የኢንሹራንስ ሽፊን ወደፉት ለሚደርስ አደጋ የሚሰጥ የመድን ሽፊን በመሆኑ በልዩ ሁኔታ በግልጽ ስምምነት ካልተደረገ በቀር በዋናው ኢንሹራንስ ውል ላይ ሳይካተት የቀረውን የአደጋ ምክንያት ለማካተት የሚደረግ የመድን ሽፊን ማስፉያ (Extension) ውል ወደ ኋላ ተመልሶ ዋናው የኢንሹራንስ ውል ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ ተፈፃሚ እንዱሆን መወሰን መሰረታዊ የህግ ስህተት ስለመሆኑ የንግድ ህግ አንቀጽ 659/1
No summary available.
የሰ/መ/ ጥር 25 ቀን 2012 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ ተሾመ ሽፈራዉ ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግሥቱ ነጻነት ተገኝ አመልካች፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተጠሪ፡- ብርሃን ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ መዝገቡ ተመርምሮ ከዚህ የሚከተለዉ የፍርድ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ በአየር በሚጓጓዝ እቃ(ካርጎ) ላይ በመጥፊት እና በመበላሽ ጉዲት ሲደርስ ካሳ ስለሚከፈልበት አግባብ የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረዉ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን በዚህ ፍርድ ቤት የአሁን ተጠሪ ከሳሽ የአሁን አመልካች ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።ከክርክሩ እንደተረዲነዉ የአሁን ተጠሪ በመሰረተዉ ክስ በአሁን ተጠሪ የኢንሹራንስ ሽፊን የተሰጠዉ ንብረትነቱ የገደብ ኢንጂነሪንግ ኃላ/የተ/የግ/ማኅበር የሆኑ የጆንደር የእርሻ ትራክተር የተለያዩ መለዋወጫዎች 48 ፓላት ከደቡብ አፍሪካ ወደ አዱስ አበባ አመልካች ተረክቦ ሲያጓጉዝ ቁጥራቸዉ 144 የሆኑ መለዋወጫዎች በዝናብና በፀሐይ በመበላሸታቸዉ እንዱሁም ብዛታቸዉ 18 የሆኑት ደግሞ በመጥፊታቸዉ ተጠሪ ጉዲቱን በባለሙያ በማስመርመር ለተበላሹትና ለጠፈት በድምሩ ብር 210,942.64 ለደንበኛዉ ካሳ መክፈለን በመግለጽ አመልካች እቃዎቹን በተረከበበት አኳኋን በደህና ሁኔታ ባለማስረከቡ የደረሰ ጉዲት ነዉ በሚል ብር 210,942.64 አመልካች እንዱተካለት እንዱወሰን ዲኝነት ጠይቋል።
የአሁን አመልካች የተጠሪ ክስ የማቅረብ መብት በይርጋ ታግዶል የሚል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ የሚመለከት መከራከሪያ እና ፍሬ ነገርን በተመለከትም ጉዲቱ የደረሰዉ በአስተሻሸግ ጉድለት በመሆኑ ኃላፉነት የለብኝም፤ ኃላፉነት አለብህ ከተባለም ተጠሪ ወይም ድንበኛዉ በእቃዉ ልዩ ጥቅም እንዲለዉ በመግለጽ ተጨማሪ የጭነት ዋጋ ባለመከፈለ የጉዲት ካሳዉ መጠን ሉሰላ የሚገባዉ በኪል ግራም 17 ስፔሻል ድሮዊንግ ራይት ማለትም በኪል ግራም 20 የአሜሪካን ድላር ሂሳብ በመሆኑ ለተጠሪ ሉከፈለዉ የሚገባዉ 1,809.00 የአሜሪካን ድላር ወይም በኢትዮጵያ ብር 36,192.00 ብቻ በመሆኑ ለተጠሪ ብር 36,192.00 እንድከፍልና ተጠሪ የእቃዎቹን ቅሪት እንዱያስረክበኝ ይወሰንልኝ በማለት መከራከሩን የዉሳኔዉ ግልባጭ ያሳያል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ ዲኝነት ሥልጣን ያየዉ የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ የግራ ቀኙን ክርክር እና የአመልካችን ምስክር ሰምቶ በቀን 27/11/2009 ዓ/ም በዋለዉ ችልት በሰጠዉ ዉሳኔ አመልካች ጉዲቱ በአስተሻሸግ ጉድለት መድረሱን አላስረዲም በሚል አመልካች ከዚህ አኳያ ያቀረበዉን ክርክር ዉድቅ በማድረግ በሞንትሪያል ፕሮቶኮል ቁጥር 4 እንደተሻሻለዉ አንቀጽ 18 መሰረት አመልካች አጓጉዞ ለተጠሪ እስከሚያስረክብ ድረስ በእቃዉ ላይ ለደረሰዉ ጉዲት አመልካች ካሳ የመክፈል ኃላፉነት አለበት በማለት ወስኗል። የጉዲት ካሳ መጠን በተመለከተም በዋርሶዉ ስምምነት አንቀጽ 22(2/ሀ) ስር የካሳ መጠን የእቃዉ የግዥ ዋጋ መጠን ይሆናል በሚል በተደነገገዉ መሰረት 144 መለዋወጫዎች መጎዲታቸዉና ቁጥራቸዉ 18 የሆኑት መጥፊታቸዉን አመልካች ካለመካደም በተጨማሪ ተጠሪ በማስረጃ አስረድቷል በሚል የ162 መለዋወጫዎች የግዥ ዋጋቸዉ በግዥ እና በባለሙያ ሰነድ ላይ በተመለከተዉ መሰረት በክፍያዉ እለት በነበረዉ ምንዛሬ ምጣኔ መሰረት በብር 19,942.64 ሂሳብ ስላት መሰረት ብር 210,942.64 ይሆናል በማለት አመልካች ከ9% ወለድ ጋር ለተጠሪ እንዱከፍል ወስኗል።
አመልካች በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ያቀረበዉ መከራከሪያ ዉድቅ መደረጉ እና ካሳ የተወሰነበትን አግባብና የካሳዉን መጠን በሚመለከት በተሰጠዉ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቦ ፍርድ ቤቱም በመ/ ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ በቀን 13/05/2011 ዓ/ም በዋለዉ ችልት በሰጠዉ ዉሳኔ በሞንትሪያል ፕሮቶኮል ቁጥር 4 አንቀጽ 26 ስር የተደነገገዉ የይርጋ ድንጋጌ ባለመሆኑ የይርጋ መቃወሚያ ዉድቅ መደረጉም ሆነ የተወሰነዉ ካሳ በፕሮቶኮለ አንቀጽ 22(2/ሀ) እና በንግድ ሕጉ አንቀጽ 683/1 መሰረት ተገቢ ነዉ በማለት የስር ፍርድ ቤትን ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል። አመልካች በቀን 14/06/2011 ዓ/ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረበዉም በስር ፍርድ ቤቶች በተሰጡ ዉሳኔዎች መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን ይዘቱ በአጭሩ የሚከተለዉ ነዉ።
ተጠሪ በ14 ቀን ዉስጥ የደረሰበትን ጉዲት ለአመልካች በጽሁፍ ያላሳወቀ በመሆኑ ክስ የማቅረብ መብቱ በይርጋ ቀሪ ሆኗል በሚል በሞንትሪያል ፕሮቶኮል ቁጥር 4 አንቀጽ 26.2 እና 26.4 ስር የተደነገገዉን ይርጋ ተጠቅሶ የቀረበዉ መቃወሚያ ዉድቅ መደረጉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ። እንዱሁም በሞንትሪያል ፕሮቶኮል ቁጥር 4 አንቀጽ 11 መሰረት የጉዞ ሰነድ (Air Way Bill) በተዋዋዮች መካከል ላለዉ ግንኙነት ዉል መኖሩን የሚያረጋግጥ ሰነድ እንደሆነ ስለተደነገገ ከዚህ ዉጭ የሚቀርብ ማንኛዉም ሰነድ ተቀባይነት ስለማይኖረዉ የስር ፍርድ ቤቶች ተጠሪ ያቀረበዉን ላላ ሰነድ መሰረት በማድረግ ካሳ መወሰናቸዉ፤ ተጠሪ በእቃዉ ላይ የተለየ ፍላጎት እንዲለዉ ያልገለጸና ተጨማሪ ክፍያ ከፍል የልዩ እቃ ዋጋ መግለጫ ባለመፈጸሙ የአየር ጉዞ ሰነደ ላይ ይሄዉ እንዲልተደረገ ለማመልከት የልዩ እቃ እና ዋጋ መግለጫ አልተደረገም (No Value Declared/NVD) ተብል እንደተጻፈበት ተጠሪ ከማመኑም በተጨማሪ ሰነደም ይህንኑ የሚያሣይ ነዉ። በመሆኑም የተጓጓዙት እቃዎች ክብደታቸዉ 4343 ኪል ግራም ከሆኑት ዉስጥ 48 ጥቅል(ፓላት) ዉስጥ 1 ጥቅል (ፓላት) መለዋወጫ መበላሸቱ(መጥፊቱ) ስለተረጋገጠ 4343 ኪል ግራም ለ48 ጥቅል(ፓላት) ሲካፈል የአንድ ጥቅል ክብደት 90.48 ኪል ግራም ስለሚሆን ይህም በወቅቱ በነበረዉ የኢትዮጵያ ብር ምንዛሬ በብር 20.00 ሲባዛ ብር 36,192.00 ስለሆነ በዋርሶዉ ስምምነት አንቀጽ 22.2/ለ እና ከዚህ በፉት የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/፣144915 ላይ በተመሳሳይ ጉዲይ በሰጠዉ ትርጉም መሰረት የስር ፍርድ ቤቶች ዉሳኔዎች ተሻሽል ይወሰንልኝ በማለት በመጠየቅ አቤቱታዉን አቅርቧል።
የሰበር አጣሪ ችልት የሰበር አቤቱታዉን እና በሥር ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ዉሳኔዎችን መርምሮ የስር ፍርድ ቤቶች ዉሳኔዎች አግባብነት ከዋርሶዉ ስምምነት አንጻር ለማጣራት ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ እና ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡ ትእዛዝ ሰጥቷል።
ተጠሪ በቀን 09/09/2011 ዓ.ም በተጻፈ መልሱ ተጠሪ የጉዲቱን ልክ በበቂ የሰነድ ማስረጃ ማስረዲቱን፤የአየር ጭነት ማዘዣ ሰነድ (Air Way Bill) ላይ የእቃዉን መጠን እና ምንነት ተጠቅሶ በማስረጃነት ያቀረባቸዉን ሰነድች የስር ፍርድ ቤቶች መርምረዉ ክስ የቀረበበት ገንዘብ ከእቃዉ ዋጋ ጋር እኩል መሆኑን አረጋግጠዉ የሰጡት ዉሳኔዎች አግባብነት ያላቸዉ እንደሆነ፤ አመልካች እንዲለዉ የፕሮቶኮል ቁጥር 4 አንቀጽ 22(2/ለ) ተፈጻሚነት አለዉ ቢባል እንኳን አመልካች እየጠየቀ ባለዉ መሰረት የካሳ መጠኑ ኪል ግራምን መሰረት አድርጎ በቁርጥ ለማስላት የሚያስፈልጉት መስፈርቶች በሙለ አልተሟለም።ምክንያቱም አመልካች በዚሁ የማሻሻያ ፕሮቶኮል ለመጠቀም ያስችለዉ ዘንድ በዚሁ ዉል ላይ የተጠቀሰዉ የተጨማሪ ክፍያ(Supplementary Fee) ለጉዲዩ መነሻ ለሆነዉ ካርጎ ተፈጻሚነት ያለዉ መሆኑንና ይኸዉ ክፍያ አለመፈጸሙን አመልካች ማስረዲት እያለበት ከዚህ አኳያ ያለበትን የማስረዲት ግዳታዉን አልተወጣም። ስለሆነም አመልካች በፕሮቶኮል ቁጥር 4 አንቀጽ 22(2/ለ) ስር የሰፈረዉን የማስረዲት ሸክም ያልተወጣ በመሆኑ አመልካች ያቀረበዉ አቤቱታ ዉድቅ ተደርጎ የስር ፍርድ ቤቶች ዉሳኔ ይጽናልኝ በማለት ተከራክሯል።
አመልካች በቀን 06/10/2011 ዓ/ም የተጻፈ የመልስ መልስ በማቅረብ ክርክሩን በማጠናከር ተከራክሯል።
ከዚህ በላይ የተመዘገበዉ የግራ ቀኝ ክርክርና በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ዉሳኔዎች ይዘት ሲሆን እኛም ለአከራካሪዉ ጉዲይ ተፈጻሚነት ያለዉ የትኛዉ የሕግ ማእቀፍ ነዉ? አመልካች በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ያነሳዉ መከራከሪያ መታለፈ በአግባቡ ነዉ ወይ? መቃወሚያዉ መታለፈ አግባብ ነዉ የሚባል ከሆነና አመልካች ለደረሰዉ ጉዲት ኃላፉ ነዉ የሚባል ከሆነ ለተጠሪ ምን ያህል ካሳ በምን አግባብ ተሰልቶ ሉከፈለዉ ይገባል? ከሚለ ጭብጦች አንጻር በስር ፍርድ ቤቶች በተሰጡ ዉሳኔዎች የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ መርምረናል።
