የገንዘብ መጠኑ እና ቀን ሳይፃፍበት በቼክ አውጭው ተፈርሞ የተሰጠ ቼክ (Blank Cheque) ቀንና የገንዘብ መጠን ተሞልቶ ለከፊዩ ባንክ በቀረበ ጊዜ በንግድ ህጉ አንቀጽ 827 እና 828 ስር አንድን ሰነድ ቼክ የሚያሰኙ መገለጫዎችን ስለሚያሟለ እንድ ቼክ የሚቆጠሩ እና ህጋዊ ውጤት ያላቸው አቶ ሐበን ጉዕሽ እና ናይል ፔትሮሉየም ካምፓኒ ሉሚትድ ኢትዮጵያ
No summary available.
የሰ/መ/ ጥቅምት 28 ቀን 2012 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ ተሾመ ሽፈራዉ ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግስቱ ነጻነት ተገኝ አመልካች፡- የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ተጠሪ፡- ሐበሻ ሲሚንቶ አክሲዮን ማኅበር መዝገቡ ተመርምሮ ከዚህ የሚከተለዉ የፍርድ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የኢንሽራንስ ዉል መጽናት ከሚጀምርበት ጊዜ እና ኢንሹራንስ ሰጪዉ መድን ከሚሆንበት አደጋ ጋር በተያያዘ የተደረገዉን ክርክር አስመልክቶ የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 26/04/2010 ዓ/ም የሰጠዉ የፍርድ ዉሳኔ እና ይህንን ዉሳኔ በመቃወም የቀረበዉን ይግባኝ በመሰረዝ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 19/06/2011 ዓ/ም የሰጠዉ ትእዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ተብል የቀረበ ሲሆን በስር ፍርድ ቤት የተደረገዉ ክርክርና በቀን 08/07/2011 ዓ/ም ተጽፍ የቀረበዉ የሰበር አቤቱታ ይዘት ከዚህ የሚከተለዉ ነዉ።
በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በነበረዉ ክርክር የአሁን ተጠሪ ከሳሽ ሲሆን አመልካች ደግሞ ተከሳሽ ነበር። ተጠሪ በስር በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በቀን 14/03/2009 ዓ/ም ጽፍ ባቀረበዉ ክስ ከአመልካች የመድን ሽፊን ለሁለት የአለት መቆፈሪያ ማሽኖች(Rock Drilling Ring) ላይ በጦርነት፣በብጥብጥ፣ በሕዝባዊ አመጽን ጨምሮ በላልች በመደበኛነት የሚሰጡ ሽፊን ለመስጠት የአሁን አመልካች በቀን 21/08/2007 ዓ/ም የዋጋ ማቅረቢያ ልኮ በቀን 22/11/2007 ዓ/ም የኢንሹራንስ ዉል ቢዋዋለም በዋጋ ማቅረቢያዉ ላይ የተዘረዘረዉ የአደጋ አይነት በኢንሹራንስ ዉለ ላይ ባለመካተቱ በቀን 05/04/2008ዓ/ም በተፈጸመ የማሻሻያ (የሽፊን ማስፉያ/Extension) ዉል በጦርነት፣ በአድማ፣ በአመጽ እና ሆን ተብል (በተንኮል) ሳቢያ ለሚደርስ ጉዲት