አንድ እቃ በአየር መንገድ ተጭኖ ሲጓጓዝ ባለእቃው ሲያስረክብ በእቃው ያለውን ልዩ ጥቅም በመግለጽ ተገቢውን ተጨማሪ ዋጋ መከፈለን ካላስረዲ በቀር እቃው ተጓጉዞ ርክክብ እስከሚፈፀም ድረስ ባለው ጊዜ ቢጠፊ ወይም ጉዲት ቢደርስበት ካሳ ሉከፈል የሚገባው በጠፊው እቃ ወይም ጉዲት ለደረሰበት እቃ በአንድ ኪል ግራም 17 ስፔሻል ድሮዊንግ ራይት በመክፈል ስለመሆኑ የሞንትሪያል ቃል ኪዲን (Montreal Convention of 1999) አንቀጽ 22 (3) አና አዋጅ ቁጥር 820/2006
No summary available.
መጋቢት 24 ቀን 2012 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ ተሾመ ሽፈራዉ ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግሥቱ ነጻነት ተገኝ አመልካች፡- ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጄነራል ኢንሹራንስ አ.ማ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ሀሪያ ታደሰ ደስታ መዝገቡ ተመርምሮ ከዚህ የሚከተለዉ የፍርድ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ መድን ሰጪ ለሦስተኛ ወገን የከፈለዉን ካሳ ከመድን ገቢዉ ለማስመለስ ዲኝነት ተጠይቆ በሚያቀርበዉ ክስ ላይ ተፈጻሚነት የሚኖረዉን ይርጋ እና አቆጣጠሩን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በመቀላ መእከላዊ(ከፍተኛ) ፍርድ ቤት ሆኖ በዚህ ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ በመሆን ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል። ከክርክሩ እንደተረዲነዉ አመልካች ንብረትነቱ የተጠሪ ለሆነ በሰላዲ ቁጥር 3-06609 ትግ ለሚታወቅ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በሦስተኛ ወገን ላይ ለሚያደርሰዉ ጉዲት ከቀን 16/07/2008ዓ/ም እስከ ቀን 15/07/2009ዓ/ም ድረስ ለሚቆይ ጊዜ በፖሉሲ ቁጥር ኤምኬ/ዱአይ/ ኤምቲ-ፒኤስ/0381/16 የሦስተኛ ወገን የመድን ሽፊን ሰጥቶ ባለበት ጊዜ ተሽከርካሪዉ በቀን 22/09/2008ዓ/ም መስመሩን ስቶ የሰላዲ ቁጥር 3-18362አ.አ ተሽከርካሪ ገጭቶ በ4 ተሳፊሪዎች ላይ ሞት በ8 ተሳፊሪዎች ላይ ደግሞ የአካል ጉዲት በማድረሱ አመልካች ለሟች ቤተሰቦችና ጉዲት ለደረሰባቸዉ ሦስተኛ ወገኖች ብር 103,030.45 የካሳ ክፍያ ፈጽሟል። ይህንን ተከትል አመልካች የተጠሪ ተሽከርካሪ የመጫን አቅሙ 11 ሰዉ ሆኖ እያለ አደጋዉ በደረሰበት ጊዜ በትራንስፖርት ባለስልጣን ከተፈቀደለት የመጫን አቅም በላይ 14 ተሳፊሪዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ እንደነበር በፖሉስ ሪፖርት ስለተረጋገጠ የመድን ዉልን ጥሳለች በሚል ለሦስተኛ ወገን በከፈለዉ ካሳ ልክ ተመላሽ እንድታደርግለት በተጠሪ ላይ ክስ በመመስረት ዲኝነት ጠይቋል።