ከክርክሩ እንደተረዲነዉ ተጠሪ የኢንሽራንስ ሽፊን የተሰጠዉ ንብረትነቱ የገደብ ኢንጂነሪንግ ኃላ/የተ/የግ/ማኅበር የሆኑ የጆንደር የእርሻ ትራክተር የተለያዩ 48 ፓላት መለዋወጫዎች በአመልካች አየር መንገድ አማካኝነት በእቃ ጭነት (Cargo) መልክ ተጭኖ ከደቡብ አፍሪካ ወደ አዱስ አበባ ሲጓጓዝ ቁጥራቸዉ 144 የሆኑ መለዋወጫዎች በዝናብና በፀሐይ በመበላሸታቸዉ እንዱሁም ብዛታቸዉ 18 የሆኑት ደግሞ በመጥፊታቸዉ ተጠሪ ለደንበኛዉ በኢንሹራንስ ዉለ መሰረት የከፈለዉ ብር 210,942.64 በአሁን አመልካች እንዱተካለት እንዱወሰንለት ዲኝነት ጠይቋል። የአሁን አመልካች በበኩለ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ባነሳዉ ክርክር ለጉዲዩ ተፈጻሚነት ያለዉ ሕግ የዋርሶዉ ስምምነት ለማሻሻል የወጣዉ ሞንትሪያል ፕሮቶኮል ቁጥር 4 ስለሆነ በዚህ ፕሮቶኮል አንቀጽ 26.2 እና 26.4 መሰረት ተጠሪ በ14 ቀን ዉስጥ የደረሰበትን ጉዲት ለአመልካች በጽሁፍ ያላሳወቀ በመሆኑ ክስ የማቅረብ መብቱ በይርጋ ቀሪ ሆኗል በሚል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ከማቅረቡም በተጨማሪ በፍሬ ነገር ረገድም አመልካች ለደረሰዉ ጉዲት ኃላፉነት አለበት የሚባል ከሆነ ተጠሪ በእቃዉ ላይ የተለየ ፍላጎት እንዲለዉ ያልገለጸና ተጨማሪ ክፍያ ከፍል የልዩ እቃ ዋጋ መግለጫ ባለመፈጸሙ የአየር ጉዞ ሰነደ ላይ ይሄዉ እንዲልተደረገ ለማመልከት የልዩ እቃ እና ዋጋ መግለጫ አልተደረገም (No Value Declared/NVD) ተብል ስለተገለጸ መበላሸቱ(መጥፊቱ) የተረጋገጠዉ የእቃ ክብደት 90.48 ኪል ግራም ስለሚሆን ይህም በወቅቱ በነበረዉ የኢትዮጵያ ብር ምንዛሬ በብር 20.00 ሲባዛ 36,192.00 ስለሆነ በዋርሶ ስምምነት አንቀጽ 22.2/ለ ለተጠሪ ሉከፈለዉ የሚገባዉ ብር 36,192.00 ነዉ በማለት ተከራክሯል። የስር ፍርድ ቤቶች ከዚህ አኳያ የአሁን አመልካች ያቀረባቸዉን መከራከሪያዎች ባለመቀበል ተጠሪ ባቀረበዉ ክስ መሰረት የዋርሶ ስምምነት እና የሞንትሪያል ፕሮቶኮል ቁጥር 4 ድንጋጌዎችን በመጥቀስ በክሱ መሰረት አመልካች ለተጠሪ ካሳ እንዱከፍል ወስነዋል።
በመጀመሪያም ለአከራካሪዉ ጉዲይ ተፈጻሚነት ያለዉ የትኛዉ የሕግ ማእቀፍ ነዉ? የሚለዉን ጭብጥ እንደመረመርነዉ ለክሱ መነሻ የሆነዉ ጉዲይ በአመልካች አየር መንገድ ከደቡብ አፍሪካ በእቃ ጭነት (Cargo) መልክ ተጭኖ ተጓጉዞ ወደ አዱስ አበባ በመጣ የተጠሪ ደንበኛ ንብረት በሆኑ እቃዎች ላይ የደረሰ ጉዲት ነዉ በሚል የተጠየቀ ካሳ መሆኑን ክርክሩ ያሳያል።አመልካች ለክርክሩ ተፈጻሚነት ያለዉ ሕግ በ1955 የወጣዉ የዋርሶ ስምምነትና ይህንን ስምምነት ለማሻሻል የወጣዉ ሞንትሪያል ፕሮቶኮል ቁጥር 4 ነዉ በሚል ያሰማዉን ክርክር የስር ፍርድ ቤቶችም ተቀብለዉ እንዚህን ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ለዉሳኔዎቻቸዉ መሰረት አድርገዋል።
ሆኖም ዓለም አቀፍ የአየር ጉዞ (INTERNATIONAL CARRIAGE BY AIR) የሚመለከተዉ እ.ኤ.አ.
