No summary available.
የሰ/መ/ የካቲት 30 ቀን 2013 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ ተሾመ ሽፈራዉ ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግሥቱ ነጻነት ተገኝ አመልካች፡- ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ ተጠሪዎች፡-
ጉዲዩ የሦስተኛ ወገን የመድን ሽፊን የተገባለት ተሽከርካሪ በሦስተኛ ወገኖች ላይ ጉዲት አድርሷል ተብል ካሳ ለማስከፈል ዲኝነት ተጠይቆ በቀረበ ክርክር መድን ሰጪዉ በሦስተኛ ወገኖች ላይ ጉዲቱ የደረሰዉ በመድን ገቢዉ ጥፊት ነዉ በሚል የሚያነሳዉን ክርክር ሕጋዊ ዉጤት የሚመለከት ነዉ። 1ኛ ተጠሪ በምስራቅ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአሁን አመልካች ፣በ2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ላይ እና በስር 3ኛ ተከሳሽ ላይ በመሰረቱት ክስ ንብረትነቱ የአሁን 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች በሆነ በሰላዲ ቁጥር አማ03-12248 በሚታወቅ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ተሳፍረዉ ሲጓዙ በግምት 40 ሜትር ዝቀታማ ቦታ ላይ በመግባቱ ምክንያት በደረሰዉ አደጋ የግራ እግራቸዉ የጭን አጥንት የመሰበር ጉዲት እና የሕሉና ጉዲት እንደደረሰባቸዉ በመግለጽ ለህክምና የወጣ ወጪ፣ከጉዲቱ ለማገገም ለአልሚ ምግብ የወጣ ወጪ፣ለህክምና ለመመላለስ ለትራንስፖርትና ለአልጋ የወጣ ወጪና የሞራል ጉዲት ካሳ ጨምሮ በድምሩ ብር 74,358.00 አመልካች፣የአሁን 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች እንዱሁም የስር 3ኛ ተጠሪ አሽከርካሪዉ በአንድነትና በነጠላ ኃላፉነት እንዱከፍለ እንዱወሰንላቸዉ ዲኝነት ጠይቀዋል።
2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች በ1ኛ ተጠሪ ላይ ጉዲት የደረሰባቸዉ በተሽከርካሪዉ ተሳፍረዉ ሲሄደ በመሆኑ ሉከፈላቸዉ የሚገባዉ የካሳ መጠን በንግድ ሕጉ አንቀጽ 579 መሰረት ከብር 40,000.00 ሉበልጥ አይገባም። የህሉና ጉዲት ካሳም ከብር 1000.00 በላይ ልንጠየቅ አይገባም። ለምግብ፣ ለአልጋና ለትራንስፖርት አወጣሁኝ ብለዉ የጠየቁት የሕግና የማስረጃ ድጋፍ የላለዉና የተጋነነ ነዉ በማለት ተከራክረዋል።
አመልካች ለክሱ በሰጠዉ መልስ በፖሉስ ሪፖርት መሰረት አደጋዉ የደረሰዉ ተሽከርካሪ መጫን ከሚገባዉ በላይ ከ40 እስከ 48 ሰዉ ጭኖ ሲሄድ በመሆኑ በአመልካችና የተሽከራከሪዉ ባለሀብቶች በሆኑት 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች መካከል በተደረገዉ የኢንሹራንስ ዉል የማግለያ አንቀጽ 2 መሰረት ጉዲቱ ተሽከርካሪዉ በሕጋዊ መንገድ እየተሽከረከረ ባለበት ሂደት የደረሰ ባለመሆኑ አመልካች ካሳ የመክፈል ኃላፉነት የለብኝም ሲል ተከራክሯል።ኃላፉነት አለብህ ከተባለም 1ኛ ተጠሪ እንዱከፈላቸዉ የጠየቁት ካሳ የተጋነነ በመሆኑና በኢንሹራንስ ዉለ መሰረት የአመልካች ኃላፉነት ከብር 40,000.00 በላይ ላሆን አይገባም።የሞራል ካሳ ለመክፈል የመድን ሽፊን አልሰጠሁም በማለት ተከራክሯል።