ተጠሪ ለቀረበባት ክስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በማቅረብ አደጋዉ የደረሰዉ በቀን 22/09/2008ዓ/ም ሆኖ ክሱን ሁለት ዓመት ካለፈ በኋላ በቀን 11/11/2010ዓ/ም ስላቀረበ የአመልካች ክስ በይርጋ ታግዶል በማለት ተቃዉማለች።አመልካች በበኩለ የይርጋ ጊዜዉ መቆጠር ያለበት አመልካች ለተጎጂዎች ክፍያ ከፈጸመበት ከቀን 13/07/2009 ዓ/ም ጀምሮ ላሆን ስለሚገባ ከዚህ ቀን ጀምሮ ክስ እስከተመሰረተበት ቀን ድረስ ያለዉ ጊዜ ሲቆጠር ሁለት አመት ባለማለፈ ክስ የማቅረብ መብቴ በይርጋ ቀሪ አልሆነም በማለት ተከራክሯል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ ዲኝነት ስልጣን ያየዉ የመቀላ ከተማ መእከላዊ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 29/04/2011 ዓ/ም በዋለዉ ችልት በሰጠዉ ብይን አደጋዉ በንግድ ሕጉ አንቀጽ 674/1 በግልጽ እንደተደነገገዉ በኢንሹራንስ ዉል ምክንያት የሚነሳ ክርክር ጉዲት ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ በሁለት ዓመት ዉስጥ ካልቀረበ በይርጋ እንደሚታገድ ስለተደነገገ ጉዲቱ በቀን 22/09/2008ዓ/ም ደርሶ ክሱ በቀን 11/11/2010 ዓ/ም ስለቀረበ ክሱ የቀረበዉ የሁለት ዓመት ጊዜ ካለፈ በኋላ በመሆኑ በይርጋ የታገደ ነዉ በማለት መዝገቡን ዘግቷል።አመልካች በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ለትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ቢያቀርብም ፍርድ ቤቱ በመ/ ላይ በቀን 27/07/2011ዓ/ም በዋለዉ ችልት በሰጠዉ ትእዛዝ ይግባኙን በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዟል።አመልካች ለዚህ ችልት በቀን 26/10/2011 ዓ/ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረበዉ ከላይ በተመለከተዉ መሰረት በተሰጠ ብይንና ትእዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን የአቤቱታዉ ይዘት አጭሩ የሚከተለዉ ነዉ።
በተያዘዉ ጉዲይ ጉዲት የደረሰዉ በሦስተኛ ወገኖች ላይ በመሆኑ አመልካች በተጠሪ ላይ የመድን ዉለን አላከበረም በሚል ክስ መስርቶ የከፈለዉን የጉዲት ካሳ ተመላሽ የመጠየቅ መብት የሚያገኘዉ ለሦስተኛ ወገኖች ካሳ ከከፈለ በኋላ በመሆኑ ክሱ የቀረበዉም በአዋጅ ቁጥር 799/2005 አንቀጽ 6/2 ስር የተደነገገዉን መሰረት በማድረግ ነዉ።የይርጋ ጊዜዉ መታሰብ የሚገባዉ የካሳ ክፍያ በአመልካች ከተፈጸመበት ቀን ከመጋቢት 16 ቀን 2009ዓ/ም ጀምሮ ስለሆነ ክሱ በተመሰረተበት በቀን 11/11/2010 ዓ/ም ሁለት ዓመት አልሞላም።በመሆኑም የስር ፍርድ ቤቶች ከንግድ ሕጉ በኋላ የወጣዉን አዋጅ ቁጥር 799/2005ን ባገናዘበ ሁኔታ የይርጋ ጊዜዉን ሳይመረምሩ ክሱ በይርጋ ታግዶል በማለት መወሰናቸዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ።እንዱሁም በተጠሪ ተሽከርካሪ በሶስተኛ ወገን ላይ የሞትና የአካል ጉዲት የደረሰ በመሆኑ ድርጊቱ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 572 መሰረት በ5 ዓመት እስራት የሚያስቀጣ በመሆኑ ይህንን መነሻ ያደረገ የካሳ ክስ ሲቀርብ ተፈጻሚነት የሚኖረዉ ለወንጀል ጉዲይ የተደነገገዉ ይርጋ በመሆኑ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2143/2 መሰረት አደጋዉ ከደረሰበት ከግንቦት 22 ቀን 2008ዓ/ም ጀምሮ ሲሰላ 5 ዓመት ስላልሞላ የአመልካች ክስ የማቅረብ መብት በይርጋ ቀሪ ሳይሆን በይርጋ ቀሪ ሆኗል ተብል መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ ተብል እንዱታረም በመጠየቅ አቤቱታዉን አቅርቧል።
የሰበር አጣሪ ችልት አቤቱታውን መርምሮ የመድን ዉል ባላከበረ ደንበኛ ላይ በአዋጅ ቁጥር 799/2005 አንቀጽ 6/2 መሰረት የሚቀርብ ክስ የይርጋ ጊዜዉ መታሰብ ያለበት ከመቼ ጀምሮ ነዉ የሚለዉን ነጥብ ለማጣራት ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልት ያስቀርባል ብል ትዕዛዝ በመስጠቱ ተጠሪ በቀን 12/02/2012 ዓ/ም የተፃፈ በአጭሩ የሚከተለዉን መልስ አቅርባለች።
የአዋጅ ቁጥር 799/2005 አንቀጽ 6/2 የመድን ፖሉሲ የዉል ሁኔታዎችን የሚመለከት እንጅ ስለ ይርጋ ጊዜ የሚመለከት ድንጋጌ ባለመሆኑ አመልካች ከዚህ ድንጋጌ ጋር በማያያዝ ያቀረበዉ ክርክር ዉድቅ ላሆን ይገባል።ለዚህ ጉዲይ አግባብነት ያለዉ የይርጋ ድንጋጌ በንግድ ሕጉ አንቀጽ 674/1 ስር የተደነገገዉ ሲሆን በዚህ ድንጋጌ መሰረት አመልካች ክሱን ጉዲቱ ከደረሰበት ቀን ጀምሮ ባለዉ ሁለት አመት ጊዜ ዉስጥ ባለማቅረቡ የስር ፍርድ ቤቶች የአመልካች ክስ የማቅረብ መብት በይርጋ ቀሪ ሆኗል በማለት በመወሰናቸዉ የተፈጸመ ስህተት ባለመኖሩ አቤቱታዉ ዉድቅ ይደረግልኝ በማለት ተከራክራለች።
አመልካች በተጠሪ በቀረበ መልስ ላይ በቀን 29/03/2012 ዓ/ም የተጻፈ የመልስ መልስ በማቅረብ ተከራክሯል።
ከዚህ በላይ የተመዘገበዉ የግራ ቀኝ ክርክርና በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ዉሳኔዎች ይዘት ሲሆን እኛም የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩ ለሰበር ችልት ያስቀርባል ሲል ከያዘዉ ጭብጥ አንጻር በስር ፍርድ ቤቶች በተሰጡ ዉሳኔዎች የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ መርምረናል።
እንደተመረመረዉም አመልካች በፖሉሲ ቁጥር ኤምኬ/ዱአይ/ኤምቲ-ፒኤስ/0381/16 በሦስተኛ ወገን ላይ ለሚደርስ አደጋ የመድን ሽፊን ሰጭ ሲሆን ተጠሪ ደግሞ የሰላዲ ቁጥር 3-06609 ትግ የሆነ ተሽከርካሪያቸዉ በሦስተኛ ወገን ላይ ለሚያደርሰዉ አደጋ ከአመልካች የሦስተኛ ወገን የመድን ሽፊን የገዙ መድን ገቢ እንደሆነች ከክርክራቸዉ ተረድተናል። አመልካች በተጠሪ ላይ በቀን 11/11/2010 ዓ/ም የመሰረተዉ ክስ ይህ ለተጠሪ ተሽከርካሪ የተሰጠዉ የመድን ሽፊን ከቀን 16/07/2008ዓ/ም እስከ ቀን 15/07/2009ዓ/ም ድረስ ጸንቶ በቆየበት ጊዜ የተሽከርካሪዉ የተፈቀደለት የመጫን አቅም 11 ሰዉ ሆኖ እያለ አደጋዉ በደረሰበት ጊዜ በትራንስፖርት ባለስልጣን ከተፈቀደለት የመጫን አቅም በላይ 14 ተሳፊሪዎችን አሳፍሮ እንዱጓዝ በማድረጓ ተሽከርካሪዉ በቀን 22/09/2008ዓ/ም መስመሩን ስቶ የሰላዲ ቁጥር 3-18362አ.