በ1929 የወጣዉ የመጀመሪያዉ የዋርሶዉ ቃል ኪዲን፣ በተከታታይ እ.ኤ.አ. በ1955 በወጣዉ የሄግ ፕሮቶኮል (the 1955 Hague Protocol)፣ እ.ኤ.አ በ1961 በወጣዉ የጓድአላጃራ ተጨማሪ ቃል ኪዲን (the Guadalajara Supplementary Convention of 1961) እ.ኤ.አ በ1971 በወጣዉ የጓትማላ ከተማ ፕሮቶኮል(1971 Guatemala City Protocol)፣ እ.ኤ.አ. በ1975 በወጡ ቁጥር 1፣2፣እና 3 የሞንትሪያል ፕሮቶኮልች (Montreal Protocols 1, 2 and 3 of 1975) እና እ.ኤ.አ በ1975 በወጣዉ ሞንትሪያል ፖሮቶኮል ቁጥር 4 (1975 Montreal Protocol number 4) በተለያየ ሁኔታ እየተሻሻለና እየተለወጠ ከፕሮቶኮልቹ ጋር ጎን ለጎን ተፈጻሚ ሲሆኑ የቆዩ ዓለም አቀፍ የአየር ጉዞ የሕግ ማእቀፍች እንደሆኑ ይታወቃል። እነዚህ ዓለም አቀፍ የአየር ጉዞ የሕግ ማእቀፍች ወጥነት የላላቸዉና ተበታትነዉ የሚገኙ በመሆናቸዉ የአጓጓዦችንና የተጠቃሚዎችን መብትና ጥቅም በሚዛናዊነት እና ፍትሐዊነት ሉያስከብር የሚችል በዓለም አቀፍ ደረጃ ተፈጻሚ የሚሆን የተዋሃደ ዘመናዊ ዓለም አቀፍ ሕግ ማዉጣት በማስፈለጉ ዓለም አቀፍ የአየር ትራንስፖርት የሚገዛባቸዉን ደንቦች ለማዋሃድ ሞንትሪያል ቃልኪዲን ተብል የሚታወቅ እ.ኤ.አ. ሜይ 28 ቀን 1999 (Montreal Convention of 1999) በሞንትሪያል ተፈርሞ እ.ኤ.አ. ከኖቬምበር 04 ቀን 2003 ዓ/ም ጀሞሮ ተፈጻሚ እንዱሆን ተደርጓል። አገራችንም በዚህ ቃል ኪዲን አንቀጽ 57(ሀ እና ለ) የተደነገገዉን ባለመቀበል ታቅቦ(Reserevation) በማስመዝገብ ቃልኪዲኑን በአዋጅ ቁጥር 820/2006 መሰረት አጽድቃ ከየካቲት 10 ቀን 2006ዓ/ም ጀምሮ ተፈጻሚ እንዱሆን አድርጋለች። ስለሆነም በተያዘዉ ጉዲይ ከክርክሩ እንደተረዲነዉ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ጉዲይ በዓለም አቀፍ የአየር ትራንስፖርት በአመልካች አየር መንገድ አማካኝነት ተጭኖ ሲጓጓዝ በነበረ የተጠሪ ደንበኛ እቃ ላይ ጉዲት ደረሰ የተባለዉ ሞንትሪያል ቃልኪዲን 1999 በአገራችን ጸድቆ ተፈጻሚ እንዱሆን ከተደረገ በኋላ በመሆኑ ለጉዲዩ ተፈጻሚነት ያለዉ የሕግ ማእቀፍ በስር ፍርድ ቤቶች የተጠቀሰዉ የሞንትሪያል ፖሮቶኮል ቁጥር 4 ሳይሆን የሞንትሪያል ቃልኪዲን 1999(ከዚህ በኋላ ቃልኪዲን ተብል የሚጠቀስ) በመሆኑ የስር ፍርድ ቤቶች ተፈጻሚነት የላላቸዉን ተጠቃሾቹን ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ለዉሳኔያቸዉ መሰረት ማድረጋቸዉ ስህተት መሆኑን ማረጋገጥ ችለናል።