የአሁን አመልካች የመድን ሽፊን ለመስጠት እንደተስማማ እና የማራዘሚያ ዉለ ስምምነት ተፈጻሚነት የሚጀምረዉ ከግንቦት 19 ቀን 2007 ዓ/ም ጀምሮ እንዱሆን መስማማታቸዉን በመግለጽ በፉንፉኔ ዙሪያ በነበረዉ ሕዝባዊ አመጽ ምክንያት የመድን ሽፊን ከተገባላቸዉ 2 መቆፈሪያ ማሽኖች በአንደ ላይ በቀን 04/04/2008ዓ/ም ጉዲት ደርሶበት ጉዲቱ መድረሱን በማሳወቅ ጉዲት ለደረሰበት ማሽን መለዋወጫ ለመግዛት ብር 399,424.50 እንዱሁም ለእጅ ዋጋ ብር 31,289.00 በድምሩ ብር 430,713.70 እንዱከፈለዉ ዲኝነት በመጠየቅ ክስ መስርቷል።
የአሁን አመልካች ለክሱ በሰጠዉ መልስ የመድን ሽፊን የሚሰጠዉ ያልታወቀ አደጋ የሚደርስ ከሆነ ካሳ ለመክፈል በመሆኑ የማራዘሚያ ዉል ከመደረጉ በፉት በቀን 04/04/2008 ዓ/ም ጉዲት ስለደረሰ ጉዲቱ ከደረሰ በኋላ በተደረገ የመድን ዉል ካሳ ለመክፈል እንደማይገደድ፤ ዉል ተፈጻሚነት የሚኖረዉ ከተፈረመበት ጊዜ ጀምሮ በመሆኑና ወደኋላ ተመልሶ የማይሰራ በመሆኑ የዉል ማራዘሚያ የተደረገዉ ማራዘሚያ ከተደረገ በኋላ ጉዲት ቢደርስ ካሳ ለመስጠት መሆኑን፤ የአሁን ተጠሪ የማስፉያ ዉል ተፈርሞ እንዱሰጠዉ የጠየቀዉ በዋናዉ ዉል ማግለያዎች ፉደል "ቀ" ስር የተገለለትን ስጋቶች ሆኖ አመልካች በስህተት በዋና ዉል ማግለያዎች ፉደል "ቸ" ስር ለተገለለ ስጋቶች ሽፊን ስለሰጠና በሁለቱ መካከል ልዩነት ስላለ በተዋዋይ ወገኖች መካከል የሃሳብ ስምምነት የላለበትና በስህተት የተቋቋመ ዉል በመሆኑ አመልካች ይህንን ቢያዉቅ ኖሮ ዉል ዉስጥ ሉገባ ስለማይችል ዉለ ፈራሽ ስለሆነ ተከሳሽ ካሳ የመክፈል ኃላፉነት እንደላለበት፤በኦሮሚያ ክልል ፉንፉኔ ዙሪያ ከታህሳስ 4-6/2008 ዓ/ም ድረስ ተነስቶ የነበረዉና ጉዲት ያደረሰዉ ድርጊት የፖሉቲካ ተቃዉሞ አካል ስለሆነና ሽፊን የተሰጠዉ በመድን ገቢዉ ሰራተኞች የሚፈጠርን ብጥብጥ እንዱሁም በፊብሪካዉ አካባቢ ያለ ማህብረሰብ ክፍልች ከፊብሪካዉ ጋር ተያይዞ የጥቅም ጥያቄ/ተቃዉሞ/ ለማቅረብና ጫና ለመፍጠር የሚፈጠር አመጽ ለማለት እንጂ ብዙ ሕዝብ ቁጥር የተሳተፈበትን ሕዝባዊ አመጽ/ተቃዉሞን(popular uprising) በመድን ሽፊኑ የሚሸፈን አይደለም የሚለ መከራከሪያዎች እና የደረሰዉን ጉዲት ተጠሪ ካሳ እንዱከፈላቸዉ የጠየቁት ድረሰ ያለትን ጉዲት በገለልተኛ ገማች ሳያስገምቱ ከአንድ ድርጅት ብቻ በመጠየቅ ያቀረቡት የተጋነነ ነዉ በሚል መከራከሩን ከፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፍርድ ተረድተናል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የግራ ቀኝ ክርክር በመ/ ላይ በቀን 26/04/2010ዓ/ም በዋለዉ ችልት በሰጠዉ የፍርድ ዉሳኔ ግራ ቀኝ በቀን 05/04/2008 ዓ/ም የማርዘሚያ ዉል ያደረጉ ቢሆንም ከቀን 19/09/2007 ዓ/ም ጀምሮ ተፈጻሚ እንዱሆን ስለተስማሙ የንግድ ሕጉ አንቀጽ 659/1 ይህንነኑ ስለሚፈቅድ ከዚህ አኳያ የአሁን አመልካች ያቀረበዉ ክርክር ተቀባይነት እንደላለዉ፤የማራዘሚያ ዉል የተደረገዉ ዋናዉ ዉል ላይ በፕርፍርማዉ ላይ የተገለጸዉ በስህተት ሳይካተት በመቅረቱ በማካተት ለማሻሻል የተደረገ በመሆኑ ተፈጻሚነት የሚኖረዉ የመጀመሪያዉ ዉል ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ ላሆን እንደሚገባ፤ ተጠሪ የዉል ማርዘሚያ የጠየቀዉ ቀድሞ በፕርፍርማ ላይ የተገለጸዉ በዋናዉ ዉል ላይ ሳይገለጽ በመቅረቱ ምክንያት ለማካተት ታሳቢ በመሆኑ ማራዘሚያ ተጠይቆ በተጠሪ በተሞላ ጥያቄ ላይ "ቀ" ተብል የጠሞላ ሆኖ በተራዘመዉ ሰነድ ላይ በፉደል "ቸ" ላይ የተገለጸዉን ማግለያ በማሻሻል የተራዘመ ቢሆንም ይህም ከሀሳባቸዉ አንጻር ሲታይ የፉደል ስህተት ብቻ እንጂ መሰረታዊ ስህተት ካለመሆኑም በተጨማሪ በዚህ ስህተት ምክንያት ዉለ እንዱፈርስ ካለማድረጉም በተጨማሪ በዉለ ላይ አመልካች ብቻዉን መፈረም የሚችልበት አሰራር ቢኖርም በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1725/ለ፣1726 እና 1727(1 እና 2) ስር በተደነገገዉ መሰረት የኢንሹራንስ ዉል በጽሁፍ ተደርጎ በተዋዋይ ወገኖችና በሁለት ምስክሮች መፈረም የሚገባዉ ዉል ሆኖ እያለ በአመልካች ብቻ መፈረሙ ስለተረጋገጠ በሕግ ፉት የሚጸና ዉል አይደለም በሚል በማስፉያ ዉለ ላይ የተጠቀሱት ማግለያዎች የአሁኑን ተጠሪ(ከሳሽን) አያስገድደም በሚል በአንድ በኩል ከወሰነ በኋላ በልላ በኩል ደግሞ ተጠሪ ይህንን የማስፉያ ዉል መሰረት በማድረግ ያቀረቡትን ክርክር በመቀበል የአሁን አመልካች በማስፉያ ዉለ መሰረት በማሽኑ ላይ ለደረሰዉ ጉዲት ካሳ የመክፈል ኃላፉነት አለበት በማለት የመለዋወጫ ዋጋ ከተለያዩ ድርጅቶች ማቅረብ አለመቻለን ምክንያት በማድረግ ከደረሰዉ ጉዲት ጋር እኩል ሆኖ የሚመዛዘን ካሳ መወሰን አልተቻለም በማለት አመልካች ለተጠሪ ብር 400,000.00 ካሳ እንዱከፍል በርትእ መወሰኑን ከዉሳኔዉ ይዘት ተመልክተናል።
ከላይ በተገለጸዉ መሰረት በተሰጠ የፍርድ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት የአሁን አመልካች ይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ ቢያቀርብም ፍርድ ቤቱ በቀን 19/06/2011 ዓ/ም በሰጠዉ ትእዛዝ ይግባኙን ሰርዟል።