አ ተሽከርካሪ ገጭቶ በ4 ተሳፊሪዎች ላይ ሞት በ8 ተሳፊሪዎች ላይ ደግሞ የአካል ጉዲት በማድረሱ አመልካች ለሟች ቤተሰቦችና ጉዲት ለደረሰባቸዉ ሦስተኛ ወገኖች ብር 103,030.45 የካሳ ክፍያ ስለፈጸመ ይህ አደጋ ሉደርስ የቻለዉ ተጠሪ የመድን ዉለንና የትራፉክ ደንብ በመጣሷ ምክንያት ነዉ በሚል ተጠሪ ለሦስተኛ ወገኖች የተከፈለዉን ገንዘብ እንድትተካልኝ ይወሰንልኝ የሚል ዲኝነት የጠየቀበት ክስ መሆኑን ተገንዝበናል። የስር ፍርድ ቤቶች ተጠሪ ክሱ በይርጋ ታግዶል በሚል ያቀረበችዉን መቃወሚያ በመቀበል የይርጋ ጊዜዉን አደጋዉ ከደረሰበት ከግንቦት 22 ቀን 2008ዓ/ም ጀምሮ ክሱ እስከቀረበበት ቀን ሐምል 11 ቀን 2010 ዓ/ም ድረስ ያለዉን ጊዜ በመቁጠር አመልካች ክሱን ያቀረበዉ በንግድ ሕጉ አንቀጽ 674/1 ስር የተደነገገዉ የሁለት ዓመት ጊዜ ካለፈ በኋላ ነዉ በማለት መዝገቡን ዘግተዋል።
ከላይ እንደተመለከተዉ አመልካች በተጠሪ ላይ የመሰረተዉ ክስ አመልካች በሰጠዉ የሦስተኛ ወገን መድን ፖሉስ ሽፊን መሰረት በተጠሪ ተሽከርካሪ ምክንያት የሞትና የአካል ጉዲት ለደረሰባቸዉ ሦስተኛ ወገኖች የካሳ ክፍያ ከፈጸመ በኋላ ጉዲቱ በሦስተኛ ወገኖች ላይ ሉደርስ የቻለዉ የመድን ዉለንና የትራፉክ ደንብ በጣሰ አኳኋን የተጠሪ ተሽከርካሪ በትራንስፖርት ባለስልጣን ከተፈቀደለት የመጫን አቅም በላይ 14 ተሳፊሪዎችን አሳፍሮ እንዱጓዝ በመደረጉ ምክንያት ስለሆነ ተጠሪ የመድን ዉል ስለጣሰች ለሦስተኛ ወገኖች በከፈልኩት ካሳ ልክ ልትተካልኝ ይገባል በማለት ነዉ። እንደሚታወቀዉ በተሽከርካሪ አደጋ በሦስተኛ ወገኖች ላይ ለሚደርስ አደጋ የሚሰጥ የመድን ሽፊን የሚመነጨዉ በመድን ሰጭዉና በመድን ገቢዉ መካከል በሚደረግ የመድን ዉል ፖሉሲ መነሻ ቢሆንም በተሽከርካሪ አደጋ በሦስተኛ ወገን ላይ ለሚደርስ አደጋ የመድን ሽፊን ለመስጠት በወጣ አዋጅ ቁጥር 799/2005 በተዘረጋዉ ስርዓት መሰረት በመድን ዉለ ተዋዋይ ወገን ያልሆኑ አደጋ የደረሰባቸዉ ሦስተኛ ወገኖች በሽፊኑ ተጠቃሚ እንዱሆኑ የሚያደርግ ግንኙነት መፈጠሩን መገንዘብ የሚቻል ነዉ። በዚህ አግባብ ምንም እንኳን ግራ ቀኝ የመድን ዉለ ተዋዋዮች ቢሆኑም ከዉለ ተጠቃሚዎች ሦስተኛ ወገኖች ጭምር በመሆናቸዉ የመድን ዉል ፖሉሲዉ እና አዋጅ ቁጥር 799/2005 የሦስትዮሽ ግንኙነትን እንዲቋቋመ መረዲት ያስፈልጋል።
አመልካች በተጠሪ ላይ ክሱን የመሰረተዉ የመድን ዉለን እና በአዋጅ ቁጥር 799/2005 አንቀጽ 6/2 ስር የተደነገገዉን መሰረት በማድረግ ስለመሆኑ ክሱ ስለሚያሳይ ግንኙነታቸዉም በመድን ዉል ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ለጉዲዩ አግባብነት የሚኖረዉ የይርጋ ድንጋጌ ይህንን በዉል ላይ የተመሰረተዉን ግንኙነት መሰረት ያደረገ ላሆን ይገባል። በመሆኑም ከዉል ዉጭ የሆነ ኃላፉነት መነሻ በማድረግ ካሳ ለማስከፈል ለሚቀርብ ክስ ተፈጻሚነት እንዱኖረዉ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2143/2 ስር የተደነገገዉ የይርጋ ድንጋጌ የዉል ግንኙነትን መነሻ ባደረገ ክርክር ላይ ተፈጻሚነት ስለላለዉ አመልካች ለጉዲዩ ተፈጻሚነት ያለዉ የይርጋ ድንጋጌ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2143/2 ስር የተደነገገዉ ነዉ በሚል ያቀረበዉን ክርክር አልተቀበልንም።
