No summary available.
መጋቢት 24 ቀን 2012 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሀኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሀኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች- ሕብረት ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ ተጠሪ- ሚካኤል አባተ ሕንፃ ተቋራጭ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ መድን ሰጪ ለሦስተኛ ወገን የከፈለዉን ካሳ ከመድን ገቢዉ ለማስመለስ በሚቀርብ ክስ ላይ ተፈጻሚነት የሚኖረዉን ይርጋ እና አቆጣጠሩን የሚመለከት ነዉ። ክርክሩ የጀመረው በፋደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ሲሆን፣ አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።
አመልካች ባቀረበው ክስ ንብረትነቱ የተጠሪ የሆነው የሰላዲ ቁጥሩ ኮድ 3-35810 ኢት የሆነ ተሸከርካሪ ተገቢ ባልሆነ የመንጃ ፍቃድ ሲሽከረከር በፈፀመው ጥፊት በልላ ሶስተኛ ወገን በሆነው የሰላዲ ቁ. ኮድ 2-A24910 በሆነ አሸከርካሪና ግለሰብ ላይ ጉዲት ያደረሰ ሲሆን አመልካች ለተጠሪ በገባው የሶስተኛ ወገን የመድን ሽፊን ግዳታ መሰረት ጉዲት የደረሰበትን ተሸከርካሪ ያስጠገነና ለደረሰው የአካል ጉዲትም ካሳ በድምሩ ብር 92,987.4 መክፈለን ጠቅሶ ይህንኑ ገንዘብ ተከሳሽ ከወጪና ኪሳራ ጋር እንዱከፍል እንዱወሰንለት ዲኝነት ጠይቋል። ተጠሪ በበኩለ ክሱ የቀረበው ጉዲቱ ከደረሰ ከሁለት ዓመት በኋላ በመሆኑ በይርጋ ይታገዲል የሚል የመጀመሪያ መቃወሚያ በማቅረቡ ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተዉ ፍርድ ቤት በመቃወሚያዉ ላይ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ ከሳሽ ክሱን ያቀረበው ለክርክሩ መነሻ የሆነው ጉዲይ ከተፈጠረ ከሁለት ዓመት በኋላ በመሆኑ በንግድ ህጉ አንቀፅ 674 መሰረት በይርጋ ይታገዲል በማለት ብይን ሰጥቷል። ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተዉ የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም መዝገቡን አስቀርቦ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ የስር ፍርድ ቤትን ዉሳኔ በማፅናት ወስኗል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ከላይ የተጠቀሱትን የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔዎች በመቃወም ለማስለወጥ ሲሆን፣ አመልካች በቀን 22/09/2011 ዓ.ም በተፃፈ 03 ገፅ የሰበር አቤቱታ በስር ፍ/ቤቶች ተፈፅመዋል ያላቸውን ስህተቶች በመዘርዘር እንዱታረሙለት ጠይቋል። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘትም በአጭሩ በስር ፍ/ቤት ባቀረብነው ክስ ድርጊቱ በሰው አካልና በንብረት ላይ ጉዲት ማድረስ ስለሆነ በወንጀል የሚያስቀጣ በመሆኑ በፍትሐ ብሓር ህጉ መሰረት የይርጋው ዘመን አምስት ዓመት ቢሆንም በተፈፀመው ድርጊት ምክንያት የመጨረሻውን የካሳ ክፍያ ከተፈፀመበት 12/11/2009 ዓ.ም ጀምሮ የተሻሻለው ክስ እስከቀረበት ጊዜ ድረስ አንድ አመት እንኳ አልሞላውም። የይርጋ ጊዜው ሉቆጠር የሚገባውም አደጋው ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ ሳይሆን ካሳውን ከከፈልንበት ጊዜ አንስቶ መሆን አለበት። በዚህ ረገድ የስር ፍ/ቤቶች መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ነዉ የሚል ነው።
ጉዲዩም በሰበር አጣሪ ችልት ተመርምሮ በግራ ቀኙ መካከል ላለው ክርክር ተፈፃሚነት ያለው የንግድ ህጉ አንቀፅ 674 ነው? ወይስ የፍ/ህ/ቁ 2143 ነው? የሚለው መጣራት አለበት በሚል ታምኖበት ለዚህ ሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጓል። በዚሁም መሰረት ተጠሪ በጠበቃው አማካኝነት በቀን 23/03/2012 የተፃፈ መልሱን ያቀረበ ሲሆን የመልሱ ይዘትም አመልካች ለፈፀመው የካሳ ክፍያ ተጠሪ ወጪውን እንዱተካለት የጠየቀው ግንቦት 27 ቀን 2007 ዓ.ም ሲሆን ተጠሪ ወጪውን እንደማይተካ በግንቦት 29 ቀን 2007 ዓ.ም አሳውቋል። በዚህም ምክንያት ተጠሪ በስር ፍ/ቤት ክሱን ያቀረበው ሰኔ 22 ቀን 2009 ዓ.ም ስለመሆኑ በስር ፍ/ቤት በማስረጃ የተረጋገጠ ጉዲይ ነው። በልላ በኩል በአመልካችና በተጠሪ መካከል ያለው የኢንሹራንስ ውል ስምምነት ሲሆን ይህንን መሰረት አድርጎ ለሚቀርብ ክስ ተፈፃሚነት የሚኖረው የንግድ ህጉ እንጂ የፍትሐ ብሓር ህጉ አይደለም የሚል ነው።
አመልካችም በሰጠው የመልስ መልስ የሰበር አቤቱታውን በሚያጠናክር መልኩ ተከራክሯል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀውን ሲመስል ይህ ችልትም የአመልካችን የሰበር አቤቱታ በሰበር አጣሪ ከተያዘው ጭብጥና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸዉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መዝገቡን እንደሚከተለዉ መርምሮታል። እንደመረመረዉም አመልካች የሰላዲ ቁጥሩ 3-35810 ኢት ሆኖ ንብረትነቱ የአሁኑ ተጠሪ በሆነዉ ተሽከርካሪ በፈጸመዉ ጥፊት በሦስተኛ ወገን ላይ ለሚደርስ አደጋ የመድን ሽፊን መስጠቱ አላከራከረም። አመልካች በዚህ ተሽከርካሪ ምንክያት በ3ኛ ወገን ላይ ለደረሰ ጉዲት ካሳ ከከፈለ በኋላ በተጠሪ ላይ ባቀረበዉ ክስ ለጠየቀዉ ዲኝነት መሰረት ያደረገዉ ጉዲቱ የደረሰዉ ተገቢ ባልሆነ መንጃ ፍቃድ በያዘ አሽከርካሪ ምክንያት መሆኑን እና ይህም ሲሆን በአዋጅ ቁጥር 799/2005 መሰረት ከተጠሪ የማስመለስ መብት ያለዉ መሆኑን በመጥቀስ ነዉ። ለጉዲቱ መንስኤ የሆነዉ አደጋ የደረሰዉ በ17/05/2007 ዓ.ም መሆኑ፣ አመልካች ክፍያዉን ለሦስተኛ ወገን የፈጸመዉ ሐምል 12 ቀን 2008 ዓ.