ፍርድ ቤቱም በመ/4 ላይ ግራ ቀኙን ክርክርና ምስክሮች በመስማት የአሁን 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ከስር 3ኛ ተከሳሽ ጋር በመሆን በአንድነትና በነጠላ ኃላፉነት በአሁን 1ኛ ተጠሪ ላይ በደረሰዉ ጉዲቱ ምክንያት 1ኛ ተጠሪ ያወጡትን ልዩ ልዩ ወጪዎች በተመለከተ እና ለህሉና ጉዲት ካሳ ብር 63,858.00 እንዱከፍለ ወስኗል።እንዱሁም አመልካች በክርክሩ ላይ እንደገለጸዉ መኪናዉ በ1ኛ ተጠሪ ላይ ጉዲት በደረሰበት ጊዜ ብዙ ሰዎች በትርፍነት ጭኖ ሲያጓጉዝ የነበረ መሆኑ በማስረጃ የተረጋገጠ ቢሆንም አመልካች ከ2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ጋር የፈጸመዉ የመድን ዉል የ2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ተሽከሪካሪ በሦስተኛ ወገን ላይ ለሚያደርስ ጉዲት ካሳ ለመክፈል የተደረገ በመሆኑና አመልካች በክርክሩ በገለጸዉ መሰረት በኢንሹራንስ ዉለ ላይ በማግለያነትም እንዲልተመለከተ ገልጾ አመልካች ካሳ የመክፈል ኃላፉነት የለብኝም ብል መከራከር አይችልም በማለት 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎችና የስር 3ኛ ተከሳሽ ይክፈለ ከተባለዉ ገንዘብ ላይ አመልካች ብር 40,000.00(አርባ ሺህ ብር) ለአሁን 1ኛ ተጠሪ እንዱከፍል ወስኗል። እንዱሁም በክሱ ምክንያት የአሁን 1ኛ ተጠሪ ያወጡትን ወጪዎች በተመለከተም አመልካች፣ የአሁን 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎችና የስር 3ኛ ተከሳሽ ብር 4,585.00 ለአሁን 1ኛ ተጠሪ እንዱከፍለ ወስኗል።
አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢያቀርብም ፍርድ ቤቱ በመ/ ላይ በቀን 26/09/2012 ዓ/ም በሰጠው ትዕዛዝ ይግባኙን በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞበታል።አመልካች በቀን 10/02/2013 ዓ/ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረበዉ በዚህ መልኩ በተሰጡ ዉሳኔዎች መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን የአቤቱታዉ ይዘት በአጭሩ የሚከተለዉ ነዉ።