በልላ በኩል አመልካች በተጠሪ ላይ ክሱን የመሰረተዉ በአዋጅ ቁጥር 799/2005 አንቀጽ 6/2 ስር የተደነገገዉን መሰረት በማድረግ ቢሆንም እንዱህ አይነት ክስ መቅረብ ያለበትን የይርጋ ጊዜ በተመለከተ በአዋጅ ቁጥር 799/2005 ስር አልተደነገገም። ከኢንሹራንስ ዉል ጋር የተያያዙ ክሶችን ይርጋ በተመለከተ በጠቅላላዉ በንግድ ሕጉ አንቀጽ 674/1 ስር በኢንሹራንስ ዉል ምክንያት የሚቀርብ ማንኛዉም ክስ የሚታገደዉ ለክሱ ምክንያት የሆነዉ ጉዲት ከተደረገበት ወይም በጉዲዩ ጥቅም ያላቸዉ ወገኖች ጉዲቱን ካወቁበት ቀን ጀምሮ (በእንግሉዘኛዉ ቅጅ፡ …from the occurrence giving rise to the claim or from the day when the parties knew of the occurrence)ከሁለት ዓመት በኋላ ነዉ ሲል የይርጋ ጊዜና የይርጋ ጊዜዉ የሚቆጠርበት ሁኔታ ተደንግጓል። ይህ የይርጋ ጊዜ ከኢንሹራንስ ዉል የመነጨ ማንኛዉንም ክስ የሚመለከት መሆኑን የድንጋጌዉ ይዘት የሚያሳይ በመሆኑ ለተያዘዉ ጉዲይ ልዩ ሕግ የሆነዉ አዋጅ ቁጥር 799/2005 የተሽከርካሪ አደጋ በሦስተኛ ወገን ከሚያደርሰዉ አደጋ ጋር በተያያዘ ለሦስተኛ ወገን መድን ሰጭዉ የከፈለዉን ካሳ መድን ገቢዉ እንዱተካለት የሚያቀርበዉን ክስ የሚመለከት የይርጋ ጊዜ ስላልደነገገ ለተያዘዉ ጉዲይ ተፈጻሚነት ያለዉ ይርጋ በንግድ ሕጉ አንቀጽ 674/1 ስር የተደነገገዉ እንደሆነ ተገንዝበናል።ከዚህ አኳያ የስር ፍርድ ቤቶች ለጉዲዩ ተፈጻሚነት ያለዉ የይርጋ ድንጋጌ በንግድ ሕጉ አንቀጽ 674/1 ስር የተደነገገዉ ነዉ ማለታቸዉ የሚነቀፍ አይደለም።
ሆኖም በፍትሐብሕር ሕጋችን ስለ ይርጋ በጠቅላለዉ በሚደነግገዉ ክፍል በአንቀጽ 1846 ‛የይርጋው መነሻ ጊዜ“ በሚል ርእስ ሥር ‛የይርጋው ቀን መቆጠር የሚጀምረው ግዳታዉን ለመጠየቅ ተገቢ ከሆነዉ፤ወይም ዉለ የሚሰጠዉ መብት ከተሰራበት ቀን ጀምሮ ነዉ“ በማለት ደንግጓል። የንግድ ሕጉን አንቀጽ 674/1 እና የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1846 ድንጋጌዎች ይዘት መንፈስና ዓላማ መሰረት በማድረግ በአመልካችና በተጠሪ መካከል ያለዉን ግንኙነትና የክሱን ምክንያት መሰረት አድርገን እንደመረመርነዉ በአዋጅ ቁጥር 799/2005 መሰረት አመልካች በተጠሪ ላይ ሉያነሳ የሚችለዉን ማንኛዉንም መከራከሪያ ጉዲት በደረሰባቸዉ ሦስተኛ ወገኖች ላይ ማንሳትና ካሳ አልከፍልም ማለት ስለማይችል በዚህ አዋጅና በሦስተኛ ወገን የመድን ሽፊን ዉል መሰረት ለሦስተኛ ወገኖች የካሳ ክፍያ መክፈል ይጠበቅበታል።