አመልካች በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ያነሳዉ መከራከሪያ መታለፈ በአግባቡ ነዉ ወይ? በሚል የተያዘዉን ሁለተኛዉን ጭብጥ እንደመረመርነዉ ለጉዲዩ ተፈጻሚነት ባለዉ የሞንትሪያል ቃልኪዲን 1999 አንቀጽ 29 ስር በተደነገገዉ መሰረት በዓለም አቀፍ የአየር ትራንስፖርት ተጭኖ በሚጓጓዝ እቃ (cargo) ላይ ከደረሰ ጉዲት ጋር በተያያዘ ቃልኪዲኑን ወይም ዉልን ወይም ከዉል ዉጭ የመነጨ ኃላፉነትን መሰረት በማድረግ ክስ የሚያቀርብ ማንኛዉም ሰዉ በቃልኪዲኑ የተደነገጉ ሁኔታዎችን እና የኃላፉነት ወሰንን መሰረት በማድረግ ክሱን ማቅረብ አለበት። በቃል ኪዲኑ ከተጠቀሱት ሁኔታዎች መካከል አንደ በአይሮፕላን ተጭኖ ሲጓጓዝ በነበረ እቃ (Cargo) ላይ የደረሰ ጉዲት ምክንያት በማድረግ ካሳ ከመጠየቁ በፉት እቃዉን ከተረከበበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 14 ቀን ዉስጥ ቅሬታ ወይም አቤቱታ(complaint) በጽሁፍ ለአጓጓዡ ማቅረብ እንዲለበትና በዚህ ጊዜ ቅሬታዉን ወይም አቤቱታዉን(complaint) ማቅረብ ካልቻለ ጊዜዉ ያለፈበት በመታለለ ምክንያት መሆኑን ካላስረዲ በስተቀር በአጓጓዡ ላይ ክስ መመስረት እንደማይችል በቃል ኪዲኑ አንቀጽ 31(2-4) ስር ተደንግጓል።
አመልካች ከዚህ ጋር በማያያዝ የተጠሪ ክስ የማቅረብ መብት በይርጋ ይታገደል በሚል መቃወሚያ በማቅረቡ የስር ፍርድ ቤቶች ይህ መከራከሪያ ይርጋን የሚመለከት ካለመሆኑም በተጨማሪ ክሱ 2 ዓመት ሳያልፍ የቀረበ በመሆኑ ክሱ በይርጋ አልታገደም በሚል የአመልካችን መቃወሚያ ዉድቅ አድርገዋል። ሆኖም የስር ፍርድ ቤቶች መቃወሚያዉ በቀጥታ ከይርጋ ጋር የተያያዘ አይደለም በሚል መወሰናቸዉ ስህተት ባይሆንም በቃል ኪዲኑ አንቀጽ 31(2-4) ስር በተደነገገዉ አግባብ የተጠሪ ደንበኛ በእቃዉ ላይ የደረሰዉን ጉዲት በጽሁፍ በ14 ቀን ዉስጥ ለአጓጓዡ (ለአመልካች) ማሳወቅ አለማሳወቁን የስር የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር በመስማት እንዱሁም አስፈላጊ ከሆነም ፍሬ ነገሩን በማስረጃ በማረጋገጥ መወሰን ሲገባዉ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ጉዲዩን በይግባኝ ሲያይ በዚህ አግባብ ክርክሩ ተጣርቶ እንዱወሰን ማድረግ ሲገባዉ የሁኔታዉ መሟላት ክስ ለማቅረብ ብቁ የሚያድርግ ቅደመ ሁኔታ ሆኖ If no complaint is made within the times aforesaid no action shall lie against the carrier… በሚል በአስገዲጅነት ተደንግጎ እያለ መከራከሪያዉን ከይርጋ ጋር በማያያዝ የይርጋ ጊዜዉ አላለፈም ከሚል አቅጣጫ ብቻ በማየት ማለፊቸዉ ቃል ኪዲኑ የዘረጋዉን የክስ አቀራረብ ስርዓት ያልተከተለ በመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ።
