የኑዛዜ ወራሽነት የምስክር ወረቀት ይሰረዝልን ጥያቄ ሰፉና ዉስብስብ ክርክሮች ተደርጎ፣ በሕጉ አግባብ ተገቢ ማጣራትና ምርመራ ተደርጎበት ዉሳኔ የሚሰጥበት እንጂ የምስክር ወረቀቱን ለማግኘት ከሚቀርብ አቤቱታ ጋር ተመሳሳይነት ያለዉ ባለመሆኑ የኑዛዜ ወራሽነት የምስክር ወረቀት እንዱሰረዝልኝ በማለት የሚቀርብ አቤቱታን መርምሮ ዉሳኔ ለመስጠት የሥረ-ነገር ስልጣን የፍደራል ፍ/ቤቶች እንጂ የአዱስ አበባ ከተማ ፍ/ቤቶች አቶ ጌታቸዉ ሙለጌታ እና እነ አቶ መላኩ ሙለጌታ (3 ሰዎች)
No summary available.
መጋቢት 21 ቀን 2012 ዓ.ም ዳኞች፡ ….1.ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) 2. ቀነዓ ቂጣታ 3. ደጀኔ አያንሳ 4. ኑረዱን ከድር 5. ብርቅነሽ እሱባለዉ አመልካች፡ ………….አቶ ጌታቸዉ ሙለጌታ ተጠሪዎች፡ ………. ..1. አቶ መላኩ ሙለጌታ 2. አቶ ምንተስኖት ሙለጌታ 3. ወ/ሮ ልኬለሽ ወልዳ የሟች አቶ ፊሲል ሙለጌታ ተተኪ ወራሽ ይህ መዝገብ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የዉርስ ሀብት ክርክር የተጀመረዉ በአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን፣የአሁን አመልካች የሥር የመቃወም ተጠሪ፣ የአሁን ተጠሪዎች የሥር የመቃወም አመልካቾች ሆነው ሲከራከሩ ነበር።ጉዲዩ ለዚህ ችልት ላቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ.ቁ.28837 ጥር 21 ቀን 2011 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱታረምልኝ በማለት በማመልከታቸዉ ነዉ።
የጉዲዩ አመጣጥ ሲታይ የአሁን አመልካች በአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረበዉ አቤቱታ ሟች አቶ ሙለጌታ ጉዱሳ በሕይወት እያለ ጥቅምት 11 ቀን 1977 ዓ.ም የተጻፈ ኑዛዜ ስላተረፈልኝ የዉርስ ሀብቱ እንዱጣራልኝ በማለት ያቀረበዉን ተከትል፣ ፍ/ቤቱ የዉርስ አጣሪ ያቀረበዉን ሪፖርት መሰረት በማድረግ የአሁን አመልካች የሟች አቶ ሙለጌታ ጉዱሳ የኑዛዜ ወራሽ ነዉ በማለት የኑዛዜ ወራሽነት የምስክር ወረቀት እንዱሰጠዉ ወስኗል።
ይህን ዉሳኔ ተከትል የአሁን ተጠሪዎች የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.358 መሰረት በማድረግ ባቀረቡት የመቃወም አቤቱታ ሟች አቶ ሙለጌታ ጉዱሳ ጥቅምት 11 ቀን 1977 ዓ.ም አድርገዋል በተባለዉ ኑዛዜ እኛ ወደ ታች የሚቆጠሩ ተወላጆች እና የመጀመሪያ ደረጃ ወራሾች ሆነን እያለ ከዉርስ የነቀለን ስለሆነ እኛ ባልተከራከርንበት ኑዛዜዉን መሰረት አድርጎ የተሰጠዉ ዉሳኔ መብታችን የሚጎዲ ስለሆነ ለአሁን አመልካች የተሰጠዉ የኑዛዜ ወራሽነት የምስክር ወረቀት እንዱሰረዝልኝ እና ዉሳኔዉ እንዱሻርልኝ በማለት አመልክቷል። የአሁን አመልካች በዚህ አቤቱታ ላይ ባቀረበዉ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ፍ/ቤቱ ይህን አቤቱታ ለማየት የዲኝነት ስልጣን የለዉም፤ የቀረበዉ አቤቱታ በይርጋ የሚታገድ ነዉ፤ የአሁን ተጠሪዎች በኑዛዜዉ ከዉርስ አልተነቀለም፣ የተሰጠኝ የወራሽነት ማስረጃ በአግባቡ ስለሆነ አቤቱታዉ ዉድቅ ነዉ በማለት ተከራክሯል።
