በሦስተኛ ወገኖች ላይ በተሽከርካሪ ለሚደርስ አደጋ የኢንሹራንስ ሽፊን የሰጠ ኢንሹራንስ ኩባንያ በአንሹራንስ ዉለ ላይ ኢንሹራንስ ገቢዉ ይህንን ካደረገ ወይም ካላደረገ ተጠያቂነት አይኖርብኝም በማለት ያስቀመጠዉን ሁኔታ መሰረት በማድረግ በሦስተኛ ወገን ላይ ለደረሰዉ ጉዲት ካሳ ላለመክፈል ጉዲት ለደረሰበት ሦስተኛ ወገን መከራከሪያ ለማድረግ የማይችል ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 799/2005 አንቀጽ 6/1 በኢንሹራንስ ዉል ፖሉሲዉ ላይ የተቀመጠዉን የማግለያ ወይም ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ እና እነ አቶ ሃብቴ አንማዉ (3 ሰዎች) ሁኔታ መሰረት በማድረግ ኢንሹራንስ ሰጪዉ በኢንሹራንስ ገቢዉ ላይ መከራከሪያ ሉያደርግ የሚችለዉ በቅድሚያ ጉዲት ለደረሰበት ሦስተኛ ወገን በአዋጅ ቁጥር 799/2005 አንቀጽ 16 እና በኢንሹራንስ ዉል ፖሉስዉ መሰረት ካሳ ከከፈለ በኋላ ስለመሆኑ አዋጁ ቁጥር 799/2005 አንቀጽ 6/2
No summary available.
የሰ/መ/ የካቲት 24 ቀን 2013 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ ተሾመ ሽፈራዉ ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግሥቱ ነጻነት ተገኝ አመልካች፡- አቶ ሐበን ጉዕሽ ተጠሪ፡- ናይል ፔትሮሉየም ካምፓኒ ሉሚትድ ኢትዮጵያ መዝገቡ ተመርምሮ ከዚህ የሚከተለዉ የፍርድ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የገንዘብ መጠኑ እና ቀን ሳይጻፍበት በቼክ አዉጭዉ ተፈርሞ የተሰጠ ቼክ (Blank Cheque) የሚኖረዉን ሕጋዊ ዉጤት የሚመለከት ነዉ።ተጠሪ በአመልካች ላይ በፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአጭር ሥነ ሥርዓት ታይቶ እንዱወሰንለት በመሰረተዉ ክስ አመልካች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዱስ አበባ ቅርንጫፍ በሂሳብ 02172 ካለዉ ገንዘብ ላይ በቼክ ቁጥር ID3905680 ብር 6,988,527.14 እንዱሁም በቼክ ቁጥር ID 3905681 ብር 5,136,773.70 በድምሩ ብር 12,125,300.84(አሥራ ሁለት ሚሉዮን አንድ መቶ ሃያ አምስት ሺህ ሦስት መቶ ብር ከሰማንያ አራት ሳንቲም) በያዙ ቼኮች ባንኩ ክፍያ እንዱፈጽም አመልካች ቼኮቹን ፈርሞ ለተጠሪ ሰጥቷል።ሆኖም ተጠሪ ቼኮቹን ለባንኩ ሲያቀርብ ባንኩ በአመልካች ሂሳብ ዉስጥ በቂ ገንዘብ የላለ በመሆኑ መክፈል እንደማይችል በመግለጽ በቀን 10/09/2008ዓ/ም የተጻፈ ማስረጃ ሰጥቷል።ስለሆነም አመልካች በቼኮቹ ላይ የተመለከተዉን ብር 12,125,300.84(አሥራ ሁለት ሚሉዮን አንድ መቶ ሃያ አምስት ሺህ ሦስት መቶ ብር ከሰማንያ አራት ሳንቲም) ቼኮቹን ከሰጡበት ከቀን 03/09/2008ዓ/ም ጀምሮ ከሚታሰብ ህጋዊ ወለድና ክሱ ከሚያስከትለዉ ወጪ ጋር እንዱከፍለ እንዱወሰንለት ዲኝነት ጠይቋል።
ተጠሪ ለክሱ መከላከያ እንዲላቸዉ ገልጸዉ ያቀረቡትን ማስፈቀጃ ፍርድ ቤቱ መቀበለን ተከትል ባቀረቡት መልስ ለክሱ መነሻ የሆኑ ቼኮች ተጠሪ እጅ ሉገቡ የቻለት አመልካች ነዲጅ ለመግዛት ከተጠሪ ጋር ባደረገዉ የቃል ንግግር መሰረት ዉል ለመዋዋል በሂደት ላይ ስለነበርን ለቅድመ ክፍያ ለዋስትና ተብል የገንዘብ መጠንና ቼኩ የሚከፈልበትን ቀን ሳይጻፍ ፊርማ ብቻ በመፈረም ለተጠሪ የተሰጠ ነዉ።በቼኮቹ ላይ የገንዘብ መጠኑ እና ቼኩ የሚከፈልበት ቀን የሚጻፈዉ ግን ዉል ከተፈራረምንና የነዲጁ ዋጋ ታዉቆ በዉለ መሰረት ነዲጅ ከወሰድኩ በኋላ ነዉ።ስለሆነም ተጠሪ ክፍያ እንዱፈጸምለት ለባንኩ ከማቅረቡ በፉት የተደረገ ዉልና የተሰራ ሥራ ካለ በዚሁ መሰረት አመልካች ያልተወጣሁት ግዳታ መኖሩን አረጋግጦ መሆን እያለበት ተጠሪ ያለምንም ምክንያት ቼኮቹ ላይ የገንዘብ መጠኑንና ቀኑን ሞልቶ ክፍያ መጠየቁ የቅን ልቦና አሰራርን የሚቃረንና ቼኮቹ ከተሰጠበት ዓላማ ዉጭ ነዉ።
ተጠሪ ዉል ስለመኖሩ ወይም የተወሰደ ነዲጅ ስለመኖሩ በክሱ ካለመግለጹም በተጨማሪ ይህንን የሚያሳይ ማስረጃ ባለማቅረቡ ክሱ ዉድቅ ይደረግልኝ በማለት ተከራክረዋል።