ም መሆኑ እንዱሁም ክሱ የቀረበዉ ሰኔ 22 ቀን 2009 ዓ.ም ስለመሆኑ በግራ ቀኝ የታመነ ነዉ። ከፍ ሲል እንደተመለከተዉ የስር ፍርድ ቤቶች የተጠሪን የመጀመሪያ መቃወሚያ በመቀበል የአመልካችን ክስ በይርጋ ዉድቅ በማድረግ ለሰጡት ዉሳኔ መሰረት ያደረጉት አደጋዉ ከደረሰበት ቀን ጀምሮ ክሱ እስከቀረበበት ቀን ድረስ ያለዉ ጊዜ ሲቆጠር ከሁለት ዓመት በላይ መሆኑን በንግድ ህጉ አንቀጽ 674 (1) ላይ የተመለከተዉን ድንጋጌ በዋቢነት በመጥቀስ ስለመሆኑ ከዉሳኔዎቹ ይዘት የምንገነዘበዉ ነዉ።
በተሽከርካሪ አደጋ በሦስተኛ ወገኖች ላይ ለሚደርስ ጉዲት የሚሰጥ የመድን ሽፊን የሚመነጨዉ በመድን ሰጭዉና በመድን ገቢዉ መካከል በሚደረግ የመድን ዉል ፖሉሲ መነሻ ቢሆንም በተሽከርካሪ አደጋ በሦስተኛ ወገን ላይ ለሚደርስ አደጋ የመድን ሽፊን ለመስጠት በወጣ አዋጅ ቁጥር 799/2005 በተዘረጋዉ ስርዓት መሰረት በመድን ዉለ ተዋዋይ ወገን ያልሆኑ አደጋ የደረሰባቸዉ ሦስተኛ ወገኖች በሽፊኑ ተጠቃሚ እንዱሆኑ የሚያደርግ ግንኙነት መፈጠሩን መገንዘብ የሚቻል ነዉ። በዚህ አግባብ ምንም እንኳን ግራ ቀኝ የመድን ዉለ ተዋዋዮች ቢሆኑም ከዉለ ተጠቃሚዎች ሦስተኛ ወገኖች ጭምር በመሆናቸዉ የመድን ዉል ፖሉሲዉ እና አዋጅ ቁጥር 799/2005 የሦስትዮሽ ግንኙነትን እንዲቋቋመ መረዲት ያስፈልጋል። አመልካች በተጠሪ ላይ ክሱን የመሰረተዉ የመድን ዉለን እና በአዋጅ ቁጥር 799/2005 መሰረት በማድረግ በመሆኑ ግንኙነታቸዉ በመድን ዉል ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ለጉዲዩ አግባብነት የሚኖረዉ የይርጋ ድንጋጌ ይህንን በዉል ላይ የተመሰረተዉን ግንኙነት መሰረት ያደረገ ላሆን ይገባል። ግንኙነቱም የመድን ዉልን መሰረት ያደረገ በመሆኑ ለጉዲዩ ተፈፃሚነት ያለዉ በንግድ ህጉ አንቀጽ 674 ላይ የተመለከተዉ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤቶች በዉሳኔያቸዉ ይህን ድንጋጌ መጥቀሳቸዉ በመሰረቱ የሚነቀፍ አይደለም። በመሆኑም ከዉል ዉጭ የሆነ ኃላፉነት መነሻ በማድረግ ካሳ ለማስከፈል ለሚቀርብ ክስ ተፈጻሚነት እንዱኖረዉ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2143/2 ስር የተደነገገዉ የይርጋ ድንጋጌ ለዚህ ጉዲይ ተፈጻሚነት ስለላለዉ አመልካች ለጉዲዩ ተፈጻሚነት ያለዉ የይርጋ ድንጋጌ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2143/2 ስር የተደነገገዉ ነዉ በሚል ያቀረበዉን ክርክር አልተቀበልነዉም።
ይልቁንም የዚህን ችልት ምላሽ የሚሻ ጭብጥ የሁለት ዓመቱ የይርጋ ጊዜ የሚቆጠረዉ ለጉዲቱ ምክንያት የሆነዉ አደጋ ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ ነዉ የሚል የስር ሁለቱ ፍርድ ቤቶች የደረሱበት ድምዲሜ የግራ ቀኝን ክርክር መሰረታዊ ባህርይ ያገናዘበ መሆን ያለመሆኑ ነዉ። ስለ ሦስተኛ ወገን ኢንሹራንስ የሚደነግገዉ አዋጅ ቁጥር 799/2005 አንቀጽ 6/2 መድን ሰጪዉ በአደጋ ምክንያት ለደረሰ ጉዲት ካሳ ለሦስተኛ ወገን ከከፈለ በኋላ መድን ገቢዉ እንዱተካለት መጠየቅ እንደሚችል ያመለክታል።