ከዚህ በኋላ የሥር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የግራ ቀኛቸዉን ክርክር በመመርመር በሰጠዉ ዉሳኔ ሟች አቶ ሙለጌታ ጉዱሳ ጥቅምት 11 ቀን 1977 ዓ.ም አድርገዋል የተባለዉ ኑዛዜ ሲታይ የአሁን ተጠሪዎች ከዉርስ ስላልተነቀለ ለአሁን አመልካች የተሰጠዉ የኑዛዜ ወራሽነት ማስረጃ ሉሰረዝ አይገባም በማለት ወስኗል።
የአሁን ተጠሪዎች በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ያቀረቡ ሲሆን ፍ/ቤቱ ግራ ቀኛቸዉን በማከራከር በሰጠዉ ዉሳኔ ሟች አቶ ሙለጌታ ጉዱሳ ጥቅምት 11 ቀን 1977 ዓ.ም ያደረጉት ኑዛዜ ልጆቻቸዉ የሆኑትን የአሁን ተጠሪዎች ከዉርስ የነቀላቸዉ ስለሆነ የአሁን ተጠሪዎች የኑዛዜዉ ተጠቃሚ ከሆነዉ ከአሁን አመልካች ጋር የዉርስ ሀብቱን እኩል እንዱካፈለ በማለት የሥር ዉሳኔ በመሻር ወስኗል። ይህ ጉዲይ የቀረበለት የአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ግራ ቀኛቸዉን በማከራከር የሥር የይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል። የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ለማስለወጥ ነዉ።
የአሁን አመልካች የካቲት 11 ቀን 2011 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ፡ በዚህ ጉዲይ የከተማዉ ሰበር ሰሚ ችልት ከዚህ ቀደም በሰጠዉ ዉሳኔ ጭብጥ በመያዝ ወደ ሥር ፍ/ቤት ሲመለስ ጥቅምት 11 ቀን 1977 ዓ.ም የተሰጠዉ የኑዛዜ ወራሽነት ማስረጃ ሉሰረዝ ይገባል በማለት የአሁን ተጠሪዎች ያቀረቡት አቤቱታ ላይ አከራክሮ ዉሳኔ እንዱሰጥ የሚል ሆኖ የሥር የይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ከዚህ ዉጭ በመዉጣት ተጠሪዎች ከኑዛዜ ተጠቃሚዎች ጋር እኩል እንዱካፈለ በማለት የሰጠዉ ወሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ስለሆነ ዉድቅ እንዱደረግልን በማለት አመልክቷል።
የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩን በማየት፣በዚህ ጉዲይ የአዱስ አበባ ከተማ ፍ/ቤቶች ኑዛዜዉ ተጠሪዎችን ከዉርስ ነቅሎል እና ንብረቱን እኩል እንዱካፈለ በማለት የመወሰን ስልጣን ያለዉ መሆን አለመሆኑን፣ ለመመርመር ሲባል የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል በማለት ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡ ባዘዘዉ መሰረት በ22/9/2011 ዓ.ም በተጻፈ መልስ፡ በዚህ ጉዲይ የአዱስ አበባ ከተማ ፍ/ቤቶች ሟች ያደረጉት ኑዛዜ የመጀመሪያ ደረጃ ወራሾች የሆኑትን ተጠሪዎች ከዉርስ የነቀለ መሆኑን በማየት ከኑዛዜ ተጠቃሚ ጋር እኩል እንዱካፈለ በማለት ለመወሰን ስልጣን ያላቸዉ ስለሆነ ዉሳኔዉ እንዱጸናልን አቤቱታዉ ዉድቅ እንዱደረግልን በማለት በዝርዝር ተከራክሯል።
የአሁን አመልካች የመልስ መልስ አቅርቧል።