ፍርድ ቤቱ በመ/ ላይ የግራ ቀኙን ክርክር እና ምስክሮች በመስማት በቀን 20/02/2012 ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ ቼክ እንደቀረበ ሉከፈል የሚገባ ሰነድ መሆኑን በንግድ ሕግ አንቀጽ 732፣827/ሀ እና 854 ላይ መደንገጉን፤አመልካች በድምሩ ብር 12,125,300.84 ዋጋ ያላቸዉን ቼኮች መስጠታቸዉን፤ቼክ አዉጪዉ በባንክ ሂሳቡ በቂ ስንቅ እንዲለዉ እርግጠኛ መሆን እንዲለበት በንግድ ሕጉ አንቀጽ 830/2 ላይ መደንገጉን ፤አመልካች ለተጠሪ በሰጡት ቼኮች ለመክፈል የማይገደደት በንግድ ሕጉ አንቀጽ 717 ስር የተመለከቱትን መቃወሚያዎች በማስረዲት እንደሆነ፤አመልካች ያቀረቡት መከራከሪያ ለክርክሩ መነሻ በሆኑት ቼኮች ላይ የተጻፈዉን ገንዘብ ተጠሪ ራሱ በሚያመቸዉ መንገድ የሞላዉ ስለሆነ ለመክፈል አልገደድም የሚል ቢሆንም ቼኮቹን መስጠታቸዉን በቼኮቹ ላይ ያለዉ ፊርማ የራሳቸዉ እንደሆነ ስላልካደ ቼኮቹ የሚከፈለበት ቀንና የገንዘብ መጠኑ በተጠሪ መሞላቱ ቼኩን ዋጋ እንደማያሳጣዉ፤ተጠሪ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 137 መሰረት ባቀረበዉ ማስረጃ ከዚህ ቀደም በነበራቸዉ ግንኙነት መነሻ አመልካች ለተጠሪ በቼክ ቁጥር ID 3905671 የሚታወቅ ቼክ ፈርመዉ ሰጥተዉ ተጠሪ በቼኩ ላይ ብር 1,544,941.38 ጽፍ ቼኩን በመመንዘር ክፍያዉን በቀን 24/06/2008 ዓ/ም መቀበለን ተጠሪ ማስረዲቱን፤ይህም ክሱ ከመመስረቱ በፉት በግራ ቀኙ መካከል ግንኙነት እንደነበረና በቼኩ ላይ የገንዘብ መጠን እየሞላ ተጠሪ ገንዘቡን ሲቀበል የነበረ መሆኑን፤አመልካች በቼኮቹ ላይ የተጻፈዉን ቀን ገንዘብ እንዲልጻፈ በመግለጽ በፍሬንሲክ እንዱመረመር ቢጠይቁም ይሕንን መከራከሪያ ያነሱት ከተጠሪ ጋር የቀደመ ግንኙነት እንደላላቸዉ አስመስለዉ ቢሆንም በመካከላቸዉ የቀደመ ግንኙነት እንደነበራቸዉ በመረጋገጡ ከዚህ አኳያ አመልካች ያቀረቡት ክርክር ተአማኚነት የላለዉ ከመሆኑም በተጨማሪ በንግድ ሕጉ አንቀጽ 717 ስር ከተዘረዘሩት መቃወሚያዎች ስር የሚካተት አለመሆኑን፤እንዱሁም መከላከያ እንዲላቸዉ በመግለጽ መልስ እንዱሰጡ እንዱፈቀድላቸዉ ባቀረቡት ማስፈቀጃ ላይ ቼኮቹን ለተጠሪ የሰጡት ወንድማቸዉ ከአቶ ቢነጋ ጉዕሽ ጋር የፔትሮሉየም ምርቶች ለማከፊፈል ከተጠሪ ጋር በተዋዋለት ዉል መነሻነት ላልተከፈለ ክፍያ የተጠየቀ ክፍያ እንደሆነ በመግለጽ መልሳቸዉን እንዱያቀርቡ ካስፈቀደ በኋላ ባቀረቡት መከላከያ መልስ ላይ ደግሞ ለክሱ መነሻ የሆኑትን ቼኮች ለተጠሪ የሰጡት ራሳቸዉ ከተጠሪ ጋር በቃል ባደረጉት ንግግር የፔትሮሉየም ምርቶች የማከፊፈል ስምምነት እስከሚፈጸም ለቅድሚያ ክፍያ ዋስትናነት ነዉ በማለት መልስ መስጠታቸዉ ክርክራቸዉ እርስ በእርሱ የሚቃረን መከራከሪያ መሆኑን ያሳያል እንዱሁም የተጠሪ ምስክሮች በግራ ቀኝ መካከል ዉል መኖር አለመኖሩን እንደማያዉቁ መመስከራቸዉ በሁለቱም መካከል ዉል የለም ብል ለመደምደም አያስችልም የሚለትን ምክንያቶች በመዘርዘር አመልካች ክስ የቀረበበትን ብር 12,125,300.84(አሥራ ሁለት ሚሉዮን አንድ መቶ ሃያ አምስት ሺህ ሦስት መቶ ብር ከሰማንያ አራት ሳንቲም) ከቀን 03/09/2008 ዓ/ም ጀምሮ ከሚታሰብ ሕጋዊ ወለድ ጋር ለተጠሪ እንዱከፍለ ወስኗል።
አመልካች በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ፍርድ ቤቱ በመ/ ላይ በቀን 13/06/2012 ዓ/ም በሰጠዉ ትእዛዝ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞባቸዋል።አመልካች በቀን 22/11/2012 ዓ/ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረቡትም በዉሳኔዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን የአቤቱታቸዉ ይዘት በአጭሩ የሚከተለዉ ነዉ።
አመልካች ለክሱ መነሻ የሆኑትን ቀንና የገንዘብ መጠን ያልተጻፈባቸዉን ቼኮች ለተጠሪ የሰጠሁት ከተጠሪ ለምረከበዉ ነዲጅና ቅባት አከፊፈል ለዋስትና እንዱሆን በቃል በተነጋገርነዉ መነሻ ቢሆንም ዉል ባለመፈጸማችን የተረከብኩት ምንም አይነት ምርት አልነበረም። በሁለቱም ባድ ቼኮች ላይ ቀንና የገንዘብ መጠኑን አመልካች አለመጻፋንና የሞላዉ ተጠሪ መሆኑን ተጠሪ አምኖ እያለ ቼኮቹን አመልካች ሰጥቷል በማለት ከተጠሪ እኔም ሆንኩ ወንድሜ የተረከብነዉ ምርት መኖሩ ሳይረጋገጥ የሥር ፍርድ ቤት ዉሳኔ መስጠቱ ስህተት ነዉ።በንግድ ሕጉ አንቀጽ 827 እና 828 መሰረት በቼኮቹ ላይ የተመለከተዉ ገንዘብና የመክፈያዉ ቀን ከአመልካች እዉቅና እና ፈቃድ ዉጭ የተጻፈ በመሆኑ ለክሱ መነሻ የሆኑት እንደቼክ የሚቆጠሩ አይደለም።የሥር ፍርድ ቤት ቀንና የገንዘብ መጠኑ ያልተገለጸ ቼክ አመልካችን ያስገድደዋል ወይ?ተጠሪስ በቼኩ ላይ እነዚህን ነጥቦች ከአመልካች እዉቅና ዉጭ ራሱ ሞልቶ ክፍያ መጠየቅ ይችላልን?እንዱሁም ከዚህ ቀደም አመልካች ለተጠሪ የሰጠዉ አንድ ባድ ቼክ ለክሱ መነሻ ከሆኑ ቼኮች ጋር ምን ግንኙነት አላቸዉ?