አመልካች የሰበር አቤቱታ ያቀረበዉ በዚህ መልኩ በተሰጠ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን ለተጠሪ የተሰጠዉ የመድን ሽፊን በአመጽ፣ በእርስ በእርስ ጦርነት፣ በአድማ፣በአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ፣በወታደራዊ አመጽ የሚመጡትን ማንኛዉንም ፖለቲካዊ ይዘት ባላቸዉ ምክንያቶች የሚደርስ ጉዲት እንደማይሸፍን በዉለ ማግለያ ፉደል "ቸ" እንደተመለከተ፤እንዱሁም በማስፉያ ዉለ አንቀጽ 2/ለ ስር እንዱገለል የተደረገ ምክንያት መሆኑን፤ ከዚህ አንጻር የቀረበዉን ክርክር የስር ፍርድ ቤት ጭብጥ ይዞ ሳይመረምርና ዉሳኔ ሳይሰጥ ማለፈን፤ የስር ፍርድ ቤት በህዝባዊ አመጽ የሚደርስ አደጋ በፕርፍርማዉ ላይ ተካቶ እያለ በዋናዉ ዉል ላይ ሳይካተት በመቅረቱ ስህተቱን ለማረም የማስፉያ ዉለ ስለተፈጸመ የማስፉያ ዉለ ተፈጻሚ ላሆን የሚገባዉ የመጀመሪያዉ ዉል ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ ነዉ ብል የወሰነዉ ፕርፍርማዉ የዉለ አካል ባልሆነበትና ፕርፍርማ የሚሰጠዉ የመድን ሽፊን አይነትና የእያንዲንደን ዋጋ ዝርዝር የሚገልጽ መግለጫ (offer) ብቻ መሆኑን ባለማገናዘብ መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት እንደሆነ፤ የስር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከተጠሪ ክርክር አንጻር የመድን ሽፊን ማስፉያዉ ዉል አመልካችና ተጠሪ መካከል የመጀመሪያዉ ዉል ሲቋቋም የተፈጠረዉን መሰረታዊ ስህተት ለማረም የተገባ ዉል ነዉ ብል ዉጤት እንዱኖረዉ ያደረገዉን ዉል በልላ በኩል ከአመልካች ክርክር አንጻር ደግሞ የማስፉያ ዉለ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1725/ለ፣ 1726 እና 1727(1 እና2) መሰረት ሁለቱም ተዋዋይ ወገኖች ሉፈርሙበት ሲገባ በዉል ማስፉያዉ ላይ በዉል ማስፉያዉ ላይ ተጠሪ ስላልፈረሙበት በተጠሪ ላይ አስገዲጅነት የለዉም ሲል መወሰኑ አንድን የሕግ ነጥብ ለተጠሪ ሲሆን የጸና የመድን ዉል ነዉ በማለት ለአመልካች ሲሆን ድግሞ የጸና አይደለም ሲል መወሰኑ ዉለ በመድን ሰጪዉ ከተፈረመበት በቂ ነዉ ተብል በሰበር መ/ ላይ የተሰጠዉን ትርጉም ጭምር ያላገናዘበ በመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መሆኑን፤ የመድን ዉለ ማስፉያ ዉል ወደ ኋላ ተመልሶ ይሰራል ሲል የንግድ ሕጉን አንቀጽ 659/1ን ጠቅሶ መወሰኑ መሰረታዊ የአተረጓጎም ስህተት መሆኑን፤ አደጋ ከደረሰ በኋላ የደረሰዉን አደጋ ለመሸፈን የሚሰጥ የመድን ሽፊን ፖሉስ በላለበት በተሰጠዉ ዉሳኔ እና ከካሳ አወሳሰን አኳያም በርትዕ መወሰኑ በንግድ ሕጉ አንቀጽ 665 እና 677 ስር የተደነገገዉን የሚጥስ በመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ሰህተት ተፈጽሟል ተብል እንዱታረም በመጠየቅ አቤቱታዉን አቅርቧል።