በተሽከርካሪዉ ላይ አደጋ በደረሰ ጊዜ ተሽከርካሪዉ መጫን ከሚገባዉ 24 ሰዉ በላይ ከ40-48 ሰዉ ጭኖ እንደነበር በማስረጃ ተረጋግጧል።የኢንሹራንስ ዉል አንደማንኛዉም ዉል ሕጋዊ ተግባራት ሲከናወኑ ለሚደርስ አደጋ የካሳ ክፍያ የሚፈጸምበት ዉል እንጂ በሕገ-ወጥ ድርጊት ምክንያት ለመጣ ጉዲት ጭምር የመካስ ኃላፉነት የሚያስከትል አይደለም።የኢንሹራንስ ዉለ ተሽከርካሪዉ ከአቅሙ በላይ ጭኖ ሲሽከረከር ለሚደርስ አደጋ አመልካች የመድን ሽፊን እንደማይሰጥ ወይም በዉል እንደተገለለ የተገለጸዉን ባለማገናዘብ ካሳዉን ሙለ በሙለ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች እንዱከፍለ መወሰን ሲገባዉ የስር ፍርድ ቤት አመልካች ብር 40,000.00 ካሳ እንዱከፍል መወሰኑ ከመድን ዉለና ከሕጉ ዉጭ ስለሆነ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ። አመልካች ካሳ የመክፈል ኃላፉነት አለበት ከተባለም የአመልካች ኃላፉነት እስከ ብር 40,000.00 ሆኖ እያለ አመልካች ከላልች ተከሳሾች ጋር በክሱ ምክንያት የወጣዉን ወጪ ብር 4,585.00 ለ1ኛ አመልካች እንዱከፍል መወሰኑ ከኢንሹራንስ ዉለ ዉጭ በመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ በማለት አቤቱታዉን አቅርቧል።
የሰበር አጣሪ ችልት አቤቱታውን መርምሮ ጉዲት አድራሹ ተሽከርካሪ ከተፈቀደለት ተሳፊሪ በላይ በመጫኑ የተነሳ አደጋዉ የደረሰ መሆኑ በተገለጸበት አመልካች በኢንሹራንስ ዉለ መሰረት ካሳ ሉከፍል ይገባል በሚል የተወሰነበትን አግባብ ከሕጉና ከኢንሹራንስ ዉለ አንጻር እንዱጣራ ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልት አንዱቀርብ ትዕዛዝ በመስጠቱ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች በቀን 06/04/2013 ዓ/ም የተፃፈ በአጭሩ የሚከተለዉን መልስ አቅርበዋል።
ተሽከርካሪዉ መጫን ከሚገባዉ ሰዉ በላይ ጭኖ አልተገኘም።ከአቅም በላይ ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ተሽከርካሪ በሰዉም ሆነ በንብረት ላይ በሚያደርሰዉ ጉዲት የመድን ሽፊን እንደማይሰጥ የመድን ዋስትና ዉለ ላይ በግልጽ የደነገገዉ ነገር የለም።ስለሆነም አመልካች ካሳ ሉከፍል አይገባም በማለት ያቀረበዉ የዉልና የሕግ ድጋፍ ያለዉ ባለመሆኑ ዉድቅ ይደረግልን በማለት ተከራክረዋል።አመልካችም በቀን 06/05/2013 ዓ/ም የተጻፈ የመልስ መልስ በማቅረብ ተከራክሯል።
1ኛ ተጠሪ መጥሪያ ደርሷቸዉ መልሳቸዉን ባለማቅረባቸዉ መልስ የመስጠት መብታቸዉ ታልፎል።
ከዚህ በላይ የተመዘገበዉ የግራ ቀኝ ክርክርና በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ዉሳኔዎች ይዘት ሲሆን እኛም ሰበር አጣሪ ችልት ከያዘዉ ጭብጥ አንጻር የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን አግባብነት ካለዉ ሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ መርምረናል።