በባድ ቼኮች ላይ ተጠሪ የፈለገዉን የገንዘብ መጠን ጽፍ ቢጠይቅ ተጠሪ የጻፈዉን ሁለ አመልካች ለመክፈል ይገደዲልን?የሚለ ጭብጦችን ይዞ መርምሮ መወሰን ሲገባዉ ተገቢ ጭብጦች ሳይዝና ክርክሩን በአግባቡ ሳይመራ የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃዎች በአግባቡ ሳይመረምር ዉሳኔ መስጠቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ።ተጠሪ በነዲጅ ኩባንያዎችና በነዲጅ ገዥዎች መካከል በቼክ ላይ የገንዘብ መጠን ሳይጻፍ (Blank Cheque) የሚሰጥበት አሰራር በዓለም አቀፍም ሆነ በኢትዮጵያ የተለመደ አሰራር ነዉ በማለት የተከራከረ ቢሆንም ተጠሪ አመልካች የነዲጅ ምርት መዉሰዳን ካለማስረዲቱም በላይ በቀን 29/06/2011 ዓ/ም በተጻፈ አቤቱታዉ ተጠሪ ክስ የመሰረተበትን ገንዘብ የጠየቀዉ የአመልካች ወንድም አቶ ቢነጋ ጉዐሽ ለወሰደዉ ምርት ክፍያ እንደሆነ ያረጋገጠዉን ታልፍ አመልካችን በማይመለከተኝ ጉዲይ ባለእዲ የሚያደርገኝ ዉሳኔ መሰጠቱ ስህተት ነዉ።በቼኮቹ ላይ የፈለገዉን ገንዘብ መጠን በፈለገዉ ቀን እንዱከፈለዉ የጻፈዉ ራሱ ተጠሪ በመሆኑ አመልካች ለራሴም ሆንኩ ለወንድሜ እዲ ለመክፈል የምገደድበትን የዉል ወይም የሕግ ምክንያት ተጠሪ በክርክሩና በማስረጃ እንዱያስረዲ ሳያደረግ መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ።እንዱሁም በንግድ ሕጉ አንቀጽ 717 መሰረት መቃወሚያ በማቅረብ መከራከር የሚቻለዉ በንግድ ሕጉ አንቀጽ 827 እና 828 መስፈርት መሰረት የተሟላ ቼክ በተሰጠ ጊዜ ሆኖ እያለ ቼኮቹ ላይ የተጻፈዉን ገንዘብና ቀን እኔ አልጻፍኩም ብዬ ያነሳሁትን ክርክር ባላገናዘበ መልኩ ለድንጋጌዎቹ የተሳሳተ ትርጉም በመስጠት የደረሰበት ድምዲሜ ነዉ።በተጨማሪም አመልካች በቼክ ክፍያ ለመፈጸም ትእዛዝ ሰጥተሃል ልባል የሚገባዉ በቼኮቹ ላይ የገንዘብ መጠን እና ቀን በመጻፍ ትእዛዝ ስሰጥ እንጂ የቼኩ አምጪ ሲጽፍባቸዉ አይደለም።በንግድ ሕጉ አንቀጽ 827(ሀ እና መ) እና 828 መሰረት ለክፍያዉ ተጠያቂ የሆነዉ ቼክ አዉጪ በቼኩ ላይ የገንዘብ መጠንና ቀን ጽፍ ፈርሞ ካልሰጠ እንደቼክ ስለማይቆጠር የስር ፍርድ ቤቶች ዉሳኔዎች መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ ተጠሪ በክሱ በተጠቀሱት ቼኮች መነሻ አመልካችን ክፍያ መጠየቅ አይችልም ተብል ይታረምልኝ በማለት አቤቱታቸዉን አቅርበዋል።
ሰበር አጣሪ ችልት አቤቱታዉን መርምሮ አመልካች በንግድ ሕጉ አንቀጽ 827 እና 828 መሰረት አስገዲጅ የሆነ ክፍያ ሉፈጸምበት የሚችል ቼክ ለተጠሪ መስጠት አለመስጠታቸዉ ተጣርቶ መወሰን አለመወሰኑ? በአከራካሪዎቹ ቼኮች መሟላት ያለባቸዉ ፍርማሉቲዎች በአመልካች ተሟልተዋል ወይስ አልተሟለም ?አመልካች ሰጡ በተባለት ባድ ቼኮቾ በተጠሪ የገንዘብ መጠን እንዳት እንደተሞላ ከመሰረታዊ የማስረጃ ሕግ አንጻር የስር ፍርድ ቤቶች አጣርተዉ መወሰን አለመወሰናቸዉን ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልት ቀርቦ እንዱመረመር ትእዛዝ በመስጠቱ ተጠሪ በቀን 25/03/2013 ዓ/ም የተጻፈ መልስ የሰጠ ሲሆን ይዘቱ በአጭሩ የሚከተለዉ ነዉ።
በንግድ ሕጉ አንቀጽ 827 እና 828 ላይ ቼክ እንደ ቼክ ለመቆጠር በቼኩ ላይ የተጠቀሰዉን ገንዘብና የመክፈያዉ ቀን በቼክ አዉጪ መጻፍ አለበት በሚል አልተደነገገም።በቼኩ ላይ ቀንና የገንዘቡ መጠን በቼክ አዉጪ አለመሞላቱ ወይም በቼኩ ተካፊይ በሆነ ሰዉ መሞላቱ በአመልካች ለተጠሪ የተሰጠዉ ሰነድ ቼክ መሆኑን ቀሪ አያደርገዉም።የገንዘብ መጠንና ቀን በቼክ ላይ መጻፍ ያለበት በቼኩ አዉጪ ብቻ ነዉ ብል የሚያስገድድ ሕግ የለም።እንዱህ አይነት የሕግ ግዳታ ባለመኖሩም ባንኮች ለሚቀርብላቸዉ የቼክ ክፍያ ጥቄያ ቼኩ ላይ የተጠቀሰዉ ገንዘብ እና ቀን በቼክ አዉጪዉ በእርግጥም መጻፈን የማረጋገጥ ልማድም ሆነ አሰራር የለም። ነዲጅና የነዲጅ ዉጤቶችን በማከፊፈል ሥራ ላይ የተሰማሩ እንደ አመልካች ያለ ነጋዳዎች በሙለ በሚባል ደረጃ ተጠሪን ከመሰለ ነዲጅና የነዲጅ ዉጤቶችን ከሚያቀርቡ ድርጅቶች ምርቶቹን በደቤ ስለሚወስደ ተጠሪን የመሰለ ነጋዳዎች በደቤ ለሚሰጡት ምርት ክፍያቸዉን በቀላለ መሰብሰብ ይችለ ዘንድ ቀን እና የገንዘብ መጠን ያለተጻፈባቸዉን ቼኮች (Blank Cheque) በመቀበል ሥራዉ እንደሚሰራ በስፊት የተለመደና የታወቀ አሰራር ነዉ።የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ዉሳኔ ይህንን የተለመደ የንግድ ሥራ ተግባር እና ሕጉን በሚጠብቅና በማያፈርስ መልኩ የሰጡት ዉሳኔ ስለሆነ የተፈጸመ ስህተት የለም።