በዚህ መሰረት አመልካች ለሦስተኛ ወገኖች ካሳ የከፈለዉ መጋቢት 16 ቀን 2009 ዓ/ም መሆኑ በስር ፍርድ ቤቶች የተረጋገጠ ነዉ።አመልካች በዉለና በሕጉ መሰረት ተገድ ካሳ በመክፈለ ገንዘቡን ወጪ ያደረገዉ መጋቢት 16 ቀን 2009 ዓ/ም በመሆኑ ከዚህ ቀን በፉት ለሦስተኛ ወገን የከፈለዉ ካሳ ባለመኖሩ የመድን ዉል ፖለሲዉንም ሆነ አዋጅ ቁጥር 799/2005 አንቀጽ 6/2ን መሰረት በማድረግ ለሦስተኛ ወገኖች የከፍልኩትን ትተካልኝ በማለት በመድን ገቢዋ(በተጠሪ) ላይ ክስ ለመመስረት የሚያስችል የበሰለ መብት የለዉም። በእንዱህ አይነት ጉዲይ በመድን ገቢዉ ላይ ለክሱ ምክንያት የሆነ ጉዲት ደረሰበት ማለት የሚቻለዉ(the occurrence giving rise to the claim) እና በመብቱ ሉሰራ የሚችለዉ ለሦስተኛ ወጎኖች የካሳ ክፍያ ከፈጸመበት ቀን ከመጋቢት 16 ቀን 2009 ዓ/ም ጀምሮ ባለዉ ሁለት ዓመት ጊዜ ዉስጥ እንጅ በሦስተኛ ወገኖች ላይ አደጋዉ ከደረሰበት ቀን ጀምሮ አይደለም።
ከተያዘዉ ጉዲይ ጋር በተያያዘ በሦስተኛ ወገኖች ላይ አደጋ የደረሰበት ጊዜ ለይርጋ አቆጣጠር መነሻ ላሆን የሚችለዉ መድን ሰጭዉን ካሳ ለማስከፈል ከሚቀርብ ክስ ጋር በተያያዘ ነዉ።
ሲጠቃለል አመልካች ከተጠሪ ጋር በፈጸመዉ የመድን ዉል መሰረት በተጠሪ ተሽከርካሪ አደጋ ደረሰባቸዉ ለተባለት ሦስተኛ ወገኖችና ለተጎጂ ቤተሰቦች የካሳ ክፍያ የፈጸመበት ጊዜ በተጠሪ (በመድን ገቢዋ) ለመሰረተዉ ክስ ይርጋ አቆጣጠር መነሻ ላሆን ይገባል። በዚህ መሰረት አመልካች ካሳ የከፈለዉ መጋቢት 16 ቀን 2009 ዓ/ም ሆኖ በተጠሪ ላይ ክስ የመሰረተዉ በንግድ ሕጉ አንቀጽ 674/1 ሥር የተደነገገዉ የሁለት ዓመት ጊዜ ሳያልፍ ሐምል 11 ቀን 2010 ዓ/ም በመሆኑ የአመልካች ክስ የማቅረብ መብት በይርጋ ቀሪ አልሆነም። ስለሆነም የመቀላ ማእከላዊ ፍርድ ቤት የተጠሪን መቃወሚያ በመቀበል ለተያዘዉ ጉዲይ አግባብነት የላለዉን አደጋዉ የደረሰበትን ቀን ለይርጋ አቆጣጠር መነሻ በማድረግ የአመልካች ክስ የማቅረብ መብት በይርጋ ታግዶል በማለት መዝገቡን መዝጋቱና ጉዲዩን በይግባኝ ያየዉ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ስህተቱን ሳያርም ማለፈ ሉታረም የሚገባዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ። በመሆኑም ተከታዩን ዉሳኔ ሰጥተናል።
የመቀላ ከተማ መእከላዊ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 29/04/2011 ዓ/ም የሰጠዉ ብይን እና የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 27/07/2011ዓ/ም የሰጠዉ ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
የመቀላ ከተማ መእከላዊ ፍርድ ቤት መ/ በማንቀሳቀስ ፍሬ ነገሩን በተመለከተ ግራ ቀኙን አከራክሮና እንደአስፈላግነቱ ማስረጃ ሰምቶና መርምሮ ሕግን መሰረት ያደረገ ዉሳኔ እንዱሰጥ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 343/1 መሰረት ጉዲዩ ተመልሶለታል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
የዚህ ዉሳኔ ግልባጭ ለክልለ ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ።
ዉሳኔዉ ይታተም ዘንድ ለህግና ምርምር ክፍል ይተላለፍ።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.