ተገድድ የመያዝ ህጋዊነትን የማረጋገጥ ጉዲይ አስመልክቶ የዲኝነት ስልጣኑ ተለይቶ ለፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያልተሰጠ በመሆኑ የሚቀርብ አቤቱታን ተቀብል የማየት የመጀመሪያ ደረጃ የዲኝነት ስልጣን ያለው የፍደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ስለመሆኑ የፋዳራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀፅ 5(1(ኘ)) እና 11(1)፣ (3)
No summary available.
ሐምል 28/2014 ዓ.ም ዳኞች፡ እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሳዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡- የአዱስ አበባ ፖሉስ ኮሚሽን ተጠሪዎች፡-
በሶስቱም መዝገቦች ላይ የቀረበው ጉዲይ ተገድድ የመያዝ ህጋዊነትን ለማረጋገጥ የቀረበ አቤቱታን የሚመለከት ነው። ጉዲዩ ለዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ላቀርብ የቻለውም የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተገድድ የመያዝ ህጋዊነትን ለማረጋገጥ የሚቀርብን አቤቱታ ተቀብል የማየት የሥረ ነገር ሥልጣን ያለው መሆኑን መርምሮ ለመወሰን ነው።
ክርክሩ የተጀመረው የአሁን ተጠሪዎች በተናጠል ለፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ባቀረቡት አካልን ነፃ ማውጣት አቤቱታ ነው። የአቤቱታቸው ፍሬ ቃልም በአሁን አመልካች አቤቱታ አቅራቢነት ለወንጀል ምርመራ በሚል የጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቶባቸው የተጠረጠሩበት ወንጀል ሲጣራ ከቆየ በኋላ አመልካች በድጋሚ ያቀረበው የተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ይሰጠኝ አቤቱታ ውድቅ የተደረገ ቢሆንም አመልካች ከህግ አግባብ ውጭ አስሮ ያቆያቸው መሆኑን በመግለፅ ድርጊቱ ህገ ወጥ ነው ተብል ከእስር እንዱለቀቁ የሚጠይቅ ነው።
አመልካች በበኩለ ፍርድ ቤቱ የቀረበውን አቤቱታ ተቀብል ለማየት የዲኝነት የሥረ ነገር ስልጣን የለውም የሚል መቃወሚያ እና ተጠሪዎች በእስር የቆዩት በህግ አግባብ ነው የሚልባቸውን ምክንያቶች ጠቅሶ አቤቱታው ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክሯል።
ጉዲዩ የቀረበለት ፍርድ ቤትም በፋዳራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 መሰረት ተገድድ የመያዝን ህጋዊነት ማጣራት የፋዳራል ፍርድ ቤቶች የዲኝነት ስልጣን ሲሆን ስልጣኑም ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአዋጁ አንቀፅ 11 ስር በዝርዝር በተሰጠ የፍትሓ ብሕር ስልጣን ውስጥ አልተጠቀሰም፤ ለፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባልተሰጠ የፋዳራል ጉዲይ ላይ የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የመጀመሪያ የዲኝነት ስልጣን ያለው ስለመሆኑ በአዋጁ አንቀፅ 14 ስር ተመልክቷል የሚል እና ላልች ምክንያቶችን ጠቅሶ ጉዲዩን የማየት ስልጣን አለኝ በሚል መቃወሚያውን በብይን ውድቅ አድርጓል። የተጠሪዎችን በእስር የመቆየት ህጋዊነትንም አስመልክቶ የግራ ቀኙን ክርክር ከመረመረ በኋላ እስሩ ህገ ወጥ ነው በሚል ተጠሪዎች በዋስትና ከእስር እንዱለቀቁ ወስኗል። አመልካች ይህንኑ በመቃወም ለፋዳራል ክፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረበው የይግባኝ አቤቱታ ተቀባይነት አላገኘም።
የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በዚሁ ጉዲይ ላይ ነው። አመልካች በሶስቱም መዝገቦች ላይ በተለያየ ቀን በፃፊቸው የሰበር አቤቱታዎች በስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ ተፈፅሟል ያላቸውን መሰረታዊ የህግ ስህተት ጠቅሶ በዚህ ችልት እንዱታረምለት ጠይቋል። በሶስቱም መዝገቦች ላይ አመልካች ያቀረባቸው የሰበር አቤቱታዎች ተመርምረው ከላይ በዚህ ፍርድ መግቢያ ላይ የተመለከተውን ነጥብ ለማጣራት ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ክርክር ያስቀርባል በመባለ ግራ ቀኙ በፅሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና መሰረታዊ የክርክሩ ይዘት ጠቅለል ባለ መልኩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ችልቱም በሰበር አጣሪው ችልት ሉጣራ ይገባዋል ተብል የተያዘውን ነጥብ ከግራ ቀኙ ክርክር፤ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ መርምሯል።
ከክርክሩ አመጣጥ መገንዘብ እንደሚቻለው የግራ ቀኙ ክርክር ከፍርድ ቤት የሥረ ነገር የዲኝነት ስልጣንን ጋር የተያያዘ ነው። የዲኝነት የሥረ ነገር ስልጣን አንድን በፍርድ ቤት የቀረበ ክርክርን አይቶ የመወሰን የዲኝነት ችልታን የሚመለከት ነው። የዲኝነት የሥረ ነገር ስልጣን የሚመነጨው በዋናነት ከጉዲዩ ዓይነት እና ለክርክር ምክንያት ከሆነው የገንዘብ መጠን ነው። ከጉዲዩ ዓይነት የሚመነጭ የዲኝነት ሥረ ነገር ስልጣን ማለት ተለይተው የታወቁ ጉዲዮችን አስመልክቶ የሚነሱ ክርክሮችን የመዲኘት ስልጣን በህግ ተለይቶ ለአንድ ፍርድ ቤት ሲሰጥ ማለት ነው። ለክርክር ምክንያት ከሆነው የገንዘብ መጠን የሚመነጨው የዲኝነት ስልጣን ደግሞ በገንዘብ ሉተመን የሚችልን ጉዲይ መሰረት አድርጎ የሚኖር ስልጣን ማለት ነው።
በዚሁ አግባብ የፋዳራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 የፋዳራል መንግስቱን ፍርድ ቤቶች በሶስት ደረጃ ካዋቀረ በኋላ ፍርድ ቤቶቹ በወንጀልም ሆነ በፍትሐ ብሕር በወል እና በተናጠል ስለሚኖራቸው የዲኝነት የሥረ ነገር ሥልጣን በዝርዝር አስቀምጧል። የፋዳራል ፍርድ ቤቶች የፍትሓ ብሕር የዲኝነት ስልጣን በአዋጁ አንቀፅ 5 ስር ዘርዝሯል። በእነዚህ በፋዳራል መንግስቱ ፍርድ ቤቶች የዲኝነት ሥልጣን ስር ከሚሸፈኑ የፍትሓ ብሕር ጉዲዮች ውስጥ በሶስቱም ደረጃ ያለት ፍርድ ቤቶች የሚኖራቸው የመጀመሪያ ደረጃ እና የይግባኝ ስልጣን በአንቀፅ 10፣ 11 እና 14 ስር በተናጠል ተመልክተዋል።
በአዋጁ መሰረት የፍትሓ ብሕር ጉዲይን አስመልክቶ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተሰጠውን የመጀመሪያ ደረጃ የዲኝነት ስልጣን በሁለት ከፍል ማየት ይቻላል። የመጀመሪያ በክርክሩ የገንዘብ መጠን ተለይቶ የተሰጠ ሲሆን ላላኛው ደግሞ በጉዲይ ዓይነት ተለይቶ የተሰጠ የዲኝነት ስልጣን ነው። ከክርክሩ የገንዘብ መጠን አንፃር የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፋዳራል ፍርድ ቤቶች የዲኝነት ሥረ ነገር ሥልጣን ሥር በሚሸፈኑ እና ግምታቸው ከብር 10,000,000(አስር ሚሉዮን ብር) በላይ በሆኑ ማናቸውም የፍትሓ ብሕር ጉዲይ ላይ የመጀመሪያ ደረጃ የዲኝነት ስልጣን ያለው ስለመሆኑ በአዋጁ አንቀፅ 11(1) ስር ተመልክቷል። ከጉዲዩ ዓይነት አኳያ ደግሞ ለፍርድ ቤቱ የተሰጠው የዲኝነት ስልጣን በአዋጁ አንቀፅ 11(2) እና (3) ስር ተመልክቷል። በጉዲይ ዓይነት ለፍርድ ቤቱ ተለይተው የተሰጡት የዲኝነት ስልጣናት በአዋጁ አንቀፅ 5(1(ሀ) እስከ (ሰ)) ስር የተመለከቱት ጉዲዮች፣ በህግ በሚወሰን መሰረት የሚቀርብ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመታየት ላይ ያለን የክስ ይዛወርልኝ ጉዲይ፤ እንዱሁም በፍርድ ታይተው ሉወሰኑ በሚችለ በህገ መንግስቱ ምዕራፍ ሶስት ስር የተመለከቱት መሰረታዊ መብቶች እና ነፃነቶች ለማስከበር የሚቀርብን አቤቱታ ነው። በዚህ መልኩ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በግልፅ ያልተሰጠ የዲኝነት ስልጣን የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ስልጣን ስለመሆኑ ከአዋጁ አንቀፅ 11፣ እና 14 ድንጋጌዎች አቀራረፅ እና የቃላት አጠቃቀም መገንዘብ ይቻላል።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስ የቀረበው ክርክር ተገድድ የመያዝን ህጋዊነት ለማረጋጥ የሚቀርብን አቤቱታ የሚመለከት ነው። በዚህ መልኩ የሚቀርብ አቤቱታ በፋዳራል ፍርድ ቤቶች የዲኝነት የሥረ ነገር ሥልጣን ስር የሚሸፈን ሰለመሆኑ በአዋጁ አንቀፅ 5(1(ኘ)) ደንግጓል። ይህ ዓይነት ጉዲይ ለፋዳራል ክፍተኛ ፍርድ ቤት በጉዲይ ዓይነት ተለይተው በተሰጡት የመጀመሪያ ደረጃ የዲኝነት የሥረ ነገር ሥልጣን ስር በግልፅ አልተመለከተም። በእርግጥ ከህግ አግባብ ውጭ ያለመታሰር መብት በህገ መንግስቱ ምዕራፍ ሶስት ውስጥ ህገ መንግስታዊ ጥበቃ ከተደረገላቸው መሰረታዊ መብቶች ውስጥ አንደ ስለመሆኑ የህገ መንግሰቱ አንቀፅ 17 ድንጋጌ ያስገነዝባል።