በአመልካች እና በተጠሪ መካከል በነበረዉ ግንኙነት አመልካች የሰጠዉ ቀን እና የገንዘብ መጠን ያልተጻፈበት ቼክ- ቼክን መሆኑ የሚያረጋግጠዉ ላላኛዉ ጉዲይ የገንዘብ መጠንና ቼኩ የተጻፈበትን ቀን ሳይጠቅስ ቁጥሩ ID3905671 የሆነ ቼክ አመልካች ለተጠሪ በመስጠቱ ብር 1,544,941.38 የሆነ ገንዘብ እና ቀን ተጠሪ ቼኩ ላይ ጽፍ ይህንኑ ቼክ በመመነዘር ክፍያዉን ቼኩን መንዝሮ መቀበለ ተረጋግጧል።ይህም በቼክ ላይ የገንዘብ መጠንና ቀን በተጠሪ እየተጻፈ በቼክ ክፍያ መፈጸሙ በአመልካችና በተጠሪ መካከል የቆየ የንግድ ሥራ ግንኙነት በግልጽ የሚያሳይ ሆኖ እያለ አመልካች በደቤ ለወሰደት የነዲጅና የነዲጅ ዉጤቶች ምርት በተጠቀሰዉ መልክ ክፍያ ሲፈጽሙ ቆይተዉ አሁን ለተጠሪ የሰጡትን ቀን እና የገንዘብ መጠን ያልተጻፈበት ስለሆነ እንደ ቼክ ሉቆጠር አይገባም በማለት ከቅን ልቦና ዉጪ በሆነ መንገድ ያቀረቡት ክርክር ነዉ።በስር ፍርድ ቤት የተያዘዉ ጭብጥ አመልካች ለክሱ ከሰጡት መልስ አንጻር ተገቢ በመሆኑና አመልካች መያዝ ነበረበት ያለት ጭብጦች ተይዘዉ እንኳን ቢሆን በክርክሩ ዉጤት ላይ የሚያመጣዉ ለዉጥ ባለመኖሩ በዚህም ረገድ የተፈጸመ ስህተት የለም።እንዱሁም የስር ፍርድ ቤት በግራ ቀኙ የቀረቡ ማስረጃዎችን ሰምቶና መርምሮ የመመዘን ሥልጣኑን ተጠቅሞ የሰጠዉ ዉሳኔ ሆኖ እያለ የትኛዉ ማስረጃ ሳይመረመር እንደቀረ እንኳን ሳይገልጹ ያቀረቡት መከራከሪያ በመሆኑ ተቀባይነት ሉሰጠዉ አይገባም በማለት መልሱን በመስጠት ተከራክሯል።አመልካችም በቀን 09/04/2013ዓ/ም የተጻፈ የመልስ መልስ በማቅረብ ተከራክረዋል።
ከዚህ በላይ የተመዘገበዉ የግራ ቀኝን ክርክርና በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ዉሳኔዎች ይዘት የሚመለከት ሲሆን እኛም የሰበር አጣሪ ችልት ማስቀረቢያ ነጥብ ከግምት በማስገባት የገንዘብ መጠኑ እና ቀን ሳይጻፍበት በቼክ አዉጪዉ ተፈርሞ ለአምጪዉ የተሰጠ ቼክ (Blank Cheque) የሚኖረዉን ሕጋዊ ዉጤት እና ከዚህ አንጻር የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ መርምረናል።
እንደመረመርነዉም በቼክ አዉጪዉ ተፈርሞበት ነገር ግን የሚከፈለዉ ገንዘብ መጠን እና ቀን ሳይጻፍበት ለአምጪዉ የተሰጠ ቼክ በአገራችን ሕግ ያለዉን ቦታና የሚኖረዉን ሕጋዊ ዉጤት ከማየታችን በፉት እንዱህ አይነት ቼክ ምንነት መመልከቱ ጠቃሚ ይሆናል ። እንዱህ አይነት ቼክ በዘርፈ በእንግሉዝኛ መጠሪያዉ “Blank Cheque” ተብል የሚታወቅ ነዉ። በታዋቂዉ ብላክስ ልዉ መዝገበ ቃላት ይህ አይነት ቼክ(Blank Check):- is a check signed by the drawer but left blank as to the payee or the amount, or both.( Black's Law Dictionary (8th ed. 2004) P. 711) የሚል ፍቺ የተሰጠዉ ሲሆን በልላ መዝገበ ቃላት ላይም በተመሳሳይ Blank Cheque is a cheque that has been signed but does not yet have the amount of money written on it.(Cambridge Dictionary) የሚል ፍቺ ተሰጥቶታል።ይህም አዉጪዉ በቼኩ ላይ ፈርሞበት ነገር ግን በቼኩ ላይ በተለይም የሚከፈለዉን ገንዘብ መጠን ሳይጽፍበት ለቼክ አምጪዉ የሚሰጠዉ ቼክ አይነት እንደሆነ የሚያሳይ ነዉ። በንግድ ሥራ ዘርፍ ቀን እና የገንዘብ መጠን ያልተጻፈበት ቼክ (Blank Cheque) በቼክ አዉጪዉ (drawer) ተፈርሞበት ለቼክ አምጪ (bearer) የሚሰጥበት አሰራር በተለይም በሚተማመኑ የንግድ ዘርፍ ሰዎች መካከል የተለመደ አሰራር እንደሆነ በዘርፈ የተጻፈ የሕግ ድርሳናት ያሳያለ። በእኛም አገር እንዱህ አይነት ቼክ (Blank Cheque) የመጠቀሙ ልማድ በሚተማመኑ ነጋዳዎች መካከል የሚሰተዋል ወይም በቼክ አዉጪዉና አምጪ መካከል ባለ መተማመን ላይ ተመስርቶ የሚፈጸም የክፍያ አፈጻጸም ልማድ እንዲለ የንግደ ዘርፍ ነባራዊ ሁኔታ ያሳያል።
በልላ በኩል በቼክ አዉጪዉ ተፈርሞበት ነገር ግን የሚከፈለዉ ገንዘብ መጠን እና ቀን ሳይጻፍበት ለአምጪዉ የተሰጠ ቼክ በአገራችን ሕግ ያለዉን ቦታና የሚኖረዉን ሕጋዊ ዉጤት መርምረናል።