የሰበር አጣሪ ችልት የሰበር አቤቱታ እና በስር ፍርድ ቤት የተሰጠ ዉሳኔ መርምሮ አመልካች በተጠሪ ንብረት ላይ ለደረሰዉ ጉዲት ከዋናዉ የመደበኛ የመድን ሽፊን ዉልም ሆነ በማስፉያ ሽፊን ዉል ከታህሳስ 05 ቀን 2008ዓ/ም በተደረገዉ ዉል ሽፊን ላለመስጠት አግልየዋለሁ እያለ ኃላፉ ነህ የመባለን አግባብነት ከግራ ቀኙ ዉልና ከንግድ ሕጉ አንቀጽ 654 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች አንጻር ለማጣራት መዝገቡ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ እና ተጠሪ መልስ እንዱሰጥ ትእዛዝ ሰጥቷል።
ተጠሪ በቀን 23/11/2011 ዓ/ም የተጻፈ መልስ በማቅረብ አመልካች በቀን 05/04/2008 ዓ/ም ፈርሞ ለተጠሪ በሰጠዉ ዉል በአመጽ ድርጊት ለሚመጣ ዉድመት የመድን ሽፊን በመስጠቱና የሽፊኑ ተፈጻሚነት የሚጀምረዉ በዋናዉ ዉል ሉካተት የሚገባዉ ጉዲይ የነበረ ከመሆኑ አንጻር ወደኋላ ተመልሶ የመድን ሽፊን ዉለ ከተቋቋመበት ከቀን 01/09/2007 ዓ/ም ጀምሮ እንደሆነ በግልጽ ተጽፍና ተፈርሞ የተሰጠዉ ዉል መሆኑን፤ የኢንሽራንስ ዉል ሽፊን ወደፉት ለሚደርስ አደጋ የሚገባ(የሚሰጥ) ሽፊን ቢሆንም የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በንግድ ሕግ አንቀጽ 659/1 የተደነገገዉን በመጥቀስ ዉለ ወደኋላ ተመልሶ ይሰራል ሲል መወሰኑ አግባብ እንደሆነና በዚህ መሰረት እንዲይተረጎም የሚከለክል ሕግ እንደላለ፤ጉዲቱ የደረሰዉ ከቀን 04/04/2008ዓ/ም እስከ 06/04/2008ዓ/ም ድረስ በነበረዉ ሕዝባዊ አመጽ ምክንያት በመሆኑ ይህም በመድን ማስፉያ ዉለ የተሸፈነ ምክንያት መሆኑን፤አመልካች በስህተት የተዋዋለዉ ዉል የለም እንጂ በስህተት የተዋዋለዉ ዉል ቢኖር እንኳን ዉለን ያላስፈረሰ በመሆኑ ከዚህ አንጻር የስር ፍርድ ቤት የሰጠዉ ዉሳኔ ተገቢ እንደሆነ፤ እንዱሁም የካሳ መጠኑን በተመለከተ የስር ፍርድ ቤት ማስረጃዉ ከብቸኛ ማሽን አቅራቢ የቀረበ ማስረጃ ሆኖ እያለ ይህንን ማስረጃ ማለፈና ከተጠየቀዉ ካሳ ቀንሶ መወሰኑ ተገቢ አይደለም ልባል ከሚችል በስተቀር የመለዋወጫ ዋጋዉ የተጋነነ መሆኑን ለማስረዲት አመልካች ለስር ፍርድ ቤት ያቀረበዉ ማስረጃ የለም ተብል የሰበር አቤቱታዉ ዉድቅ ተደርጎ እንዱወሰን በመጠየቅ ተከራክሯል።
አመልካችም በቀን 23/01/2012 ዓ/ም የተጻፈ የመልስ መልስ በማቅረብ የሰበር አቤቱታዉን በማጠናከር ተከራክሯል።
የግራ ቀኝ ክርከር እና የክርክሩ አመጣጥ እንዱሁም በስር ፍርድ ቤት የተሰጠዉ ዉሳኔ ከላይ የተመለከተዉ ሲሆን እኛም የሚከተለትን ጭብጦች፡-
የዋናዉ ኢንሹራንስ ዉል ሽፊን ማስፉያ (Extension) ዉል ወደ ኋላ ተመልሶ ይሰራል ተብል መወሰኑ አግባብ ነዉ ወይ ?