እንደሚታወቀዉ የኢ.ፋ.ዳ.ሪ. ሕገ መንግስት የፋዳራል ጉዲዮች፣ ለላላ በሕግ የዲኝነት ስልጣን ለተሰጠዉ አካል እስካልተሰጠ ድረስ፣ በዲኝነት የማየት ስልጣን የፋዳራል ፍ/ቤቶች መሆኑን ይደነግጋል። ይህን የሕገ መንግስቱን ድንጋጌ ተከትል ደግሞ የፋዳራል ፍ/ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/1988 መሰረት የፋዳራል ፍ/ቤቶች የፍትሐ ብሕርም ሆነ የወንጀል ጉዲዮችን የዲኝነት ስልጣን በዝርዝር ተመልክቶ እናገኛለን።
በልላ በኩል በኢ.ፋ.ዳ.ሪ. ሕገ መንግስት የአዱስ አበባ ከተማ በተመለከተ የተደነገገዉን ተከትል የአዱስ አበባ ከተማ ፍ/ቤቶች የፍትሐብሕርም ሆነ የወንጀል/የደንብ መተላለፍ ዲኝነት ስልጣን በተሻሻለዉ የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ቻርተር ላይ ተመልክቶ አናገኛለን።የተሻሻለዉ የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/1995 በአንቀጽ 10 [1፣ መ] መሰረት ካደራጃቸዉ አካላት መካከል የከተማዉ የዲኝነት አካላት እንደሆነ ያመለክታል። በዚህ አዋጅ አንቀጽ 41 መሰረት ደግሞ የአዱስ አበባ ከተማ ፍ/ቤቶች የዲኝነት ስልጣን ተደንግጓል። እንዱሁም የተሻሻለዉ የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ቻርተር አዋጅ ለማሻሻል የወጣ አዋጅ ቁ.408/1996 አንቀጽ 2 [1] መሰረት የአዱስ አበባ ከተማ ፍ/ቤቶች የወራሽነት፣ የባልና ሚስትነት፣ የሞግዚትነት እና የምስክር ወረቀት ለማግኘት የሚቀርብ አቤቱታ ለማየት ስልጣን እንዲላቸዉ ይደነግጋገል።
የዚህ ድንጋጌ እንግሉዚኛ ቅጂ ደግሞ “The Addis Ababa City Courts shall have jurisdiction over application for certificates of succession, marriage and guardianship” በማለት ይደነግጋል። ይህ ማለት የአዱስ አበባ ከተማ ፍ/ቤቶች የወራሽነት የምስክር ወረቀት፣ የባልና ሚስትነት የምስክር ወረቀት፣ የሞግዚትነት የምስክር ወረቀት ለማግኘት የሚቀርብ አቤቱታ ለማየት የሥረ-ነገር ስልጣን እንዲላቸዉ ያስገነዝባል። የወራሽነት የምስክር ወረቀት ደግሞ በሕግ ወራሽ የሆነዉን እና የኑዛዜ ወራሽ የሚያካትት መሆኑ ግልጽ ነዉ። ከዚህ ጋር ተያይዞ መታየት ያለበት ጉዲይ የአዱስ አበባ ከተማ ፍ/ቤቶች በአዋጁ አንቀጽ 2 [1] ሥር የተመለከተዉን የምስክር ወረቀት ለመስጠት ስልጣን ያላቸዉ ከሆነ፣ እነዚህ የምስክር ወረቀቶች እንዱሰረዝ የሚቀርበዉን አቤቱታ ተቀብል ተከራካሪ ወገኖችን አከራከሮ ሰምቶ ዉሳኔ ለመስጠት የስረ-ነገር ስልጣን አለዉ ወይስ የለዉም? የሚለዉ ነጥብ ነዉ።
በዚህ ረገድ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በ
ጥቅምት 1 ቀን 2008 ዓ.ም በሰጠዉ ዉሳኔ የአዱስ አበባ ከተማ ፍ/ቤት የሰጠዉን የወራሽነት የምስክር ወረቀት በመቃወም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.358 መሰረት የሚቀርበዉን የመቃወሚያ አቤቱታ በማየት የማስረጃዉን ትክክለኛ እና ህጋዊነት በማረጋገጥ ዉሳኔ ለመስጠት ስልጣን ያላቸዉ አዱስ አበባ ከተማ ፍ/ቤቶች መሆናቸዉን አስገዲጅ የህግ ትርጉም ሰጥቶበታል። በልላ በኩል የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በ