በ1952 ዓ/ም በወጣዉ የንግድ ሕግ አራተኛ መጽሐፍ ስለሚተላለፈ የገንዘብ ሰነድችና የባንክ ሥራ ሕግ በሚል አብይ ርእስ ስር ባለ ጠቅላላ ድንጋጌዎች እና በተለይ ደግሞ ስለቼክ በተደነገጉት የሕጉ አንቀጽ 827 እና ተከታዮች ስር ቼክ በሁለት ሰዎች መካከል የክፍያ ስምምነት መኖሩን የሚያሳይ የሚተላለፍ የንግድ ወረቀት (Commercial Negotiable Instrument) እንደሆነ የሚያሳዩ በርካታ ድንጋጌዎች ያለ ቢሆንም በሕጉ ቀን እና የገንዘብ መጠን ያልተጻፈበት ነገር ግን በአዉጪዉ ስለተፈረመበት ቼክ (Blank Cheque) በግልጽ ተዘርዝሮ የተደነገገ ነገር የለም።ይህ ማለት ግን እንዱህ አይነት ቼክ በሕጉ ምንም ቦታ የለዉም ወይም ሕጉ በእንዱህ አይነት ቼክ ለሚፈጸም ክፍያ ሕጋዊ ዉጤት አይሰጠዉም ማለት እንዲልሆነ ልብ ማለትና ሕጉንና በንግድ ሥራ ዘርፈ የክፍያ አፈጻጸም ለማሳለጥ የካበተዉን ልማድ ማየትና መመርመር ያስፈልጋል።
በቼክ ላይ የሚጻፈ አስፈላጊ መግለጫዎች ናቸዉ ተብለዉ በንግድ ሕግ አንቀጽ 827 ከፉደል ሀ እስከ ሰ ባለት ንኡሳን አናቅጽ የተጠቀሱ መግለጫዎች(Contents)፡- ሀ) የተወሰነ ገንዘብ ለመክፈል ሐተታ የላለበት ትእዛዝ፤ ለ) መክፈል የሚገባዉ ከፊይ ስም፤ ሐ) የሚከፈልበት ቦታ፤ መ) ቼኩ የወጣበት ቦታና ጊዜ እና ሰ) ቼኩን ያወጣዉ ሰዉ ፊርማ የሚለ ናቸዉ።በዚሁ ሕግ አንቀጽ 828 ስር ባለዉ የመግቢያ ዐረፍተ ነገር ላይ እንደተመለከተዉ ከእነዚህ መግለጫዎች አንደ እንኳን የላለበት ሰነድ እንደ ቼክ እንደማይቆጠር ተመልክቷል።በዚህ ድንጋጌ ላይ ‛ከእነዚህ መግለጫዎች አንደ እንኳን የላለበት ሰነድ እንደ ቼክ አይቆጠርም“ የሚለዉ አገላለጽ ላይ ላዩን ሲታይ ግልጽ ቢመስልም አገላለጹ የሚያገለግለዉ መግለጫዎቹ ያልተሟላ ቼክ በቼክ አዉጪዉ ተፈርሞ ለአምጪዉ በሚሰጥበት ጊዜ ነዉ ወይስ ቼኩ ለክፍያ ሲቀርብ ነዉ የሚል ጥያቄ በማንሳት ሲታይ ግን ግልጽነት የሚጎድለዉ (አሻሚ) ስለሚሆን ትርጉም የሚያሻ እንደሆነ ተገንዝበናል።
በመርህ ደረጃ እነዚህ በሕጉ አንቀጽ 827 ስር በቼክ ላይ መጻፍ ያለባቸዉ ናቸዉ ተብለዉ የተዘረዘሩ መግለጫዎች በቼክ አዉጪዉ መጻፍ እንዲለባቸዉ የሚጠበቅ ቢሆንም መግለጫዎቹ አንድ በአንድ ሲታዩ ግን የቼክ አዉጪዉን ፊርማ ከሚመለከተዉ መስፈርት በስተቀር ቀሪዎቹ መግለጫዎች በቼክ አዉጪዉ ስምምነት ወይም ፈቃድ በቼክ አምጪዉ ወይም በልላ ሰዉ ሉጻፈ(ሉሞለ) የሚችለ ናቸዉ።
ይህም በአንቀጽ 827 ስር በዝርዝር ከተጠቀሱ መግለጫዎች (Contents) መካከል አንደ ወይም የተወሰኑት በአንድ ቼክ ላይ ሳይሞላ ቼኩ ለባንክ ለክፍያ ቢቀርብ ሰነደ እንደ ቼክ ተቆጥሮ በባንክ አይመነዘርም ወይም ክፍያ አይፈጸምም ከሚል መንፈስና አላማ የተደነገገ እንደሆነ ያሳያል። በልላ አገላለጽ በድንጋጌዉ ከተጠቀሱት መግለጫዎች(ይዘቶች) በተለይም በቼኩ ላይ መጻፍ ያለበት ቀን እና የገንዘብ መጠን ቼኩ ከቼክ አዉጪዉ ሲወጣ ባይሞላም(በቼክ አዉጪዉ ባይጻፍም) በቼኩ ላይ ላልች መግለጫዎች በቼክ አዉጪዉ ተሞልተዉና ተፈርሞ ሰነደ ለቼክ አምጪዉ ከተሰጠ በኋላ በአምጪዉ የቼኩን መክፈያ ቀን እና የሚከፈለዉን ገንዘብ መጠን ሞልቶ ሰነደን ለባንክ ባቀረበ ጊዜ ሰነደ እንደ ቼክ አይቆጠርም የሚል እንድምታ ያለዉ አይደለም።ይልቁንም በአንድ የቼክ ሰነድ ላይ በንግድ ሕጉ አንቀጽ 827 ስር የተደነገጉ መግለጫዎች ተሞልቶበትና በቼክ አዉጪዉ ተፈርሞበት ለባንክ ከቀረበ ባንኩ ቀኑንና የገንዘብ መጠኑን ማን ጻፈዉ የሚለዉን ማረጋገጥ ሳይጠበቅበት በቼኩ ላይ ያለዉ ፊርማ በቼክ አዉጪዉ መፈረሙን ባለዉ አሰራር መሰረት አመሳክሮ አረጋግጦ በቼኩ ላይ የተመለከተዉን ገንዘብ መጠን ከቼክ አዉጪዉ ተንቀሳቃሽ(የቼክ) ሂሳብ ላይ ቀንሶ የመክፈል ግዳታ ይኖርበታል። ምክንያቱም በንግድ ሕጉ አንቀጽ 829፣ 830 እና 840 ላይ በተደነገገዉ እና በድንጋጌዎቹ በስተጀርባ ባለዉ አስተሳሰብ መሰረት ከአምጪዉ የቼክ ሰነድ ተቀብል ክፍያ የሚፈጽመዉ ባንክ ወይም በሕግ እንደ ባንክ የሚቆጠር የፊይናንስ ተቋም በመሆኑ ቼኩ ለባንክ ሲቀርብ በንግድ ሕጉ አንቀጽ 827 ስር የተጠቀሱትን መግለጫዎች የሚያሟላ እስከሆነ ድረስ ባንኩ/ተቋሙ ቼኩን ተቀብል ከቼክ አዉጪዉ ሂሳብ ላይ ቀንሶ በቼኩ የተመለከተዉን ገንዘብ ለአምጪዉ ለመክፈል የሕግ ግዳታ ስላለበት ነዉ። ስለሆነም አንድ ቼክ እንደሚተላለፍ የንግድ ወረቀት (Commercial Negotiable Instrument) ወይም እንደሚተላለፍ የክፍያ ሰነድ የሚቆጠረዉም ይህንኑ በመተማመን በመሆኑ በአንቀጽ 827 እና 828 ስር ‛ከእነዚህ መግለጫዎች አንደ እንኳን የላለበት ሰነድ እንደ ቼክ አይቆጠርም“ የሚለዉ አገላለጽ የቼክን ልዩ ባህርይና በዚህ ሰነድ የሚፈጸመዉን የክፍያ ሥርዓት በሚያሳልጥ መልኩ በቼኩ ክፍያ እንዱፈጸም በመጠየቅ ለባንክ ሲቀርብ ተፈጻሚ የሚሆን እንደሆነ ተቆጥሮ ተግባራዊ ላደረግ የሚገባ ነዉ።ይህም የቼክ ሰነድ በአዉጪዉ ተፈርሞ ለአምጪዉ በተሰጠ ጊዜ ከንግድ ሕጉ አንቀጽ 827 አንጻር የተሟላ ባይሆንም ለከፊዩ ባንክ በቀረበ ጊዜ ተሟልቶ ከቀረበ ሕጉ ለእንዱህ አይነት ቼክ (Blank Cheque) ሕጋዊ ዉጤት ይሰጠዋል ወደሚል ድምዲሜ የሚያደርስ ነዉ።