የዋናዉ ኢንሹራንስ ዉል ሽፊን ማስፉያ (Extension) ዉል ወደ ኋላ ተመልሶ ይሰራል የሚባል ከሆነ በሽፊን ማስፉያ (Extension) ዉለ በተመለከተዉ ማግለያ መሰረት ሲታይ የአሁን አመልካች ለደረሰዉ ጉዲት የመድን ካሳ ይክፈል መባለ አግባብ ነዉ ወይስ አይደለም ?
የሚለትን ጭብጦች በመያዝ መዝገቡን እንደሚከተለዉ መርምረናል።
የመጀመሪያዉን ጭብጥ እንደመረመርነዉ ንብረትነታቸዉ የተጠሪ በሆኑ ሁለት የአለት መቆፈሪያ ማሽኖች(Rock Drilling Ring) ላይ በኢንሹራንስ ዉለ ላይ በተገለጹ አደጋ ምክንያቶች ለሚደርስ ጉዲት የመድን ካሳ ለመክፈል አመልካች ከተጠሪ ጋር ዋናዉን የኢንሹራንስ ዉል ግራ ቀኝ የተዋዋለት በቀን 22/11/2007 ዓ/ም በተጻፈ ዉል መሆኑን በስር ፍርድ ቤት ያደረጉት ክርክር ያሳያል።በዚህ በዋናዉ የኢንሹራንስ ዉል ላይ የተገለለትን የአደጋ ምክንያቶች በማካተት የመድን ሽፊን ማስፉያ (Extension) ዉል በአመልካች ተፈርሞ የተሰጠዉ በቀን 05/04/2008 ዓ/ም መሆኑ በግራ ቀኝ የታመነና በዉለ ማስረጃነትም በሥር ፍርድ ቤት የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነዉ። የመድን ሽፊን ማስፉያ ዉለ ላይ አመልካች ብቻ መፈረማቸዉን በተመለከተ የተነሳዉን ክርክር አስመልክቶ የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በሰጠዉ ፍርድ ላይ በዉለ ላይ አመልካች ብቻዉን መፈረም የሚችልበት አሰራር ቢኖርም በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1725/ለ፣1726 እና 1727(1 እና 2) ስር በተደነገገዉ መሰረት የኢንሹራንስ ዉል በጽሁፍ ተደርጎ በተዋዋይ ወገኖችና በሁለት ምስክሮች መፈረም የሚገባዉ ዉል ሆኖ እያለ በአመልካች ብቻ መፈረሙ ስለተረጋገጠ በሕግ ፉት የሚጸና ዉል አይደለም በሚል በማስፉያ ዉለ ላይ የተጠቀሱት ማግለያዎች የአሁኑን ተጠሪ(ከሳሽን) አያስገድደም ሲል የደረሰበትን ድምዲሜ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰበር/መ/ በቀን 16 ቀን 1999 ዓ.ም ከተሰጠዉ አስገዲጅ ትርጉም አንጻር እንደመረመርነዉ የኢንሹራንስ ውል የአጻጻፍ ፍርምን በሚመለከት ገዥው ሕግ የፍትሀብሓር ሕጉ አንቀጽ 1725 ቢሆንም በዚህ ህግ መሰረት የአጻጻፍ ፍርሙን መከተል የሚጠበቅባቸው ለብዙ ዘመን (for a long period of time) የሚቆይ የኢንሹራንስ ዉል ሲሆን ብቻ እንደሆነና ለአጭር ጊዜ የሚደረጉ የኢንሹራንስ ውልች የህጉን አንቀጽ 1725 እና 1727ን በማጣቀስ በጽሁፍ አልተደረጉም፣ በተዋዋየች አልተፈረሙም ፣በሁለት ምስክርም አልተረጋገጡም በማለት ህጋዊ ውጤት እንዲይኖራቸው ማድረግ የሕጉን ዓላማ ግምት ውስጥ ያስገባ አተረጓጎም አይደለም በሚል ትርጉም የሰጠ በመሆኑ በተያዘዉም ጉዲይም ግራ ቀኝ የተዋዋለት ዋናዉ የመድን ዉል