነት ያለበት እና የተወዲዲሪን የንግድ ጥቅም የሚጎዲ ወይም ሉጎዲ የሚችል ድርጊት ለመፈጸም በማሰብ ወይም የአንደኛዉን ተወዲዲሪነት ለመቀነስ በማለም እና በመሰል ተግባራትና ዓላማ የተፈጸመ ነገር መኖሩ ሲረጋገጥ የንግድ ምልክቱ ወይም የንግድ ስሙ ከተመዘገበበት ዓላማ ዉጭ ተገቢ ያልሆነ የንግድ ዉድድር በመፍጠር የንግደን ማኅብረሰብና ሕዝቡን የሚጎዲ አለታዊ ተጽእኖ ይፈጥራል። ስለሆነም እንዱህ አይነት ክርክር ሲነሳ በንግድ ምልክት እና በንግድ ስም መካከል መመሳሰል ኖሮ ሕዝቡን በሚያሳስት ሁኔታና አስመዝጋቢዉን በሚጎዲ መልኩ አገልግልት ላይ ሲዉል አለመግባባቱን ለመፍታት የሚያስችል የሕግ ማእቀፍ የለም ተብል የሚታለፍ ሳይሆን ከንግድ ዉድድርና የሸማቾች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 813/2006 ፣ከንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 980/2008፣በንግድ ምልክት ምዝገባና ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 501/1998 እና የእነዚሁ አዋጆች ማስፈጸሚያ ደንቦችን ጨምር መመርመርና ተገቢውን መወሰን ይገባል።
ከላይ ከተመለከተዉ አንጻር የያዝነዉን ጉዲይ ስንመለከት አመልካች አጥብቆ የሚከራከረዉ የንግድ ምልክቱ ሲመዘገብ ተጠሪ ተቃዉሞ አቅርቦ ተቃዉሞዉ በአእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት ዉድቅ ተደርጎ ለአመልካች በንግድ ምልክትነት ከተመዘገበ በኋላ ተጠሪ ከንግድ ምልክቱ ጋር አንድ አይነት የሆነ አሳሳች የንግድ ስም እና የንግድ ምልክት እየተጠቀመ በመሆኑ በንግድ ስም ስያሜነት እና በንግድ ምልክትነት መጠቀሙን እንዱያቆም ይወሰንልን በሚል ነዉ።ተጠሪ ደግሞ ተቃዉሞ አቅርቤ የነበረዉ አመልካች የንግድ ምልክቱን ለንብረት አስተዲደር አገልግልት ያስመዘግባል በሚል ስጋት ቢሆንም መቃወሚያ ካቀረብኩ በኋላ የንግድ ምልክቱ ለአመልካች እየተመዘገበ ያለዉ ለንብረት አቻ ግመታ መሆኑን ሳረጋግጥ በተቃዉሞዬ አልገፊሁም እንዱሁም ‛እንደራስ“ ከሚለዉ ቃል በስተቀር የአመልካች የንግድ ምልክትና የተጠሪ የንግድ ስም ስለማይመሳሰል ሕዝቡን አያሳስትም በማለት ተከራክሯል።የግራ ቀኙ ክርክር ይህንን የሚመስል ከሆነ የስር ፍርድ ቤት ተጠሪ ተቃዉሞዉን ለአእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት ያቀረበዉ አመልካች በንግድ ምልክትነት እንዱመዘገብለት የጠየቀዉ መለያ ተጠሪ በንግድ ምልክትነትና በንግድ ስምነት ሲጠቀም ከነበረዉ ጋር አንድ አይነት ስለሆነ ወይም ስለሚመሳሰል ሕዝቡን ስለሚያሳስት ለአመልካች ሉመዘገብለት አይገባም በሚል ነዉ ወይስ አይደለም የሚለዉ ሉጣራና ሉረጋገጥ ይገባል።