በተጨማሪም በንግድ ሕጉ አንቀጽ 732 ስር እንደተመለከተዉ ቼክ በንግድ ሥራ እንቅስቃሴ ዉስጥ ጥሬ ገንዘብን ተክቶ ግብይትን እንዱያሳልጥ የተፈጠረ የሚተለለፍ የንግድ ወረቀት (Commercial Negotiable Instrument) እንደመሆኑ ቼክ አዉጪ የተፈረመበትን የቼክ ጥራዝ/ወረቀት በጥንቃቄ መያዝ ፣ገንዘቡን በቼክ ሉያዝበት መብት እንዲለዉ እና ቼኩን ከሰጠበት ጊዜ ጀምሮ ቼኩ ለክፍያ እስከሚቀርብበት ቀን ድረስ ከከፊዩ ባንክ ዘንድ የገንዘብ ሥንቅ እንዲለዉ ማረጋገጥና ሰነደን ከታለመለት ዓላማ አንጻር መጠቀም ይኖርበታል። ይህንን ባለማድረግ ለሚመጣበት ኃላፉነት በንግድ ሕጉ አንቀጽ 840 በመጀመሪያዉ ኃይለ ቃል ላይ እንደተመለከተዉ ቼክ አዉጪዉ በቼኩ ላይ ስለተጻፈዉ ገንዘብ አከፊፈል ዋስ እንደሆን ሕግ ግዳታ ይጥልበታል። ስለሆነም አንድ የቼክ ሰነድ በቼክ አዉጪዉ ተፈርሞበት ነገር ግን የሚከፈልበት ቀን እና የገንዘብ መጠን በቼክ አዉጪዉ ሳይጻፍ ለቼክ አምጪ ከተሰጠና በዚህ የቼክ ሰነድ (Blank Cheque) ላይ አምጪዉ የገንዘብ መጠን እና የሚከፈልበትን ቀን ጽፍበት ለባንክ ካቀረበ ቼኩ በቼክ አዉጪዉ ተሞልቶ እንደተሰጠ ቼክ ተቆጥሮ ሉመነዘር የሚገባ እንጂ በቼኩ ላይ ያለዉ ቀን እና የገንዘብ መጠን በአምጪዉ በመጻፈ ብቻ ሰነደ የቼክነት ባህርይዉንና ሕጋዊ ዉጤቱን ሉያጣ አይችልም።
እንዱሁም ቼክ አዉጪ በቼኩ ላይ የተመለከተዉ ገንዘብ ለአምጪዉ እንዱከፈል ስለመስማማቱ/ስለማዘዙ ማረጋገጫ የሚሆነዉ ቼክ አዉጪዉ ቼኩ ላይ ፊርማዉን አኑሮ ቼኩን ለአምጪዉ መስጠቱ ነዉ። በመሆኑም ቼክ አዉጪዉ በቼኩ ላይ ፊርማዉን ብቻ ጽፍ በቼኩ የሚከፈለዉን የገንዘብ መጠን እና ቀን ሳይጽፍ ለአምጭዉ መስጠቱ ከተረጋገጠ ላላ በሕጉ የተፈቀደ ተቃራኒ መከራከሪያ በማስረጃ ተደግፍ እስካልቀረበ ድረስ ይህንን ያደረገዉ ከቼክ አምጪዉ ጋር ያለዉን መተማመን መሰረት አድርጎ በቼኩ ላይ የሚጻፈዉን ገንዘብ መጠንና የሚከፈልበትን ቀን አምጪዉ ጽፍ ለባንክ አቅርቦ ክፍያ እንዱጠይቅ ቼክ አዉጪዉ የመዋዋል ነፃነቱን (Freedom of Contract) ተጠቅሞ እንደተስማማ ይቆጠራል።
በልላ በኩል ቼክ አዉጪዉ መከራከሪያ አድርጎ ማንሳት የሚችላቸዉ በሕግ የተፈቀደ መቃወሚያዎች ምንድን ናቸዉ የሚለዉን መመርመር ለያዝነዉ ጉዲይ ተገቢዉን ዉሳኔ ለመስጠት ጠቃሚ ይሆናል።
ተደጋግሞ እንደተገለጸዉ ቼክ እንደ ገንዘብ ወደተለያዩ ሰዎች በቀላለ ሉተላለፍ የሚችል ባህርይ ስላለዉ የቼክ አከፊፈል ላይ በሕጉ በግልጽ ተለይተዉ ከተመለከቱት በስተቀር ማንኛዉንም መቃወሚያ ማቅረብ አይቻልም።በዚህ አግባብ በመከራከሪያነት ሉነሱ የሚችለ መቃወሚያዎች በንግድ ሕጉ አንቀጽ 717 ፣841 እና 850 ስር የተደነገጉት ናቸዉ። በጥቅለ በእነዚህ ድንጋጌዎች መሰረት መቃወሚያ ሆነዉ ሉነሱ የሚችለ መከራከሪያዎች ሁለት ገጽታዎች ያላቸዉ ሆነዉ አንደኛዉ ሰነደ ከሚመለከተቻዉ ሰዎች መካከል(ጋር) ያለዉን የግል ግንኙነትን መነሻ ያደረገ (Defense in Personal Relation) ሲሆን ሁለተኛዉ ደግሞ ማንኛዉም በቼክ የተከሰሰ ሰዉ ሉያነሳቸዉ የሚችልና የቼኩን ሰነድ መሰረት ያደረገና በዚህ የሕግ ዘርፍ Real Defense ተብል የሚታወቅ ነዉ። በንግድ ሕጉ አንቀጽ 717 ፣841 እና 850 ስር በመቃወሚያነት ሉነሱ የሚችለ መከራከሪያዎች፡- በቼክ አዉጪዉ(እዲ ከፊዩ) እና ከአምጪዉ (ሰነደን በያዘዉ ሰዉ) መካከል ያለዉን የግል ግንኙነት መሰረት ያደረገ፣በሰነደ አጻጻፍ ፍርም፣በሰነደ ላይ በተጻፈ ቃልች ላይ በተደረገ ለዉጥ (Alteration)፣ፊርማዉ ተመሳስል የተፈረመ መሆኑን የሚመለከት፣ ቼኩ ሲወጣ ቼክ አዉጪዉ ችልታ ወይም የዉክልና ሥልጣን የላለዉ መሆን፣ ክስ ለማቅረብ አስፈላጊ የሆኑት ሁኔታዎች አለመሟላት፣በቼክ አምጪዉ ቼኩ የተገኘዉ በክፈ ልቦና እዲ ከፊዩን ለመጉዲት በማሰብ ወይም ከባድ ጥፊት በመፈጸም መሆኑን የሚመለከቱ ናቸዉ።
ከዚህ ጋር ተያይዞ በንግድ ሕጉ አንቀጽ 841 ስር የተደነገገዉን ለይተን ያየን እንደሆነ ቼኩ በሚወጣበት ጊዜ ጉድለት ቢኖርበት እንኳን (incomplete when issued) ቼክ አዉጪዉ ቼኩ በቼክ አምጪዉ የተገኘዉ በክፈ ልቦና መሆኑን ወይም አምጪዉ ቼኩን ከባድ ጥፊት በመፈጸም ያገኘዉ መሆኑን በማስረዲት ካላረጋገጠ በስተቀር ስለቼኩ አሞላል የተደረጉ ስምምነቶችን በሚቃረን መልኩ የተሞላ ቼክ ቢሆንም እንኳን ቼክ አዉጪዉ በስምምነቶቹ መሰረት አለመፈጸሙን በአምጪዉ ላይ መቃወሚያ ሉያደርግ እንደማይችል ተደንግጓል። ይህ ድንጋጌ በአንድ በኩል የንግድ ሕጉ በአንቀጽ 827 ላይ የተመለከቱ መግለጫዎች ተሟልቶ ያልተገለጸ ቼክ ተፈርሞ ለአምጪዉ የሚስጥበትን አግባብ በመደንገግ ለእንዱህ አይነት ቼክ (Blank Cheque) እዉቅና መስጠቱን የሚያሳይ ሲሆን በልላ አግባብ ደግሞ በቼክ ላይ የሚጻፈ መግለጫዎች ካለመሟላት ጋር በተያያዘ ሉነሱ የሚችለ መቃወሚያዎች በድንጋጌዉ ተለይተዉ የተገለጹት እንጂ ማናቸዉም መቃወሚያዎች እንዲልሆኑ የሚያስገነዝብ ነዉ።