የተፈጸመበትን ቀን መነሻ በማድረግ ስናይ የኢንሹራንስ ዉለ ለአጭር ጊዜ የተደረገ ነዉ ልባል የሚችል ከመሆኑ አኳያ ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠዉ ዉሳኔ በአዋጅ ቁጥር 454/97 አስገዲጅ ትርጉም በመሆኑ የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ይህንን ትርጉም ለዚሁ ተመሳሳይ ጉዲይ ተፈጻሚ ማድረግ ሲገባዉ የመድን ሽፊን ማስፉያ ዉለ በተጠሪ አለመፈረሙን ምክንያት በማድረግ የመድን ሽፊን ማስፉያ ዉለ በህግ ፉት የሚጸና አይደለም ሲል መደምደሙ መሰረታዊ የህግ ስህተት በመሆኑ ይህ ምክንያት ዉለ በሕግ ፉት እንዲይጸና አያደርግም ብለናል።
ወደያዝነዉ ጭብጥ ስንመለስ የመድን ሽፊን ማስፉያ (Extension) ዉል በአመልካች ተፈርሞ የተሰጠዉ በቀን 05/04/2008 ዓ/ም መሆኑ አላከራከረም። ተጠሪ ወይም የስር ከሳሽ ኢንሹራንስ በተገባለት ማሽን ላይ ጉዲት ደርሶበታል ብል በክሱ የጠቀሰበት ቀን ታህሳስ 04 ቀን 2008 ዓ/ም መሆኑን የስር ፍርድ ቤት ፍርድ ይዘት ያሳያል። ተጠሪ በማሽኑ ላይ ጉዲት ያደረሰዉ ምክንያት(አደጋ) የኢንሹራንስ ካሳ የሚያስከፍል ምክንያት ነዉ ሲል ለክሱ መሰረት ያደረገዉ ዋናዉን የኢንሹራንስ ዉል ሳይሆን ዋናዉን የኢንሹራንስ ዉል በማሻሻል በቀን 05/04/2008 ዓ/ም ተፈርሞ የተሰጠዉን የመድን ሽፊን ማስፉያ ዉል ነዉ።በንግድ ሕጉ አንቀጽ 659/1 ስር በተደነገገዉ መሰረት ተቃራኒ ዉሳኔ ከላለ በቀር የኢንሹራንስ ዉል ፖሉሲዉ ከተፈረመበት ጊዜ አንስቶ የጸና እንደሚሆን ተደንግጓል። በተያዘዉ ጉዲይ የመድን ሽፊን ማስፉያ ዉል ወይም በዋናዉ ዉል ማሻሻያ ላይ የመድን ሽፊኑ ተፈጻሚ የሚሆነዉ ዋናዉ ዉል ከተደረገበት ከቀን 22/11/2007 ዓ/ም ወይም በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፍርድ ላይ ከተጠቀሰዉ ከግንቦት 19 ቀን 2007 ዓ/ም ጀምሮ ነዉ ተብል በተዋዋይ ወጎኖች በግልጽ የተደረገ ስምምነት የለም። በዚህ አግባብ የመድን ሽፊን ማስፉያ ዉለ ወደኋላ ተመልሶ እንዱሰራ ተዋዋዮች በዉላቸዉ ላይ በግልጽ ባልወሰኑበት ሁኔታ የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የመድን ሽፊን ማስፉያ ዉለ የተደረገበት ዓላማ በዋናዉ ዉል ላይ በስህተት ሳይካተት የቀረዉን የአደጋ ምክንያት ለማካተት የተደረገ ማራዘሚያ(ማስፉያ) ዉል ስለሆነ ወደኋላ ተመልሶ ዋናዉ የኢንሹራንስ ዉል ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ ተፈጻሚ ላሆን ይገባል ሲል የሰጠዉ ትርጉም በንግድ ሕጉ አንቀጽ 659/1 ስር በግልጽ የተደነገገዉን የሚቃረን በመሆኑ መሰረታዊ የህግ አተረጓጎም ስህተት ነዉ።