በአዋጁ አንቀፅ 11(3) መሰረት በህገ መንግስቱ ምዕራፍ ሶስት ስር የተመለከቱትን መሰረታዊ መብቶች እና ነፃነቶችን አስመልክቶ የሚቀርቡ ጉዲዮችን የማየት የዲኝነት ስልጣን የተሰጠው ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመሆኑ ተገድድ የመያዝ ህጋዊነትን ለማረጋገጥ የሚቀርብ አቤቱታ መቅረብ ያለበት ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው ልባል ይችል ይሆናል። ሆኖም ህግ አውጪ አካልን ነፃ የማውጣት ጉዲይ በአዋጁ አንቀፅ 11(3) ማዕቀፍ ውስጥ እንዱታይ ሀሳብ ቢኖረው ኖሮ በህገ መንግስቱ ምዕራፍ ሶስት ስር ጥበቃ ከተደረገላቸው በርካታ መሰረታዊ መብቶች እና ነፃነቶች ውስጥ ነጥል እራሱን በቻለ አንቀፅ መደንገግ አያስፈልገውም ነበር።
በአዋጁ አንቀፅ 11(3) ስር የተመለከለተው ሀሳብ ቀደሞ በነበሩት ህጎች ውስጥ ያልነበረ እና አዋጁ ካስተዋወቃቸው አዲዱስ ሀሳቦች ውስጥ አንደ ነው። ሀሳቡ አዱስ እንደመሆኑ መጠን በአተገባበር ረገድ በርካታ ውስብስብ እና እንግዲ የሆኑ ነገሮች ሉፈጠሩ እንደሚችል ይጠበቃል። እንዱህ ዓይነት ጉዲይ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንዱታይ የተፈለገበት አንደ ምክንያትም ይኸው ላሆን እንደሚችል ይታመናል። በአንፃሩ ተገድድ የመያዝ ህጋዊነትን ለማረጋገጥ የሚቀርብ አቤቱታ በህገ መንግስቱ ጥበቃ ከተደረገላቸው መሰራዊ መብቶች እና ነፃነቶች ውስጥ አንደ ቢሆንም አዋጅ ቁጥር 1234/2013 ከመውጣቱ በፉትም ቢሆንም በፍርድ ቤት በዲኝነት ሲታይ የነበረ እና የተለመደ ጉዲይ በመሆኑ ያን ያክል ውስብስብነት ያለው አይደለም። ከዚህ አንፃር በአዋጁ አንቀፅ 11(3) ስር የተመለከተው አዱስ ሀሳብ በአዋጁ አንቀፅ 5(1(ኘ)) ውጭ ያለትን በህገ መንግስቱ ምዕራፍ ሶስት ስር የተመለከቱትን እና በፍርድ ሉያልቁ የሚችለ መሰረታዊ መብቶች እና ነፃነቶችን ለማመልከት እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል። ተገድድ የመያዝ ህጋዊነትን የማረጋገጥ ጉዲይ አስመልክቶ የዲኝነት ስልጣኑ ተለይቶ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያልተሰጠ በመሆኑ በአዋጁ አንቀፅ 11(1) እና 14 መሰረት የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ስልጣን ነው።
በመሆኑም የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተገድድ የመያዝ ህጋዊነትን ለማረጋገጥ የሚቀርብ አቤቱታን የማየት የዲኝነት ስልጣኑ የእኔ ነው ማለቱ በህጉ አግባብ በመሆኑ የሚነቀፍበት መሰረታዊ የህግ ስህተት የለውም። የአቤቱታውን ጭብጥ አስመልክቶም የተጠሪዎች እስር ህገ ወጥ ስለመሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ አረጋግጦ የወሰነ በመሆኑ በውሳኔው ላይ የተፈፀመ መሰረታዊ የህግ ስህተት አልተገኘም። ስለሆነም ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
ይህንኑ በማፅናት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፍ/መ/ቁ/293599 ላይ ሰኔ 28/2014 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል።
የዚህ ፍርድ ግልባጭ ከሰ/መ/ቁ/230168 ጋር ይያያዝ።
በሶስቱም መዝገቦች ላይ ተሰጥቶ የነበረው የእግድ ትዕዛዝ ተነስቷል። ይፃፍ።
መዝገቡ ተዘግቷል። ይመለስ።
No topics extracted.