እንዱሁም ቼክ በዋስትናነት አይሰጥም በሚል በሕግ የተደነገገ ክልከላ ባለመኖሩ በመርህ ደረጃ ቼክ ለዋስትና ላሰጥ ይችላል።ሆኖም በሰ/መ/ ላይ በቀን 26/08/2012 ዓ/ም በተሰጠ ዉሳኔ ላይ ቼኩ የተሰጠዉ ለዋስትና አላማ እንደሆነ ተገልጾ በጽሁፍ የዋስትና ዉል ስምምነት ካልተደረገ በስተቀር ቼክ ለዋስትና አላማ ተሰጥቷል በሚል የሚቀርብ ክርክር ተቀባይነት እንደላለዉ አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ተሰጥቷል።
ከላይ እንደተመለከተዉ ዕዲ ከፊዩ ወይም ቼክ አዉጪዉ በሕጉ የተፈቀደትን መቃወሚያዎች በማንሳትና ተገቢዉን ማስረጃዎች በማቅረብ ማስረዲት የሚችል መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ አምጪዉ ቼኩን ለባንክ አቅርቦ ባንኩ በቼክ አዉጪዉ ሂሳብ ዉስጥ በቂ ስንቅ አለመኖሩን ምክንያት በማድረግ ወይም በልላ መሰል ምክንያት በቼኩ የተመለከተዉን ገንዘብ ለአምጪዉ መክፈል እንደማይችል የሚገልጽ የእንቢታ ማስታወቂያ ለመስጠት ይገደዲል።አምጭዉም የእንቢታ ማስታወቂያዉን በማያያዝ ወይም ክስ ለማቅረብ አስፈላጊ የሆነዉን ሁኔታ በማሟላት በቼኩ ላይ የተመለከተዉ ገንዘብ ከወለድና አግባብነት ካላቸዉ ወጪዎች ጋር እንዱከፈለዉ ዲኝነት በመጠየቅ በአዉጪዉ ላይ ክስ መመስረት እንደሚችልና ጉዲዩን የሚዲኘዉ ፍርድ ቤትም በዚሁ አግባብ ሉወስን እንደሚችል በንግድ ሕጉ አንቀጽ 716/1 እና 873 ስር ከተደነገገዉ መገንዘብ ይቻላል።
ከላይ በዝርዝር የተመለከተዉን መሰረት በማድረግ የያዝነዉን ጉዲይ ስንመለከት አመልካች በቼኮቹ የሚከፈለዉን ገንዘብ መጠን እና ቀን በቼኮቹ ላይ ራሳቸዉ ባይጽፈም ለክርክሩ መነሻ የሆኑትን ቼኮች ፈርመዉ ለተጠሪ መስጠታቸዉ የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነዉ። በቼኮቹ ላይ የተጻፈዉን ቀን እና የገንዘብ መጠን የሞላዉ ተጠሪ መሆኑም የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነዉ። አከራካሪዉና በስር ፍርድ ቤት በተሰጠ ዲኝነት የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን ለመመርመር ያስፈለገዉ ነጥብ የገንዘብ መጠኑ እና ቀን ሳይጻፍበት በቼክ አዉጭዉ ተፈርሞ ለአምጪዉ የተሰጠ ቼክ (Blank Cheque) የሚኖረዉን ሕጋዊ ዉጤት የሚመለከት ነዉ።ከላይ በዝርዝር እንደተዲሰሰዉ በንግድ ሕጉ አንቀጽ 827 ስር ከተዘረዘሩት መግለጫዎች አንደ እንኳን የላለበት ሰነድ እንደ ቼክ አይቆጠርም በሚል በአንቀጽ 828 የተደነገገዉ ተፈጻሚ መሆን ያለበት የቼክን ልዩ ባህርይና በቼክ የሚፈጸመዉን የክፍያ ሥርዓት በሚያሳልጥ መልኩ በቼኩ ክፍያ እንዱፈጸም በመጠየቅ የቼኩን ሰነድ ተቀብል ክፍያ ለሚፈጽመዉ ባንክ ቼኩ በሚቀርብበት ጊዜ ነዉ። በመሆኑም ለክርክሩ መነሻ የሆኑት ሁለቱም ቼኮች በአመልካች ተፈርመዉ ለተጠሪ በተሰጡ ጊዜ ከንግድ ሕጉ አንቀጽ 827 አንጻር ቀንና የገንዘብ መጠናቸዉ ባለመጻፈ የተሟለ ባለመሆናቸዉ እንደ Blank Cheque የሚቆጠሩ ቢሆኑም ተጠሪ ቀንና የገንዘብ መጠን ሞልቶ ለከፊዩ ባንክ ባቀረበ ጊዜ ተሟልተዉ ቀርበዋል።ክፍያ ያልተፈጸመባቸዉም በአመልካች ተንቀሳቃሽ ሂሳብ በቂ ስንቅ ባለመኖሩ ምክንያት እንደሆነ ስለተረጋገጠ የንግድ ሕጉ አንቀጽ 827 እና 828 ያስቀመጣቸዉን አንድን ሰነድ ቼክ የሚያሰኙ መገለጫዎችን የሚያሟለ ወይም እንደ ቼክ የሚቆጠሩ እና ሕጋዊ ዉጤት ያላቸዉ ናቸዉ።
እንዱሁም የንግድ ሕጉ አንቀጽ 827ም ሆነ 828 በቼኩ ላይ የሚጻፈዉን ቀን እና በቼኩ የሚከፈለዉን የገንዘብ መጠን የግድ ቼክ አዉጪዉ ወይም ወኪለ ብቻ መጻፍ አለበት የሚል አቋም የለዉም።