በተጨማሪም በንግድ ሕጉ አንቀጽ 654 ስር በተደነገገዉ ትርጓሜ መሰረት የኢንሹራንስ ዉል በዉለ የተመለከተዉ አደጋ በደረሰ ጊዜ ኢንሹራንስ ሰጪዉ ኢንሹራንስ ለገባዉ ሰዉ የተወሰነ ገንዘብ ለመክፈል ግዳታ የሚገባበት ዉል ነዉ።ይህ ትርጉም እንደሚያሳየዉ የኢንሹራንስ ዉል የሚገባዉ ገና ያልደረሰ ወይም ወደፉት የሚደርስ በዉለ ላይ የተመለከተዉ አደጋ የሚያደርሰዉን ጉዲት ኢንሹራንስ ሰጪዉ እንዱተካ (እንዱክስ) ለማድረግ ነዉ። ይህ ትርጓሜ የኢንሽራንስ ዉል ሽፊን ወደፉት ለሚደርስ አደጋ የሚሰጥ ሽፊን መሆኑን ስለሚያሳይ የኢንሹራንስ ዉልን ልዩ የሚያደርግ መሰረታዊ ባህሪይም ይሄዉ እንደሆነ የሚያስገነዝብ ነዉ።ከዚህም አኳያ የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የኢንሹራንስ ዉል መሰረታዊ ባህሪይ ያላገናዘበ አተረጓጎም በመከተል መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መሆኑን አረጋግጠናል።
ሲጠቃለል የዋናዉን ኢንሹራንስ ዉል ሽፊን ለማስፊት በቀን 05/04/2008ዓ/ም የተፈረመዉ ማሻሻያ (ማስፉያ /Extension) ዉል ወደ ኋላ ተመልሶ እንዱሰራ በተዋዋዮች ግልጽ ስምምነት ያልተደረገ ከመሆኑም በተጨማሪ የኢንሹራንስ ዉል ከመፈረሙ በፉት ለደረሰ ጉዲት ኢንሹራንስ ሰጪዉ ካሳ እንዱከፍል ተጠይቆ የሚቀርብ ክስ የኢንሹራንስ ዉል መሰረታዊ ባህሪይ ያላገናዘበ ሆኖ እያለ የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የኢንሹራንስ ዉለ ወደኋላ ተመልሶ ዉጤት እንዱኖረዉ አድርጎ በመተርጎም የአሁን አመልካች ለተጠሪ ካሳ እንዱከፍል መወሰኑና በዚህ መሰረት በተሰጠዉ ዉሳኔ አመልካች ቅር ተሰኝቶ ያቀረበዉን ይግባኝ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተቀብል ስህተቱን ማረም ሲገባዉ ይግባኙን በመሰረዝ ትእዛዝ መስጠቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት በመሆኑ ሁለተኛዉን ጭብጥ መመርመር ሳያስፈልግ የሚከተለዉን ወስነናል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 26/04/2010 ዓ/ም የሰጠዉ የፍርድ ዉሳኔ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 19/06/2011 ዓ/ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ትእዛዝ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ተሽሯል።
አመልካች ክስ የቀረበበትን ካሳ ለተጠሪ የመክፈል ኃላፉነት የለበትም ።
ግራ ቀኝ በዚህ ፍርድ ቤት ደረጃ ያወጡትን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን እንዱችለ ተወስኗል።
የዚህ የፍርድ ዉሳኔ ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤት ይተላለፍ።
የስር ፍርድ ቤት መዝገብ ይመለስ። መዝገቡ ተዘግቷል
No topics extracted.