ይሁንና እንዱህ ዓይነት ክስ መቅረብ ያለበትን የይርጋ ጊዜ በተመለከተ አዋጁ በተለይ አይደነግግም።
ከኢንሹራንስ ዉል ጋር የተያያዙ ክሶችን ይርጋ በተመለከተ የንግድ ሕጉ አንቀጽ 674/1 ስር በኢንሹራንስ ዉል ምክንያት የሚቀርብ ማንኛዉም ክስ የሚታገደዉ ለክሱ ምክንያት የሆነዉ ጉዲት ከተደረገበት ወይም በጉዲዩ ጥቅም ያላቸዉ ወገኖች ጉዲቱን ካወቁበት ቀን ጀምሮ (በእንግሉዘኛዉ ቅጅ፡ …from the occurrence giving rise to the claim or from the day when the parties knew of the occurrence) ከሁለት ዓመት በኋላ ነዉ በማለት ይደነግጋል። ይህ ድንጋጌ የይርጋ ጊዜዉ መቁጠር የሚጀምረዉ ጉዲቱ ከደረሰበት ወይም መብት ያላቸዉ ወገኖች ጉዲት ስለመድረሱ ካወቁበት ጊዜ ጀምሮ እንደሆነ ያሳያል። መድን ሰጪዉ ለሦስተኛ ወገን የከፈለዉን ካሳ መድን ገቢዉ እንዱተካለት፣ በመካከላቸዉ ያለዉን የመድን ዉል ወይም ህግ መሰረት በማድረግ፣ መጠየቅ የሚችለዉ በቅድሚያ ካሳዉን ለሦስተኛ ወገን መክፈለ ሲረጋገጥ ስለመሆኑ እሙን ነዉ። ይህ ደግሞ ሦስተኛ ወገኑ ካሳዉ እንዱከፈለዉ የሚያቀርበዉን ጥያቄ መሰረት በማድረግ በመሆኑ የመድን ሰጪዉ የይተካልኝ ዲኝነት ጥያቄ የሚያቀርበዉ ሦስተኛ ወገኑ ካሳ እንዱከፈለዉ በሚያቀርበዉ ሁኔታ እና ጊዜ ላይ የሚወሰን መሆኑን የሚያሳይ ነዉ። ስለሆነም መድን ሰጪዉ ለሦስተኛ ወገን የከፈለዉ ካሳ በመድን ገቢዉ እንዱተካለት ለመጠየቅ ባለዉ መብቱ መስራት የሚችለዉ በሦስተኛ ወገን ጥያቄ መሰረት ካሳዉን ከከፈለዉ በኋላ በመሆኑ ጉዲቱ ከደረሰበት ወይም ስለጉዲቱ ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ የይተካልኝ ክስ ያቀርባል ተብል አይጠበቅም። ይህ እየታወቀ የሁለት ዓመት ጊዜዉ መቆጠር የሚጀምረዉ ጉዲቱ ከደረሰበት ወይም ጉዲቱ መድረሱ ከታወቀበት ጊዜ ጀምሮ ነዉ በሚል መወሰን ‛መብታቸዉን በተገቢዉ ጊዜ ለማስከበር የሚተጉ ሰዎችን ለማበረታት (to encourage diligence and to discourage negligence) ነዉ“ የሚለዉን የይርጋን መሰረታዊ ዓላማ የሚያፊልስ ከመሆኑም በላይ እንደ አመልካች ያለ ሰዎችን ፍትሕ የማግኘት መብት የመገደብ ዉጤት ሉያስከትል እንደሚችል መገንዘቡም ተገቢ ነዉ። ይህ በመሆኑም ለያዝነዉ ዓይነት ጉዲይ የሁለት ዓመት የይርጋ ጊዜ መቆጠር የሚጀምረዉ መቼ ነዉ? ለሚለዉ ነጥብ በግራ ቀኝ መካከል የተደረገዉ የመድን ዉል በባህሪዉ የሦስትዮሽ ግንኙነትን የሚመለከት ከመሆኑ አንፃር በማገናዘብ ትርጉም መስጠቱ ተገቢ ይሆናል።