በተጨማሪም የስር ፍርድ ቤት በማስረጃ እንዲረጋገጠዉ ለዚህ ክስ መነሻ የሆኑ ቼኮችን ለተጠሪ ከመስጠታቸዉ በፉት ግራ ቀኝ በመካከላቸዉ አስቀድመዉ የመሰረቱትን መተማመን መሰረት በማድረግ አመልካች ቀንና የገንዘብ መጠን ያልተጻፈበትን ቼክ ፊርማቸዉን ብቻ አኑረዉ ለተጠሪ ሰጥተዉ ተጠሪም ቀንና የገንዘብ መጠን ሞልቶ ቼኩን ለባንክ አቅርቦ ከአመልካች ሂሳብ ላይ በቼኩ ላይ የተጻፈዉን ገንዘብ እንዱከፈልዉ አድርጎ መቀበለ በስር ፍርድ ቤት በማስረጃ ተረጋግጧል።ይህም በግራ ቀኙ መካከል በመተማመን ላይ የተመሰረተ የቀደመ ግንኙነት መኖሩን እና በዚህም መነሻ አመልካች ለተጠሪ ክፍያ ለመፈጸም ተመሳሳይ ቼክ ፈርመዉ ለመስጠት ያስቻለ የሥራ ግንኙነት እንደነበራቸዉ የሚያሳይ ነዉ። እንዱሁም አመልካች የመዋዋል ነጻነታቸዉን በመጠቀም ለክርክሩ መነሻ የሆኑትን ቼኮች ፈርመዉ ነገር ግን ቀንና የሚከፈለዉን የገንዘብ መጠን ሳይጽፈ ለተጠሪ መስጠታቸዉን ፈቅደዉ ያደረጉት መሆኑን የሚያሳይ ነዉ።ከዚህ ጋር በተያያዘ በሁለቱም ቼኮች ላይ ያለዉ ፊርማ የራሳቸዉ ፊርማ እንዲልሆነ በመግለጽ አመልካች አልካደም።በቼኮቹ ላይ የተጻፈዉ ቀንና የገንዘብ መጠን በተጠሪ መጻፈ ያልተካደ በመሆኑ በፍረንሲክ ማስመርመሩ ፊይዲ ስለማይኖረዉ ከዚህ አኳያ አመልካች ይህ የቼኮቹ ይዘት በፍሬንሲክ እንዱመረመር ያቀረቡትን ጥያቄ ፍርድ ቤቱ ባለመቀበለ የተፈጸመ ስህተት የለም።
በተጨማሪም አመልካች በአንድ በኩል ቼኮቹን ለተጠሪ የሰጡት ወንድማቸዉ ከተጠሪ ለወሰደት የፔትሮሉየም ምርቶች ለዋስትና አላማ እንደሆነ ገልጸዉ ክሱን እንዱከላከለ እንዱፈቀድላቸዉ ባቀረቡት ማመልከቻ አስፈቅደዋል። በልላ በኩል ደግሞ በመከላከያ መልሳቸዉ ላይ ይህንን ምክንያት ቀይረዉ ራሳቸዉ ከተጠሪ የፔትሮሉየም ምርቶችን ወስደዉ ለማከፊፈል ከተጠሪ ጋር ባደረጉት የቃል ንግግር መነሻ ለቅድመ ክፍያ ዋስትና እንዱሆኑ ቼኮቹን ቢሰጡም ባደረጉት ንግግር መሰረት ዉል ባለመፈጸሙ የነዲጅ ምርቶችን ከተጠሪ ባለመረከባቸዉ ተጠሪ ከቅን ልቦና ዉጭ ቼኮቹ ላይ ቀንና የገንዘብ መጠን በመሙላት ክፍያ እንዱፈጽምለት በመጠየቅ ለባንክ እንዲቀረበ በመግለጽ ክርክር ማቅረባቸዉን የስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ ግልባጭ ስለሚያሳይ ከዚህ አኳያ ያቀረቡት ክርክር እርስ በእርሱ የሚጣረሰ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤት የአመልካች ክርክር ተአማኚነት የለዉም ማለቱም የሚነቀፍ አይደለም።ይህ መከራከሪያቸዉም በንግድ ሕጉ አንቀጽ 841 ስር በመቃወሚያነት ሉነሱ የሚችለ መከራከሪያዎች ናቸዉ ተብለዉ ከተመለከቱት አንጻር ሲታይ ቼኮቹን ፈርመዉ ለተጠሪ ሲሰጡ ተጠሪ ቼኮቹን ያገኘዉ በክፈ ልቦና አመልካችን ለመጉዲት አስቦ ከባድ ጥፊት በመፈጸም እንደሆነ በመግለጽ ካለመከራከራቸዉም በተጨማሪ ይህንን የሚያሳይ ተገቢዉን ማስረጃ በማቅረብ ባለማስረዲታቸዉ ተጠሪ የገንዘብ መጠኑን የሞላዉ ስለቼኩ ቀን እና የገንዘብ መጠን አሞላል ያደረጉትን ስምምነት በሚቃረን አኳኋን ነዉ በሚል የሚያነሱት በሕጉ ተቀባይነት ያለዉ መከራከሪያ ባለመሆኑ በዚህ ረገድ የተፈጸመ ስህተት የለም።
ከዚህም በተጨማሪ ለክርክሩ መነሻ የሆኑትን ቼኮች ለተጠሪ ፈርመዉ የሰጡት በመካከላቸዉ ባለዉ ስምምነት መነሻ የፔትሮሉየም ምርት ሲቀበለ ለቅድሚያ ክፍያ ዋስትና እንዱሆን በሚል ነዉ በማለት የተከራከሩ ቢሆንም አመልካች ለክርክሩ መነሻ የሆኑ ቼኮችን ለተጠሪ ፈርመዉ የሰጡት ለቅድመ ክፍያ ዋስትና አላማ እንደሆነ የሚያሳይ በጽሁፍ የተደረገ የዋስትና ዉል በማስረጃነት አላቀረቡም።በመሆኑም አመልካች ከዚህ አኳያ ያቀረቡትንም ክርክር በሰ/መ/ ላይ በቀን 26/08/2012 ዓ/ም በተሰጠ አስገዲጅ የሕግ ትርጉም መሰረት ለክሱ መነሻ የሆኑ ቼኮችን ለዋስትና መስጠታቸዉን በማስረጃ ያላስረደ በመሆኑ በዚህም ረገድ በስር ፍርድ ቤት በተሰጠ ዉሳኔ የተፈጸመ ስህተት የለም።የሥር ፍርድ ቤት ተገቢዉን ጭብጥ ሳይዝና ማስረጃ በአግባቡ ሳይመዝን እንደወሰነ በመግለጽ የቀረበ መከራከሪያም ቢሆን የስር ፍርድ ቤት በጉዲዩ ላይ ዉሳኔ የሰጠዉ ተገቢዉን ጭብጥ በመያዝና ለጉዲዩ አግባብነት ያላቸዉን የግራ ቀኙን ማስረጃዎች በመመዘን እንደሆነ የዉሳኔዉ ይዘት ስለሚያሳይ በዚህም ረገድ በዚህ ችልት ደረጃ ሉታረም የሚችል የተፈጸመ ስህተት አላገኘንም። ስለሆነም ተከታዩን ወስነናል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 20/02/2012 ዓ/ም እና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 13/06/2012 ዓ/ም የሰጠዉ ትእዛዝ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ጸንተዋል።
ግራ ቀኝ በዚህ ችልት ያወጡትን ወጭ የየራሳቸዉን እንዱችለ ተወስኗል።
ት እ ዛ ዝ
የዉሳኔዉ ግልባጭ ለሥር ፍርድ ቤት ይተላለፍ። ግራ ቀኙ ሲጠይቁም ግልባጩ ይሰጣቸዉ።
በመዝገቡ ላይ የተሰጠ እግድ ካለ ተነስቷል።ይጻፍ።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.