በተጨማሪም ከላይ እንደተመለከተዉ አመልካች በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ያነሳዉ መከራከሪያ ከላይ በተገለጸዉ መሰረት ተጣርቶ ተጠሪ ክስ ለማቅረብ በቃልኪዲኑ በቅድመ ሁኔታነት የተደነገገዉን ያሟላል ተብል መቃወሚያዉ ዉድቅ ተድርጎ በእቃዉ ላይ ለደረሰዉ ጉዲት እና ለጠፊዉ እቃ አመልካች በቃል ኪዲኑ መሰረት ካሳ የመክፈል ኃላፉነት አለበት የሚባል ከሆነ ካሳ የመክፈል ኃላፉነት መጠን እና ካሳ የሚሰላበት መንገድ በመርህ ደረጃ በቃልኪዲኑ አንቀጽ 22(3) ስር በተደነገጉት ሁኔታዎች መሰረት ላሆን ይገባል። በዚህ አግባብ የእቃዉ ባለቤት ወይም የተጠሪ ደንበኛ ወይም በተያዘዉ ጉዲይ የእቃዉን ላኪ ወይም ባለቤት በመተካት የቀረበዉ የአሁን ተጠሪ እቃዉን በአየር መንገደ ጭኖ እንዱያጓጉዝ ለአመልካች እቃዉን ሲያስረክብ በእቃዉ ላይ ያለዉን ልዩ ጥቅም በመግለጽ ተገቢዉን ተጨማሪ ዋጋ መከፈለን ካላስረዲ በስተቀር አመልካች ካሳ ለመክፈል የሚገደደዉ በጠፊዉ ወይም ጉዲት ለደረሰበት እቃ በአንድ ኪል ግራም 17 ስፔሻል ድሮዊንግ ራይት በመክፈል እንደሆነ በግልጽ ተደንግጓል።በእቃዉ ላይ ልዩ ጥቅም መኖሩ ተገልጾ ተጨማሪ ክፍያ እንዱከፈል መደረጉ ከተረጋገጠ የደረሰዉ ተጨባጭ ጉዲት(actual damage) የእቃዉ ዋጋ ነዉ ተብል ከተገለጸዉ አጠቃላይ ዋጋ የሚበልጥ መሆኑ ካልተረጋገጠ በስተቀር የሚከፈለዉ ካሳ የእቃዉ ዋጋ ነዉ ተብል ከተገለጸዉ ሉበልጥ እንደማይችል ተደንግጓል። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በቃል ኪዲኑ አንቀጽ 22(4-6) የተጠቀሱት ተጨማሪ ሁኔታዎች በተሟለ ጊዜ በቃል ኪዲኑ አንቀጽ 22/3 ስር ከተደነገገዉ የካሳ ስላትና መጠን በተለየ ሁኔታ ተጨማሪ ካሳ ሉከፈል የሚችልበት ሁኔታ ተደንግጓል።
ከላይ ከተገለጸዉ አንጻር የስር ፍርድ ቤቶች የዋርሶዉ ስምምነት አንቀጽ 22(2/ሀ)ን በመጥቀስ እና ተጠሪ በማስረጃነት ያቀረባቸዉን እቃዉ የተገዛባቸዉን ዋጋ የሚያሳዩ ሰነድች መሰረት በማድረግ አመልካች ለተጠሪ የእቃዉን ዋጋ ብር 210,942.64 እንዱከፍል የወሰኑበት አግባብ ሲታይ በመጀመሪያ ደረጃ የዋርሶዉ ስምምነት ከላይ በተገለጸዉ መሰረት በሞንትሪያል ቃል ኪዲን 1999 የተተካ ከመሆኑም በተጨማሪ የዋርሶዉ ስምምነት አንቀጽ 22(2/ሀ) ካርጎን የሚመለከት ባለመሆኑ ለተያዘዉ ጉዲይ ተፈጻሚነት ያለዉ አይደለም። በልላ በኩል ካሳ የወሰኑበት አግባብ አና የወሰኑት የካሳ መጠን ከላይ ከተጠቀሱት የሞንትሪያል ቃልኪዲን 1999 ድንጋጌዎች አንጻር ሲታይ የተጠሪ ደንበኛ ለአመልካች እቃዉን ሲያስረክብ በእቃዉ ላይ ያለዉን ልዩ ጥቅም በመግለጽ ተጨማሪ ክፍያ መክፈል አለመክፈለን በተመለከተ ግራ ቀኝ ክርክር አድርገዉ የተረጋገጠዉ ፍሬ ነገር ምንነት፣የእቃዉ ኪል ግራም ምን ያህል እንደሆነ ፣ በቃልኪዲኑ አንቀጽ 22/3 ስር በተደነገገዉ አግባብ በአንድ ኪል ግራም በ17 ስፔሻል ድሮዊንግ ራይት ተሰልቶ ወደ አሜሪካን ድላር እና ወደ ኢትዮጵያ ብር የተለወጠበት የምንዛሪ ምጣኔ በቃልኪዲኑ ላይ በተመለከተዉ አግባብ ስለመሆኑ በግልጽ በማሳየት የተሰጡ ዉሳኔዎች ባለመሆናቸዉ በቃልኪዲኑ በግልጽ ስለካሳ አወሳሰን እና መጠን በቅደምተከተል የተደነገጉትን ሁኔታዎችን ያልተከተለ በመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ።