እንደመረመርነውም በ2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ባለቤትነት በሰላዲ ቁጥሩ አማ03-12248 በሚታወቅ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በሦስተኛ ወገኖች ላይ ሉሚያደርሰዉ አደጋ አመልካች የኢንሹራንስ ሽፊን መስጠቱና በዚህ ተሽከርካሪ ተሳፍረዉ ሲጓዙ ተሽከርካሪዉ ገደል ዉስጥ በመግባት በ1ኛ ተጠሪ ላይ ጉዲት መድረሱ ተረጋግጧል።ግራ ቀኙን ያከራከረዉ 1ኛ ተጠሪ ላይ ጉዲት የደረሰዉ ተሽከርካሪዉ እንዱጭን ከተፈቀደለት በላይ ብዙ ሰዉ ትርፍ ጭኖ በማጓጓዝ ላይ እያለ በመሆኑ በኢንሹራንስ ዉለ የማግለያ (Exception) አንቀጽ 2 መሰረት በእንዱህ አይነት ምክንያት ጉዲት ሲደርስ ካሳ የመክፈል ኃላፉነት የለብኝም ሲል አመልካች ያቀረበዉ መከራከሪያ ነዉ።
እንደሚታወቀዉ በተሽከርካሪ አደጋ ምክንያት በሦስተኛ ወገኖች ላይ ለሚደርስ ጉዲት የሚሰጥ የኢንሹራንስ ሽፊን የሚመነጨዉ በኢንሹራንስ ሰጪዉና በኢንሹራንስ ገቢዉ መካከል በሚደረግ የኢንሹራንስ ዉል ፖሉሲ መነሻ ነዉ።ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በተሽከርካሪ አደጋ በሦስተኛ ወገን ላይ ለሚደርስ አደጋ የኢንሹራንስ ሽፊን ለመስጠት በወጣ አዋጅ ቁጥር 799/2005 በተዘረጋዉ ስርዓት መሰረት በኢንሹራንስ ዉለ ተዋዋይ ወገን ያልሆኑ አደጋ የደረሰባቸዉ ሦስተኛ ወገኖች በሽፊኑ ተጠቃሚ እንዱሆኑ የሚያደርግ ግንኙነት በሕግ ተፈጥሯል። በዚህ አግባብ ምንም እንኳን አመልካችና የአሁን 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች የኢንሹራንስ ዉለ ተዋዋዮች ቢሆኑም ከዉለ ተጠቃሚዎች ሦስተኛ ወገኖች ጭምር በመሆናቸዉ የኢንሹራንስ ዉል ፖለሲዉ እና አዋጅ ቁጥር 799/2005 የሦስትዮሽ ግንኙነትን እንዲቋቋመ መረዲት ያስፈልጋል።
አመልካች ክርክሩን ያቀረበዉ በኢንሹራንስ ዉለ ማግለያ አንቀጽ 2 ስር የተደነገገዉን ኢንሹራንስ ሰጪዉ ኃላፉ የማይሆንበትን የማግለያ ድንጋጌ መሰረት በማድረግ ነዉ። ሆኖም የኢንሹራንስ ዉለ በተሽከርካሪ አደጋ በሦስተኛ ወገኖች ላይ የሚደርሰዉን ጉዲት ለመካስ የተደረገ እንደመሆኑ ይህ የአመልካች መከራከሪያ በአዋጅ ቁጥር 799/2005 አንቀጽ 6 ስር ከተደነገገዉ አንጻር ተገናዝቦ መታየት ይኖርበታል።በአዋጁ አንቀጽ 6/1 ስር በኢንሹራንስ ዉል ፖሉሲዉ ዉስጥ ተጠያቂነትን አያስከትልም የሚል ወይም በፖሉሲዉ መሰረት ለካሳ ጥያቄ መነሻ የሚሆነዉ ክስተት ከደረሰ በኋላ የተወሰነ ድርጊት ከተፈጸመ ወይም ሳይፈጸም ከቀረ ኃላፉነት ቀሪ ይሆናል የሚል ሁኔታ ቢቀመጥ ሕጋዊ ዉጤት እንደማይኖረዉ ተድንግጓል።ከዚህ መገንዘብ የሚቻለዉ በሦስተኛ ወገኖች ላይ በተሽከርካሪ ለሚደርስ አደጋ የኢንሹራንስ ሽፊን የሰጠ ኢንሹራንስ ኩባንያ በአንሹራንስ ዉለ ላይ ኢንሹራንስ ገቢዉ ይህንን ካደረገ ወይም ካላደረገ ተጠያቂነት አይኖርብኝም በማለት ያስቀመጠዉን ሁኔታ መሰረት በማድረግ በሦስተኛ ወገን ላይ ለደረሰዉ ጉዲት ካሳ ላለመክፈል ጉዲት ለደረሰበት ሦስተኛ ወገን መከራከሪያ ሉያደርግ እንደማይችል ነዉ።በኢንሹራንስ ዉል ፖሉሲዉ ላይ የተቀመጠዉን የማግለያ ወይም ላላ ሁኔታ መሰረት በማድረግ ኢንሹራንስ ሰጪዉ በኢንሹራንስ ገቢዉ ላይ መከራከሪያ ሉያደርግ የሚችለዉ በመጀመሪያ ጉዲት ለደረሰበት ሦስተኛ ወገን በአዋጅ ቁጥር 799/2005 አንቀጽ 16 እና በኢንሹራንስ ዉል ፖሉስዉ በተመለከተዉ መሰረት ካሳ ከከፈለ በኋላ እንደሆነ በአዋጁ አንቀጽ 6/2 ስር የተደነገገዉ ያስገንዝባል።