ይህንን ፍሬ ነገር ለማጣራት ተጠሪ በቀን 05/12/2008 ዓ/ም በቁጥር እንአ/01/012/2008 ጽፍ ለአእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት ያቀረበዉ መቃወሚያ ነዉ ብል አመልካች በማስረጃነት ያቀረበዉ ሰነድ ይዘትና አእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት በጉዲዩ ላይ በቀን 09/10/2009ዓ/ም የሰጠዉ ዉሳኔ እንደሆነ በመግለጽ በማስረጃነት ያቀረበዉ ማስረጃ ተገቢዉ ዋጋ ተሰጥቶት ከክርክሩ ጋር ተገናዝቦ ሉመዘን ይገባል።ሆኖም የሥር ፍርድ ቤቶች እነዚህ ማስረጃዎች ለጉዲዩ አግባብነት ያላቸዉ ሆነዉ እያለ ተገቢዉን ዋጋ በመስጠት አለመመዘናቸዉ መሰረታዊ የሆነ የማስረጃ ምዘና መርህ የሚጥስ በመሆኑ ሉታረም የሚገባዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ።
እንዱሁም አመልካች የንግድ ምልክቱን ያስመዘገበዉ ለንብረት አቻ ግመታ ዓለም አቀፍ ምድብ 36 መሆኑ አከራካሪ አይደለም። ሆኖም ተጠሪ ማንኛዉንም የንግድ ምልክቱን በሚመስል አኳኋን በንግድ ስምነት ምልክቱ ከተመዘገበበት አገልግልት ጋር በተያያዘ ወይም ሕዝብን ሉያሳስት በሚችል አኳኋን ከሚሰጠዉ አገልግልቶች ጋር በተያያዘ የአመልካችን ጥቅም ሉጎድ በሚችል አኳኋን መጠቀም አለመጠቀሙን አመልካች በምስክርነት የቆጠራቸዉን ምስክሮች በመስማት ሉጣራና ሉረጋገጥ ይገባል።በተጨማሪም ምስክሮቹ በሚሰጡት ምስክርነት ቃል መነሻ ወይም ከክርክሩ ባህርይ በመነሳት ለክርክሩ ዉሳኔ አሰጣጥ ጠቃሚ መስል ከታየም የሥር ፍርድ ቤት በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 136 መሰረት ልዩ አዋቂ(ኤክስፔርት) በማስረጃነት አስቀርቦ በመስማት ማረጋገጥ ሲገባዉ በዚህ አግባብ ሳያጣራ ተጠሪ በንግድ ስምነት የሚጠቀመዉ መለያ ከአመልካች የንግድ ምልክት ጋር አይመሳሰልም፤ተጠሪ የሚጠቀመዉ የንግድ ስም ከአመልካች የንግድ ምልክት ጋር ሲነጻጸር አማካይ የሆነ (Average)ተጠቃሚን አያሳክርም በማለት ችልቱ በራሱ ግንዛቤ ድምዲሜ ላይ መድረሱ ፍርድ ቤቱ የገለልተኝነት መርህ ጠብቆ አንድን ፍሬ ነገር በመጀመሪያ ተከራካሪ ወገኖች አስቀድሞ የማስረዲት ሸክም ቅደም ተከተል በጠበቀ መልኩ እንዱያስረደ ተደርጎ ፍርድ ቤቱ አንጻራዊ እዉነታ ለማረጋገጥ ካለበት ኃላፉነት አንጻር ተጨማሪ ማስረጃ ማስቀረብ ካለበትም በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 136 እና 264 መሰረት አግባብነት ያለዉን ማስረጃ አስቀርቦ አጣርቶ መወሰን እንደሚገባዉ የሚያስገነዝበዉን የክርክር አመራርና የማስረጃ አቀራረብ ሥርዓት ያልተከተለ በመሆኑ ተቀባይነት ያለዉ አይደለም። በተጨማሪም ፍርድ ቤቶች ግምት (presumption) በመዉሰድ መወሰን የሚችለት ሕግ በግልጽ ሲፈቅድና ግምት የሚወሰድበት ነገር በገሀደ አለም በአብዛኛዉ ሰዉ ዘንድ የሚታወቅ እና የተፈጥሮ እዉነታ ሲሆን እንጂ ሕግ ግምት በመዉሰድ የሚረጋገጥ ፍሬ ነገር ነዉ ብል በግልጽ ያልደነገገዉን የተጠቀሰዉን አይነት በልዩ አዋቂ ምስክርነት ጭምር በማስረጃ ሉረጋገጥ የሚገባ ፍሬ ነገር ሁለ በግምት ላይ ተመስርቶ እንዱወሰን በተግባር የዲበረዉ የዲኝነት አሰጣጥ ፍልስፍና (Judicial Jurisprudence) እና የማስረጃ ሕግን የሚመለከቱ መርሆዎች ስለማይፈቅደ ሉታረም የሚገባዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ።በመሆኑም ተከታዩን ወስነናል።
የፍደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 26/06/2011 ዓ/ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና የፍደራል የከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 23/04/2012 ዓ/ም የሰጠዉ ዉሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ተሽረዋል።
የፍደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መዝገቡን አንቀሳቅሶ፡- 2.1 ተጠሪ ተቃዉሞዉን ለአእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት ያቀረበዉ አመልካች በንግድ ምልክትነት እንዱመዘገብለት የጠየቀዉ መለያ ተጠሪ በንግድ ምልክትነትና በንግድ ስምነት ሲጠቀም ከነበረዉ ጋር አንድ አይነት ስለሆነ ወይም ስለሚመሳሰል ሕዝቡን ስለሚያሳስት ለአመልካች ሉመዘገብለት አይገባም በሚል ነዉ ወይስ አይደለም፣ ተጠሪ ተቃዉሞዉን ያቀረበዉ አመልካች እንዱመዘገብለት የጠየቀዉ የንግድ ምልክት ከተጠሪ በንግድ ስምነትና ምልክትነት ከሚጠቀመዉ ጋር ስለሚመሳሰል ሕዝቡን ያሳክራል በሚል መሆኑን የቀረበዉ ማስረጃ የሚያሳይ ከሆነም ለማስረጃዉ ተገቢዉ ዋጋ ሰጥቶ መዝኖ ሉወሰን ይገባል ብለናል።
2.2 ተጠሪ በንግድ ስምነት የሚጠቀመዉ መለያ ከአመልካች የንግድ ምልክት ጋር የሚመሳሰል መሆን አለመሆኑን እና ተጠሪ የሚጠቀመዉ የንግድ ስም ከአመልካች የንግድ ምልክት ጋር ሲነጻጸር ምክንያታዊ በሆነ ሰዉ መመዘኛ ሲታይ ሕዝብን ያሳስታል ወይስ አያሳስትም፤ ያሳስታል ወደሚል ድምዲሜ ላይ ከተደረሰም አመልካች ባቀረበዉ ዲኝነት ጥያቄዎች ላይ ተመስርቶ የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃዎች መርምሮና ምስክሮች በመስማት እንዱሁም እንደነገሩ ሁኔታ ተገቢዉን ተጨማሪ ማስረጃና ምስክሮች አስቀርቦ ሰምቶና መርምሮ ከላይ በፍርደ ላይ ከተመለከቱት የሕግ ማእቀፍች ጋር አገናዝቦ ተገቢዉን እንዱወስን ጉዲዩን በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 343/1 መሰረት መልሰንለታል።
ት እ ዛ ዝ 1.የዉሳኔዉ ግልባጭ ለሥር ፍርድ ቤት ይተላለፍ። ለግራ ቀኙም ሲጠይቁ ግልባጩ ይሰጣቸዉ።
በትእዛዝ የመጣዉ የፍደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መ/ የሆነዉ መዝገብ ለምድብ ችልቱ ይመለስ።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.