እንዱሁም የተጠሪ ደንበኛ ለአመልካች እቃዉን ሲያስረክብ በእቃዉ ላይ ያለዉን ልዩ ጥቅም መግለጽ አለመግለጹና ተጨማሪ ክፍያ መክፈል አለመክፈለ በጭብጥነት ተይዞ ክርክር ተደርጎበት በማስረጃ ሳይረጋገጥ በቃልኪዲኑ በአንድ ኪል ግራም 17 ስፔሻል ድሮዊንግ ራይት ይከፈላል ተብል የተደነገገዉን በመተዉ የእቃዉ የግዥ ዋጋ መሰረት ተደርጎ አመልካች ካሳ እንዱከፍል ሲወስኑ የተከተለበት የክርክር አመራር በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ከቁጥር 246-248 ስር በተደነገገዉ መሰረት ተገቢዉን ጭብጥ ሳይዙና ከማስረጃ ወይም ከሕግ አንጻር ተገቢዉን ሳያረጋግጡ መወሰናቸዉን ስለሚያሳይ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ።ስለሆነም ተከታዩ ተወስኗል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 27/11/2009 ዓ/ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ዉሳኔ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 13/05/2011ዓ/ም የሰጠዉ ዉሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ተሽረዋል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መ/ በማንቀሳቀስ፡- 2.1. አመልካች በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ያነሳዉን መከራከሪያ በተመለከተ በሞንትሪያል ቃልኪዲን አንቀጽ 31(2-4) ስር በተደነገገዉ አግባብ የተጠሪ ደንበኛ በእቃዉ ላይ የደረሰዉን ጉዲት በጽሁፍ በ14 ቀን ዉስጥ ለአጓጓዡ (ለአመልካች) ማሳወቅ አለማሳወቁን በተመለከተ የግራ ቀኙን ክርክር ከፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 245/1 አንጻር በመስማትና በማስረጃ የሚረጋገጥ ነገር ሲኖር በማስረጃ እንዱረጋገጥ በማድረግ ተገቢዉን እንዱወስን ጉዲዩን መልስናል።
2.2 . ከላይ በተራ ቁጥር 2.1. ስር በተወሰነዉ መሰረት ተጣርቶ ተጠሪ ክስ ለማቅረብ በሚያስችለዉ ሁኔታ በቃልኪዲኑ በቅድመ ሁኔታነት የተደነገገዉን መስፈርት አሟልቷል ተብል አመልካች በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ያነሳዉ መከራከሪያ ዉድቅ የሚያደርግ ከሆነ ፍሬ ነገሩን በተመለከተ ከላይ በፍርደ ሀተታ ከገጽ 6-7 በተመለከተዉ አግባብ የአመልካችን ኃላፉነት እና ካሳ መጠን በተመለከተ ቃልኪዲኑን መሰረት ያደረገ ዉሳኔ እንዱሰጥ በ/ፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 341/1 መሰረት ጉዲዩን መልሰናል።
No topics extracted.