ከላይ እንደተመለከተዉ ለዚህ ክርክር መነሻ የሆነዉ ጉዲይ የዉል ግንኙነትን መሰረት ያደረገ ነዉ። ከዉል የሚመነጩ ግንኙነቶች የሚገዙበት የይርጋ ደንቦች ስለ ዉልች በጠቅላላዉ በሚደነግገዉ የፍትሐብሕር ህጉ ክፍል ከአንቀጽ 1845-1856 የተመለከቱ ሲሆን፣ ከእነዚህም ድንጋጌዎች ዉስጥ አንደ ‛የይርጋው መነሻ ጊዜ“ በሚል በአንቀጽ 1846 ላይ የተመለከተዉ ድንጋጌ ነዉ። ይህ ድንጋጌ ‛የይርጋ ቀን መቆጠር የሚጀምረው ግዳታዉን ለመጠየቅ ተገቢ ከሆነዉ፤ ወይም ዉለ የሚሰጠዉ መብት ከተሰራበት ቀን ጀምሮ ነዉ“ በማለት የሚደነግግ ሲሆን፣ እንግሉዝኛዉ ‛The period of limitation shall run from the day when the obligation is due or the rights under the contract could be exercised‛ በማለት ይደነግጋል። በልላ በኩል የመድን ዉልን መሰረታዊ ባህርይ ከግምት ዉስጥ በማስገባት የንግድ ህጉ አንቀጽ 674/1 ከመድን ዉል የሚመነጩ ክሶች የሚቀርቡበትን የይርጋ ጊዜ በተለይ የሚደነግግ ቢሆንም፣ ከላይ እንደተገለጸዉ፣ ‛በመብት መስራት መጀመር“ የይርጋ መቁጠሪያ መነሻ ጊዜ ላሆን የሚችል ስለመሆኑ በግልጽ አላመላከተም። በመሆኑም የይርጋ መቁጠሪያ መነሻ ጊዜን በተመለከተ በፍትሐብሕር ህጉ እና በንግድ ህጉ መካከል ቅራኔ (contradiction) አለ ለማለት አይቻልም። በተለያዩ የህግ ክፍልች በሚገኙ ድንጋጌዎች መካከል ቅራኔን ከማፈላለግ ይልቅ ተደጋጋፉ ሆነዉ የጋራ ዓላማ የሚያሳኩበትን የህግ ትርጉም መሻት የህግ ባለሙያዎች ሉመርጡት የሚገባ የህግ አተረጓጓም ዘይቤ በመሆኑ ልዩ ህግ ጠቅላላ ዓላማ ካለዉ ህግ ቅድሚያ ይሰጠዋል (the special prevails over the general) የሚለዉን የህግ አተረጓጓም ተከትል ዉሳኔ ላይ ከመድረስ በፉት በሁለቱ የህግ ክፍልች መካከል የማይታረቅ፣ ምክንያታዊ የሆነ፣ በላቀ የህግ አዉጪዉ ፍላጎት የተደገፈ ግጭት መኖሩን ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ ይህ ሰበር ችልት በሰ/መ/ ላይ በሰጠዉ የህግ ትርጉም ላይ ካሰፈረዉ ሃሳብ መገንዘብ ይቻላል። ስለሆነም ከይርጋ ጊዜ አቆጣጠር ጋር በተያያዘ በንግድ ህጉ እና በፍትሐብሕር ህጉ ላይ በተመለከቱት ድንጋጌዎች መካከል የሚታይ ቅራኔ (apparent contradiction) የላለ በመሆኑ የይርጋ ጊዜ አቆጣጠርን አስመልክቶ በንግድ ህጉ ላይ የተመለከተዉን ብቻ በመቀበል አንድ ሰዉ ለፍርድ ቤት ክስ ማቅረብ የሚችለዉ በመብቱ መስራት ከሚችልበት ጊዜ ጀምሮ መሆኑን ከአጠቃላይ የይርጋ መሰረታዊ ዓላማ ጋር በማገናዘብ በፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 1846 ላይ የተመለከተዉን ድንጋጌ ወደ ጎን በመተዉ ከዉሳኔ ላይ መድረስ ትክክለኛ የህግ አተረጓጎም ዘይቤ አይደለም። በዚህ ችልት እምነት በዚህ ጉዲይ ላይ ተመራጭ የሚሆነዉ የአተረጓጓም ዘይቤ በንግድ ህጉ ላይ የተመለከተዉን የሁለት ዓመት የይርጋ ጊዜ በመዉሰድ፣ የይርጋዉ ጊዜ መቆጠር የሚጀምርበትን ጊዜ አስመልክቶ ግን የያዝነዉን ጉዲይ መሰረታዊ ባህርይ ግምት ዉስጥ በማስገባት በፍትሐብሕር ህጉ ላይ የተመለከተዉን ድንጋጌ ተፈፃሚ በማድረግ ሁለቱ የህግ ክፍልች ተደጋጋፉ ሆነዉ ተፈፃሚ እንዱሆኑ በማድረግ የይርጋን መሰረታዊ ዓላማ ሉያሳካ የሚችል ዘዳን መከተል ነዉ።