ሐምል 26 ቀን 2004 ዓ.ም በሰጠዉ ዉሳኔ የአዱስ አበባ ከተማ ፍ/ቤቶች የባልነት ወይም የሚስትነት ማስረጃ በተመለከተ የቀረበዉን ጥያቄ ትክክለኛነቱን እና ሕጋዊነቱን በማረጋገጥ በማስረጃነቱ ዉሳኔ [Declaratory Judgment] ከመስጠት ዉጪ ማስረጃዉ የተሰጠበትን ዉሳኔ መሰረት በማድረግ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.358 መሰረት የተቃዉሞ አቤቱታ በመቀበልና የጋብቻ መኖር አለመኖርንና ላልች ተያያዥነት ያላቸዉን ክርክሮችን ለማስተናገድ የሥረ-ነገር ስልጣን የላቸዉም፤ የጋብቻ መኖር ያለመኖር ዉስብስብ ያልሆነ ክርክር የሚቀርብበት ሳይሆን ክርክር ተደርጎበት ዉስብስብ የህግ ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥበት በመሆኑ የአዱስ አበባ ከተማ ፍ/ቤቶች ጉዲዩን ለማየት ስልጣን የላቸዉም በማለት አስገዲጅ የህግ ትርጉም ሰጥቷል።
እንዱሁም ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በ
የካቲት 27 ቀን 2012 ዓ.ም በሰጠዉ አስገዲጅ የህግ ትርጉም የሞግዚትነት የምስክር ወረቀት መሰጡቱን በመቃወም፣ ማስረጃዉ እንዱሰረዝ የሚቀርብ አቤቱታ ሲታይ አስቀድሞ ማስረጃዉን የወሰደዉ እና ማስረጃዉ እንዱሰረዝልኝ በማለት አቤቱታ ባቀረበዉ ሰዉ መካከል ከልጆች አስተዲደግ ጋር በተያያዘ የፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ እና አግባብነት ካላቸዉ ከአለም አቀፍ ሰነድችና ኢትዮጵያ ተቀብላ ካጸደቀቻቸዉ እነዚህ የቃልኪዲን ሰነድች እና የሀገራችን ሕጎች መሰረት ሙለ ክርክርን ማድረግንና አግባብነት ባለዉ ማስረጃ ጉዲዩን አጣርቶ መወሰንን የሚጠይቅ ጉዲይ ነዉ። የሞግዚትነት የምስክር ወረቀት ይሻርልኝን ጥያቄ በዚህ አግባብ ክርክሩን በመምራትና አግባብነት ካላቸዉ ሕጎች አንጻር ሰፉና ዉስብስብ ክርክር ተደርጎ እና ተገቢ የሆነ የማጣራት ሂደት ተካሂድ መወሰንን የሚጠይቅ መሆኑን የሚያስገነዝብ ነዉ። በመሆኑም የሞግዚትነት የምስክር ወረቀት እንዱሻርልኝ በማለት የሚቀርብ አቤቱታን ተቀብል ተከራካሪ ወገኖችን ሰምቶ አከራከሮ አግባብነት ካላቸዉ የህግ ድንጋጌዎች አንጻር አጣርቶ መርምሮ ዉሳኔ ለመስጠት የሥረ-ነገር ስልጣን ያላቸዉ የፋዳራል ፍ/ቤቶች እንጂ የአዱስ አበባ ከተማ ፍ/ቤቶች አይደለም በማለት መወሰኑን መገንዘብ ተችሎል።
በዚህ መሰረት አሁን ወደ ተያዘዉ ጉዲይ ስንመለስ የአሁን ተጠሪዎች የአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሟች አቶ ሙለጌታ ጉዱሳ ጥቅምት 11 ቀን 1977 ዓ.ም አድርገዋል የተባለዉ ኑዛዜ መሰረት በማድረግ የአሁን አመልካች የሟች የኑዛዜ ወራሽነት በማረጋገጥ የኑዛዜ ወራሽነት የምስክር ወረቀት መስጠቱን በመቃወም የምስክር ወረቀቱ እና ዉሳኔዉ እንዱሰረዝላቸዉ ማመልከታቸዉን ከግራ ቀኛቸዉ ክርክር መረዲት ተችሎል። ይህ ጥያቄ ደግሞ ለክርክር መነሻ የሆነዉ ኑዛዜ የህጉን ፍርማሉቲዎችን አሟልቶ የተደረገ ነዉ ወይስ አይደለም? ኑዛዜዉ በሕጉ የተመለከተዉን መስፈርቶችን አሟልቶ የተደረገ እንደሆነ የሟች ወደ ታች የሚቆጠሩ ተወላጆችን ከዉርስ ነቅሎል