በመሆኑም አመልካች ከ2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ጋር በፈጸመዉ የኢንሹራንስ ፖሉሲ ላይ የተመለከተዉን ኃላፉነት የሚያስቀር ማግለያ በመጥቀስ በ2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ላይ መከራከሪያ ሉያደርግ የሚችለዉ አስቀድሞ በተሽከርካሪዉ በ1ኛ ተጠሪ ላይ የደረሰዉን ጉዲት ከካሰ በኋላ ነዉ ብለናል።ስለሆነም የሥር ፍርድ ቤቶች አመልካች ለ1ኛ ተጠሪ ካሳ የመክፈል ኃላፉነት የለብኝም ሲል ያቀረበዉን መከራከሪያ ዉድቅ በማድረግ በኢንሹራንስ ዉለ መሰረት 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ይክፈለ ተብል ከተወሰነዉ ላይ ብር 40,000.00 አመልካች ለ1ኛ ተጠሪ እንዱከፍል መወሰናቸዉ ሕግን መሰረት ያደረገ በመሆኑ የተፈጸመ ስህተት የለም።
እንዱሁም በኢንሹራንስ ዉል ፖሉሲ እና በአዋጅ ቁጥር 799/2005 አንቀጽ 16(1/ለ) መሰረት አመልካች በ1ኛ ተጠሪ ላይ ለደረሰዉ የአካል ጉዲት ለመክፈል የሚገደደዉ የካሳ መጠን እስከ ብር 40,000.00 ድረስ ብቻ እንደሆነ የተመለከተ ቢሆንም ይህ ኃላፉነት በቀጥታ ኢንሹራንስ በተገባለት ተሽከርካሪ ሦስተኛ ወገን በሆኑት 1ኛ ተጠሪ አካል ላይ የደረሰዉን ጉዲት ከመካስ ጋር የተያያዘ ነዉ።በክሱ ምክንያት የወጣ ወጪ ለ1ኛ ተጠሪ እንዱከፈላቸዉ የተወሰነዉ ደግሞ በኢንሹራንስ ዉለና በሕግ በተደነገገዉ መሰረት ካሳ ባለመከፈለ ምክንያት 1ኛ ተጠሪ ለክስ በመዲረጋቸዉና በክርክሩ በመርታታቸዉ በክሱ ምክንያት ያወጡት ወጪ ሉተካላቸዉ እንደሚገባ በመታመኑ ነዉ።
በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 462 ስር በተደነገገዉ መሰረት በክርክሩ የረታዉ ሰዉ በክሱ ምክንያት ያወጣዉን ወጪ ተረቺዉ እንዱተካለት ፍርድ ቤቱ ትክክል ነዉ ብል በሚገምተዉ መሰረት መወሰን እንደሚችል ተደንግጓል። በመሆኑ 1ኛ ተጠሪ በክሱ ምክንያት ያወጡትን ወጪ አመልካች ከላልች ተከራካሪዎች ጋር በመሆን መጠኑ ከላይ የተጠቀሰዉን ገንዘብ ለ1ኛ ተጠሪ እንዱከፍል መወሰኑ ሥነ ሥርዓት ሕጉን የተከተለ በመሆኑ በዚህም ረገድ የተፈጸመ ስህተት የለም። በመሆኑም ተከታዩን ወስነናል።
1.በምስራቅ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/4 ላይ በቀን 03/06/2012ዓ/ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 26/09/2012 ዓ/ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ጸንተዋል።
ት እ ዛ ዝ
የዉሳኔዉ ግልባጭ ለሥር ፍርድ ቤት ይተላለፍ። ግራ ቀኙ ሲጠይቁም ግልባጩ ይሰጣቸዉ።
በመዝገቡ ላይ የተሰጠ እግድ ካለ ተነስቷል።ይጻፍ።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.