በዚህም መሰረት፣ በንግድ ህጉ አንቀጽ 674/1/ ላይ የተመለከተዉ የይርጋ ጊዜ ለተያዘዉ ጉዲይ ተፈፃሚነት ያለዉ ቢሆንም ጉዲዩ የሦስተኛ ወገን ኢንሹራንስ ዉል ያለዉን ልዩ ባህርይ ግምት ዉስጥ ባስገባ መልኩ ከሳሹ በመብቱ መስራት የቻለበት ቀን የይርጋዉ መቁጠሪያ መነሻ ቀን እንደሚሆን በግልጽ አላመለከተም። ይህ የህጉ ክፍተት በመሆኑም በፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 1676(1) ላይ በተመለከተዉ ድንጋጌ መሰረት የይርጋ ጊዜ መቆጠር የሚችለዉ ከሳሹ በመብቱ መስራት ከጀመረበት ቀን ጀምሮ ነዉ በሚል በህጉ አንቀጽ 1846 ላይ የተመለከተዉ ድንጋጌ ተፈፃሚ ማድረጉ ተገቢ ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም ጉዲት ለደረሰበት ሦስተኛ ወገን የሚገባዉን ክፍያ ከፈጸመ በኋላ መድን ሰጭዉ በመድን ገቢዉ ላይ የሚያቀርበዉ የካሳ ይተካልኝ ክስ ሲሆን፣ በንግድ ህጉ ላይ የተመለከተዉ የሁለት ዓመት የይርጋ ጊዜዉ መቆጠር የሚጀምረዉ ጉዲቱ ከደረሰበት ቀን ጀምሮ ሳይሆን መድን ሰጪዉ በአደጋዉ ምክንያት በሦስተኛ ወገን ላይ ለደረሰዉ ጉዲት ካሳ ከከፈለበት ቀን ጀምሮ ላሆን ይገባል።
ከዚህ አንፃር ወደ ተያዘዉ ጉዲይ ስንመለስ፣ ከፍ ሲል እንደተመለከተዉ ለጉዲቱ መንስኤ የሆነዉ አደጋ የደረሰዉ በ17/05/2007 ዓ.ም ቢሆንም፣ አመልካች ክፍያዉን ለሦስተኛ ወገን የፈጸመዉ ሐምል 12 ቀን 2008 ዓ.ም ሆኖ ክሱ የቀረበዉ ሰኔ 22 ቀን 2009 ዓ.ም መሆኑ ተረጋግጧል። ይህም አመልካች ክሱን ያቀረበዉ ለሦስተኛ ወገን ካሳ ከፍል የሁለት ዓመት ጊዜ ከማለቁ በፉት በመሆኑ ክሱ በሁለት ዓመት ይርጋ የሚታገድ አይደለም። ስለሆነም የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተጠሪን መቃወሚያ በመቀበል ለተያዘዉ ጉዲይ አግባብነት የላለዉን አደጋዉ የደረሰበትን ቀን ለይርጋ አቆጣጠር መነሻ በማድረግ የአመልካች ክስ የማቅረብ መብት በይርጋ ታግዶል በማለት መዝገቡን መዝጋቱና ጉዲዩን በይግባኝ ያየዉ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ይህን ስህተቱን ሳያርም ማለፈ ሉታረም የሚገባዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ። በመሆኑም ተከታዩን ዉሳኔ ሰጥተናል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 19/11/2010 ዓ/ም የሰጠዉ ብይን የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 27/06/2011ዓ/ም የሰጠዉ ዉሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተዘግቶ የነበረዉን መዝገብ በማንቀሳቀስ ፍሬ ነገሩን በተመለከተ ግራ ቀኙን አከራክሮና እንደአስፈጊነቱ ማስረጃ ሰምቶና መርምሮ ተገቢዉን ዉሳኔ እንዱሰጥ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 341/1/ መሰረት ጉዲዩ ተመልሶለታል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
No topics extracted.