ወይስ አልነቀለም? ዉጤቱስ ምን ይሆናል? የሚለትን የክርክር ጭብጦችን የሚያስነሳ መሆኑን ማየት ይቻላል። ይህ ከሆነ ደግሞ ከግራ ቀኛቸዉ የሚቀርበዉን ሰፉና ዉስብስብ ክርክሮችን መሰረት በማድረግ፣ የፍትሐብሕር ሕጉን ኑዛዜን የሚመለከቱትን ድንጋጌዎች መሰረት በማድረግ የሚቀርበዉን ክርክር ሰምቶ አጣርቶ መርምሮ ዉሳኔ መስጠትን የሚመለከት ጉዲይ ነዉ። በመሆኑም የኑዛዜ ወራሽነት የምስክር ወረቀት ይሰረዝልን ጥያቄ ሰፉና ዉስብስብ ክርክሮች ተደርጎ፣ በሕጉ አግባብ ተገቢ ማጣራትና ምርመራ ተደርጎበት ዉሳኔ የሚሰጥበት ነዉ እንጂ የምስክር ወረቀቱን ለማግኘት ከሚቀርብ አቤቱታ ጋር ተመሳሳይነት ያለዉ ሆኖ አይገኝም። በመሆኑም የኑዛዜ ወራሽነት የምስክር ወረቀት እንዱሰረዝልኝ በማለት የሚቀርበዉን አቤቱታ መርምሮ ዉሳኔ ለመስጠት የሥረ-ነገር ስልጣን ያላቸዉ የፋዳራል ፍ/ቤቶች ናቸዉ እንጂ የአዱስ አበባ ከተማ ፍ/ቤቶች አይደለም ብለናል።
ሲጠቃለል የአዱስ አበባ ከተማ ፍ/ቤቶች በሰጡት ዉሳኔ የኑዛዜ ወራሽነት የምስክር ወረቀት እንዱሰረዝልን በማለት የሚቀርበዉን አቤቱታ ተቀብል የግራ ቀኛቸዉን ሙለ ክርክር ሰምቶ አግባብነት ካላቸዉ የሕግ ድንጋጌዎች አንጻር አጣርቶ መርምሮ ዉሳኔ ለመስጠት የሥረ-ነገር ስልጣን ያላቸዉ የፋዳራል ፍ/ቤቶች እንጂ የአዱስ አበባ ከተማ ፍ/ቤቶች አይደለም በማለት የአሁን ተጠሪዎች ያቀረቡትን አቤቱታ ዉድቅ በማድረግ መወሰን ሲገባቸዉ የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ የሚከተለዉ ተወስኗል።
የአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ.2586/01 በ26/8/2010 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና የአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት በመ.ቁ.28443 በ20/11/2010 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና የአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ.ቁ.28837 ጥር 21 ቀን 2011 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመባቸዉ ስለሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 [1] መሰረት ተሽሯል።
የኑዛዜ ወራሽነት የምስክር ወረቀት እንዱሰረዝልኝ በማለት የሚቀርበዉን አቤቱታ ተቀብል ግራ ቀኛቸዉን አከራክሮ ሰምቶ እና በሕጉ አግባብ ተገቢዉን ማጣራትና ምርመራ በማድረግ ዉሳኔ ለመስጠት የሥረ-ነገር ስልጣን ያላቸዉ የፋዳራል ፍ/ቤቶች እንጂ የአዱስ አበባ ከተማ ፍ/ቤቶች አይደለም። የአሁን ተጠሪዎች ለአሁን አመልካች የተሰጠዉ የኑዛዜ ወራሽነት የምስክር ወረቀት ሉሰረዝልን ይገባል የሚለበት ሕጋዊ ምክንያት ያላቸዉ እንደሆነ አቤቱታቸዉን ስልጣን ላለዉ ፍ/ቤት ከማቅረብ ይህ ዉሳኔ አያግዲቸዉም ብለናል።
የዚህ ዉሳኔ ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤቶች ይድረስ።
ግራ ቀኛቸዉ በዚህ ችልት የደረሰባቸዉን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን ይቻለ።